YeneTube
118K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በየሰፈሩ #ደመራ ለመደመር እየተዘጋጃችሁ ያላችሁ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ሰፈር ውስጥ ያዘጋጃችሁት #ደመራ መለኮስ የሚገባችሁ በየከተማችሁ ላይ የተደመረው ደመራ ሲገባደድ መሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አሳስባለች።

@YeneTube @Fikerassefa
የግብፅ ፖሊስ የርዕሠ-ከተማ ካይሮን የተሕሪር አደባባይን ዛሬ ሙሉ በሙሉ ዘግቶ ዋለ።

እንደ ግሪጎሪያኑ አቆጣጠር በ2011 የተደረገዉ ሕዝባዊ አመፅ ዋና ማዕከል የነበረዉን አደባባይ ፖሊስ የዘጋዉ ፕሬዝደንት አብድል ፈታሕ አስ ሲሲን አገዛዝ የሚቃወመዉ ሕዝብ ተቃዉሞዉን ባደባባይ እንዳያሰማ ለማገድ ነዉ።ፕሬዝደንቱና ከፍተኛ የጦር ጄኔራሎቻቸዉ በሙስና ተዘፍቀዋል የሚል ዘገባ ከተሰራጨ ወዲሕ ፕሬዝደንቱ ሥልጣን እንዲለቁ የግብፅ ሕዝብ በተለይም ወጣቶች ባደባባይ ሰልፍ እየጠየቁ ነዉ።ባለፈዉ ሳምንት አርብ በሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ በተለያዩ ከተሞች አደባባይ በመዉጣት ፕሬዝደንቱ ሥልጣን እንዲለቁ ጠይቆ ነበር።

የግብፅ ፀጥታ አስከባሪዎች ሰልፈኛዉን በአስለቃሽ ጢስ በትነዉታል።ፀጥታ አስከባሪዎች በሰልፉ ላይ ተካፍለዋል ያሏቸዉን ከ2000 በላይ ሰዎች ማሰራቸዉንም ጠበቆችና የእስረኞቹ ቤተሰቦች አስታዉቀዋል።የቀድሞዉ ጄኔራል አብደል ፈታሕ አስ ሲሲ እንደ ግሪጎሪያኑ አቆጣጠር በ2014 በሕዝብ የተመረጡትን ፕሬዝደንት መሐመድ ሙርሲን በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን አስወገደዉ የመሪነቱን ስልጣን ከያዙ ወዲሕ ሊቃወሟቸዉ በሞከሩ የሐገሪቱ ዜጎች ላይ ጠንካራ እርምጃ እየወሰዱ ነዉ።አስ ሲሲ በሰብአዊ መብት ረጋጭነት ቢወቀሱም የምዕራባዉያን መንግስታት በተለይም የዩናይትድ ስቴትስ እና የአረብ ነግስታት ጠንካራ ድጋፍና ርዳታ አልተለያቸዉም።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
የ2012 ደመራ ማስታወሻ:- መስቀል አደባባይ መግቢያ ላይ በፍተሻ የተያዙ "ቁሳቁሶች"።

@YeneTube @Fikerassefa
በግብፅ ከጁምዓ ፀሎት በኋላ ፕሬዚዳንት አል ሲ ሲ ከስልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰለፍ ተቀሰቀሰ

በግብፅ ከጁምዓ ፀሎት በኋላ ፕሬዚዳንት አል ሲ ሲ ከስልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰለፍ እየተካሄደ ነው፡፡

ይህንንም ተከትሎም ዋና ከተማዋ ካይሮን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከፍተኛ ውጥረት መፈጠሩ ነው እየተነገረ የሚገኘው፡፡
ከዕለተ አርብ ፀሎት በኋሏ ዋራቅ በሚባል አካባቢ ፕሬዚዳንት አል ሲ ሲ ከስልጣን እንዲለቁ የሚጠይቅ መልዕክት እያሳሙ መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ተቃዋሚዎቹ በሀገሪቱ ያለው የኑሮ መመሰቃቀል እና የሙስና መስፋፋት እንዲቆም መጠየቃቸው ተሰምቷል። የጁምዓ ተቃውሞ በደቡብ ግብፅ በምትገኘው ሉክሰር እና በቁስ አካባቢዎች መቀስቀሱም ተጠቁሟል፡፡
 

በዋና ከተማዋ ካይሮ ደግሞ የ2011 የተቃውሞ እምብርት የነበረውን የታሂር አደባባይ መግቢያ የፀጥታ አካላት እንደዘጉት ተነግሯል፡፡
ፕሬዚዳንት አል ሲ ሲ በአስተዳደራቸው ላይ የተነሳው ተቃውሞ  ተገቢ እንዳልሆነ በመግለፅ ለተቃውሞ ምንም ምክንያት የለም ያሉ ሲሆን የፀጥታ አካላት በዋና ከተማዋ የፀጥታ ቁጥጥሩን እንዲያጠናከሩ ማዘዛቸው የሚታወስ ነው፡፡

Via:- FBC
@YeneTube @Fikerassefa
በስኬት ተጀምሮ በስኬት የተጠናቀቀ ግሩም በዓል፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶኮስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እና ልጆቿ በመስቀል አደባባይ ሁልጊዜም ለመስቀል በዓል እንደሚያደርጉት ለአይን በሚያስደምም፣ ለጆሮ በሚጥም፣ መንፈስን በሐሴት በሚያመጥቅ መንፈሳዊ ትርዒት ደምቀው አድምቀዉናል። በዓሉ በታላቅ ስኬት እንዲከበር ሌት ከቀን የለፋችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ፣ እንኳን ደስ አለን።

በድጋሚ መልካም የመስቀል በዓል።
Via:- ኢንጂነር ታከሉ ኡማ
@YeneTube @Fikerassefa
"የአባቶቼን ርስት አልሰጥም
ስለ ጽዮን ዝም አልልም"

እነኚህ የሽሮ ሜዳ ወጣቶች ከላይ የተጠቀሰውን መልዕክት በቲሸርታቸው ላይ አሳትመው ወደ መስቀል አደባባይ ሲጓዙ በቲሸርታቸው ላይ ባሳተሙት #ፅሁፍ ምክንያት ወደ መስቀል አደባባይ እንዳይሄዱ ተደርገዋል።

@YeneTube @Fikerassefa
በሰላም ተከብሯል!

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የደመራ በዓል በሰላም መከበሩን አስታወቀ።

እጅግ በርካታ ቁጥር ያለው የኃይማኖቱ ተከታዮች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፣ መቀመጫቸውን ኢትዮጵያ ውስጥ ያደረጉ የውጪ ሀገራት ዲፕሎማቶች እና የተለያዩ ሀገራት ጎብኝዎች የታደሙበት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በዓሉ በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡

በያዝነው ዓመት በርካታ ህዝብ የታደመባቸው ሃይማኖታዊ እና ስፖርታዊ ዝግጅቶች በሰላም መከበራቸውን ያስተወሰው ኮሚሽኑ የደመራ በዓል በሰላም እንዲከበር ህብረተሰቡ ላደረገው ቀና ትብብር ምስጋናውን አቅርቧል፡፡በነገው ዕለት የሚከበረው የመስቀል በዓልም በሰላም እንዲከበር ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን ማስተላለፉን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ምንጭ:ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
#ቢሾፍቱ (ደብረዘይት) ደመራ አልተደመረም!!

በቢሾፍቱ (በደብረ ዘይት) ከተማ የተዘጋጀው ደመራ ሳይበራ ፕሮግራሙ ተዘግቷል። መንስዔውም የቅድስት ኪዳነምህረት ካህናት ወደ ዳመራው በተደመረበት አደባባይ ቤ/ክ የምትጠቀመውን ሰንደቅ አላማ ለምን ይዛችሁ መጣቹህ በማለት በተለያዩ አካላት #ከበሩ ሊመለሱ ችለዋል።

በዚህም ምክንያት ካህናቱ በሩ ላይ ብዙ ሰዓት ከቆሙ በዋላ ሊመለሱ ችለዋል። ይህንንም የሰሙ ወጣቱ አባቶች ሣይገኙ ደመራውን አናበራም በማለት ደመራውን ሣያበሩ በጸሎት ፕሮግራሙ ሊዘጋ ችሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፌደራል ፓሊስ ከሀገሪቱ ባንዲራ ውጪ ይዞ መገኘት እንደማይቻል ትላንት ያስታወቀ ሲሆን ዛሬ መልሶ የቤተክርስቲያን የራሷን አርማ እና ሎጎ መጠቀም እንደምትችል ማስታወቁ ይታወሳል።

Via:- #Mike_YeneTube
@YeneTube @Fikerassefa
ድሬደዋ ⬆️
ድሬደዋ ደመራ ስነስርዓት በሰላም ተጠናቋል።
@YeneTube @Fikerassefa
ባህር ዳር ⬆️
የደመራ ስነስርዓት በሰላም ተጠናቋል።
@YeneTube @Fikerassefa
መቐለ ⬆️
መቐለ የደመራ ስነስርዓት በሰላም ተጠናቋል።
ኡጋንዳ ካምፓላ ⬆️
ሀረር⬆️
የደመራ ስነስርዓት በሰላም ተጠናቋል።
@YeneTube @Fikerassefa
አርባምንጭ⬆️
የደመራ ስነስርዓት በሰላም ተጠናቋል።
ዱባይ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ⬆️

የደመራ ስነስርዓት በሰላም ተጠናቋል።
@YeneTube @Fikerassefa
ቤንሻንጉል ጉምዝ
የደመራ ስነስርዓት በሰላም ተጠናቋል።

@YeneTube @Fikerassefa
የም ልዩ ወረዳ ደሪ ከተማ የደመራ ስነስርዓት በሰላም ተጠናቋል።

@YeneTube @Fikerassefa
አዲስ አበባ⬆️
የደመራ ስነስርዓት በሰላም ተጠናቋል።
@YeneTube @Fikerassefa
በዛሬው የመስቀል ደመራ በአል አከባበር ላይ 55 የበዓሉ ታዳሚዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ህዝብ ግንኙነት እና ጉዳይ አስፈፃሚ መላከ ሕይወት አባ ወልደየሱስ ሰይፉ ለቢቢሲ ገለፁ።

መላከ ህይወት አባ ወልደየሱስ እንደገለፁት 33ቱ ምእመናን በቁጥጥር ስር የዋሉት ቤተክርስትያኗ ላይ የሚሰነዘር ጥቃት እንዲቆም የሚያወግዝ ፅሁፍ ያለበት ቲሸርት ለብሰው በመገኘታቸው ነበር።ምእመናኑ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ምክንያት የሆኑት ቲሸርቶች 'የቤተክርስትያን ጉዳይ ያገባኛል'፣ የቤተክርስትያን መቃጠልና ጥቃት ይቁም' የሚሉ ፅሁፎች ያለባቸው እንደነበሩ አባ ወልደየሱስ አስረድተዋል።

አራቱ ደግሞ የሌላ ሰው ባጅ አድርገው በመገኘታቸው በቁጥጥር ሲውሉ ቀሪዎቹ 12 የሚሆኑት ደግሞ ስለት ይዘው ተገኝተዋል በሚል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ያስረዳሉ።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች የተወሰዱት ካዛንችዝ ከሚገኘው ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደነበርና በኋላ እሳቸው ወደ ፖሊስ ጣቢያው ሄደው ሃላፊዎች ከነጋገሩ በኋላ 37 በዋስ መለቀቃቸውን መላከሕይወት አባ ወልደየሱስ ተናግረዋል።

ምንጭ:- ቢቢሲ አማርኛ
@YeneTube @Fikerassefa
ትናንት በካታር ዶሃ በተጀመረው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ለግማሽ ፍፅሜ እና ፍፃሜ አልፈዋል።

በ17ኛው የዓለም ሻምፕዮና ለኢትዮጵያ የመጀመርያ በሆነው የሴቶች 800 ሜትር የመጀመሪያ ዙር ድርቤ ወልተጂ በተወዳደረችበት ምድብ አራት 02፡02.71 ደቂቃ በመግባት አምስተኛ ሆና አጠናቃለች። ሆኖም የዓለም ከ20 ዓመት በታች ሻምፕዮኗ ከተሸናፊዎች ፈጣን ሰዓት ባስመዘገበ በሚለው ህግ ነገ መስከረም 17/2012 ዓ.ም ለሚካሄደው ግማሽ ፍፃሜ አልፋለች።

በሴቶች 3000ሜ መሰናክል የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቷ መቅደስ አበበ የግሏን ፈጣን ሰዓት በማስመዝብ ከሦስት ቀናት በኋላ ለሚደረግው የፍፃሜ ውድድር አልፋለች።በወንዶች 5000ሜ ያለፈው የዓለም ሻምፕዮኑ ሙክታር ኢድሪስ፣ የዓመቱ ፈጣን ሰዓት ባለቤት ጥላሁን ሃይሌ፣ እንዲሁም ሰለሞን ባርጋ ለፍፃሜ ውድድሩ አልፈዋል። አባዲ ሃዲስ አልተሳካለትም።

Via VOA
@YeneTube @FikerAssefa