በግብይት ቦታዎች አካላዊ መራራቅ እንዲጠበቅ ጠ/ሚ ዐቢይ አሳሰቡ
ግብይት ቦታዎች ውስጥ ኮቪድ-19ን ለመከላከል በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ደንብ መሠረት አካላዊ መራራቅ እንዲጠበቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሳስበዋል።
“ገበያዎች ለብዙዎች የገቢ ምንጭ በመሆናችው የማኅበረሰባችንን የኑሮ ደኅንነት ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በፌስ ቡክ ገፃቸው፣”ሸማቾችም ለኑሮ ሸመታዎቻቸው በገበያ ላይ ጥገኛ ናቸው”ብለዋል።
ይሁን እንጂ “በገበያዎቻችን ውስጥ ኮቪድ-19ን ለመከላከል በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ደንብ መሠረት አካላዊ መራራቅን በማክበር የቫይረሱን ሥርጭት ለመቆጣጠር እያንዳንዳችን የራሳችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባል” ብለዋል።
Via:- Walta
@Yenetube @Fikerassefa

#Update
ጅቡቲ ባንድ ቀን 83 በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን በማግኘቷ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 298 እንደደረሱ ሆርን ዲፕሎማት በድረገጹ ዘግቧል፡፡ ኬንያ ደሞ ዛሬ 11 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች እና የ1 ሰው ሞት ማስመዘገቧን የሀገሪቱ ጋዜጦች ዘግበዋል፡፡

እስካሁን ድረስ አንድም የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ሪፖርት ያላደረጉ ሀገራት:
1. ኮሞሮስ
2. ኪሪባቲ
3. ሌሶቶ
4. ማርሻል ደሴቶች
5. ሚክሮኔዥያ
6. ናውሩ
7. ሰሜን ኮሪያ
8. ፓላው
9. አሜሪካ ሳሞኣ
10. ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፕል
11. ሶሎሞን ደሴቶች
12. ታጂክስታን
13. ቶንጋ
14. ቱርክሜንስታን
15. ቱቫሉ
16. ቫኗቱ
ምንጭ: አልጃዚራ
@YeneTube @FikerAssefa
1. ኮሞሮስ
2. ኪሪባቲ
3. ሌሶቶ
4. ማርሻል ደሴቶች
5. ሚክሮኔዥያ
6. ናውሩ
7. ሰሜን ኮሪያ
8. ፓላው
9. አሜሪካ ሳሞኣ
10. ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፕል
11. ሶሎሞን ደሴቶች
12. ታጂክስታን
13. ቶንጋ
14. ቱርክሜንስታን
15. ቱቫሉ
16. ቫኗቱ
ምንጭ: አልጃዚራ
@YeneTube @FikerAssefa
በኢኳዶር በኮሮና የሞቱ ሰዎች አስክሬን በየመንገዱ እየተጣለ ነው!
በኢኳዶሯ ትልቋ ከተማ ጉዓያኪል ነዋሪዎች በኮሮናቫይረስ ምክንያት የሞቱ ዘመዶቻቸውን ሳይቀብሩ ለቀናት መቆየት ግድ ሆኖባቸዋል።የሟቾች ቁጥር ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ መንግሥት የሚሞቱ ሰዎችን አስክሬን ለመቅብር ከአቅሙ በላይ ሆኗል።
Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በኢኳዶሯ ትልቋ ከተማ ጉዓያኪል ነዋሪዎች በኮሮናቫይረስ ምክንያት የሞቱ ዘመዶቻቸውን ሳይቀብሩ ለቀናት መቆየት ግድ ሆኖባቸዋል።የሟቾች ቁጥር ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ መንግሥት የሚሞቱ ሰዎችን አስክሬን ለመቅብር ከአቅሙ በላይ ሆኗል።
Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በሀረር ከተማ ተቋርጦ የነበረው የታክሲ አገልግሎት በከፊል መጀመሩ ተገለጸ።
በሀረር ከተማ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ተቋርጦ የሰነበተው የታክሲ አገልግሎት በከፊል መጀመሩን የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ገለጸ። የሀረሪ ክልል መንገድ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮው ሃላፊ አቶ ፈርሃን ዚያድ እንደገለጹት በክልሉ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የታክሲ አገልግሎት ተቋርጦ ቆይቷል።በአሁኑ ወቅት ግን የትራንስፖርቱ አገልግሎት በከፊል እንዲጀምር መወሰኑን ገልጸዋል።
በትራንስፖርቱ አገልግሎቱም ተሽከርካሪዎቹ በሙሉና ጎዶሎ ቁጥር ለህብረተሰቡ አገልግሎት ይሰጣሉ ሲሉም ተናግረዋል።በተለይ የታክሲ አሽከርካሪዎቹ ተሳፋሪዎቹ ከኮሮና ቫይረስ እራሳቸውን እንዲከላከሉ የሳኒታይዘር ካልሆነም ውሃና ሳሙና በማቅረብ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባና በዚህም ስራ ላይ ቁጥጥር እንደሚደረግ ተናግረዋል።በፊት ከሚጭኑት የተሰፈሪዎች ቁጥር 50/100 ሀምሳ በመቶ መቀነስ እንደለበቸውም አስገንዝበዋል።
ምንጭ: የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ዙሪያ የአፍሪካ መረጃ!
➡️52 የእፍሪካ ህብረት አባላገራት ቫይረሱን ሪፖርት አድርገዋል።
➡️14,744 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።
➡️793 ሰዎች ተይዘው ሞተዋል።
➡️2760 ሰዎች አገግመዋል።
ምንጭ:CDC Africa
@YeneTube @FikerAssefa
➡️52 የእፍሪካ ህብረት አባላገራት ቫይረሱን ሪፖርት አድርገዋል።
➡️14,744 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።
➡️793 ሰዎች ተይዘው ሞተዋል።
➡️2760 ሰዎች አገግመዋል።
ምንጭ:CDC Africa
@YeneTube @FikerAssefa
የዩናይትድ ስቴትስ ደቡብ ምስራቃዊ ግዛቶችን በመታው ሃይለኛ ንፋሳማ ዝናብ ቢያንስ 18 ሰዎች ሞቱ።
ቴክሳስ፣ ሉዊዝያና፣ ሚሲሲፒ፣ ጆርጅያና ቴኒሲን የመታው ከባድ ዝናብና አውሎ ንፋስ መኖሪያ ቤቶችን አውድማል፤ 8 መቶ 60ሺህ ሰዎችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳጥቷል።
Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
ቴክሳስ፣ ሉዊዝያና፣ ሚሲሲፒ፣ ጆርጅያና ቴኒሲን የመታው ከባድ ዝናብና አውሎ ንፋስ መኖሪያ ቤቶችን አውድማል፤ 8 መቶ 60ሺህ ሰዎችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳጥቷል።
Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
ፈረንሳይ በ24 ሰዓት ውስጥ 574 ሞት ስታስተናግድ በሀገሪቱ እስካሁን የሞቱ ሰዎች ቁጥር 14,967 ደርሷል።
ምንጭ:France 24
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ:France 24
@YeneTube @FikerAssefa
በባሕር ዳር፣ እንጅባራ፣ ቲሊሊና አዲስ ቅዳም ከተሞች ተጥሎ የነበረው የእንቅስቃሴ ገደብ ከነገ ጀምሮ ተነሳ።
በፌዴራል መንግሥት ደረጃ የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ብቻ ተግባራዊ እንደሚደረግም የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ አስታውቀዋል።
Via:- AMMA
@Yenetube @Fikerassefa
በፌዴራል መንግሥት ደረጃ የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ብቻ ተግባራዊ እንደሚደረግም የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህ አስታውቀዋል።
Via:- AMMA
@Yenetube @Fikerassefa
ዶ/ር ሊያ ታደሰ :-
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ከፊት ለፊት ሆነው በመዋጋት የህክምና አገልግሎት እየሰጡ ላሉት የጤና ባለሙያዎቻችን ለሶስት ወር የሚቆይ መኖሪያ እንዲሆን የኖህ ሪል ስቴት አዲስ አፓርታማ ለጤና ሚኒስቴር በማስረከብ ላደረጉት እጅግ በጎ እና ቸርነት የተሞላው ተግባር በራሴ እና በጤና ሚኒስቴር ስም ማመስገን እወዳለሁ::
@Yenetube @FikerAssefa

በማህበራዊ ሚዲያዎች "የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ የውጭ ሀገር ዜጎች ለቫይረሱ መስፋፋት ምክንያት እየሆኑ ስለሆነ ከሀገር እንዲወጡ አዘዋል" በሚል ሲሰራጩ ያሉ ዜናዎች ፈፅሞ ሀሰት መሆናቸውን የደቡብ አፍሪካ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ጽ/ቤትን ጠቅሶ የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ Fact check ክፍል ዘግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
በሶማሊያ ዛሬ የተመዘገበው የኮቪድ-19 ተጠቂዎች ቁጥር እስከ ትናንት ከነበረው በ140% ጨምሯል።ዛሬ ብቻ 35 አዲስ ተጠቂዎች ሲመዘገቡ አጠቃላይ ቁጥራቸው ደግሞ 60 ደርሷል።
ምንጭ:CGTN
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ:CGTN
@YeneTube @FikerAssefa
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከዚህ ቀደም ዜጎች በቤት ውስጥ እንዲያሳልፉ የወጣውን አዋጅ አራዝሟል። እንደ አውሮፕያውያን አቆጣጠር ሜይ 11 ድረስ እንዲቆይ ወስኗል።
@Yenetube @Fikerassefa
@Yenetube @Fikerassefa
ጠ/ሚ ዐቢይ ከማይክ ፖምፒዮ ጋር ተወያዩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኮቪድ- 19 ን ተጽዕኖ ለመቀነስ ከአሜሪካ ጋር ስለሚኖረው ትብብር ዙሪያ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ጋር ውጤታማ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ገለፁ፡፡
የአፍሪካ ኢኮኖሚ በቫይረሱ ምክንያት እየተዳከመ ስለሆነ ከሰሐራ በታች ባሉ ሀገራት የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ፈታኝ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የከፉ ችግሮችን ለመከላከልና ለመቀነስ የጋራ አመራርን ተግባራዊ በማድረግ ዙሪያ መወያየታቸውን ከፌስቡክ ገፃቸው የተገኘ መረጃ ጠቁሟል፡፡

"ኢኮኖሚያችን ከሒወታችን " አይበልጥም በማለት ህንድ ዜጎቿን ለተጨማሪ ሶስት ሳምንት ከቤት አንዳይወጡ አዛለች።
የህንዱ ጠ/ ሚ ናሬንድራ ሙዲ በሀገራቸው እየተስፋፋ ያለውን የኮሮና ቫይረስን ለመግታት እስከ ሚያዝያ 25 ድረስ ዜጎቻቸው ከቤት እንዳይወጡ አዘዋል።
መጋቢት 16 ,2012 የጀመረው ከቤት አለመውጣት ዛሬ ማክሰኞ ነበር የሚያበቃው ።
1.3 ቢልየን ህዝብ ያላት ህንድ አስከአሁን በቫይረሱ 358 ሲሞትባት 10,000 በላይ ሰው ተጠቅቶባታል።
" ኢኮኖሚያችን ከሒወታችን አይበልጥም ።ከቤት አትውጡ ስንል ትልቅ ዋጋ እየከፈልን ነው ።" በማለት ዜጎቻቸው በሽታውን ለመከላከል ሀገሪቱ ያወጣችውን መመርያ እንዲተገበሩ ጠይቀዋል።
Via:- Tesfay Getnet

ቻይና በ24 ሰዓት ውስጥ 89 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል። በተመሳሳይ ትላንት 108 ሰዎች መያዛቸው ይታወሳል። እነዚህ ኬዞች ከውጪ ሀገር የገቡ መሆናቸው ተነግሯል።
@Yenetube @Fikerassefa
@Yenetube @Fikerassefa
ከኢትዮ ቴሌኮም ቦነስ እና የቅናሽ አገልግሎት ስንጠብቅ በገንዘባችን ከገዛነው ላይ ያለአግባብ እየቆረጠባቸው መሆኑን ደንበኞች ተናገሩ፡፡
ደንበኞቹ ብዙዎቻችን ቤት በተቀመጥንበት በዚህ ሰዓት ቦነስ እና የቅናሽ አገልግሎት ስንጠብቅ ተቋሙ ገንዘባችንን ያለአግባብ እየቆረጠብን ነው ሲሉም ቅሬታቸውን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።
ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ሰዎች በቤታቸው እንዲቆዩ ሆነዋል፡፡
በቤት በሚቆዩበት ጊዜ ደግሞ ረጅሙን ጊዜአቸውን የሚያጠፉት በስልኮቻቸው ኢንተርኔት በመጠቀም መሆኑን ነግረውናል፡፡
ነገር ግን እንዚህ ተጠቃሚዎች በተለይ ለኢንተርኔት አገልግሎት የሚሞሉት ጥቅል አልበረክት እንዳላቸው እና ቴሌ ያለአግባብ ገንዘብ እየቆረጠባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ገንዘብ ካለአግባብ ከመቁረጥ ባለፈም የኢንተርኔት አገልግሎቱ የተቆራረጠ እና ፈጣን አይደለም ሲሉ ቅሬታቸው ነግረውናል፡፡
የተለያዩ የመንግስትም ሆነ የግል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ለደንበኞቻቸው የዋጋ ቅነሳ እያደረጉ በሚገኙበት በዚህ ወቅት ኢትዮ ቴሌኮምም እንደ ተቋም የዋጋ ቅነሳ ማድረግ ሲኖርበት ጭራሽ ያለ አግባብ ገንዘባችንን መቁረጡ አሳስዝኖናልም ብለውናል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም ያአግባብ ገንዘብ እየቆረጠብን ነው፣ የኢንተርኔት አገልግሎቱም ፈጣን አይደለም የሚለው ቅሬታ ላይ ምላሽ እንዲሰጠን ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ተደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም ተቋሙ ምላሽ ሊሰጠን አልፈቀደም፡፡
Via:- Ethio FM

በኢትዮጵያ 1 ሚልየን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተባለ!
በኢትዮጵያ 1 ሚልየን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስልጋቸዉ የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና ግብርና ተቋም ፋኦ የኢትዮጵያ ቢሮ በድረ ገፁ አስነብቧል፡፡አስቸኳይ ድጋፉ ያስፈለገዉም በሀገሪቱ በተከሰተዉ የበረሀ አንበጣ መንጋ ባስከተለዉ ችግር መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ድጋፍ ከሚስፈልጋቸዉ ዜጎችም 390, 000 ሰዎች በሶማሌ ክልል፣ 360, 000 በኦሮሚያ ክልል እና ድሬዳዋ ከተማ፣ 100, 000 በአፋር ክልል፣ 72, 000 በአማራ ክልል፣ 43, 000 በትግራይ እና ክልል 13, 000 ደቡብ ክልል እንደሚገኙ ተቋሙ ከኢትዮጵያ መንግስት እና ባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት ባደረገዉ ጥናት ማወቁ አስታውቋል፡፡
በጥናቱ እንደተመላከተዉ የበረሀ አንበጣዉ 200, 000 ሄክታር የእርሻ መሬት ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና ግብርና ተቋም የኢትዮጵያ ተወካይ ወ/ሮ ፋጡማ ሰኢድ እንዳሉት የኮሮና ቫይረስ በሀገሪቱ መከሰቱን ተከትሎ ስጋቱ መጨመሩን ገልፀዉ ፋኦ ለአርሶ አደሮች እና ለአርብቶ አደሮች የሚደርገዉን ድጋፍ ሁኔታዎች በሚፈቅዱት መጠን እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡በተያያዘም በምስራቅ አፍሪካ ለሁለተኛ ጊዜ በአንበጣ መንጋ ልትወረር እንደምትችል ስጋት እንዳለ ፋኦ አስታውቋል። በቅርቡ ከተከሰተው ከመጀመሪያ ዙር 20 እጥፍ እንደሚበልጥ የተሰጋው ይህ የአንበጣ መንጋ ለአንዳንድ ሀገራት ባለፉት 70 አመታት ታይቶ የማይታወቅ ይሆናል ተብሎ ተገምቷል።
ምንጭ: አሻም ቲቪ