YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
አውሮፓ ህብረት 40 በመቶ ለሚሆነው ህዝብ የኮቪድ-19 ክትባት ለመስጠት አስቧል!

የአውሮፓ ህብረት ሀገራት፣ብሪታኒያ እና የአውሮፓ ህብረት 40 በመቶ ለሚሆነው የህብረቱ ህዝብ የመጀመሪያ የኮቪድ19 ክትባት ለመስጠት ተስማምተዋል።

[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ተጨማሪ 1533 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፤ 515 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል!

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 18 ሺህ 724 የላቦራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 533ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በአጠቃላይ በአገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 45 ሺህ 221 ደርሷል።በሌላ መልኩ በትናንትናው ዕለት ሰዎች ያገገሙ 515 ሲሆን፣ በአጠቃላይ በአገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 16 ሺህ 311 ሆኗል።ካለፉት 24 ሰዓታት ምርመራ የ16 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ በኮሮናቫይረስ የተነሣ የሟቾች ቁጥር 725 ደርሷል።በአሁኑ ወቅት 327 ሰዎች በጽኑ ሕክምና ላይ ሲገኙ፣ 28 ሺህ 183 ደግሞ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች መሆናቸው ተገልጿል።በኢትዮጵያ በአጠቃላይ እስካዛሬ ድረስ 813 ሺህ 410 የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።

@YeneTube @FikerAssefa
በሐዋሳ ማረሚያ ቤት 110 ሰዎች በኮሮና መያዛቸው መረጋገጡን የሐዋሳ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙንጣሽ ብርሐኑ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የውጭ ዜጎች፣ የቀን ሰራተኞች ጭምር በኮሮና መያዛቸውን አረጋግጠዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
"ሥራችንን እንድናቋርጥ ተደርገናል" - የሳቢያን ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች

የድሬዳዋ አስተዳደር የኮቪድ 19 ህሙማን ለይቶ ማከሚያ የሆነው የሳቢያን ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች “ሥራችንን እንድናቋርጥ ተደርገናል” ብለዋል።ከቤተሰቦቻቸው ጋር ከመቀላቀላቸው በፊት ምርመራ እንዳልተደረገላቸውና ደንቡ በሚያዘው መሠረትም ወደ ለይቶ ማቆያ አለመግባታቸውን ተናግረዋል።

ለሦስት ወራት ያልተከፈለ የጥቅማጥቅም ጥያቄዎች እንዳሏቸውም አመልክተዋል።“ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲቀላቀሉ የተወሰነው በአንዳንድ የህክምና ባለሙያዎች ጥያቄ” መሆኑን የገለፀው የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ሊያገኙ የሚገባቸው ጥቅሞችም መፈቀዳቸውን አስታውቋል።

[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ በሚሌኒየም አዳራሽ በኮቪድ-19 ለተያዙ የሕክምና አገልግሎት የሚሰጠው ማዕከል የጽኑ ሕሙማን ክፍል አልጋዎች ሙሉ በሙሉ በሕሙማን ሲያዙ፤ ከፊል ጽኑ ሕሙማን ክፍልን የሚያስተናግደው ክፍልም እየሞላ መሆኑን ዳይሬክተሩ ተናገሩ።

ማዕከሉ በኮቪድ-19 የታመሙ እና የሕክምና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች ሕክምና እንዲያገኙበት በሚል የተደራጀ ነው።

በሚሊኒየም አዳራሽ ለይቶ ማቆያ ከሁለት መቶ በላይ ታካሚዎች መኖራቸውን የማዕከሉ ዳይሬክተር ዶ/ር ውለታው ጫኔ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

https://telegra.ph/BBC-08-27
YeneTube
በኒውዚላንዱ የመስጊዶች ጥቃት የተጠረጠረው ግለሰብ ፍርድ ቤት ቀረበ በኒውዚላንድ ክሪስትቸርች ከተማ ሁለት መስጊዶች ላይ ጥቃት በመፈፀም 49 ሰላማዊ ዜጎችን ህይዎት በማጥፋት ከተጠረጠሩ ግለሰቦች ውስጥ አንዱ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት ቀርቧል። ድርጊቱን የፈፀመው ተጠርጣሪ ብሬንቶን ታራንት የሚባል ሲሆን፥ በዜግነትም አውስትራሊያዊ መሆኑ ነው የተገለፀው። የ28 ዓመቱ ብሬንቶን ታራንት በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት…
ከአመት ተኩል በፊት በኒውዚላንድ ክራይስትቸርች በመስጊድ ውስጥ ተኩስ ከፍቶ 51 ሰዎችን የገደለው ብሬንቶን ሃሪሰን ታራንት የተባለው አውስትራልያዊ ግለሰብ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት።

ይህ የእድሜ ልክ እስራት የምህረት እድል የማይኖርበት (Life sentence without parole) መሆኑም ተገልጿል ፣ ይህንን ተክትሎም እድሜ ልኩን በእስር ቤት የሚያሳልፍ ይሆናል። ይህም በሀገሪቱ ህግ ከፍተኛው ቅጣት መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ሞባይል ስልክ በማስመሰል አደንዛዥ ዕፅ ወደ ክልል ለመላክ የሞከሩ ሦስት ግለሰቦች ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ነሃሴ 13 ቀን 2012 ዓ/ም የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው አዲስ አበባ የገበያ ማዕከል አካባቢ የተለያዩ ሦስት ግለሰቦች ወደ ክልል የሚላክ ሞባይ ስልክ ነው በማለት በካርቶን አሽገው ንብረት በአደራ ተቀብለው ለሚያስጭኑ ሦስት ግለሰብ እንዳስረከቡ ነገር ግን የእቃው ትክክለንነት ሲጣራ አደንዛዥ እፅ መሆኑን የተረዱ ሰዎች ለፖሊስ ጥቆማ መስጠታቸውን ተከትሎ ሦስት ተጠርጣሪዎች ተይዘው ምርመራ እየተጣራ መሆኑን የጉዳዩ መርማሪ ዋና ሳጅን አንበሴ ምርኮ አስታውቀዋል፡፡አደንዛዥ ዕፅ በማዘዋወር ከተጠረጠሩት ሦስቱ ግለሰቦች እጅ ከ50 ኪሎ ግራም በላይ አደንዛዥ ዕፅ እንደተያዘ ሦስቱም ግለሰቦች ወንጀሉን የፈፀሙት በተመሳሳይ ቀን በተለያዬ ሰዓት መሆኑን መርማሪው አስታውሰው ንብረት ተረክበው የሚጭኑ ተቋማት ሆኑ ግለሰቦች የሚረከቡትን ንብረት ትክክለኝነት የማረጋጋጥ ስራ መስራት እንዳለባቸው ከተፈፀመው የወንጀል ድርጊት ሊረዱ ይገባል ሲሉ ዋና ሳጅን አንበሴ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

[Addis Ababa Police Commission]
@YeneTube @FikerAssefa
ቻይና ለ3ኛ ዙር የኮሮና መከላከያ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች!

የቻይና መንግስት ለ3ኛ ዙር የኮሮና መከላከያ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ለኢትዮጵያ ለግሷል።በዚኛው ዙር ድጋፍ 500 ሺህ ሰርጂካል የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል፣ 65 ሺህ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል፣ 10 ሺህ የሜዲካል አልባሳት እና የጫማ መሸፈኛ እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰርጂካል ጓንቶች ተካተውበታል።የቻይና መንግስት ኢትዮጵያ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል በምታደርገው ዘርፈ ብዙ ጥረት ድጋፉ እንዳልተለየ እና ወረርሽኙ ወደ አገሪቱ ከገባበት ከመጋቢት ወር ጀምሮ የሚያደርገው ድጋፍ ሳይቋረጥ መቀጠሉንም በአዲስ አበባ የሚገኘው የቻይና ኢምባሲ አስታውቋል።ሚያዝያ ወር ከቻይና የመጡ የህክምና ቡድን አባላት ለ15 ቀናት በኢትዮጵያ የህክምና ድጋፍ መስጠታቸውም ይታወሳል።

[ETV]
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል ካጋጠሙ ሰሞንኛ የጸጥታ ችግሮች ጋር በተያያዘ በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ተመጣጠኝነቱ አጠራጣሪ የሆነ
እርምጃ መውሰዱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) አስታወቀ።ከነሀሴ 11 ቀን 2012 ዓ.ም አመሻሽ ጀምሮ በአሳሳ፣ በአዳባ፣ በዶዶላ፣ በሻሸመኔ፣ በባሌ ሮቤ፣ በጊኒር ፣ በአሰቦት ፣ በጭሮ ፣ በአወዳይ እና በሌሎችም የክልሉ ከተሞች በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተወሰዱ የኃይል እርምጃዎች የዜጎች ህይወት ተቀጥፏል። ይህ ተመጣጣኝነቱ አጠያያቂ የሆነ የጸጥታ ኃይሎች እርምጃ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታን ወደ አሳሳቢ ደረጃ እንዳይወስደው መንግስት በቂ ጥንቃቄ ሊወስድ እንደሚገባ ኢሰመጉ አሳስቧል።

[አሐዱ ሬዲዮ 94.3]
@YeneTube @FikerAssefa
አሁን ላይ እየጣለ ያለው ዝናብ ጤፍ ላይ ጉዳት እንደማያስከትል ተገለፀ!

ጤፍ ከፍ ያለ ሙቀት እና የፀሐይ ብርሃን ቢያስፈልገውም አሁን ባለበት የዕድገት ደረጃ የሚያገኘው የዝናብ መጠን የሚያስከትለው ጉዳት እንደሌለ ተገለፀ።በደብረዘይት ግብርና ምርምር ማዕከል መሪ የጤፍ ተመራማሪ ዶክተር ክበበው አሰፋ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት ፤ ከሌሎች ሰብሎች በበለጠ ጤፍ ውሃን መቋቋም የሚችል ነው። ስለሆነም አሁን ያለው የዝናብ መጠን ሰብሉ አሁን ባለበት የዕድገት ደረጃ ብዙም ጉዳት አያደርስበትም።በተለይም ጥቁር አፈር ላይ የተዘራ ጤፍ ዝናቡ ሲበዛበት እህሉን በጣም ያፍነውና የመቀጨጭ ባህሪም ያሳያል ያሉት ተመራማሪው፤ ቀለል ያለ አፈር ላይ ለአብነትም ወደ ቆላ፣ ዓለም ጤና እና ቆቃ አካባቢ ዝናቡ ቢበዛም የሚሸረሽረው ካልሆነ በስተቀር አፈሩ ውሃ መውሰድ የሚችል በመሆኑ ጉዳት የለውም።

የዝናቡ መብዛት ከሌሎች ሰብሎች አንፃር ሲታይ ጤፍ ላይ ብዙም ጉዳት እንደማያስከትል አብራርተዋል።ይሁንና ሌሎች ማለትም እንደ ስንዴ በቆሎና የመሳሰሉት ሰብሎች በተለይም በጥቁር አፈር ላይ የተዘሩ ከሆነ ዝናብ ከበዛባቸው ለመብቀል የሚቸገሩ መሆኑን የገለፁት ተመራማሪው፤ ለዚህም ከጤፍ ውጭ ላሉት ሰብሎች የዝናቡ መጠን በሚበዛበት ወቅት የውሃ ማንጠፍጠፍ ዘዴን በመጠቀም ምርታማ መሆን እንደሚቻል አስረድተዋል። ተመራማሪው አያይዘውም እስካሁን በምርምር እንደታየው ጤፍን በውሃ የማንጠፍጠፍ ዘዴ በመጠቀም ምርታማ ማድረግ አለመቻሉን ገልፀዋል።ጤፍ ውሃ ሲበዛበት ለሰብሉ ዕድገት የሚጠቅመው ናይትሮጂን የተባለው ማዳበሪያ ከውሃው ጋር ይሄዳል።በዚህ ጊዜ ጤፉ ቢጫ መሆንና መቅላት ይታይበታል ብለዋል።

[Addis Zemen]
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ የሰላም ምክር ቤት ተመሠረተ፡፡

ምክር ቤቱ በከተማችን ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን፣ የሚከሰቱ ግጭቶችና አለመግባባቶችን ቀድሞ ለመከላከል፣ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እና ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ህብረተሰቡን በማሳተፍ የነዋሪውን የሰላም ባለቤትነት ለማረጋገጥ የተቋቋመ ነው፡፡በምስረታ ጉባኤው ላይ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ የኃይማኖት አባቶች ፣ ታዋቂ ግለሰቦች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የምክር ቤት ማቋቋሚያ መርሃ-ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የበርካታ ዓለምአቀፍ ተቋማት መቀመጫ የሆነችው መዲናችን አዲስ አበባ የነዋሪዎቿን ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ ማረጋገጥ የምክር ቤቱ መሠረታዊ ተግባር ነው ብለዋል፡፡የሰላሟ ጠንቅ የሆኑ የምሽት ቅሚያን ጨምሮ የተሽከርካሪ ስርቆት ፣ በቡድን በመደራጀት የህብረተሰቡን ሰላም የማደፍረስ እና ህገ-ወጥ የመሬት ወረራ ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ የነዋሪውን ሰላም ማረጋገጥ እንደሚገባ ወይዘሮ አዳነች አሳስበዋል፡፡

የከተማዋ ነዋሪ ከምንጊዜውም በላይ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በቅርበት በመስራት የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ ያለውን ቁርጠኝነት ሊያረጋግጥ ይገባልም ብለዋል ወይዘሮ አዳነች፡፡የሰላም ምክር ቤቱ በከተማ ፣ በክፍለ ከተማና በወረዳ ደረጃ የሚቋቋም፣ ተጠሪነቱ ለከተማው ምክር ቤትና ለከተማው ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሲሆን በወረዳና በክፍለ ከተማ ደረጃ የሚቋቋሙት ደግሞ በየወረዳዎቹ ለሚገኙ የሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤቶች ይሆናል፡፡

[Addis Ababa Mayor Office]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ በማሰብ መጠን (IQ) ከዓለማችን 180 አገራት 163ኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠች።

ዓለም አቀፉ የህዝብ ጥናት ተቋም ወይም (WPR) የ2020 የዓለም አገራት የማሰብ መጠን ዓመታዊ ሪፖርትን በድረገጹ ይፋ አደርጓል።ተቋሙ ለዚህ ሪፖርቱ እንደ መስፈርት የተጠቀመው በትምህር ቤት ምን ያህል ተማሪዎች ውጤታቸው ከፍተኛ ነው? እንደዲሁም ምን ያህል ዜጎች የኖብል ሽልማት አሸነፉ? የሚለው የማሰብ መጠን የተለካባቸው ናቸው፡፡የሀገራት የትምህርት ጥራት እና የግብአት አቅርቦቱም እንደ መስፈርት ከተወሰዱት መስፈርቶች መካከል ይገኙበታል፡፡በነዚህ መስፈርቶች መሰረትም የኢትዮጵያዊያን የማሰብ መጠናቸው የ115 ሚሊየን ህዝቧ የአይኪው መጠኑ 69 ሲሆን የኤርትራ አማካይ የአይኪው መጠን ደግሞ 85 ሆኖ ከአፍሪካ በቀዳሚነት ላይ ተቀምጣለች፡፡

ኢትዮጵያ አማካይ የአይኪው ደረጃዋ 69 ሆኖ ከአለም 163ኛ ደረጃን ይዛ ተቀምጣለች፡፡180 ሀገራት የአይኪው መጠናቸው በአማካይ ይፋ ሲያደርግ ኢትዮጵያ የ115 ሚሊየን ህዝቧ የአይኪው መጠኑ 69 ሆኖ ከአለም 163ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል፡፡ከአለም ሀገራት ከፍተኛ የአይኪው መጠን ያላት ሀገር ሲንጋፖር ስትሆን አማካይ የአይኪው መጠኗ 108 እንደሆነ ነው መረጃው የሚያሳየው፡፡እንዲሁም ሆንግ ኮንግም እንደ ሲንጋፖር ሁሉ የህዝቧ አማካይ የአይኪው መጠን 108 መሆኑንም ነው የተገለጸው፡፡

ከአለም በሶስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ሀገር ደቡብ ኮርያ ስትሆን የህዝቧ አማካይ የአይኪው መጠኑ 104 ነው፡፡ከአፍሪካ ከፍተኛ የአይኪው መጠን አላት ብሎ ያስቀመጣት ሀገር ኤርትራ ስትሆን አማካይ የአይኪው መጠኗ 85 ነው ይላል፡፡ከአፍሪካ በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠችው ደግሞ ሞሮኮ ስትሆን አማካይ የአይኪው መጠኗ 84 ነው፡፡ዩጋንዳም እንደ ሞሮኮ ሁሉ አማካይ የአይኪው መጠኗ 84 ላይ እንደሚገኝ መረጃው የሚያሳየው፡፡ደረጃ ላይ ከተቀመጡት180 የአለም ሀገራት የመጨረሻ ደረጃ ላይ የተቐመጠችው ኢኳቶሪያል ጊኒ ስትሆን አማካይ የአይኪው ደረጃዋ 59 እንደሆነ ነው መረጃው የጠቆመው፡፡ከፍተኛ የሚባለው የአይኪው መጠን 131 ሲሆን መካከለኛ የሚባለው ደግሞ ከ90 አስከ 110 እንደሚደርስ ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት፡፡

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበጀት ዓመቱ የ50 ሺህ ስማርት ቆጣሪዎች ተከላ እንደሚጀምር አስታወቀ!

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2013 በጀት ዓመት የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ትግበራን በማጠናከር የ50 ሺህ ስማርት ቆጣሪዎች ተከላ እንደሚጀምር አስታወቀ።ተቋሙ በበጀት ዓመቱ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን በማስፋት የደንበኞችን ቁጥር ማሳደግም በትኩረት እንደሚሠራ ገልጿል።የኃይል ብክነትን በመቀነስ፣ የኔትዎርክ ማሻሻያዎችን በማድረግ፣ የኃይል መቆራረጥን እና የአቅርቦት ችግርን በመፍታት ለደንበኞች ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚለውም ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫው አድርጎ ማስቀመጡን ጠቁሟል።ይህን ተግባራዊ በማድረግም በበጀት ዓመቱ 25 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን ነው ያስታወቀው።በሌላ በኩል በ2012 በጀት ዓመት 25.38 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ 14.97 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 59 በመቶ ብቻ ማሳካት መቻሉን አስታውቋል።

[OBN]
@YeneTube @FikerAssefa
የአምቦ ሰንቀሌ ፖሊስ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በስምንተኛ ዙር የተሃድሶ ሥልጠና ለሁለት ወራት ያሰለጠናቸውን 728 መደበኛ ፖሊሶችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በባህርዳር ከተማ ትልቅ የነዳጅ ኦኘሬሽን ዲፖ እየተገነባ መሆኑ ተገለፀ፡፡

አሁን በባህርዳር ከተማ እየተገነባ ያለው ኦኘሬሽናል ዲፖ በቀን ከ7 መቶ ሺህ ሊትር በላይ የማደል አቅም ያለው በመሆኑ በሰዓት ከ28ዐ እስከ 300 መኪኖችን ከማስተናገዱም ባለፈ ለ4መቶ ስራ ፈላጊዎች በቋሚነትና በጊዜያዊ የስራ እድል መፈጠሩ ተገልጿል፡፡አጠቃላይ ኘሮጀክቱ በ20ሺ ካሬ ላይ ያረፈና እያንዳንዳቸው በደቂቃ 80 ሊትር የሚያድሉ 24 መቅጃዎች ያሉት ማደያ ተገንብቶ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን ገልፀው በቀጣይ አዲሱ ዓመት 2013 ስራ የሚጀምር መሆኑን መሆኑን የኢላ ፔትሮሊየም የነዳጅ ኩባንያ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ደመቀ ምስጋናው ተናግረዋል ፡፡

[የከተማው ኮምኒኬሽን ቢሮ]
@YeneTube @FikerAssefa
ርዋንዳ አሎይስ ንትዊራጋባኦን አሳልፋ እንድትሰጣት ፈረንሳይን ጠየቀች!

በወቅቱ የመከላከያ የመረጃ ኃላፊ የነበረው ጄነራሉ የዘር ጭፍጨፋውን ካቀናበሩ ሰዎች መካከል አንዱ ነው ያለው የካጋሜ መንግስት ተላልፎ እንዲሰጠው በጻፈው ደብዳቤ ጠይቋል፡፡

[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
ሀብታቸውን ያላስመዘገቡ 184 ባለስልጣናት ሊከሰሱ ነው!

የፌደራል ስነምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ሀብታቸውን ለማስመዝገብ ፍቃደኛ ያልሆኑ 184 ባለስልጣናት በወንጀል እንዲከሰሱ ስም ዝርዝራቸውን ለፌደራል ፖሊስ መስጠቱን አስታውቋል፡፡

[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa
በሳዑዲ ዓረቢያ እና በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች በችግር ውስጥ ያሉ ከ25 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን በቅርቡ ወደ አገራቸው ሊመለሱ መሆኑን የየሀገሩ አምሳደሮች ለኢዜአ ተናግረዋል።

በሳዑዲ ዓረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አብዱልአዚዝ አህመድ፣ ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው በርካታ ኢትዮጵያዊያን በሀገሪቱ እንደሚገኙ ለኢዜአ ገልጸዋል።
በመሆኑም በችግር ውስጥ የሚገኙትን ኢትዮጵያዊያን ደህንነታቸው ተጠብቆ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ከሳዑዲ መንግስት ጋር በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።በተመሳሳይ በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው በርካታ ኢትዮጵያዊያን እንደሚገኙ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ ገልጸዋል።ከእነዚህም አምስት ሺህ የሚሆኑትን ወደ አገራቸው ለመመለስ አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ ነው ነው ብለዋል።

[ENA]
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል ከ12 ሺህ በላይ ሰዎች በጎርፍ ምክንያት መፈናቀላቸው ተገለፀ!

በኦሮሚያ ክልል ከሐምሌ ወር ጀምሮ ከ12 ሺህ በላይ ሰዎች በጎርፍ አደጋ ምክንያት ከአካባቢያቸው መፈናቀላቸውን የክልሉ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።በክልሉ የበልግ ዝናብ መጣል ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች በጎርፍ ምክንያት ለጉዳት መደረጋቸውም ተመልክቷል።የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ገረመው ኦሊቃ እንዳሉት በተለያዩ ጊዜያት በተከሰቱ የጎርፍ አደጋዎች በሰው ህይወት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ አፋጣኝ ምላሽ ሲሰጥ ቆይቷል።ለተጎጂዎች የምግብ እና የአልባሳት ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ጀልባ ጭምር በመጠቀም ሰዎችን ከውሃ ውስጥ የማውጣት ሥራዎች ተሰርቷል ብለዋል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1186 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፤ 518 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል!

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 18 ሺህ 060 የላቦራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 186 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በአጠቃላይ በአገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 46 ሺህ 407 ደርሷል። በሌላ መልኩ በትናንትናው ዕለት ሰዎች ያገገሙ 518 ሲሆን፣ በአጠቃላይ በአገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 16 ሺህ 831 ሆኗል። ካለፉት 24 ሰዓታት ምርመራ የ20 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተከትሎ በኮሮናቫይረስ የተነሣ የሟቾች ቁጥር 745 ደርሷል። በአሁኑ ወቅት 330 ሰዎች በጽኑ ሕክምና ላይ ሲገኙ፣ 28 ሺህ 831 ደግሞ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች መሆናቸው ተገልጿል። በኢትዮጵያ በአጠቃላይ እስካዛሬ ድረስ 831 ሺህ 470 የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።

@YeneTube @FikerAssefa