የሩዋንዳ መንግሥት በሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ፓድን ኤግዘምትድ ታክስ ከሚጣልባቸው ምርቶች ዝርዝር ውስጥ ማስወጣቱን የሀገሪቱ ማዕከላዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል። በኢትዮጵያም ተመሳሳይ እርምጃ ሊወሰድ በዝግጅት ላይ መሆኑን ምዘገባችን ይታወሳል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የዓለም የሰላም የኖቤል ተሸላሚ ለሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በነገው እለት የአቀባበል ስነ ስርዓት እንደሚደረግ ተገለፀ።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በትናንትናው እለት በኖርዌይ ኦስሎ ተገኝተው የዓለም የሰላም የኖቤል ሽልማታቸውን መቀበላቸው ይታወሳል።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳስታወቁት፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ነገ ከኖርዌይ ኦስሎ ሲመለሱ የጀግና አቀባበል ስነ ስርዓት ይደረግላቸዋል።የአቀባበል ስነ ስርዓቱም በነገው እለት ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ብሄራዊ ቤተ መንግስት እንደሚደረግም አስታውቀዋል።
የአቀባበል ስነ ስርዓቱንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት ጋር በጋራ ያዘጋጁት መሆኑን ገልፀዋል። የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ወጣቶች እና የማርሽ ባንዶች እና የሰራዊት አባላት ለአቀባበል ስነ ስርዓቱ ዝግጅት እያደረጉ እንደሆነም ነው ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የተናገሩት። ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በሚደረገው የጀግና አቀባበል ፕሮግራም ላይም ሁሉም የከተማዋ እና የአዲስ አበባ ዙሪያ ከተማ ነዋሪዎች እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
Via FBC

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በረብሻ የተሳተፉ ተማሪዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃዎችን ከመውሰድ በተጨማሪ በወንጀል ክስ እንዲመሰረትባቸው እያደረገ መሆኑን ገልጿል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ የተሰጠ ማሳሰቢያ!!
በአንዳንድ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ለመጀመር የቅበላ መስፈርቶች የማያሟሉ አመልካቾችን እየተማራችሁ ታሟላላችሁ እያሉ የሚከተሉትን መሠረታዊ መስፈርቶች ሳያሟሉ መዝግበው እያስተማሩ እንደሆነ ኤጀንሲው ደርሶበታል፡-
1. የመሰናዶ ትምህርት ያጠናቀቁ ተማሪዎችን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለትምህርት ዘመኑ ያሳውቀውን የመቁረጫ ነጥብ ሳያሟሉ፡፡
2. ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋም የተመረቁ ባለሙያዎች ከሠለጠኑበት የሙያ መስክ ጋር ተዛማጅ በሆነ የሥልጠና መስክ በአዲሱ የትምህርት ፖሊሲ በደረጃ 4 (ወይም በቀድሞ 10+3 ወይም 12+2) ሳያጠናቀቁ ፡-
📌 የደረጃ 4 የብቃት ማረጋገጫ (COC level 4) ተፈትነው ሳያልፉ
📌 በሙያው ቢያንስ አንድ ዓመት የሥራ ልምድ ሳይኖራቸው እና
3. በየተቋማቱ የሚዘጋጁትን የመግቢያ ፈተናዎች ሳያለፉ እና በምዝገባው ዕለት ሙሉ ለሙሉ መረጃዎች አሟልተው ማቅረብ ሳይችሉ ማስተማር በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
በተጨማሪም፡- በ2011ዓ.ም ወደ ግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎች በአዲሱ የከፍተኛ ትምህርት ፖሊሲ የተዘጋጀውን የፍሬሽማን ኮርስ እንዳይወስዱና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚኖራችሁን የ4 ዓመት የቆይታ ጊዜ ወደ 3 ዓመት እንዲያጥርላችሁ እናደርጋለን ብለው ተማሪዎች ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ተቋማቸው ገብተው እየተማሩ እንዳሉ በማስመሰል ህገወጥ ተግባር እየፈጸማችሁ የምትገኙ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዳላችሁ ለኤጀንሲው ጥቆማ የደረሰ በመሆኑ ይህንን ህገወጥ ተግባር እንድታቆሙ እናሳስባለን፡፡ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን እና ሌሎች ህጋዊ መመሪያዎችን ጥሶ የተገኘ ተቋም በከፍተኛ ትምህርት ተቋም የስነ ስርዓት መመሪያ መሠረት በወንጀልና በፍትሐብሄር ተጠያቂ እንደሚሆን ኤጀንሲዉ እየገለጸ ከህግ ውጪ ገብተው የሚማሩ ተማሪዎችም በጊዜያቸውና በገንዘባቸው ላይ ለሚደርሰው ኪሳራ ኃላፊነቱ የራሳቸውና የተቋሙ ብቻ ስለሚሆን አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ያሳስባል ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ፡- የኤጀንሲውን ድረ -ገፅ
www.herqa.edu.et ይጎብኙ ወይም በስልክ ቁጥሮች 011 23 61 30 /0111 23 22 30 ይደውሉ ፡፡
መረጃውን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲን ጠቅሶ የዘገበው BGRS Mass Media ነው።

"ኦስሎ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ እስክትመስል ድረስ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማና በኢትዮጵያ ባነሮች ተውባ ሰነበተች፡፡ ሚዲያዎች ሁሉ ስለ ኢትዮጵያ በኩራት መሰከሩ፡፡ ኢትዮጵያን በድህነትና በጦርነት፣ በረሐብና በእልቂት የሚያውቋት ሁሉ አዲስ ታሪክ ሆነባቸው፡፡ በሩጫ ስናሸንፍ ነበር የሚያውቁን፤ ዛሬ ደግሞ በሰላም ሥራችን በዓለም አቀፍ መድረክ ስናሸንፍ አዩን፡፡ ከግሪን ላንድ እስከ ኒውዚላንድ፣ ከቺሊ እስከ ጃፓን ዓይኖች ሁሉ ወደ ኦስሎ ተተክለው ስለ ኢትዮጵያ ተመለከቱ፡፡
በመላው ዓለም ተበትነው የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን የዜግነት ክብራቸውን ከፍ የሚያደርግ ሥራ በታሪክ ውስጥ ሲመዘገብ አዩ፡፡ ልጆቻቸው በባዕድ ሀገር በታሪካቸው ኮሩ፡፡ ሀገራቸው በምሳሌነትና በአርአያነት ስትነሣ በዓይናቸው ብሌን ተመለከቱ፤ ሰሙ፡፡ በዓረብ ሀገር የሚኖሩ ዜጎቻችን አሠሪዎቻቸው ወደታች ሳይሆን ወደላይ እንዲዩዋቸው የሚያደርግ ታሪክ በዓለም አደባባይ ሲከወን ዕንባ በተሞሉ ዓይኖቻቸው አደነቁ፡፡
ሁለት ዓይነት ታሪክ ሲሠራ የዓለም ዓይኖች ታዘቡ፡፡ በጦርነት የምትታወቅ ሀገር የሰላም ሽልማት ተሸለመች፡፡ የሰላምን ዋጋ የሚያውቀው ዓለም፤ የሰላም ሽልማት በቀላሉ እንደማይገኝ የሚያውቁ የዓለም ዜጎች በደስታና በክብር አብረውን ከረሙ፡፡
ለሕዝቦች መቀራረብ፣ ለሕዝቦች መገናኘት፣ ለሕዝቦች ዕርቅና ሰላም መሥራት የሚያሸልም ተግባር መሆኑን የሚያውቁ ሁሉ፤ የቻሉ በኦስሎ ጎዳናዎች ተገኝተው፤ ያልቻሉ በየቴሌቭዥን መስኮቶች አፍጥጠው ክብር ሰጡን፡፡በኦስሎ ያገኘነው ክብር የሀገራችን ጉዞ ከትናንት የዛሬው፣ ከዛሬውም የነገው እጅግ የተሻለ መሆኑን አመላክቶናል፡፡
ይህ ለኢትዮጵያውያን የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ አይሆንም፡፡በሰላም፣ በሳይንስ፣ በሥነ ጽሑፍ ገና ብዙ ኢትዮጵያውያን ወደ ኖቤል ሀገር ወደ ኖርዌይ ይመጣሉ፡፡ዛሬ ያገኘነውን አክብረን አያሌ ኢትዮጵያውያን በዓለም አቀፍ መድረኮች ሀገራቸውን እንዲያስጠሩ እንሠራለን። ለዚህ ደግሞ ሁላችንም ሀገር የሚያስጠራ ጥረት እንድናደርግ ጥሪ አቀርባለሁ፡፡"
-ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

በሰኔ አስራ አምስቱ ግድያ የተጠረጠሩ ግለሰቦች የክስ መቃወሚያ አቀረቡ!
ከሰኔ 15ቱ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮችና የፀጥታ ኃሎች ግድያ ጋር በተያያዘ በእነ ሻምበል መማር ጌትነት መዝገብ የተጠረጠሩ ግለሰቦች የክስ መቃወሚያቸውን በጽሑፍ ለፍርድ ቤት አቀረቡ።ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ 55 ግለሰቦች ላይ የክስ ማመልከቻ (ቻርጅ) ከተደመጠ በኋላ ነበር ለዛሬ የተቀጠረው።
ዝርዝር ዘገባው👇👇👇👇
https://telegra.ph/Sene15-12-11

ቦሌ መድሃኒአለም ጀርባ አንድ ሰው ሃዩንዳይ አውቶሞቢል መኪና ሰርቆ ለማምለጥ ሲሞክር ተያዘ።
☝️☝️በፎቶው ላይ እንደምትመለከቱት ቦሌ አደይ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም አካባቢ መኪናዋን ሰርቆ ለማምለጥ ሲሞክር በአካባቢው ነዋሪ እና በፖሊስ መያዙን በአካባቢው የነበሩ የአይን እማኞች ተናግረዋል።
ምንጭ:Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
☝️☝️በፎቶው ላይ እንደምትመለከቱት ቦሌ አደይ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም አካባቢ መኪናዋን ሰርቆ ለማምለጥ ሲሞክር በአካባቢው ነዋሪ እና በፖሊስ መያዙን በአካባቢው የነበሩ የአይን እማኞች ተናግረዋል።
ምንጭ:Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ምርጫ ቦርድ ለዘጠኝ ፓርቲዎች የምዝገባ እውቅና ሰጠ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሚከተሉት በምዝገባ ሂደት ላይ የነበሩ ፓርቲዎች እውቅና መስጠቱን አስታውቋል።እውቅና የተሰጣቸው ፓርቲዎች ዝርዝር፦
1. አፋር ህዝባዊ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢህፍዴፓ)
2. አፋር ህዝብ ነጻነት ፓርቲ (አህነፓ)
3. ጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ጋዴፓ)
4. ሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ሞዴፓ)
5. ቁማ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቁህዴፓ)
6. ካፋ አረንጓዴ ፓርቲ (ካአፓ)
7. ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ)
8. ዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዎብን) እና
9. ሱማሌ አንድነት ፓርቲ (ሱአፓ) መሆናቸውን ቦርዱ በፌስ ቡክ ገጹ አስታውቋል።

ከ7.7 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃና ዶላር ተያዘ!
በጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ከምሽት 3፡00 ሰዓት ከብር 7.7 ሚሊዬን በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ሥር ውሏል፡፡በሰሌዳ ቁጥር 45074/14652 ኮንቴነር የጫነ ተሽከርካሪ ሀሰተኛ ሰነድ በመያዝ ወደ አዲስ አበባ በመጓጓዝ ላይ እያለ ደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ ሀርቡ ከተማ ላይ በክልሉ ፖሊስ አባላት እና በጉምሩክ ሰራተኞች ትብብር ሊያዝ ችሏል፡፡
በቁጥጥር ስር የዋሉት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ‹‹40 ጫማ›› መጠን ባለው ኮንቴነር ተጭነው የነበረ ሲሆን ብር 5.6 ሚሊዬን ግምታዊ ዋጋ ያላቸው መድሃኒቶች እና ብር 2,184,000 ግምታዊ ዋጋ ያለው ልባሽ ጨርቅ በድምሩ ብር 7,784,000 ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ናቸው።
በተመሳሳይ ዜና በቀን 30/03/2012 መሀመድ አብዱላሂ አብዲ የተባለ ግለሰብ በህገወጥ መንገድ ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጲያ 26,400 የአሜሪካን ዶላር /ሀያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ዶላር/በኢትዮጵያ ብር ዛሬ በዋለዉ የምንዛሪ ዋጋ 828,960 ብር/ ደብቆ ለማስገባት ሲሞክር በድሬዳዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በደወሌ መቆ/ጣቢያ ሰራተኞች ተይዟል፡፡ገንዘቡም ወደ ባንክ ገቢ የተደረገ ሲሆን ግለሰቡ ላይ በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ድሬዳዋ ዲቪዥን ተላልፎ ምርመራ ተጀምሮበታል፡፡
Via Ministry of Revenue

አነጋጋሪው የኤክሳይስ ታክስ ህግ ነገ ለፓርላማ ይቀርባል፡፡
በቢራ እና አልኮል ምርቶች ላይ እንዲሁም ወደ ሀገር በሚገቡ ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ ያስከትላል ተብሎ ሲያነጋገር የሰነበተው የኤክሳይስ ታክስ ህግ ነገ ለፓርላማ እንደሚቀርብ ታውቋል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት በሚኒስትሮች ምክርቤት ጸድቆ አዋጅ ሆኖ እንዲጸድቅ ለፓርላማ የተላከው ረቂቅ አዋጅ በነገው የፓርላማ ውሎ ለዝርዝር ዕይታ እና የህብረተሰብ ወይይት ወደ ቋሚ ኮሚቴ ይመራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ቀደምት ከሚባሉት የታክስ አይነቶች አንዱ ኤክሳይስ ታክስ ሲሆን ከጣልያን ወረራ በፊት አንስቶ በቅንጦት እቃዎች እንዲሁም በአልባሳት ላይ ሲጣል የቆየ ሲሆን አሁን ላይ በ19 የምርት አይነቶች ላይ ከ 10 እስከ 100 በመቶ ሲጣል ቆይቷል፡፡
የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ አፈፃፀምን አስመልክቶ ዛሬ ማለትም ታህሳስ 1 በፅ/ቤታቸው መግለጫ የሰጡት የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታው ዶ/ር እዮብ ተካልኝ በጉዳዩ ላይ በርካታ ጥያቄዎች የቀረቡላቸው ሲሆን ከእነሱም መካከል በረቂቅ አዋጁ ላይ በቂ ውይይት ከ ባለድርሻዎች ጋር አልተደረገም የሚል ቅሬታ መኖሩ ነበር፡፡
ሚኒስቴር ዲኤታው ሲመልሱ የተነሳውን ጥያቄ ተቃውመው በሀገሪቱ የህግ ማውጣት ሂደት ላይ እንደ አክሳይስ ታክሱ ላይ የተደረገውን ያህል ውይይት በሌሎች ላይ አልተደረገም ብለው ተከራክረዋል፡፡
Via ShegerTime Magazine

የአካባቢ ጥበቃ አክቲቪስት የሆነችው የ16 አመቷ ስዊድናዊት ግሬታ ተንበርግ የታይምስ መፅሄት Person of the Year ተብላ ተመርጣለች።
@YendTube @FikerAssefa
@YendTube @FikerAssefa
የዓለም ባንክ እና አይ ኤም ኤፍ ለሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ከሚያስፈልገው ገንዘብ ውስጥ 60 በመቶውን ለመሸፈን ተስማሙ!
የዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ኢትዮጵያ ለሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ከሚያስፈልጋት 10 ቢሊየን ዶላር ውስጥ ከግማሽ በላዩን ለመሸፈን ተስማሙ።ኢትዮጵያ ዘላቂነት ያለው እና የህዝብን ተጠቃሚነት ያረጋግጣል ያለችውን ሃገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በቅርቡ ይፋ ማድረጓ ይታወሳል።ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው የማክሮ ኢኮኖሚ ዘርፉን ማሻሻል፣ የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠርና የእዳ ጫናን መቀነስ እንዲሁም የወጪ እና ገቢ ንግዱን ሚዛን ማስጠበቅን የትኩረት አቅጣጫው አድርጓል።የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታው ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ ከማሻሻያ ስራዎቹ ጋር በተያያዘ በሰጡት አስተያየት፥ የፋይናንስ ስርአቱ የነበሩበትን ችግሮች ለማስተካከል የገንዘብ ፖሊሲው መሻሻሉን ተናግረዋል።
Via Fana

"የሐረማያ ዮንቨርስቲ ማስተማር ካቋረጠ ከአንድ ወር በላይ እንደሆነው የዩኒቨርስቲዉ ሠራተኛ እና ተማሪዎች አስታወቁ።" -የጀርመን ድምፅ ራዲዮ
«ከተመዘገብን አንስቶ እስካሁን በአግባቡ የተማርነው አንድ ሳምንት ቢሆን ነው» የሚለው አንድ የዩንቨርስቲው ተማሪ በዚሁ መስተጓጎል ምክንያት ወደ ቤተሰቦቹ ከተመለሰ አንድ ወር እንደሆነው ገልፆልናል። በስልክ ያነጋገርናቸዉ አንድ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የዩንቨርስቲው ባልደረባ እንደገለፁልን ደግሞ ትምህርት መልሶ ከተጀመረ 10 ቀን ገደማ ቢሆነውም ክፍል የሚገባው ተማሪ ቁጥር በጣም ውስን ነው። ለዚህም ባልደረባው በምክንያትነት የጠቀሱት አንዳንድ ተማሪዎች በድብቅ በሚያሰራጩት የማስፈራሪያ እና የአድማ ወረቀቶች ምክንያት ነው።
«በሐሮማያ ዩንቨርስቲ ግጭት ከተቀሰቀሰ አንስቶ የከፋ ችግር እንዳይከሰት ለመቆጣጠር ዩኒቨርስቲዉ ቅጥር ግቢ የሰፈረዉ የፌደራል ፖሊስ ቁጥር እንዲጨምር ተደርጓል ፣መከላከያም ገብቷል። የኦሮሚያ አድማ በታኝ እና የዩንቨርስቲው ጥበቃም በግቢው ይገኛሉ» ተብሏል። በሐረማያ ዮንቨርስቲ ግጭት የተጀመረው ጥቅምት መጨረሻ ወልዲያ ዩንቨርስቲ ሁለት ተማሪዎች ከመገደላቸው ጥቂት ቀናት አስቀድሞ ነው። የዩንቨርስቲው ተማሪዎች ሰልፍ በመውጣት ወለጋ ላይ የተደነገገዉ የኮማንድ ፖስት አገዛዝ ይነሳ፣ መከላከያ ሠራዊት ከኦሮሚያ ይውጣ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስልጣን ይውረዱ በሚል የፖለቲካ ጥያቄዎች አንስተው መንግሥት በአፋጣኝ ምላሽ ይስጠን ብለው ትምህርት አቁመው እንደነበር የዩንቨርስቲው ባልደረባ ተናግረዋል።
« በካፍቴሪያ ውስጥ ከዚህ ቀደም ከሚመገቡት 13000 ገደማ ተማሪዎች በአሁን ሰዓት 5000 ተማሪዎች ብቻ የሚገኙበት ሁኔታ አለ» ብለዋል የዮንቨርስቲው ባልደረባ። የተለያዩ የዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች አዲስ አበባ ውስጥ ትናንት እና ዛሬ በጋራ በተለያዩ ዮንቨርስቲዎች የተነሱትን ግጭቶች ተከትሎ በቀጣይ ሂደቱ ላይ በመምከር ላይ እንደሚገኙም ታውቋል።
ዘገባው የዶይቸ ቨሌ ነው

ነገ ታህሳስ 02 ቀን/2012 ከለሊቱ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ የጠቅላይ ሚንስትሩ የአቀባበል ሥነ ሥርዓት እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጀምሮ እስከ ብሔራዊ ቤተ-መንግስት ባሉት ግራና ቀኝ መንገዶች ላይ ተሸከርካሪን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ማቆም የተከለከለ ሲሆን ፡-አሽከርካሪዎችም አማራጭ መንገድ እንዲጠቀሙ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
📌 ከኡራኤል ቤ/ክርስቲያን ወደ መስቀል አደባባይ
📌 ከቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ወደ መስቀል አደባባይ
📌 ከቦሌ ኤድናሞል ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ
📌 ከብሔራዊ ቤተ-መንግስት ፤ ከፍል ውኃ ፤ ከለገሀር ፤ከካሳንችስ፤ከሳንጆሴፍ ትምህርት ቤት ፤ከስታዲየምንና ከሃራምቤ ሆቴል አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለጊዜው ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
አሽከርካሪዎች በሥራላይ ያሉ የፀጥታ አካላት የመንገድ መረጃን በመጠየቅና ሌሎች አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘት እና መረጃ ለመስጠት በስልክ ቁጥሮች ፡-
በ011-1-11- 01-11
፣011-5-52-40-77
፣011-5-52-63-02
፣011-5-52-63-03 ወይም በነጻ ስልክ መስመር 991 እና 987 መጠቀም እንደሚቻል ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
Via Addis Ababa Police Commission

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከዛሬ ጀምሮ ለተወሰኑ ቀናት በሁሉም ካንፓሶች ከምሽቱ 2:00 ብኃላ ከግቢው መውጣትም ሆነ መግባት የማይቻል መሆኑን በጥብቅ አሳስቧል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
ጥምቀት በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት ከዓለም የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶች አንዱ ሆኖ ተመዘገበ።
በኢትዮጵያ እና በኤርትራ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በየአመቱ ጥር 11 ቀን የሚከበረው ጥምቀት ኢትዮጵያ ካስመዘገበቻቸው የማይዳሰሱ የዓለም ባህላዊ ቅርሶች አራተኛው ሆኗል።ገዳ–የኦሮሞ የአስተዳደር ሥርዓት በ2016፣ ፊቼ ጨምበላላ–የሲዳማ የአዲስ አመት ክብረ በዓል በ2015 እንዲሁም የመስቀል በዓል በ2013 የማይዳሰሱ የዓለም ባህላዊ ቅርሶች ተብለው ተመዝግበዋል።
የዓለም የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶች ጥበቃ የበይነ መንግሥታት ጉባኤ ጥምቀትን ጨምሮ አምስት ባህላዊ ቅርሶችን የመዘገበው በካምቦዲያ ዋና ከተማ በመካሔድ ላይ በሚገኘው ስብሰባው ነው። ምዝገባው ነገም ይቀጥላል።ዛሬ ረቡዕ በነበረው ስብሰባ ባቻታ የተባለ የዶሚኒካን ሪፐብሊክ ማኅበረሰባዊ ሙዚቃ እና ዳንስ፣ አልፒኒዝም የተባለ በፈረንሳይ፣ ጣልያን እና ስዊትዘርላንድ ተራራ የመውጣት ማኅበረሰባዊ ባህል፣ በኢራን ዶታር የተባለ ማኅበረሰባዊ የሙዚቃ መሳሪያ የመስራት እና የመጫወት ባህል፣ በሜክሲኮ ውብ እና በአይነቱ ልዩ የሆነ ሸክላ የመስራት ጥበብ (artisanal talavera) ተመዝግበዋል።
Via Sheger Tribune