YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት እስካሁን 550 ሚሊዮን ዶላር ማጣቱን ካፒታል ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኮሮና ቫይረስ መከሰትን ተከትሎ የደም ልገሳ መቀነሱ ተገለጸ!

በአሁኑ ጊዜ በሃገራችን የኮሮና ቫይረስ በሽታ(COVID-19) ወረርሽኝ እንዳይስፋፋ የህዝብ እንቅስቃሴ መገደብ የበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች ቁጥር መቀነስ ሃገራዊ የደም ክምችቱ ላይ እጥረት እያስከተለ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል፡፡ በዚህ ወረርሽኝ ወቅት በቂ የደም አቅርቦትን ማረጋገጥ እጅግ አስፈላጊ መሆኑንና በተለይ በወሊድ ወቅት የሚፈጠረው የደም መፍሰስ፣ የድንገተኛ አደጋ እንዲሁም የካንሰር ህመምተኞች የሚያጋጥማቸው የደም እጥረት ለመቅረፍ የበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች ደም እንዲለግሱ ጥሪ ቀርቧል፡፡

Via MoHE
@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ለኮሮና ቫይረስ መከላከል ስራ የሚውል 70 ሚሊየን ብር በጀት መደበ!

የደቡብ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በቪዲዮ ኮንፈረንስ ዛሬ ባካሄደው 111ኛ መደበኛ ስብሰባው አሳሳቢ የሆነውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት አስቀድሞ ለመከላከል ይረዳ ዘንድ 70 ሚሊየን ብር በጀት እንዲመደብ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ የክልሉ መንግስት የኮሮና ቫይረስ በሽታ ስርጭት ለመከላከል በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የሚመራ ግብረ ሀይል አደራጅቶ በዘርፉ በርካታ ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ህብረተሰቡ የበሽታውን ወረርሽኝ ለመከላከል ከክልሉ መንግስት ጎን በመቆም በገንዘብ፤በጉልበት፤በአይነት እና በእውቀት እያደረገ ያለውን ድጋፍ አስመልክቶ መስተዳድር ምክር ቤቱ ምስጋና አቅርቧል፡፡

Via SRTA
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚያግዝ የአንድ ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን ገለጸ።

የተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል አቶ ኢየሱስወርቅ ዛፉ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተገኝተው ድጋፍ መደረጉን ለብሔራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አስታውቀዋል።

ምንጭ: ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
ደቡብ አፍሪካ የኮሮና ቫይረስን በተመለከተ የተሳሳተ መረጃ አሰራጭቷል ያለችዉን ግለሰብ ፍርድ ቤት አቆመች፡፡

የ55 ዓመቱ ስቴቨን ብሪች ፍርድ ቤት የቀረበዉ፣ በሀገሪቱ ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉት የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ መሳሪያዎች ንጽህናቸዉ ያልተጠበቀና ሰዎችን ለበሽታዉ የሚዳርጉ ናቸዉ የሚል የሃሰት መረጃ በማሰራጨወቱ ነዉ ተብሏል፡፡

ግለሰቡ ባሰራጨዉ በምስል የታገዘ መረጃም ሰዎች ቤት ለቤት ለሚደረግ የሙቀት ልየታና ምርመራ ተባባሪ እንዳይሆኑ የሚቀሰቅስ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በሃገሪቱ የኮቪድ 19ኝን በተመለከተ የተሳሳቱ መረጃዎችን የሚያስራጭ ማንኛዉም ሰዉ የ6 ወራት እስር እንደሚጠብቀዉ ሀገሪቱ ደንግጋለች፡፡

Via:- Ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
በእንግሊዝ ሌሎች 758 ሰዎች በቫይረሱ መሞታቸው ተነገረ!

በእንግሊዝ በኮሮናቫይረስ ተይዘው ህክምና ሲደረግላቸው የነበሩ ተጨማሪ 758 ሰዎች መሞታቸውን የአገሪቷ ብሔራዊ ጤና አገልግሎት አስታወቀ። ይህም በእንግሊዝ እስካሁን በሆስፒታል በክትትል ላይ ሳሉ የሞቱ ሰዎችን ቁጥር 5 ሺህ 655 አድርሶታል።ትናንት አጠቃላይ የሟቾቹ ቁጥር 4 ሺህ 897 የነበረ ሲሆን፤ ዛሬ ግን ቁጥሩ ጨምሯል፡፡

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ሰው ሠራሽ የምግብ ዘይት እጥረት ተከሰተ!

የምርት ወይም የአቅርቦት እጥረት ባልተከሰተበት ሁኔታ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ የተከሰተውን ወረርሽኝ ተከትሎ የምግብ ዘይት ዋጋ ይጨምራል በሚል በነጋዴዎች ዘንድ ያለአግባብ ዘይት በመደበቅ ምክንያት በአዲስ አበባ ከተማ የምግብ ዘይት እጥረት መፈጠሩን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ።ሚኒስቴሩ ጨምሮ እንደገለጸው፣ የምግብ ዘይት እጥረት ሳይኖር ነገር ግን የአቅርቦት እጥረት ሊመጣ ይችላል በማለት እና ከዛም ከወጣለት ዋጋ በላይ ጭማሪ አድርጎ ለመሸጥ በማሰብ በመጋዘን ሲያከማቹ የነበሩ ነጋዴዎች አሉ። ሚኒስቴሩም ባደረገው ክትትል እነዚህን ነጋዴዎች መለየታቸውንና እርምጃ በመውሰድ ላይ እንደሚገኝ ተጠቅሷል።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
በኒውዮርክ ዛሬ ብቻ 8147 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች መኖራቸው ተነግሯል። እንዲሁም 731 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ሞተዋል።

በኒውዮርክ በአጠቃላይ 138,836 በኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ሲኖሩ 5489 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
3 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች የኮሮና ቫይረስ አንደተገኘባቸውና በጤና ሚኒስቴር ክትትል ስር እንዳሉ ስራ አስፈፃሚውን አቶ ተወልደ ገ/ማርያም እንደተናገሩ ጠቅሶ CGTN ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ደሴ ከተማ ውስጥ በህገወጦች የተከማቹ መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶች ተያዙ።

በአማራ ክልል ደሴ ከተማ በአንድ መጋዝን ውስጥ በህገ ወጥ መንገድ የተከማቹ የዘይትና ሌሎች መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶች በፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውለዋል።የምርቶቹ ብዛት ገና በውል እንዳልታወቀ፣ ድርጊቱን የፈጸሙት ግለሰቦች ላይም ምርመራ እንደሚጀመር ፖሊስ አስታውቋል።

ምንጭ: አብመድ
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ክልል 13,231 የሕግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ ወሰነ!

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ምክንያት በማድረግ 13,231 የሕግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰናቸውን ከኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
በኦሮሚያ ክልል የኮሮና ቫይረስ መመርመረያ ላቦራቶሪ ዛሬ ስራ ጀመረ!

በኦሮሚያ ክልል ኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ በአንድ ቀን 500 ሰዎችን የመመርመር አቅም ያለው ላቦራቶሪ ዛሬ ሥራ ጀመረ።በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማእረግ የክልሉ ማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ ላቦራቶሪውን በአዳማ ተገኝተው ዛሬ በይፋ ሥራ አስጀምረዋል። የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ወሳኝ ሚና ካላቸው አንዱ የመመርመሪያ መሳሪያ መሆኑን የገለጹት አቶ አዲሱ፤ ከዚህ በፊት በህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ብቻ ሲደረግ የነበረውን የምርመራ ሥራ ከዛሬ ጀምሮ በክልሉ ተጀምሯል።

ምንጭ: ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
በጉራጌ ዞን 4 መቶ14 ታራሚዎች ዛሬ ከእስር ተፈተዋል።

በወልቂጤ ማረሚያ ተቋም 275 ታራሚዎች ከእስር የተፈቱ ሲሆን ከነዚህም መካከል 5ቱ ሴት ታራሚዎች ናቸው። በተመሳሳይ በቡታጀራ ከተማ አስተዳደር 139 ታራሚዎች መፈታታቸዉም ታዉቋል።

የጉራጌ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ሀላፊ አቶ መስፍን ተካ እንደገለጹት በዞኑ በተለያዩ ጥፋት ታስረዉ የነበሩ 4 መቶ 14 ታራሚዎች ዛሬ ከእስር እንደፈቱተደርጓል።

ታራሚዎቹ ከቤተሰቦቻቸዉ እንዲቀላቀሉ በማድረግ እራሳቸዉን ከኮሮና ቫይረስ
እንዲከላከሉ ርቀታቸዉን በመጠበቅ ፣ እጃቸዉን በተደጋጋሚ በሳሙና መታጠብ
እንዳለባቸዉም ለታራሚዎች አስገንዝበዋ።

ምንጭ :-Gurage zone Government Communication Affairs
@YeneTube @Fikerassefa
ሶማልያ ዛሬ አንድ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው እንደተገኘ ይፋ አድርጋለች። ግለሰብ 58 አመቱ ሲሆን ምንም የጉዞ ታሪክ የለው።በሀገሪቱ በአጠቃላይ 8 ሰዎችን በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
አሜሪካ የታጣቂ ቡድን አል ሻባብ መስራች አባል የነበረውን ዩሱፍ ጂስ በሶማሊያ በፈጸመችው የአየር ጥቃት መግደሏን አስታወቀች።

አል-ሻባብ ግን እስካሁን ድረስ በጉዳዩ ላይ ያለው ነገር የለም፡፡የአሜሪካ ኃይል የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ የሆኑት ጀነራል ስቴፈን ታውንሴንድ፤ በአል- ሸባብ ውስጥ ከፍተኛ ኃላፊነት የነበረው ዩሱፍን ጨካኝና እና ገዳይ ሲሉ ገልጸውታል፡፡
ግለሰቡ በሶማሊያ እንዲሁም ከሶማሊያ ውጭ ጥቃቶችን ይፈጽሙ ነበር ተብሏል፡፡

via:- BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በዓለም ላይ ከኮሮና ወረርሽኝ ተጠቂዎች መብዛት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ዕጥረት የታየበት የኦክስጅን ቬንትሌተር በኢትዮጵያ ለማምረት ዝግጅት መጠናቀቁ ተገለጸ።

Via:- Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
⬆️ባለሀብቱ ለኮሮና ህክምና እንዲውል የሰውነት የሙቀት መለከያ መሳርያ ለጤና ቢሮዎች አበረከቱ

በሆቴልና ኢንደስትሪ ላይ የተሰማሩት አቶ አይሸሹም ተካ ዛሬ 200 የሰውነት ሙቀት መለከያዎችን ከጓደኞቻቸው ጋር በመቀናጀት ከውጭ አስመጥተው ለዘጠኙ የክልልየጤና ቢሮ ተወካዮች ዛሬ አሰረክበዋል።
የሙቀት መለከያዎቹ ዋጋ በብር ሲገመት ሁለት ሚለየን ብር ያወጣል።

በርክክቡ ወቅት አቶ አይሸሹም እንዳሉት " ወቅቱ ጊዜው ነግደን የምናተርፍበት ጊዜ ሳይሆን የወገናችንን ጤና ከኮሮና ለመጠበቅ የምንረባረብበት ጌዜ ነው ።እኛም ይሄን መሳርያ ስናበረክት በቂ ነው ብለን አስበን ሳይሆን የአቅማችንን ለመወጣት ነው " ብለዋል።
የንግዱ ማህበረሰብ ወቅቱ ነግዶ የሚያተረፍበት ሳይሆን፤ ወገን እና ሃገርን ከኮሮና ወረርሽኝ ተረባርቦ የሚያተርፍብት ሊሁን ይገባል

ነግዶ ለማትረፍ የሚቻለው ከምንም በላይ ወገን እና ሃገር በጤና ውለው ማደር ሲችሉ ብቻ ነው ።

“በዚህ ወቅት የተጋረጠብን ስጋት በሃገር እና በወገን ላይ የሚያደርሰው ጉዳት እና ጥፋት አሳሳቢ ነው። የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት በመፍራት ሳይሆን በብልሃት፤ በመጨነቅ ሳይሆን በመጠንቀቅ፤ በእየለቱ በዜና በምንሰማው ቁጥር ሳይሆን አደጋውን በመቆጣጠር . እንደምንሻገረው አምናለሁ።”

“የሃያላን ሃገራት በርካታ ዜጎችን ህይወት የቀጠፈው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ምድር ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት በተቻለ ዓቅም ለመቀነስ፤ የንግዱ ማህበረሰብ የመንግሥትን ጥረት በባለቤትነት ስሜት መደገፍ አለብን።”

“ሃገሪቱ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከገጠማት ፈተና እንድትወጣ፤ የጤና ባለሙያዎች የሚሰጡትን ሳይንሳዊ የጥንቃቄ መመሪያዎች ህብረተሰቡ በማስተዋል ተግባራዊ ማድረግ አለበት።”

“የተደቀነብብንን ስጋት የሚያሳጣንን ብቻ ሳይሆን ያመጣልንን ዕድል ማስተዋል ይገባል። በትውልድ ሰንሰለት በተግባር ተፈትነው የነገሱ ኢትዮጵያዊ እሴቶችን በትኩረት እና በአፅንዖት ለመተግበር ወገን ለወገን የመደጋገፍ ዕድል የሚሰጥ መሆኑን መገዘብ ያሻል።”

” በዘመን የገጠሙን ስጋት እና አደጋዎችን የቀደሙት አባቶችና እናቶች ሀገርን በጥበብ አሻግረው አስረክበውናል።

እኛም ከመጣብን ፈተና ሃገር እና ወገንን ለመታደግ መደጋገፍ ይኖርብናል።ዛሬ አቅም የፈቀደውን መደገፍ፤ ለነገ ዓቅምን አሟልቶ የሚደግፍ ትውልድና ሃገር ለማስቀጠል የምንረባረብበት ጌዜ ነው ።እኛም ይሄን መሳርያ ስናበረክት በቂ ነው ብለን አስበን ሳይሆን የአቅማችንን ለመወጣት ነው ” ብለዋል።

Via :- Fidelpost.com
@Yenetube @Fikerassefa
የቻናላችን ቤተሰቦች ወደ ቻናላችን አዲስ ሰው በመጋበዝ ተባበሩን።

በዚህ ሳምንት በቻናላችን የተለያዩ ውድድሮች እናዘጋጃለኝ እርሶ ከቤት አይ ውጡ
#መረጃዎችን ቀድምን እናደርሶታለን።

@Yenetube @Fikerassefa
በኬንያ 17 የፓርላማ አባላት የኮሮና ቫይረስ እንዳለባቸው በምርመራ መረጋገጡን ዘ ስታር የተባለ የሀገሪቱ ጋዜጣ አስነብቧል።

ባለፈው ሳምንት ከ200 የሚመበልጡ የሀገሪቱ የፓርላማ አባላት የቫይረሱን ምርመራ አድርገው ውጤታቸው ባለፈው ሰኞ እንደተሰጣቸው ጋዜጣው ገልፆ ስማቸውን ግን ማግኘት እንዳልቻለ ፅፏል።

Via:- Tesfay Getnet
@Yenetube @Fikerassefa