YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
እንኳን ለ2012 ዓ·ም የ # ኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!

የሰላም እና የፍቅር በዓል እንዲሆን እንመኛለን።
Ummata Itoophiyaa Hundaaf Bagaa Ayyaana

#Irreechaa Bara 2012 Isiin Gahe!
Ayyaanni Irreechaa Baranaa Nageenyif Jaalalli kan itti dammaqu Nuuf yaata'uu!

Happy #Irreecha2019 Festivity!
በቅማንት ህዝብ ላይ ጭፍጨፋ፣ እንግልትና ወከባ እየደረሰበት ነው ሲል የቅማንት ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ድርጅታዊ መግለጫ አውጥቷል።

የቅማንት ብሄረሰብ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በድሮዉ ሰሜን ጎንደር ዞን በወገራ ፤በላይ አርማጭሆ፣ በጎንደር ዙሪያ፣ በጎንደር ከተማ፣ በደንቢያ፣ በጭልጋ፣ በመተማና ቋራ ወረዳዎች በኩታ ገጠምነት ሰፍሮ የሚገኝ እንዲሁም እንደማንኛዉም ኢትዮጵያዊ በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች ከሌሎች የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ጋር ተሰባጥሮ የሚኖር እና እኔ ቅማንትነኝ የሚል አንድ አይነት የሆነ የስነልቦና ባለቤት የሆነ ህዝበ ነዉ፡፡

ሙሉ መግለጫውን ያንብቡ👇👇👇👇

https://telegra.ph/YeneTube-10-04-2
በአማራ ክልል ልዩ ሃይልና የቅማንት ታጣቂዎች ግጭት፣ ባለፉት 5 ቀናት ብቻ 22 ሰዎች እንደተገደሉ #ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ታጣቂዎች በመኪና ሲጓዙ የነበሩ 10 ንጹንን፣ በኋላም 12 የልዩ ሃይል አባላትን በደፈጣ ገድለዋል- ብሏል የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄን ጠቅሶ፡፡ የቅማንት ኮሚቴ ውንጀላውን አስተባብሏል፡፡ አሜሪካ ኢምበባሲ ወደ ክልሉ ዜጎቹ እንዳይጓዙ ትናንት አስጠንቅቋል፡፡

Via:- Wazema
@YeneTube @Fikerassefa
ንግድ ባንክ በውጪ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወይም ዳያስፖራዎች ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ ቅርንጫፍ ዛሬ አስመረቀ!

የተከፈተው ቅርንጫፍ ለአገራዊ ልማት ማስፈፀሚያዎች የሚያስፈልግ የውጪ ምንዛሬ ለማሰባሰብ እንደሚረዳ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት እና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባጫ ጊና በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተናግረዋል፡፡የቁጠባ አገልግሎት፣ የቤት መስሪያ እና መግዣ ብድር፣ እንዲሁም የውጪ ምንዛሬ ግብይት በቅርንጫፉ እንደሚሰጥም ሰምተናል፡፡

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ባንኩ ለእነሱ ብቻ የከፈተውን ቅርንጫፍ በመገልገል ለአገራቸው የራሳቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ጠይቀዋል፡፡ዛሬ የተመረቀው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ እንደ ሌሎቹ ባንኮች የአገልግሎት መስጫ መስኮቶች የሉትም፡፡በምትኩ ተገልጋዮች ከባንኩ ሰራተኞች ፊት ለፊት ተቀምጠው አገልግሎት የሚያገኙባቸውን መቀመጫዎች አዘጋጅቷል፡፡ይህም የደንበኞቹን ምቾች በመጠበቅ አገልግሎት ለመስጠት በማሰብ የተደረገ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
በአሶሳ ከተማና አካባቢው የመብራት አገልግሎት ከተቋረጠ ሳምንት ሆኖታል!

በአሶሳ ከተማና አካባቢው የመብራት አገልግሎት የተቋረጠው በመንዲና ነጆ መካከል ሁለት የመስመር ማስተላለፊያ ተሸካሚ ምሰሶዎች በመውደቃቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታወቀ ፡፡ የወደቁ የመስመር ማስተላለፊያ ተሸካሚ ምሰሶዎችን መልሶ ገንብቶ በአጭር ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል እየተሰራ መሆኑም ተገልጸዋል፡፡በአሶሳና አካባቢዋ መስከረም 17 ጀምሮ የተቋረጠውን የመብራት አገልግሎት አስመልክቶ ከክልሉ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ከበደ እንዳሉት በመንዲና ነጆ መካከል ሁለት ከፍተኛ የመስመር ማስተላለፊያ ተሸካሚ ምሰሶዎች በመውደቃቸው የመብራት አገልግሎት መቋረጡን ገልጸው በዋናነት የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ችግሩ ከተፈጠረ ጊዜ ጀምሮ አስፈላጊውን ቁሳቁስና ባለሙያዎችን በቦታው አሰማርቶ እየሰራ ነው ብለዋል ፡፡

የመስመር ማስተላለፊያ ተሸካሚ ምሰሶወች የወደቁበት ቦታ ገደላማ በመሆኑና ከዋናው መንገድ ርቀት ስላለው ለስራው የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ለማድረስ መኪና መግባት ባለመቻሉ ብልሽቱን አስተካክሎ ቶሎ አገልግሎት መስጠት እንዳልተቻለ የገለጹት ስራ አስፈጻሚው የመስመር ማስተላለፊያ ተሸካሚ ምሰሶወች ተሰተካክለው በአጭር ጊዜ ውስጥ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል በቦታው በርካታ የሰው ሃይል ተሰማርቶ መልሶ የመገንባት ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡ምሰሶወቹ የወደቁበት ቦታ ምቹ ባለመሆኑ ችግሩ ተስተካክሎ የመብራት አገልግሎት ሚጀምርበትን ቀን እርግጠኛ ሆኖ መናገር አይቻልም ያሉት አቶ ካሳሁን የመብራት አገልግሎት መቋረጡ በማህበረሰቡ የእለት ተእለት የስራ እንቅስቃሴ ላይ የሚያሳድረው ተጽኖ ከፍተኛ ቢሆንም ችግሩ ተሰተካክሎ አገልግሎት መስጠት እስኪጀምር ድረስ ህብረተሰቡ በትግስት እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል ፡፡

ምንጭ: ቤመብድ
@YeneTube @FikerAssefa
በ3000ሜ መሰናክል ለሜቻ ግርማ ለኢትዮጵያ የብር ሜዳልያ አስገኝቷል ሰዓቱ ደግሞ 8:01.36 ነው፣ 0.01 ሰከንድ ብልጫ ተወስዶበት ነው ወርቅ ያመለጠው።ጌትነት 4ኛ ሆኗል።

@YeneTube @FikerAssefa
የኢሬቻ በዓል በሆራ ፊንፊኔ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል ።ለበዓሉ በባህል አልባሳት ደምቀው ሆራ ፊንፊኔ የተገኙ የኦሮሞ እና የሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ተወላጆች ኢሬቻን በጋራ በመክበር ላይ ይገኛሉ።

Via OMN
@YeneTube @FikerAssefa
በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ያለው የእሬቻ በዓል በፎቶ!

via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
ሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

የሙዚቃ አቀናባሪው፣ የግጥም እና ዜማ ደራሲው፣ ጊታሪስቱ፣ ፒያኒስቱ ኤልያስ መልካ ከ40 በላይ አልበሞችን እንዳቀናበረ ይነገርለታል፡፡በዘመናዊ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ላይ አይረሴ አሻራውን ያኖረው ኤልያስ መልካ የኩላሊት እና የስኳር ሕመም ገጥሞት ሕክምናውን ሲከታተል ነበር፤ትናንት ለሊት ባጋጠመው ድንገተኛ ሕመም ወደ ሆስፒታል ተወስዶ በዚያው ሕይወቱ ማለፉን ለመረዳት ችለናል።ሸገር በሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ ሕልፈት የተሰማውን ሐዘን እየገለፀ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ፣ ለጥበብ ወዳጆቹ፣ ለአድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል፡፡

Via Sheger
@YeneTube @FikerAssefa
በአፋር ክልል የቀድሞ ባለስልጣናት እና ግለሰቦች እየታሰሩ ነው!

ከስፍራው የደረሰኝ መረጃ እንደሚያመለክተው በአፋር ክልል በተለይ በአሳይታ እና ሎጊያ ከተሞች አንዳንድ የቀድሞ የክልሉ ባለስልጣናት፣ ነጋዴዎች እና ሌሎች ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው። የእስሩ ምክንያት በግልፅ ባይታወቅም በክልሉ ከሚወጣው የጨው ምርት ጋር ተያይዞም በርካታ እስር እንደተከናወነ ታውቋል። ባለፈው ሳምንት አንዳንድ የክልሉ መሪ ፓርቲ የቀድሞ ባለስልጣናትም ከአውሮፕላን ማረፊያ ጭምር እየተያዙ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

Via Elias Meseret
@YeneTube @FikerAssefa
“‘የቅማንት የራስ አስተዳደር ጥያቄ አልተመለሰም’ የሚሉ አካላት ትክክል አይድሉም ጥያቄዉ እንደተመለሰላቸዉ የፌዴሬሽን ም/ቤት ተቀብሎ አጽድቋል" አቶ ወርቁ አዳሙ በፌዴሬሽን ም/ቤት የሕገ መንግሥት ትርጉምና የማንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጽ/ቤት ኃላፊ

"‘ሌሎች ተጨማሪ ሦስት ቀበሌዎች ወደ ቅማንት ይካለሉ’ የሚሉ ጥያቄዎችም ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀርበዋል፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤትም የጥናት ቡድን ልኮ ቀበሌዎቹ ኩታ-ገጠም አለመሆናቸዉን አረጋግጧል፤ ስለዚህ ጥያቄያቸው ተገቢ አይደለም ተብሏል”

Via Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
ተማሪዎች ከተመደቡበት ዩኒቨርስቲ ወደሌላ ዩኒቨርስቲ መቀያየር እንደማይችሉ ተገለፀ።

ማንኛውም ተማሪ ከተመደበበት ዩኒቨርስቲ ወደሌላ ዩኒቨርስቲ መቀያየር እንደማይችል የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል። ከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ድልድል ተጠናቆ ትናንት ይፋ መደረጉ አይዘነጋም፡፡

ምንጭ: ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች በመዋሃድ በሚመሰርቱት አዲስ ድርጅት ውስጥ ህወሃት እንደማይኖርበት የአዴፓ ም/ሊቀመንበር አቶ ዮሐንስ ቧያለው ተናገሩ።

አቶ ዮሀንስ በኢህአዴግ ውህደት ዙሪያ ከክልሉ የካቢኔ አባላት አባላትና የፀጥታ አመራሮች ጋር በተወያዩበት ወቅት ''ኢህአዴግን በምናፈርስበትንና ሌላ ውህድ ፓርቲ በምንመሰርትበት ሁኔታ ተግባብተናል። በውስጣችን ሆኖ ኢትዮጵያን ከሚያሸብረው ድርጅት ጋር እንደምንፋታም ተመሳሳይ አቋም ይዘናል ሲሉ ተደምጠዋል።አቶ ዮሃንስ አዴፓ ውህደቱ በፍጥነት እንዲፈጸም እንደሚፈልግም የገለጹ ሲሆን፣ ይህ የማይሆን ከሆነ ግን "በህዝቦች ደም በተጨማለቀው ኢህአዴግ ጥላ ስር ያውም 'ከትህነግ' ጋር አብሮ አይቀመጥም የጋራ ውሳኔም አያሳልፍም'' በማለት ከኢህአዴግ ራስን በማግለል ''ከሚመስሉን ጋር እንወሃዳለን'' ብለዋል።

ምንጭ:Ethiopia Live Updates
@YeneTube @FikerAssefa
የኢሬቻ በዓል በሰላም መከበሩን ፖሊስ አስታወቀ!

በርካታ ህዝብ የታደመበት እና በመስቀል አደባባይ የተከበረው የኢሬቻ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ ለዚህም ህብረተሰቡ ላደረገው ቀና ትብብር ኮሚሽኑ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡ ኮሚሽኑ በዓሉ በሰላም እንዲከበር ከሀገር መከላከለያ፣ ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራቱን ገልጿል፡፡

Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa
ኦሮምኛ፣ ሶማልኛና ትግርኛ የፌዴራል የስራ ቋንቋ ሊሆኑ ነው።

ሰሞኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከOBN ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ከአማርኛ ቋንቋ በተጨማሪ የፌዴራል የስራ ቋንቋዎችን ለመጨመር እንደታቀደ ከሚጨመሩትም መካከል ኦሮምኛ አንዱ እንደሆነ ቢናገሩም ሌሎቹ የሚጨመሩ ቋንቋዎች የትኞች እንደሆኑ አልተናገሩም ነበር።ነገር ግን አዲስ ማለዳ በዛሬ እትሙ ሶማሊኛና ትግርኛ ከሚጨመሩት ቋንቋዎች መካከል እንደሆኑ ይዞ ወጥቷል ።

@YeneTube @FikerAssefa
#NewsAlert

የታጠቁ አካላት በኤፍራታና ግድም ወረዳ ተኩስ ከፍተው አካባቢውን ለመረበሽ ያደረጉት ሙከራ መክሸፉን የወረዳው አስተዳድርና ፀጥታ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ ከተራራ ሥፍራ በመሆን ወደ አጣዬ ከተማ በመተኮስ የአካባቢውን ሰላም እየረበሹ መሆኑን የወረዳው አስተዳድርና ፀጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው የሽጥላ ገልፀዋል።አቶ ጌታቸው እንዳስታወቁት ከተራራ ወደ ከተማዋው በተከፈተው ተኩስ ስጋት የአጣዬ ቅዳሜ ገበያ ተበትኗል፤ ነዋሪውም እየተረበሸ ነው።
የአማራ ክልል ልዩ ኃይልና የመከላከያ ሠራዊት ሕዝቡን ለማረጋጋት እየሠሩ እንደሆነም ኃላፊው አስታውቀዋል። የታጠቁ ኃይሎቹ በርከት ያሉ መሆናቸውንና በብዙ አቅጣጫ እንደሚተኩሱ ከመግለጻቸው ባለፈ ማንነታቸውና በሰው ላይ ያደረሱት ጉዳት ስለመኖሩ አልተገለጸም።

የሰሜን ሸዋ ዞን የሠላምና ደኅንነት ግንባታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ካሳሁን እምቢያለ ግን የታጠቁ ቡድኖቹ በልዩ ኃይል ላይ ጥቃት ሊፈጽሙ መሞከራቸውንና በአጸፋው ከጥፋት ኃይሎቹ አንዱ መገደሉን አስታውቀዋል። መምሪያው ሁኔታው ወደ መረጋጋት መመለሡንም አስታውቋል። አካባቢውን ልዩ ኃይል፣ ፌዴራል ፖሊስና መከላከያ ሠራዊት መቆጣጠሩም ተብራርቷል።በኤፍራታና ግድም የተከሰተው ሁኔታ ከሰሞኑ በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አጋጥሞ እንደነበር ከተገለጸው ክስተት ጋር የማይገናኝ ስለመሆኑም የመምሪያው ኃላፊ አስታውቀዋል።

Via AMMA
@YeneTube @FikerAssefa