YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ሼር ይደረግ !!

የነገው የሀረርጌ ሰልፍ ወደ ሚቀጥለው ማክሰኞ ተዛውሯል! - አህመዲን ጀበል - #Share

የክርስትና እምነት ተከታዮች የሚያከብሩትን ዓመታዊ የቁሉቢ ገብርኤል በዓልን አስታከው የሃይማኖት ግጭት ለመፍጠር ጸረ ሰላም ኃይላት እንቅስቃሴ እያደረጉ እንዳሉ ምክልክቶች በመታየታቸው እና የክርስትና እምነት ተከታዮች በዓላቸውን በሰላም አሳልፈው እስኪያጠናቅቁ ድረስ በሰላም ለማሳለፍ ሲባል በሀረርጌ በሚከተሉት ከተሞች የነገው ሰልፍ ወደ ማክሰኞ ተዛውሯል። የነገው ሰልፍ የተዛወሩባቸው ከተሞች በሀረር ከተማ፣ አወዳይ ከተማ፣ ሀረማያ፣ ደንገጎ፣ ቀርሳ፣ ላንጌ፣ ቁሉቢ፣ ጨለንቆና ቆቦ ናቸው። በመሆኑም ከላይ በተጠቀሱት ከተሞች ምንም አይነት ሰላማዊ ሰልፍ አለመኖሩ ይታወቅ። ሌሎች አከባቢዎችም ሰላማችሁን በንቃት ጠብቁ።


Hirriirri Harargee bori gara sulasaiitti dabarfateera!

Hirriirri mormi Harargee magaaloota Harar, Awaday, Haramaayaa, dhangaggoo, Qarsaa, Laangee, Qullubbii, Calanqoo fi Qobboo gara kibxata (sulasaa'iiti) Dabarfateera. Sababni isaammoo ayyaana waggaa amantaa kirstaanaa Qullubbi Gabrieliin walqabatee qamoonni jeequmsa amantaa kaasuuf qophaahan sochirra akka jiran mallattoon mulachu hubachuudhan marii godhameen ayyaanni amantaa kiristaana nagaadhaan akka kabajamu fi warraa

Via:- አህመዲን ጀበል
@YeneTube @Fikerassefa
የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ የተሰጠ መግለጫ
@YeneTube @Fikerassefa
መልካም ቀን ይሁንላችሁ
#ጁመዐ
#BCAA
#ሰበር_ዜና

98 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውሮፕላን ካዛኪስታን ውስጥ ተከሰከሰ ንብረትነቱ የቤክ ኤይር አየር መንገድ የሆነው ፎከር 100 የተሰኘው አውሮፕላን ካዛኪስታን አልማቲ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ተከስክሶ እስካሁን በትንሹ 14 ሰዎች ሞተዋል።

ባለሁለት ወለለል ህንጻ ላይ በተከሰከሰው አውሮፕላን ውስጥ ከነበሩት ውስጥ 93 መንገደኞች እና አምስት የበረራ ሰራተኞች መሆናቸውም ታውቋል።

የአውሮፕላን ማረፊያው ባለስልጣናት እንዳሉት አውሮፕላኑ ከአልማቲ ወደ ኑር ሱልጣን ከተማ ለመጓዝ በረራ እንደጀመረ በጥቂት ደቂቃዎች ልዩነት ነው የተከሰከሰው።
ህጻናትን ጨምሮ ጉዳት የደረሰባቸው ከ60 የማያንሱ ሰዎች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።
የአውሮፕላን አደጋው ምክንያት እስካሁን አልታወቀም።

Via:- BBC
@yenetube @Fikerassefa
በሞጣ ከተማ የደረሰውን የመስጂዶችና ንብረት ቃጠሎ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች አወገዙ።

በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ አስተዳደር ታኅሣሥ 10 ቀን 2012ዓ.ም በመስጅዶችና ንብረት ላይ የደረሰውን ቃጠሎ የደሴ ከተማ አስተዳደር ሙስሊሞች በሠላማዊ ሰልፍ አወገዙ፡፡ ነዋሪዎቹ ከጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ በደሴ ከተማ ሠላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡

Via:- አብመድ
@Yenetube @FikerAssefa
የሀዋሳ ከነማ እግር ኳስ የደጋፊዎች ማኅበር አባላትየሀዋሳ ከተማን አጸዱ

የሀዋሳ ከነማ እግር ኳስ የደጋፊዎች ማኅበር አባላት በዛሬው ዕለት የሀዋሳ ከተማን አጽድተዋል፡፡

የማኅበሩ አባላት የጽዳት ሥራውን ያከናወኑት የፊታችን እሑድ የሚከበረውን የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አስመልክቶ መሆኑንም ነው ያስታወቁት፡፡

በጽዳት ዘመቻው የክለቡ ደጋፊዎች እና የከተማዋ ኅብረተሰብ መሳተፉን ክለቡ በፌስቡክ ገጹ አስነብቧል፡፡

ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ በተካሄደው የጽዳት ዘመቻ ላይ የሀዋሳ ከተማ ወደ ቀደመው ሰላሟ መመለሷ እንግዶቿን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኗን ደጋፊዎቹ አስታውቀዋል፡፡

በመጪው እሑድ ለሚከበረው በዓል ሁሉም ሃይማኖት ሳይገድበው ሀዋሳ ለእንግዶች ጽዱ ከተማ ሆና እንድትታይ በማለት ከተማዋን እንዳጸዱ ተገልጿል፡፡

Via:- EBC
@Yenetube @Fikerassefa
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ኮርፖሬሽን የቀላል ባቡር ጥገናና እድሳት ማዕከል ለመገንባት ከቻይና መንግስት ጋር መስማማቱን ገለፀ፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉቀን አሰፋ በተለይ እንደገለፁት በከተማዋ ቀደም ሲል ሁለት የጥገና ማዕከላት ቢኖሩም የጥገና አገልግሎት ቀላል ለሆኑ ብልሽቶች ብቻ በመሆኑ ባቡሮች ሲበላሹ ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ወደ ቻይና በመላክ ሲያስጠግን ቆይቷል። ይህ ደግሞ በትራንስፖርት አገልግሎቱ ላይ ከሚፈጥረው ጫና ጋር ተዳምሮ ከፍተኛ ችግር ሆኖ ቆይቷል።

አዲስ አበባ ላይ የሚገነባው ጥገናና እድሳት ማዕከል ወደ ቻይና የሚደረገውን ጉዞ ያስቀራል ተብሏል።

ፎቶ :- ፋይል
@Yenetube @Fikerassefa
የኢትዮ ኤርትራ የቴሌኮም ንግድ ልውውጥ

ኢትዮጵያና ኤርትራ እርቅ ማውረዳቸው ተከትሎ በተከፈተው የስልክ ጥሪ አገልግሎት እስካሁን የ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር የንግድ ልውውጥ ማድረጋቸው ተሰማ፡፡
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ጉብኝት ሲያደርጉ ለነበሩት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሽኝት እራት በጋበዙበት ወቅት ነው ይህን ያሉት፡፡

በአየር መንገድ ዘርፍም ከኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ በረራ መጀመሩን ተከትሎ ከቴሌኮሙ የሚልቅ የንግድ ልውውጥ ተደርጓል ብለዋል፡፡
ለሁለት ቀናት ኢትዮጵያ የነበሩት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር እና ኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የተለያዩ የማምረቻ ማዕከላትን ሲጎበኙ እንደነበር ይታወቃል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ታኅሣሥ 17 ረፋድ ወደ አስመራ ተሸኝተዋል፡፡//

Via:- አሐዱ ቴሌቪዥን
@yenetube @Fikerassefa
በኢትዮጵያ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው የጉዞ እቅድ መተግበሪያ ካርታ (ዲጂታል ማፕ) በይፋ ተመረቀ

በኢትዮጵያ የህዝብ ትራንስፖርት ለማሻሻል ወሳኝ ነው ተብሎ የሚታመነው የጉዞ እቅድ መተግበሪያ (ዲጂታል ማፒንግ) ዛሬ በሂሊተን ሆቴል የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በተገኙበት በይፋ ተመርቋል።

@Yenetube @Fikerassefa
#HIV

በካፒታል ሆቴል በ HIV ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው።

በጉባኤው ላይ እንደተነገረው፣ በአሁኑ ወቅት በአመት 23ሺ ኢትዮጵያዊያን በቫይረሱ ይያዛሉ ተብሏል። 11 ሺ 049 በየአመቱ ይሞታሉ። ቫይረሱ እየተስፋፋ ነው። ጦርነት መክፈት ያለብን HIV እንዳይስፋፋ ነው።

via:-Tibebu Belete
@Yenetube @Fikerassefa
በደሴ በአዳማ በወልዲያ በአርሲ ነገሌ በአፋር በደንቢዶሎ በመርሳ በመካነሰላም በሀርቡ በበዴሌ በጅማ በደጋን በሥልጤ በባኮ ትቤ ባሌ ጊንዲር ባቲ መደወላቡ ደጋን እስክካሁን ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደባቸው የሚገኙ አከባቢዎች ናቸው::

@Yenetube @Fikerassefa
በሰላማዊ ሰልፎቹ ላይ የተሰሙ ድምፆች...

* "መንግሥት በእምነት ተቋማት ላይ ጥቃት የሚያደርሱ አካላት ላይ አፋጠኝ እርምጃ ሊወስድ ይገባል!

* የሚዲያዎች የሃይማኖት አድሎ ይቁም!

* መንግሥት ለተቃጠሉ የእምነት ተቋማትና ንብረታቸው ለወደመባቸው ግለሰቦች ተገቢውን ካሳ ሊከፍል ይገባል!

* በሃይማኖትም ሆነ በፖለቲካ ጽንፈኛ አካላትን መንግሥት እንዲያሰተካክል" የሚሉ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።

#ኢትዮጵያ_የሁሉም_እምነቶች_ደሴት_ነት
@Yenetube @Fikerassefa
VACANCY - Fortune

We, at INMP, publisher of the largest English weekly in #Ethiopia, are searching for hardcore programmers who are passionate about breaking things and hacking solutions into microservices out of complex specifications in an effective, iterative manner.

@Yenetube @Fikerassefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ክብር ለኢትዮጵያ
ክብር ለሴቶች
ሰላም ለኢትዮጵያ

ከፍሬወይኒ 🎬BBC
@Yenetube @Fikerassefa
የክልል ልዩ ኃይል አደረጃጀት ላይ ማሻሻያ ለማድረግ ታስቧል

በአገሪቱ የተለያዩ ክልሎች ያለው የደህነነት እና ፖሊስ ሰራዊት አደረጃጀት ላይ ለውጥ የማድረግ ውጥን መኖሩ ተገለጸ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ድኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ‹‹የፀጥታ ተቋማት በፖለቲካ ሽግግር ውስጥ›› በሚል ርዕስ ደህንነትና የፀጥታ አካላት አሠራርና ማሻሻያን አስመልክቶ በተደረገ ውይይት ላይ እንደተናገሩት፤ አሁን ባለው ሁኔታ የደህንት መዋቅር ለውጦች መደረግ እንዳለባቸው የታመነ ሲሆን የክልል ልዩ ኃይልና ፖሊስ አካላትም በዚሁ ታሳቢ ተደርገዋል፡፡

እነዚህ ኃይሎች የሚጠቀሙት መሳሪያን ጨምሮ ዩኒፎርማቸውም ታሳባቢ እየተደረገ ነው፡፡ በክልል ያለው ልዩ ኃይል ሆነ ሌላ አደረጃጀት መፍትሄ እንደሚሰጠውም ሚኒስተር ድኤታው አረጋግጠዋል።

Via:- EPA
@Yenetube @Fikerassefa