በሰሜን ሸዋ ዞን ተፈጥረው በነበሩ ግጭቶች 22 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ነው።
የሰው ሕይወትን የነጠቁ ግጭቶች ባጋጠሙባቸው ወረዳዎች እርቅ መፈፀሙና ጥብቅ የፀጥታ ቁጥጥር ማድረግ መጀመሩ አሁን ላይ አንፃራዊ ሰላም እንዲኖር ማድረጉንም የዞኑ አስተዳደር ለአሐዱ ቴሌቪዥን ገልጿል። ዞኑ ከኦሮሚያ እና አፋር ክልሎች እንዲሁም በዚያው በአማራ ክልል ውስጥ ከሚገኘው የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጋር የሚዋሰን ነው፡፡ ይህን ተከትሎ የሚነሱ የአስተዳዳር ወሰን ጥያቄዎች፣ የአርብቶ አደሮች ልቅ ግጦሽ እንዲሁም ግጭቶቹ ተከስተው በነበሩበት የ2011 መገባደጃና 2012 መጀመሪያ ወራት በአካባቢው ሲንቀሳቀስ የነበረ ሕገ ወጥ የታጠቀ ቡድን ተጠያቂ ናቸው ሲል አስተዳደሩ ይከሳል፡፡
እንደ አጣዬና አካባቢው፣ ምንጃር ሸንኮራ እና በረከት ባሉት ወረዳዎች በተከሰቱት ግጭቶች የሰው ሕይወት መጥፋቱን ያስታወሱት የዞኑ አስተዳደርና ፀጥታ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ካሳሁን እምቢአለ፤ በአካባቢዎቹ የግጭት ምንጮች መለየታቸውንና ዳግም እንዳይከሰቱ እየተሰራ መሆኑን አክለዋል፡፡ኃላፊው አጋጥመው የነበሩ የፀጥታ ችግሮች እንደ አዲስ እየተነቃቃ ባለው የዞኑ የመዋዕለ ነዋይ ፍሰት ላይ ጫና አለማሳደሩን ይናገራሉ፡፡ሆኖም በመርሐቤቴ ወረዳ የመንገድ ሥራ ላይ በተነሱ የሥራ እድል ፈጠራ ፍትሐዊነት፣ የአነስተኛ ደመወዝና ሌሎች የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የተከሰተው ግጭት ሁለት የመንገድ ሥራ ፕሮጀክቶችን አቋርጦ ይገኛል፡፡
ምንጭ: አሐዱ ቴሌቪዥን
@YeneTube @FikerAssefa

Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council የሞጣውን የሽብር ጥቃት አስመልክቶ የተዋቀረው አጣሪ ኮሚቴ ነገ መግለጫ እሰጣለው ብሏል::
@YeneTube @Fikerassefa
@YeneTube @Fikerassefa
ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ታሕሳስ 25 እና 26 መስራች ጉባኤ እንደሚያካሂድ ይፋ ኣድርጓል።
ፓርቲው ዛሬ ለሚዲያዎች በሰጠው ይፋዊ መግለጫ እንዳስታወቀው በሚቀጥሉት ቅዳሜና እሁድ ፖለቲካዊ ፕሮግራሙን በጉባኤተኞች ያስጸድቃል፣ አመራሮቹን ይመርጣል።
ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) ብሄራዊ ድርጅት ሆኖ በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ የሚንቀሳቀስ ነው። የትግራይ ህዝብ እያጋጠሙት ያሉት ሁለንተናዊ ችግሮች ጠንካራ ተቋማዊ አሰራር የሚከተልና ሕግና ስርዓት የሚያከብር ብሄራዊ መንግስት ባለመገንባቱ ነው ሲል ፓርቲው ገልፅዋል። ትግራይ ላይ መሰረት ያደረገ ብሄራዊ ፓርቲና የፖለቲካ ፕሮግራም ባለመኖሩ ህዝቡ ራሱን የሚከላከልበትና የሚለማበት ተቋሞችና ስርዓት መገንባት እንዳልቻለ የገለጸው ፓርቲው፣ ይህ ፖለቲካዊ ችግር ለመፍታት እንደተቋቋመ አብስሯል።
ትግራይ ውስጥ አዲስ የፖለቲካ የትግል ባህል እና ነባራዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበ ፕሮግራምና ፖሊሲ እናስተዋውቃለን ያለው ፓርቲው የአክሱም ስልጣኔ፣ ከዛ በኋላ የተካሄዱ በጎ የሆኑ ማሕበረሰባዊ እንቅስቃሴዎችና ህዝባዊ ትግሎች እንደ መሰረት ተቀብሎ፣ አዲስ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ትግል እንደሚያካሂድ አስታውቋል።
በተጨማሪም የትግራይ ብሄራዊ ጥቅሞች ብሎ ለለያቸው እንደሚታገል ይፋ ኣድርጓል። በጉባኤው የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማሕበራት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ሚዲያዎች ተወካዮች እንደሚገኙም ኣብራርቷል።
Via:- አውሎ ሚዲያ

የአምራች አድራሻቸው የማይታወቁና ተጭበርብረው የተሰሩ 27 የምግብ ዓይነቶች ገበያ ላይ እየዋሉ መሆኑን የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
ባለስልጣን መ/ቤቱ ባካሄደው የገበያ ቅኝት መሰረት የታሸጉ ምግቦች የተሟላ የገላጭ ጽሁፍ የሌላቸው፣ አስገዳጅ ብሔራዊ ደረጃን ያላሟሉ፣ የአምራች ድርጅቶቻቸው የማይታወቅና ህጋዊ ፈቃድ የሌላቸው፤ የአምራች አድራሻ እና መለያ ቁጥር የሌላቸው፣ የመጠቀሚያና የተመረቱበት ጊዜ በትክክል ያልታተሙ የተለያዩ ምርቶች በገበያ ላይ በተደረገው ቁጥጥር መገኘቱን ባለስልጣኑ አስታውቋል ፡፡የአምራች አድራሻቸው የማይታወቁና ተጭበርብረው ገበያ ላይ ከሚገኙ የምግብ አይነቶች ውስጥ፡-
📌የምግብ ዘይት ዝርዝር
ንጹህ የኑግ ዘይት፣
ኢዛና ዘይት፣
ጣና ዘይት፣
ኦሊያድ ዘይት፣
ስኬት የተጣራ ዘይት፣
በቅሳ የምግብ ዘይት፣
አሚን የምግብ ዘይት፣
ቀመር የምግብ ዘይት፣
ሎዛ የምግብ ዘይት፣
ዘመን የኑግ እና የለዉዝ ዘይት፣
ዘቢብ ቃህ የምግብ ዘይት፣
📌የለውዝ ቂቤ ዝርዝር
ማኢዳ የለዉዝ ቅቤ፣
ሮዛ ክሬሚ ለዉዝ ቅቤ፣
📌ቪምቶ ዝርዝር
ዳና ቪንቶ
ቪንቶ
📌የምግብ ጨው ዝርዝር
አዋሽ የገበታ ጨዉ፣
ሳራ እና ኑስራ ጨዉ፣
ሴፍ የገበታ ጨዉ (በተለያየ እሽግ)፣
ሽናጉ የገበታ ጨዉ፣
ወዛቴ አዮዳይዝድ ጨዉ፣
ቃና የገበታ ጨዉ፣
አስሊ የገበታ ጨዉ፣
📌የማር ዝርዝር
ሲሳይ ንጹህ ማር እና ቅቤ አቅራቢ፣
ወለላ ማር፣
📌የከረሜላ ዝርዝር
ካርቶንስ ካንዲ ፍሩትስ፣
ሊዛ ሎሊፖፕ፣
ክሬሚ ሎሊፖፕ ይገኙበታል ተብሏል፡፡
ተመሳሳይ ምርቶች በሌሎች አካባቢ፤ የመገበያያ ስፍራዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ ህብረተሰቡ በአቅራቢያው ለሚገኝ የጤና ተቆጣጣሪ፣ ለፖሊስ አካላት ወይም በፌደራል ደረጃ በነጻ ስልክ መስመር በ8482 በመጠቆም እንዲያሳውቅ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡
Via Addis TV

ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም የተባሉ 5 የከተማይቱ የፀጥታ አስከባሪ ኃላፊዎች መታሰራቸዉን የምሥራቅ ጎጃም ፖሊስ ዐስታወቀ።
ባለፈዉ ታኅሣሥ 10 ሞጣ ምሥራቅ ጎጃም ዉስጥ፣ መሳጂዶችን፣ የንግድ ተቋማት ሲቃጠሉና ቤተክርስቲያን ላይ ቃጠሎ ሲሞከር ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም የተባሉ 5 የከተማይቱ የፀጥታ አስከባሪ ኃላፊዎች መታሰራቸዉን የምሥራቅ ጎጃም ፖሊስ ዐስታወቀ። የተቃጠሉትን መሳጂዶችና የንግድ ድርጅቶች መልሶ ለመገንባት የተለያዩ ወገኖች የገንዘብ ድጋፍ እየሰጡ ነዉ። መሳጂዶቹንና የንግድ ድርጅቶቹን አቃጥለዋል ተብለዉ የተጠረጠሩ 33 ሰዎች መያዛቸዉን ፖሊስ ከዚሕ ቀደም ዐስታዉቆ ነበር። የመሳጂዶቹና የንግድ ተቋማቱ መቃጠል የአማራ መስተዳድር ቃጠሎዉን አለመከላከሉና ወንጀለኞቹን ፈጥኖ አለመያዙ ያስቆጣቸዉ የኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ድርጊቱን ማዉገዛቸዉን እንደቀጠሉ ነዉ።
Via DW

ኢትዮጵያ በፖርት ሱዳን ለሎጅስቲክ አገልግሎት የተሰጣትን መሬት በቅርቡ መጠቀም ትጀምራለች፡፡ ሱዳን መሬቱን የሰጠችው በ1990ዎቹ አጋማሽ ነበር፡፡ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅትም በፖርት ሱዳን ማስተባበሪያ ቢሮ ይኖረዋል፡፡ ለወደቡ አጠቃቀም የጋራ ኮሚቴ እንደሚቋቋም የመንግሥት ዜና አውታሮች ዘግበዋል፡፡ ይህ የተወሰነው ትራንስፖርት ሚንስትር ዳግማዊት ሞገስ በፖርት ሱዳን ባደረጉት ጉብኝት ነው፡፡
Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮ ቴሌኮም የኤክሳይስ ታክሱ በድጋሚ እንዲታይለት ጠየቀ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኤክሳይስ ታክሱ ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ ዛሬ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በአዲስ አበባ ተወያይቷል።በውይይቱ ላይ ከተሳተፉ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም የቴሌኮምኒኬሽን አገልግሎቶች ላይ 5 በመቶ የኤክሳይስ ታክስ መጣሉ ተገቢ ስላልሆነ በድጋሜ ይታይልኝ ብሏል፡፡የኢንተርኔት ፣ የድምፅ እና የፅሑፍ መልክት ላይ በኤክሳይስ ታክስ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የቴሌኮምኒኬሽን አገልግሎቶች ላይ 5 በመቶ የኤክሳይስ ታክስ መጣሉ በድጋሜ ቢታይ ጥሩ ነው ብሏል፡፡
Via Ethio FM

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በመደበኛ ፖሊስነት እና የአድማ መከላከል ፖሊስ ተቀጥሮ ለማገልገል ፍቃደኛ የሆኑ ወጣቶችን በትምህርትና ስልጠና መመልመያ መስፈርቱ መሰረት በመመልመል ቀጥሮ በማሰልጠን ወደ ስራ ማሰማራት ይፈልጋል፡፡
ተጨማሪ መረጃ ይመልከቱ ⬇️
https://telegra.ph/Yenetube-01-01
ተጨማሪ መረጃ ይመልከቱ ⬇️
https://telegra.ph/Yenetube-01-01
🇪🇹አፄ ዮሐንስ ሙዚየም መቐለ ኢትዮጵያ🇪🇹
-ከሚያለያየን ይልቅ የሚያስተሳስረን ይበልጣል 💚💛❤️
-ከሚያጣላን ይልቅ የሚያፋቅረን በእጅጉ ይበልጣል 💚💛❤️
--ብሩህ ቀን ይሁንላችሁ --
የናንተው ቻናል t.me/YeneTube
-ከሚያለያየን ይልቅ የሚያስተሳስረን ይበልጣል 💚💛❤️
-ከሚያጣላን ይልቅ የሚያፋቅረን በእጅጉ ይበልጣል 💚💛❤️
--ብሩህ ቀን ይሁንላችሁ --
የናንተው ቻናል t.me/YeneTube
የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት እና የጅቡቲ አብያተ ክርስቲያናት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ዐረፉ
ትላንት ማምሻውን በመንበረ ፓትርያሪኩ በሚገኘው መኖሪያቸው ያረፉት ብፁዕነታቸው፣ ከልብ ሕመም ጋራ በተያያዘ በሀገር ውስጥ እና በአሜሪካ የሕክምና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይቷል።
ከሳምንት በፊት በአሜሪካ በነበሩበት ወቅት የልብ ቀዶ ሕክምና እንዲደረግላቸው ቢጠየቁም፣ "አልፈልግም፤ አገሬ ገብቼ ልሙት፤" ብለው እንደተመለሱ ታውቋል።
የቀብራቸው ሥነ ሥርዐት ነገ ዓርብ፣ ታኅሣሥ 24 ቀን 2012ዓ.ም. በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚከናወን ተጠቁሟል።
በፊት ስማቸው አባ ፍቅረ ማርያም ይባሉ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ዳንኤል፣ በሐምሌ ወር 1997 ዓ.ም. በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አንብሮተ እድ ኤጲስ ቆጶስነት ከተሾሙት 17 አባቶች አንዱ ነበሩ።
ምንጭ:- ሐራ ተዋህዶ
@Yenetube @Fikerassefa

ጅቡቲ ለምታካሔደው የፀረ ወባ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ አውሮፕላኖችን መላኳ ተገለፀ
ኢትዮጵያ በጅቡቲ መንግሥት እየተካሔደ ያለውን የፀረ ወባ እንቅስቃሴ በመደገፍ የፀረ ወባ ርጭት የሚያካሒዱ አነስተኛ አውሮፕላችን ወደ ጅቡቲ መላኳ ተገለፀ።
ኢትዮጵያ እንቅስቃሴውን በመደገፍ የዘመን የበረራ አገልግሎት ንብረት የሆኑትን ቀላል አውሮፕላኖች የላከች ሲሆን አውሮፕላኖቹም ከሰኞ ታህሳስ 20/2012 ጀምሮ የኬሚካል ርጭት ስራውን መጀመራቸውም ታውቋል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞም በጅቡቲ የኢትዮጵ አምባሳደር አብዱላዚዝ መሐመድ በፀረ ወባ እንቅስቃሴው ኢትዮጵያ ለጅቡቲ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታውቀዋል
Via:- አዲስ ማለዳ

በአዲስ አበባ ከተማ በብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራምና ህገ ደንብ ዙሪያ የግንዛቤ ሲካሄዱ የነበሩ ማስጨበጫ መድረኮች ማጠቃለያ እየተካሄደ ነው።ከተማ አስተዳደሩ "በህብር ወደ ብልጽግና" በሚል መሪ ቃል በየደረጃው ሲደረግ የነበረው የውይይትና የምክክር መድረክ ማጠቃለያ መርሃ ግብር በሚሊኒየም አዳራሽ በመካሄድ ላይ ይገኛል።በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ ላይም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጠምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም ከ10 ሺህ በላይ የከተማዋ ወጣቶች ታድመዋል።
ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አጽድቋል።
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።በዚህም በህግ፣ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የቀረበ ረቂቅ አዋጅን ጨምሮ ሌሎች አጀንዳዎችን ተመልክቷል።አቶ አበበ ጎዴቦ የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የቀረበው ረቂቅ አዋጅን አስመልክተው ባቀረቡት ሪፖርት፥ የሽብር ድርጊት በሰው ህይወት፣ አካል እና ስነ ልቦና እንዲሁም ንብረትና ማህበራዊ መስተጋብር ላይ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽእኖ አብራርተዋል።ቋሚ ኮሚቴው በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ ከጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ከመጡ የስራ ሃላፊዎች፣ክሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ከተውጣጡ የፍትሃ አካላት፣ ከህዝብ እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ዝርዝር ውይይት ማድረጉንም አንስተዋል።
በዚህም ረቂቅ አዋጁን አስመልክቶ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ መሰጠቱን እና ለረቂቅ አዋጁ ግብዓት የሚሆኑ ሃሳቦች መገኘታቸውን አውስተዋል።ስለሆነም በአሁኑ ወቅት በሀገራችን እየተስተዋለ ያለውን ችግር ለማስወገድ እና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ረቂቅ አዋጁ ቢጸድቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክት መሆኑን አብራርተዋል።የምክር ቤቱ አባላትም የቀረበው ሪፖርት በተመለከተ መስተካከል ይገባቸዋል ያሏቸውን ሃሳቦች አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። በመጨረሻም ምክር ቤቱ የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1176/2012 በአንድ ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ አጽድቋል።
Via FBC

ለመንግስት ሥራ ከአሶሳ ወደ ነቀምት በመጓዝ ላይ የነበሩት የክልሉ ምክር ቤት የኢኮኖሚ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አብዱላሂ ሶጃር በታጠቁ ኃይሎች ተገደሉ!
ለመንግስት ሥራ ጉዳይ ከአሶሳ ወደ ነቀምት በመጓዝ ላይ የነበሩት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት የኢኮኖሚ ዘርፍ ሰብሳቢ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አብዱላሂ ሶጃር በታጠቁ ኃይሎች ተገደሉ፡፡የክልሉ ምክር ቤት የኢኮኖሚ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የነበሩት አቶ አብዱላሂ ሶጃር ዛሬ ጠዋት ከአሶሳ ወደ ነቀምት በመጓዝ ላይ እያሉ የዳቡስ ወንዝን ተሻግሮ በኦሮሚያ ክልል ቤንጓ አካባቢ በታጣቂዎች መገደላቸውን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሠ በየነ ተናግረዋል፡፡በዚህም የክልሉ መንግስት የተሠማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሠቦች፣ ዘመድ ወዳጆች እና መላው የክልሉ ህዝብ መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
የጽ/ቤት ኃላፊው ጉዳዩን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በሠጡት መግለጫ ዛሬ ከጠዋቱ 1፡30 ላይ ወደ ነቀምት በመጓዝ ላይ የነበሩት አቶ አብዱላሂ ሶጃር በሸኔ ታጣቂዎች በአሠቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ገልጸዋል፡፡በጥቃቱም በመኪናው ውሰጥ የነበሩ 1 ወንድ እና 1 ሴት ላይ ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና እርዳታ ላይ እንደሚገኙም አቶ መለሠ ጠቅሰዋል፡፡ከክልሉ ተነስቶ አሮሚያ ክልልን የሚያቋርጠው መንገድ ባለፉት ዓመታት ከፍተኛ ስጋት የነበረበት በመሆኑን ያታውሱት ኃላፊው፣ የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጦ መቆየቱን ነው የገለጹት፡፡
በአሁኑ ወቅት ሁለቱ ክልሎች እያከናወኗቸው ባሉ የጋራ የሠላምና የልማት ሥራዎች አንጻራዊ ሠላም ተፈጥሮ እንደነበርም አቶ መለሠ ገልጸዋል፡፡ክልሎቹ እና ህዝቦቹ ሠላምን ለመስጠበቅ በጋራ እየሠሩ ቢሆንም፣ ታጣቂ ቡድኑ ጫካ ውስጥ መሽጎ በተለይም አመራር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በማድረስ ላይ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡በቅርቡ 1 የፖሊስ አመራር በታጣቂዎች መገደላቸውን ያስታወሱት ኃላፊው፣ የሁለቱን ተጎራባች ክልሎች ሠላም ለማጠናከር የበለጠ እየተሠራ በሚገኙበት በዚህ ወቅት፣ ይህ ጥቃት መፈጸሙ እጅግ የሚያሳዝን ስለመሆኑም ጠቅሰዋል፡፡
"ክስተቱ የሁለቱን ክልል ህዝቦች አይወክልም" ያሉት አቶ መለሠ፣ "የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የኦሮሚያ ክልሎች የጀመሩት የጋራ የሠላምና የልማት ሥራ አጠናክረው ይቀጥላሉ"
ብለዋል፡፡ሁለቱ ክልሎች ጸረ-ሠላም ኃይሎችን አሁንም በጋራ መታገል እንደሚገባቸው በመጠቆም፣ የፌዴራል መንግስትም ችግሩን ለመፍታት የተለዬ ትኩረት ሠጥቶ ሊሠራ እንደሚገባም አመልክተዋል፡፡የሁለቱ ክልል ህዝቦችም እነዚህን ጸረ-ሠላም ኃይሎች ከህዝብ ለመነጠል በሚደረገው ጥረት ውስጥ ከመንግስት ጎን በመሆን የደርሻውን መወጣቱን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
Via Benishangul Communication Office

በጠገዴ ወረዳ ታግተው ከነበሩ ታዳጊዎች የ7ኛው ህይወት አልፏል። በአጋቾቹ በጥይት ተመቶ ቆስሎ የነበረው ታዳጊ በጎንደር ሬፈራል ሆስፒታል የህክምና እርዳታ ቢደረግለትም መትረፍ አልቻለም።ታህሳስ 9 ቀን ከጠገዴ ወረዳ ከብት በመጠበቅ ላይ በነበሩበት ወቅት በታጣቂዎች ከታገቱ 8 ታዳጊዎች መካከል 6ቹ በአጋቾቻቸው መገደላቸው ይታወሳል። ታዳጊዎቹ የተገደሉት አጋቾች በአንድ ሰው የጠየቁትን 100ሺህ ብር ወላጆች መክፈል ባለመቻላቸው ነው።
Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
የጋዜጠኛ ፍቃዱ ማኅተመወርቅ ሰባት አመት ፍርድ ፀንቷል።
የግዮን መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማኅተመወርቅ ዛሬ ታኅሳስ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ ወንጀል የቀረበ ሲሆን ከዚህ ቀደም የተፈረደበት የሰባት አመት ፍርድ ይግባኝ ቢልም እንዲፀና ተደርጓል።
ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማኅተመወርቅ፣ በዓለማየሁ የሕትመትና ማስታወቂያ ሥራ ድርጅት ሥር ትታተም በነበረው ዕንቁ መጽሔት በገቢዎች ባለስልጣን ከታክስ ጋር በተያያዘ ወንጀል መከሰሱ ይታወሳል።
Via:- Tsefay Getnet

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በኢህአዴግ ውኅደት ዙርያ የመጨረሻ ውሳኔው ያሳውቅበታል ተብሎ የሚጠበቀው የፓርቲው አስቸኳይ ጉባኤ በመጪው ቅዳሜና እሁድ እንደሚያደርግ ገለፀ።
ዛሬ በህወሓት ፖለቲካዊ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለም ገብረዋህድ ተፈርሞ ለመገናኛ ብዙኃን የተሰራጨው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው የህወሓት አስቸኳይ ጉባኤ በመጪው ታሕሳስ 25 እና 26 ቀን፣ 2012 ዓ.ም. በመቐለ እንደሚካሔድ ይፋ አድርጓል። የህወሓት ሊቀ መንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በቅርቡ ሰጥተውት በነበረ ጋዜጣዊ መግለጫ በህወሓት በኩል «የውኅደት አጀንዳው» የመጨረሻ ውሳኔ የሚያገኘው በድርጅቱ አስቸኳይ ጉባኤ መሆኑ ጠቅሰው ነበር።
ህወሓት መጪው ቅዳሜና እሁድ በሚያደርገው አስቸኳይ ጉባኤ በውኅደቱ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ከማስተላለፍ በተጨማሪ ቀጣይ የፓርቲው ጉዞ የሚያመላክት ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ የመቐለው ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለሥላሴ ዘግቧል።
ከህወሓት ውጪ ሁሉም የኢህአዴግ አባልና አጋር ተብለው ይታወቁ የነበሩ ድርጅቶች ራሳቸው አክስመው «ብልፅግና ፓርቲ» የተባለ ውሁድ የፖለቲካ ድርጅት መመስረታቸው ይታወቃል። የህወሓት ስራ አስፈፃሚ እና ማዕከላዊ ኮሚቴዎች የኢህአዴግ ውኅደት ሲቃወሙ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡
Via:- Dw

የተሽከርካሪ አስመጪዎች በኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ ላይ አቤቱታ አሰሙ!
ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውሳኔ የቀረበው የኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጅ የሕዝቡን የመግዛት አቅም ያላገናዘበና የመንግሥትን ገቢም የሚጎዳ መሆኑን፣ የኢትዮ ተሽከርካሪዎች አስመጪ ባለቤቶች ማኅበር አስታወቀ፡፡ ረቂቅ አዋጁ የአገሪቱን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚና የሰላም ሁኔታን ያላገናዘበ በመሆኑ መቅረት አለበት የሚል አቋም ይዟል፡፡በኢትዮጵያ አስመጪዎች እንዲከፍሉ የሚጠየቀው የተሽከርካሪ ቀረጥ ከፍተኛ ሆኖ ሳለ በአንድ መኪና ላይ እስከ 500 በመቶ ድረስ ኤክሳይዝ ታክስ እንዲከፈል የሚጠይቀው ረቅቅ አዋጅ፣ የተጋነነ እንደሆነ ለሪፖርተር የገለጹት የማኅበሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መሐመድ አመዴ ናቸው፡፡
‹‹ኤክሳይዝ ታክሱ የአንድን መኪና ዋጋ በአንዴ በብዙ እጥፍ የሚያንርና አስመጪዎችንም ሆነ የደንበኞችን አቅም ያላገናዘበ ስለሆነ፣ አስመጪዎች ማስመጣት እንዲያቆሙና መንግሥት ከጉምሩክ የሚያገኘው ገቢም በእጅጉ እንዲቀንስ የሚደርግ ነው፤›› ብለዋል፡፡ባገለገሉ መኪኖች ላይ ይታሰብ የነበረው 33 በመቶ የእርጅና ቅናሽ መነሳቱ ዓለም አቀፍ አሠራርን የሳተ ‹‹ትልቅ ወንጀል›› ሆኖ ሳለ፣ ባገለገሉ ተሽከርካሪዎች ላይ እስከ 500 በመቶ ታክስ የሚጥለው ረቂቅ ሲዘጋጅ እንደ ባለድርሻ አካል ለውይይት ባለመጋበዛቸው አስቆጥቶናል የሚል መልዕክትም አስተላልፈዋል፡፡በረቂቁ የተዘጋጀው ኤክሳይዝ ታክስ በየትኞቹ ተሽከርካሪዎች ላይ ተፈጻሚ ሊሆን ይገባል የሚለው በጥንቃቄ መታየት እንደሚገባው፣ አዲሱ ታክስ የነዳጅ ፍጆታና ጥራትን፣ እንዲሁም ተሽከርካሪዎቹ በሚሰጧቸው ጥቅሞች ታይቶ ሊጣል ይገባል ሲሉ አቶ አህመድ ተናግረዋል፡፡
ትልልቅ የነዳጅ ፍጆታ ያላቸው ተሽከርካሪዎች ከአየር ብክለት አኳያ፣ በነዳጅ ወጪም ረገድ ተለይተው ኤክሳይዝ ታክሱ ሊጣልባቸው እንደሚገባ፣ በሊትር እስከ 20 ኪሎ ሜትር በሚነዱት ላይ የተለየ አተያይ እንዲኖር ጠይቀዋል፡፡ቀደም ሲል ኤክሳይዝ ታክስ የማይመለከታቸው የሕዝብ ማመላለሻ ሚኒባሶች፣ ዶልፊኖች፣ አባዱላዎች፣ ኮስተሮች፣ አይሱዙዎች፣ ፒክ አፖችና አውቶቢሶች በአዲሱ የኤክሳይዝ ታክስ መረብ ውስጥ እንዳይገቡም ጠይቀዋል፡፡እነዚህ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ከኤክሳይዝ ታክስ ነፃ ከመሆን ባሻገር ወደ አገር ውስጥ ሲገቡ ይከፈልባቸው የነበረው ቀረጥም ከአሥር እስከ 30 በመቶ ነበር ብለዋል፡፡ ይህ ቀርቶ በረቂቁ ውስጥ የሚካተቱ ከሆነ ግን የትራንስፖርት ዋጋ በከፍተኛ መጠን እንዲጨምር ያደርጋል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ተሽከርካሪዎች ጥንካሬ፣ የነዳጅ ፍጆታ፣ ከጋራዥ ባለሙያዎች ጋር ያላቸው ቁርኝት ታይቶ ‹‹የብራንድ መረጣ›› እንዲደረግም ሐሳብ አቅርበዋል።ረቂቁ አዋጁ የግድ ተግባራዊ መሆን ካለበትም ከመረቀቁ በፊት አገር ውስጥ በመግባት ሒደት ላይ የሚገኙ ተሽከርካሪዎች በነበረው የታክስ ሥርዓት እንዲታዩ ጠይቀዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ምን ያህል ተሽከርካሪዎች አገር ውስጥ በመግባት ሒደት ላይ እንደሚገኙ በውል ባይታወቅም 4,500 ያህል አስመጪዎች እንዳሉ፣ እያንዳንዳቸው በአንድ ጊዜ ከአሥር እስከ 120 መኪኖችን እንደሚያስገቡ፣ አንድ መኪና ግዥው ተጠናቆ አገር ውስጥ እስኪገባም ከሦስት እስከ አምስት ወራት እንደሚፈጅ በመግለጽ፣ የኤክሳይዝ ታክሱ ተፈጻሚነት ይህንን እንዲያገናዝብ ጠይቀዋል፡፡
Via Reporter

Forwarded from YeneTube
💥ማስታወቂያ💥
School of American English
📌ቻይንኛ
📌ፈረንሳይኛ
📌ጀርመንኛ
📌ጣልያንኛ
📌አፋን ኦሮሞ
📌አረብኛ
አንቱታን ባተፈሩ መምህራን እናስተምራለን
አድራሻዎቻችን ⬇️
ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ +251919913021
ፒያሳ ፒያሳ ገበያ ማዕከል +251919913023
22 ጎላጎል ህንፃ 6ተኛ ፎቅ +251919913022
💥💥💥10% Discount 💥💥💥💥
ቅናሹን ለመጠቀም
ይህንን ፓስት screenshot አድርገው መያዝና ስመጡ ማሣየት ይኖርብዎታል
T.me/SCHOOLOFAMERICAN

ነባሩ ሥርዓተ - ትምህርት በ2017 ዓ.ም ሙሉ ለሙሉ በአዲስ ሥርዓተ -ትምህርት እንደሚተካ ተገለጸ።
በትምህርት ሚኒስቴር የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እሼቱ አስፋው እንደገለጹት፥ አሁን በስራ ላይ የሚገኘውን ስርዓተ - ትምህርት ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በአዲስ ለመተካት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም ነባሩን ሥርዓተ - ትምህርት ሙሉ በሙሉ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ለመተካትና ተግባራዊ ለማድረግ የነባሩን ሥርዓተ - ትምህርት ጠንካራ ጎኖችና ያሉበትን ችግሮች በሚገባ ፈትሾ ከመለየት በተጨማሪ የሚሰሩ ሦስት ዋና ዋና ሥራዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
ከሥራዎቹ መካከልም የሥርዓተ - ትምህርት ማዕቀፍ ዝግጅት፣ የመርሃ - ትምህርት ዝግጅት እና የመጽሃፍት ዝግጅት ይገኙበታል ነው ያሉት። ሥራዎቹን በሦስት አመታት ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑንም ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።የዝግጅት ሥራውም የሁሉንም ክልሎች እና ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ተወካይ ባለሙያዎችን በማሳተፍ እየተከናወነ መሆኑን ነው የገለጹት።በአሁኑ ወቅት ከሦስቱ ዋና ዋና ሥራዎች መካከል ወሳኝና መሠረታዊ የሆነውን የሥርዓተ ትምህርት ማዕቀፍ ዝግጅት መጠናቀቃቸውንም ተናግረዋል።
በቀጣይ ጊዜያት በቅደም ተከተልና ጎን ለጎን የሚሠሩ ሥራዎችን በማጠናቀቅ በሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት የሚገመገም መሆኑንም አንስተዋል። ከ2014 ዓ.ም ጀምሮም ከቅድመ መደበኛ እስከ 12ኛ ክፍል ባሉ የትምህርት ደረጃዎች ላይ ሀገራዊ ተጨባጭ ሁኔታን በሚገልጽ መልኩ ትምህርት ቤቶችንና ክፍሎችን በናሙናነት በመምረጥ የሙከራ ትግበራ ይከናወናል ብለዋል።