YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል በተከቷዮቿና በደብሮቿ ላይ አነጣጥሮ የተፈጸመ ነው ያለችውን ጥቃት በተመለከተ ዛሬ፣ ነሐሴ 20 ቀን፣ መግለጫ ልትሰጥ ነው። መግለጫው ጥቃት የተፈጸመባቸውን አካባቢዎች ተዘዋውሮ በጎበኘው የቤተ ክርስቲያኒቱ ልኡካን ቡድን ቀዳሚ ሪፖርት ላይ የተመሠረተ እንደሚሆን ታውቋል።

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮ ቴሌኮም የሦስት አመት የስትራቴጂክ ዕቅድን በተመለከተ እና አመታዊ የንግድ ዕቅዱን በሚመለከት በዋና አስፈፃሚዋ ፍሬህይወት ታምሩ በኩል መግለጫ እየሰጠ ነው።

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
የኮምፒውተር ተህዋስ' የተገጠመላቸው የቻይና ሥልኮች ኢትዮጵያና ሌሎች የአፍሪካ አገራት ውስጥ ተሽጠዋል!

የኮምፒውተር ተህዋስ [ማልዌር] የተገጠመላቸው በሺዎች የሚቆጠሩ የቻይና ስሪት የሆኑ ስልኮች አፍሪካ ውስጥ መቸብቸባቸው ተሰምቷል።አፕስትሪም የተሰኘ አንድ ተቋም ነው ይህን ይፋ ያደረገው።ቢያንስ በ53 ሺህ ይህ ተህዋስ የተገጠመላቸው የቴክኖ ስልኮች ኢትዮጵያ፣ ካሜሩን፣ ግብፅ፣ ጋና እና ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መሸጣቸው ተነግሯል።የስልኮቹ አምራች የሆነው ትራንዚሽን የተሰኘ ኩባንያ ተህዋሱ የተገጠመው ከእኔ እውቅና ውጪ በአከፋፋዮች ነው ይላል። አፕስትሪም የተሰኘው የመሰል ተህዋሶች አጋላጭ ድርጅት በዚህ አይስማማም።"ይህ ማልዌር [የኮምፒውተር ተህዋስ] ሚሊዮኖችና ገቢያቸው አናሳ የሆኑ ሰዎች በሚገዙት ስልክ ላይ መሰል ተህዋስ ያለ ተጠቃሚዎች መገጠሙ ኢንዱስትሪው ምን ያክል የሰዎችን ግላዊነት እየተጋፋ እንዳለ የሚያሳይ ነው" ይላሉ የአፕስትሪም ባለሙያ የሆኑት ጄፍሪ ክሊቭስ።

'ትሪያዳ' የተሰኘው ተህዋስ አንድሮይድ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ላይ የሚገጠም ሲሆን 'ኤክስሄልፐር' የተባለ ኮድ ተጠቅሞ ከተጠቃሚዎች እውቅና ውጪ ያሻውን የሚያደርግ ነው።ይህ ማልዌር ብዙ ጊዜ ተጠቃሚዎች ሳያውቁ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን የሚቀላቀል ነው። ይህ ተህዋስ ሞባይል ስልክዎ ላይ ያለዎትን ገንዘብ [የአየር ሰዓት] ያለ ፈቃድዎ የሚወስድ ነው።በርካታ የአፍሪካ አገራት ውስጥ የበይነ መረብ ክፍያ የሚፈፀመው በአየር ሰዓት ነው።አፕስትሪም የተሰኘው ተቋም ቢያንስ 200 ሺህ ስልኮች ያለፈቃዳቸው 'ሰብስክራይብ' ካደረጓቸው አገልግሎቶች እንዲወጡ አድርጓል።ትራንዚሽን ሆልዲንግስ የተሰኘው ተንቀሳቃሽ ስልክ አምራች ኩባንያ ቻይና ውስጥ ካሉ ግዙፍ ኩባንያዎች አንዱ ሲሆን አፍሪካ የምርቶቹ ቁጥር አንድ ገዢ ናት።ቴክኖ፤ ችግሩ ያረጀና ያፈጀ ነው። ከሁለት ዓመት በፊት ቀርፌዋለሁ ይላል።

ለቢቢሲ ጉዳዩን የተመለከተ የጽሑፍ መግለጫ የላከው ድርጅቱ፤ "ቴክኖ ደብለዩ2 ስልኮች ያላቸው ሰዎች መሰል ችግር እንዳያጋጥማቸው መጫን የሚችሉት መተግበሪያ [አፕሊኬሽን] አለ። ወደ ቴክኖ ሱቆች መጥተው እርዳታ መጠየቅም ይችላሉ" ይላል።ከወራት በፊት አንድ ሌላ ድርጅት ተመሳሳይ ችግር ያለባቸው ዩኤምኤክስ የተሰኙ የቻይና ምርት የሆኑ ስልኮች ላይ ማግኘቱ አይዘነጋም። ይህ ስልክ አሜሪካ ውስጥ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሰዎች በመንግሥት መከፋፈሉ ይታወሳሉ።በፈረንጆቹ 2016 ራያን ጆንሰን የተሰኙ ተመራማሪ 700 ሚሊዮን አንድሮይድ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ማልዌር እንደተገጠመባቸው ይፋ አድርጎ ነበር።ማልዌር ማለት ስልኮችና ሌሎች የቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ ከተጠቃሚዎች እውቅና ውጪ የሚገጠመው ተህዋስ ሲሆን መረጃ ከመመዝበር አልፎ ስልኮችንና ኮምፒውተሮች ከጥቅም ውጪ ሊያደርግ ይችላል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮ ቴሌኮም በስራ ላይ ያለው ኔትወርኩን ለ5G የሞባይል አገልግሎት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ። የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ እየሰጡት ባለው መግለጫ እንደተናገሩት ተቋማቸው ለ5G ኔትወርክ ቢዘጋጅም አገልግሎቱን በቅርቡ አይጀምርም። እንዲሁም በመጪው 2013 የበጀት ዓመት ዓመት 55 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱም ተነግሯል።

[Ethiopia Insider]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮ ቴሌኮም የ4G አገልግሎት በክልሎች ሊያስጀምር አቅዷል።አሁን ላይ አገልግሎቱ በአዲስ አበባ ብቻ የተወሰነ ነው።

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
ፍርድ ቤቱ አርቲስት ሃጫሉ ሲገደል  አብራው በነበረችው ላምሮት ከማል ላይ አቃቤ ህግ በ15 ቀናት ውስጥ ክስ እንዲመሰርት ፈቀደ!

በሰኔ 22 ቀን 2012 ዓመተ ምህረት ከምሽቱ 3 ሰዓት አካባቢ በገላን ኮንዶሚኒየም አካባቢ  አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሲገደል  አብራው የነበረችው ላምሮት ከማል ላይ አቃቤ ህግ በ15 ቀናት ውስጥ ክስ እንዲመሰርት ፍርድ ቤቱ ፈቀደ።መርማሪ ፖሊስ ጉዳዩን ለተመለከተው በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት  ምርመራ ማጠናቀቁን ገልፆ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ አስረክቧል።አቃቤ ህግም በወንጀለኛ መቅጫ ስነስርዓት ህግ 109 መሰረት 15 ቀን ክስ መመስረቻ ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ተጠርጣሪዋ በበኩሏ “አርቲስት ሃጫሉ ጓደኛዬ ነው፣ በወቅቱም አብሬው ነበርኩ፣ ይህንን አልክድም፣ ለህይወቴ ሳልሳሳ ወንጀለኞቹን አሳይቻለሁ፣ ፍርድ ቤቱ የቤተሰቦቼ ማህበራዊ ህይወት እንዳይሰተጓጎል  በዋስ ይልቀቀኝ” ስትል ጠይቃለች።ፍርድ ቤቱም በወንጀለኛ መቅጫ ስነስርዓት ህግ 63 መሰረት ጉዳዩ የግድያ ወንጀል የተፈፀመበት በመሆኑና ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ክስ ሲመሰረት ከ15 ዓመት በላይ እስራት የሚያስቀጣ በመሆኑ ዋስትና የሚያስከለክል ነው በማለት የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ አድርጓል።ነገር ግን አቃቤ ህግ በ15 ቀን ውስጥ ክስ ካልመሰረተ የዋስትና ጥያቄ አቤቱታን ማቅረብ ይቻላል ብሏል።

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢንተርኔት ጥቅል አገልግሎት ላይ እስከ 35 በመቶ ቅናሽ ተደረገ!

የኢንተርኔት ጥቅል አገልግሎት ላይ እስከ 35 በመቶ ቅናሽ ተደረገ።እንዲሁም በቤትዎ ይቆዩ የጥቅል አገልግሎትም 59 በመቶ ቅናሽ ተደርጓል።የድምፅ ጥቅል አገልግሎት ላይም የ29 በመቶ ቅናሽ የጠደረገ ሲሆን አገልግሎቱም ከነገ ነሐሴ 21/2012 ጀምሮ በስራ ላይ ይውላል።በተያያዘም እስከ 11 የሚደርሱ ሀገራት ላይ የውጭ ጥሪ አገልግሎት 50 በመቶ ቅናሽ መደረጉም ታውቋል።ከውጭ አለም አቀፍ ጥሪ ለሚቀበሉ ደንበኞች ከኢትዮ ቴሌኮም ስጦታ ይበረከትላቸዋል

[Addis Maleda]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል በተከቷዮቿና በደብሮቿ ላይ አነጣጥሮ የተፈጸመ ነው ያለችውን ጥቃት በተመለከተ ዛሬ፣ ነሐሴ 20 ቀን፣ መግለጫ ልትሰጥ ነው። መግለጫው ጥቃት የተፈጸመባቸውን አካባቢዎች ተዘዋውሮ በጎበኘው የቤተ ክርስቲያኒቱ ልኡካን ቡድን ቀዳሚ ሪፖርት ላይ የተመሠረተ እንደሚሆን ታውቋል። [Wazema] @YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከድምጻዊ ሀጫሉ ግድያ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ሁከት በኦሮሚያ ክልል 67 ምዕመናን እንደተገደሉባት አስታወቀች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በተፈጠረው ሁከት ምክንያት ተጎድተዋል ወደ ተባሉ አካባቢዎች ተሰማርታ ምልከታ ካካሄደች በኋላ በአዲስ አበባ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት መግለጫ በመሰጠት ላይ ትገኛለች።

ቤተክርስቲያኗ በዚህ ጊዜ እንዳለችው ከድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ገድያ ጋር ተያይዞ በኦሮሚያ ክልል በተፈጠረ ሁከት 67 ምዕመናን ሲገደሉ ከ7 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።

በአጠቀላይም ሁከቱን መነሻ በማድረግ ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የምዕመናን ንብረት መውደሙም በመግለጫው ላይ ተገልጿል።

በኦሮሚያ ክልል፣በድሬዳዋ ከተማ አስተዳድር እና በሌሎች አካባቢዎች ምዕመናን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል፣ እንደ ሰውም አስክሬናቸው በክብር አልተቀበረም ፣ ሴቶች በባለቤታቸው፣በወንድምና በአባታቸው ፊት መደፈራቸው በምልከታ መረጋገጡ በመግለጫው ላይ ተገልጿል።
[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ትምህርቶችን ከወረቀት ነፃ ለመስጠት መታቀዱ ተገለጸ!

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች እና አመራሮች በየደረጃው በትምህርት ዘርፉ የ10 አመት እቅድ ላይ ውይይት ጀምረዋል።የትምህርት ዘርፉ በዲጂታል ቴክኖሎጂ አለመደገፍ፣ ፍትሃዊ የትምህርት ተደራሽነት አለመኖር፣ ግልፅነትና ተጠያቂነት አለመስፈን በትምህርት ጥራቱ ላይ ተፅዕኖ መፍጠሩ ተነስቷል።በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ትምህርት በመስጠት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ብቁ ዜጋን ለማፍራት የሚያስችሉ አሰራሮች በእቅዱ ውስጥ ተካቷል።

ከ9 እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ትምህርቶች ከወረቀት ነፃ በማድረግ በዲጂታል መልክ መሰጠት የእቅዱ አንዱ አካል ነው ተብሏል።ይህም መንግስት ለወረቀትና ህትመት የሚያወጣውን ከፍተኛ ወጪ ከማስቀረት በተጨማሪ ተማሪዎች የዲጂታል አለሙን በቀላሉ እንዲቀላቀሉ ያግዛቸዋል ተብሏል።ወደ ዲጂታል ስርዓቱ ለመግባት ለተማሪዎች ታብሌቶችን ለማሟላት የተለያዩ አማራጮች እየተፈለጉ ነው ተብሏል።የትምህርት ዘርፉ የ10 አመት እቅድ በኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓት ውስጥ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል ተብሎም ይጠቃል መባሉን ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa
የተማሪዎች ምዝገባ በሚካሄድባቸው ትምህርት ቤቶች ላይ የተለየ መስፈርት አለመውጣቱን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ገለፀ፡፡

ወላጆች ተማሪዎችን ትምህርት ቤት ሲያስመዘግቡ የአለም ጤና ድርጅትና የጤና ሚኒስቴር ያወጣውን መመሪያ በመከተል እንደሆነ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ለአሐዱ ገልፀዋል፡፡ ከምዝገባው ጋር በተያያዘ በቢሮው በኩል የተለየ መስፈርት አለመውጣቱን የገለፁት አቶ ዘላለም ትምህርት መቼና እንዴት ይጀምራል የሚለው በቀጣይ የሚታይ ነው ብለዋል፡፡አሁን ላይ ትኩረት የተደረገው የቅበላና የድልድል ስራ ላይ መሆኑን ጠቁመው ኅብረተሰቡ መመሪያዎችን በመተግበር ሊሰራ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

[አሐዱ ሬዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
ለ40/60 ቤቶች እድለኞች ቅሬታ ቢሮው የሰጠው ምላሸ!

የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ዕጣ የወጣባቸው 18ሺህ 576 የ40/60 ባለ አንድ፣ ባለ ሁለትና ባለ ሦስት መኝታ ቤት የጋራ መኖሪያ ቤቶች፤ በ2011 መጨረሻ ውል ቢዋዋሉም ቁልፍ መረከብ የጀመሩት በ2012 ሐምሌ ላይ ነው፤ ሆኖም የቁልፍ ርክክቡ ቤቶቹ ተጠናቀው ሳይሆን፤ ገና በሂደት ላይ ሳሉ ከመሆኑም ባሻገር ውልም ሆነ የቁልፍ ርክክቡ ሲጀመር በግልፅ በመገናኛ ብዙሃን አለመነገሩን በመጠቆም የቤት ዕድለኞቹ የመረጃ መስጠት ክፍተት ስለመኖሩ ቅሬታ ማቅረባቸውን ባለፈው ሳምንት ማስነበባችን ይታወሳል።

የቤቶቹ ዕጣ በወጣ ሰሞን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፤ በከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር እንዲሁም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መካከል አለመግባባቶች እንደነበሩ መገለፁ እና ‹‹100 በመቶ ለቆጠብን ቅድሚያ ማግኘት አለብን›› የሚለውን ቅሬታ እና ውዝግብ እንዳይቀጣጠል በመስጋት ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን ገልፀው፤ በዚህ ሳቢያ ዕድለኛ ሆነው ብዙዎች ሳይዋዋሉም ሆነ ቁልፍ ሳይረከቡ መቅረታቸውን ምንጮቻችን ተናግረዋል።

የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውል ሊፈፀም መሆኑ በግልፅ በመገናኛ ብዙሃን አልተዋወቀም። በዚህ ሳቢያ ብዙዎች ሳያውቁ ውል የሚዋዋሉበት ተራ አምልጧቸው፤ ብዙ ተንገላተዋል። በሌላ በኩል አሁንም የቁልፍ ርክክቡን መስማት የተቻለው በወሬ ወሬ ወይም አንዳንድ የተለያዩ ማህበራዊ ድረገፆችን ከሚመለከቱ ሰዎች እንጂ በመገናኛ ብዙሃን አልተገለፀም በሚል ለቀረበው ጥያቄ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ መልስ ሰጥቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ አቶ ሰሎሞን ዲባባ እንደሚገልፁት፤ የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ዕጣው በግልፅ በአደባባይ ሲወጣ በመገናኛ ብዙሃን ተላልፏል። ዕጣ የወጣላቸው ሰዎች ከተለዩ በኋላ ግን ስልክ ቁጥራቸው በመኖሩ ውል የመወያያው ጊዜ ሲደርስ በቅደም ተከተል በወጣው ዝርዝር መሰረት ስልክ ተደውሎላቸዋል።

የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሥራ አስኪያጆች እንደተናገሩት፤ ለሁሉም እንዲያውቁ ተደርጓል። የቁልፍ ርክክቡ ሲጀመር በኮቪድ ምክንያት ጋዜጠኞችን ጠርቶ መግለጫ ለመስጠት አልተቻለም። በመገናኛ ብዙሃን ለማስተላለፍ ያን ያህል ትኩረት አልተሰጠም። ነገር ግን ዕድለኞቹ እንዲያውቁ ተደርጓል።

ዕጣው ወጥቶላቸው ውል ሳይዋዋሉ የቀሩት ሰዎችም አሁንም እስከ መስከረም 30 መጥተው ውል እንዲፈፅሙ ተወስኗል። የውል ጊዜውን ባለማወቅ ብቻ ሳይሆን በሌሎች የተለያዩ ምክንያቶች ውሳኔ የሚፈልጉ ጉዳዮች ነበሩ። ከእነዚህ ውስጥ በኮሚቴ ሊወሰንላቸው የሚገቡ እየተወሰነላቸው ሲሆን፤ ዕጣ ወጥቶላቸው ውል ተዋውለው አሁንም ቤቱን እንዲወስዱ እየተደረገ ነው ይላሉ።

በተጨማሪ ዕድለኞቹ ህንፃዎቹ ያሉበት ቦታም የመረጃ ግልፅነት የለም። የሚገነቡት ተቋራጮች፣ የቀን ሰራተኞች፣ የጥበቃ ሰዎች አንዳንዴ ከቤቶች ልማት የተገኙ ሰዎች እንኳ ‹‹ሃያት አንድ ሳይት አንድ የትኛው ነው? ሃያት ሁለት የትኛው ነው? የትኛው ሳይት አራት ነው?›› ሲባሉ በትክክል መልስ አይሰጡም። ምክንያቱም ለይተው አያውቋቸውም። አንዱ ሌላ ቦታ ሲያሳይ፤ ሌላው ደግሞ ሌላ ቦታ ያሳያል። በቀላሉ በአነስተኛ ብረት ነገር ታፔላ መለጠፍ እየተቻለ ያ አልተደረገም። መፍትሔው ቀላል ቢሆንም እየፈጠረ ያለው ችግር ከባድ እና ለቤት ዕድለኞቹ ወሳኝ ናቸው በሚል ለቀረበው አቤቱታ አቶ ሰሎሞን መልስ ሰጥተዋል።

‹‹ምናልባት ብሎኮች እና ሳይቶች የተለዩበት ሁኔታ የሚታወቀው በግንባታ እና በዲዛይን ላይ ይሆናል። በዌብ ሳይቶች እና በማህበራዊ ድረገፆችም ተለይተው የሚታዩበት ሁኔታ አለ። ኮንትራክተሩ እና ቢሮው አብረው የሚሰጡት ነገር አለ። የማይሰጡ ነገርም ይኖራል። አሁን ደግሞ 40/60 ወደ ቤቶች ልማት ገብቷል። ሌሎችም የተያያዙ የተቀያየሩ የመዋቅር ነገሮች አሉ። በእነዚህ ለውጦች ሳቢያ ግልፅ መረጃ ለማግኘት አዳግቶ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ሳይትና ብሎካቸው የሚለጠፍበት ሁኔታ ይመቻቻል። ›› ይላሉ።

ማህበረሰቡ ጥያቄውን ሊያቀርብ ይችላል። በዛ ልክ ያሉት ክፍተቶች ወደ ፊት ይስተካከላሉ። ነገር ግን ሁሉም መረጃ እንዲኖራቸው የሚደረግበት ሁኔታ ይኖራል ካሉ በኋላ፤ ለጊዜው ግን በየሳይቶቹ የቅርንጫፍ ቢሮዎች ስላሉ እዛ ቢሄዱ ግልፅ የሆነ መረጃ ማግኘት እንደሚችሉ ይናገራሉ።

ሌሎች ዕድለኞቹ ካቀረቧቸው ጥያቄዎች መካከል ‹‹አንዳንዶቹ የጋራ በረንዳዎቻቸው እና ደረጃዎቻቸው በእብነበረድ አሸብርቀው፤ የምግብ ማብሰያ እና መታጠቢያ ቤታቸው ሴራሚክ ተሰርቶላቸው፤ ከሞላ ጎደል ተጠናቀዋል የሚያስብል ደረጃ ላይ ደርሰዋል። ሌሎቹ ህንፃዎች ደግሞ በረንዳዎቻቸውም ሆነ በምግብ ማብሰያ እና በመታጠቢያ ክፍል አሸዋ ተደፍቷል። ሳሎን እና ኮሊደር እንዲሁም መኝታ ቤቶች ሊሾ ቢሆኑም አንዱ ከሌላው ይለያል። መዝጊያቸውም እንዲሁ የተለያየ ነው። ›› በማለት አንዳንዶቹ ያላለቁ ሌሎች ደግሞ ከሞላ ጎደል የተጠናቀቁ መሆናቸውን በመግለፅ አሰራሩ ጉራማይሌ ነው የሚል አቤቱታ አቅርበው ነበር።

ለዚህ ጥያቄ አቶ ሰለሞን ሲመልሱ ከመጠናቀቅ እና አለመጠናቀቅ ጋር ተያይዞ የተለያየ ነገር አለ። አንዳንዱ ተጠናቋል። በአንድ ወለል ላይ 10 ቤት ቢኖር አንድ ቤት ቢጠናቀቅ ለአንዱ ብቻ ቁልፍ በመስጠት የሌሎቹ ይዘግይ ማለት አይቻልም። የምግብ ማብሰያ ክፍል ቁሳቁስም ለአንዱ ተገጥሞ የዘጠኙ ክፍት ከሆነ ጥሩ አይሆንም። ስለዚህ የሚገጠሙ ነገሮች ላይ በማዕከል ለሁሉም አንድ ላይ እንዲያገኙ ይደረጋል። ከኮንትራክተር ጋር ተያይዞ አንዳንዴ ትንሽ የግብአት አለመሟላት እና ክፍተት ካለ እዛው ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ላይ ሥራ አስኪያጆች አሉ። ውል የገባው ኮንትራክተር አለ። ስለዚህ በዛው አካሄድ እዛው አካባቢ ቢጠይቁ መፍትሔ የሚገኙበት ሁኔታ ይኖራል ሲሉ ያብራራሉ።

ህንጻዎቹን የተለያዩ ኮንትራክተሮች የገነቧቸው በመሆናቸው ቤቶቹ የተለያዩ ናቸው። በአጠቃላይ ግንባታውን የማጠናቀቅ ሁኔታን አስመልክቶ ከቅርንጫፍ መጠየቅ እና ማወቅ ይችላል። በተለያዩ ምክንያቶች ቶሎ የሚጨርሱ ቶሎ የማይጨርሱ ኮንትራክተሮች አሉ። ስለዚህ ያለውን ችግር እዛው በቅርንጫፍ መነጋገር ይሻላል። ምክንያቱም ሳይቶቹ የተለያየ ቦታ ላይ ስለሚገኙ ለሁሉም ከአንድ ቦታ ተጠናቀዋል ወይም አልተጠናቀቁም ብሎ መመለስ ይከብዳል በማለት ይናገራሉ። አቶ ሰለሞን በቅርቡ ይፋ የሚሆን የሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚነት እና ፍላጎት የሚያረጋግጥ አሰራር የተጠና መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህም በቅርቡ ይፋ የሚደረግ መሆኑን ይጠቁማሉ።

[EPA]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መንግሥት ኤምባሲውን በተመለከተ ቅሬታውን አሰማ!

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ለንደን ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባጋጠመው ክስተት አዲስ አበባ ውስጥ ላሉ የእንግሊዝ ኤምባሲ ከፍተኛ ባለስልጣን በይፋ ቅሬታቸውን አሰሙ።ቅሬታቸውን ያሰሙት በዩናይትድ ኪንግደም ለንደን ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደጅ ላይ ከሰሞኑ ለተቃውሞ በተሰበሰቡ ኢትዮጵያዊያን ሰልፈኞች የኢትዮጵያ ባንዲራ እንዲወርድ በመደረጉና በኤምባሲው ሠራተኛ ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ እንደሆነ ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የእነ ጃዋር መሐመድን የቀዳሚ ምርመራ መዝገብ የሚመለከተው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፤ የ6 ተጠርጣሪዎችን የኮሮና ምርመራ ለመጠበቅ እና ተጠርጣሪዎች ባቀረቧቸው አቤቱታዎች ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ለአርብ ነሐሴ 22 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ። በዛሬው ችሎት በቀዳሚ ምርመራ መዝገቡ ላይ በቀዳሚነት የተጠቀሱት አቶ ጃዋር እና በሁለተኛነት የተቀመጡት አቶ በቀለ ገርባ፤ በአጠቃላይ የፍትህ ስርዓቱ ላይ እየታዩ ነው ያሏቸውን ችግሮች በተመለከተ ለችሎቱ አቤቱታዎችን አሰምተዋል።

[Ethiopia Insider]
@YeneTube @FikerAssefa
የፖሊስን የደንብ ልብስ በመልበስ ህገ-ወጥ ተግባር የሚፈጽሙ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አሳሰበ፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የተጠናከረ ፖሊሳዊ ስነ-ምግባር ያላቸው አባላትን ለማፍራት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የገለጹት የአስተዳደር ልማት ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል ጌቱ ተ/ዮሐንስ የደምብ ልብሶቹ በሦስተኛ ወገን እጅ እንዳይገቡና የወንጀል መፈጸሚያ እንዳይሆኑ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል ብለዋል፡፡ምክትል ኮሚሽነር ጄነራሉ አክለውም የፖሊስ አባላቱና ህብረተሰቡ በቅርቡ የሚቀየረውን አዲሱን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አባላት የደምብ ልብስ እንዲያውቁት በማድረግ በነባሩና በአዲሱ ደንብ ልብስ ህገ-ወጥ ተግባር እንዳይፈጸም የመከላከል ስራዎች እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

ከፖሊስ ሙያ ውጭ ያለው ማንኛውም አካል ደምብ ልብሱን መጠቀምና ከዩኒፎርሙ ጋር አመሳስሎ መስራት እንደማይችል በመግለጽ ይህንን ድርጊት የሚፈጽም አካል በህግ ይጠየቃል ሲሉ ገልጸዋል፡፡የፖሊስ አባላትም የራሳቸውን የደምብ ልብስ ለሶስተኛ ወገን መስጠት በህግ እንደሚያስጠይቃቸው ተገንዝበው ተገቢ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ሁሉም የሀገሪቱ የፖሊስ ተቋማት ወጥ የሆነ አሰራር በመከተል ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለማህበረሰቡ መስጠት እንዲችሉ እየተሰራ መሆኑንም ምክትል ኮሚሽነር ጄነራሉ ጠቁመዋል፡፡

[Federal Police Commission]
@YeneTube @FikerAssefa
በክልሉ የጥፋት ተልዕኮ ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 5 ተጠርጣሪዎች በኩርሙክ ወረዳ በኩል ወደ ሱዳን በመውጣት ላይ እያሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ!

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አብዱልአዚም መሀመድ እንደገለጹት፣ የጥፋት ቡድኑን ሲመሩ የነበሩትን ሠሩቅ ሃምዳንን ጨምሮ በክልሉ የጥፋት ተልዕኮ ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 5 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡እነዚህ የጥፋት ኃይሎች በኩርሙክ ወረዳ አቀንደዩ ቀበሌ ወደ ሱዳን በመውጣት ላይ እያሉ በክልሉ የጸጥታ ኃይልል፣ በአመራሩ እና በህብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮሚሽነር አብዱላዚዝ ገልጸዋል፡፡ባለፉት ቀናት የመከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ፖሊስ ከክልሉ የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን በተሠራው ኦፕሬሽን በጉባ ወረዳ መሠል የጥፋት ተልዕኮ ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 158 የጥፋት ኃይሎችና ተባሪዎቻቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አስታውሰዋል፡፡

አሁን በቁጥጥር ስር የዋሉትም መሠል የጥፋት አጀንዳ የያዙ እና ከህወሃት ጋር ጥብቅ ግንኙነት በመመስረት በክልሉ አለመረጋጋት እንዲፈጠር አልመው ሲሠሩ የነበሩ መሆናቸውንም ነው ኮሚሽነሩ በመግለጫቸው ያመለከቱት፡፡የጥፋት ቡድኑ "ከመስከረም 30 በኋላ የሚመራ መንግስት የለም" በሚል ህብረተሰቡን በመቀስቀስ ላይ የነበሩ ናቸው ያሉት ኮሚሽነር አብልአዚዝ፣ ውጪ ተቀምጠው የጥፋት ተልዕኮ ከሚያራምዱ አካላት ጋር ግንኙነት እንዳላቸውም አስታውቀዋል፡፡ህብረተሰቡ ሠላም ፈላጊ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፣ መሠል ምልክቶችን ሲመለከት ለጸጥታ አካላት እየሠጠ ያለው ጥቆማ ትልቅ አቅም መሆኑን ጠቁመው፣ በቀጣይ ይህንኑ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

[የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮ/ጉ/ጽ/ቤት]
@YeneTube @FikerAssefa
የፀረ-ኤች አይ ቪ መድሃኒት የሚወስዱ ሰዎች የበሽታ የመከላከል አቅማቸው ስለሚቀንስ ከሌሎች ሰዎች በበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ይመከራል፡፡

በመሆኑም
1. ወደ ጤና ተቋም የሚያደርጉትን ምልልስ በመቀነስ የቀጠሮ ጊዜ እንዲረዝም ማድረግ
2. መድሃኒታቸውን በትክክልና ሳያቋርጡ መውሰድ
3. ከአደገኛ ሱሶች መራቅ
4. እራስን አለማጨናነቅ፣ የአካልብቃትእንቅስቃሴማድረግ
5. ሌሎች ለኮቪድ 19 መከላከያዎችን መተግበር
6. ህመም ከተሰማ ወዲያውኑ ወደ አቅራቢያ ጤና ተቋም መሄድ እና ሪፖርት ማድረግ፡፡
7. የጸረ-ኤችአይቪ ህክምና የምናገኝበትንና መድሃኒት የምንወስድበትን ጤና ተቋም እንዲሁም የባለሙያ ስልክ ቁጥር መያዝ፣ በስልክ የጤና ባለሙያዎችን ምክር መጠየቅ፣ ማማከር ተገቢ ነው። ተጨማሪ መረጃ ወይም ምክር ከፈለጉ በ952 በነፃ ይደውሉ።

-Lia Tadese, MoH
@YeneTube @FikerAssefa
የአዶኒስ የቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ!

የደራሲ አድነው ወንድይራድ ወይንም አዶኒስ የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡አዶኒስ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በዕሁድ መዝናኛ ፕሮግራም የተላለፉት የገመና እና መለከት ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች ደራሲ ነበር፡፡በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ህንጻ ንድፍ ያጠናው አዶኒስ ከቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማዎች በተጨማሪ የአና ማስታወሻን በመተርጎም ለንባብ አብቅቷል።እንዲሁም የአዶልፍ ሔክማን መጽሐፍ ተርጓሚ፣ የፕሮፌሰሩ መጽሐፍ ፣ የሕጻናት መዝሙሮች እና የበርካታ ፊልሞች፣ የኪነ ጥበብ ሥራዎች ደራሲ እና ተርጓሚ ነበር።ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት የነበረው አዶኒስ ትውልዱ አዳማ ከተማ ነበር፡፡ወዳጆቹ በባህሪው ብዙም ወደ መገናኛ ብዙኀን የመቅረብ እና የመታየት ፍላጎት እንዳልነበረው ይናገራሉ፡፡አዶኒስ በኒሞንያ ህመም ምክንያት በምኒልክ ሆስፒታል ህክምና ሲከታተል የቆየ ሲሆን ከትናንት በስቲያ ህይወቱ አልፏል፡፡

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በማረሚያ ቤቶች በፍጥነት በመስፋፋት ላይ የሚገኘውን የኮሮና ወረርሽኝ ለመቆጣጠር "የይቅርታ እና የአመክሮ መስፈርት የሚያሟሉ የሕግ ታራሚዎች" እንዲለቀቁ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ ሐሳብ አቀረበ።የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ ኃላፊነት በተያዘው ነሐሴ ወር መጨረሻ እንደሚያበቃ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል።

[Eshete Bekele]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ ነው ያለውን ጥገና ማድረጉን አስታወቀ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጥገና ባለሙያዎች ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅን እና የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ የሚያስችል የአውሮፕላን ክንፍ ላይ የምህንድስና ማሻሻያ አድረገዋል።ማሻሻያው በአመት እስከ 500 ሺህ ጋሎን ነዳጅ እንዲቆጥብ ያስችለዋል ተብሏልም።ከዚህም በተጨማሪ ማሻሻያው 277 ሺህ ሜትሪክ ቶን የካርበን ልቀትንም የሚያስቀር በመሆመኑ አየር መንገዱ በአካባቢ ጥበቃ የሚያደርገውን ጥረት የሚያግዝ ነው። 69 የሚሆኑ የአየር መንገዱ የአውሮፕላን ጥገና ባለሙያዎች ሌት ተቀን እና በእረፍት ቀናቸውም በመስራት ጭምር ፕሮጀክቱን በስኬት አጠናቀዋል።

[Ethiopian Airlines]
@YeneTube @FikerAssefa
ዐቃቤ ሕግ ይግባኝ በጠየቀባቸው የኦፌኮ አመራር ደጀኔ ጣፋ፣ የኦሮሞ ሜዲያ ኔትወርክ ጋዜጠኛ ጉዮ ዋርዮ እና ሌሎች ተከሳሾች ላይ በ5 ቀናት ውስጥ ክስ እንዲመሠርት ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዳዘዘ አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል። ዐቃቤ ሕግ በትዕዛዙ መሠረት ክስ ካልተመሠረተ፣ በዋስትና እንዲወጡ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የወሰነውን ብይን አጸናለሁ- ብሏል ችሎቱ።

[AS & Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa