ሶማልያ ጤና ሚንስትር ሁለተኛው በኮሮና ቫይረስ ተጠቂ መገኘቱ አስታውቋል። ግለሰብ በመንግስት ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንደነበረም ተገልጷል።
@Yenetube @FikerAssefa
@Yenetube @FikerAssefa
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በትግራይ ክልል ዝርዝር መረጃል
የትግራይ ክልላዊ መንግስት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል የሚያስችል ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቋል፡፡
በትግራይ ክልል ደረጃ የቫይረሱ ስርጭት የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ በ22 ዋና ዋና ጉዳች ላይ ከመከረ በኋላ ሶስት ዐበይት ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ማሳለፉን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ ሚካኤል አስታውቀዋል፡፡
ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ በሰጡት መግለጫ በትግራይ ክልል ከገጠር ወደ ከተማ ፣ ከከተማ ወደ ገጠር፣ ከከተማ ወደ ከተማ የሚደረጉ ዝውውሮች ለሚቀጥሉት 15 ቀናት ታግደዋል፡፡ ህዝብ የሚበዛባቸው ገበያዎችም እንዳይካሄዱ መታገዳቸውንም ዶ/ር ደብረጽዮን ገልፀዋል፡፡
እንደ ሠርግና ተስካር ያሉ ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ ጉዳዮችም ለጊዜው እንዳይካሄዱ የክልሉ ስራ አስፈጻሚ ወስኗል፡፡
ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እንዳሉት የተላሉፉት ውሳኔዎች ለሚቀጥሉት 15 ቀናት ተግባራዊ እንሚደረጉና በሽታው ያለበት ወቅታዊ ሁኔታ እየተገመገመ የተለያዩ ውሳኔዎች እንደሚተላለፉ መናገራቸውን የትግራይ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡
Via:- የትግራይ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት
@Yenetube @Fikerassefa

የሚሊኒየም አዳራሽን የጤና አገልግሎት መስጫ አድርጎ ለመጠቀም ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልፀዋል!
በሽታው የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ግለሰቦች እና ተቋማት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
via:- Eliasmeseret
@Yenetube @Fikerassefa
በሽታው የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ግለሰቦች እና ተቋማት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
via:- Eliasmeseret
@Yenetube @Fikerassefa
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ባዘጋጀው የኢትዮጵያ የተቀናጀ የኮሮና ቫይረስ መከታተያና መቆጣጠሪያ መረብ ሲስተም ላይ በትናንትናው እለት የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 20 ተብሎ የተጠቀሰው በስህተት መሆኑን ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 12 መሆኑን ሚኒስትሯ አስታውቀዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 12 መሆኑን ሚኒስትሯ አስታውቀዋል።
@Yenetube @Fikerassefa
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኮቪድ-19 ላይ ጥናት ለማካሄድ 10 ሚሊየን ብር መደበ!
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኮቪድ-19 ላይ ጥናት ለማካሄድ 10 ሚሊየን ብር መደበ፡፡ በዛሬው እለት በኮቪድ-19 ላይ ጥናት የሚያኪያሂድ የጥናት ቡድን የተቋቋመ ሲሆን ቡድኑ ጥናቱን ለመጀመር ይችል ዘንድ ከተመደበው አጠቃላይ ፈንድ ውስጥ አንድ ሚሊየን ብር ወጪ ሆኖ ተሰጥቶታል፡፡ የጥናት ቡድኑ አባላት ከተለያዩ ኮሌጆችና ተቋማት ከልዩ ልዩ መስክ የተውጣጡ ምሁራንን ያካተተ ሲሆን የመጀመሪያ ስብሰባውንም በዛሬው እለት መጋቢት 17 ቀን 2012 ዓ.ም አድርጓል፡፡ የጥናት ቡድኑ ይህን ገዳይ የኮሮና ቫይረስ ለመዋጋት ለሚደረገው ጥረት አስተዋፅኦ ለማድረግ ጠቃሚ ግብአት ሊሆን የሚችል የጥናት ግኝቱን እንደሚያቀርብ ይጠበቃል፡፡ ለጥናቱ የተመደበው ቀሪው ገንዘብ በውድድር ላይ ተመስርቶ በመሰል ጥናት ለመሳተፍ ለሚሹ የአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ ስታፍ አባላት የሚቀርብ ይሆናል፡፡
ጣሰው ወልደሐና (ፕሮፌሰር)
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት
መጋቢት 17 ቀን 2012 ዓ.ም
@YeneTube @FikerAssefa

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በወሰነው መሰረት ዛሬ መጋቢት 17/2012 ዓ. ም. በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ማስተባበሪያ ጽ/ቤትና በኢፌዲሪ ጤና ሚኒስቴር በመገኘት ለህዳሴ ግድቡ ግንባታና ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የሚውል ሁለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉም በበኩሏ የአራት መቶ ሺህ ብር ድጋፍ አድርጋለች።
ምንጭ: EAF
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ: EAF
@YeneTube @FikerAssefa
የአሜሪካ ኤምባሲ ላልተወሰነ ጊዜ ተዘጋ በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በኮሮናቫይረስ ስርጭት ምክንያት ላልተወሰ ጊዜ ዝግ ተደረገ።
ኤምባሲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ከቫይረሱ ስርጭት እና የኢትዮጵያ መንግሥት ስርጩቱን ለመግታት ከሚያደርገው ጥረት አንጻር ኤምባሲውን በጊዜያዊነት መዝጋት አስፈልጓል ብሏል።
ኤምባሲው ለዜጎቹ ጭምር ያደረግ የነበረውን የፓስፖርት እድሳት፣ ከአገር ውጪ የወሊድ እና የሞት ምዝገባን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶችን እንደማይሰጥ አስታውቋል።
- BBC

የጎመጁ ኦይል ባለቤት አቶ ቴዎድሮስ የሺዋስ እስከ 100 ሰዎች ሊያሳርፍ የሚችል ህንፃ ከውጭ ለሚመጡ ዜጎች ማቆያ ይሆን ዘንድ ላልተወሰነ ጊዜ መፍቀዳቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ አስታወቀዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የአምባሳደሮች ምደባ ቦታ ይፋ ተደረገ!
የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያን በተለያዩ አገራት የሚወክሉ 15 አዳዲሰ አምባሳደሮችን ሹመት የካቲት 24 ቀን 2012 ዓም ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። በዚሁ መሰረት ክቡራን አምባሳደሮቹ የሚመደቡባቸው አገራት ከዚህ በሚከተለው መሰረት ተወስኗል።
ክቡራን ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደሮች
1. ክቡር አምባሳደር ብርሁኑ ፀጋዬ አውስትራሊያ ካንቤራ
2. ክብርት አምባሳደር ያለም ፀጋይ ኩባ ሃቫና
3. ክብርት አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ቤልጄም ብራሰልስ
4. ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ማርቆስ ተክሌ ግብጽ ካይሮ
5. ክቡር አምባሳደር ባጫ ጊና ሞሮኮ ራባት
6. ክቡር አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ሱዳን ካርቱም
7. ክቡር አምባሳደር ምህረታብ ሙሉጌታ ኤርትራ አስመራ
8. ክቡር አምባሳደር ነብያት ጌታቸው አልጀሪያ አልጀርስ እንዲሁም
9. ክቡር አምባሳደር ተፈሪ መለስ እንግሊዝ ለንደን እንዲሰሩ ተመድበዋል።
እንዲሁም ክቡራን አምባሳደሮች
1. ክቡር አምባሳደር አድጎ አምሳያ ስዊድን ስቶክሆልም ምክትል ሚሲዮን መሪ
2. ክቡር አምባሳደር ጀማል በከር ባህሬን ማናማ ቆንስል ጄኔራል
3. ክቡር አምባሳደር አብዱ ያሲን ሳኡዲ አረቢያ ጄዳ ቆንስል ጄኔራል
4. ክቡር አምባሳደር ለገሠ ገረመው ካናዳ ኦታዋ ቆንስል ጄኔራል
5. ክብርት አምባሳደር እየሩሳሌም አምደማርያም የተባበሩት አረብ ኢሚሪቶች ዱባይ ቆንስል ጄኔራል
6. ክቡር አምባሳደር ሽብሩ ማሞ አሜሪካ ሚኒሶታ ቆንስል ጄኔራል እንዲሰሩ ተመድበዋል።
አምባሳደሮቹ በተመደቡባቸው አገራት የፕሮቶኮል አሰራር መሰረት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተጠናቅቆ በቅርቡ ወደ ምድብ ቦታቸው ተንቀሳቅሰው ስራቸውን በይፋ የሚጀምሩ ይሆናል።
ምንጭ: የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ

በቤልጅዬም በዛሬው ዕለት 1298 አዲስ ተጠቂና 42 ሞት ተመዝግቧል። እስካሁን ባለው ደግሞ በአጠቃላይ 6235 ተጠቂዎች እና 220 ሞት በሀገሪቱ ተመዝግቧል ።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ቻይና ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ሰራተኞችን በመለያ ክፍል አስቀመጠች!
ባለፈው ቅዳሜ መጋቢት 12 ወደ ቤይጂንግ የበረረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤየረ ባስ አውሮፕላን ታዩያን በምትባል የቻይና ከተማ አድርጎ በሯል። እዚያ ሲያርፍ የኮሮና የተጠረጠሩ መንገደኞች እና የበረራ ሰራተኞች ስልነበሩ ለተጨማሪ ምርመራ ለአስራ አራት ቀን በለይቶ ማቆያ እንዲኖሩ መደረጉን ከፖይለቶቹ ጋር የቅርብ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች ለፊደል ፖስት ተናግረዋል።
ፓይለቶቹን ጨምሮ መለያ ክፍል ውስጥ የተቀመጡት የበረራ አስተናጋጆቹ ቁጥር 25 እንደሚሆንና የምርመራ ውጤታቸውን እየተጠባበቁ እንደሚገኝ ለፊደል ፖስት ተናግረዋል።ፊደል ፖስት እንደተረዳው ፓይለቶቹ ባዶውን አውሮፕላን ከታዩያን ወደ ቤይጂንግ ይዘው ሄደዋል ።ቀጠሎ ግን አብራሪዎችን እዚያው ታዩያን በለይቶ ማቆያ እንዲቀመጡ ተደርገዋል።በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ለማግኘት ፊደል ፖስት የአየር መንገድ ህዝብ ግኑኝነት ክፍሉን ቢጠይቅም መልስ ማግኘት አልቻለም።
Via Fidelpost.com

የዕለቱ የኮሮና ቫይረስ መረጃ!
(በአብመድ የተጠናቀረ)
የኮሮና ቫይረስ ስርጭ ዓለማቀፍ ሁኔታ ዛሬ ምን እንደሚመስል መረጃዎችን ዳስሰናል፤ ስፔን ከፍተኛ አዲስ በኮሮና ቫይረስ የተያዙና የሞቱ ሰዎችን አስመዝግባለች፡፡ ስፔን 6 ሺህ 673 በአዲስ የኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች የተመዘገበባት ሀገር ስትሆን ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ 442 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል፤ ጠቅላላ የሟቾች ቁጥርም 4 ሺህ 87 ደርሷል፡፡ኢራን ደግሞ 2 ሺህ 389 ሰዎች በቫይረሱ በአዲስ ተይዘዋል፤ 157 ሰዎችም ሕይወታቸው አልፏል፡፡ ጠቅላላ በኢራን ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥርም ወደ 2 ሺህ 234 አድጓል፡፡
በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 492 ሺህ 56 ደርሷል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ 21 ሺህ 88 ሰዎች በአዲስ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡ ናቸው፤ 118 ሺህ 22 ሰዎች ደግሞ ከሕመሙ አገግመዋል፡፡ ጠቅላላ የሟቾች ቁጥር 22 ሺህ 175 የደረሰ ሲሆን 897 ሰዎች ዛሬ እንደሞቱ የተረጋገጡ ናቸው፡፡
የቫይረሱ ስርጭት በአፍሪካ ሀገራት ላይም አድማሱን እያሰፋ መሆኑ ተስተውሏል፡፡ጋና 64 ሰዎች በቫይረሱ በአዲስ መያዛቸውን አረጋግጣለች፤ በቱኒዚያ እና በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ደግሞ የአንድ አንድ ሰው ሕይወት ማለፉ ታውቋል፡፡ ሴኔጋል 6 ሰዎች፣ ሞሪሽየስ 4 ሰዎች፣ ጋቦን 1 ሰው፣ ሞሪታኒያ 1 ሰው፣ ሶማሊያ አንድ ሰው ዛሬ በቫይረሱ መያዛቸውን አረጋግጠዋል፡፡
በኢትዮጵያ የተመዘገበ አዲስ በቫይረሱ የተያዘ ሰው የለም፤ ከዚህ ቀደም በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎችም በመልካም ሁኔታ እንዳሉ መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡በስፔን፣ ጀርመንና ኢራን የኮረና ቫይረስ መስፋፋት ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቧል፤ በአንፃሩ በቻይና ደግሞ የተሻለ ለውጥ መመዝገቡ ቀጥሏል፡፡አካላዊ ንክኪን አለማስቀረት አሁንም ለቫይረሱ መስፋፋት ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረ እየተነገረ ነው፡፡ ራስን ከቫይረሱ መጠበቅ ቤተሰብን፣ ሀገርን፣ ዓለምን ከቫይረሱ መጠበቅ ነው፡፡
ምንጭ፡-ወርልዶ ሜትር ዶት ኮም

ከውጭ ሀገር የተላከላችሁን ስጦታ የቀረጥና ማጓጓዣ ከፍላቹ ውሰዱ በማለት ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ያጭበረበሩ 13 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ!
ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ናይጄሪያ፣ ሱዳን እና ኢትዮጵያ ለህገወጥ ማታለል ስራ ተደራጅተው በማህበራዊ ድረገጽ በማታለል ወንጀል ላይ ተሰማርተው የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ግለሰቦቹ በዋናነት ሴቶችን በመተዋወቅና በማግባባት ከውጭ ሀገር የተለያዩ ስጦታ ልከናል ቀረጥና ማጓጓዣ በባንክ ከፍላቹ ውሰዱ በማለት ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ አጭበርብረው በወስደው ተሰውረው የነበሩ ናቸው።
በአሁኑ ወቅትምን በቁጥጥር ስር የዋሉት 13 ግለሰቦች ጉዳያቸው በህግ የተያዘ መሆኑን ያስታወቀው የፌደራል ፖሊስ፥ ሌሎችም በተመሳሳይ ተግባር የተሰማሩ መኖራቸው ጠቁሟል።
በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የፋይናንስና ንግድ ጉዳዮች ወንጀል ምርመራ ዳይሬክተር ኮማንደር ብርሀኑ አበበ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮሮፖሬት እንደተናገሩት፥ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ሰዎችን በተለይም ሴቶችን በማህበራዊ ድረገጽ በመተዋወቅ ውጭ እንደሚኖሩ፣ ከውጭ እርዳታ እንደሚያደርጉና የውጭ ሀገር ጉዞ እድል እንደሚሰጡ በማግባባት ያሳምናሉ ብለዋል።
ይህን እምነታቸውን ተጠቅመው ከውጭ ሀገር የተለያዩ ስጦታዎችን ልከንላችኋል በማለት የተለያዩ የማታለል ተግባራትን እንደሚፈፅሙም ነው ኮማንደር ብርሃኑ የገለፁት።በዚሁ ወቅትም ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ቡድኖች ደግሞ በስልካቸው በመደወል የተላከላቸውን እቃ በባንክ ሂሳብ የማጓጓዣ እና ቀረጥ ከፍላችሁ ውሰዱ በማለት እደሚያታልሉ ገልጸዋል።
በዚህ መንገድም ገንዘቡ ባንክ እዲገባ በማድረግ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ወስደው ተሰውረው የነበረ ሲሆን፥ በተደረገ በክትትል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል።
የመታለል ወንጀል ደርሶብናል ያሉ 70 ግለሰቦች ቀርበው ማሳወቃቸውንም ነው ኮማንደር ብርሃኑ የተናገሩት።አሁንም ሌሎች በዚህ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች መኖራቸውን የጠቆሙት ኮማንደሩ ፥ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።ህብረተሰቡም በመሰል የማታለል ወንጀል ከተሰማሩ አካላት ራሱን እንዲጠብቅ አሳስበዋል።
Via FBC

ቻይና ለውጪ አገር ዜጎች ድንበሯን ዝግ አደረገች!
የቻይና መንግሥት የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የውጪ አገር ዜጎች ወደ አገሪቱ እንዳይገቡ ክልከላ አደረገ።የቻይና መንግሥት ከዚህ ውሳኔ የደረሰው በአሁኑ ወቅት በኮሮናቫይረስ መያዛቸው የሚረጋገጡ ሰዎች፤ ከሌሎች አገራት ወደ ቻይና የገቡ እንጂ በቻይና የሚገኙ ሰዎች ባለመሆናቸው ነው ተብሏል።
Via BBC

በምእራብ ሸዋ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ17 ሰዎች ህይወት አለፈ!
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ሚዳቀኝ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ17 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ። የትራፊክ አደጋው በዛሬው እለት በምዕራብ ሸዋ ዞን ሚዳቀኝ ወረዳ ባላሚ በተባለ ከተማ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ከ30 ላይ ነው የደረሰው።በትራፊክ አደጋው ህይወታቸው ካለፈ 17 ሰዎች በተጨማሪም 13 ሰዎች ላይ ከከባድ እስከ ቀላል አካላዊ ጉዳት መድረሱም ነው የተገለፀው።ከእነዚህም ውስጥ 9 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት 4 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የሚዳቀኝ ወረዳ የትራፊክ ደህንነት አስተባባሪ ምክትል ኢንስፔክተር አዲሱ ኮሬ ተናግረዋል። በትራፊክ አደጋውም ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወደ አምቦ እና በጌዶ ሆስፒታሎች ተወስደው የህክምና ክትትል እንዲያገኙ መደረጉንም አስታውቀዋል።
Via Fana

ኢትዮጵያን ከሱዳን የሚያገናኘው የየብስ ትራንስፖርት እንቅስቃሴ ቢዘጋም ጥበቃ ከሚደረግበት ኬላ ውጭ ባሉ ጫካዎች የጉልበት ሠራተኞች ስለሚዘዋወሩ የቁጥጥር ሥራውን አስቸጋሪ እንዳደረገበት የምዕራብ ጎንደር ዞን አስታውቋል፡፡ኢትዮጵያ የየብስ ድንበሯን መዝጋቷ ይታወቃል።
Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
በጎረቤት ሀገር ኬንያ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ሞት ተመዝግቧል!
ሟቹ የ66 አመት ሰው ሲሆን ለረዥም ጊዜ በስኳር በሽታ ይሰቃይ የነበረ፣ ከ13 ቀን በፊት ከስዋዚላንድ የገባው።
ከዚህ በተጨማሪ በኬንያ ዛሬ 3 ተጨማሪ ተጠቂዎች የተገኙ ሲሆን እስካሁን ድረስ የተመዘገበው ደግሞ 31 ደርሷል።
ምንጭ:Daily Nation