YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ግብፅን ለ30 አመታት በፕሬዝዳንትነት የመሯት ሆስኒ ሙባረክ መሞታቸው ተሰምቷል።

እ.አ.አ በ2011 የተቀሰቀሰው የአረቡ አብዮት ሰለባ የነበሩት ሆስኒ ሙባረክ በ91 አመታቸው ህይወታቸው ማለፉን ፍራንስ 24 ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ የአመራሮች ሥልጠና በዛሬው እለት መካሄድ ጀምሯል፡፡ ስልጠናው በኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማን ጨምሮ በሰንዳፋ ፣ አዳማ እና ባቱ ከተሞች እየተካሄደ ነው፡፡
በስልጠናው ትኩረት የሚደረገው በብልፅግና ፓርቲ መሠረታዊ አስተሳሰቦች ምንነትና ይዘት ላይ እንደሚሆን ታውቋል።
@Yenetube @Fikerassefa
ሰበር ዜና!

ክሳቸው ከተቋረጠላቸው 63 ግለሰቦች መካከል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊው ክርስቲያን ታደለ፤ ኮሎኔል ቢኒያም ተወልደ እና ኤርሚያስ ጠቅል አመልጋ ይገኙበታል፡፡

ምንጭ:አሐዱ ቴሌቪዥን
@YeneTube @FikerAssefa
በተጨማሪም

ኮ/ል ቢኒያም ተወልደ

ረ/ፕሮፌሰር ተሰማ ኤልያስ

አቶ ሳሙኤል በላይነህ

አቶ አሮስ ቃኒሶ ክሳቸው ከሚቋረጥላቸው መካከል እንዳሉበት ሸገር ታይምስ ዘግባለች፣ ሙሉ ዝዝራቸው እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞ የሜቴክ ሀላፊ ብርጋዴል ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ክሳቸው አልተቋረጠም።

Via Tesfaye Getinet
@YeneTube @FikerAssefa
በጊንጪ ከተማ በሚገኝ የፖሊስ ካምፕ ላይ የቦንብ ጥቃት ደረሰ!

በትናንትናው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ጊንጪ ከተማ በሚገኝ የፖሊስ ካምፕ ላይ የቦንብ ጥቃት ደርሷል፡፡በከተማው ትናንት ከምሽቱ 2 ሰዓት በደረሰው በዚህ ጥቃት በወቅቱ በስራ ላይ በነበሩ ሁለት የፖሊ አባላት ላይ በጭስ የመታፈን መጠነኛ ጉዳት ከመድረሱ በቀር የከፋ አደጋ አለመድረሱን የክልሉ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ገልፀዋል፡፡ጥቃቱን በማድረስ የተጠረጠሩ ስድስት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አቶ ጌታቸው በተለይ ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡ድርጊቱን ፈጽመዋል በሚል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ማንነት እስካሁን በተደረገው ምርመራ አለመታወቁን ተናግረዋል፡፡

ምንጭ: ኢቲቪ
@YeneTube @FikerAssefa
የጠብታ አምቡላንስ መስራች አቶ ክብረት አበበ ለመጀመሪያ ጊዜ ማህበራዊ ሀላፌነትን ከመወጣት ጎን ለጎን ቢዝነስ ሞዴልን በማዘጋጀት 1 ሚሊዮን ዶላር ተሸላሚ በሚያደርገዉ ሳን ካልፕ ሽልማት ላይ እጩ ሆኑ፡፡

Via:- Arts TV
@YeneTube @Fikerassefa
የኢራን የጤና ሚንስትር ዴኤታ ኢራጅ ሀሪጂ(በስተግራ የሚታዩት) በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የሚንስቴር መስሪያቤቱ ቃል አቀባይን ጠቅሶ አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የ63ቱ ስም ዝርዝር...

በኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ክሳቸዉ እንድቋረጥ የተደረጉ ግለሰቦች ስም ዝርዝር

የካቲት 17 ቀን 2012 ዓ.ም
1. ሌ/ኮ/ ቢኒያም ተወልደ
2. ሌ/ኮ/ል ሰላይ ይሁን
3. ሌ/ኮ/ል ጸጋዬ አንሙት
4. ኮ/ል ሸጋው ሙሉጌታ
5. ኮ/ል ግርማ ማንዘርጊያ
6. ኮ/ል ዙፋን በርሄ
7. ኮ/ል አሰመረት ኪዳኔ
8. ሻ/ል ይኩኖአምላክ ተሰፋዬ
9. አቶ አለም ፍጹም
10. አቶ ሰለሞን አብርሃ
11. አቶ ሰመረ ኃይለ
12. አቶ ክፍላይ ንጉሴ
13. ሌ/ኮ/ል መንግስቱ ከበደ
14. ሌ/ኮ/ል እሥራኤል አሰፋው
15. ሌ/ኮ/ል ከተማ ከበደ
16. ሌ/ኮ/ል ለተብርሃን ደሞዝ
17. አቶ ኡስማን ከበደ
18. ሌ/ኮ/ል ዋቅቶላ አዲሱ
19. ሌ/ኮ/ል ታቦር ኢዶሳ
20. ሻ/ል ዩሐንስ ትኬሳ
21. ወ/ሮ ወላንሳ ገ/ኢየሱስ
22. ሻ/ቃ ረመዳን ለጋስ
23. አቶ ሙሉጌታ ሰይድ
24. አቶ ዋሴዕ ሳድቅ
25. አቶ ሲሳይ ደበሌ
26. አቶ አክሊሉ ግርማይ
27. ወ/ሮ ራህማ መሀመድ
28. ወ/ሮ ዘምዘም ሀሰን
29. ኮ/ር ፋሩቅ በድሪ
30. አቶ አሳጥረው ከበደ
31. አቶ ሲሳይ አልታሰብ
32. አቶ አበበ ፋንታ
33. አቶ አሰቻለዉ ወርቁ
34. አቶ ተሾመ መለሰ
35. አቶ አለምነህ ሙሉ
36. አቶ ከድር ሰይድ
37. አቶ አዲስ አማረ
38. አቶ አማረ ብሌ
39. አቶ ክርስቲያን ታደሰ
40. አቶ በለጠ ካሳ
41. አቶ ሚፍታህ ሸምሱ
42. ዶ/ር ማቴ ማንገሻ
43. አቶ ታሪኩ ለማ
44. አቶ ጌታሁን ዳጉይ
45. አቶ በላይ በልጉዳ
46. ሪ/ፓ/ር አመሉ ጣሚሶ
47. አቶ ተፈራ ቄንፈቶ
48. ረዳት ፕሮፈሰር ተሰማ ኤልያስ
49. አቶ አማኑኤል በላይነህ
50. አቶ አዲሱ ቃሚሶ
51. ሱ/ኢ/ አሰገል ወ/ጊዩርጊስ
52. ሱ/ኢ/ አሰፋ ኪዳኔ
53. ሱ/ኢ/ ገ/እግዚአብኤር ገ/ሃዋርያት
54. አቶ ግርማ አቡ
55. አቶ አብዱልሙኒየር አብዱልጀሊስ
56. አቶ ቶፊቅ አብዱልቃድር
57. አቶ ከማል መሃመድ
58. ኮ/ር ኡስማን አህመድ
59. ኮ/ር ኤዶሳ ጎሽ
60. አቶ ባበከር ከሊፋ
61. ዋ/ሳ/ እቴነሽ አርፋይኔ
62. አቶ ኤርሚያስ አመልጋ
63. አቶ ሙሉጌታ ሰይድ

https://youtu.be/KQXBZl1TiUk
@YeneTube @Fikerassefa
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ሁለት አዳዲስ ሹመቶችን ይፋ አደረገ

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በዛሬው ዕለት ሁለት አዳዲስ ሹመቶችን ይፋ አድርጓል፡፡
በዚሁ መሰረት፦

1. አቶ ዮሐንስ ቧያለው የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ፕሬዝዳንት

2. ዶ/ር አምባሳደር አዲስዓለም ባሌማ ደግሞ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዮት ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ሁለቱም ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ከጥር 14 ጀምሮ መሾማቸውን መረጃው ጨምሮ ገልጿል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
ሸገር የብዙኃን ትራንስፖርት ድርጅት 28 ሚሊዮን ደንበኞችን በማጓጓዝ ከ87.1 ብር በላይ ሚሊዮን ብር ገቢ ሰበሰበ፡፡

በ2012 ዓ.ም ግማሽ ዓመት 28 ሚሊዮን ደንበኞችን በማጓጓዝ ከትኬት ሽያጭ ከትኬት ሽያጭ 78.3 ሚሊዮን ብር እንዲሁም በተማሪዎች ሰርቪስ አገልግሎት 5.48 ሚሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን ሸገር የብዙኃን ትራንስፖርት ድርጅት አስታውቋል፡፡በተጨማሪም በ94 የተማሪ አውቶብሶች ፣ ከኮንትራት አገልግሎት ፣ ከክሬን ኪራይ እና ጥገናን ጨምሮ በጠቅላላው 87.1 ሚሊዮን ብር መሰብሰብ ገቢ መሰብሰብ እንደቻለ ድርጅቱ ገልጿል፡፡

ምንጭ: የከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬተሪያት
@YeneTube @FikerAssefa
ከገረሴ ወረዳ ወደ አርባምንጭ ከተማ ሲጓዝ የነበረ ኮድ 3-14167 ሚኒባስ መኪና በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ ሾፌሩንና ረዳቱን ጨምሮ 8 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተገለፀ፡፡

የጋሞ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ረታ ተክሉ እንዳሉት ከገረሴ ወረዳ መንገደኞችን ጭኖ ወደ አርባምንጭ ሲጓዝ የነበረ ሚኒባስ መኪና በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ቆላ ሼሌ መግቢያ ሲደርስ የመገልበጥ አደጋ ደርሶበታል ፡፡

ከቀኑ 9፡00ሰዓት አካባቢ በደረሰው አደጋ ሾፌሩን እና ረዳቱን ጨምሮ 8 ሰዎች ለህልፈተ ሲዳረጉ 13 ሰዎች ደግሞ ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል በህክምና ላይ ይገኛሉ፡፡የአደጋው መንስዔ እየተጣራ መሆኑን የመምሪያው አዛዥ ኮማንደር ረታ ተክሉ ተናግረዋል፡፡

ምን: የጋሞ ዞን ህዝብ ግኑኝነት መምሪያ
@YeneTube @FikerAssefa
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ የካቲት 17 ቀን 2012 ዓም ማምሻውን ወደ ጣሊያን አቅንተዋል።

ክቡር አቶ ገዱ ከጣሊያኑ አቻቸው ጋር በሚኖራቸው ውይይት በሁለቱ አገሮች መካከል እያደገ የመጣውን የሁለትዮሽ ግንኙነትና ትብብር የበለጠ ለማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ።ክቡር አቶ ገዱ በጣሊያን ቆይታቸው ከዓለም የእርሻና ምግብ ድርጅት፣ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም እንዲሁም ከዓለም አቀፍ የእርሻ ልማት ፈንድ ሃላፊዎች ጋር ውይይቶችን ያደርጋሉ። ክቡር አቶ ገዱ ከድርጅቶቹ ሃላፊዎች ጋር በሚኖራቸው ውይይት ወቅት ድርጅቶቹ በአገራችን የሚያከናውኗቸው የልማት ፕሮጀክቶች በአገራችን ከተጀመረው የሪፎርም ፕሮግራም ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ሃሳብ እንደሚለዋወጡ ይጠበቃል።

ምንጭ: የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
@YeneTube @FikerAssefa
ጥያቄ

ከኮሮና ቫይረስ እና ከሀገራ አቀፍ ምርጫ የቱ ያሰጋችዋል ?
Anonymous Poll
50%
ኮሮና ቫይረስ
50%
ሀገር አቀፍ ምርጫ
ኮሮና ቫይረስ አልጄሪያ መግባቱ ተረጋግጧል።ተጠቂው ጣልያናዊ ዜግነት ያለው ወደ አልጄሪያ ለጉብኝት እንደመጣ የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል።

Join @Coronavirusliveupdate
@YeneTube @Fikerassefa
Forwarded from YeneTube
🎊| አስደሳች ዜና ራሰ-በርሃ ለሆኑ ሴትና ወንዷች ፂም ማሳደግ ለሚፈልጉ||💯💯💯
📌🇺🇸🇺🇸🇺🇸 አሜሪካ ሰራሹ ተአምረኛው ትሪትመንት በድጋሚ አገራችን ገባ በ ቀናት ውስጥ ከ መላጣነት ወደ ማበጠሪያ ተጠቃሚነት ይዞራሉ,100% በተግባር የታየ ፀጉር እና ፂም ማሳደጊያ
አናም የእርሶ ፀጉር
👉🏼 አላድግም ብሎ ለቀረ 👉🏼 ራሰ በርሃ ለሆነ
👉🏼 ወደራሰ በርሃነት የተጠጋ ለሳሳ ፀጉር
👉🏼 ወደውስተጥ ለገባ ፀጉር
👉🏼 ፐረም ወይም ጄል ለጨረሰው ፀጉር
👉🏼ላሽ ለበላው #ፂም #ፀጉር
👉🏼 ተፈግፍጎም ሆነ በሌላ ምክንያት አላድግ ብሎ ለቀረ ፂም 👉🏼 በዘር ፂም ለማያበቅል
100% በተግባር የታየ ፀጉር እና ፂም ማሳደጊያ 🔽USA🇺🇸 አሁኑኑ ያናግሩን @Fabulousss 
በተጨማሪም በተለያዩ አማራጮችየቀረቡ የዉፍረት መቀነሻ ቀበቶዎች, [Human hair ] +ለ እስፖርታዊ እንቅስቃሴ ገንቢ የሆኑ ፕሮቲኖች (protein shake),በተለያየ ምክንያት ለመጣ ጠባሳ ማጥፊያ የሚሆኑ ትሪትመንቶችን ከኛ ያገኛሉ፡፡➡️ ✆ +251991203033
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEpoRsmLNv7NNj3K_g