ለዩኒቨርሲቲ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች በተዘጋጀው የታሪክ ሞጁል ላይ የግምገማ መድረክ ተከፈተ
የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለዩኒቨርሲቲ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች በጋራ ከሚወስዷቸው ትምህርቶች አንዱ በሆነው የታሪክ ሞጁል ላይ የጋራ ግምገማ መድረክ ታኅሣሥ 16 ቀን 2012 አዲስ አበባ ውስጥ ጀመረ።
በግምገማ መድረኩ ላይ ከዩኒቨርሲቲ ምሁራን እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የተውጣጡ ባለሞያዎች እንደሚሳተፉ ታውቋል።
ግምገማው ከታኅሣሥ 16-18 ቀን 2012 ባሉት ሦስት ቀናት ውስጥ እንደሚካሔድም ተገልጿል።
@Yenetube @Fikerassefa

የኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የአዳማ የኢንዱስትሪ ፓርክንና ገልመ አባገዳን ጎበኙ!
በትናንትናው ዕለት ለይፋዊ ጉብኝት ኢትዮጵያ የገቡት የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ የአዳማ የኢንዱስትሪ ፓርክን እና ገልመ አባገዳን ጎብኝተዋል። የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ለመሪዎቹ አቀባበል አድርገዋል።
የአዳማ ሕዝብ ለመሪዎቹ ደማቅ አቀባበል ከማድረግም ባሻገር በኦሮሞ ሕዝብ ባህል እና እሴት መሠረት የፈረስ ስጦታ እንዳበረከተላቸው ከኦቢኤን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
@YeneTube @FikerAssefa

አንበሳ ባንክ ከታክስ በፊት ከ695 ሚሊዮን ብር በላይ አተረፈ!
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አክሲዮን ማኅበር በ2011 የሒሳብ ከታክስ በፊት ያገኘው ትርፍ በ45 በመቶ በማደግ 695.5 ሚሊዮን ብር መሆኑን ገለጸ፡፡ ባንኩ የ2011 ዓመት የሒሳብ ዓመት ሪፖርቱ እንደሚያመላክተው፣ ከታክስ በኋላ ያገኘው የትርፍ መጠን 539 ሚሊዮን ብር ሆኗል፡፡ ባንኩ የሒሳብ ዓመቱ አፈጻጸም ውጤታማ እንደነበር የሚያመላክት ሲሆን፣ በተለይ በሁሉም የተቀማጭ ሒሳብ ዓይነቶች 4.8 ቢሊዮን ብር ማሰባሰብ መቻሉ ለአብነት ተጠቅሷል፡፡
https://telegra.ph/Anbesa-12-26

👍1
የወራቤ- ቦዣባር አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ስራ በይፋ ተጀመረ።
በዛሬው እለት የሰላም ሚንስትር መፈርያት ካሚል፣ የትራንስፖርት ሚንስትር ዳግማዊት ሞገስ፣የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው እና የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋናዳይሬክተር ኢ/ር ሀብታሙ ተገኘን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ የክልል እና የፌደራል የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት የፕሮጀክቱን ስራ በይፋ አስጀምረዋል። የወራቤ - ቦዣበር መንገድ ግንባታ ስራው ከ795 ሚልዮን በጀት ተመድቦለታል።በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ላይ የሚጀምረው ፕሮጀክቱ 40.5 ኪ.ሜ ርዝመት አለው።ለመንገዱ ግንባታ የሚውለው ወጪ በኢትዮጵያ መንግስት ይሸፈናል።
Via ERA

የኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዱከም የሚገኘው የኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞንን ዛሬ መጎብኘታቸውን ከኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
@Yenetube @FikerAssefa
@Yenetube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ የኤርትራ ኤምባሲ ግንባታ የመሠረተ ድንጋይ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ እና የሃገረ ኤርትራ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ በተገኙበት በዛሬው ዕለት ተቀምጧል፡፡
Via Mayor Office of Addis Ababa
@YeneTube @FikerAssefa
Via Mayor Office of Addis Ababa
@YeneTube @FikerAssefa
የሲኤንኤን የዓመቱ ጀግና በመቀለ ደማቅ አቀባበል ተደረገላት
ሲኤንኤን የዓመቱ ‘ጀግና’ ሲል የሸለማት ፍረወይኒ መብራህቱ ዛሬ ከሰዓት መቀለ ከተማ ስትደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላታል።
ፍረወይኒ በሲኤንኤን የዓመቱ ጀግና ተብላ እንድትመረጥ ያደረጋት፤ በመቀለ ከተማ ከ13 ዓመታት በፊት በመሰረተችው ማርያምሰባ ፍብሪካ በምታመርተው የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ምርት ነው።
ይህ ምርት በአነስተኛ ዋጋ ተገዝቶ በድጋሚ ጥቅም ላይ ከመዋሉም ባሻገር፤ ሴት ተማሪዎች በወር አበባ ምክንያት በሚያጋጥማቸው የስነ ልቦና ተጽእኖ ከትምህርት ቤት እንዳይቀሩ አስችሏል።
Via:- BBC

❤1
አሊባባ እና የቻይና ኤሌክትሪክ ፓዎር የተባሉ ድርጅቶች ከ700 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ የሕክምና መሣሪያዎችን ለፈለገ ሕይወት አጠቅላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ድጋፍ አድርገዋል፡፡ ከ15 በላይ የሚሆኑ የቻይና የሕክምና ቡድን አባላት በፈለገ ሕይወት አጠቅላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከትናንት ታኅሣሥ 15/2012 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ቀን የሚቆይ የሕክምና ድጋፍ እያደረጉ ነው፡፡
Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
🔥1
በምዕ/ጎንደር ዞን በቋራ ወረዳ ከነፍስ ገቢያ ወደ ጎንደር በመጓዝ ላይ የነበረ ተሽከርካሪን ታጣቂዎች አስቁመው 5 ሰዎችን ማገታቸውን የቋራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ። ጽ/ቤቱ እንዳስታወቀው "እገታው ማንነትን መሰረት ያደረገ ነው።"
Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
ለመጪው ምርጫ ወደ 300 ሺህ ገደማ የምርጫ አስፈጻሚዎች እንደሚመለመሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባል ብዙወርቅ ከተተ ተናግረዋል።ቦርዱ የምርጫ አስፈጻሚዎችን ለመመልመል እና ለማሰልጠን ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ለፋና ገልጸዋል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የአማራ ልዩ ሀይል በኦሮሞ ልዩ ዞን እንደገና ሊሰማራ በሚችልበት ሁኔታ ላይ ዛሬ በከሚሴ ከተማ ውይይት ተካሄደ። በውይይቱም ልዩ ሀይሉ ወደ ዞኑ ተመልሶ እንዲገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል።በውይይቱ የዞኑ አስተዳዳሪዎች፣ የልዩ ሀይሉ ሀላፊዎችና አባላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የመከላከያ ሰራዊት፣ የፌድራል ፖሊስ፣ እና ሌሎችም ተሳትፈዋል።
Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሥራን ባደናቀፉ 10 ተማሪዎች ላይ አሰተዳደራዊ ዕርምጃ ወስጃለሁ ብሏል። ዕርምጃ የተወሰደባቸው ተማሪዎች ሌሎች ሰላማዊ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ በሃይል አስገድደዋል፤ ደኅንነት ሰጋትም ፈጥረዋል። ቅጣቱ እስከ 2 ዐመት ከትምህርት ማገድ ጀምሮ ጨርሶ እስከማሰናበት የዘለቀ መሆኑን ኢዜአ ዩኒቨርስቲውን ጠቅሶ ዘግቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
በደቡብ ክልል ጎፋ ዞን በ«ኮሌራ መሰል አጣዳፊ የተቅማጥና ትውከት በሽታ» አራት ሰዎች መሞታቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ እና የጎፋ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቁ።
በሽታው የታየው በዞኑ ኡባ ደብረ ፀሐይ እና ዛላ በተባሉ ወረዳዎች ነው። ሕይወታቸው ካለፉት አራት ሰዎች በተጨማሪ አንድ መቶ ሃያ አንድ ታማሚዎች በሕክምና ላይ እንደሚገኙ በክልሉ ጤና ቢሮ የጤና እና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዋና የሥራ ሂደት ባለቤት አቶ እንዳሻው ሽበሩ ተናግረዋል። አቶ እንዳሻው «ነገሩ የተከሰተው ከእሁድ ጀምሮ ነው። በመጀመሪያው ቀን አራት ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። አሁን እስካለንበት ሰዓት ድረስ አገልግሎት ያገኙ በሽተኞች 121 ደርሰዋል። ሕሙማኑ ከሁለቱም ወረዳ ነው እየመጡ ያሉት። አጣዳፊ ተቅማጥ እና ትውከት ብዙ መንስኤዎች አሉት። አንዱ ኮሌራ ነው። ኮሌራ መሆኑን የሚረጋግጥልን ከሐዋሳ ነገ ማታ የሚመጣው የላብራቶሪ ውጤት ነው» ብለዋል።ኃላፊው እንዳሉት ሕሙማኑ ከክልሉ ጤና ቢሮ እና ከጎፋ ዞን በተውጣጡ ባለሙያዎች ሕክምና እየተደረገላቸው ነው። ኮሌራ መሰል የተባለው አጣዳፊ የተቅማጥና የትውከት በሽታ ወደ ሌሎች አጎራባች ወረዳዎች እንዳይዛመት የቅኝትና የክትትል ሥራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙ አቶ እንዳሻው መናገራቸውን ዶይቸ ቨሌ ዘግቧል።

ደላሎች ባዘጋጁት መጋዝኖች ተዘግቶባቸው የነበሩ 84 ኢትዮጵያዊያን ከሱዳን ወደ አገራቸው ተመለሱ፡፡
በሱዳን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲ ከዓለምአቀፉ የፍልሰት ድርጅት ( I.O.M) ጋር በመተባበር በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ የሆኑ 84 ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።ተመላሾቹ በሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች አማካይነት በሱዳን በኩል ወደ መካከለኛው ምስራቅ አገራት ለመሄድደላሎች ባዘጋጁት መጋዝኖች ተዘግቶባቸው የነበሩ መሆኑ ተገልጿል። ኤምባሲው ከሱዳን የሰዎች ሕገ-ወጥ ዝውውር ቁጥጥር መስሪያ ቤት ጋር በቅርበት በመስራት ከአደጋ በማዳን በካርቱም የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ማቆያ ማዕከል ድጋፍ ሲደረግላቸው የቆዩ መሆናቸው ነው የተጠቀሰው።
ተመላሾቹ በካርቱም የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ማቆያ ማዕከል በቆዩባቸው ጊዜያት ኮሚዩኒቲው የምግብ፣ ህክምና፣ የንጽህና፣ ምክር አገልግሎትና እንክብካቤ ሲደረግላቸው ቆይቷል።በሱዳን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኤምባሲ ከዚህ ቀደም ከሦስት መቶ በላይ የሚሆኑ የሕገወጥ ሰዎች ዝውውር ሰለባ የሆኑ እና በእስር ላይ የነበሩ ዜጎችን ከሱዳን ባለሥልጣን መስሪያ ቤቶችና የተለያዩ ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ና በቅርበት በመስራት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉ ይታወሳል።
ምንጭ: ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

በሞጣ የደረሰውን የቤተ እምነቶች ውድመት ለማውገዝ በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ሠላማዊ ሰልፎች እንደሚደረጉ እየተገለፀ ይገኛል፡፡ የትና መቼ እንደሚካሄድ በግልፅ ለኮሚሽኑ የደረሰ መረጃ አለመኖሩንና ከማኅበረሰቡ ግን በተለያዩ አካባቢዎች ሰልፍ እንደሚኖር እንደሚወራ ተናግረዋል፡፡ በጥንቃቄ ኅብረተሰቡ እንዲመለከተውም የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ አሳስበዋል።
Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa
ዘመን ባንክ ከታክስ በፊት 636 ሚሊዮን ብር አተረፈ!
ዘመን ባንክ በ2011 የሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት ያገኘው የ636 ሚሊዮን ብር ትርፍ ከባለፈው ዓመት ትርፉ 86 በመቶ ዕድገት ያለውን መሆኑን ገለጸ፡፡ባንኩ የ2011 የሒሳብ ዓመት አፈጻጸሙን ይፋ ባደረገበት ሪፖርቱ፣ በሒሳብ ዓመቱ ከታክስ በፊት ያገኘው ትርፍ ከባለፈው ባንኩ በሒሳብ ዓመቱ አገኘዋለሁ ብሎ በዕቅድ ከያዘው አንፃርም በ55 በመቶ ብልጫ ያለው መሆኑን ይጠቀሳል፡፡ በሒሳብ ዓመቱ ከታክስ በፊት ያገኘው ትርፍ ከባለፈው ዓመት የ293.5 ሚሊዮን ብር ብልጫ ያለው ሲሆን፣ ከታክስ በኋላ ያገኘው ትርፍ ደግሞ 483.7 ሚሊዮን ብር ነው፡፡ ይህ የትርፍ መጠን ዘመን ባንክ ባለፉት 12 ዓመታት ውስጥ በአንድ ዓመት ውስጥ ዓመታዊ ትርፉን በ86 በመቶ ያሳደገበት ወቅት ያልነበረ በመሆኑ፣ የ2011 የሒሳብ ዓመቱ የትርፍ ምጣኔው በባንኩ ታሪክ በከፍተኛነቱ የሚጠቀስ ነው፡፡
Via Reporter

በአዲስ አበባ ከተማ 11 ሽጉጦች እና ከ1 ሺ 600 በላይ ጥይቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የለቡ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ከህገ ወጥ የጦር ማሳሪያ ዝውውር ጋር በተያያዘ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት አስፈላጊውን ጥናትና ክትትል በማድረግ በክፍለ ከተማው ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ሀይሌ ጋርመንት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአንድ ግለስብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተደብቀው የተገኙ 10 ቱርክ ሰራሽ እና 1 ኮልት ሽጉጦችን እንዲሁም 1ሺ 663 የሹጉጥ ጥይቶችን ከሶስት ተጠርጣሪዎች ጋር ታህሳስ 11 ቀን 2012 ዓ.ም በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር የሚያስከትለውን ጉዳት የአካባቢው ህብረተሰብ በመገንዘብ ላበረከተው ቀና አስተዋፅኦ ፖሊስ ኮሚሽኑ ላቅ ያለ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
ምንጭ: የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

የ45 የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ከንጋት 12 ሰዓት በፊትና ከምሽቱ 1 ሰዓት በኋላ ከቅጥር ግቢዎቻቸው ውጪ እንዳይገኙ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ አሳለፈ። ከምሽቱ 4 ሰዓት በኋላ ከመኝታ ክፍሎቻቸው ውጪ መቆየት አይችሉም።
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa