YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#News_alert በጣልያን በ24 ሰዐት ውስጥ 3,493 አዲስ ኬዝ እና 575 ሞት ተመዝግቧል።

በጣልያን 172,434 በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ሲኖሩ 22,745 ህይወታቸውን አተዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
በትግራይ የኮሮና ቫይይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በተካሄደው የቤት ለቤት ዳሰሳ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ቤቶችን ማዳረሱን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ!

በትግራይ ክልል ኮሮና ቫይይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በተካሄደው የቤት ለቤት ዳሰሳ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ቤቶች በማየት ውጤታማ ስራ ማከናወኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ።አጠቃላይ በቫይረሱ የተጠረጠሩ 33 ሰዎች ተለይተው የደም ናሙናቸው ለምርመራ እየተወሰደ መሆኑ ተመልክቷል።

የቢሮው ኃላፊ ዶክተር ሓጎስ ጎደፋይ ዛሬ ጥዋት በሰጡት መግለጫ “ቫይረሱን ለመከላከል ባለፉት አራት ቀናት በመላው የክልሉ ከተሞችና ወረዳዎች የተደረገው የዳሰሳ ስራ ውጤታማ ነበር” ብለዋል።በዳሰሳ ስራውም በእያንዳንዱ ቤተሰብ አባላት የኮሮና ቫይረስ ግንዛቤን፣ያሉት የመከላከያ ግብአት፣በቫይረሱ የተጠረጠሩ ሰዎችና በቅርብ ጊዜ አዳዲስ ወደ ክልሉ የገቡ ሰዎችን መለየት መቻሉን ዶክተር ሓጎስ ተናግረዋል።

ምንጭ: ኢፕድ
@YeneTube @FikerAssefa
ኢራን" የጦር ሰራዊት " ቀኗን በወታደር ሳይሆን በህክምና መሳሪያዎች ትዕይንት አክብራለች።

ዛሬ በኢራን" የጦር ሰራዊት " ቀን ላይ ወታደሮች ፣የጦር መሳርያና ጀቶች በአደባባይ አልታዩም።ይልቁንስ በኮሮናቫይስ የሞቱ ፣የታመሙ እና ቫይረሱ ከገባ ቀን ጀምሮ ለተዋደቁ ዜጎቿን ለማሰብ ወታደሮች የህክምና ጋዎን በማድረግ በተንቀሳቃሽ ክሊኒክ የሆስፒታል እቃዎችን አንዲሁም መድሀኒቶችን ወደ መንገድ በማውጣት ምንም ታዳሚ በሌለበት መንገድ በመኪና በማዘዋወር ቀኑን አስባለች።

" ለጤናችን ስንል ትዕይንቱን ሰው አንዲታደመው አላደረግንም ።አሁን ሀገራችንን የገጠመው ጠላትን እየተዋጉልን ያሉት ዶክተሮችና ነርሶች ናቸው ።ትልቅ ክብር ይገባቸዋል " ሲሉ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሮሀኒ ተናግረዋል።

Via:- Tesfay genet
@Yenetube @Fikerassefa
ቻይና የኮሮና ወረርሽኝን ስፋት ደብቃለች፤ ከዓለም ጤና ድርጅት የተለየ ግንኙነት አላት በሚል ከአሜሪካ እና ምዕራባውያን የቀረበባትን ወቀሳ አስተባበለች።

ወረርሽኙ በተቀሰቀሰባት የውኻን ከተማ በኮሮና የሞቱ ሰዎች ቁጥር ቀድሞ የቻይና መንግሥት ካሳወቀው 50 በመቶ ጨምሯል።

የቻይና ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ዢያዎ ሊጅያን መንግሥታቸው ለዓለም ጤና ድርጅት፣ የሚመለከታቸው አገሮች እና ቀጠናዎች የወረርሽኙን ኹኔታ በግልፅነት እና በኃላፊነት ያሳውቅ እንደነበር በዛሬው ዕለት ተናግረዋል። ቻይና ከዓለም ጤና ድርጅት እጅግ የቀረበ ግንኙነት አላት በሚል ከአሜሪካ እና ምዕራባውያን ፖለቲከኞች የሚቀርበውን ወቀሳም "ስም የማጥፋት ዘመቻ" ሲሉ ቃል-አቀባዩ አጣጥለዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቻይና የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የወሰደቻቸው እርምጃዎች እና ስለወረርሽኙ የምታቀርባቸውን መረጃዎች በተደጋጋሚ ሲያጣጥሉ ሰንብተዋል።
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኤማኑዌል ማክሮ እና የብሪታኒያው ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ዶሚኒክ ራብ በጉዳዩ ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው ገልጸዋል።
አስራ አንድ ሚሊዮን ሰዎች በሚኖሩባት የውኻን ከተማ በኮሮና ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ቀደም ሲል ቻይና ይፋ ካደረገችው በላይ ሆኖ መገኘቱ ተጨማሪ ጥርጣሬ ጭሯል።

የከተማው ባለሥልጣናት በወረርሽኙ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 3,869 መሆኑን ዛሬ ይፋ አድርገዋል። ይኸ ከቀደመው በ1,290 ሰዎች ሞት ከፍ ያለ ነው። የቻይና ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ዢያዎ ሊጅያን ግን አገራቸው ምንም የደበቀችው ነገር የለም ሲሉ ማስተባበያ ሰጥተዋል። የቻይና ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ዢያዎ ሊጅያን "ወረርሽኙ በአቅም ማነስ ምክንያት አንዳንድ ሆስፒታሎች ከበሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ የመረጃ ሥርዓት ጋር በሰዓቱ መገናኘት አልቻሉም ነበር።

ሆስፒታሎች ተጨናንቀው፤ የሕክምና ባለሙያዎች ሕሙማንን በመርዳት ተወጥረው ነበር። ዘግይተው የቀረቡ፤ ጭርሱን ያልቀረቡ እንዲሁም ሐሰተኛ ሪፖርቶች ነበሩ። ይሁንና ምንም መሸፋፈን አልነበረም። እንደዚያ እንዲደረግም አንፈቅድም" ሲሉ ተናግረዋል።

ቃል-አቀባዩ የቻይናን ስም ያጠፋሉ ያሏቸውን አገሮች በስም አልጠቀሱም። አገራቸው በሑባይ ግዛት ውኻን ከተማ የተቀሰቀሰውን የኮሮና ወረርሽኝ ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ በመጣል የተቆጣጠረችው ከግዛቷ ተሻግሮ ዓለምን ካዳረሰ በኋላ ነበር። በቻይና መንግሥት መረጃ መሠረት 4,632 ሰዎች በኮሮና ሳቢያ ሕይወታቸውን አጥተዋል።

Via:- DW
@Yenetube @Fikerassefa
#አዲስ_አበባ_ዛሬ

#በአከባቢያችሁ_ያለውን የቀንድ ከብት ገበያ ፎቶ አጋሩን ጥንቃቄ የጎደለው ወይንም ጥንቃቄ የተሞላበት ከሆነም እናጋራለን።

አላማው አንዱ ከሌላው እንንዲማር ነው።
ሠመራ ዩንቨርሲቲ Covid-19 ለመከላከል ይረዳ ዘንድ ሳንታይዘር እና ከእጅ ኒኪኪ ነፃ የሆነ የእግር መርገጫ ያለው የውሃ መታጠቢያ እና ሣሙና ማድረጊያ machine ሠርቶ ፤ገዝተው መጠቀም የማይችሉትን የማህበረሰብ ክፍል በመለየት፤ ለማከፋፈል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ዝግጅቱን መጨረሱን የዩንቨርስቲ የሚዲያ አካላት አሳውቀውናል።

@YeneTube @Fikerassefa
የጃፓኑ ጠቅላይ ሚንስትር፡ “ወረርሽኙ ሲገታ የዓለም ጤና ድርጅት መገምገም አለበት”

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚንስትር ሽንዞ አቤ፤ ወረርሽኙ ካለፈ በኋላ የዓለም ጤና ድርጅት መገምገም አለበት አሉ።

ሆኖም ግን መንግሥታቸው ድርጅቱን መደገፍ እንደማያቆም ገልጸዋል።

“አሁን የዓለም ጤና ድርጅትን የምንደግፍበት ወቅት ነው። ያለንበት ሁኔታ እልባት ሲያገኝ ግን ድርጅቱ መፈተሽ አለበት። እውነታው ብዙ ጉዳዮችና ፈተናዎች መኖራቸው ነው” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህን አስተያየት የሰጡት፤ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አገራቸው ለድርጅቱ የምታደርገውን ገንዘብ ድጋፍ እንደምታቆም ይፋ ካደረጉ ከቀናት በኋላ ነው።

Via:- BBC
ምስል፦ ጌቲ ኢሜጅስ
@Yenetube @Fikerassefa
ጀርመን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን መቆጣጠሯን ገለጸች

የጀርመን ጤና ሚኒስትር የንስ ስፓን በአገራቸው በኮሮናቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነስ ማሳየቱን ተከትሎ አገራቸው ወረርሽኙን መቆጣጠሯን ተናገሩ።

ሚኒስትሩ እንዳሉት ከቅርብ ቀናት ወዲህ ከበሽታው የሚያገግሙት በበሽታው ከሚያዙት ሰዎች ቁጥር በቋሚነት እየጨመረ መሄዱ የእንቅስቃሴ ገደቡ ውጤታማ እንደሆነ ያሳያል ብለዋል።

"ዛሬ ወረርሽኙ መቆጣጠር የሚቻል መሆኑን ተገንዝበናል" ሲሉ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተናገሩት ሚኒስትሩ የአገራቸው የጤና እንክብካቤ ሥርዓት እስካሁን በወረርሽኙ ምክንያት ከአቅሙ በላይ የሆነ ችግር እንዳላጋጠመው ተናግረዋል።

Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa
በአፍሪካ በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር ባለፈው ሳምንት በ51%፤በተሕዋሲው የሞቱ ሰዎች 60% መጨመሩን ዶ/ር ቴድሮስ ተናገሩ።«የመመርመሪያ ቁሳቁሶች ለማግኘት ባለው ወቅታዊ ፈተና ምክንያት ትክክለኛው ቁጥር ሪፖርት ከተደረገው ሊበልጥ ይችላል» ብለዋል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
“በማንኛውም ጊዜ ጠንቃቃና ዝግጁ ሆኖ መገኘት የጠቢብነት መገለጫ ነው”

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህ


በማንኛውም ጊዜ ጠንቃቃና ዝግጁ ሆኖ መገኘት የጠቢብነት መገለጫ ነው።የምናውቀውንና የምናምነውን መተግበር ሲያቅተን ለምን ? ብለን መጠየቅ ይኖርብናል።በከፍታ የሚኖር እኛነታችንን ከልዕልና ወደ ዝቅታ የሚገፋብንን አጋጣሚ በሌሊት ጨለማ እንደሚመጣ ውስጥ አዋቂ ሌባ መቁጠር ነው።

በጨለማ ውስጥ አድብቶ ሀብታችንን ሊቀማ የሚመጣን ውስጥ አዋቂ ሌባ ጠመንጃ ታጥቀን አንመልሰውም።ጩቤ ታጥቆ መጠበቅም ቢሆን ብዙም ከጉዳት አያድነንም።

በጨለማ ከሚመጣ ውስጥ አዋቂ ሌባ በሚገባ መከላከል የምንችለው በአዕምሯዊ ብርሃን ነው። አዕምሯዊ ብርሃን ማለት ልቡና ነው። ልብ ማድረግ ማለት መረጃን መቀበል፣ ማሰላሰል፣ ማገናዘብና ባገናዘቡት ልክ መተግበር ነው። ጨለማ ሁሉ በብርሃን ይሸነፋል።ጥፋትም

የሚሸነፈው በልቡና ነው። ጠንቃቃና ሥነ ምግባራዊ መሆን ከልቡና የሚገኝ ነው። ነገሮችን ልብ እንበል፤ ጊዜ ሰጥተን እናሰላስል፣ እንገንዘብ፣ ከዚያም በተገነዘብነው ልክ እንተግብር፣ ባወቅነው ልክ እንኑር።

ከስሜት ርቀን፣ በልቡና ተመርተን የሰውን ልጅ የማስተዋል ደረጃ በሚመጥን ምግባርና ሰብአዊነት የምንደምቅበት ፣ ኢትዮጵያዊነትን ደግሞ በአልማዝ የምናስጌጥበት ታሪካዊ ወቅት ላይ እንገኛለን። ወደታች ስንሄድ ጨለማ ነው። ወደ ላይ ስንሄድ ብርሃን። ወደ ላይ ወደ ዕውቀትና ምግባር ከፍታ እንሂድ። በብርሃንም መንገድ እንመላለስ፡፡

Via:- EPA
@Yenetube @Fikerassefa
የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለሁለተኛ ጊዜ በሀዋሳ ከተማ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ የኬሚካል እርጭት ዛሬ በዓል ዋዜማ ከ12:00 ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል።

ወቅቱም የትንሳኤ በዓል እንደመሆኑ ህብረተሰባችን በዓሉን ለማክበር በሚያከናውናቸው ሀይማኖታዊና የበዓሉ ስነ-ስርዓቶች ላይ ያለምንም ቸልተኝነት የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል የሚተላለፉ መልዕክቶችን ተግባራዊ በማድረግ ፣ በከብት እርድ ፣ በገበያ ቦታዎች፣ በቤት ውስጥ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳይዘነጋ ሲል የከተማው ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ አስታውቋል ።

@Yenetube @Fikerassefa
ጥብቅ ማሳሰቢያ ለስጋ ቤቶች (ሉካንዳ ቤቶች) በሙሉ;-

የኮሮናን ቫይረስ ወረርሽኝም ሆነ ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን ስርጭት ለመከላከልና ለመከላከል ሲባል በፌዴራል ደረጃ አዋጅ መውጣቱ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዴታዎች መፈፀም የበሽታውን ስርጭት ለመግታት አስተዋፅኦ የሚያደርግ በመሆኑ ሁሉም ስጋ ቤት (ሉካንዳዎች) ለተግባራዊነቱ አስፈላጊውን ትብብር እንድታደርጉ የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ጥሪውን ያስተላልፋል።

ዋና ዋና ግዴታዎች !!!

1. ማንኛውም ስጋ ቤት (ሉካንዳ) ስጋ አስገብቶ ከመሸጡ (አገልግሎት ላይ እንዲውል) ከመደረጉ በፊት ሙሉ ለሙሉ ስጋ ቤቱንና መጠቀሚያ ቁሳቁሶችን በውሃ ሳሙናና በረኪና በመጠቀም መፀዳት አለበት፣

2. ማንኛውም ስጋ ቤት (ሉካንዳ) የሚያስገባው ስጋ ህጋዊ እና ከታወቀ ቄራ ታርዶ የቀረበ መሆን አለበት፣

3. ማንኛውም በስጋ ቤት (በሉካንዳ) የሚሰራ ሰራተኛ የስጋ ሽያጭ በሚያከናውንበት ጊዜ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል (ማስክ)፣ ቆብ፣ ጋዎን መጠቀም አለበት፣

4. በማንኛውም በስጋ ቤት (በሉካንዳ) ገንዘብ የሚቀበልና ስጋ የሚቆርጥ ሰራተኛ መለየት አለበት፣

5. በማንኛውም ስጋ ቤት (ሉካንዳ) ውስጥ ለሰራተኞች የእጅ ሳሙናና ውሃ ተዘጋጅቶ በየጊዜው እጃቸውን በመታጠብ አገልግሎት መስጠት አለባቸው፣

6. በማንኛውም ስጋ ቤት (ሉካንዳ) ሽያጭ በሚከናወንበት ወቅት ተገልጋዮች ከመሸጫ መስኮቱ 1 (አንድ) ሜትር ርቀው እንዲቆሙና እንዲገለገሉ መደረግ አለበት፣

7. በማንኛውም ስጋ ቤት (ሉካንዳ) ድርጅት ውስጥ የተገልጋይ ቁጥር ከሁለት በላይ በሚሆንበት ወቅት ድርጅቱ ተገልጋዮችን እያንዳንዳቸው ርቀታቸውን በየሁለት እርምጃ ጠብቀው እንዲቆሙና እንዲገለገሉ መደረግ አለበት፣

8. ከምግብ ቤቶች ጋር የተያየዙ ሉካንዳ ቤቶች ውስጥ ያልበሰለ ስጋ (ቁርጥ/ጥሬ ስጋ፣ ያልበሰለ ክትፎ) ለምግብነት ማቅረብ ለበሽታው ስለሚያጋልጥ የተከለከለ ነው፣

ምንጭ:- አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
@Yenetube @FikerAssefa
ህብረተሰቡ ከልኳንዳ ቤቶች ስጋ ሲገዙ በቄራ ውስጥ ስለመታረዱ ማረጋገጥ አለባቸው ዶ/ር ገ/እግዚአብሔር ገ/ዮሐንስ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አሳስበዋል ።

@Yenetube @Fikerassefa
በኢትዮጵያ በመንገድ ስራ ተቋራጭነትእና በአማካሪ ድርጅትነት የተሰማሩ ድርጅቶች 12 ባለሃብቶች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያግዝ 15 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር አበረከቱ ፡፡

በዛሬው እለት በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋናው መ/ቤት በተዘጋጀው በዚሁ መርሃ ግብር ላይ አስራ ሁለት አገር በቀል የመንገድ ግንባታ ስራ ተቋራጮች ናቸው የ15.3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረጉት ፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይም የሰንሻይን ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና ኮንስትራክሽን ባለቤት የክብር ዶ/ር ሳሙኤል ታፈሰ ተቋራጮችን በመወከል የብር ስጦታውን ለተቋቋመው የብሔራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አባላት አስረክበዋል፡፡

በመድረኩ ላይም እኛ በመንገድ ግንባታ ዘርፍ እየተሳተፍን ያለን የደረጃ አንድ ተቋራጮች ወቅታዊው ወረርሽኝ በህይወት፣ በጤና፣በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ ይበልጥ ሀገራዊ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል ከመንግስት ጎን በመቆም በራሳችን ተነሳሽነት ድጋፍ በማድረጋችን ደስተኞች ነን ብለዋል ፡፡ በቀጣይም ይህን መሰሉ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡

ባለሃብቶቹ ለወጎኖቻቸው ያበረከቱትን የገንዘብ ድጋፍ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ሃብታሙ ተገኘ እንዲሁም የብሔራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ እና የንግድ እና ኢንደስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋናው አርጋው ተረክበዋል ፡፡

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሃብታሙ ተገኘ የተከሰተውን አስከፊ ወረርሽኝ ለመከላከል በሚደረገው ሂደት ባለሃብቶቹ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የብሔራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ እና የንግድ እና ኢንደስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋናው አርጋው በበኩላቸው ባለሃብቶቹ ሀገራዊ ሃላፊነታቸውን በመወጣት ለወገኖቻቸው ላሳዩት አለኝታነት ያላቻውን ምስጋና እና አድናቆት ገልጸዋል::

የገንዘብ ድጋፉን ያበረከቱት ድርጅቶች እና የገንዘብ መጠን
ተ.ቁ የተቋራጭ ስም የገንዘብ መጠን

1. ሰንሻይን ኮንስትራክሽን - 2 ሚሊዮን ብር
2. አለማየሁ ከተማ - 2 ሚሊዮን ብር
3. ኤን ኬ ኤች ኮንስትራክሽን - 2 ሚሊዮን ብር
4. ተክለብርሃን አምባዪ ኮንስትራክሽን - 2 ሚሊዮን ብር
5. ዮቴክ ኮንስትራክሽን - 2 ሚሊዮን ብር
6. ራማ ኮንስትራክሽን - 1 ሚሊዮን ብር
7. ሜልኮን ኮንስትራክሽን -1 ሚሊዮን ብር
8. እንይ ኮንስትራክሽ -1 ሚሊዮን ብር
9. ማርካን ኮንስትራክሽን - 1 ሚሊዮን ብር
10. ፓወርኮን ኮንስትራክሽን -500 ሺብር
11. ዮንአብ ኮንስትራክሽን - 500 ሺ ብር

12. ራባ እና ሶን ኃ /የተ/ የግ/ማ 300 ሺብር

ድምር 15 ሚሊዮን 300 ሺ ብር

Via:- ERA
@Yenetube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕከት.
@YeneTube @Fikerassefa
የኢሰመኮ ጋዜጣዊ መግለጫ

- የመዘዋወር ነጻነትን በተመጣጣኝ መንገድ ብቻ ስለመገደብ

- በመዘዋወር ነጻነትና የትራንስፖርት ገደብ ላይ በቅድሚያ ማስጠንቀቂያ መስጠት ያስፈልጋል።

https://bit.ly/34Lxrxf