YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በሞጣ ጉዳት ለደረሰባቸው የእምነት ተቋማት 5.4 ሚሊዮን ብር ተሰበሰበ!

በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ ጉዳት የደረሰባቸውን የእምነት ተቋማት ለመገንባት በተደረገ የገንዘብ ማሰባሰብ አምስት ነጥብ አራት ሚሊዮን ብር በጥሬ ገንዘብ የተገኘ ሲሆን 725 ሺህ ብር ቃል ተገብቷል።ገንዘቡ የተገኘው ከባለሀብቶች፣ ከግለሰቦች፣ ከመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ ከተለያዩ ማህበራት እና ከእምነት ተቋማት ነው።የሞጣ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት የህዝብና ሚዲያ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መንግስቱ አለማየሁ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ አቶ ወርቁ አይተነው የተባሉት ባለሀብት ቃል የገቡትን አምስት ሚሊዮን ብር በተከፈተው የባንክ ሒሳብ አስገብተዋል።

የሞጣ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት 100 ሺህ ብር፣ የሁለት እጁነሴ ወረዳ አስተዳደር 500 ሺህ ብር፣ የማቻከል ወረዳ አስተዳደር 50 ሺህ ብር ቃል የገቡ ሲሆን ከአዋበል ወረዳ የተውጣጡ ዕድሮች 42 ሺህ 200 ብር በጥሬ ገንዘብ ገቢ አድርገዋል።በሌላ በኩል የአዋበል ወረዳ ቤተ ክህነት 10 ሺህ ብር ለመስጠት ቃል የገባ ሲሆን በሞጣ ከተማ ውስጥ የሚገኝ አንድ ወጣትም 65 ሺህ ብር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብቷል።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
መልካም ወጣት ለዎላይታ በረከት በሚል መሪ ርዕስ በዎላይታ ሶዶ ከተማ በሚካሄደው የመልካም ወጣት ማስተባበሪያ ማዕከል ግንባታ መሠረተ ድንጋይ የሚቀመጥበትን ልዩ ዝግጅት አስመልክቶ በከተማዋ የተለያዩ ፕሮግራሞች እየተከናዎኑ ይገኛሉ፡፡ የሩጫ፤ ችግኝ ተከላ እና ሌሎች በመልካም ወጣት የታጀቡ ትዕይንቶች ተከናውነዋል።

-የዎላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ህዝብ ግንኙነት ዩኒት
@YeneTube @FikerAssefa
ኢ/ር ታከለ ኡማ በመሃል አዲስ አበባ ጎተራ አከባቢ የሚገነባውን የአሚባራ መንደር ግንባታ በዛሬው ዕለት አስጀምረዋል፡፡

ይህ ዘመናዊ የመኖሪያ መንደር በአፋር ባለሃብቶችና በከተማ አስተዳደሩ በጋራ የሚገነባ ሲሆን የ35ሺ ካሬ ሜትር ነባር ይዞታቸው ላይ የከተማ አስተዳደሩ 15ሺ ካሬሜትር ይዞታ በመጨመር በድምሩ በ50 ሺ ካሬሜትር መሬት ላይ የሚገነባ ይሆናል፡፡ዘመናዊ የመኖሪያ መንደሩ በውስጡ ከ450 በላይ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን ጨምሮ የገበያ ማዕከላት፣ ሆቴል፣ ተመራጭ የመዝናኛና የንግድ ማዕከል ፣ ኣረንጓዴ ስፍራዎች እና የአፋር ባህል ማዕከልን ያካተተ ነው፡፡ግንባታው በ11 ቢሊዮን ብር የሚከናወን ሲሆን ከ10 ሺ በላይ ለሚሆኑ የከተማችን ወጣቶች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል የሚፈጥር ይሆናል።

ምንጭ: የከንቲባ ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ "የሀላባ ብሄረሰብ ዘመን መለወጫ ሴራ በዓል" በደማቅ ስነ-ስረዓት ተከበረ።

@YeneTube @FikerAssefa
ብልፅግና ፓርቲ ምርጫው በዚህ አመት እንዲካሄድ ጠንካራ አቋም አለው - አቶ ብናልፍ አንዷለም

የብልፅግና ፓርቲ የ2012 ብሄራዊ ምርጫ በያዝነው አመት እንዲካሄድ ጠንካራ አቋም መያዙን አስታውቋል። የፓርቲው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ትናንት በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ እና በሀገራዊ ምርጫው ዙሪያ ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን ማሳለፉንም ነው የፓርቲው ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ የጠቆሙት።ብልፅግና ፓርቲ በምርጫው ዙሪያ የአቋም ለውጥ አላደረገም ያሉት ሀላፊው፤ ፓርቲው ምርጫው በዚህ አመት መካሄድ አለበት የሚል እምነት እንዳለው አብራርተዋል።

ይህ ማለት ግን ፈታኝ ነገሮች የሉም ማለት አይደለም፤ ስራ አስፈፃሚው በስብሰባው የምርጫው ስጋቶች እና መልካም እድሎች ዙሪያ በስፋት መክሮ የመፍትሄ ውሳኔዎችን ማሳለፉን ነው አቶ ብናልፍ ያነሱት።ብልፅግና ፓርቲ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆነ ህብረተሰቡ ከምርጫው መካሄድ ጋር ተያይዞ የሚያነሷቸው ስጋቶችን እንደተወያየባቸው የጠቀሱት ሀላፊው፤ የምርጫው መካሄድ አልያም መራዘም የሚያስገኛቸው ጥቅሞች እና ጉዳቶች ላይ በስፋት መምከሩን ተናግረዋል። “ምርጫው ወቅቱን ጠብቆ የሀገሪቱን የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ እውን ለማድረግ ያግዛል፤ ህብረተሰቡ የመረጥኩት መንግስት ነው የሚያስተዳድረኝ የሚል እምነት እንዲኖረውም ያደርጋል” ነው ያሉት አቶ ብናልፍ በመግለጫቸው።

በብዙ መለኪያዎች ምርጫው ቢካሄድ የተሻለ መሆኑን በስራ አስፋፃሚው ስብሰባ ገምግመናል ያሉት ሃላፊው፤ በሀገሪቱ አሁን ላይ የሚታዩ ችግሮችን ግን በቀላሉ አናያቸውም ብለዋል። ብልፅግና ፓርቲ የቀደመ አቋሙን ያፀናው ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ከተወጣ ችግሮቹን መፍታት እንችላለን ከሚል መነሻ እንጂ ችግር የለም ከሚል አይደለም ሲሉም ተናግረዋል።የፀጥታ ችግሮቹን ለመፍታት የፀጥታ እና የፍትህ ተቋማት ሀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል፤ ህብረተሰቡም አጥፊዎችን በማጋለጥ የሰላም ቀናኢነቱን አሁንም አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ነው ያሉት ሀላፊው።

ተፎካካሪ ፓርቲዎችም አባላት እና ደጋፊዎቻቸውን ሰላምን ከሚያውኩ ተግባራት እንዲያርቁ የበኩላቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ ጠይቀዋል።ህዝቡ የሚወከልባቸው ፓርቲዎች ሀላፊነታቸውን ካልተወጡ ምርጫው ቢራዘምም ችግሩ የመቀጠል እድሉ ሰፊ መሆኑን ነው ያብራሩት።የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በትናንትናው ስብሰባው የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ሀገሪቱን ወደ ተሟላ መረጋጋት ለመመለስ በየደረጃው ያሉ የፀጥታ መዋቅሮች ፀጥታ የማስከበር ሀላፊነታቸውን በሚገባ እንዲወጡ አቅጣጫ አስቀምጧል።ስራ አስፈፃሚው በብልፅግና ፓርቲ የ10 አመት እቅድ ላይም ዝርዝር ውይይት አካሂዶ አፅድቆታል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ትምህርት ሚኒስቴር የሥርዓተ-ትምህርት ዝግጅትና ትግበራን ከሙከራ እስከ ትግበራ ድረስ ያሉትን ሂደቶች በተሳካ ሁኔታ ለመፈጸም እንዲቻልኝ ይህንን መርሃ-ግብር አዘጋጅቻለው ብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa
1443 ኢትዮጵያውያንን ከታንዛኒያ እስር ቤቶች በማስፈታት ወደ አገር ቤት ለመመለስ ዝግጅቱ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ በቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ውስጥ የማግጓጓዝ ስራው ይጀመራል ። ይህ በእንዲህ እንዳለ በታንዛኒያ መንግሥት በአስቸኳይ ከታንዛኒያ እንዲወጡ የታዘዙ 20 ዜጎቻችን ቅድሚያ በመስጠት ዛሬ ጠዋት ከዳሬሰላም ተነስተው አዲስ አበባ እንዲገቡ ተደርጓል ።

ምንጭ: በዳሬሰላም የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ በየቀኑ 65 ሰዎች በኤች አይ ቪ ቫይረስ እየተያዙ ነው ተባለ።

የፌደራል የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር ፅ/ቤት ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ ከጤና ሚንስትር የስራ ሀላፊዎች እና በህመሙ ዙሪያ ከሚሰሩ ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።በመድረኩ እንደተነገረውም በሀገሪቷ በቀን ቢያንስ 65 ሰዎች በኤች አይ ቪ ቫይረስ የሚያዙ ሲሆን 30 ያህል ወገኖች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ይሞታሉ።የፅህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፅጌረዳ ክፍሌ እንዳሉት በ2030 በኤች አይ ቪ ዙሪያ ለማሳካት እቅድ ከተያዙ ጉዳዮች መካከል ከእናት ወደ ልጅ ያለውን የስርጭት መጠን ዜሮ ማድረስ ዋነኛው ነው።

ከእናት ወደ ልጅ የሚስተዋለው የስርጭት መጠን መቀነስ ይቅርና እየጨመረ መሆኑን ተናግረው አሁን ላይ ያለው ከእናት ወደ ልጅ የቫይረሱ የስርጭት መጠን ከ60 በመቶ ወደ 71 በመቶ ማደጉን ተናግረውል።ዳይሬክተሯ የቫይረሱን የስርጭት መጠን በሴቶች ላይ 1ነጥብ 2 በመቶ በወንዶች ደግሞ 0ነጥብ 6 በመቶ መሆኑም ተናግረዋል። የቫይረሱ አጠቃላይ ስርጭት ደግሞ በከተሞች 2 ነጥብ 9 ሲሆን በገጠር 0 ነጥብ 5 በመቶ መሆኑንም ሃላፊዋ ተናግረዋል።በቀጣይ የስርጭት መጠኑ በስፋት የሚታይባቸው ቦታዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበትም ጠቁመዋል።

ምንጭ: ደቡብ ቲቪ
@YeneTube @FikerAssefa
የኤሊክትሮኒክስ አንድ መስኮት አገልግሎት ሥርዓት ዛሬ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ተመርቆ ወደስራ ገብቷል፡፡

ፕሮግራሙ ተመርቆ በይፋ ስራ በጀመረበት ወቅት ንግግር ያደረጉት የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፤ የኤሊስትሮኒስ አንድ መስኮት አገልግሎት ሥርዓት በዓለም አቀፍ ንግድ አገልግሎት ረገድ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ተግባራዊ እየተደረገ ያለ ፕሮጀክቶ ሲሆን በዘርፉ ተሳታፊ የሆኑ ተቋማትን የአሠራር ሂደቶች በማቃለልና በማቀናጀት በአንድ የኤሌከትሮኒክ ማዕቀፍ ለተገግልጋዮች የሚያቀርብ ሥርዓት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ትናንት ምሽት ወደ መቀለ ለመጓዝ ወደ ቦሌ ኤርፖርት ቢያመራም በመንግስት ጉዞ እንዳያደርግ መከልከሉንና ለሰዐታት መታሰሩን ተናግሯል።

Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
6ኛው የብዙሃን ስፖርት በአዲስ አበባ
ነገ ጠዋት መስቀል አደባባይ ይካሄዳል።

@YeneTube @FikerAssefa
"አዲሱ ኤክሳይዝ ታክስ ታስቦ የተዘጋጀ ነው ።አሮጌ መኪና ማከማቻ አይደለንም " ጠ/ሚ አብይ።

ዛሬ ከባለሀብቶች በቢሯቸው የተገናኙት ጠ/ሚ አብይ አህመድ አዲስ የተዘጋጀው ኤክሳይዝ ታክስ "የሀገራቷን ነባራዊ ችግር ያገናዘበ ነው ።አሮጌ መኪና እያስገባን በጭስ ምንበከልበት ፣ሲጃራ በገፍ እያስገባን ከመድሀኒት እኩል ለዶላር ወረፋ የምንጋፋበት ምክንያት የለም ብለዋል።ሀገሪቷ ኢኮኖሚ በጤናማ መልኩ ለማስኬድ አዲሱ የታክስ መመርያ እገዛ ያደርጋል" ብለዋል።

Via Tesfaye Getinet
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ በዚህ አመት ይካሔዳል ተብሎ በሚጠበቀው ምርጫ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትን ሥልጣን ለመያዝ እንዳቀደ ሊቀ-መንበሩ መረራ ጉዲና ተናገሩ።

ፓርቲው በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ አዲሱን ፅህፈት ቤቱን ሲያስመርቅ ባደረጉት ንግግር ፕሮፌሰር መረራ ከተሳካ ኦፌኮ ብቻውን አሊያም ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ሥልጣን በመጋራት የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የማቋቋም ዕቅድ እንዳለው ተናግረዋል። «ኦፌኮ ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እያዘጋጀን ያለንው ስትራቴጂ ቢያንስ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሥልጣንን መጋራት፤ ከተሳካልን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትን ማቋቋም ነው። ነገ እና ከነገ ወዲያ ሕዝባችንን ሲያስሩ እና ሲያሰቃዩ የነበሩትን በክብር ወደ ቦታቸው እንዲመለሱ ማድረግ ይኖርብናል።

ከሕዝባችን ጋር ወደ ጀመርንው ትግል መግባት እንፈልጋለን ለሚሉ ደግሞ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንደመሆናችን መጠን እና የብሔራችን አካል በመሆናቸው ጥሪ እናደርግላቸዋለን። ንስሀ ገብተው መመለስ ከፈለጉ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለን እንቀበላቸዋለን። ከሀዲዎች ለነበሩት እና ዛሬም ከሀዲነታቸውን መቀጠል ለሚፈልጉ ሕዝባችንን አሳልፈው ለመስጠት መሬታችንን ለመሸጥ፤ ለማዘረፍ እና ለመዝረፍ ለሚፈልጉ የኦሮሞ አምላክ ይፋረዳችሁ እንላለን» ብለዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
ቻይና የኢራንን ጦር አዛዥ የገደለችው አሜሪካ ኃይሏን ያለ አግባብ መጠቀም እንድታቆም አሳሰበች።

የቻይናው ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ዋንግ ይ ከኢራኑ አቻቸው ባደረጉት የስልክ ውይይት የአሜሪካ ጦር እርምጃ የዓለም አቀፍ ግንኙነት መሠረታዊ ባህልን የሚጣረስ፤ የመካከለኛው ምሥራቅን ውጥረት የሚያባብስ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በዕለተ አርብ ማለዳ አሜሪካ በሰው አልባ አውሮፕላን ከፈጸመችው ግድያ በኋላ በመካከለኛው ምሥራቅ የሰፈነው ውጥረት ያሳሰባቸው የጀርመን፤ የቻይናና እና የፈረንሳይ ውጭ ጉዳይ ምኒስትሮች ውይይት አድርገዋል።

ኢራን እንደዛተችው የበቀል እርምጃ እንደምትወስድ የሚያምኑ ተንታኞች እና ፖለቲከኞች የሁለቱ አገሮች ፍጥጫ ከመካከለኛው ምሥራቅ ተሻግሮ ዳፋው ለዓለም እንደሚተርፍ አስግቷቸዋል።

Via:- DW
@YeneTube @Fikerassefa
መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንላችሁ።
#ሀረር_ግንብ
እንደተለመደው መረጃዎችን እውነተኛነታችውን እንደተጠበቀ ሳይበርዱ በትኩሱ እናደርሳችዋለን።

ለጓደኛዎ t.me/yenetube ማጋበዝ አይዘንጉ!!
Don't forget to subscriber

https://youtu.be/W0tFAfbklt8
ባዕድ ነገር ከማር፣ ከቅቤ እና ከጠጅ ጋር ቀምመው ለበዓል ገበያ ሊያቀርቡ የነበሩ 72 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ መጪውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ ባዕድ ነገር ከቅቤና ከማር ጋር ቀምመው የሚሸጡ 72 ተጠርጣዎችን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቡድን ከኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ጋር ባካሄዱት የጋራ ኦፕሬሽን በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ሰአት ማር ባለ 50 ኪሎ ግራም 1196 ማዳበሪያ፣ ማር 80 ባልዲ ፣ ለጠጅ የተዘጋጀ 10 በርሜል ማር፣ አንድ ደርዘን ወይም አስር ፍሬ ነጭ ቀለም ያለው የማር መቀመሚያ፣ ግማሽ ማዳበሪ ጨው ፣ ጨው መሰል የውሃ ማጣሪያ ባዕድ ነገር፣ 45 ኪሎ ግራም ስኳር፣እንዲሁም ቅቤ 228 መዳበሪያ ባለ 50 ኪሎ ግራም ፣ አራት ካርቶን ቅቤ ፣ 14 ባልዲ/ አንዱ ባልዲ 24 ኪሎ ግራም የሚይዝ/ 96 ባልዲ ቪክተቢል (የቅቤ መቀመሚያ)፣ 35 ባልዲ ቦቼ የሚረጋ ዘይት እንደተያዘባቸው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በማህበራዊ ሚዲያው ገልጾአል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት በሰበታ ፣ ፉሪ ፣ መርካቶ ይርጋ ኃይሌ አካባቢ፣ አውቶቡስ ተራ ፣ ዳንኤል ሆቴል አካባቢ፣ እህል በረንዳ ፣ ወለጋ ሆቴል አካባቢ፣ አሰፋ ፍለታ ሆቴል አካባቢ፣ ጎጃም በረንዳ አካባቢ፣ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አዲሱ ሚካኤል አካባቢ፣ ጉለሌ ደቻስ ገነሜ ትምህርት ቤት አካባቢ፣ ሲሆን በወንጀል የተጠረጠሩት 72 ግለሶች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል። ያለው ፖሊስ ህብረተሰቡ ለበዓል የሚያስፈልጉትን መጠቀሚያዎች በሚሸምትበት ወቅት ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል፡፡

Via:- ethio FM
@Yenetube @Fikerassefa
የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ኤጀንሲ መዋቅሩ ለስራው ማነቆ እንደሆነበት አስታወቀ፡፡ መዋቅሩ እንዲሻሻል ጥያቄ ቢያቀርብም መፍትሄ እንዳላገኘ ጠቅሷል፡፡

በኤጀንሲው የዕውቅና አሰጣጥ ዳይሬክተር አቶ አብይ ደባይ እንደገለፁት፤ የኤጀንሲው መዋቅር ለስራቸው ማነቆ በመሆኑ ይህንኑ ለማስተካከል ባለፉት አራት ዓመታት አጥንተን ማስተካከያ ለማድረግ ለሚመለከታቸው አካላት ተደጋጋሚ ጥያቄ ብናቀርብም መፍትሄ አልተሰጠንም ብለዋል።

በአገሪቱ ላለው የትምህርት ጥራት ችግር በህዝብና በመንግስት መግባባት ተደርሶበታል ያሉት አቶ አብይ፤ ከችግሩ ምክንያቶች መካከል ባለፉት ዓመታት በትምህርት አግባብነትና ጥራት ላይ በሚፈለገው ደረጃ ቁጥጥርና ክትትል አለመደረጉ አንዱ ነው ብለዋል።

Via:- EPA
@YeneTube @Fikerassefa
የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጎ #አቅጣጫ ማስቀመጡን የፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ስራ አስፈፃሚው በሃይማኖትና በትምህርት ተቋማት ጥቃት ዙሪያ እንዲሁም በዘንድሮው ምርጫ ላይ መክሮ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

የፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ወቅታዊ በሆኑ ጉዳዮች ውይይት ማድረጉን ተከትሎ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት፤ በአገሪቱ የሰላም እና የፀጥታ እንዲሁም በወቅታዊ ጉዳዮች ጥልቅ ውይይት ተደርጓል።

በሃይማኖትና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ በቡድንና በተናጠል በተደራጀ መልኩ ጥቃት የማድረሱ ዘመቻ እየተባባሰ መጥቷል። ይህ እኩይ ተግባር የኅብረተሰቡን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ችግር ውስጥ እንደሚከት ስራ አስፈፃሚው ገምግሟል።

Via:- EPA
@YeneTube @Fikerassefa