YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
3 ኢትዮጵያዊያን ባለሃብቶች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያግዙ 200 የሙቀት መለኪያዎችን ለ9 ክልሎች አከፋፈሉ፡፡

አቶ አይሸሹም የተባሉ በንግዱ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሃብት በግላቸው ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ 120 የሙቀት መለኪያዎችን ለዘጠኙም ክልሎች አበርክተዋል፡፡ሁለት ባልደረቦቻቸው በእርሳቸው አነሳሽነት እያንዳንዳቸው 40 የሙቀት መለኪያ መሳሪያዎችን መስጠታቸው ተገልጿል፡፡ ባለሃብቶቹ በጋራ ባደረጉት የድጋፍ ተሳትፎ 200 የሙቀት መለኪያ መሳሪያዎችን ለክልል ጤና ቢሮ ተወካዮች አስረክበዋል፡፡እኛ ተርፎን አይደለም የምንደግፈው ያሉት አቶ አይሸሹም ወቅቱ ነግደን የምናተርፍበት ሳይሆን ለወገንና ለሃገር የምንደርስበት ጊዜ በመሆኑ የቻልነውን ድጋፍ አድርገናል ብለዋል፡፡ኢትዮጵያውያን በወረርሽኙ ሳይደናገጡ የመንግስትንና የጤና ባለሙያዎችን ምክር በመስማት ራሳቸውን እንዲጠብቁ ያሳሰቡት ባለሃብቱ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመነድ የአንድ ማዕድ ለአንድ ወገን ጥሪ መሰረትም ወገኖቻቸውን እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
በአሜሪካ በአንድ ቀን ከፍተኛው ሞት ተመዘገበ!

በአሜሪካ በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ በኮሮናቫይረስ ምክንያት 1914 ሰዎች ሞቱ።ወረርሽኙ ከጀመረ ወዲህ በየትኛውም አገር በአንድ ቀን ይህን ያህል ሰው ሞቶ አያውቅም ተብሏል። አሜሪካ ማክሰኞ ዕለት ብቻ በ24 ሰዓት 1ሺህ 736 ሰዎች ሞተውባታል፡፡ይህም እስካሁን በአሜሪካ ምድር የሟቾችን ቁጥር 12ሺህ 722 ያደርሰዋል፡፡በአሜሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ጠቅላላ ቁጥር 400 መቶ ሺ ለመድረስ 2ሺ ሰዎች ብቻ ናቸው የቀሩት፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር 1 ሚሊዮን 400ሺ እያለፈ ይገኛል፡፡

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ ዛሬ ይጀምራል!

የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ በዛሬው ዕለት እንደሚጀምር የፓርቲው ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክሮ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍም ነው የሚጠበቀው።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
⬆️⬆️
የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የ48 ሰዓት የኮሮና ቫይረስ መግለጫ

ከድሬዳዋ የተላከው የ6 ሰዎች ናሙና ሁሉም ውጤታቸው ከቫይረሱ ነፃ ሆኗል::

@YeneTube @FikerAssefa
ፓኪስታን የሕክምና ቁሳቁስ ይሟሉልን ያሉ ከ50 በላይ ዶክተሮችን አሰረች፡፡

የፓኪስታን ፖሊሶች ከ50 በላይ ዶክተሮችን እንዳሰሩ አልጀዚራ ዘግቧል። ዶክተሮቹ ለእስር የዳረጋቸው ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የፊት መሸፈኛ ጭብሎች እንዲቀርቡላቸው በመጠየቃቸው ነው ተብላል፡፡የወጣት ዶክተሮች ማህበር ተወካይ ለአልጀዚራ እንደተናገረው የሀገሪቱ ፖሊሶች ከ67 በላይ የማህበሩ ዶክተሮች ታስረዋል።ለእስር የተዳረጉት ዶክተሮች እንዲፈቱ ማህበሩ የጠየቀ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ግን እንዳልተፈቱ ተገልጿል። ፓኪስታን ከኮሮና ቫይረስ ጋር ትልቅ ትግል እያደረገች የምትገኝ ሀገር ስትሆን በሀገሪቷ ኮሮናን ለመከላከል የሚያግዙ ግብአቶች እጥረት ሊያሰራቸው እንዳልቻለ ሐኪሞቹ በመናገር ላይ ናቸው።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
አፈር ውስጥ ገብተው በቀላሉ የማይበሰብሱ እና መጠናቸው ከ0.03 ሚሊሜትር በታች የሆኑ ስስ የላስቲክ ዕቃ መያዣዎችን (ፌስታሎችን) ሲጠቀሙ የተገኙ ግለሰቦች ከ2 ሺሕ 500 ብር ጀምሮ ቅጣት ሊጣል እንደሆነ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን፣ ሙሉ በሙሉ እንዳይመረቱና ከውጪ እንዳይገቡ በታገዱ የማይበሰብሱ ስስ ፌስታሎችን ሲጠቀም የተገኘ ግለሰብ የሚቀጣበትን አዲስ አዋጅ አርቅቆና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ እየተገመገመ ሲሆን፣ በቅርቡ እንደሚጸድቅም ይጠበቃል ሲል አስታውቋል።

@YeneTube @Fikerassefa
የአዲስ አበባ ቤት አከራዮች ለተከራዮቻቸው ምህረት እንዲያደርጉ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ጠየቁ።

የአዲስ አበባ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በአነስተኛ ንግድ የተሠማሩ ነጋዴዎችና ቤተሰቦቻቸው በእንቅስቃሴ መቀነስ እንዳይጎዱ አከራዮች የኪራይ ምሕረት እንዲያደርጉላቸው ጠይቀዋል፡፡

የከንቲባ ጽሕፈት ቤት በፌስ ቡክ ገጹ እንዳስታወቀው ምክትል ከንቲባው ‘‘የጊዜውን ፈተና፣ በጊዜው ብልሃት እና ጸሎት ታግለን ለማለፍ ስንለፋ አንዳንድ የግድ የሆኑ መሠዋዕትነቶች ይደቀናሉ’’ በመሆኑም አከራዮች ምህረት እንዲያደርጉ የተማጽኖ ጥሪ አስተላልፈዋል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
እናሆ ምስጋና - ኢንጂነር ታከለ ኡማ

ሰባራ ባቡር አካባቢ የሚገኘው ዕድገት በህብረት ህንጻ ባለቤቶች 150 ለሚሆኑ ተከራዪቻቸው ለሁለት ወር በነፃ እንዲገለገሉበት ፈቅደውላቸዋል።
ለአከራዮች ያቀረብነውን ጥሪ ተከትሎ ይሄንን ውሳኔ በመወሰናቸው አክብሮቴን መግለጽ እፈልጋለሁ።

ሌሎች አከራዮችም የእነሱን ፈለግ እንደሚከተሉ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ።
@Yenetube @Fikerassefa
ለ20 አመት የሚያገለግል አና በአገሪቱ የትራንስፖርት ፍሰቱን በማሳለጥ ለኢኮኖሚው እድገት ከፍተኛ ድረሻ ይኖረዋል ተብሎ የሚጠበቀው ፕሮጀክቱ ይፋ መሆኑን ካፒታል ዘግቧል። ዝርዝር መረጃ ሲደርሰን እንመለስበታለን።

@YeneTube @FikerAssefa
ኮሮና ቫይረስ በህንድ ከተከስተ ጀምሮ :-

-ከ1 ወደ 2500 ሰው ለመዛመት 9 ሳምንታት ፈጅቶበታል

-ከ2500 ወደ 5000 ለመድረስ 6 ቀናት ነው የፈጀው።

ውድ ኢትዮጵያዊያን ይህ በሽታ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይፈልጋል

ከቤት አይዉጡ ከወጡም ርቀታችሁን ጠብቀው ይንቀሳቀሱ።
@Yenetube @Fikerassefa
ሰበር ዜና!

የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሮና ወረርሽኝ እየተባባሰ በመምጣቱ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ ዐውጇል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ሰበር ዜና! የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሮና ወረርሽኝ እየተባባሰ በመምጣቱ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ ዐውጇል፡፡ @YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እየተባባሰ በመምጣቱ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ ማወጁን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስታወቁ፡፡

አዋጁ በሀገሪቱ ሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 93 መሠረት የተፈጸመ መሆኑንም ገልጸዋል።

@Yenetube @Fikerasssefa
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

መጋቢት 30 /2012 (ኢዜአ) ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 225 ሰዎች ውስጥ 3 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የተረጋገጠ ሲሆን ቁጥሩም ወደ 55 ከፍ ብሏል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት፤ ቫይረሱ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ እስካሁን ባለው ሂደት ለ2 ሺህ 496 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።

ዛሬ የተገለጸውን ጨምሮ በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ወደ 55 ከፍ ብሏል።

ባለፉት 24 ሰዓታት ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠው ሶስቱም ግለሰቦች ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ ሁለቱ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው።

ሁለቱ ግለሰቦች የ29 ዓመት እድሜ ያላቸውና ከዱባይ መጥተው በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ መሆናቸውንም ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

አንደኛው ግለሰብ የ36 ዓመት እድሜ ያለውና በአማራ ክልል የአዊ ዞን አዲስ ቅዳምን ከተማ ነዋሪ ነው።

ግለሰቡ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌለው ሲሆን፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንዳለው ተጠርጥሮ ምርመራ እንደተደረገበት ተገልጿል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል አንድ ሰው ወደ ጽኑ ህሙማን ማቆያ መግባቱንና ይህም በጽኑ ህሙማን መቆያ ውስጥ ያሉ ዜጎች ቁጥር 2 እንዳደረሰው ዶክተር ሊያ ተናግረዋል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው ግለሰቦች ባሉበት ክልል በተዘጋጀ የነጻ የስልክ መስመሮች በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉም ሚኒስትሯ ጥሪ አቅርበዋል።

ህብረተሰቡ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የወጡ መመሪያዎችን ተግባራዊ እንዲያደርግም ነው ያሳሰቡት።

በኢትዮጵያ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል አራቱ ያገገሙ ሲሆን፤ ሁለቱ ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል። ሌላ ሁለት ግለሰቦች ደግሞ ወደ አገራቸው ተሸኝተዋል።

Via:- ENA
@Yenetube @Fikerassefa
የተማሚዎቹ ሁኔታ :-

ሁለቱ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው።

- ሁለቱ ግለሰቦች የ29 ዓመት እድሜ ያላቸውና ከዱባይ መጥተው በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ መሆናቸውንም ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

- አንደኛው ግለሰብ የ36 ዓመት እድሜ ያለውና በአማራ ክልል የአዊ ዞን አዲስ ቅዳምን ከተማ ነዋሪ ነው። ግለሰቡ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌለው ሲሆን፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንዳለው ተጠርጥሮ ምርመራ እንደተደረገበት ተገልጿል።

@YeneTube @Fikerassefa
የመስቀል አደባባይ መልሶ ማልማት እና የአረንጓዴ ስፍራ ግንባታ ዛሬ ረቡዕ፤ መጋቢት 30፤ 2012 ተጀምሯል። መልሶ ግንባታው ስፍራውን ለህዝባዊ አደባባይነት በሚመጥን መልኩ ለማስተካከል ያለመ መሆኑን የአዲስ አበባ አስተዳደር ገልጿል።

Via:- Ethiopia Insider
@Yenetube @Fikerassefa
#Ethiopia : የሀዋሳ ግራንድ ሞል ባለቤት ወይዘሮ አማረች ዘለቀ ህንፃውን ለተከራዮት ነጋዴዎች የሁለት ወር ኪራይ ነፃ አርገዋል ። ለከተማ አስተዳደሩም 150,000 ብር ለኮሮና ቫይረስ ሰርጭት መግቻ ስራ እንዲሆን ሰጥተዋል።

Via:-Tesfaye getnet
@YeneTube @Fikerassefa
የኮሮናቫይረስ ህሙማንን ለሚረዱ የጤና ባለሙያዎች 645 መኖሪያ ቤቶች ተዘጋጁ!

ለኮሮናቫይረስ ህመምተኞች እርዳታ የሚሰጡ የጤና ባለሙያዎች የሚያርፉባቸው ከ645 በላይ የመኖሪያ ቤት መዘጋጀታቸውን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።ዶክተር ሊያ ታደሰ እንደተናገሩት፤ ይህንን ወረርሽኝ በመቆጣጠርና ምላሽ በመስጠት ሂደት ውስጥ ትኩረት የሚሰጠው የጤና ባሙያዎች ጉዳይ ነው።ይህም የጤና ባለሙያዎቹ ከየተኛውም የኅብረተሰብ ክፍል በተለየ ለበሽታው ተጋላጭና ህይወታቸውንም አደጋ ላይ ጥለው ስለሚሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።

Via ENA
@YeneTube @FikerAssefa
ጎረቤት ሀገር ሱማልያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተጀምሮ የነበረው የ2019 - 2020 ትምህርት ዘመን እንደማይቀጥል መንግስት አስታውቋል።

@Yenetube @Fikerassefa