YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በኢትዮጵያ በደረሰው የጎርፍ አደጋ 130 ሺህ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል!

በኢትዮጵያ እስከ ነሐሴ ወር አጋማሽ ድረስ የጣለው ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ የተነሳ 170 ሺህ ያህል ነዋሪዎች ጉዳት ሲደርስባቸው 130 ሺህ ሰዎች ደግሞ ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ምክትል ኮሚሽነር ለቢቢሲ ገለፁ።ኮሚሽነሩ አቶ ዳመነ ዳሮታ ከዚህ በፊት የነበረውን ልምድ ከግንዛቤ በማስገባት በዚህ ዓመት ክረምት ወቅት በጎርፍ ምክንያት ወደ 2 ሚሊየን ያህል ሰዎች ሊጎዱ እንዲሁም 434 ሺህ ያህሉ ደግሞ ሊፈናቀሉ ይችላሉ ተብሎ ግምት መያዙን ተናግረዋል።እንደ ኮሚሽነሩ ገለፃ ከሆነ እስካሁን ድረስ በአዋሽ ወንዝ ሙላት የተነሳ በአፋር ክልል የተጎዱ ሰዎች ቁጥር ወደ 67 ሺህ 885 አካባቢ ሲሆን፣ 40 ሺህ 130 አካባቢ ደግሞ መፈናቀላቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

ኮሚሽነር ዳመነ አክለውም ደቡብ ኦሞ ዳሰነች አካባቢ በኦሞ ወንዝ ሙላትና የግቤ 3 የኃይል ማመንጫ ግድብ ውሃ በተወሰነ መልኩ መልቀቁን ተከትሎ በደረሰ የጎርፍ አደጋ በኦሞ በሚገኙ ከ15 ሺህ በላይ ሰዎች እንዳይጎዱ ከሚኖሩበት አካባቢ የማውጣት ሥራ መከናወኑን ገልፀዋል።እነዚህ ሰዎች በጊዜያዊ መጠለያ እንዲቆዩ መደረጉን ገለፀው ከ10ሺህ በላይ ለሚሆኑት የተለያዩ ድጋፎች ደርሷል ብለዋል። ለቀሪዎቹ 5ሺ ሰዎች ደግሞ ድጋፍ ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን አክለዋል።ዘንድሮ በጎርፍ የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ለቢቢሲ የገለፁት ኮሚሽነሩ፣ ነገር ግን ኮሚሽኑም ሆነ መንግሥት ከሌሎች ጊዜያት በተሻለ ሁኔታ ዝግጅት ያደረጉበት ዓመት እንደነበር ለቢቢሲ አብራርተዋል።በዚህ ዓመት በልግ ወቅት በደረሰው የጎርፍ አደጋ ምክንያት 470 ሺህ ያህል ነዋሪዎች ጉዳት ሲደርስባቸው ከ300 ሺህ በላይ ደግሞ መፈናቀላቸውን ኮሚሽነሩ ጨምረው አስረድተዋል።

ኮሚሽኑ ይህን የበልግ ወቅት አደጋን በመቋቋም ላይ ባለበት ወቅት የክረምቱ ዝናብ ከበልጉ ዝናብ ጋር ተያይዞ በመምጣቱ ወንዞችና ግድቦች በመሙላታቸው በርካቶች ለአደጋ መጋለጣቸውን ተናግረዋል።ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ከነበረው ልምድ በተለየ ሶስት ጊዜ የጎርፍ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ማውጣቱን ገልፀው ሁለቱ ማስጠንቀቂያዎች የወጡት በዚህ ክረምት ወቅት መሆኑን አብራርተዋል።እስከ መስከረም መጨረሻ ተከታታይ ዝናብ ስለሚኖር ጎርፍና የመሬት መንሸራተት ሊከሰት እንደሚችል የገለፁት ኮሚሽነሩ ነሐሴ መጨረሻዎቹ ላይ የተንዳሆ ግድብ ሊሞላ ስለሚችል ቀጣይም ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ፣ እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስም የከሰምና፣ የቆቃ ግድቦች እየሞሉ እንደሚሄዱ በመግለጽ ሁሉም አካላት አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።በመከላከኛውና፣ የታችኛው አዋሽ ላይ ከፍተኛ የመከላከል ስራ እየተሰራ መሆኑን ጨምረው በመግለፅ በዚህም የተነሳ በአዋሽ ወንዝ ሙላት የተነሳ በዚህ የክረምት ወቅት የደረሰው ጉዳት መቀነሱን ተናግረዋል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa
በጋሞ ዞን 10 ወረዳዎች ላይ በተከሰተው የመሬት መሠንጠቅ ፤ ናዳ እና ጎርፍ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ አርሶአደሮች የሰፈራ ፕሮግራም እቅድ ቀረበ።

የጋሞ ዞን ም/ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሀኑ ዘውዴ ለዞኑ ካቢኔ አባላት እንዳስረዱት በዞኑ 10 ከፍታ ላይ የሚገኙ የገጠር ወረዳዎች ዝናብ በጣለ ቁጥር በሰውና ንብረት ላይ በተደጋጋሚ የሚደርሰውን አደጋ በዘላቂነት ለመቅረፍ የተዘጋጀው የሰፈራ ፕሮግራም እቅድ በ3 ዙር ይተገበራል።በ1ኛው ዙር ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያ የሚገኙ 9 ሺ 588 አባወራዎች 52ሺ800 የቤተሰብ አባላት በምራብ አባያ (ቆርጋ እና ሀመሳ)፤በገረሴ(ኮሻሌ )እና በቁጫ ወረዳ (ጎገራ ዳሆ) የሚሰፍሩ ይሆናል።
ለሰፈራው ስኬታማነት 1ቢሊየን 4መቶ ሚሊየን ብር ይፈለጋል።ከፌደራል እስከ ወረዳ መዋቅር ድርሻቸው ምን እንደሆነ የተለየ ሲሆን በዞኑ የሚገኙ የፌዴራል እና የክልል ተቋማት፤ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ብሎም ባለሀብቶች የማይተካ አስተዋጾአቸውን እንዲያበረክቱ የሚያስችል የጋራ ምክክር መድረክ በቅርቡ ይፈጠራል።

የመኖሪያና የእርሻ ቦታ ዝግጅት በምዕራብ አባያ ሀመሳ ቀበሌ በመመቻቸት ላይ መሆኑ የታወቀ ሲሆነ የሰፈራ ፕሮግራሙ በእርሻ ማሳ እጦት፤በምርታማነት መቀነስ ምክንያት የሚቸገረውንና ህይወቱ ክረምት በመጣ ቁጥር ሲፈተን የቆየውን የህብረተሰብ ክፍልን የምግብ ዋስትና ያረጋግጣል። የሰፈራ ጣቢያው መካናይዝድ የግብርና አስተራረስ ተሞክሮ ቅመራ ማእከልም እዲሆን ታቅዶ እየተሰራ ነው።በዞኑ 10 ወረዳዎች በተደጋጋሚ የተፈጥሮ አደጋ በሰው ህይወት ላይ የሚደርሰውን ሞት እና የንብረት ውድመትን በዘላቂነት ለማስወገድ የዞኑ አስተዳዳሪ ለወሰዱት ቆራጥ አመራር እና ውሳኔ በዞኑ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ምክር ቤት ስም ምስጋና ቀርቦላቸዋል።በዞኑ 5 አመት ውስጥ 45 ሰው ህይወት የጠፋ ሲሆን 2012 ዓ.ም ብቻ 24 ሰው ሞቷል።ከዚህ ውስጥ በጋጮ ባባ ወረዳ ብቻ 17 ሰው ህይወት አልፏል ።

[የዞኑ መንግሥት ኮምኒኬሽን]
@YeneTube @FikerAssefa
የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ግድብ ግንባታ ከ35 በመቶ በላይ ደረሰ!

በሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዩሮ ወጪ እየተገነባ ያለው የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ግድብ ግንባታ 35 ነጥብ አንድ በመቶ መድረሱን የውሃ፣መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።የሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ሞቱማ መቃሳ የኮይሻን ግድብ ግንባታ በተመለከተ እንደገለጹት፤ እኤአ መጋቢት 21 ቀን በ2016 ኮንትራት ውል የተፈረመውና በ2,525,054,520 ዩሮ ወጪ እየተገነባ የሚገኘው የኮይሻ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት እስከ ነሐሴ 2012 ዓ.ም መጀመሪያ ወር ድረስ የግንባታው አፈጻጸም 35 ነጥብ አንድ በመቶ ደርሷል።መንግስት የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነትን ለማስፋትና ኢንዱስትሪዎች የሚፈልጉትን ኃይል ለማሟላት የኮይሻን የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫና የታላቁን የህዳሴ ግድብ ጨምሮ ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተገነቡ እንደሚገኙ ገልጸው፤ 2106 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የኮይሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ በሚፈለገው የግንባታ ፍጥነት እየተሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
25 ሚሊዮን ብር ለተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ድጎማ እንደመደበ የትግራይ ክልል ምርጫ ኮሚሽን ገለፀ፡፡

ለ5ቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለእያንዳንዳቸው 1 ሚሊዮን ብር በጥሬው እንዲደርሣቸው እና ቀሪው የቁሣቁስ ድጋፍ እንደሚሆን ኮሚሽነሩ አቶ ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም ተናግረዋል፡፡ለግል ተወዳዳሪዎችም ቢሆን በመገናኛ ብዙሃን የቅስቀሣ ሰዓት እንዲያገኙ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የሚገልፁት ኮሚሽነሩ ነገር ግን በጥሬ ገንዘብ የሚሰጥ ድጎማ የላቸውም ብለዋል፡፡6 የግል ተወዳዳሪዎች ጳጉሜ 4 በትግራይ ክልል 6ኛው ምርጫ ላይ እንደሚሣተፉ ታውቋል፡፡ለግል ተወዳዳሪዎች የተወሰነ የአይነት ድጋፍ እንደሚደረግ ኮሚሽነሩ አቶ ሙሉወርቅ ጠቁመዋል፡፡

[አሃዱ ሬዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
በቤሩት በሕገ ወጥ መንገድ የገቡ ወደ 180 የሚሆኑ ዜጎች የጉዞ ሰነድ ተዘጋጅቶላቸው ወደ አገር ቤት ለመመለስ መዘጋጀቱን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቋል።

[አዲስ ማለዳ]
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ክልላዊ መንግስት ለሚካሄደው የክልል ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ዛሬ ጠዋት ተጀምሯል።የትግራይ ክልል የምርጫ ኮሚሽን ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ክልላዊ ምርጫው በጷግሜ 04/2012 ይከናወናል።

[Addis Standard]
@YeneTube @FikerAssefa
የዓለም ጤና ድርጅት እና ዩኒሴፍ በአፍሪካ ትምህርት ቤቶች ዳግም እንዲከፈቱ ጥሪ አቀረቡ!

የዓለም ጤና ድርጅት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህጻናት አድን ድርጅት የአፍሪካ ሃገራት ትምህርት ቤቶችን ዳግም እንዲከፍቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ድርጅቶቹ ረዘም ላለ ጊዜ ትምህርት ቤቶችን መዝጋት በተማሪዎች ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንደሚያስከትል ገልጸዋል፡፡መንግስታት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዳይስፋፋ ንጽህና መጠበቅ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታወችን መፍጠር ይገባልም ብለዋል፡፡ተማሪዎቹ ረዘም ላለ ጊዜ ቤት ውስጥ ሲቆዩ ለምግብ እጥረት፣ ለቤት ውስጥ ጥቃት እና ያለ እድሜ ለሚከሰት እርግዝና እንደሚጋለጡም ገልጸዋል ፡፡

በአፍሪካ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለህፃናት “ደህና ስፍራ” ናቸው ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ማትሺዲሶ ተናግረዋል፡፡እስካሁን ስድስት የአፍሪካ ሃገራት ብቻ ትምህርት ቤቶችን ሙሉ ለሙሉ ክፍት ሲያደርጉ አንዳንድ ሃገራት የተከፈቱ ትምህርት ቤቶችን በወረርሽኙ ዳግም መስፋፋት ምክንያት ዳግም ዘግተዋል፡፡ሌሎችም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ፈተና ላይ እንዲቀመጡ ትምህርት ቤቶችን ክፍት ሲያደርጉ ኬኒያ በበኩሏ የትምህርት አመቱን ሙሉ በሙሉ ዝግ አድርጋለች፡፡

ምንጭ፡- BBC/FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ከወላይታ ሶዶ-አዲስ አበባ የተዘረጋው ሁለተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር አገልግሎት መስጠት ጀመረ!

ከወላይታ ሶዶ-አዲስ አበባ የተዘረጋው ሁለተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር በነባሩ የጊቤ III- ወላይታ ሶዶ- አዲስ አበባ ታወር ወይም ማማ ላይ በተጨማሪ የተዘረጋ መሆኑን የ400 ኪ.ቮ ፕሮጀክት ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ መሐመድ ሽኩር ተናግረዋል፡፡በፕሮጀክቱ በዋናነት የኤሌክትሪክ ኮንዳክተር እና ኢንሱሌተር ዝርጋታ እንዲሁም የተለያዩ መሳሪያዎች ገጠማ መከናወኑን ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለፃ የተዘረጋው ሁለተኛ መስመር በነባሩ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ይስተዋል የነበረውን የኃይል መጨናነቅ በማስቀረት አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማቅረብ ያግዛል፡፡የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ 400 ኪ.ቮ የኤሌክትሪክ ኃይል የመሸከም አቅም ያለው እና 260 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው ሲሆን ግንባታውን ለማከናወን 7 ነጥብ 8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እና 43 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል፡፡የፕሮጀክቱን ግንባታ የቻይናው ሻንጋይ ኤሌክትሪክ ኩባንያ ያከናወነው ሲሆን የዚህ ፕሮጀክት አካል የሆነው የጊቤ III- ወላይታ ሶዶ ሁለተኛ መስመር ዝርጋታ ለማከናወን በሂደት ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

[EEPCo]
@YeneTube @FikerAssefa
በየመን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ 1ሺህ 200 ኢትዮጵያዊያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ኢትዮጵያን በተለያዩ አገራት ወክለው የሚሰሩ አምባሳደሮች ዓመታዊ ስብሰባቸውን የፊታችን ሰኞ ጀምሮ በአዲስ አበባ እንደሚሰበሰቡ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው።ቃል አቀባዩ በዚህ ጊዜ እንዳሉት በየመን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ 1ሺህ 200 ኢትዮጵያዊያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት IOM ጋር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።እነዚህ ዜጎች በየመን ያለው የእርስበርስ ጦርነት በተጨማሪ የኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ከባድ እንዳደረገባቸው አምባሳደር ዲና ተናግረዋል።

በመሆኑን እነዚህን ዜጎች ወደ አገራቸው ለመመለስ መረጃዎች እየተደራጁ መሆኑን ተናግረዋል።ቃል አቀባዩ አክለውም ባለፉት ሁለት ሳንምታት ውስጥ ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ውይይት መካሄዱን ተናግረዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ከአባይ ተፈሰስ ሀገራት ሚሲዮኖች ጋር የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስከበር ውይይት መካሄዱንም ገልጸዋል።ቃል አቀባዩ አክለውም ኢትዮጵያን በተለያዩ አገራት ወክለው የሚሰሩ አምባሳደሮች ዓመታዊ ስብሰባቸውን የፊታችን ሰኞ ጀምሮ በአዲስ አበባ እንደሚሰበሰቡ ተናግረዋል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ገርጂ በሶስት ቢሊዮን ብር ለሚያስገነባው ዘመናዊ መንደር ከአገር ውስጥና ከውጭ ተቋራጮች ጋር በዛሬው ዕለት ስምምነት ፈፅሟል።

ኮርፖሬሽኑ ስምምነቱም ያደረገው ከኮሪያ ፣ ከህንድና ከኢትዮፕያዊያን የህንጻ ተቋራጮች ጋር ነው።ፕሮጀክቱን ይፋ ያደረጉት የጠቅላይ ሚኒስተሩ የካቢኔ ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊና የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የቦርድ ኃላፊ ወ/ሮ ደሚቱ ሀምቢሳ ናቸው።በስምምነቱ መሰረት በገርጂ መኖሪያ መንደር በሚቀጥሉት 18 ወራት ውስጥ 510 መኖሪያ ቤቶች ይገነባሉ።የሚገነቡት መኖሪያ ቤቶች ባለ 10 ወለል የሚኖራቸው 16 ህንጻዎች ይኖሯቸዋል።የመኖረያ መንደሩ ሲጠናቀቅ በከተማዋ የሚታዩ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ችግርን በተወሰነ መልኩ የሚያቃልል መሆኑን ነው የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ረሻድ ከማል የገለጹት።ግንባታው በዘመናዊ መንገድ የሚገነባ በመሆኑ የግንባታ ወጪውንም ሆነ ጊዜውን የሚያቀላጥፍ መሆኑ ተመክቷል፤አንድ የህንጻ ወለልን በአምስት ቀናት ውስጥ ሰርቶ የሚያጠናቅቅ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ይውላል ተብሏል።ሲኤምሲ ከሚገኘው የኮርፖሬሽኑ የመኖሪያ መንደር ልምድ ተወስዶ ፣ በ3 ሺህ ሄክታር ላይ የሚገነባው ይህ መንደር ሲጠናቀቅ ዘመናዊነትን የተላበሰ ቅንጡ የመኖሪያ መንደር ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

[EBC]
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ሊሸጥ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ሊሸጥ መሆኑን የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ገለጸ።የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የፕሪሚየር ሊግ ውድድር በቴሌቪዥን ማስተላለፍ ለሚችሉ የሚዲያ ተቋማት ሊሸጥ መሆኑ ታውቋል፡፡በሀገሪቱ የሚካሄደው የወንዶች እግር ኳስ የፕሪሚየር ሊግ ውድድር በ16 ክለቦች መካከል በሜዳ እና ከሜዳ ውጭ በሚል የውድድር "ፎርማት" ይካሄዳል፡፡

የኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን በድህረ ገፁ እንዳስነበበው በቀጣይ የሚካሄደውን የፕሪሚየር ሊግ ውድድር በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት የማስተላለፍ ፈቃድ ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ የሚዲያ ተቋማት ለመሸጥ ጫረታ ሊያወጣ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ሊግ "ካምፓኒው" የፕሪሚየር ሊግ ውድድሩን ስም ለመሸጥ በሚቀጥለው ሳምንት ጫራታ እንደሚያወጣም ታውቋል፡፡ከቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት እና ከውድድር ስያሜ ሽያጭ የሚያገኘው ገቢ የ"ካምፓኒውን" እና የተወዳደዳሪ ክለቦችን የገንዘብ አቅም ያሳድጋል ተብሎ ይጠበቃል ሲል ኮሚሽኑ አስነብቧል፡፡

[አብመድ]
@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ አበባ በመረጠችው ከንቲባ እንድትተዳደር ኢዜማ አሳሰበ!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ አዲስ አበባ አንድም በመረጠችው ከንቲባ ለመተዳደር አልቻለችም አሁን እየታዩ ያሉት የሹመት ሂደቶች ለውጥ የሚፈጥሩ አይደለምም ብሏል ዛሬ በሰጠው መግለጫ።የኢዜማ ምክትል መሪ አንዷለም አራጌ እንዳሉት የከንቲባ ሹመት ሂደቱ ጉልቻ ቢቀየር ወጥ አያጣፍጥ ነውና ትክክለኛ መፍትሄ መሆን ያለበት ህዝቡ በሚፈልገው መንገድ ከንቲባውን እንዲመርጥ ምርጫ ማካሄድ ብቻ ነው ብለዋል።በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የተራዘመው ሀገራዊ ምርጫም ቢሆን በቀጣይ ጊዜ ስለመካሄዱ የሚያመላክት ፍንጭ የለም የሚሉት ምክትል መሪው በሀገሪቱ ምርጫ የሌለ እስኪመስል ድረስ ለምርጫ የሚደረገው እንቅስቃሴ ሞቷልተ ብለዋል።በመሆኑም ለቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ በቂ ዝግጅት ይደረግ ዘንድ ከወዲሁ እንቅስቃሴዎች ሊጀመሩ ይገባል ሲል ጠይቋል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
"ለውጡን ለማስጠበቅ የመንግስት ሆደ-ሰፊነትና ትዕግስት አስፈላጊ ነበር።አሁን ላይ ግን ያ አብቅቷል።የህግ የበላይነትን እናስከብራለን።"

የኦሮምያ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ታዬ ደንዳአ ለአሐዱ መድረክ

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በ2012 በጀት ዓመት ከ1.5 ቢሊዬን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን የወባ በሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ የወባ መከላከያ ኬሚካል፣ አጎበሮች እና የወባ መድኃኒቶች አሰራጭቻለው ብሏል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ሪችላንድ ፒልሲ በቡሬ ኢንደስትሪ ፓርክ በ991,000,000 ብር ወጭ የገነባው የአኩሬ አተር ፕሮቲንና የምግብ ዘይት ማምረቻ ፋብሪካ ስራውን ጀመረ:: በሙሉ አቅሙ ሲያመርትም ከኤክስፖርት 61,680,000 ዶላር ያስገኛል ለሀገር ውስጥ ፍጆታ ደግሞ 22,500,000 ሊትር ዘይት ያመርታል::

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
ያሸጉትን ንግድ ቤት ለመክፈት 50 ሺ ብር ጉቦ የተቀበሉ አምስት የንግድና ኢንዱስትሪ ሰራተኞች እጅ ከፍንጅ ተያዙ፡፡

ያሸጉትን ንግድ ቤት ለመክፈት 50 ሺ ብር ጉቦ የተቀበሉ አምስት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ንግድና ኢንዱስትሪ ሰራተኞች እጅ ከፍንጅ ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ዋጋ ጨምረሻል በሚል ምክንያት የወረዳው ንግድና ኢንዱስትሪ ሰራተኞች ነሃሴ 11 ቀን 2012 ዓ/ም የስሚንቶ ማከፋፈያ ንግድ ቤታቸውን እንዳሸጉባቸው ወ/ሮ ሂሩት አላታ ገልፀዋል፡፡አንድ መቶ ሺ ብር ጉቦ ከሰጡ ንግድ ቤቱ እንደሚከፈት ነገር ግን በድርድር 50 ሺ ብር ለመስጠት እንደተስማሙ እና ጉዳዮን ለፖሊስ ሪፖርት ማድረጋቸውን ወ/ሮ ሂሩት አስረድተዋል፡፡መረጃው የደረሰው የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ባደረገው ክትትል ግለሰቦቹ ነሃሴ 13 ቀን 2012 ዓ/ም የታሸገውን ንግድ ቤት በመክፈት ገንዘቡን ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የጉዳዩ መርማሪ ሳጅን ተስፋ ወልደሃና መግለጻቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ያሳያል፡፡

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
“በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ሰባት ቀናት ብቻ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር የ 58 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡”-ጤና ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ሰባት ቀናት (ከነሃሴ 8-14) 4ሺህ 767 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው በምርመራ ተረጋግጧል፡፡በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከነሃሴ ወር መጀመርያ ተመዝግቦ ከነበረው 3016 አንጻር የ 1 ሺህ 751 ወይም የ 58 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን የከተማዋ ጤና ቢሮ አስታውቋል፡፡ይህም የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ያሳያል ተብሏል፡፡በሌላ በኩል ባለፉት ሰባት ቀናት በከተማዋ 119 ሰዎች በኮቪድ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል፡፡በነሃሴ ወር መጀመርያ 93 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን በዚህ ሳምንት 119 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል፡፡24 በመቶ የሚሆነው የሞት መጠን የተመዘገበው በያዝነው ወር በሁለተኛ ሳምንት በነበሩት ሰባት ቀናት መሆኑ ተገልጿል፡፡ይህም ከባለፈው ሳምንት አንጻር የ 26 ሰዎች ህልፈት ወይም 28 በመቶ ጭማሪ እንዳለው ቢሮው አስታውቋል፡፡

[AMN]
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮ ቴሌኮምን በከፊል ወደ ግሉ ዘርፍ ለማዞር እና ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በዘርፉ ለመሰማራት የሻቱ የውጭ አቻ ኩባንያዎች ምዘና ተጠናቆ፣ ዘርፉን ለመምራት አማካሪ ድርጅት ተቀጠረ ተባለ።

[በሸገር ራዲዮ]

ወደ ኢትዮጵያ የቴሌኮምን አገልግሎት ለማቀላጠፍ ፈቃድ የሚሰጣቸው ኩባንያዎች የዋጋቸው ግምት ተሠርቶ መጠናቀቁን ሰምተናል። ባለፉት ጥቂት ቀናት የኢትዮጵያ መንግሥት በቴሌኮም ዘርፍ በሚያደርገው ሪፎርም ሂደት ዙርያ አወዛጋቢ ሪፖርቶች ተሰምተዋል።ሰሞኑን በተሰማው አወዛጋቢ ሪፖርቶች እና ዘርፉን በከፊል ለግሉ ክፍት በማድረግ ዙሪያ የመንግሥትን ቁርጥ ሐሳብ ለመስማት ሸገር የገንዘብ ሚኒስቴር ሚንስትር ደኤታ የሆኑት ዶ/ር እዮብ ተካልኝን ማብራርያ እንዲሰጡት ጠይቋል።ዶ/ር እዮብ ሰሞኑን በተሰራጩት አወዛጋቢ ሪፖርቶች የተፈጠሩ ውዥንብሮችን ለማጥራት የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን በቅርቡ መግለጫ ይሰጣል ብለውናል።

ዶ/ር እዮብ በ'ፕራይቬታይዜሽን' እና 'ሊበራላይዜሽን' ዙሪያ ብዙ ጊዜ ብዥታ አለ ብለውናል።የኢትዮ ቴሌኮምን 40 በመቶ ድርሻ መሸጥ እና 2 አዳዲስ የውጭ የቴሌኮም አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን ሐገር ቤት ማስገባት የተለያዩ ሥራዎች እንደመሆናቸው፣ ለያይቶ ማየት ያስፈልጋል ብለዋል።የቴሌኮም ሥራ እንዲሠሩ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የውጭ ኩባንያዎች የሚሰጣቸው ፈቃድ ብዙ ዋጋ ተሰጥቶታል ብለዋል።ቴሌኮምን በከፊል ወደግል ለማዞር ሥራዎች ተጠናቅቀው ተወዳድሮ ያሸነፈው አማካሪ ድርጅት ወደ ሥራ ይገባል ተብሏል።ኢትዮ ቴሌኮም ለዚህ ሪፎርም ከፍተኛ ሥራ እንዳከናወነ የፋይናንስ ሚኒስትር ደኤታው ተናግረዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም ለዚሁ ሥራ አዋጁ ሲዘጋጅ ጀምሮ በየጊዜው ከፍ ያለ ድጋፍ እያደረገ የቆየ ሲኾን፣ አሁንም እያደረገ እንደሆነ ሰምተናል።ከ'ሊበራላይዜሽን' በኋላ ኢትዮ ቴሌኮም ራሱ እንደ አንድ አገልግሎት ሰጪ ተቋም ቁጥጥር ይደረግበታል ብለዋል ዶ/ር እዮብ።በቅርቡም በጉዳዩ ላይ መንግሥት ከሕዝቡ ጋር እንደሚመክር ዶ/ር እዮብ ተናግረዋል።መንግሥት የጀመረውን የቴሌኮም ሪፎርም ሥራ እንደማያቆምና በብርቱ እንደሚጓዝበት ያስረዱት ሚንስትር ደኤታው፣ በዚህ ዙሪያ የተቀየረም ሆነ የሚቀየር ነገር የለም ብለዋል።በኢትዮጵያ ተግባራዊ የሚደረገው በከፊል የቴሌኮም ድርሻ ሽያጭን በተመለከተ፣ አዲስ ለሚገቡት ሁለቱ ኩባንያዎችና ለኢትዮ ቴሌኮም የቴሌ ማማ እየተከሉ ለማከራየት የናፈቁ የውጭ ኩባንያዎች ፈቃድ እንዲሰጣቸው እየጠየቁ ቢሆንም፣ ይህ ግን አልተፈቀደም ተብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ እስር ቤቶች እና ማጎሪያ ጣቢያዎች ኮሮና ቫይረስ እየተስፋፋ እንደሆነ እንግሊዝኛው ቪኦኤ ዘግቧል፡፡ በኦሮሚያ ክልል የአዳማ ከተማ ጤና ባለሙያዎችን የጠቀሰው ዘገባው፣ በከተማዋ አንዳንዴ በእስር ቤቶች ባንድ ክፍል ውስጥ እስከ 150 ታሳሪዎች ይገኛሉ ብሏል፡፡ በሰኔ በክልሉ የተከሰተውን ሁከት ተከትሎ በርካታ ሰዎች በመታሰራቸው፣ በቫይረሱ የሚያዙ ታሳሪዎች ቁጥር እያሻቀበ ነው፡፡

[Wazema]
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,829 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲያዙ፣ 17 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል!

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገው 23,035 የላብራቶሪ ምርመራ 1,829 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል።በተጨማሪም 377 ሰዎች አገግመዋል።በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 37,665 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 637 ደርሷል፤ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 13,913 ደርሷል።

@YeneTube @FikerAssefa