YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በኢትዮጵያው በተከሰከሰው የቦይንግ 737 አውሮፕላን የሟቾች ጠበቆች በቦይንግ ኩባንያ ላይ የመሠረቱት ክስ ዛሬ በቺካጎ ፍርድ ቤት እንደሚታይ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ኩባንያው ስለ አውሮፕላኑ ስሪት፣ ዲዛይን እና ስለደረሱት አደጋዎች ሙሉ ሰነዶችን እንዲሰጣቸው ነው ጠበቆቹ የከሰሱት፡፡ ጠበቆቹ ኩባንያው ቁልፍ መረጃዎችን ከምርመራው ቡድን እንደደበቀ ያምናሉ፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
#ኦነግ #OLF #ABO

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከ350 በላይ የሚሆኑ አባሎቹ በመንግስት መታሰራቸውን አስታወቀ።

ፓርቲው እንዳስታወቀው በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ከ350 በላይ አባሎቼ እና ደጋፊዎቼ በጅምላ ታስረውብኛል ብሏል።

ፓርቲው እንዳስታወቀው በቀጣዩ አገር አቀፍ ምርጫ ለመወዳደር ዝግጅት እያደረገበሚገኝበት በዚህ ወቅት ይህ የጅምላ እስር መፈጸሙ አሳስቦኛል የተጀመረውን የዲሞክራሲ ጭላንጭልም ያከስማል ብሏል።

ሰሞኑን ባልታወቀ ሁኔታ በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች የጅምላ እስራት በዘመቻ መልኩ በኦነግ አባላት እና ደጋፊዎች ላይ ተፋፍሞ ይገኛል፡፡ ይህን የጅምላ እስራት እየፈጸመ የለዉ አካል የኦሮሚያ ፖሊስ እንደሆነም ፓርቲው አስታውቋል።

የጅምላ እስሩ በተለይም ከአንድ ሳምንት ወድህ ብቻ በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች (በ7 የኦሮሚያ ዞኖች እና በ26 ወረዳና የከተማ አስተዳደሮች) በጅምላ ከታሰሩት አባላቶቻችን እና ደጋፊዎቻችን መካከል እስከ አሁን ባገኛነዉ መረጃ መሰረት ወደ 350 የሚጠጉ የፓርቲው አመራሮች እና አባላት ታስረውብኛል መንግስት በአስቸኳይ ይፍታቸው ሲል አሳስቧል።

Via:- Ethio FM
@YeneTube @Fikerassefa
መንግስት በታገቱት የደንቢ ደሎ ዪንቨርሲት ተማሪዎች አጥጋቢ ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ በኦሮሚያ ክልል የሚማሩ የአማራ ተማሪዎች ወደቦታቸው እንዲመለሱ አደርጋለው ሲል የአማራ ወጣቶች ማህበር አሳሰበ፡፡

የአማራ ወጣቶች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ አስናቀ መንገሻ ለአሐዱ እንደተናገሩት ከሁለት ወራት በፊት በደንቢዶሎ ዩንቨርስቲ 17 የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች የታገቱ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል 40ሺ የሚሆኑት ደግሞ ከትምህርት ገበታቸው መፈናቀላቸውን አንስተዋል::

መንግስት በታገቱ ተማሪዎች ላይ አፋጣኝ ምላሽ የማይሰጥና ሀላፊነቱን የማይወጣ ከሆነ በሁሉም የኦሮሚያ ክልል ዩንቨርሲቲዎች የሚማሩ የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች ወደየቤታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ በቅርቡ መግለጫ እንደሚሰጥ የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ አስናቀ ተናግረዋል፡፡

#Bringbackourstudents

Via:- Ahadu radio
@YeneTube @Fikerassefa
"ተባርኮ የተሰጠን ጽላት[ፈይሳ አዱኛ] አለን” ያሉት ማደናገርያ መኾኑን አረገጠናል፣ ምእመናን በዚህ እንዳይሳሳቱ ሲሉ በመግለጫው አሳስበዋል።

@YeneTube @Fikerassefa
ሜቴክ ‹‹ኢንተግሬትድ ኢንዱስትሪያል ቴክኖሎጂ ኮርፖሬሽን›› በሚል ስያሜ በድጋሚ ሊቋቋም ነው!

በርካታ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ ባለመቻሉና ከዚሁ ጋር በተገናኘ የአገር ሀብት እንዲባክን አድርጓል ተብሎ የሚወቀሰው የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ)፣ ‹‹ኢንተግሬትድ ኢንዱስትሪያል ቴክኖሎጂ ኮርፖሬሽን›› በሚል ስያሜ በድጋሚ ሊቋቋም ነው።ሜቴክን በድጋሚ ለማቋቋም የተረቀቀው ማቋቋሚያ ደንብ፣ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መላኩን ሪፖርተር ከታማኝ ምንጮች ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ሜቴክ ‹‹ኢንተግሬትድ ኢንዱስትሪያል ቴክኖሎጂ ኮርፖሬሽን›› በሚል ስያሜ በድጋሚ እንደሚቋቋም፣ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 25/1984 መሠረት እንደሚተዳደርም ረቂቅ ደንቡ ይገልጻል።

ሜቴክ ኢንተግሬትድ ኢንዱስትሪያል ቴክኖሎጂ ኮርፖሬሽን በሚል መጠሪያ በድጋሚ ከተቋቋመ በኋላ፣ እንዲያሳካቸው የሚፈለጉ ዓላማዎችንም ረቂቅ ደንቡ ይዘረዝራል። ከተዘረዘሩት ዓላማዎች መካከል የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ለማፋጠን፣ እንዲሁም የዕውቀትና የፋይናንስ እጥረትን ለመፍታት በሚያስችለው መንገድ ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ኩባንያዎች ጋር በአጋርነት መሥራት አንዱ ሲሆን፣ ለወታደራዊ አገልግሎት የሚውሉትን ጨምሮ በማንኛውም ቴክኖሎጂ ላይ መመራመር፣ ማልማትና ወደ ፋብሪካ ውጤትነት መቀየር ሌላው የኮርፖሬሽኑ ዓላማ እንደሚሆን ተመልክቷል።

Via Reporter
@YeneTube @FikerAssefa
ግራ አጋቢው ዘመን
አዲስ መፅሐፍ በገበያ ላይ

የወባ ትንኞችን ከመግደል ሀሳቦችን ወደ መግደል፤
ከስራ አጥነት ወደ ስራ አልባነት እያመራን ነው… ምን ይሻላል?

ግራ አጋቢው ዘመን መፅሐፍ መፍትሄ አለው፡፡

መፅሐፉ እንዴት ከጀግንነት ወደለየለት ብሔርተኝነት፣
ከኃይማኖተኝነት ደግሞ ወደ ሽብርተኝነት እያመራን እንዳለን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ መጨረሻችንስ?

መልሱ ግራ አጋቢው ዘመን መፅሐፍ ውስጥ ይገኛል፡፡

እንኳን ወደ ግራ አጋቢው ዘመን መፅሐፍ ግራ ተጋብተው መጡ!!

የእውነት ይሄ መፅሐፍ አስተሳሰባችሁን ያሰፋዋል!!

በየመፅሀፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል!!
ባይብል ኮድ

ስለ እያንዳንዳችን ዕጣ ፈንታ ጨምሮ በአለም ላይ ያሉ መሪዎች ስለሚገደሉበት ቦታ፣ ስለሚገድሏቸው ሰዎች ስም…

በአለም ላይ ስለተከናወኑ ነገሮችና ወደፊትም ስለሚከናወኑ ነገሮች ሁሉ በስም፣ በቀንና በቦታ ሳይቀር ከዛሬ ሶስት ሺ አመት በፊት…

በየቤታችን በሚገኘው መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ በኮድ ተቀጧል!!

በአንድ ምሽት ሽያጭ ብቻ ሪከርድ የያዙት ባይብል ኮድ ቁጥር 1፣ ቁጥር 2 እና የመጨረሻው ቁጥር 3 ኮዶቹን እየፈቱ ያስደምሙናል፡፡

ሶስቱንም መጽሐፎች በየመፅሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኟቸዋል፡፡
@teklutilahun
Forwarded from HEY Online Market
Galaxy A51 (2019)
Display: 6.4"
Storage: 128 GB
Camer: 48 MP + 5 MP
Battery: 4000 mAh
Ram: 6 GB

Price : 13,200 Birr

Contact US @heymobile
0925927457
0953964175
0910695100
@HEYOnlinemarket
Forwarded from YeneTube
📌 Minoxidil የወንዶች ፀጉርና ፂም ማሳደግያ

📌 ፀጉሮት እየሳሳ አስቸግሮታል አልያም ፂም ማብቀል ይፈልጋሉ ? መፍትሔውን ይዘንሎት መተናል

ከቆዳችን ስር የሚገኘውን የፀጉር ጉጥ በማንቃት የሳሳን ፀጉር ወደ ቀድሞው የሚመልስ

📌📌 በ"FDA" እውቅናና ማረጋገጫ የተሰጠው ደግሞም በebay ፣ amazon እና በመሳሰሉት የ online መገበያያዎች ላይ "5" ★★★★★ ኮኮብ ያገኘ ነው

በቀን 2 ጊዜ ለሚጠቀሙ ሰዎች በ 1 ወር ውስጥ ውጤት የሚያሳይ

📞 0993944661
📞 0953928523
Forwarded from YeneTube
ሁሉንም ሰብስቦ በአንድ ላይ የያዘ የግብይት ድረገፅ
በድረ ገፁ ላይ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ዕቃዎቹን መሸጥ ይችላል።
ከ2700 በላይ ዕቃዎች

@SebsibieEthiopia
www.sebsibie.com
📞 0953707070
83ኛው የሰማዕታት ቀን በአዲስ አበባ 6 ኪሎ የሰማዕታት መታሰቢያ ሀውልት አደባባይ እየተከበረ ነው።

ዕለቱ አባት አርበኞችና የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት ነው እየተከበረ ያለው።የሀገር መከላከያና የፌደራል ፖሊስ ማርሽ ባንድ አባላት በስፍራው በመገኘት የተለያዩ ጣዕመ ዜማዎችን አሰምተዋል።ዕለቱ በ1929 ዓ.ም በወቅቱ የኢትዮጵያ አገረ ገዢ በነበረው ሮዶልፎ ግራዚያኒ በግፍ የተጨፈጨፉ ከ30 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን የሚታወሱበት ነው።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
አዲስ የመንግሥት ሠራተኞች ውሎ አበል ደንብ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀረበ!

የኢፌዴሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አዲስ የመንግሥት ሠራተኞች ውሎ አበል ደንብ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ማቅረቡን አስታወቀ።በኮሚሽኑ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አለባቸው ዓለሙ፣ ረቂቅ ደንቡ ካለው ነባራዊ ሁኔታ በመነሣት በጥናት ላይ ተመሥርቶ መዘጋጀቱን አመልክተዋል።ደንቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተመርምሮ ማስተካከያ ከተደረገበት በኋላ፣ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመርቶ ተግባር ላይ እንዲውል የሚደረግ መሆኑም ተጠቁሟል።ከሐምሌ 1 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ የዋለው የመንግስት ሠራተኞች የቀን ውሎ አበል መመሪያ እንደሚያመለክተው የመንግሥት ሠራተኛው በየትኛውም ክልል ሄዶ ቢሰራ ከፍተኛ ደመወዝ አለው የሚባለው 225 ብር የሚታሰብለት ሲሆን፤ አነስተኛ ደመወዝ ተከፋይ ነው የሚባለው ደግሞ በቀን የሚያገኘው 111 ብር ነው።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
ህዝብዊ የድጋፍ ሰልፍ በሀዋሳ ከተማ እንደሚደረግ ተገለጸ!

አርብ የካቲት 13/2012 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ማግስት ጀምሮ በሀገራችን እያስመዘገቡ ያሉትን ለውጥ በመደገፍና ለውጡን ለማስቀጠል ህዝቡ ከጎናቸው የሚቆም መሆኑን ለማረጋገጥ ታላቅ ህዝባዊ የምስጋናና የድጋፍ ሰልፍ እንደሚደረግ ተገለጸ።በመሆኑም የከተማው ነዋሪዎችና የሲዳማ ህዝብ የሚያደርጉት ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ፍጽም ሰላማዊና የደመቀ እንዲሆን የዞኑና የከተማው አስተዳደር አስፈላጊውን ዝግጅት ያጠናቀቁ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ህዝብ ግንኙነት ጽህፈት ቤትን ጠቅሶ ደቡብ ቲቪ ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሸገር ዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ደረሰ!

በሜድሮክ እህት ኩባንያ ‹‹ሆራይዘን ፕላንቴሽን›› እየተገነባ ያለው የሸገር ዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ ተጠናቆ ሥራ ሊጀምር የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደደረሰ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ:: በሆራይዘን ፕላንቴሽን የእቅድ ቢዝነስ ልማትና ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ ይበልጣል ሽመልስ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት ግንባታው ከተጀመረ ወራትን ያስቆጠረው የሸገር ዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል።የመሰረት ድንጋይ ከተጣለ ጀምሮ ሥራው በጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እየተመራ እንደነበር የተናገሩት ሥራ አስኪያጁ በቀን 18 ሰዓት በመስራት ግንባታውን ማፋጠን እንደተቻለና ጎን ለጎንም የማሽነሪዎችንና የሌሎች ግብዓቶችን ግዢ ተፈፅሞ ሀገር ውስጥ መግባታቸውን ገልጸዋል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
ከ20 አመታት በፊት ከኢትዮጵያ የወጣው ታሪካዊው የዘውድ ቅርስ ወደ አገር ተመለሰ።

ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት ከሀገር የወጡ በርካታ ቅርሶች እንዳሏት ይታወቃል፡፡ከነዚህ መካከል አንዱ የሆነው እና ከ20 አመታት በፊት ባልታወቀ ሁኔታ ከኢትዮጵያ የወጣዉና ከ400 ዓመታት በላይ እድሜ ያለው የኢትዮጵያ ታሪካዊ የዘውድ ቅርስ ነዉ፡፡የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀዉ፤ቅርሱ ተሰርቆ ለ20 አመታት ያህል በኔዘርላንድ እንደነበር የተነገረ ሲሆን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርና በሌሎችም ትብብር ቅርሱን ወደ አገር ቤት መመለስ እንደታቸለ አስታዉቋል፡፡

ለቅርሱ መመለስ እና መገኘት የትውልደ ኢትዮጵያውያን ትብብር ቅርሱ ሚና ከፍተኛ እንደነበር የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡በዛሬዉ እለት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ለብሔራዊ ሙዚየም የርክክብ ስነ ስርዓት መደረጉንም ሰምተናል፡፡ኢትዮጵያ በጣሊያን እና ከዚያም ቀደም በነበሩ ወራራዎች ወቅትዊና ታሪካዊ ቅርሶቿ በአዉሮፓዉያኑ እንደተበዘበዘች የዘርፉ ምሁራን ይናገራሉ፡፡በቅርቡም የአፄ ቴዎድሮስ ፀጉር ቁንድላ ከአገረ እንግሊዝ ወደ አገር መመለሱ አይዘነጋም፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ በብድር ጫና ከከፍተኛ ወደ መካከለኛ ስጋት ተሸጋግራለች ተብሏል!

ኢትዮጵያ ከውጭ አገራት የወሰደችው የብድር መጠን ከ27 ቢሊዮን ዶላር በላይ ቢሆንም፣ አገሪቱ ከብድር ጫና ከከፍተኛ ስጋት ወደ መካከለኛ ስጋት መሸጋገሯን የገንዘብ ሚኒስቴር ገለጸ።ይህም የተረጋገጠው የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም እና ዓለም ባንክ ጋር በጋራ ባከናወኑት የብድር ጫና ትንተና ላይ መሆኑን ያስታወሰው ሚኒስቴሩ ለዚህም እንደ ምክንያት ያነሳው የቻይና የንግድ አበዳሪዎች የዕዳ ክፍያ ጊዜ ሽግሽግ እንዲራዘም መደረጉን ነው።

ኢትዮጵያ በግማሽ ዓመቱ ከዓለም ባንክ እና ከሌሎች የገንዘብ ተቋማት 2ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ብድር ያገኘች ሲሆን በእርዳታ ደግሞ 13 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር አግኝታለች።ከቻይናና ከልማት አጋር መንግስታት ደግሞ 9ነጥብ3 ቢሊዮን ብር ብድር ስታገኝ 13 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር እርዳታ ማግኘቷን ሚኒስቴሩ አስታውቋል። በአጠቃላይ ኢትዮጵያ በ2012 ግማሽ ዓመት ውስጥ ከ39 ነጥብ ቢሊዮን ብር ብድርና እርዳታ ማግኘቷን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
የኢንጅነር ስመኘው በቀለ የመታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ!

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ የነበሩት የኢንጅነር ስመኘው በቀለ የመታሰቢያ ሐውልት በዛሬው ዕለት ተመረቀ፡፡በመታሰቢያ ሐውልቱ የምርቃት ሥነ-ስርዓት ላይ በኦርቶዶክስ እምነት ስርዓት መሰረት የፍትሃትና የፀሎት ሥነ - ስርዓት ተካሂዷል፡፡ከዚህ በተጨማሪም በሐውልቱ ምርቃት ሥነ-ስርዓት ላይ የተገኙ የተለያዩ ድርጅቶ፣ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፡፡ለምርቃት የበቃውን የኢንጅነር ስመኘውን የስርዓተ ቀብር ሐውልት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያሰራው መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል፡፡

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
Audio
⬆️⬆️

በደቡብ እና ምዕራብ ኦሮሚያ በነበረው የፀጥታ ችግር ወደ 1,200 በሚጠጉ ቀበሌዎች በህገ-ወጦች ተዋቅሮ የነበረ አስተዳደራዊ መዋቅር ፈርሶ ህጋዊ የመንግስት መዋቅር ተዘርግቷል ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ፡፡

⬆️ዝርዝሩን ከላይ ያለውን የድምፅ ፋይል ከፍተው ያዳምጡ!

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
የcopy እና paste ፈጣሪው የኮምፕዩተር ሳይንቲስት ላሪ ቴስለር በ74 ዓመቱ አረፈ።

@YeneTube @Fikerassefa
ወይዘሮ ፍሬአለም ሽባባው የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው እንዲያገለግሉ በጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ተሾሙ።

Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa