YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.91K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Forwarded from YeneTube
ማስታወቂያ💥

Buy and Order Quality clothes we will bring any orders from USA 🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸 in 8 to 15 days
for more info: @order_us1_inbox
0911073577 (abrsh)
👉tops 👚
👉Demin👖
👉Dress 👗
👉underwear 👙
👉T- shirt 👕
For more 👇🏾👇🏾👇🏾join the chanal
👉🏻 https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFeEeXHsZxR6KmWVxA

🏠location: medihanialem mall, 3rd floor , 306
Forwarded from YeneTube
Macbook Pro😍 15.4" 256GB SSD Intel Core i7 9th Gen 2.60 GHz 16GB Touch Bar - Space
Call now🏃‍♂+251912894363
Or via ZenachBrands1
Join our channel 😍😍@ZenachBrands for more items
Brand New Samsung A20 (2019)
32GB Internal Storage
3GB RAM
FOR MORE INFORMATION GO TO
https://m.dalibr.com/ProductDetailM.php?proid=11
"የህዳሴውን ግድብ በጥራት እና በተያዘው ዕቅድ መሠረት ለማጠናቀቅ ቁርጠኛ ነን'' ሳሊኒ

የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክቱን በጥራት እና በተያዘው ዕቅድ መሠረት ለማጠናቀቅ ቁርጠኛ እንደሆነ የግድቡን ግንባታ እያከናወነ ያለው ሳሊኒ ካምፓኒ አስታወቀ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከሳሊኒ ካምፓኒ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሚስተር ሳሊኒ ኢምፐርጂሊ ጋር ትናንት ሮም ጣሊያን ተገናኝተው ተወያይተዋል።ከምክትል ጠ/ሚር ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ውይይታቸው በታላቁ ህዳሴ ግንባታ ፕሮጀክት ላይ ያተኮረ ሲሆን፤ በፕሮጀክቱ ግንባታ ሂደት እና አፈፃፀም በተመለከተ ተነጋግረዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በበኩላቸው፤ መንግሥት ባወጣው የጠራ ዕቅድ እና መርህ መሠረት የፕሮጀክቱ ግንባታ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።ሚስተር ሳሊኒ ደግሞ በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ የሰጣቸውን ታሪካዊ ሃላፊነት በስኬት ለመወጣት ፕሮጀክቱን በጥራት እና በተያዘው ዕቅድ መሠረት ለማጠናቀቅ ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል።

ምንጭ፡-ኢ.ፕ.ድ
@YeneTube @FikerAssefa
በሦስት ወራት ውስጥ 113 የሳይበር ጥቃቶች እና ሙከራዎች ተመዘገቡ።

በተያዘው በጀት ዓመት 2012 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት 113 የሳይበር ጥቃቶችና ሙከራዎች መመዝገባቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ አስታወቀ። የበጀት ዓመቱ ከጀመረበት ሐምሌ 1/2011 እስከ መስከረም 30/2012 ድረስ 42 አጥፊ ሶፍትዌሮች፣ 29 በድረ ገፅ፣ 22 በመሰረተ ልማት ቅኝቶች፣ 13 ወደ አልተፈቀደ ሲስተም ዘልቆ መግባት እና 7 የሳይበር መሠረተ ልማቶችን ሥራ ማቋረጥ አይነት ጥቃቶች መከሰታቸውን ኤጀንሲው ይፋ አድርጓል።

ባለፉት ሦስት ወራት ጥቃቶች በአገሪቱ እንዳይሰነዘሩ የቅድመ መከላከል ሥራዎችን ኤጀንሲው ሲሰራ መቆየቱን እና ጥቃት የተሰነዘረባቸውንም ከዚህ ቀደም ወደ ነበሩበት ይዞታቸው የመመለስ ሥራም መሰራቱን በኤጀንሲው የብሔራዊ አደጋ ዝግጁነትና ምላሽ መስጫ ዲቪዥን ኃላፊ አብረሃም ገብረጻዲቅ ገልፀዋል።ኤጀንሲው በኢትዮጵያ ለተሰነዘሩ ጥቃቶች ምላሽ ሰጠ ሲሆን በተጨማሪም ጥቃት ለማድረስ በቅኝት ላይ በነበሩት ላይም የመቅጨት ስራ እንደተሰራም ታውቋል። የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ በአገሪቱ የሚሰነዘሩ የሳይበር ጥቃቶች ቅድመ የመከላከል እና ከተከሰቱ በኋላም አፋጣኝ ምላሾችን የሚሰጥ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ኤጀንሲው የአገሪቱን የኢንፎርሜሽን እና የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን መሰረተ-ልማቶችን ከጥቃት ለመከላከል የሚያስችል አቅም በመገንባት ብሔራዊ ጥቅሞችን የማስጠበቅ ተልዕኮውን በአግባቡ እየተወጣ ይገኛል፡፡

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa
የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ገመድ በመቀየር ላይ የነበረ ባለሙያ ድንገት ሃይል በመለቀቁ ህይወቱ አለፈ።

በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ገመድ በመቀየር ላይ የነበረ ባለሙያ ድንገት ሃይል በመለቀቁ ህይወቱ አለፈ፡፡በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 በተለምዶ ሾላ ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ ቀለመወርቅ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ከቀኑ 7 ሰአት ገደማ ነው አደጋው ያጋጠመው፡፡ባለሙያው ከፍተኛ የሃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ገመድ እየቀየረ በነበረበት ወቅት ድንገት ሃይል በመለቀቁ በኤሌክትሪክ አደጋው ህይወቱ ማለፉ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎቱን ለማሻሻልና የኤሌክትሪክ ሃይል መቆራረጥን ለመቀነስ ያረጁ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮችና ተሸካሚ ምሰሶዎችን በአዲስ መልክ የመቀየር ተግባር እያከናወነ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡ስራውንም በተቋራጭነት የቻይናው የኤሌክትሪክ ሃይል ኩባንያ ፓወር ቻይና በመስራት ላይ እንደሚገኝም ይታወቃል።ህይወቱ ያለፈው ወጣት ለፓወር ቻይና ተቀጥሮ የሚሰራ እንደሆነና የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ገመድ እየቀየረ ሳለ ከፍተኛ የሃይል ማስተላለፊያ መስመር በጥንቃቄ ጉድለት ሃይል ተለቆ ህይወቱ እንዳለፈ የአይን እማኞች ገልጸዋል።ህይወቱ ያለፈው ወጣት አስክሬኑ ለምርምራ ወደ ሆስፒታል ተልኳል፡፡

ምንጭ:ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
በሱማሌ ክልል ጥቃትን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ።

በሱማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የወጡ ሰልፈኞች በክልሉ ሲቲ ዞን ተፈፀመ ያሉትን ጥቃት እንደሚያወግዙ አስታወቁ። ሰልፉን አስመልክቶ አስተያየታቸውን የሰጡት የሱማሊ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ኃላፊ ሂቦ አህመድ፣ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ የተደረገበት ምክንያት በሱማሊ እና በአፋር ክልል አዋሳኝ ቦታዎች ላይ የተፈጠረው ግጭት ለማወገዝ ያለመ ነበር።በሰልፉ ላይ “በሁለቱ ህዝቦች ግጭት የሚፈጥሩ ሶስተኛ ወገን እጃቸውን ይሰብስቡ፣ የሱማሌ እና የአፋር ክልል ህዝብ ለተፈጠረው ችግር ዘላቂ መፍትሔ ያግኝ” የሚሉ መፈክሮች እንደነበሩ ተናግረዋል።

“ከለውጡ ጀምሮ እስካሁን በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ጥቃት እየተፈፀመም ነው” ብለዋል።“የአፋር እና ሱማሌ ወንድማማች ህዝቦች ነበሩ፤ አሁንም ይቀጥላሉ። አልፎ አልፎ ድሮም ግጭት ይከሰት ነበር፤ ይህን ለማባባስ የሚፈልጉ ጸረ ሰላም ኃይሎች ወገኖች አሉ” ሲሉ ኃላፊዋ ገልጸዋል። “ወንደማማችነት በአንዴ የሚቋረጥ አይደለም፣ ስለሆነም ሁለቱ ክልሎች ዘላቂ መፍትሔ ሲሰጡ እንደሚገባ የሱማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን ኃላፊ ሂቦ አህመድ ጠይቀዋል።

ምንጭ: EBC
@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ክልል ምክር ቤት ለሲዳማ ሕዝበ ውሳኔ ማስፈጸሚያ ሕጎችን አጽድቋል፡፡ የሕግ ማዕቀፉ በ168 ድጋፍ፣ በ55 ተቃውሞና 23 ድምጸ ተዓቅቦ ነው የጸደቀው፡፡ የሀዋሳ ከተማ ተጠሪነት ለአዲሱ ክልል ይሆናል፤ ደቡብ ክልል አማራጭ መቀመጫ እስኪያመቻች ለ2 ሀገራዊ ምርጫዎች ከተማዋን ከአዲሱ ክልል ጋር በጋራ ይጠቀማል፡፡ የቋሚና ተንቀሳቃሽ ሃብቶች ክፍፍል በሀገሪቱ የንብረት ክፍፍል ሕጎች አማካኝነት ይፈጸማል መባሉን DW ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ከኢህአዴግ ምክር ቤት ፅ/ቤት የተሰጠ መግለጫ!

ኢህአዴግን ከግንባርነት ወደ አንድ ህብረ ብሄራዊ ውህድ ፓርቲ የማሸጋገር ጉዳይ በ1996 ዓ.ም ከተካሄደው 5ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ጀምሮ በተከታታይ በተካሄዱት የድርጅቱ ጉባዔዎችና የተለያዩ ድርጅታዊ መድረኮች ሲነሳ የቆየ ጥያቄ እንደሆነ ይታወቃል። በሁሉም የኢህአዴግ መድረኮች በውህደቱ አስፈላጊነት ላይ ስምምነት እየተያዘበት የሄደ ሲሆን በየጉባዔዎቹ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ውህደቱን በጥናት ላይ ተመስርቶ ለመፈፀም የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች ሲደረጉ ቆይተዋል። ይልቁንም በቅርብ ጊዜያት በተካሄዱ ጉባዔዎች ይነሳ የነበረው ቁልፍ ችግር በአፈፃፀሙ ላይ የታየው ከፍተኛ መጓተት ነበር።

ሙሉ መግለጫ👇👇👇👇

https://telegra.ph/EPRDF-10-18

@YeneTube @FikerAssefa
ኢሕአዴግ በመግለጫው የውህደቱ አስፈላጊነት ብሎ የጠቆማቸው ነጥቦች:

📌 አሁን ያለው የግንባሩ አደረጃጀት አባል ድርጅቶች የጋራ አሰራርን በሚጥሱ ጊዜ የድርጅቱ የውስጥ ጥንካሬ አደጋ ላይ የሚወድቅ መሆኑ

📌 የግንባሩ የተጠናከረ ሀገራዊ አንድነት በመፍጠር አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ የመፍጠር ግቡን በተሟላ ሁኔታ ማሳካት አለመቻሉ

📌 አጋር ተብለው የሚጠሩ ድርጅቶችን ከውሳኔ ሰጪነት ያገለለና የሚመሯቸውን ክልሎችና ህዝቦች አቃፊ ባለመሆኑ

📌 ማንኛውም የሀገሪቱ ዜጋ በቀጥታ የድርጅቱ አባል ሆኖ መታገል የሚችልበትን እድል የሚሰጥ ያለመሆኑን እና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል አደረጃጀት እንዲኖር ታሳቢ በማድረግ እንደሆነ ተጠቁሟል።

@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል የገቡትን 25 ሺህ ዩሮ ለመልካም ወጣት አገልግሎት አስረከቡ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሄሰን የሰላም ሽልማት ያገኙትን 25 ሺህ ዩሮ ለመልካም ወጣት አገልግሎት ለመስጠት ቃል መግባታቸውን ተከትሎ፣ ዛሬ ከሰዓት ዮናታን አክሊሉን አግኝተው ቃል የገቡትን ገንዘብ አስረክበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በወርሀ ጳጉሜን ዮናታን አክሊሉ የኢትዮጵያ ወጣቶችን ለመደገፍ እየሠራ ላለው የላቀ ሥራ እውቅና መስጠታቸው የሚታወስ ነው።

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የደቡብ ክልል ምክርቤት ያጸደቀው የሕግ ማዕቀፍ:

በ168 ድጋፍ በ55 ተቃውሞ በ23 ድምፀ-ተዐቅቦ በጸደቀው በዚሁ የህግ ማዕቀፍ የደቡብ ክልል ወደፊት አማራጭ የአስተዳደር ከተማውን እስኪያመቻች ለ10 ዓመታት ከተማውን ከአዲሱ ክልል ጋር በጋራ እንደሚጠቀም ተገልጿል።በነባሩ ክልል ባለቤትነት የቆዩ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ሀብቶች ክፍፍልምአገሪቱ የንብረት ክፍፍል ህግ መሰረት ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል። የደቡብ ክልል ምክር ቤት ፣የሲዳማ ብሔር ፣ህዝበ ውሳኔን ለማስፈጸም ያስችላል ባለው እና ዛሬ ባጸደቀው የሕግ ማዕቀፍ የሀዋሳ ከተማ ተጠሪነቱ አዲስ ለሚቋቋመው ክልል እንደሚሆን ሰፍሯል። ያም ሆኖ በ168 ድጋፍ በ55 ተቃውሞ በ23 ድምፀ  ተዐቅቦ በጸደቀው በዚሁ የህግ ማዕቀፍ  ፣የደቡብ ክልል ወደፊት አማራጭ የአስተዳደር ከተማውን እስኪያመቻች ለ 10 ዓመታት ከተማውን ከአዲሱ ክልል ጋር በጋራ እንደሚጠቀም ተገልጿል።በነባሩ ክልል ባለቤትነት ስር የቆዩ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ሀብቶችን በተመለከተም በአገሪቱ የንብረት ክፍፍል ህግ መሰረት ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን DW ዘግቧል።

@YeneTube @FikerAssefa
በአፋርና በሱማሌ ክልል ህዝቦች መካከል የሚከሰቱ ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት መስማማታቸውን የሁለቱም ክልሎች አመራሮች ተናገሩ!

በአፋርና በሱማሌ ክልል ህዝቦች መካከል የሚከሰቱ ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት ከፌደራል የፀጥታ ሀይል ጋር በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን የሁለቱም ክልሎች አመራሮች በሰጡት የጋራ መግለጫ ተናግረዋል፡፡
ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከአፋርና ሱማሌ ክልል አመራሮች ጋር የመከላከያና የሰላም ሚኒስቴር አመራሮች በተገኙበት በፀጥታ ጉዳይ ውይይት አድርገዋል፡፡የሱማሌ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሀሰን እና የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ በጋራ በሰጡት መግለጫ የተከሰተውን ግጭት ለመፍታት የአመራሩ ቁርጠኝነት እንዳለ ተናግረዋል፡፡ችግሩን በህግ አግባብ እንዲፈታ በሀላፊነት ስሜት እንደሚንቀሳቀሱም የሁለቱም ክልሎች አመራሮች አስታውቀዋል፡፡

Via ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በአሜሪካ የኢኮኖሚ፣ የልማትና የኢነርጂ ምክትል ጸሃፊ ጋር ተወያዩ።

ክቡር የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በአሜሪካ የኢኮኖሚ፣ የልማት፣ የአካባቢና የኢነርጂ ዘርፍ ምክትል ጸሃፊ ኬት ክራች (Keith Krach) ጋር ዛሬ መስከረም 7 ቀን 2012 ዓ.ም ተወያይተዋል።ኢትዮጵያ እያካሄድ ያለውን ወቅታዊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ የለውጥ እርምጃዎች አስመልክቶ ክቡር ሚነስትሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።በአገር በቀል የኢኮኖሚ መርሆዎች በመነሳት የአሜሪካን ጨምሮ የውጭ ባለሃብቶችን ለመሳብ ሰፊ ስራዎች እየተካናወኑ መሆኑን ክቡር ሚኒስትሩ ገልጸዋል።ምክትል ጸሃፊ ኬት ክራች በበኩላቸው ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን ለውጥ እንደሚያደንቅ በመግለጽ የሁለቱ አገራት ግንኙነት የበለጠ እንዲጎለብት የአገራቸው ፍላጎት መሆኑን ተናግረዋል።

ምንጭ: በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@YeneTube @FikerAssefa
Brand New Samsung A10 (2019)
32GB
2GB RAM
Fast Face Unlock
FOR MORE INFORMATION GO TO 👉 https://m.dalibr.com/ProductDetailM.php?proid=10
Forwarded from YeneTube
ማስታወቂያ 💥

BLUE Brand Solutions

Blue Brand Solutions brought you the latest
📌Technologies(smartphones,Laptops)

📌 Men's and women's clothing👔

📌 Human hair 🙆‍♀

📌Musical instruments

📌Mens and Women's Perfume

Contact; @sherlockseller @Nah22
Call us
+251947896322&+251945421100

ቻናላቸውን ተቀላቅለሁ ይመልከቱ⬇️
https://tttttt.me/blueelec
Forwarded from YeneTube
ማስታወቂያ💥

Buy and Order Quality clothes we will bring any orders from USA 🇺🇸🇺🇸🇺🇸🇺🇸 in 8 to 15 days
for more info: @order_us1_inbox
0911073577 (abrsh)
👉tops 👚
👉Demin👖
👉Dress 👗
👉underwear 👙
👉T- shirt 👕
For more 👇🏾👇🏾👇🏾join the chanal
👉🏻 https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFeEeXHsZxR6KmWVxA

🏠location: medihanialem mall, 3rd floor , 306
Forwarded from YeneTube
Macbook Pro😍 15.4" 256GB SSD Intel Core i7 9th Gen 2.60 GHz 16GB Touch Bar - Space
Call now🏃‍♂+251912894363
Or via ZenachBrands1
Join our channel 😍😍@ZenachBrands for more items
ሲጠበቅ የነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ 'መደመር' መጽሀፍ በዛሬዉ ዕለት ጥቅምት 8 ቀን 2012 በሚሊኒየም አዳራሽ ስምንት ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ይመረቃል:: እንዲሁም ከ30 በላይ ከተሞች ላይ ይመረቃል:: ይህ መጽሀፍ ኢትዮጵያ በቀጣይ የምትከተለውን የኢኮኖሚ: ፖለቲካዊ እና የውጭ ግንኙነት አቅጣጫ የሚተነትንና ፋኖተ ካርታ የሚያስቀምጥ ነው።

#PMOEthiopia
@YeneTube @FikerAssefa
አዳዲስ መኪኖች ላይ የቀረጥ ቅናሽ ተደረገ።አለምአቀፉ የጉሙሩክ ድርጅት በየ5 አመቱ የሚያሻሽለውን መጽሐፍ መሠረት በማድረግ ከሁለት አመት በፊት ተከልሶ መጠናቀቅ ይገባው የነበረው የታሪፍ መጽሐፍ በማዘጋጀት ያፀደቀው የገንዘብ ሚኒስቴር በአዳዲስ መኪኖች ላይ የ5% ቅናሽ አድርጓል።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa