YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ በመስቀል አደባባይ የሚከናወኑ ልዩ ልዩ ስነ-ሥርአቶች ተጀምረው እስከሚጠናቀቁ ድረስ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ከበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም መሰረት፡-
📌ጎተራ ሼል ዴፖ
📌ጎፋ ማዞሪያ
📌ቄራ 6 ቁጥር ማዞሪያ
📌ሳር ቤቶች
📌ካርል አደባባይ
📌 ጦር ኃይሎች አደባባይ
📌ኮካኮላ ድልድይ
📌ልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት
📌ልደታ ፀበል
📌አብነት አደባባይ
📌ሞላ ማሩ መገንጠያ
📌በርበሬ በረንዳ
📌ተክለ ሃይማኖት
📌ቴዎድሮስ አደባባይ
📌ንግድ ማተሚያ ቤት
📌አሮጌው ቄራ
📌ባሻወልዴ
📌ፓርላማ መብራት
📌ጥይት ቤት
📌ጀርመን አደባባይ
📌ሲግናል
📌እንግሊዝ ኤምባሲ መገንጠያ
📌ለም ሆቴል
📌ሾላ ገበያ መብራት
📌ጎርጎሪዮስ አደባባይ
📌መስቀል ፍላወር
📌መገናኛ ላይና ታች
📌ኤድናሞል አደባባይ
📌ሰንሻይን መገንጠያ
📌ቦሌ ቀለበት እና ቦሌ ሚካኤል ወደ ዝግጅቱ ስፍራ የሚወስዱ መንገዶች ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት መረጃ ለመስጠት 991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እና 01- 11 -11- 01 -11፣ 01- 11- 26- 43- 59፣ 01- 11- 01- 02- 97፣ መጠቀም የሚችል መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

Via Addis TV
@YeneTube @FikerAssefa
ፍርድ ቤት ታሳሪ ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩን ለመስከረም 29 በድጋሚ እንደቀጠረው ጉዳዩን የተከታተሉ የማኅበራዊ ሜዲያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ፖሊስ 28 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቆ ነበር፡፡ ችሎቱ በመጭው ሐሙስ ብይን እሰጣለሁ ብሏል፡፡ ኤሊያስ ከሰኔ 15ቱ የባሕር ዳሩ ባለሥልጣናት ግድያ ጋር በተያያዘ በሽብር ነው የተከሰሰው፡፡

Via Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
እንኳን አደረሳችሁ

በ አዲስ አበባ የተለያዩ እቃዎች አስመጪ
🎖ብራንድ የወንድና የሴት ሰዓቶች
🎖የሴት ቦራሳዎች
🎖የመዋቢያ እቃዎች
🎖እንዲሁም አልባሳት

የምናስመጣቸው እቃዎች ጥራት እና በቀላሉ ገበያ ላይ አለመገኘት እንዲሁም ወደ ክልል ከተሞች መላክ መቻላችን ለየት ያደርገናል ።

ቦሌ መድኃአለም ሞል
+251993014846

ከታች ባለው ሊንክ ገብተው ይጎብኙን ይምረጡ ይዘዙን
👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAENXyUTam6WMV6_hmg
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር እና የሲዳማ ዞን የህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤቶች የጋራ መግለጫ።

የሁለቱ ጽ/ቤት ሀላፊዎች ለሚዲያ ተቋማት በሲዳማ ብሄር ህዝብ ውሳኔ፣ በምርጫ ቅስቀሳ ሂደት፣ በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም፣ ታስረው ስለሚገኙ የሲዳማ ኤጄቶዎች እና ከወንድም የኦሮሞ ህዝብ ጋር በመሆን የኢሬቻ በአል አከባበርን በሚመለከቱ ሀሳቦች እና አሰራሮች ዙሪያ ትኩረቱን ያደረገ መግለጫን ነው የሰጡት።

https://telegra.ph/Hawassa-10-03
የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ 12 የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ለማዛወር አቅጃለሁ- ብሏል ዛሬ በሰጠው መግለጫ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 6 የስኳር ፕሮጀክቶች፣ ሒልተን ሆቴል እና የላንጋኖ ሪዞርት ሆቴል እንደተካተቱ የዘገበው ሸገር ነው፡፡ መንግሥት በሒልተን አዲስ ሆቴል ካለው ድርሻ 70 በመቶውን ለግል ባለሃብቶች ለመሸጥ ታቅዷል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የሕዝብ ቤተ መፃህፍትን ወደ ዲጂታል የመቀየርና ተደራሽ የማድረግ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መፃሕፍት ኤጀንሲ አስታወቀ።

እንደ አገር የትውልዱን የንባብ ባህል ለማሳደግ ጠቃሚ የሆኑ መፃሕፍትን በዲጂታል መንገድ ለመቀየር ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ እንደሚገኝ የብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መፃሕፍት ኤጀንሲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ሽመልስ ታዩ ገልጸዋል።

Via:- ኢቢሲ
@YeneTube @Fikerassefa
የሱዳን ዜግነት ያለዉ አንድ ግለሰብ ትላንት መስከረም 21/2012 1300 የክላሽ ጥይት ከሰሜን ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ይዞ ሊገባ ሲል በጅማ ጉምሩክ አልመሀል መቆጣጠሪያ ጣቢያ በጣቢያዉ ሠራተኞች እና በፌደራል ፖሊስ ትብብር በቁጥጥር ስር ውሏል።

የኅብረተሰቡን ሰላም የሚያደፈርሱና የሚያውኩ ሕገ ወጥ መሳሪያዎችን ይዞ መንቀሳቀስ ከሕግ እንደማያስመልጥ በማሰብ ሕገወጦች ከዚህ መሰል ተግባር መታቀብ እንዳለባቸው የገቢዎች ሚኒስቴር አሳስቧል።

Via:- አዲስ ማለዳ
@YeneTube @Fikerassefa
የመጀመሪያ ቪዲዮችን የኢሬቻበዓል በሚከበርበት ቀን ይለቀቃል!

የኔቲዩብን በYouTube ላይ አሁንኑ ሰብስክራይብ ያድርጉ!!!

https://bit.ly/2pKzukZ
Forwarded from YeneTube
እንኳን አደረሳችሁ

በ አዲስ አበባ የተለያዩ እቃዎች አስመጪ
🎖ብራንድ የወንድና የሴት ሰዓቶች
🎖የሴት ቦራሳዎች
🎖የመዋቢያ እቃዎች
🎖እንዲሁም አልባሳት

የምናስመጣቸው እቃዎች ጥራት እና በቀላሉ ገበያ ላይ አለመገኘት እንዲሁም ወደ ክልል ከተሞች መላክ መቻላችን ለየት ያደርገናል ።

ቦሌ መድኃአለም ሞል
+251993014846

ከታች ባለው ሊንክ ገብተው ይጎብኙን ይምረጡ ይዘዙን
👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAENXyUTam6WMV6_hmg
ዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት በአባይና በኅዳሴ ግድብ ላይ ማምሻውን መግለጫ አውጥቷል።

የኢትዮጵያን ታላቁን ኅዳሴ ግድብ ለመሙላትና አገልግሎቱንም ለማስኬድ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ የትብብር፣ ዘላቂነት ያለውና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያመጣ ስምምነት ላይ ለመድረስ በግብፅ፣ በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል እየተካሄዱ ያሉትን ድርድሮች እንደምትደግፍ ዩናይትድ ስቴትስ አስታውቀች።ከዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት የፕሬስ ኃላፊ ማምሻውን የወጣው አጭር መግለጫ ”ሁሉም የአባይ ተፋሰስ ሃገሮች የምጣኔኃብትና የብልፅግና መብት አላቸው” ይላል። በመቀጠልም “እነዚያን መብቶች የሚጠብቅና በተመሣሣይ ጊዜም በአባይ ውኃ ላይ የሁሉንም የውኃ ድርሻ እኩልነት የሚያከብር ስምምነት ላይ እንዲደርሱ የሚያስችል ቀና ጥረት እንዲያደርጉ አስተዳደሩ ለሁሉም ወገኖች ጥሪ ያደርጋል” ብሏል።

መግለጫው የወጣበት ምክንያት አልተገለፀም።

Via VOA
@YeneTube @FikerAssefa
የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት አባላት በጥቅምት ወር አጋማሽ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ዥንዋ ዘግቧል፡፡ የልዑኩ ጉዞ ዋና ዐላማ ከአፍሪካ ኅብረት ባለስልጣናት ጋር መምከር ነው፡፡ አጀንዳዎቹ የመካከለኛው ምስራቅ ሁኔታ፣ በአፍሪካ ስላሉ የተመድ ሰላም ተልዕኮዎችና ሰላምና ጸጥታ እንደሆኑ ተጠቅሷል፡፡ ልዑኩ ወደ ደቡብ ሱዳንም ያመራል ተብሏል፡፡

ምንጭ:Wazema
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ወጣቶች ፌደሬሽን ነገ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚከበረው የእሬቻ በዓል የከተማዋን ወጣቶች በማሳተፍ በዛሬው እለት በመስቀል አደባባይ የፅዳት ፕሮግራም አካሂዷል፡፡

በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች መስቀል አደባባይና አካባቢዉን ነው ያፀዱት። የእሬቻ በዓል አስመልክተዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በተለያዩ ስፍራዎች ጽዳት በማካሄድ ላይ መሆናቸውም ታውቋል፡፡

Via EBC

@YeneTube @Fikerassefa
የ15 ሀገራት አምባሳደሮችን ያካተተ ልዑክ በትግራይ ክልል ይፋዊ የስራ ጉብኝት ሊያደርግ ነው፡፡

ልዑኩ የትግራይ ክልል የድህነት ቅነሳ ፕሮጀክቶችን፣ ቱሪዝም እና የኢንቨስትመንት ልማት እንቅቃሴዎችን ተዘዋውሮ እንደሚጎበኝ ነው የተገለጸው፡፡

የአውስትራልያ፣ አዘርባጃን ፣ ባንግላድሽ፣ ቻይና፣ ፊጂ፣ ኢንዶኖዥያ፣ ህንድ፣ ኢራን፣ ጃፖን፣ ካዛኪስታን፣ ደቡብ ኮርያ፣ ኒውዝላንድ፣ ፓኪስታን፣ ስሪላንካ እና የቱርክ አምባሳደሮች የጉብኝቶ ተሳታፊዎች ናቸው፡፡
ለዚህም አሁን ላይ የአራት ሀገራት አምባሰደሮች መቐለ ገብተዋል፡፡

እንግዶቹ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች አቀባበል ተድርጎላቸዋል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ሌሎች ቀሪ የልዑኩ አባላትም ዛሬ ከሰዓት ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Via:- FBC
@YeneTube @Fikerassefa
ከሲዳማ ከስልጤ እና ጉራጌ ዞን የተወጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች በጋራ በሀዋሳ ከተማ የምክክር መድረክ ትላንት አድርገዋል።

የጋራ መድረኩ አላማ የህዝቦቹን ለዘመናት አብሮ የኖረ በደም ተሳሰረ አንድነት ለማስቀጠል ያለመ ነው ተብሏል።

በመድረኩ ላይ የሶስቱም ዞን የስራ ሀላፊዎች ተገኝቷል።

Via:- SMN
@YeneTube @Fikerassefa
ET 302 - ጉዳይ ⬆️

እ.ኤ.አ በመጋቢት ወር 2019 ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ ናይሮቢ በረራዉን ሲያደርግ በነበረዉ ET 302 የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዉሮፕላን ቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ በመከስከሱ የ35 ሀገራት መንገደኞች ህይወት ማለፉ ይታወሳል፡፡ አደጋዉ ከደረሰ ከሁለት ቀናት በኃላ ኢትዮጵያ በጠየቀችዉ ጥያቄ መሰረት ኢንተርፖል ምላሽ ሰጪ ቡድን በመላክ ምርመራዉን ሲያከናዉን ቆይቷል፡፡

ለህልፈተ ህይወት የተዳረጉትን ለመለየት እንዲረዳዉም ኢንተርፖል የተጎጂ ቤተሰቦች ዲ ኤን ኤ በማሰባሰብ ምርመራ አድርጓል፡፡ ኢንተርፖል ለአደጋዉ ምላሽ ሰጪ ቡድን በማሰማራት ስሰራ የነበረዉን ተጎጂዎችን የመለየት ስራ ከ 6 ወራት በኃላ በተሳካ ሁነታ ማጠናቀቅ መቻሉን አፍሪፖል በድህረ ገፁ ባወጣዉ መረጃ አስነብቧል፡፡

ምላሽ ሰጪ ቡድኑ በአለም አቀፍ ደረጃ የሞት አደጋ የደረሰባቸዉን የሚለዩ ህግ አስፈፃሚዎችን በማስተባበር እና በአባል ሀገራት የቀረበዉን የቅድመ ሞት መረጃን የማቀናጀት ሚና ተጫዉቷል ተብሏል፡፡

ቡድኑ የሞት አደጋ የደረሰባቸዉን የመለየት ምርመራዉ ዓለም አቀፋዊ ደረጃዉን ጠብቆ መካሄዱን ለማረጋገጥ እንዲሁም የጣት አሻራ እና የ ዲ ኤን ኤ ናሙናዎችን በማሰባሰብ እገዛ ማድረጉም ተገልጿል፡፡ በአዲስ አበባ የሚገኘዉ የኢንተርፖል ልዩ ተወካይ ፅፈት ቤትም ለህልፈተ ህይወት የተዳረጉትን የመለየት ስራን በማስተባበር ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል፡፡

ከ14 የአፍርካ ሀገራት የተዉጣጡ መቶ የሚደርሱ ባለሙያዎች እንዲሁም የአሜሪካ እና የአዉሮፓ ሀገራት ባለሙያዎች ባካሄዱት ምርመራ 48 የሚደርሱ ሟቾችን በጣት አሻራዎቻቸዉ መለየት ችለዋል ተብሏል፡፡

Via:- ፌዴራል ፓሊስ
@YeneTube @Fikerassefa
ብሔራዊ ባንክ ሶስት ምክትል ገዢዎች ተሾሙለት። በአዲስ ፎርቹን ዘገባ መሠረት ፍቃዱ ድጋፌ፣ ሰለሞን ደስታ እና እዮብ ገብረእየሱስ የባንኩ ምክትል ገዢዎች ሆነው ተሾመዋል። ፍቃዱ ድጋፌ የባንኩ ዋና ኤኮኖሚስት ሆነዋል።

Via Eshete Bekele
@YeneTube @FikerAssefa
ነፃ የአይን ህክምና ጅማ

በጅማ ዩንቨርስቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የዐይን ክፍል ከዛሬ ጀምሮ ለ 3 ቀናት ( ከመስከረም 23 - መስከረም 25) የሚቆይ ነፃ የCataract ህክምና በስፔሻሊስት ዶክተሮች እየተሰጠ በመሆኑ ጅማ እና በአከባቢው የሚኖሩ ህሙማን ወደ ሆስፒታሉ በመምጣት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በየኔቲዩብ ቦኩል አስታውቋል ።

እንዲሁም በዚህ በ 3 ቀን ዘመቻ ከ 200-300 ለሚሆኑ ህሙማን በነፃ ቀዶ ህክምና ለመስራት ታስቧል።

@Yenetube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በኤረር ወንዝ ድልድይ ላይ ጉዳት በመድረሱ አሽከርካሪዎች በጊዜያዊ ተለዋጭ መንገድ እንድትጠቀሙ የሚያስችል ግንባታ እያከናወነ ነው።

ከሐረር ወደባቢሌ መስመር 20 ኪ.ሜ ዕርቀት ላይ የሚገኘው በኤረር ወንዝ ድልድይ ላይ በአካባቢው በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው ጎርፍ ሳቢያ ጉዳት ደርሷል። በዚህም ምክንያት ተለዋጭ መንገድ እየተሰራ ይገኛል።ተለዋጭ መንገዱ በተወሰነ ደረጃ ተሽከርካሪዎችን በማሳለፍና ግዚያዊ መፍትሄ ለመስጠት እየተስራ ሲሆን በቀጣይ ጉዳት የደረሰበትን ድልድይ በመጠገን ዘለቄታዊ አገልግሎትን እንዲቀጥል ይደረጋል። በመስመሩ ተጓዦችና አሽከርካሪዎች ለሚያጋጥማችሁ እንግልት የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ይቅርታ እየጠየቀ የተለዋጭ መንገዱ ግንባታ በአፋጣኝ እየተሰራ ሲሆን አሽከርካሪዎች በትግስት በመጠበቅና በቅደም ተከተል በመተላለፍ የበኩላችሁን አስተዋፅዖ እንድታደርጉልን በትህትና እንጠይቃልን።

ምንጭ: መንገዶች ባለስልጣን
@YeneTube @FikerAssefa