YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.89K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
⬆️
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፋዊ ሽልማት አሸነፈ!

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በጎዳና ላይ ሩጫ ዝግጅት ዘርፍ የአለም ቁንጮ ተብሎ ተመርጧል፡፡ በLets Do This የሚታገዘው እና በእውቁ የሩጫ መጽሔት Runner’s World የሚቀርበው The Challenges Award ባለፉት ሦስት ሳምንታት ገደማ በኦንላይን ሲያካሂደው በቆየው ውድድር አንዱ ተፎካካሪ ሆኖ የቀረበው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በተወዳደረበት ዘርፍ እስከ ትናንት ሌሊት ማለትም እሁድ መስከረም 4 ቀን ከተሰጠ አጠቃላይ ድምጽ 56 በመቶውን በማግኘት አሸንፏል፡፡

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ድምጽ መሠጠት ከተጀመረበት ዕለት አንስቶ በመሪነት የዘለቀ ቢሆንም ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኙት ሌሎች ተወዳዳሪዎች ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት መጥበብ ጀምሮ ነበር፡፡ ሆኖም ኢትዮጵያዊው የውድድር አዘጋጅ ተቋም በመጨረሻዎቹ ሁለት ቀናት በርካታ ድምጽ በማግኘቱ ልዩነቱን በማስፋት ሁለተኛ ደረጃን ከያዘው እና 24 በመቶ ድምጽ ከወሰደው San Diego Beach and Bay Half Marathon ርቆ በአስተማማኝ የበላይነት ውድድሩን ጨርሷል፡፡ Bay Bridge Half በ10 በመቶ ድምጽ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል፡፡

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአለም ዙሪያ አንጋፋ ከሚባሉትና በርካታ አስርተ አመታት ካስቆጠሩት ታዋቂ የጎዳና ውድድሮች ጋር ተፎካክሮ ያመጣው ውጤት ከለጋ እድሜው ጋር ሲነጻጸር ስኬቱን አስደናቂ ያደርገዋል፡፡ ዘንድሮ 19 አመት የሚሞላው የኢትዮጵያው ውድድር ከአመት አመት እያደገ መጥቶ በመጪው ህዳር 45000 ገደማ ተሳታፊዎችን የሚያስተናግድ ሲሆን ዓለም አቀፋዊ እንግዶችም ይኖሩታል፡፡

የሽልማት ስነ ሥርዓቱ ከአንድ ወር በኋላ ኦክቶበር 18 West Kensington በሚገኘው አስደናቂው Queens Club በደማቅ ዝግጅት የሚከናወን ሲሆን በስፖርቱ አለም ከፍ ያለ ስም ያላቸው እንግሊዛዊያን ዝነኞች በዝግጅቱ ይገኛሉ፡፡ በማራቶን የቀድሞዋ የአለም ሻምፒዮን ፓውላ ራድክሊፍ፤ የፓራ ኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊዎቹ ሳራ ስቶሪ እና ታኒ ግሬይ ቶምሰን እንዲሁም የቀድሞው የእግር ኳስ ኮከብ ሪዮ ፈርዲናንድ ከእንግዶቹ መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለዚህ ስኬት እውን መሆን ድምጽ ለሰጡ፤ በተለያየ መንገድ ሌሎች እንዲሰጡ የጋበዙ፤ ጥሪ ያቀረቡና ያመቻቹትን ሁሉ በእጅጉ ያመሰግናል፡፡

Via Great Ethiopia Run
@YeneTube @Fikerassefa
በዴሞክራቲክ ኮንጎው ጀልባ ሰጥሞ 34 ሰዎች ሞቱ።

በዴሞክራቲክ ኮንጎ በኮንጎ ወንዝ ላይ መንገደኞችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ጀልባ ሰጥሞ ቢያንስ 34 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ። ፖሊስ እንዳስታወቀው ከአደጋው 76 ተሳፋሪዎች በህይወት መትረፍ የቻሉ ሲሆን በወቅቱ ጀልባው ከአቅሙ በላይ በጣም ብዙ ሰው ሳይጭን እንዳልቀረ ተገምቷል።ጀልባው ከሃገሪቱ ዋና ከተማ ኪንሻሳ በመነሳት ማይ ንዶምቤ ወደተባለችው ሰሜናዊ ግዛት እየተጓዘ ነበር።የአደጋው መንስኤ እስካሁን እንዳልታወቀ የገለጸው ፖሊስ ተሳፋሪዎቹ የውሃ ላይ መንሳፈፊያ ጃኬቶችን አድርገው ነበር ብሎ ለማሰብ እጅግ አስቸጋሪ ነው ብሏል።

በዴሞክራቲክ ኮንጎ የውሃ ላይ ጉዞ በጣም የሚዘወተር ሲሆን ጀልባዎች የተለያዩ ጭነቶችና ተሳፋሪዎች ከአቅም በላይ ጨነው ሲጓዙ መመልከት የተለመደ ነው።እስከ 40 ሜትር የሚደርስ ከፍታ ያላቸውና አንዳንዴም ባለሁለት ክፍል ትልልቅ ጀልባዎች ግልጋሎት ላይ ሲውሉ ይስተዋላል። ሁሉም ተሳፋሪዎች ደግሞ ውሃ ዋና ይችላሉ ብሎ ማሰብ ከባድ ነው።የዴሞክራቲክ ኮንጎ የአስፋልት መንገዶች በጣም የተበላሹና ከጥቅም ውጪ በመሆናቸው ብዙ የሃገሬው ሰዎች በጀልባ የሚደረጉ ጉዞዎችን ምርጫቸው ያደርጋሉ።

ምንጭ:BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የብሪታኒያ የዓለም አቀፍ ንግድ ሚኒስትር ኢትዮጵያን እየጎበኙ ነው።

የብሪታኒያ የዓለም አቀፍ ንግድ ሚኒስትር ኤልዛቤት ትረስ በኢትዮጵያ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው።ሚኒስትሯ ከዛሬ ጀምሮ በሚኖራቸው ቆይታም ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።ዛሬ ረፋድ ላይም ሚኒስትሯ ከኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረእግዚአብሄር ጋር የሚወያዩ ይሆናል።በተጨማሪም ከውሃ፣ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ጋር በሚያደርጉት ውይይት በሀይል ልማት ዘርፍ ለብሪታኒያ ኩባንያዎች ባለው እድል ዙሪያ እንደሚነጋገሩ በኢትዮጵያ የብሪታኒያ ኤምባሲ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጿል።

ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
ቤንች ዞን!!

ጠ/ሚንስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ ዛሬ ወደ ቤንች ዞን ሚዛን አማን እንደሚያቀኑ ሰምተናል። ከዞኑ ማህበረሰብ ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።ዝርዝሩን የምንመለስበት ይሆናል።

(YeneTube)
@YeneTube @FikerAssefa
ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን የሞያሌ መንገድ ዘጋች።

ኢትዮጵያና ከኬንያ ጋር የሚያስተሳስረው የሞያሌ መስመር የተለያዩ ምርቶች የሚተላለፉበት መንገድ ነበር።ይሁንና ኬንያ በሞያሌ በኩል ከፍተኛ የሆኑ ህገ ወጥ ስራዎች በመበረከቱ መስመሩን ለመዝጋት እንደወሰነች ተገልጿል።የሞያሌ መስመር ኢትዮጵያዊያንና ኬንያዊያን ግብር ሳይከፍሉ በህገወጥ መንገድ ቡና፣ጥራጥሬ፣የጦር መሳሪያና ሌሎች የምርት አይነቶችን እያዘዋወሩ እንደሚገኙ የኬንያ የገቢዎች ባለስልጣን አስታውቋል።

ኬንያዊያን ነጋዴዎች በሞያሌ መስመር በኩል በቀን በትንሹ 50 ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ኢትዮጵያ ያስገባሉ። ባሳለፍነው ሳምንት በተደረገድንገተኛ ፍተሻም በርካታ ቁጥር ያላቸው የክላሽ ጦር መሳሪያና ጥይቶች፣ ግብር ያልተከፈለባቸው አልባሳትና ሌሎች ህገወጥ ቁሳቁሶች መያዛቸውን የአገሪቱ የገቢዎች ባለስልጣን አስታውቋል።

ኢትዮጵያና ኬንያ ሁለቱን አገራት የንግድ ግንኙነት ለማሳለጥ 536 ኪሎ ሜትር የሚረዝም መንገድ በጋራ በመገንብት ላይ ሲሆኑ በኬንያ በኩል ያለው የመንገድ ግንባታ ቢጠናቀቅም ኢትዮጵያ ገና በመገንባት ላይ ትገኛለች።ኢትዮጵያ መንገዱን ገንብታ እስከምታጠናቅቅና የጋራ ህጋዊ አሰራር እስከሚጀመር ድረስኬንያ የሞያሌ መስመርን ዘግታ እንደምትቆይ አስታውቃለች።ይሁንን በዚህ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ አቋም ምን እንደሆነ እስካሁን አልታወቀም።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበበ የፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ያለመ የቆሻሻ አወጋገድ ማስተር ፕላን እየተዘጋጀ ነው - የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን።
@YeneTube @Fikerassefa
በተያዘው በጀት ዓመት 278 አገልግሎቶች በኦንላይን ሊሰጡ ነው።

እስከ 2012 መጨረሻ ድረስ 278 አገልግሎቶች በኦንላይን ዲጂታል አገልግሎት እንደሚሰጡ የኢኖቪሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የኦንላይን ኤሌክትሮኒክስ አገልግሎት ለመተግበር 34 ተቋማትን በመምረጥ አገልግሎቱን እንዲሰጡ ወደ ተግባር ለማስገባት እየተሰራ መሆኑና ተቋማቱ የሚሰጡትን አገልግሎት ዓይነት በመለየት ወደ ሲስተሙ እንዲገቡ መደረጉን በኢኖቪሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የመንግስት ኤሌክትሮኒክስ አገልግሎቶችና አፕልኬሽኖች ልማትና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ አሸናፊ ጋዲሳ በተለይም ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ዛሬ መስከረም 5 ቀን 2011 ዓም የኖርዌ የውጭ ጉዳይ እና የመከላከያ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አኒከን ሁይትፈልድት እና ልኡካቸውን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሁለቱ ወገኖች በሁለትዮሽ፣ በቀጠናዊ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ዜና ሹመት!!

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ለስድስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጡ።

በዚህም መሰረት ከየካቲት ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ግዛት አብዩ ጌታው የገጠር መሬት አስተዳድርና አጠቃቀም ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።የጎንደር ከተማ ከንቲባ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት ዶ/ር ሙሉቀን አዳነ ጥሩነህ ደግሞ የክልሉ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሆነው መሾማቸው ነው የተመለከተው።

እንዲሁም አቶ ብርሀኑ ጣዕም ያለው የክልሉ ንግድ ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ፣ ዶ/ር ማማሩ አያሌው ሞገስ የክልሉ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጅ ልማት ቢሮ ኃላፊ እና ዶ/ር መለስ መኮንን ይመር የግብርና ቢሮ ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል።
ዶ/ር አያሌው ወንዴ መለሰ ደግሞ የጣና ሐይቅና ሌሎች የውሃ ነክ አካላት ጥበቃና ልማት ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው እንዲያገለግሉ መሾማቸውን የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

ምንጭ: ፋና
@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር የ“ጊፋታ አዋርድ” ሽልማት ተበረከተላቸዉ።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ “ ጊፋታ አዋርድ” የተሰኘ የምስጋናና የእዉቅና ሽልማት ተበረከተላቸዉ፡፡በወላይታ ሶዶ “አርአያዎቻችን በረከቶቻችን ናቸው” በሚል መሪ ሀሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ የምስጋናና እውቅና ስነ-ስርዓት ተካሂዷል፡፡ በስነ-ስርዓቱም አቶ ኃይለማርያምን ጨምሮ በተለዩ 5 ዘርፎች በአገርና በአለም አቀፍ ደረጃ በጎ ተጽዕኖ የፈጠሩ 45 ግለሰቦች የምስጋናና የእውቅና ሽልማትም ተበርክቶላቸዋል፡፡

“ጊዜው የይቅርታ ነው” ያሉት አቶ ኃይለማሪያም በነበራቸው የስልጣን ቆይታ ወቅት የተፈጠሩ ስህተቶችን ህዝቡ ይቅር እንዲላቸው በመጠየቅ በቀጣይም ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል።
የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ አንዱአለም ሳይዳ እንዳሉት መቻቻል፣ መከባበር፣ ይቅርታ፣ እርቅና መሰል የብሄሩ ዕሴቶችን በማጎልበት የተጀመረውን አገራዊ የለውጥ ጉዞ ለመደገፍ ዓላማ ያደረገ ስነ-ስርዓት ነው፡፡

ምንጭ፡- ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
👍1
⬆️የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት የሀገር ፍቅር ቴአትር ዋና ዳይሬክተርን ከሀላፊነት አንስተዋል!

ደብዳቤው ላይ እንደሚታየው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቴአትር ቤቱ ከጥበብ ቤትነት ይልቅ ወደ “መጠጥ ሽያጭ ቤትነት” እያደላ መምጣቱን ይገልፃል።
@Yenetube @FikerAssefa
የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪው ሲፒጄ ባወጣው ዘገባ ኤርትራ በዓለም አንደኛ የሚድያ አፈና ፈፃሚ ስትሆን ሰሜን ኮርያ ሁለተኛ፣ እንዲሁም ቱርክመኒስታን ሦስተኛ መሆናቸውን አስታወቀ።

ድርጅቱ አክሎ እነዚህ ሀገራት ውስጥ ሚድያዎች የመንግሥት አፈ-ቀላጤ ከመሆን ውጪ ሌላ ሥራ እንደማይሰሩ ገልፆ በኤርትራ ብቻ በቅርብ ዓመታት ሰባት ጋዜጠኞች የት እንደገቡ እንደማይታወቅ ይፋ አድርጓል።

@Yenetube @FikerAssefa
ሱዳን እና ኤርትራ በወታደራዊ እና ደህንነት ዘርፎች በጋራ ለመስራት ተስማሙ፡፡

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሱዳን የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፤

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስማ ሙሃሞድ አብደላህ በኢሳያስ አፈወርቂ በሱዳን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ሁለቱ ሀገራት በወታደራዊ እና ደህንነት ዙሪያ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሰቸውን ተናግረዋል፡፡

ሀገራቱ በእግረኛ ጦር፣ አየር እና ውሃ ሃይል ወታደራዊ ዘርፎች፤ የመከላከያ ኢንዱሰትሪ እና ጤና አገልግሎት በትብብር ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል ነው ያሉት፡፡

ወሰን ተሻጋሪ ወንጀሎችን መከላል፣ መረጃዎችን መለዋወጥ እና የአቅም ግንባታ ላይ መስራት ሌላው የስምምነት መስክ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

ምንጭ:- FBC
@Yenetube @FikerAssefa
ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች⬇️

የ2012 የትምህርት ዘመን ምዝገባ መስከረም 26 እና 27 ቀን 2012 ዓ.ም የሚከናወን ስለሆነ ከመስከረም 24 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲያችን መግባት እንደምትችሉ እያሳወቅን ዘግይተው የሚመጡ ተማሪዎች በቅጣት ምዝገባ የሚካሄደው ትምህርት በሚጀመርበት መስከረም 28 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች ብቻ ከመስከረም 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ግቢ ገብተው ምዝገባ መስከረም 11-12/2012 ዓ.ም የሚካሄድ ይሆናል፡፡

@Yenetube @FikerAssefa
ኢትዮጵያ ተጨማሪ ዩኒቨርሲቲዎችን የመገንባት እቅድ እንደሌላት አስታወቀች፡፡

አሁን ላይ በኢትዮጵያ 45 የመንግስት ዩንቨርሲቲዎች በየዓመቱ ተማሪዎችን ተቀብለው በማስተማር ላይ ናቸው።

325 ሚሊዮን አካባቢ የህዝብ ብዛት ያላት አሜሪካ ከ3 ሺህ 500 በላይ ዩንቨርሲቲዎች ያሏት ሲሆን ከ1 ቢሊዮን በላይ ህዝብ ብዛት ያላት አፍሪካ ያሏት ዩንቨርሲቲዎች ግን 740 ብቻ ናቸው።

በኢትዮጵያም በየዓመቱ እድሜው ለከፍተኛ ትምህርት የሚደርሰው ህዝብ ብዛት በአማካኝ ስምንት ሚሊዮን ሲሆን ወደ ዩንቨርሲቲዎች ማለትም በግልና በመንግስት ዩንቨርሲቲዎች የሚገቡት ተደምሮ ከአንድ ሚሊዮን በታች እንደሆነ የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ ሪፖርት ያስረዳል።

ይሁንና ኢትዮጵያ አሁን ላይ ተጨማሪ ዩንቨርሲቲዎችን የመገንብት እቅድ የለኝም ብላለች።

በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ደቻሳ ጉርሙ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለጹት መንግስት በቀጣይ የዩኒቨርሲቲዎችን አቅም የማጠናከር ስራ ላይ ትኩረቱን ያደርጋል፡፡

የዩኒቨርሲቲዎች መብዛት ብቻውን የትምህርት ጥራትን ሊያረጋግጥ ስለማይችል አዲስ ዩንቨርሲቲዎችን ከመገንባት ይልቅ ከዚህ በፊት የተገነቡትን በግብአት ማጠናከርና በቴክኒዮሎጂ ማዘመን ላይ ልዩ ትኩረት ይደረጋልም ብለዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የቅበላ አቅማቸው ከፍላጎቱ ጋር ሲነጻጸር ተመጣጣኝ ነው ወይ ብለን ላነሳንላቸው ጥያቄ በዚህ አመት የሚገቡ ተማሪዎችን ማስተናገድ ይችላሉ፤በሚቀጥሉት አመታትም ግንባታቸው ያልተጠናቀቁ ሶስተኛና አራተኛ ትውልድ የሚባሉት ዩኒቨርሲቲዎች ግንባታቸው ተጠናቆ በሙሉ አቅማቸው መቀበል ስለሚጀምሩ ምንም አይነት ክፍተት አይፈጠርም ብለውናል፡፡

በተጨማሪም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በርካታ ተማሪዎችን በመቀበል እያስተማሩ በመሆኑ ለተወሰኑ አመታት አዳዲስ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች አይከፈቱም ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡

ምንጭ:- EthioFM
@Yenetube @FikerAssefa
#FakeNewsAlert

"ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከጠ/ሚር ቢሮ ተባረረ" ተብሎ በአንዳንድ የፌስቡክ ገፆች የተፃፈው የሀሰት መረጃ እንደሆነ ከተለያዩ ቦታዎች ለማረጋገጥ ችያለሁ።

Via :- Elias meseret
@Yenetube @Fikerassefa
በአባይ ግድብ ላይ ለዓመታት የተካሄድው ውይይት ውጤት አላመጣም።
-የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

ግብጽ ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታንና የውሃ መሙላት ሂደትን በተመለከተ ለአራት ዓመታት ሲካሄድ የነበረው የሦስትዮሽ ውይይት ምንም ውጤት እንዳላመጣ የግብጹ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚህ ሹህሪ ተናገሩ።
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ካይሮ ውስጥ ከኬኒያዋ አቻቸው ሞኒካ ጁማ ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው ይህንን የተናገሩት።ሳሚህ ሹህሪ እንዳሉት ሃገራቸው ከአባይ የምታገኘውን የውሃ ድርሻን በከፍተኛ ደረጃ እስካልቀነሰው ድረስ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ግድብ ለመገንባት ያላትን መብት ግብጽ እውቅና እንደምትሰጥ ገልጸዋል።

ምንጭ: ቢቢሲ
@YeneTube @FikerAssefa