YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
ዩንቨርስቲ መግቢያ ውል❗️

በመላው ኢትዮጵያ በ2011 የመሰናዶ ትምህርታቸውን አጠናቀው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በ2012 ለሚቀላቀሉ ተማሪዎች ከወትሮው በተለየ ተቋማት አዲስ ገቢ ተማሪዎቻቸውን ከአንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ልብስ ባለፈ ከሚኖሩበት አካባቢ ወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት በኩል የፈረሙትን ውል ይዘው እንዲመጡ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ጉዳዩ እንዲህ ነው፤ ባሳለፍናቸው ጥቂት ዓመታት በአገሪቱ የሚገኙት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የእውቀት መገቢያነታቸው ተዘንግቶ ጎራ ተለይቶ መጠፋፊያ ቀጠና ሆነው የበርካታ ተማሪዎችን ሕይወት እንዲቀጠፍ የሆነበት ነበር።

ታዲያ ያለፉትን ዓመታት አለመረጋጋቶችና ግጭቶች በከፍተኛ ተቋማት ውስጥ ጭራሽ እንዳይከሰት በሚል በዘንድሮው ማለትም 2012 የትምህርት ዘመን አዲስ እና ነባር ተማሪዎች በሚማሩበት ዩኒቨርስቲ ውስጥ አስተዳደራዊ እና አካዳሚያዊ ሥነ ስርዓቶችን አክብረው ሊማሩ እና ሕገ ደንቦችን ጥሰው ቢገኙ ደግሞ ለሚወሰድባቸው ማንኛውም ዓይነት እርምጃ ኀላፊነቱን ራሳቸው እንደሚወስዱ ውል እንዲገቡ ተደርገዋል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ግን በዚህ ይብቃኝ ያለ አይመስልም። ወላጆችም ለጆቻቸውን በሚሔዱበት ዩኒቨርስቲዎች ያሉትን ሕጎች እንዲያከብሩ መምከራቸውን እና ተላልፈው ቢገኙ እና ለሚወሰድባቸው እርምጃ ልጆቻቸው ኀላፊነቱን እንደሚወስዱ አስታውቀው ውል ፈርመዋል።

በማኅበራዊ ትስስር ገፆች ታዲያ በርካታ ግለሰቦች የውሉን ጠቀሜታ እያሞካሹ አስተያየታቸውን ሲሰጡ እኩል በእኩል በሆነ ቁጥር ደግሞ በተቃራኒው በመቆም ተማሪዎች የሚያስሩት ውል ፋይዳው ምንድነው? የሚሉ ጥያቄዎችን በማንሳት ትችታቸውን ሲያሰሙ ከፍ ሲልም ሲሳለቁ ነበር።

ተማሪዎች በተለይም ደግሞ አዲስ ገቢዎች ገና ከጅምሩ እንደዚህ ዓይነት ኀላፊነት ተሸክመው መግባታቸው ከትምህርት ውጪ ወደ ብጥብጥና ረብሻ የሚያመሩበት አዝማሚያ በእጅጉ ይቀንሳል፤ መንግሥት እንዲያውም ከዚህ ቀደም ያላሳየውን የኀላፊነት መንፈስ አሁን እየተገበረው ነው። ይበል የሚያሰኝ አካሔድ ነው ሲሉ ድጋፋቸውን ያለመሰሰት አስተጋብተዋል።

ከዚሁ በተቃራኒው የቆሙት ደግሞ የለም መንግሥት አሁንም ”የውሃ ቢወቅጡት” ዓይነት አካሔድ ነው እየተከተለ ያለው ዘንድሮም ለውጥ ለሌለው ጉዳይ ማወናበጃ እንጂ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰላም እንዲህ በቀላል የሚመለስ ሳይሆን ትልቅ ፖለቲካዊ ውሳኔዎች ተላልፈው ከተቋማት ውጭ ያሉት ውዥንብሮች ሲረግቡ ተያይዞ የሚረግቡ ናቸው ይላሉ። እንዲያውም ከጎረቤት በተለይም ደግሞ ከኤርትራው ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የተገኘች ምክር መሆን አለባት ሲሉም የተሳለቁ አልታጡም። ቀጥለውም በወላጆች፣ በተማሪዎችና በትምህርት ጽሕፈት ቤቶች በኩል የሚገባው ውል በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚማሩ ተማሪዎች ልብ ማሰሪያስ ይሆናል ወይ? በውል የሚመጣ ሰላም ካለስ እስካሁን መንግሥት ምነው ዘገየ እና የመሳሰሉ ጥያቄዎች ከግራም ከቀኝም ሲናፈሱ ሰንብተዋል።

Via:- Maleda
@YeneTube @Fikerassefa
አዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ የመንገድ መጨናነቅ ላይ ትገኛለች።

#ኢሬቻ2019_ሆራ ፊንፊኔ
@YeneTube @Fikerassefa
አምነስቲ ኢንተርናሽናል ነሀሴ 29 ገርጂ አካባቢ በቁጥጥር ስር የዋሉ አምስት የ Sagalee Qeerroo Bilisumaa አባላት በአስቸኳይ እንዲፈቱ ዛሬ ጠይቋል!

Via:- ኤልያስ መሰረት
@YeneTube @FikerAssefa
የ12 ክፍል ተፈታኞች ምደባ 11:30 ይወጣል!!

ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የመግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ ⬇️

ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ምደባ ስለትከናወነ የተመደባችሁበትን ከፍተኛ ት/ት ተቋም ከዛሬ 23/01/2012 ዓ.ም.

ከ11: 30 ሰኣት ጀምሮ በአገር አቀፍ የት/ት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ ዌብ ሳይት ማየት የምትችሉ መሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር ያስታውቃል።

@YeneTube @Fikerassefa
11:30 ይለቀቃል የተባለው የዩንቨርስቲ የሚገቡ ተማሪዎች ምደባ ዌብሳይቱ እስካሁን መሰራት አለመጀመሩን ተመልክተናል።

@YeneTube @Fikerassefa
⬆️ኢ/ር ታከለ ኡማ በእሬቻ ፌስቲቫል ላይ ካስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ፦

"አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ከተማ እንደመሆኗ መጠን የኦሮሞ ህዝብም በከተማው የኢሬቻን በዓል ለማክበር በመቻሉ የተሰማኝ ደስታ ከፍ ያለ ነው፡፡

በቀጣይነትም ከተማችን አዲስ አበባ ኃላፊነት ወስዳ የኢሬቻን በዓልን ጨምሮ ሌሎችን የሃገራችን በዓላት እና እሴቶች በሃገር ደረጃ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ እና በዓለም መድረኮች ሁነቶችን በመጠቀም ታስተዋውቃለች።

ከተማ አስተዳደራችን እና ነዋሪዎቿ በታሪክ አጋጣሚ የዚህ ታሪካዊ ኃላፊነት አስተናጋጅ በመሆናችን ደስታ ይሰማናል፡፡

በመጨረሻም የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ በዚህ ደረጃ በተቀናጀ እና ባማረ መልኩ እንዲከበር አስተዋፅኦ ላደረጋችሁ የከተማችን ነዋሪወች እና ባለሃብቶች ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡"

@YeneTube @FikerAssefa
አሁን ምደባችሁን ማየት ትችላላችሁ!


ለማየት ይሄንን link በመጠቀም
http://twelve.neaea.gov.et/Home/Placement
በቀላሉ ቁጥሮን በማስገባት መመልከት ይችላሉ።

@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
የመጀመሪያ ቪዲዮችን የኢሬቻበዓል በሚከበርበት ቀን ይለቀቃል!

የኔቲዩብን በYouTube ላይ አሁንኑ ሰብስክራይብ ያድርጉ!!!

https://bit.ly/2pKzukZ
Forwarded from YeneTube
እንኳን አደረሳችሁ

በ አዲስ አበባ የተለያዩ እቃዎች አስመጪ
🎖ብራንድ የወንድና የሴት ሰዓቶች
🎖የሴት ቦራሳዎች
🎖የመዋቢያ እቃዎች
🎖እንዲሁም አልባሳት

የምናስመጣቸው እቃዎች ጥራት እና በቀላሉ ገበያ ላይ አለመገኘት እንዲሁም ወደ ክልል ከተሞች መላክ መቻላችን ለየት ያደርገናል ።

ቦሌ መድኃአለም ሞል
+251993014846

ከታች ባለው ሊንክ ገብተው ይጎብኙን ይምረጡ ይዘዙን
👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAENXyUTam6WMV6_hmg
የኢሬቻ በዓልን በተመለከተ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ⬇️

ከሁሉም በማስቀደም የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ወንድም ለሆነው የኦሮሞ ሕዝብ እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን ይገልፃል።

የአማራና የኦሮሞ ሕዝብ ለዘመናት አብሮ የኖረ ፣ ክፉ ደጉን በጋራ ያሳለፈ፣ የተጋባ፣ የተዋለደ፣ የተዋሃደ ሕዝብ ነው። ሃቁ ይህ ሆኖ እያለ ባለፉት 50 ዓመታት በኢትዮጵያ የተፈጠሩት ጥራዝ ነጠቅና በአማራ ጥላቻ የሰከሩ ብሔርተኞች የሁለቱን ሕዝቦች ግንኙነት የጨቋኝና የተጨቋኝ ፤ አለፍ ሲልም የቅኝ ገዢና ተገዢ አድርገው በማቅረብ በሁለቱ ህዝቦች መካከል ለዘመናት የዘለቀውን ጠንካራ ትስስር ለማላላት ቢሰሩም ሳይሳካላቸው ቀርቷል። ዛሬም እንደትላንቱ የአማራ ሕዝብ ከኦሮሞ ሕዝብ ጋር በጋራ አርሶ፣ ነግዶ፣ ሰርቶ፣ ተጎራብቶ ፣ እየተጋባና እየተዋለደ፣ በሃዘን በደስታው እየተገናኘ አብሮ እየኖረ ነው::

https://telegra.ph/Yenetube-10-04-