YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሀመድ የተመራና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር ደዔታ ክቡር ተስፋሁን ጎበዛይ እንዲሁም የአገር መከላከያ ከፍተኛ አመራሮች ያካተተ የአገራችን ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከየካቲት 12-13 ቀን 2012 ዓ.ም በሳዑዲ ዓረቢያ ሪያድ የስራ ጉብኝት አድርጓል፡፡

በቆይታውም የልዑካን ቡድኑ ከሳዑዲ አረቢያ የጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ፈያድ ቢን ሃመድ አል-ሩዋሊና የሳዑዲ ዓረቢያ የመከላከያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በመገናኘት በሁለትዮሽና ቀጠናዊ የሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይቶችን አካሂዷል፡፡ በውይይቶቹ በኢትዮጵያና ሳዑዲ ዓረቢያ መካከል በመከላከያ ዘርፍ ያለውን የሁለትዮሽ ትብብር ለማጠናከርና በሌሎች ቀጠናዊ የጋራ ስጋቶች ዙሪያ በትብብር መስራትና የልምድ ልውውጥ ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክርና የሃሳብ ልውውጦች ተደርገዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ በሪያድ የሚገኘውን የእስላማዊ ጸረ-ሽብርተኝነት ወታደራዊ ጥምረት ማዕከል (The Islamic Military Counter Terrorism Coalition (IMCTC)) ዋና ጽ/ቤት በመጎብኘትም ከማዕከሉ አመራሮች ጋር ሽብርተኝነት በመከላከል ረገድ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርጓል፡፡

ምንጭ: በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@YeneTube @FikerAssefa
ስለ COVID-19 የካቲት 13/2012 የተሰጠ ወቅታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ፡፡

Via EPHI


ከኮሮና ቫይረስ ጋር ለተያያዙ ዜናዎች Special ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEjsbjPMSsije0LoiQ

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
🎊| አስደሳች ዜና ራሰ-በርሃ ለሆኑ ሴትና ወንዷች ፂም ማሳደግ ለሚፈልጉ||💯💯💯
📌🇺🇸🇺🇸🇺🇸 አሜሪካ ሰራሹ ተአምረኛው ትሪትመንት በድጋሚ አገራችን ገባ በ ቀናት ውስጥ ከ መላጣነት ወደ ማበጠሪያ ተጠቃሚነት ይዞራሉ,100% በተግባር የታየ ፀጉር እና ፂም ማሳደጊያ
አናም የእርሶ ፀጉር
👉🏼 አላድግም ብሎ ለቀረ 👉🏼 ራሰ በርሃ ለሆነ
👉🏼 ወደራሰ በርሃነት የተጠጋ ለሳሳ ፀጉር
👉🏼 ወደውስተጥ ለገባ ፀጉር
👉🏼 ፐረም ወይም ጄል ለጨረሰው ፀጉር
👉🏼ላሽ ለበላው #ፂም #ፀጉር
👉🏼 ተፈግፍጎም ሆነ በሌላ ምክንያት አላድግ ብሎ ለቀረ ፂም 👉🏼 በዘር ፂም ለማያበቅል
100% በተግባር የታየ ፀጉር እና ፂም ማሳደጊያ 🔽USA🇺🇸 አሁኑኑ ያናግሩን @Fabulousss 
በተጨማሪም በተለያዩ አማራጮችየቀረቡ የዉፍረት መቀነሻ ቀበቶዎች, [Human hair ] +ለ እስፖርታዊ እንቅስቃሴ ገንቢ የሆኑ ፕሮቲኖች (protein shake),በተለያየ ምክንያት ለመጣ ጠባሳ ማጥፊያ የሚሆኑ ትሪትመንቶችን ከኛ ያገኛሉ፡፡➡️ ✆ +251991203033
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAEpoRsmLNv7NNj3K_g
ሰበር ዜና!

የቡራዩ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሰለሞን በጥይት ተገደሉ!

የቡራዩ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ሰለሞን ታደሰ ዛሬ ምሳ ሰዓት ላይ በቡራዩ ከተማ በጥይት ተመተው ተገደሉ። ከኮሚሽነር ሰለሞን ታደሰ ጋር አብሮ የነበሩት የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን የልዩ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ተስፋዬ ድንቁም በጥይት ተመተው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።

ሁለቱ የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ቢሮ ኃላፊዎች ላይ ጥቃቱን የሰነዘረው አካል ማንነት እስካሁን ግልጽ አለመሆኑን እና እስካሁን በወንጀሉ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር የዋለ ሰው አለመኖሩንም የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ኦቶ ጌታቸው እንዳሉት በሁለቱ ባለስልጣናት ላይ ጥቃቱ የተሰነዘረው የቡራዩ ከተማ አስተዳደር አቅራቢያ ምሳ እየተመገቡ ሳሉ ነበር።በጥይት ተመተው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው የሚገኙት ኮማንደር ተስፋዬ የሚገኙበትን ሁኔታ ማወቅ አልተቻለም።

ዘገባው የቢቢሲ ነው
ፎቶ:ኢቲቪ
@YeneTube @FikerAssefa
ቅርስ የሆነው የራስ ሙሌጌታ ቤት ደህንነት ነን ያሉ ሰዎች “አንወጣም ” በማለታቸው ሊታደስ አልቻለም

በአዲስ አበባ ቅድስተ ማርያም አካባቢ የሚገኘውና ዘጠና አመት ያስቆጠረው የራስ ሙሉጌታ ( አባ ገስጥ ቤት) ደህንነት ነን አንወጣም ስላሉኝ ቤቱን ላድስ አልቻልኩም ሲል የከተማው ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ቅሪታውን ገለፀ።

የቢሮው የቅርስ ጥበቃ ክፍል ዛሬ ለፊደል ፓስት እንደተናገረው ትናንት ሐሙስ ወደ ሰባት የሚጠጉ ፓሊሶችን ይዞ ወደ ቤቱ ቀን ስምንት ሰአት ገደማ ቢዘልቅም በውስጡ ያሉ ሰዎች ግርግር መፍጠራቸውንና ፓሊስም ሑከት ላለመፍጠር ሲል ቦታውን ለቆ ሂዷል ብሏል።
ቢሮውም ለከተማዋ ፓሊስ ኮሚሽን አቤቱታ አቅርቦ ምላሽ አየተጠባበቀ እንደሚገኝ ተናግሯል።

እንደ ቢሮው ገለፃ ቤቱ በደርግ ግዜ የፓሊት ቢሮ ሆኖ ሲያገለግል እንደነበረና ከዛም ት/ቤት ሆኖ ያገለገለ ሲሆን ከቅርብ አመታት ጀምሮ ግን የደህንነት ሰዎች ሲጠቀሙበት እንደነበረ ገልፇል።

ሆኖም ግን ያለምንም ህጋዊ ዶክመንት ወደ ስምንት የሚጠጉ አባወራዎች ከነቤተሰቦቻቸው 760 ካሬ ሜትር ገደማ የሆነውን መሬትን ይዘውት የደህንነት ስዎች ነን በሚል ምክንያት አንወጣም በማለታቸው ታድሶ ለቱሪስት አገልግሎት አንዲሰጥ የታሰበውን በህገወጥ መልኩ መያዛቸውን አስረድቷል።

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 የሚገኘው በግንብ የተሰራው ባለ አንድ ፎቅ ቤት የሰሩት ራስ ሙሉጌታ የመጀመሪው የገንዘብ ሚኒስቴር ሲሆኑ የካቲት 19,1929 ማረፋቸው የታሪክ ማህደራቸው ይናገራል።

Via:- Fidel Post
@YeneTube @Fikerassefa
ጃዋር መሐመድ የውጭ ሀገር ዜግነቱን መልሶ የኢትዮጵያ ዜግነትን ለማግኘት ማመልከቻ ማስገባቱ ብቻ በቂ እንዳልሆነ ከኢምግሬሽን ማብራሪያ አግኝቻለሁ ሲል ምርጫ ቦርድ ትናንት ለቪኦኤ ተናግሯል። ኢምግሬሽን ማብራሪያውን የሰጠው ከቦርዱ በቀረበለት ጥያቄ መሠረት ነው፡፡

Via Wazema/VoA
@YeneTube @FikerAssefa
መረጃ ለጋጣፎ

ለገጣፎ መንገድ ተዘግቷል ለምን እንደተዘጋ ባይታወቅም ብዙ መኪኖች ቆመዋል ከካራ ጀምሮ መንገዶች ዝግ ናቸው።

@YeneTube @Fikerassefa
YeneTube
መረጃ ለጋጣፎ ለገጣፎ መንገድ ተዘግቷል ለምን እንደተዘጋ ባይታወቅም ብዙ መኪኖች ቆመዋል ከካራ ጀምሮ መንገዶች ዝግ ናቸው። @YeneTube @Fikerassefa
#Update በአዲስ አበባ በአራቱም አቅጣጫ በሚባል መልኩ ከፍተኛ ፍተሻ እየተደረገ ይገኛል።
በዚህ ምክንያት የመንገድ መዘጋጋት ተከስቷል በመውጫዎች።

@YeneTube @Fikerassefa
ለማስታወስ ያክል

የካቲት 14/2012 ከቀኑ 10 ሰዐት ጀምሮ #ኢትዮጵያን_ወደ_ፍቅር የተሰኘው የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ነገ ይካሄዳል።
@YeneTube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዶ/ር አብይ አህመድ አክብሮት እና ምስጋና በተለያየ ክልል የተደረገውን የድጋፍ ሰልፍ አስመልክቶ።

@YeneTube @Fikerassefa
Channel For Sale!!

ከ47000 በላይ ተከታይ ያለው የስፓርት ቻናላችን ( @Yenesport ) ከአቅማችን በላይ በመሆነ ምክንያትን የስፖርት ዜናዎችን በአማርኛ ማቅረብ ባለመቻላችን ላለፉት 2 አመታት ስንሰራ የነበረበትን ቻናል #ለመሸጥ የተገደድን ስለሆነ ቻናላችንን ለመግዛት የምትፈልጉ ድርጅቶች ማናገር ትችላላችው።

@YeneTube @Fikerassefa
በማድሪድ የምሽቱ የቤት ውስጥ በ3000 ሜትር የወንዶች ውድድር ኢትዮጵያዊው ጌትነት ዋለ በቀዳሚነት አሸንፏል።

Via:- Ethio kickoff
@YeneTube @Fikerassefa
ጅማ የተማሪዎች ምረቃ

ጅማ ዩኒቨርስቲ በቅድመና በድህረ ምረቃ ዘርፎች ያስተማራቸውን 3 ሺህ 139 ተማሪዎች ዛሬ እያስመረቀ ነው።

ከእነዚህ ምሩቃን ውስጥም 237 የህክምና ዶክተሮች፣ 27 የጥርስ ህክምና ዶክተሮች 8ቱ ደግሞ የሶስተኛ ድግሪ ተመራቂዎች ናቸው፡፡
ከተመራቂዎች መካከልም 13ቱ ከሶማሊላንድና ከሩዋንዳ የመጡ መሆናቸው ተገልጿል ፡፡

Via:- EPA
@YeneTube @FikerAssefa
መከላከያ በምዕራብ ኦሮሚያ በሚንቀሳቀሰው ኃይል ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰድኩ ነው አለ!

ጃልመሮ አንድም ቀን መሳሪያ ተኩሶ አያውቅም፤...[ይልቁኑ] ታዳጊዎችን ከቀያቸው ሰብስቦ እያስጨረሳቸው ነው"

በምዕራብ ኦሮሚያ የተከሰተውን የጸጥታ ችግር ተከትሎ መንግሥት የአካባቢውን ደህንነት ለማስጠበቅ የጸጥታ ኃይል ወደ ስፍራው ማሰማራቱን መግለፁ ይታወሳል።መንግሥት የጸጥታ አስከባሪ ኃይል ወደ ስፍራው ያሰማራሁት ታጥቆ የሚንቀሳቀሱና የአካባቢው ነዋሪ ላይ ጥቃት የሚፈፅሙ አካላት ላይ እርምጃ ለመውሰድ ነው ቢልም፤ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች ደግሞ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በንጹሃን ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎች ላይ እጁ አለበት ሲሉ ይኮንናሉ።

ቢቢሲ በዚህ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ከምክትል ኢታማዦር ሹሙ ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ጋር ያደረገውን ቆይታ አቅርበንላችዋል አንብቡት።

👇👇👇👇
https://telegra.ph/ArmyChief-02-22
ስፖርታዊ ውርርድን በተመለከተ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ጋር በአዳማ ከተማ ምክክር እያደረገ ነው፡፡

በምክክር መድረኩ ተገኝተን እንደሰማነው የስፖርት ውርርድ ቁማር በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካቶችን በመሳብ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሥነ-ልቦናዊ ጉዳቶችን እያደረሰ ነው ተብሏል፡፡ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ያሉ ተማሪዎች ለውርርዱ በሚሰጡት ትኩረት ትምህርታቸውን እያስተጓጎሉ መሆኑ በምክክሩ ተነስቷል፡፡

በርካታ አዋቂዎችም በውርርድ በሚያጡት ገንዘብ ኪሳራ እና የሀብት ብክነት እየገጠማቸው መሆኑን ያደረግናቸው አጫጭር ዳሰሳዎች ይጠቁማሉ ሲሉ በሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር የወጣቶች ስብዕና ልማት ዳይሬክተሩ አቶ ዓለሙ ሰኢድ ተናግረዋል፡፡በውርርዱ ሱሰኛ ሆነው የትዳር መፍረስ እና የቤተሰብ መበተን ያጋጠማቸው መኖራቸውንም አቶ ዓለሙ አንስተዋል፡፡

ስንፍናን በማስፋፋት እና ጠንካራ የስራ ባህል እንዳይኖር በማድረግ በኩልም የስፖርት ውርርዱ ከፍ ያለ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል ብለዋል፡፡የምክክሩ ተሳታፊዎችም የጉዳዩ አሳሳቢነት ከፍ ያለ በመሆኑ ከወዲሁ ሊታሰብበት ይገባል ሲሉ ጠንከር ያለ ሀሳቦችን አንስተዋል፡፡

ከ11 ዓመት በፊት በወጣ አዋጅ ተግባራዊ መሆን የጀመረውን የስፖርት ውርርድ፣ ጨዋታ እና መዝናኛ ነው የሚለው ብሔራዊ ሎተሪም እየመጣ ያለውን ችግር በማየት አዋጁን በድጋሚ ሊያጤነው ይገባል ብለዋል፡፡በአሁኑ ወቅት 46 ድርጅቶች የስፖርት ውርርድ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው ሲሆን 22 የሚሆኑት በአወራራጅነት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡በአዲስ አበባ ከሚሰሩ አወራራጅ ድርጅቶች መካከል አንዱ ብቻ 65 ቅርንጫፎችን ከፍቶ ይሰራል፡፡ቁጥሩ ይለያይ እንጂ ሁሉም ድርጅቶች በርካታ ቅርንጫፎች አሏቸው ተብሏል፡፡

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
ኮሮና ቫይረስ ከቻይና ግዛት ውጪ በኢራን እና በደቡብ ኮርያ እየተስፋፋ ይገኛል ትላንት ብቻ 81 ሰዎች በደቡብ ኮርያ በቫይረሱ የተያዡ ሲሆን በአጠቃላይ 433 ሰዎችን በደቡብ ኮርያ በቫይረሱ ተይዘዋል እንዲሁም በአጠቃላይ 3 ሰዎች ሞተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በኢራን በተመሳሳይ መልኩ ማለት በሚቻል መልኩ ቫይረሱ እየተስፋፋ ይገኛል በኢራን የሟቾች ቁጥር 4 ደርሷል።

ከኮሮና ቫይረስ ጋር የተገናኘ ዘናዎችን የምንለቅበትን ቻናል ይቀላቀሉ

@coronavirusliveupdate
@coronavirusliveupdate

@YeneTube @Fikerassefa
ማንም ኢትዮጵያ ለምንም ኢትዮጵያዊ የዜግነት ሰርተፍኬት መስጠት አይችልም ይህንን ሁሉም እንዲያውቅ ያስፋልጋል።

ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና በሀዋሳ እየተካሄደ ባለው የሲዳማ ዓርነት ንቅናቄ ስብሰባ ላይ የተናገሩት

Via:- Maleda media
@Yenetube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ፣ አቶ ጌታቸው ባልቻ የቡራዩ ከተማ አስተዳደርና ፀጥታ ኃላፊ አቶ ሠለሞን ታደሰ የቀብር ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት እንደሚፈፀም ለቢቢሲ አስታውቀዋል።

@YeneTube @Fikerassefa
በአሶሳ ከተማ 46 አባላት ያለው የዘራፊ ቡድን በቁጥጥር ስር መዋሉን የከተማዋ ፖሊስ አስታወቀ።

ትናንት ምሽት የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች ለክልሉ ፖሊስ ባደረሱት ጥቆማ መሰረት ድንገተኛ አሰሳ ተደርጎ የአንድ የዘረፋ ቡድን አባል የሆኑ 45 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የኮሚንኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ መለሰ በየነ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡46ኛው የቡድኑ አባል ደግሞ ዛሬ ጥዋት መያዙን ነግረውናል፡፡

እስካሁን ባለው መረጃ ዘራፊዎቹ ከ10 ቀናት በፊት በመደራጀት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችንና ገንዘብ ሲዘርፉ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ሌሎች መረጃዎች በመጣራት ላይ መሆናቸውንና ፖሊስ ሙሉ ምርመራዎቹን ሲያጠናቅቅ ለሀዘብ ይፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡እነዚህ ግለሰቦች ከዚህ በፊት በዝርፊያ የተሰማሩ መሆናቸው ተረጋግጦ ታስረው የነበረ ሲሆን የእርምት ጊዜያቸውን ጨርሰው ታርመዋል ተብለው የተፈቱ ነበሩ በማለት አቶ መለሰ ተናግረዋል፡፡

ከዛሬ አስር ቀን በፊት በአሶሳ ከፍተኛ ዝርፊያ ተስፋፍቶ እንደነበር የገለፁት ሀላፊው ፖሊስ ጉዳዩን ሲከታተል ቆይቶ 46ቱን በቁጥጥር ስር አውሏል ብለዋል።ሌሎች ተጨማሪ አባላቶች ሊኖሩ እንደሚችልና እነርሱንም በቀጣይ በሚደረጉ ምርመራዎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ይሰራል ተብሏል፡፡እስከዛሬ የዘረፉትን ንብረት ለባለቤቶች የማስመለስ ስራ መጀመሩንም ሃላፊው ነግረውናል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa