YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ኢ/ር ታከለ ኡማ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የታክሲ አገልግሎት (ኤታስ) ከሚሰጡ 13 ተቋማት ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

በዋነኛነት የከተማ አስተዳደሩ በቅርቡ የኤታስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲከተሉት ባወጣው መመሪያ ዙሪያ እና የትራንስፖርት ሴክተሩን በዘላቂነት ዘመናዊ ለማድረግ በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከኤታስ እና ሶፍትዌር ማበልፀጊያ ተቋማት ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡የኤታስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማቱ በከተማ አስተዳደሩ ረቅቆ በቅርቡ ይፋ የሆነው መመሪያ ቴክኖሎጂው ላይ ምንም ተፅዕኖ እንደሌለው ተናግረዋል፡፡

ተቋማቱ ህጉን እንደማይቃወሙ እና ለተፈፃሚነቱ ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመቆም እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡ኢ/ር ታከለ ኡማ በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የትራንስፖርት አሰጣጥ በከተማዋ ውስጥ እንዲስፋፋ ፍላጎቱ ነው ብለዋል፡፡ በከተማዋ ውስጥ ያለውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ የሚረዱ ሌሎች ተጨማሪ ቴክኖሎጂዎችን ለሚያመጡ በራቸው ክፍት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይነትም የከተማ አስተዳደሩ የተቀላጠፈ እና ህዝቡን የሚጠቅም መመሪያ ቀርጾ በከተማዋ ውስጥ ያለውን የትራንስፖርት እጥረት ለመቅረፍ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡በመጨረሻም የኤታስ ተቋሞቹ በከተማዋ ውስጥ የታክሲ አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉ ተሽከርካሪዎች ያረጁ በመሆናቸው የከተማ አስተዳደሩ ተሽከርካሪዎቹን በአዲስ በመተካቱ ሂደት ከጎናቸው እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Via Mayor Office
@YeneTube @FikerAssefa
የኬንያ መንግሥት አውሮፕላን ቅዳሜለት የሱማሊያን እገዳ ጥሶ በቀጥታ በሱማሊያዋ ኪሲማዩ ወደብ በማረፉ፣ የሁለቱ ሀገሮች ፍጥጫ እንደገና ተካሯል፡፡ የሱማሊያ ዜና ምንጭ ሒራን ድረ ገጽ እንደዘገበው፣ ሞቃዲሾ ለተመድ ዐለም ዐቀፍ ሲቪል አቬሽን ባለሥልጣን ክስ አቅርባለች፡፡ ወደ ኪሲማዩ የሚደረግ የውጭ በረራ ሁሉ በሞቃዲሾ በኩል እንዲሆን ሱማሊያ ባለፈው ወር ነበር ያዘዘችው፡፡ መንግሥት ከጁባላንድ ራስ ገዝ ጋር ውዝግብ ውስጥ ከገባ ቆይቷል፡፡

Via Wazema Radio
@YeneTube @FikerAssefa
⬆️
#FakeNewsAlert

ዛሬ መስከረም 27 ቀን 2012 ዓ.ም “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና የፓለቲካ ፓርቲዎች ሊያደርጉት የነበረው ውይይት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ” በሚል ርእስ በኢትዮጵያ ብርድካስቲንግ ኮርፓሬሽን ፌስቡክ ገጽ የተዘገበው ዜና የተሳሳተ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለማሳወቅ ይወዳል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዛሬ እለት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ያደረገው ምንም አይነት ውይይትም ሆነ ድርድር ያላደረገ ሲሆን የኢቢሲም ሆነ የኢቢሲን ዜና መሰረት በማድረግ የዘገቡ ሌሎች ሚዲያዎች ዜናዎችን ከማሰራጨታቸው በፊት ማጣራት እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያሳስባል፡፡ ቦርዱ ማንኛውንም የመረጃ ጥያቄዎች ለመመለስ ዝግጁ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ ይወዳል፡፡

Souce: የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
@YeneTube @FikerAssefa
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በእስካሁኑ የግንባታ ስራው 99 ቢሊየን ብር ወጥቶበታል ተባለ

ቀሪው የግድቡ ስራ 40 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ወጪእንደሚጠይቅ ተነግሯል፡፡ ከሕዝብ የተሰበሰበው አጠቃላይ የገንዘብ መጠን 12 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር መድረሱንም ሰምተናል፡፡

የግድቡ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት የግድቡን አጠቃላይ ሁኔታ አስመልክቶ ከሚመለከታቸው ጋር ውይይት ሲያደርግ እንደሰማነው ባለፈው አመት ብቻ 970 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማሰባሰብ ተችሏል ተብሏል፡፡

ባለፈው አመት ሀገሪቱ የነበረችበት አጠቃላይ ሁኔታ ህዝባዊ ተሳትፎውን ያቀዘቀዘ ቢሆንም የተሰበሰበው ገንዘብ ግን ከፍተኛ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አጠቃላይ የግንባታ ስራው 68.5 በመቶ ደርሷል የተነሳ ሲሆን የሲቪል ስራዎች 84.5 በመቶ፣ የኤሌክትሮሜካኒካል ስራዎች 25 በመቶ፣ የብረታ ብረት ስራዎች ደግሞ 15 በመቶ አፈፃፀም ላይ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

Via:- shegerFm
@YeneTube @FikerAssefa
ከሴኔጋል አዲስ አበባ ይበር የነበረው ንብረትነቱም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው የበረራ ቁጥር ET-908 አውሮፕላን ባጋጠመው የቴክኒክ እክል ምክንያት እዛው ሴኔጋል ለማረፍ መገደዱ ተሰማ።

B767-300 አውሮፕላን በመደበኛ በረራ ከሴኔጋል ዲአስ በማሊ ባማኮ አድርጎ አዲስ አበባ ለመብረር ጉዞ ጀምሮ ነበር ተብሏል።
የበረራ ቁጥር ET-908 ባጋጠመው የቴክኒክ እክል ምክንያት ወደተነሳበት ኤርፖርት ተመልሶ ለማረፍ መገደዱንም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኮምንኬሽን ዳይሬክተር አቶ አስራት በጋሻው ለሸገር ነግረዋል።

በአውሮፕላኑ የነበሩ መንገደኞችም በሌላ አውሮፕላን ተሳፍረው ጉዞዋቸውን ቀጥለዋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድም ለተፈጠረው መጉላላት መንገደኞቹን ይቅርታ ጠይቋል።
አውሮፕላኑ ስላጋጠመው የቴክኒክ እክልም እንዲህም ነው እንዲያም ነው የተባለ ነገር የለም።

Via:- Shager FM
@YeneTube @Fikerassefa
“ከመጣንበት መንገድ በላይ ወደፊት አብረን የምንጓዘው ጉዞ ረጅም ነው”:- የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ODP) የአገሪቱን ህዝቦች የእኩልነት፣ የፍትሕና እና የነጻነት ጥያቄዎችን ለመመለስ፣ ብሎም የሕዝቦችን የመልማትና የመበልጸግ ፍላጎት ከግብ ለማድረስ ከእህት ድርጅቶች እና ከአጋሮቹ ጋር ኅብረት ፈጥሮ ሲታገል፣ በጋራ መሥዋዕትነት ሲከፍል መቆየቱንና አሁንም በመታገል ላይ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡

https://telegra.ph/ODP-10-09
በዶሃ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተካፈለው ልኡካን ቡድን አቀባበል ተደረገለት::

ለ17ኛ ጊዜ በኳታር ዶሃ ከመስከረም 16-25/2012ዓ.ም. በተካሄደው የዓለም አትሌቲክሰ ሻምፒዮና ላይ ተካፍሎ በሁለት ወርቅ፣ አምስት ብር እና አንድ ነሀስ በድምሩ በስምንት ሜዳልያ ከዓለም 5ኛ ከአፍሪካ 2ኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀው የአትሌቲክሰ ቡድናችን ዛሬ ከማለዳው 1፡30 ላይ አዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት ሲደርስ የኢ.ፌ.ድ.ሪ. ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚንስትር ክብርት ዶ/ር ሂሩት ካሳው፣ የኢ.ፌ.ድ.ሪ. ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሀብታሙ ሲሳይ፣ የኢ.ፌ.ድ.ሪ. ስፖርት ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ክቡር አቶ ጌታቸው ባልቻ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ክቡር ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽን ም/ፕሬዝዳንት አትሌት ገ/እግዚአብሄር ገ/ማርያም እንዲሁም የአትሌቲክስ የሙያ ማህበራትና ክለብ አመራሮች ተገኝተው የአበባ አሰጣጥና እንኳን በድል ተመለሳችሁ ያሉ ሲሆን በቀጣይ በሚዘጋጅ መርሃ ግብር ለቡድኑ አቀባበልና ሽልማት የሚደረግለት ይሆናል፡፡

Via EAF
@YeneTube @FikerAssefa
ሸጎሌ የአውቶቡስ ዴፖን ሊመረቅ ነው!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ሸጎሌ የአውቶቡስ ዴፖን ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ.ም. በይፋ ሊያስመርቅ ነው::በምረቃ ስነ ስርዓቱ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማን ጨምሮ ሌሎች የአዲስ አበባና የፌደራል ከፍተኛ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ፡፡ዴፖው በሃይለ ስላሴ ዘመነ - መንግስት ከእንጨትና ከቆርቆሮ ተዘጋጅቶ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ ሲሆን፥ በአሁኑ ወቅት በዘመናዊ መልኩ ተገንብቶ በመዲናዋ የአውቶቡስ ዴፖ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ለመክፈት ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

ሸጎሌ የአውቶቡስ ዴፖ በመሬት ላይ ብቻ የሚጠናቀቅ ሆኖ በአንድ ጊዜ ከ250 እስከ 300 አውቶቡሶችን በተመቻቸ ሁኔታ የማቆም አቅም አለው። 52 ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ይህ ዴፖ ለግንባታው ሙሉ በሙሉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድሩ የሚሸፈን 555 ሚሊየን ብር በጀት ወጪ ተደርጎበታል፡፡ ዴፖው አዉቶቡሶቹ በአንድ ማዕከል ሌሎች አገልግሎቶችን ማግኘት በሚያስችል በዘመናዊ መንገድ የተገነባ ነው፡፡ዘመናዊ ጋራዥን ጨምሮ ደህንነትና ንጽህናቸዉ የሚጠበቅበትና ከአንድ ማዕከል ሥምሪት መስጠት በሚያስችል መልኩ ተገንብቷል፡፡

ምንጭ: ኢፕድ
@YeneTube @FikerAssefa
በጭልጋ ወረዳ 45 የአማራ ልዩ ኃይል ሕይወት አለፈ!!

በማዕከላዊ ጎንደር ጭልጋ ወረዳ ከአይከል ከተማ፣ ጓንግ እና ቡሆና ድረስ ከመስከረም 17/2012 ጀምሮ ለአምስት ቀናት የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በአካባቢው የነበሩ ታጣቂዎች በከፈቱት ድንገተኛ ተኩስ ሰላም በማስከበር ላይ የሚገኙ 45 የአማራ ክልል የልዩ ኃይል አባላትን መግደላቸውን የአዲስ ማለዳ ምንጮች አረጋገጡ።

ማክሰኞ መስከረም 20/2012 በባህርዳር በሚገኘው ጽሕፈት ቤታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የተናገሩት የአማራ ክልል የሰላምና ሕዝብ ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ አገኘሁ ተሻገር፣ የፀጥታ አካላት ወደ ማደሪያ ካምፓቸው ሲገቡ ከበባ እንደተፈፀመባቸው እና ‹‹ከደረሰባቸው ውርጅብኝ›› ራሳቸውን መከላከላቸውን ይናገራሉ።

ተጨማሪ⬇️
https://telegra.ph/Amhara-10-09

@YeneTube @Fikerassefa
በአዲስ አበባና አካባቢዋ ለልማት ሲባል ከቦታቸዉ ለተነሱ አርሶ አደሮች 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ምትክ እንዲያገኙ የተወሰነው ከወራት በፊት ነው፤ ውሳኔው አዲስ አይደልም ሲል የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ገለፀ።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂኒየር ደሳለኝ ተረፈ ለዶቼ ቬለ (DW) እንደገለፁት በአዲስ አበባ ዳርቻዎች ይኖሩ የነበሩና ከቦታቸዉ የተነሱ አርሶ አደሮች በ20 / 80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መርሃ ግብር ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተወሰነው ታህሳስ 24 ቀን፣ 2011 ዓ.ም ነው።ዉሳኔዉ በከተማዉ ካቢኔ መሰሰጠቱን የገለፁት ኃላፊዉ «ይህ ውሳኔ ደግሞ ግንቦት 2011 ዓ.ም ተግባራዊ ተደርጓል። እንደ አዲስ የሚያወዛግብ ነገር አይደለም » ሲሉ ገልፀዋል። ይሁንና ይህ ውሳኔ የሚመለከታቸው ሰዎች ቁጥር ምን ያህል ነው? በሚል ከDW ለተነሳላቸዉ ጥያቄ ኃላፊው፤ «ማህበራዊ መገናኛዎች ላይ የተምታታ ቁጥር አለ፣ ትክክለኛ ቁጥር የለም ቁጥሩንም አልገልፅም » የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ውሳኔው መጀመርያውኑም እጣ ከመውጣቱ በፊት የተወሰነ ነው ያሉት ኃላፊው አሰራሩ የነበረ እና ምትክ 20 / 80 ቤቱ በሁሉም የቤት ግንባታዎች በሚከናወኑባቸው ቦታዎች የሚሰጥ መሆኑን አብራርተዋል።የልማት ተነሽዎቹ በወቅቱ ካሳ አልተከፈላቸዉም ወይ? በሚል ለተነሳላቸዉ ጥያቄ፤ ምላሽ መስጠት ያለበት ሌላ አካል መሆኑን አመልክተዋል።ተነሺ አርሶአደሮቹ በዚህ የቤት መርሃ ግብር ተጠቃሚ ሊሆኑ የቻሉት ግን መንግስት በግልጽ በወሰነው የቆየ አሠራር ነው ብለዋል።ለ20 / 80 የጋራ መኖሪያ ቤት ለዓመታት ቆጥበው እጣ የወጣላቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣ እስካሁን ወደ ቤታቸው ያልገቡ እድለኞች አሉ፤ ይህስ የት ደረሰ ብለን የጠየቅናቸው ኃላፊው፦ ጉዳዩ ኮሚቴ ተቋቁሙ እየታየ ነው ብለዋል። በተጨማሪም በሃገር ደረጃ የሚወሰነውን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ እየጠበቅን ሲሉ አመልክተዋል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
የህወሓት ማዕካላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው!

የህወሓት ማዕካላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀመረ።ማዕከላዊ ኮሚቴው በስብሳበው የ2011 ዓ.ም ቁልፍ እና ዓበይት ተግባራትን የሚገመግም ሲሆን፥ በተለይ መልካም አስተዳደርን በማስፈን እና ልማትን በማረጋገጥ በኩል ያሉትን አፈፃፀሞች በዝርዝር ይመለከታል።
ከዚህ ባለፈም በ2012 ዓ.ም አቅድ ዙሪያ በዝርዝር በመወያየት እቅዱን እንደሚያፀድቅ ነው የሚጠበቀው። እንዲሁም የድርጅቱን መመሪያዎች እና አሰራሮችን በመገምገም ያሻሽላል ተብሎ ይጠበቃል።በተጨማሪም በ2011 ዓ.ም የነበሩ ሀገራዊ እና አለማቀፋዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ ጥንካሬዎችን እና ጉድለቶችን በዝርዝር በማየት ያሉትን ተግዳሮቶች ለመከላከል የሚያስችል አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥም ተጠቁሟል።እነዚህ ተግዳሮች የሚፈጥሩትን ጫና ከክልሉ ህዝብ ነበራዊ ሁኔታ ጋር በማያያዝ በመልካም አስተዳደር፣ ልማት እና የህዝብ ህልውና ያሉትን ሁኔታዎች ገምግሞ የውሳኔ ሃሳብ እንደሚያስቀምጥ ተነግሯል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት ሊያሸንፉ እንደሚችሉ ተጠቆመ!

በመጪው አርብ በኖርዌይ መዲና ኦስሎ በሚዘጋጀው የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት ያሸንፋሉ ተብለው ከሚጠበቁ ሰዎች አንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ሊሆኑ እንደሚችሉ ታይም መፅሄት አስነብቧል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ከሁለት አስርት አመታት ፍጥጫ እልባት በመስጠት፤ ሰላም በማምጣት፣ የፖለቲካ እስረኞችን በመፍታትና ሌሎች ባመጧቸውም መሻሻሎች ሽልማቱን ሊያሸንፉ እንደሚችሉ በእንግሊዝ የተለያዩ ፖለቲካዊ ትንበያዎችን በመስጠት የሚወራረደው ላድብሮክ አሳውቋል። ድርጅቱ (4/1)(Odd) ሊያሸንፉ እንደሚችሉ ግምቱን አስቀምጧል።

ዓመታዊው ሽልማት በአለም ውስጥ ለሰላም አስተዋፅኦ ያደረጉ ግለሰቦችን ወይም ድርጅቶችን እውቅና ይሰጣል። በባለፈው ዓመት የኮንጎ ዜግነት ያለው ዶክተር ዴኒስ ሙክዌጋና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቿ ናዲያ ሙራድ ወሲባዊ ጥቃትን ለጦርነት መሳሪያነት መጠቀሚያነት ለማቆም በሰሩት ስራ አሸናፊ ሆነዋል።በዚህ ዓመቱ ሽልማት 301 ዕጩዎች ያሉ ሲሆን፤ 223 ግለሰቦች እንዲሁም 78 ድርጅቶች መሆናቸውንም የኖቤል ተቋም አስታውቋል። ምንም እንኳን እነማን ዕጩዎች እንደሆኑ ባይታወቁም የተለያዩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ግምቶቻቸውን እያስቀመጡ ነው።ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በተጨማሪ የአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋቿ ግሬታ ተንበርግና የኒውዚላንዷ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን ግምት ተሰጥቷቸዋል።

ምንጭ፡-ቢቢሲ
@YeneTube @FikerAssefa
📌ኢህአዴግ ውህድ ፓርቲ ቢሆን ኖሮ አሁን እያስተዋልን ያለነውን የአማራና ትግራይ ክልሎች ህዝብን በተለያየ መንገድ እየቀሰቀሱ ግጭት ውስጥ አይገቡም ነበር፤

📌 ኢህአዴግ ተከፋፍሎ አገርን አንድ ማድረግ አይችልም፣ መጀመሪያ ራሱ አንድ መሆን መቻል አለበት፣

📌 ስለኢትዮጵያ አንድነት ማውራት አሃዳዊነት አይደለም “Unity & Unitary” ይለያያል፤ ውህድ ፓርቲ አህዳዊነትን አያመጣም፤ ይልቁንም አንድነትን ያጠናክራል።

📌 አሜሪካ የሚመሩት ውህድ ፓርቲዎች ናቸው፤ አገሪቱ ግን ፌዴራላዊ ናት፤

📌 ኢህአዴግ ከተዋሃደ ኃላፊነት የሚሰማው ድርጅት ይሆናል ብዬ አስባለሁ፤ አፈናም ሆነ የመብት ጥበቃ ካለ በሁሉም አካባቢዎች እኩል ይሆናል ማለት ነው። አሁን ላይ ትግራይ ውስጥ ከህወሃት ውጪ ሌላ ፓርቲ አናስተናግድም እየተባለ ሌላው እየተገፋ ነው ያለው።

ኢህአዴግ ወደ ውህድ ፓርቲነት የሚያደርገው ጉዞን በተመለከተ በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከኤፍ ቢሲ ጋር ካደረጉት ቆይታ የተወሰደ።

@YeneTube @FikerAssefa
በትናንትናዉ ዕለት በዳውሮ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ 2 የሞት 29 ቀላል እና 14 ከባድ አደጋ መድረሱ ተገለፀ!

ትናንት 27/01/2012 ዓ.ም በደረሰዉ የትራፊክ አደጋ 2 የሞት 29 ቀላል እና 14 ከባድ አደጋ መድረሱን የዳዉሮ ዞን ወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዋና ሥራ ሂደት አስተባባሪ ኮማንደር አክሊሉ አሥራት ገልፀዋል።ትናንት ጠዋት ከወላይታ ሶዶ መነሃሪያ ወደ ዳዉሮ ዋካ መድረሻ ያደረገዉ ደህ-18375 የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ 43 ተሣፋሪዎችን የጫነ ሲሆን ዋካ ከተማ ለመድረስ በግምት 10 ኪ.ሜ ሲቀረዉ የመገልበጥ አደጋ ደርሶበታል።

እንደ ዞኑ ወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዋና ሥራ ሂደት አስተባባሪ ገለጻ የአደጋዉ መነሻ ሁለት የኋላ ጎማ መፈንዳት ሲሆን ከፍተኛ የሆነ ፍጥነት አደጋዉ እንዲባባስ አድርጎታል።በፍጥነት ሲጓዝ የነበረዉ ተሽከርካሪ በሾፈሩ በኩል ከወደቀ በኋላ 30ሜትር ያህል በአስፓልት ተንሸራቶ ከመንገዱ በስተቀኝ በኩል ወደሚገኘዉ ተዳፋት ቦታ ነበር የገባው።በአደጋዉ የሞቱት አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ሲሆኑ ዕድሜያቸዉ ከ30 የማይበልጥ 25 ወጣቶች ተሣፋሪዎች የአደጋዉ ተጎጂ መሆናቸዉን የዞኑ ወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ኃላፊዉ ገልፀዋል።

ምንጭ:የዳዉሮ ዞን ህዝብ ግኑኝነት ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
ጅማ ዩንቨርስቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች መግቢያ ቀን ጥቅምት 10 እና 11 መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሰበት ቀን እንድትገቡ ዩንቨርስቲው ያሳስባል።

መረጃውን ያደረሰን ዶክተር ታመነ
@YemeTube @FikerAssefa
⬆️
ፌስቡክ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ10 የአፍሪካ ሀገራት ሀሰተኛ መረጃዎችን መቀነስ የሚያስችለውን ፕሮግራም ጀመረ!

ፌስቡክ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሃራ በታች በሚገኙ ሀገራት በዛምቢያ ፣ ሶማሊያ ፣ ቡሪኪና ፋሶ ፣ ኡጋንዳ ፣ ታንዛኒያ ፣ በዲሞክራሲያዊ ረፐብሊክ ኮንጎ ፣ ኮትዲቫር ፣ ጊኔ ኮናክሬ እና ጋና ነው ሀሰተኛ መረጃዎችን መቀነስ የሚያስችለውን ፕሮግራም ነው የጀመረው:: ሶስተኛ ወገን መረጃ ማጥሪያ የተሰኘው ይህ ፕሮግራም ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመቀነስ የሚያስችል መሆኑን ፌስቡክ አስታውቋል::

ሀሰተኛ የፌስቡክ ገፆችን መዝጋት፣ እውነተኛ የዜና አማራጮችን ማስተዋወቅ እና የማያስፈልጉ መልዕክቶችን ለሚልኩ አካላት የገንዝብ ድጋፍ የሚያደርጉትን መከላከል ይህ ፕሮግራም ከሚያከናውናቸው አሰራሮች ውስጥ ይካተታሉ ተብሏል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የኬሚስትሪ ዘርፍ የኖቤል ሽልማትን 3 ሳይንቲስቶች ተጋሩት!

የዘንድሮውን የኬሚስትሪ ዘርፍ የኖቤል ሽልማት የሊቲየም አየን ባትሪን (Lithium-ion battery) ለዓለም ያበረከቱ ሶስት ሳይንቲስቶች ተጋርተውታል።በትውልድ ጀርመናዊ በዜግነት አሜሪካዊ የሆኑት ፕሮፌሰር ጆን ጉድኢነፍ፣ እንግሊዛዊው ስታንሊ ዊቲንግሃም እና ጃፓናዊው አኪራ ዮሺኖ ሽልማቱን በጋራ ወስደዋል።

የ97 ዓመቱ ፕሮፌሰር ጉድኢነፍ ከእስካሁኖቹ ኖቤል ሎሬቶች በእድሜ ትልቁ መሆናቸው ተነግሯል፡፡የሊቲየም አየን ባትሪ በየጊዜው ሊሞላ የሚችል እና ተንቀሳቃሽ ለሆኑ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የሚውል ነው።የኖቤል ኮሚቴ አባል የሆኑት ኦሎፍ ራምስትሮም እንደተናገሩት ይህ ባትሪ የሞባይሉን ዓለም ያነቃቃ የዘርፉ ይበል የሚያሰኝ ፈጠራ ነው።9 ሚሊዮን ክሮነር ወይም 738 ሺህ ፓውንድ የሚደርሰውን የገንዘብ ሽልማት ሶስቱ ሳይንቲስቶች ይካፈሉታል ተብሏል።

ምንጭ፡- ቢቢሲ/ETV
@YeneTube @FikerAssefa
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሲዳማ ብሄር የህዝበ ውሳኔ ማስፈጸሚያ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት በመጪው የህዳር ወር መግቢያ ለሚያካሂደው ህዝበ ውሳኔ የዝግጅት ስራዎችን በማከናወን ላይ አንደሚገኝ አስታውቋል ።

የፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አዳነ ገበየሁ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ «ፅህፈት ቤቱ የክልሉ መንግስትና የሲዳማ ዞን መስተዳድር በህዝበ ውሳኔው የሁሉንም አካላት ጥቅምና ፍላጎት ለማጣጣም የሚያስችሉ አስተዳደራዊና የህግ ማዕቀፎች በመዘጋጀት ላይ ይገኛሉ » ብለዋል ።

Via :-DW

@YeneTube @Fikerassefa
ሰሞኑን በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ተከስቶ የነበረውን ግጭት ሙሉ ለሙሉ ማስቆም ተችሏል፡፡

ከመስከረም 24/2012 ጀምሮ ተከስቶ የነበረው ግጭት በሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ በሀገር ሽማግሌዎች እና በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ባደረጉት ርብርብ ማስቆም ተችሏል፡፡ግጭቱ ተከስቶባቸው ከነበሩ እዝግዬ፣ አርባዋዩ እና መረዋ ሀደሬ ቀበሌዎች ተፈናቅለው የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ወደየ ቀያቸው እንዲመለሱ የማድረግ ስራ ተጀምሯል፡፡የመንግሥት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት እንዲጀምሩ ተደርጓል፡፡አከባቢውን ወደ ቀድሞ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለመመለስ እየተሰራ ነው፡፡

ምንጭ:የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ መንግሥት ኮሙኒኬሽን
@YeneTube @FikerAssefa
በምሥራቅ ጀርመንዋ ከተማ በሃለ ዛሬ ከቀትር በኋላ በእርምታ ተኩስ ቢያንስ ሁለት ሰዎች ተገደሉ።

ፖሊስ በከተማይቱ በሚገኝ ሙክራብ ፊት ለፊት በተፈጸመው በዚሁ ግድያ ከተጠረጠሩት መካከል አንዱን መያዙን አስታውቋል።ሌሎች ተጠርጣሪዎች በመኪና እንዳመለጡም አስታውቋል።

ተኩሱ ከሙክራቡ ጋር ይያያዝ አይያዝ ግልጽ ባይሆንም ቢልድ የተባለው ጋዜጣ እንደዘገበው በአንድ የአይሁዶች የመቃብር ስፍራ ላይም የእጅ ቦምብ ተወርውሯል።

አንድ የዓይን ምስክር ኤን ቴፋው በተባለው የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደተናገሩት ደግሞ አንድ የቱርክ ምግብ መሸጫ ሱቅ ላይም ተተኩሷል።

ጥቃቱ የተፈጸመበት የዛሬው እለት በአይሁዶች ዮም ኪፖር የተባለው የዓመቱ የተቀደሰ ቀን ነው።ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን በመፈለግ ላይ ሳለ ነዋሪዎች ከቤታቸው እንዳይወጡ አሳስቦ ነበር።

ብሔራዊው የጀርመን የባቡር አገልግሎት ዶቼ ባን እንዳስታወቀው የሃለ ዋናው ባቡር ጣቢያ ተዘግቶ ነበር።ከሀለው ተኩስ በኋላ ላንድስበርግ በተባለችው ጎረቤት ከተማም ተኩስ መሰማቱ ተዘግቧል። ፖሊስ ዝርዝሩን አላሳወቀም።

Via:- Dw
@Yenetube @FikerAssefa