YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ሕትመት ሊያቆም እንደሚችል ማስጠንቀቁን አዲስ ዘመን አስነብቧል፡፡ በ2 ወራት ውስት ጋዜጦችንና ፈተናዎችን ለማተም እቸገራለሁ ብሏል፡፡ ምክንያቱ ለከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት መጋለጡ ነው፡፡ ከዐመት በፊት እንዲለቀቅለት የጠየቀውን የውጭ ምንዛሬ እስካሁን አላገኘም፡፡ መለዋወጫዎችን፣ አዳዲስ ማሽኖችንና 90 በመቶ የሕትመት ግብዓቶችን በውጭ ምንዛሬ ነው የሚገዛው፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
ቱርክ ወታደሮችዋን ሰሜን ሶሪያ ከማስፈር እንድትቆጠብ ኢራን ጠየቀች።

የኢራን ፕሬዝዳንት ሃሰን ሩሀኒ ዛሬ ለቱርክ ባስተላለፉት ጥሪ ቱርክ ውሳኔዋን እንደገና እንድታጤን ጥሪ አቅርበዋል። ቱርክ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች ለቀው በወጡበት በሰሜን ሶሪያ ወታደሮቿን ለማስፈር እየተንቀሳቀሰች ነው። አንድ የቱርክ ባለሥልጣን እንዳሉት የቱርክ ኃይሎች እና ሶሪያ የሚገኙ አማጺያን አጋሮቻቸው በቅርቡ ወደ ሶሪያ ዘልቀው ይገባሉ ብለዋል። የኢራን የምድር ጦርም ከቱርክ ጋር በሚያዋስነው ሰሜን ምዕራብ የሃገሪቱ ክፍል እየዘለቀ ነው። የሶሪያው ፕሬዝዳንት የበሽር አልአሳድ የቅርብ አጋር የሆነችው ኢራን ቱርክ የሶሪያን ድንበር እድታከብር ከዚሁ ጋር ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ ሶሪያ በሕገ ወጥ መንገድ የሚገኙ የምትላቸው የውጭ ኃይላት ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ በተደጋጋሚ ስትጠይቅ ቆይታለች። ቱርክ እንደምትለው በሰሜን ምሥራቅ ሶሪያ ደህንነቱ የተጠበቀ ቃጣና ለመፍጠር ትሻለች። ዓላማዋም በሚሊዪኖች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ወደ አካባቢው መመለስ መሆኑን አስታውቃለች።

ምንጭ:ዶይቼ ወሌ
@YeneTube @FikerAssefa
የደ/ብ/ብ/ህ/ክልል በመጪው ህዳር መጀመሪያ ላይ ለሚካሄደው የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ዝግጅት ላይ መሆኑን ዐስታወቀ።

ክልሉ የሲዳማ ብሔር የህዝበ ውሳኔ ማስፈጸሚያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዳነ ገበየሁ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ህዳር 3 ቀን፤ 2012 ዓም ከሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ በፊት በህዝበ ውሳኔው ወቅት እና ከህዝበ ውሳኔው በኋላ የሚከናወኑ ተግባራት ተለይተዋል። ኃላፊው እንዳሉት የክልሉ መንግሥት እና የሲዳማ ዞን መስተዳድር በህዝበ ውሳኔው የሁሉንም አካላት ጥቅም እና ፍላጎት ማጣጣም የሚያስችሉ አስተዳደራዊ እና የሕግ ማዕቀፎችን እያዘጋጁ ነው። በህዝበ ውሳኔው ሲዳማ ራሱን ችሎ የሚደራጅ ከሆነ የጋራ የሀብት ክፍፍል እና የሥልጣን ርክክብን እንዴት እንደሚሆን ተጠይቀውም መልስ ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ ዝግጅቱ ከክልሉ መንግሥት እና ከሲዳማ ዞን መስተዳደር በኩል ተጓቷል ሲል ዐስታውቋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
Audio
በማዕከላዊ ጎንደር በቅማንት ማኅበረሰብና በአማራ ማኅበረሰብ መካከል ደም እያፋሰሰ ያለውን ችግር የፈጠሩ ናቸው የተባሉ ኃይሎች በህግ መጠየቅ አለባቸው ሲሉ የክልሉ ፕሬዚዳንት የህግ አማካሪ አስታወቁ፡፡አማራ ክልላዊ መንግሥት ችግሩን ለመፍታት አውንታዊ ርምጃዎች ወስዷል ቢባልም ዳተኛም እንደሆነም ተጠቆመ፡፡ የፌዴራል መንግሥቱ አስቸኳይ ህጋዊ ዕርምጃ አንዲወስድም ተጠይቋል፡፡

⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Via VOA
@YeneTube @FikerAssefa
እንደምን አደርሽ ኢትዮጵያ። ዛሬ የመደመር እሳቤ ማሳያ የሆነው የአንድነት ፓርክ ምረቃ ሲሆን፣ ያለፉትን ታሪካዊና ማህበራዊ እሴቶቻችን እየዘከርንና ለመጪው ትውልድ እያጎለበትን እንድንሄድ ተጋብዘናል። አንድነት ፓርክ ለጋራ ግባችን በአንድነት ቆመን የፍፃሜውን ምዕራፍ ዘመን ተሻጋሪ በሆነ የሕብረት አቅም ማጠናቀቅ የመቻላችን ተምሳሌት ነው።
__________________________________
የብሔራዊ ቤተ መንግስትን ለመጎብኘት የሚያስችልዎትን ትኬት ሊንኩን በመጫን ማግኘት ይችላሉ።

Book your ticket here the link below.

https://ticket.ethiotelecom.et/unitypark/ticket/
_____________________________

Via :-PMOffice
@YeneTube @Fikerassefa
የአንድነት ፓርክ የምረቃ ፕሮግራም ላይ የሚገኙ የሀገራት መሪዎች አዲስ አበባ እየገቡ ነው!

አዲሱ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሀምዶክ ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን የሶማልያ እና የኬንያ መሪዎችን ጨምሮ ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት መሪዎችም ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Via EPA/Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
አዲ የኦሮሚያ አርሶ አደሮች ፌዴሬሽን በገላን ከተማ ያስገነባው የዱቄት ፋብሪካ ተመረቀ!

የዱቄት ፋብሪካውም የኦሮሚያ ክልል መክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የአርሶ አደሮች ተወካዮች በተገኙበት ነው የተመረቀው።የኦሮሚያ የአርሶ አደሮች የህብረት ስራ ዩኒየን ፌዴሬሽን በገላን ከተማ ያስገነባው ፋብሪካው በቀን ከ1 ሺህ እስከ 1 ሺህ 500 ኩንታል የቦቆሎ ዱቄት የሚያዘጋጅ መሆኑን የኦሮሚያ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።በ42 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው ፋብሪካው በቆሎን በመፍጨት እና እሴት በመጨመር ለገበያ የሚያቀርብ መሆኑም ነው የተገለፀው።

ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
የተማሪዎች የምገባ መርሃ ግብር ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ወደ ስራ ይገባል!

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 300 ሽሕ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለው የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ ግብር ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል። ከተማ አስተዳደሩ እንዳስታወቀው የተማሪዎች ምገባ በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች ቀደም ብሎ የተጀመረ ሲሆን ከመጪው ሳምንት ጀምሮ ሙሉ በሙሉ እንደሚጀምር ገልጿል።ከተማሪዎች ምገባ በተጨማሪ ለ2012 የትምህርት ዘመን ደንብ ልብስ እና የመማሪያ ቁሳቁስ ከ600ሽሕ በላይ ተማሪዎች የደንብ ልብስ እና የመማሪያ ቁሳቁስ ማከፋፈሉ የሚታወስ ነው።

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
የዘንድሮው ብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን ጥቅምት 3 ይከበራል፡፡

12ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል በአገር አቀፍ ደረጃ “ሰንደቅ አላማችን የብዝሀነታችን ድምር ውጤትና የአንድነታችን ምሰሶ ነው” በሚል መሪ ቃል ጥቅምት 3 ቀን 2012 ዓ.ም ይከበራል፡፡ቀኑ ሲከበር መንግስት የሚተገብራቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር እንቅስቃሴዎች፣ ስለ ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶች፣ ስለ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችና በፌዴራል ስርዓቱ ውስጥ ስለህዝቦች ዴሞክራሲያዊ አንድነት የጋራ መግባባት በሚፈጥር መልኩ በመወያየት እንደሚሆንም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል፡፡በሕገ-መንግሥቱም ሆነ በአዋጆች ዕውቅና ያገኘውን ሰንደቅ ዓላማ ማክበርና በጋራ ከፍ አድርጎ ማውለብለብ ተገቢ እንደሆነም ምክር ቤቱ አሳስቧል፡፡የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሰንደቅ ዓላማ የአገራችን ሉዓላዊነትና የሕዝቦች በመፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ አንድነት መገለጫ ነው፡፡

-የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
የህዝበ ውሳኔ አስፈጻሚዎች ምልመላ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ህዳር 2012 ዓ.ም ለሚያካሂው የሲዳማ የክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ 6000 የሚሆኑ የህዝበ ውሳኔ አስፈጻሚዎችን በበጎ ፍቃደኝነነት ለአንድ ወር ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውን ና ኮፒ በመያዝ ንፋስ ስልክ ቡና ቦርድ ፊትለፊት በሚገኘው የቦርዱ ማሰልጠኛ ማእከል በአካል በመገኘት ከመስከረም 24 ቀን 2012 ጀምሮ በስራ ሰአት እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

• አመልካቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

• የማንኛውም የፓለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ያልሆነች

• በትምህርት ዝግጅታቸው በማንኛውም የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላት/ ያለው

• እድሜ ከ20- 45 አማት የሆነች/የሆነ
• በገጠር ቀበሌዎች ተንቀሳቅሰው መስራት የሚችሉ

• የስራ ልምድ አይጠይቅም. ሆኖም በምርጫ አፈጻጸም ዙሪያ ወይም በተለያየ ማህበራዊ አገልግሎቶች የተሳተፉ አመልካቶች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡
ቦርዱ በስራ የሚሳልፉትን ጊዜ አበል የሚከፍል ሲሆን በተጨማሪም በህዝበ ውሳኔው ላይ በበጎ ፈቃደኝነት ለተሳተፉ አስጻሚዎች የተሳትፎና የእውቅና ምስክር ወረቀት ይሰጣል፡፡

Via:- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
@YeneTube @Fikerassefa
ኢትዮ- ጅቡቲ ምድር ባቡር ከአዲስ አበባ ቀጥታ ጅቡቲ የነበረውን የጉዞ መስመር ሊቀይር ነው!

በሳምንት ሁለት ቀናት ከአዲስ አበባ ጅቡቲ የሚመላለሰውን የባቡር ትራንስፖርት በማስቀረት አዲስ የጉዞ መስመር ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅት መጨረሱን የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ጥላሁን ሳርካ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
አንድነት ፓርክ ተመረቀ!

በታላቁ ቤተመንግስት የተሰራው የአንድነት ፓርክ የምስራቅ አፍሪካ መሪዎች በተገኙበት ተመርቆ ተከፈተ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ጥቂት መረጃ ስለ አንድነት ፓርክ!

ከትናንት በስቲያ ፓርኩን እና በግቢው ውስጥ የተከናወኑ መጠነ ሰፊ እድሳቶችን የውጭ ሚድያ ጋዜጠኞች ጎብኝተን ነበር። ከጉብኝቱ የወሰድኳቸውን የተወሰኑ መረጃዎች ላካፍላችሁ:

📌 አጠቃላይ የፓርኩ ስራ፣ የግቢው አጥር እና አዳዲስ ህንፃዎች ግንባታ፣ የድሮዎቹ ህንፃዎች እድሳት እና ጥገና በግምት 5 ቢልዮን ብር ገደማ ፈጅቷል።

📌 ለፓርኪንግ የሚሆን ሌላ ሰፊ ግንባታ ከግቢው ውጪ ተጀምሯል። ይህም ተጨማሪ 1.5 ቢልዮን ብር ይፈጃል ተብሎ ተገምቷል

📌 ሙሉ ወጪውን የሸፈነው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግስት ነው

📌 ዘጠኝ ወር የፈጀው ግንባታ እየተከናወነ ባለበት የቁፋሮ ስራ ወቅት የሰው አፅምን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ተሽከርካሪዎች ተቀብረው ተገኝተዋል።

📌 የቀድሞዎቹ ጠ/ሚሮች መለስ ዜናዊ እና ሀይለማርያም ደሳለኝ ይኖሩበት የነበረው ህንፃ የቤት እቃዎች ገብተውለት የእንግዳ መሪዎች ማረፊያ እንዲሆን ታስቧል።

📌 አንዳንድ ግንባታዎች ጥቃቅን ስራ ይቀራቸዋል፣ በተለይ የአንበሳ እና ሌሎች እንስሳት ማረፊያ ቦታ። የአንበሳ ስፍራው "ጥቁር አንበሳ" የተባለው ልዩ አንበሳ መኖርያ ይሆናል። በአጠቃላይ 300 ገደማ እንስሳቶች የፓርኩ የእንስሳት ክፍል ውስጥ ሆነው ለህዝብ እይታ ይውላሉ።

Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
የግብጽ ፓርላማ ለሕዳሴው ግድብ ጊዜያዊ ኮሚቴ እንደሚያቋቁም ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡

ኮሚቴው መንግሥት ስለ ግድቡ ያቀረበለትን አቋም ይመረምራል፡፡ ግብጽ በአባይ ወንዝ ላይ ጥቅሟን ለማስጠበቅ መወሰድ ያለባቸውን ርምጃዎች ይፈትሻል፡፡ ከውጭ፣ አፍሪካ ጉዳዮች፣ መከላከያና ብሄራዊ ደኅንነት የሚውጣጣውን ኮሚቴ፣ የፓርላማው ምክትል አፈ ጉባዔ ይመሩታል፡፡ ግብጽ የሦስትዮሹን Declaration of Principles ስምምነት ተንተርሳ፣ ገለልተኛ አሸማጋይ እንዲገባ አቋም እንደያዘች ጠቅላይ ሚንስትሩ ትናንት ለፓርላማው ገልጸዋል፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በሐምሌ ኤርትራን ሲጎበኙ፣ የውጭ ሚንስቴር ምንም መረጃ እንዳልነበረው ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ባለሥልጣኖቹ ጉብኝቱን እንደ ተራው ዜጋ ከኤርትራ ዜና ምንጮችና ከማኅበራዊ ሜዲያ ነው የሰሙት፡፡ የተቋሙ መገለል፣ የሀገሪቱን ብሄራዊ ጥቅም አደጋ ላይ ሊልው ይችላል- ብለዋል ስማቸው ያልተጠቀሰ ባለሥልጣን ተናግረዋል፡፡ የዐለም ዐቀፉ ግጭት ተቋም (አይሲጄ) የአፍሪካ ሃላፊ በበኩላቸው፣ ዐቢይ የለውጥ አጀንዳቸውን በተቋማት ካልመሩት መሠረት ሊይዝላቸው አይችልም ሲሉ ተችተዋል፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
በመጪው እሁድ በአዲስ አበባ ይደረጋል ለተባለው ሰልፍ ዝግጅት መጨረሱን ‹‹የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት›› ተናገረ፡፡

የከተማዋ አስተዳደር በበኩሉ ጥያቄው ደርሶኛል፣ ለፀጥታና ለደኅንነት መዋቅሩም አሳውቄያለሁ ሲል ለአሐዱ ቴሌቪዥን አረጋግጧል፡፡የአዲስ አበባ ሕዝብ በርካታ የፖለቲካ፣ ምጣኔ ሀብትና ማኅበራዊ ጥያቄዎች አሉት፤ እነዚህንም ጥያቄዎች ይዤ እሰራለሁ ሲል መጋቢት 1/2011 የተቋቋመው ባለአደራ ምክር ቤቱ ለጥቅምት 2/2012 የጠራሁት ሰልፍ እውቅና አግኝቷል ብሏል፡፡በመስቀል አደባባይ ይደረጋል በተባለው ሰልፍም የዴሞክራሲና የሰላም መልዕክቶች ይተላለፋሉ ሲል የባለአደራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ እስክንድር ነጋ ተናግሯል፡፡

በሰልፉ የሚሳተፉ የመዲናዋ ነዋሪዎችም ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ የፖለቲካ፣ ምጣኔ ሃብትና ማኅበራዊ ጥያቄዎቻቸውን እንዲያቀረቡ ባልደራሱ የአደራ ጥሪ አቅርቧል፡፡የአደባባይ ሰልፍና ኹነቶች ላይ የተለያዩ አርማና ምልክቶች መታየትን ተከትሎ አሐዱ ባልደራሱን የጠየቀ ሲሆን፣ ‹‹ሰልፈኞቹን ይሔን ይዛችሁ ውጡ ያንን ተው ማለት አልችልም፤ ይልቁንም የመሰላቸውንና ይወክለኛል ያሉትን አርማ መያዝ ይችላሉ የሚል አቋም አለኝ›› ብሏል፡፡ዋናው ግን ሀሳብን በሰላማዊ መንገድ መግለፅና የሌላውን ማክበር ነው ሲልም አፅንኦት ሰጥቷል፡፡

አሐዱ ስለ ሰልፉ እውቅና የጠየቃቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሰክሬተሪ ፌቨን ተሾመ ጥያቄው ለአስተዳደሩ እንደደረሰውና ለፌደራልና ለከተማው የደኅነትና የፀጥታ መዋቅር ማሳወቁን ተናግረዋል፡፡ባልደራሱ ከሚያነሳቸው ጥያቄዎች መካከል የአዲስ አበባ ምክር ቤትና የካቢኔ ሥልጣን ዘመን አልቋል፣ ስለዚህም የባለ አደራ አስተዳደር መመስረት አለበት የሚለው ይገኝበታል፡፡ በተጓዳኝ የከተማዋ ነዋሪ መብቶች አልተከበሩም አስተዳዳሩም ለነዋሪው ትክክለኛ ወካይ አልሆነም ሲልም ይወቅሳል፡፡የከተማ አስተዳደሩ በአንፃሩ የከተማዋን ሕዝብ ኑሮ ለማሻሻል እየሰራ እንደሆነ በመግለፅ የባለአደራ ምክር ቤትን እንደማይቀበል ምላሽ ሲሰጥና ሲያስጠነቅቅ ከርሟል፡፡

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa