YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ለስልኮች የፊት ገጽ ማጠንከሪያ ተብሎ አገልግሎት ላይ እየዋለ ያለው የናኖ ቴክኖሎጂ ፈሳሽ ተፈትሾ ችግር አልተገኘበትም ብሏል የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለሥልጣን

ለስልኮች የፊት ገጽ ማጠንከሪያ ተብሎ አገልግሎት ላይ እየዋለ ያለው የናኖ ቴክኖሎጂ ፈሳሽ ተፈትሾ በሰው፣ በአካባቢ እና በንብረት ላይ ጉዳት የማያስከትል ስለመሆኑ መረጋገጡን የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ አቶ አወቀ ሺፈራው በተለይ ለኢቲቪ እንደገለፁት መሥሪያ ቤታቸው በደረሰው ጥቆማ መሠረት ለስልኮች የፊት ገጽ ማጠንከሪያ ተብሎ አገልግሎት ላይ እየዋለ ያለው የናኖ ቴክኖሎጂ ፈሳሽ ላይ ፍተሻ አድርገዋል።

በመሥሪያ ቤቱ ባለሞያዎች በተደረገ ምርመራ ስልኮች ላይ የሚቀባው ፈሳሽ ምንም ዓይነት ጨረራ የማያመነጭ እና ችግር የማያስከትል ስለመሆኑ አመልክተዋል።የናኖ ፈሳሽ ቴክኖሎጂውን የተለያዩ አስመጪዎች ወደ አገር ውስጥ እንደሚያስገቡት የጠቆሙት፣ አቶ አወቀ መሥሪያ ቤታቸው አስመጪዎች ማናቸውም ዕቃዎች ከውጭ ማስገባታቸውን ለተቋማቸው ሲያሳውቁ ብቻ ፍተሻ የሚያደርጉ መሆኑን ከዚህ ባለፈ ግን ወጪ እና ገቢ ዕቃዎችን የሚመለከተው ገቢዎች ባለሥልጣን እንደሆነ በአጽንኦት ተናግረዋል።

ምንጭ: ኢቲቪ
@YeneTube @FikerAssefa
አባይ ባንክ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር የዲጂታል ክፍያ መላዎችን ጀመርኩ አለ፡፡

ባንኩ ከአየር መንገዱ ጋር የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት መላዎችን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ ሀላፊዎች ጋር ተፈራርሟል፡፡ለዚሁ መላ የባንኩ ደንቦች በኦንላይን ባንኪንግ በመጠቀም ትኬት መቁረጥ ይችላሉ፡፡ ሌሎችም አገልግሎቶችን ማግኘት ይችላሉ መባሉን ሰምተናል፡፡አባይ ባንክ አገልግሎቱን በጀመረ በአንድ ሳምንት ውስጥ 1 ሚሊየን ገደማ ጥሪት መንቀሳቀሱን የስራ ሀላፊዎች ተናግረዋል፡፡በተያያዘም፣ ይህንኑ አገልግሎት ከአማርኛ በተጨማሪ በሁለት የአገር ቤት ቋንቋዎች ማግኘት ይቻላል ተብሏል፡፡ የባንኩ የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች 125 000 የደረሰ ሲሆን አጠቃላይ የደንበኞቹ ቁጥርም 700 000 እንደደረሰ ሰምተናል፡፡

Via Sheger FM
@YeneTube @FikerAssefa
የከተማ አስተዳደሩ ከጥር 2 ጀምሮ በህገወጥ መልኩ የተገነቡ ቤቶች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከጥር 2 ጀምሮ በህገወጥ መልኩ የተገነቡ ቤቶች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል፡፡ እርምጃው በተለይ በቅርብ ጊዚያት እየተስፋፋ የመጣውን የህገወጥ የመሬት ወረራ ለመከላከል ያለመ ነው ተብሏል፡፡ እርምጃው በአዲስ አበባ በሚገኙ 116 ወረዳዎች የሚወሰድ ሲሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የኦሮሚያ ፖሊስና የከተማዋ አጎራባች ወረዳዎች በመቀናጀት እርምጃ እንደሚወስድ የከንቲባ ጽ/ቤት ባወጣው መረጃ ተገልጿል፡፡በየወረዳው በህገወጥ መልኩ የተገነቡ ቤቶችን የመለየት ስራም እየተሰራ ይገኛል ተብሏል፡፡በከተማዋ ባሉ ወረዳዎች ቦታዎቸን ለመያዝ በህገወጥ መልኩ እየታጠሩ እንደሆነና ከላስቲክ ቤቶች ጀምሮ የተለያዩ ህገወጥ ግንባታዎች እየተደረጉ እንደሆነ የተሰበሰቡት መረጃዎች መጠቆማቸው የገለጸው አስተዳደሩ በጉዳዩ ላይ መግለጫ እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡

Via Addis TV
Photo: ©YeneTube
@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ከፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ እና ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተፃፉ ሁለት ደብዳቤዎች ለሳዑዲ አረቢያው ንጉስ ሳልማን አቅርበዋል። ስለ ደብዳቤዎቹ ይዘት የተባለ ነገር የለም።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ቃቃል አቀባይ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ግድያ የተጠረጠሩ ግለሰቦች ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ ለጥር 08/2012 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ችሎት ለመታደም የተገኙ ቤተሰብና ደጋፊዎቻቸው የተቃውሞ ድምጽ አሰምተዋል፡፡

Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
የጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ አማካሪ ዳንኤል ክብረት ወደ ሊቢያ አቅንተው በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እውቅና ከተሰጠው መንግሥት የውጭ ጉዳይ ምኒስትር መሐመድ ሳያላ ጋር በሊቢያ መረጋጋት እና የሁለቱ አገሮች ግንኙነት ላይ ተወያይተዋል

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ካቢኔ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ካቢኔው በዛሬው እለት ባካሄደው ስብሰባው የባሌ ዞን በሁለት ዞኖች እንደ አዲስ እንዲደራጅ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ በማሳለፍ እንዲጸድቁ ለጨፌ ኦሮሚያ መርቷል። በዚህም መሰረት የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ለካቢኔው ባቀረበው ጥናት በዞኑ ባለው የመሰረተ ልማት እና የቦታ መራራቅ ችግር የተነሳ አገልግሎት ፍጥነት ማቅረብ ባለመቻሉ ለረጅም ጊዜ የመልካም አስተዳደር ችግር ምንጭ ሆኖ መቆየቱን ጠቁሟል። ካቢኔው ጥናቱን መነሻ በማድረግ ውይይት ካካሄደ በኋላ የባሌ ዞን የነበረው፤ ምስራቅ ባሌ ዞን እና ምእራብ ባሌ ዞን ሆኖ እንደ አዲስ እንዲደራጅ በሙሉ ድምጽ ወስኗል።

የምእራብ ባሌ ዞን ዋና ከተማ ሮቤ እንዲሁም የምስራቅ ባሌ ዞን ዋና ከተማ ደግሞ ጊኒር እንዲሆን የቀረበው ምክረ ሀሳብም በሙሉ ድምጽ መጽደቁ ነው የተገለፀው።

በሌላ በኩል የክልሉ መንግስት ካቢኔ ባካሄደው ስብሰባ የኦሮሚያ ክልል የማዕድን ልማት አስተዳደርን ለመወሰን የቀረበ ረቂቅ አዋጅ እና የኦሮሚያ መንገዶች ፈንድን ለማቋቋም የቀረቡ ረቂቅ አዋጆች ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ ለጨፌ ኦሮሚያ እንዲቀርብ ውሳኔ አሳልፏል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ዜና ሹመት

ዶ/ር ጥላዬ ጌቱ በፓሪስ የኢፌድሪ ሚሲዮን በመደብ መታወቂያ ቁጥር 15አአ-1107 በባለሙሉ ስልጣን ሚኒስትር የስራ ደረጃ የዩኔስኮ ምክትል ቋሚ መልክተኛ ሆነው እንዲሰሩ ተውስኗል።

- መሉውን መረጃ ከፎቶው ላይ ያገኛሉ
@Yenetube @Fikerassefa
የዳዉሮ ህዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄ መልስ ባለማግኘቱ የቅሬታ ጥያቄ ለፌደሬሽን ምክር ቤት ቀረበ!

የዳዉሮ ዞን ም/ቤት ታህሳስ 2/2011 ዓ.ም በክልል ለመደራጀት ያስተላለፈዉ ዉሳኔ ምላሽ ሳይሰጥ ለአንድ ዓመት በመዘግየቱ ምክንያት የፌደሬሽን ምክር ቤት ስልጣንና ኃላፊነት ለመግለፅ በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 251/1993 አንቀጽ 2 እና 3ን መሰረት ያደረገ የዳዉሮ ህዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄ ምላሽ ያለማግኘቱ ቅሬታ ለፌደረሽን ም/ቤት ቀርቧል::ከታህሣስ 13 እስከ 15/2012 ዓ.ም አድስ አበባ በመቆየት ቅሬታዉን ለፌደሬሽን ም/ቤት ያቀረቡት የሃገር ሽማግሌዎች ፣ የኃይማኖት አባቶች የዞኑ ም/ቤት አባላት በፓርላማ የዳዉሮ ህዝብ ተወካዮቻችን ጋር በመሆን የዳዉሮ ህዝብ ዉሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን መጠየቃቸዉን ገልጸዋል::

በዚህ ጉዞአቸዉ በዞኑ አንገብጋቢ የነበሩትን የመሠረተ ልማት ጥያቄዎችን ለሚንስቴር መ/ቤቶች ማንሳታቸዉንም ያብራሩት የዳዉሮ ህዝብ ተወካዮች፣ በዞኑ በሁሉም ወረዳ እና ታርጫ ከተማ ያለዉን የንጹህ መጠጥ ዉኃ ፣ የመንገድ እና የመብራት ችግር እንዲሁም የወላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ታርጫ ካምፓስ ወደ ዩንቨርስቲ እንድያድግ ለየዘርፉ ሚንስትር መ/ቤቶች በተደራጀ መልኩ ማቅረባቸዉን በሪፖርቱ ገልጸዋል።እንደ ተወካዮቹ ገለጻ በክልል የመደራጀት ጥያቄ የፌደረሽን ም/ቤት የተቀበለ ሲሆን ምላሹ ከሌሎቹ ተመሳሳይ ዞኖች ጥያቄ ጋር አብሮ እንደሚታይ መገለፁንም አሣዉቀዋል።የመሠረተ ልማት ጥያቄዎችን በሚመለከትም ምላሹን በፓርላማ የዳዉሮ ተወካዮቻችን እና የዞኑ መንግስት እንዲከታተሉ መገለጹን አሣዉቀዋል::

ምንጭ:የዳዉሮ ዞን ህዝብ ግኑኝነት ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ ወገል ጤና ከተማ ሙስሊሞች በምስራቅ ጎጃም በሞጣ ከተማ በሙስሊሞች ላይ የተፈፀመውን ጥቃትና የመብት ጥሰት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ።

@YeneTube @Fikerassefa
#FakepageAlerts

ይህ ገፅ በየኔቲዩብ ስም የተከፈተ ቻናል ነው የተለያዩ ስህተት ያላቸው ዜናዎችን እያቀረበ ይገኛል ከወዲሁ የኛ ቻናል አለመሆኑ ለማሳወቅ እንወዳለን።

ትክክለኛውን የኔቲዩብን ለወዳጅ ዘመዶ በማስተዋውቅ ከውሸት ዜና እራስዎን እንዲሁም ቤተሰቦን ያርቁ።

እንዴት ለምታቁት ሰው መላክ እንደምትችሉ ከከበዳችሁ ጠይቁን!!

እናመሰግናለን!!
@YeneTube @Fikerassefa
ጃዋር ሞሐመድ የአሜሪካ ዜግነቱን ትቶ የኢትዮጵያ ዜግነቱን በማግኘት ሂደት ላይ መሆኑን ለአዲስ ስታዳርድ በሰጠው ቃለ ምልልስ ገልጧል፡፡ የኦሮሞ ሜዲያ ኔትወርክ ሥራ አስኪያጅነቱን ለሌላ #እያሰረከበ ነው፡፡

ከኦፌኮ ጋር #የረጅም_ጊዜ_ግንኙነት አለኝ ብሏል፡፡ ኦፌኮ ከኦነግ እና ሌሎች የኦሮሞ ፓርቲዎች ጋር በክልል እና ፌደራል ደረጃ ለመጭው ምርጫ #ቅንጅት ለመፍጠር ንግግር ጀምሯል፡፡

@YeneTube @Fikerassefa
የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባውን ሊያካሂድ ነው!

የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባውን ሊያደርግ እንደሆነ ተሰምቷል። ፓርቲው የተለያዩ ወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳይ ላይ የሚያካሄደው የመጀመሪያው ስብሰባ ከሰሞኑ ያካሂዳል ተብሎ ይጠበቃል።

©ማለዳ ሚድያ
@YeneTube @FikerAssefa
የአውሮፓያውያን አዲስ አመት 2020 በዓለም ዙሪያ በተለያዩ ክብረ በዓሎች፤ የርችት ተኩስ ትዕይንቶች እየተከበረ ነው።

ከሀገር ውጪ ያላችሁ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን 2020 በሰላም አደረሳችሁ!!
ፎቶ፦ ሮይተርስ
@YeneTube @FikerAssefa
ብሩህ ቀን ይሁንላችሁ | ገጠሩ የሀገራችን ክፍል

- ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ብንጓዝ ገጠሩ የሀገራችን ክፍል ከዚህ ፎቶ ጋር ተመሳሳይነት አለሁ እኛ ኢትዮጵያዊያን ከልዩነታችን በላይ የሚያመሳስለን ይበልጣል።

-እንደለመድነው ዜናዎችን ሳይበርዱ ለናንተ እናደርሳለን።

- የኔቲዩብ ለጓደኟዎ መጋበዝ መቼም አይርሱ

በድጋሜ መልካም ቀን ተመኘንላችሁ አብራችሁን ቆዮ።

💚💛❤️ t.me/YeneTube 💚💛❤️
የመንግሥት ሠራተኞች የውሎ አበል መመሪያ ይሻሻል!

በመንግሥትም ይሁን በግል ተቋማት አንድ ሰራተኛ ከስራው ቦታ ወደ ሌላ አካባቢ አልያም ቢሮ ተንቀሳቅሶ እንዲሰራ ሲፈለግ የትራንስፖርት፣ የምግብና የማደሪያ ወጪውን ሊሸፍንለት የሚችል የውሎ አበል ይታሰብለታል። ይህ አሰራር በተለይ በግል ተቋማትና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች አካባቢ የተሻለ ገጽታ ቢኖረውም ወደ መንግስት ሰራተኞች ስንመጣ ግን አንዳንድ ጊዜ ‹‹እንዲህም ይኖራል›› ወይ የሚያሰኝ ሆኖ እናገኘዋለን።ከሐምሌ 1ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ የዋለው የመንግስት ሠራተኞች የቀን ውሎ አበል መመሪያ እንደሚያመለክተው የመንግሥት ሠራተኛው በየትኛውም ክልል ሄዶ ቢሰራ ከፍተኛ ደመወዝ አለው የሚባለው 225 ብር የሚታሰብለት ሲሆን፤ አነስተኛ ደመወዝ ተከፋይ ነው የሚባለው ደግሞ በቀን የሚያገኘው 111 ብር ነው።

Via EPA
@YeneTube @FikerAssefa
"በአሁኑ ወቅት ለጡረተኞች የሚከፈለው ዝቅተኛ ወርሀዊ ክፍያ 1,258 ብር ሲሆን ትልቁ ደግሞ 153,000 ይደርሳል"--- የመንግሥት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ

- በሀገሪቱ ለሚገኙ 750,000 የሚደርሱ ጡረተኞች በዓመት ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ ይከፈላል

- የማህበራዊ ዋስትና ሽፋን ካላቸው 2.1 ሚሊዮን ዜጎች በአመት አስራ ሁለት ቢሊዮን ብር እየተሰበሰበ ነው

- ከፍተኛ የጡረታ አበል የሚከፈላቸው ዜጎች ቁጥር አነስተኛ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ካፕቴኖች ይጠቀሳሉ

Via:- Ethiopian Press
@YeneTube @Fikerassefa