YeneTube
117K subscribers
31.5K photos
485 videos
79 files
3.88K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
Forwarded from YeneTube
ማስታወቂያ⬆️ ጤናማ በሆነ መልኩ ከበቂ የባለሙያ ምክር ጋር የሰውነት ክብደትዎን ለመቆጣጠር እንዲሁም ቦርጮን ለማጥፋት በአማራጭ ያሉ የሰውነት ክብደት መቀነሻዎችን ይጠቀሙ።
@ABENIFAB
+251912690194 @ETHIOAMAZON2
የአዲስ ዓመት በዓል ከድንገተኛ አደጋና ወንጀል ድርጊቶች ነጻ በሆነ መልኩ መከበሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በአዲስ አበባ ከተማ የአዲስ ዓመት በዓል የድንገተኛ አደጋና ከወንጀል ድርጊቶች ነጻ በሆነ መልኩ በሰላማዊ መንገድ መከበሩን የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።የኮሚሽኑ የኢንዶክትሪኔሽንና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፈንታው እንደገለጹት፥ የአዲስ ዓመት በዓል ከዋዜማው ጀምሮ እጅጉን ሰላማዊ በሆነ መልኩ ተከብሯል።

ይህ ዜና እስከተዘገበበት ድረስ “በትራፊክ አደጋ ሰው አልሞተም፤ ከባድ የአካል ጉዳት አልደረሰም፤ ከጸጥታና ከወንጀል ጉዳይ ጋር በተያያዘም ምንም የተከሰሰተ ነገር የለም” ብለዋል።የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ከህብረተሰቡ ጋር የተቀናጀ ተግባር በማከናወናቸው በዓሉ ሰላማዊ በሆነ መንገድ መከበሩን ጠቁመው፥ለዚህም ቀደም ብሎ ከመዲናው ነዋሪ ጋር ተወያይቶ ወደ ስራ በመግባቱ ውጤታማ እንዳደረገ ተናግረዋል።ህብረተሰቡ በዓሉ በሰላም አንዲከበር ከፖሊስ ጎን በመቆም ላደረገው ትብብር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የአዲስ ዓመት በዓል ከመድረሱ በፊት ወንጀልን ለመከላከል በተደረገ ዘመቻ ሀሰተኛ የብር ኖቶች፣ የውጭ አገር ገንዘቦች፣ የሀሺሽ እቃዎች፣ ሀሰተኛ ፓስፖርቶች፣ ህገ ወጥ መታወቂያዎች መያዛቸውንም ጠቅሰዋል።በሌላ በኩል በአዲስ ዓመት በዓል ምንም አይነት የእሳትና ድንገተኛ አደጋ አለመከሰቱን የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።የኮሚሽኑ የኮምዩኒኬሽ ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን መኮንን ከበዓሉ በፊት ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ በተለያዩ መንገዶች መልዕክቶችን የማስተላለፍ ስራ መከናወኑን ጠቅሰው ። በዚህም የአዲስ ዓመት በዓል ከአደጋ ነጻ ሆኖ መከበሩን ተናግረዋል።ህብረተሰቡ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ተግባራዊ በማድረግ ላሳየው ትብብርም ምስጋና ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ምንጭ: ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
ለኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ነባር የመደበኛ መርሀ ግብር ተማሪዎች በሙሉ!!

ኣክሱም ዩኒቨርሲቲ እንኳን ለ 2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ እያለ የ2012 የትምህርት ዘመን የምዝገባ መርሀ ግብር

1) ለጤና ሳይንስ ነባር የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች መስከረም 8 እና 9 ቀን 2012
ዓ.ም

2) ለሌሎች ነባር ቅድመ ምረቃና ድህረ ምረቃ የመደበኛ መርሀ ግብር ተማሪዎች
መስከረም 19 እና 20 ቀን 2012 ዓ.ም መሆኑን ይገልፃል፡፡

የአንደኛ ዓመት ቅድመ ምረቃና ድህረ ምረቃ የመደበኛ መርሀ ግብር ተማሪዎች
የምዝገባ ጊዜ ወደፊት ይገለፃል።

የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
በያዝነዉ የግሪጎሪያን 2019 ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ዉስጥ ብቻ 11 ሚሊዮን ያሕል ሕዝብ ከቤት ንብረቱi መፈናቀሉ ተዘገበ።

IDMC በሚል ምሕፃረ ቃል የሚጠራዉ ዓለም አቀፍ የተፈናቃዮች ጉዳይ አጥኚ ድርጅት እንደሚለዉ ከጥር እስከ ሰኔ ማብቂያ በነበረዉ ስድስት ወር በደረሰ የተፈጥሮ አደጋ 7 ሚሊዮን ሰዉ ከቤት ንብረቱ ተፈናቅሏል።በዚሁ ጊዜ በተለያዩ ሐገራት የተደረጉና የሚደረጉ ጦርነትና ግጭቶች ደግሞ ከ3.8 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ አፈናቅለዋል።በጥናቱ መሠረት በጦርነትና ግጭት በርካታ ሕዝብ ከተፈናቀለባቸዉ ሐገራት አንዷ ኢትዮጵያ ናት።ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ሶሪያ፣ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና የመንን የሚያብጠዉ ጦርነትና ግጭት በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ አፈናቅሏል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa
በጠርሙስ በላኩት መልዕክት ሕይወታቸው የተረፈው ቤተሰብ።


አሜሪካ ውስጥ ባላሰቡት ሁኔታ የውሃ ፏፏቴ ውስጥ ገብተው አደጋ ላይ የነበሩ ሦስት የቤተሰብ አባላት ለማንኛውም ብለው የድረሱልን መልዕክታቸውን በጠርሙስ ላይ ጽፈው ወደ ወንዝ ከተው ነበር።በሚያስገርም ሁኔታ በጠርሙሱ ላይ የነበረውን መልዕክት ሰዎች አግኝተው የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ሕይወታቸውን መታደግ ችለዋል።

ከርቲስ ዊትሰን፣ የፍቅር ጓደኛውና የ13 ዓመት ልጃቸው ባሳለፍነው ሰኔ ወር ላይ ነበር ወደ ማዕከላዊ ካሊፎርኒያ ግዛት በመሄድ የቤተሰብ ጉዟቸውን የጀመሩት። እቅዳቸው ደግሞ አሮዮ ሴኮ የተባለውን ወንዝ በመከተል መጨረሻ ላይ የሚገኘውን ፏፏቴ መመልከት ነበር።ልክ ፏፏቴው ጋር ሲደርሱም በገመድ ታግዘው በመውረድ እዛው አካባቢ ጊዜያዊ መጠለያቸውን ሠርተው ለመቆት ነበር ያሰቡት።በሦስተኛው ቀን ግን ከትልልቅ ቋጥኞች ሥር መውጣት በማይችሉበት ሁኔታ እራሳቸውን አግኝተዋል።ቋጥኞቹ በሁለቱም በኩል 15 ሜትር ወደላይ ከፍታ ያላቸው ሲሆን፤ ይዘውት የነበረውም ገመድ ወደታች ለመውረድ እንጂ ወደላይ ለመውጣት የሚያገለግል አልነበረም።በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ፤ እነሱ የነበሩበትና በቋጥኞቹ መካከል ያለው ቦታ ከወንዙ በሚመጣ ውሃ መሞላት ጀመረ።''ውሃው ከፍ እያለ ሲመጣና ምን አይነት አደጋ ውስጥ እንደገባን ስረዳ ልቤ ቀጥ ብላ ነበር'' ብሏል ከርቲስ ከሲኤንኤን ጋር ባደረገው ቆይታ።

ምንም አይነት የስልክ ኔትዎርክ በቦታው ስላልነበር የድረሱልን መልዕክት ማስተላለፍ እንኳን አቅቶት የቆየው ቤተሰብ በመጨረሻ ያለውን አማራጭ ለመጠቀም ወሰነ።በእጃቸው ላይ የነበረውን ጠርሙስ በመፈቅፈቅ ''በፏፏቴው በኩል መውጣት አቅቶን ተይዘናል፤ እባካችሁ ድረሱልን'' የሚል መልእክት ጽፈው ወደ ወንዙ ወረወሩት።ጠርሙሱ ግማሽ ኪሎ ሜትር ያህል በወንዙ ላይ እየተንሳፈፈ ከተጓዘ በኋላ በአካባቢው ጉዞ እያደረጉ የነበሩ ሁለት ሰዎች ያገኙታል።ወዲያውም ጉዳዩን ለአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ያሳውቃሉ።የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችም ወዲያው ፍለጋቸውን የጀመሩ ሲሆን፤ እኩለ ሌሊት አካባቢ ሦስቱንም የቤተሰብ አባለት ከባድ የሚባል ጉዳት ሳይደርስባቸው አግኝተዋቸዋል።ከርቲስ ዊትሰን እና ቤተሰቡ "ሕይወታችን በመትረፉ እጅግ ደስተኞች ነን። ሕይወታችንን ያተረፉት እነዛ ሁለት ተጓዦችን አግኝተን ማመስገን እንፈለጋለን" ብለዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ለአዲግራት ዩንቨርስቲ ነባር የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን መስከረም 5 እና 6/2012ዓ/ም መሆኑ አውቃችሁ በተጠቀሰው ቀን ተገኝታችሁ እንድትመዘገቡና ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ እናሳውቃለን።

ሬጅስትራር ፅ/ቤት
@YeneTube @FikerAssefa
Forwarded from YeneTube
HAPPY NEW YEAR!
RJ SHOES presents to you all the latest,variety and catchy brand shoes.
We have all kind of shoes for adults and kids with a fairly affordable price.
👉Adress:-Addis ababa(Gerji mebrat haile)
👉Phone:-+251900628132
:-+251911859997
👉We have a 2 days return policy.
👉Flexible Shoe order with Customers Desire.
👉Delivery to Regional distincts
👉We Are Trustworthy and Best suited for Customers wish.
To Join us on telegram click here👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAE3CCBtJE8NBy8ZShA
Forwarded from YeneTube
የሴቶች አልባሣት እና ኮስሞቲክስ ማዘዝ ምትፈልጉ ገፃችን ላይ ያገኛሉ ከታች ባለው ሊንክ መርጠው ይላኩልን

የአውሮፓ ስታዳርድ
Imported from England
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/AAAAAFW3ZmuRfJiwNyWX7g
Forwarded from YeneTube
ማስታወቂያ⬆️ ጤናማ በሆነ መልኩ ከበቂ የባለሙያ ምክር ጋር የሰውነት ክብደትዎን ለመቆጣጠር እንዲሁም ቦርጮን ለማጥፋት በአማራጭ ያሉ የሰውነት ክብደት መቀነሻዎችን ይጠቀሙ።
@ABENIFAB
+251912690194 @ETHIOAMAZON2
አዋሽ ኤፍ ኤም ራዲዮ ጣቢያ የማን ነው?

ከቅርብ ቀናት ወዲህ አዋሽ ኤፍ ኤም የተባለ ራዲዮ አዲስ አበባና አካባቢው ስርጭት እያካሄደ ነው።ስርጭቱ ባለፉት ዓመታት ዛሚ ኤፍ ኤም ሲተላለፍበት በነበረው 90.7 የአየር ሞገድ እየተላለፈ ይገኛል። በርካቶች በኪሳራና በፖለቲካዊ ምክን ያቶች ለመዘጋት ተቃርቦ የነበረው ዛሚ ኤፍ ኤም ለሌላ ወገን ተሽጦ መተላለፉን ሲተነብዩ ስንብተዋል።

የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ስራ አስኪያጅ ጃዋር መሀመድ ይህን ራዲዮ ጣቢያን መግዛቱ ሲነገር ነበር። ጃዋር መሀመድም ስለ አዋሸ ራዲዮ (የቀድሞው ዛሚ) በአዲስ መልክ ስራ መጀመር በማህበራዊ ገፁ አጋርቷል። ይህም የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ አዋሽ ራዲዮን ሙሉ በሙሉ አልያም በከፊል ገዝቶታል የሚለውን ግምት አጠናክሮታል።ዛሚ የወይዘሮ ሚሚ ስብሀቱና የባለቤታቸው የአቶ ዘሪሁን ተሾመ ንብረት ነው።በኢትዮጵያ ብሮድካስት ህግ መሰረት ለአንድ ራዲዮ ጣቢያ የተሰጠ የራዲዮ ሞገድ በሽያጭም ሆነ በዝውውር ወደ ሌላ እንዲተላለፍ አይፈቅድም። ጉዳዩን አስመልክቶ የሚመለከታቸውን የመንግስት አካላት ዋዜማ ራዲዮ አነጋግሯል።

የዛሚ ስራ አስኪያጅና ባለቤት አቶ ዘርይሁን ተሾመ:

ዛሚ ሬድዩ ጣቢያ ተሸጠ እየተባለ እየተናፈሰ ያለው ወሬ ከእውነት የራቀ ነው። ዛሚ የስም ቅያሬ አርጎ በአዲስ መልክ ስራ ጀምሯል ፣ እስካሁን ለማንም አልሸጥንም ከዚ በፊት ከናሁ ቲቪ ጋር ለሽያጭ ውል የተዋዋልን ቢሆንም ስላልተስማማን በፍርድ ቤት በግልግል ዳኝነት ላይ ነን ያለነው፡፡ ነገር ግን አሁን እየተባለ ያለው ፍፁም ውሸት ነው። ይህን ቃለምልልስ እስከሰጠሁበት ደቂቃ ዛሚ ለማንም አልተሽጠም። ነገ ከነገ ወዲያ የተወሰነ ድርሻ ልንሸጥ እንችላለን፣ ምክንያቱም ቢዝነስ ነው። በአሁኑ ሰአት ሬድዩ ጣቢያችን በአዲስ ስያሜ ፤ በአዲስ አመራር ወደስራ እየገባን ነው እንጂ ምንም የተሸጠ ነገር የለም – ሲሉ ተናግረዋል፡፡

[ዋዜማ ራዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባ ከአዲስ ዓመት ዋዜማ አንስቶ በትራፊክ አደጋ 4 ሰዎች ሞተዋል።

የከተማዋ ፖሊስ ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለፀው ከ2012 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በአል ዋዜማ አንስቶ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 4 ሰዎች ሲሞቱ በ2 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።ይሁንና አደጋውን ያደረሱት አሽከርካሪዎች ተጎጅዎችን ጥለው በማምለጣቸው ፖሊስ ከተጠርጣሪዎቹን በማሰስ ላይ የገኛል።ከነዋሪዎች የሚሰወር ነገር የለምና ተጠርጣሪዎችን ካያችሁ ጠቁሙኝ ብሏል።በአንፃሩ በከተማዋ ከዋዜማው ጀምሮ እስከ በዓሉ ድረስ ምንም የእሳት አደጋ አልደረሰም ተብሏል።

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
አዋሽ ኤፍ ኤም ራዲዮ ጣቢያ የማን ነው? ከቅርብ ቀናት ወዲህ አዋሽ ኤፍ ኤም የተባለ ራዲዮ አዲስ አበባና አካባቢው ስርጭት እያካሄደ ነው።ስርጭቱ ባለፉት ዓመታት ዛሚ ኤፍ ኤም ሲተላለፍበት በነበረው 90.7 የአየር ሞገድ እየተላለፈ ይገኛል። በርካቶች በኪሳራና በፖለቲካዊ ምክን ያቶች ለመዘጋት ተቃርቦ የነበረው ዛሚ ኤፍ ኤም ለሌላ ወገን ተሽጦ መተላለፉን ሲተነብዩ ስንብተዋል። የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ…
በተያያዘ ዜና፣ ኤል ቲቪስ ሊሽጥ ነው?

የ ኤል ቲቪ (LTV) ስራ አስኪያጅ አቶ መስፍን ብሩ የሚወራው ወሬ ውሸት ነው፡፡ ከዚህ በላይ በዚህ ጉዳይ ላይ ማውራት አልፈልግም ያሉ ሲሆን የዋዜማ ምንጮች ግን ድርጅቱን ገዛ እየተባለ ያለው አቶ ጃዋር መሀመድ ከሁለት ሳምንት በፊት ሚዲያውን እየጎበኘ እንደ ነበር የተናገሩ ሲሆን በመስሪያ ቤቱ አስተዳደር ምንም የተጣራ ነገር እንዳልተነገራቸው ለዋዜማ ተናግረዋል፡፡

የብሮድካስት ባለስልጣን ስለጉዳዩ ያውቃል?

የስም ቅያሬ እና ሚዲያን መሸጥ ህጉ ምን እንደሚል ዋዜማ ያነጋገረቻቸው የኢትዩጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ሀላፊ ዛሚ ሬድዩ የስም ቅያሬውን ያደረገው ለባለስልጣኑ አሳውቆ እንደሆነና ተሸጧል የተባለውን ግን ምንም መረጃ ወደ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እንዳልመጣ ያስረዳሉ። LTV ሆነ ዛሚ ተሽጠዋል የሚለውን በ ሶሻል ሚዲያ ላይ የተመለከትን ቢሆንም ገዝቻለሁም ሸጫለሁም ያለ አካል ወደ ባለስልጣን መስራቤቱ እንዳልመጣ ጠቁመዋል። ህጉ መሸጥን ይፈቅዳል ብለን ላቀረብንላቸው ጥያቄ መሸጥ አይቻልም ፣ እቃቸውን መሸጥ እንጂ ፍሪኬንሲውን (የዓየር ሞገድ) መሸጥ አይቻልም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አቶ ገብረጊዩርጊስ አብርሀ የኢትዩጵያ ብሮድካስት የኮሚኒኬሽን ዳሬክተር የሚዲያዎቹ ተሸጠዋል ወይ? ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሚያውቀው ነገር ካለ? ብለን ላቀረበንላቸው ጥያቄ ‹‹ስትነግሩኝ ሰማው እንጂ መረጃው የለኝም ለመሸጥም ህጉ አይፈቅድም ›› ብለዋል።

[ዋዜማ ራዲዮ]
@YeneTube @FikerAssefa
የመጀመሪያው የወባ ክትባት በኬንያ ስራ ላይ ዋለ

የመጀመሪያው ፍቱን የወባ ክትባት በዛሬው ዕለት በኬንያ ስራ ላይ መዋሉ ተገልጿል፡፡

ክትባቱ በአፍሪካ አህጉር ደረጃ በጋና፣ ማላዊ እና ኬንያ ስራ ላይ እንደዋለ ተነግሯል፡፡

ክትባቱ በሶስቱ ሀገራት እድሜያቸው ከሁለት ዓመት በታች ለሆነ 300 ሺህ ህፃናት በየዓመቱ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

በዓመት በወባ ምክንያት ከሚሞቱ 400 ሺህ ሰዎች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት የሚገኙ ህፃናት መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ክትባቱ ውጤታማ መሆኑን የገለፀው የዓለም የጤና ድርጅት ከክትባቱ ጎን ለጎን አጎበር መጠቀሙና መድሃኒት መርጨቱም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስቧል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ
@YeneTube @Fikerassefa
ትናንት በቡራዩ በኦሮሚያ አድማ በታኝ ፖሊስ ላይ በደረሰው የቦንብ ጥቃት 9 ሰዎች ቆሰሉ።

ትናንት ምሽት 1:30 ገደማ በቡራዩ በኦሮሚያ አድማ በታኝ ፖሊስ ማረፊያ ቦታ ላይ በደረሰው የቦምብ ጥቃት 9 ሰዎች ላይ ቀላል የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ተገልጿል፡፡ጥቃት ከደረሰባቸው 9 ሰዎች መካከል አንዱ ሕክምና ተደርጎለት ወደ ቤት የተመለሰ ሲሆን፣ ስምንቱ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ሆስፒታል ተልከው ሕክምና እያገኙ ነው ተብሏል፡፡

ጥቃት ከደረሰባቸው ሰዎች ውስጥ አንዷ ለፖሊሶች ምግብ የምታዘጋጅ እንደሆነች ተገልጿል፡፡ጥቃት በማድረስ የተጠረጠሩት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ከኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት የ2012 ዓ.ም. መማር ማስተማርና የተማሪዎች ቅበላ ዝግጅትን አስመልክቶ ውይይት አደረገ

ዶክተር ፋሲል ንጉሴ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ዲን ከ 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ለሚገቡ አዲስ ተማሪዎች በ 4 ዓመት ቆይታ ጊዜአቸው ተማሪዎቹን መሰረታዊ እውቀት ሊያስጨብጧቸው የሚችሉ የትምህርት ዓይነቶች እንደሚሰጡና ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደትን ለማረጋገጥ የሚያስችል በቂ የዝግጅት ምዕራፍ እንደተወጠነ ገልጸዋል፡፡

“ለሰላም መደፍረስ መነሻ የሚሆኑ ጉዳዮችን እየለየን ከሚመለከታቸው ጋር በማቀናጀት መፍትሔ እንዲያገኙ እንጥራለን፤የመማር ማስተማር ሂደቱ መስመሩን ጠብቆ እንዲሄድ የቁጥጥር ሥርአቶችን አጠናክረን እንቀጥላለን፤ብሔርን፣ሀይማኖትንና ፖለቲካን መሰረት ያላደረጉ የዶርም ድልድሎችን እናደርጋለን” በማለት ዶ/ር ፋሲል በ 2012 ዓ.ም. ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደትን ለማረጋገጥ የምንከተላቸው አቅጣጫዎች በሚል ርእስ ባቀረቡት ፕረዘንቴሽን ላይ ጠቁመዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃናም የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ዲን የጠቆሙትን ሲያጠናክሩ “ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ በብሔር እየተደራጁ የሚመጡ ማናቸውም አይነት የተማሪዎች አደረጃጀት፣የተማሪዎች ክበባት ወዘተ አናስተናግድም” በማለት አሳስበዋል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ተፈጥረው በነበሩ ብሔር ተኮር የተማሪዎች ግጭትን አስመልክተው ዶ/ር ፋሲል የሚከተለውን ብለዋል፡- “ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮ በዩኒቨርሲቲያችን ውስጥ በብሔርና በሃይማኖት መሰባሰብ፣መከፋፈል፣መጣላት፣መደባደብ የንብረት የአካልና የሕይወት መጥፋት ጉዳት የማድረስ እኩይ ተግባራት እንዳይኖሩ ተቋማችን ጠንክሮ ይሰራል” በማለት አስረድተዋል፡፡

በዋነኝነት ለ 2012 ዓ.ም. አዲስ ገቢና ነባር የቅድመ ምረቃ መርሃ ግብር ተማሪዎች የሚደረግላቸውን የአቀባበልና ኦሪየንቴሽን አሰጣጥን አስመልክተው ፕሮፌሰር ጣሰው ሲያብራሩ፡-“ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ ስራ ላይ መዋል የሚጀምር በተማሪዎች፣በወላጆቻቸውና በዩኒቨርሲቲያችን መካከል የሚፈረም ውል ይኖረናል፤ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲያችን እንደገቡ በቅድመ ምረቃ ትምህርት አስተባባሪዎች እና ነባርና ልምድ ባላቸው መምህራን ስለ ዩኒቨርሲቲያችን አጠቃላይ መረጃ ይሰጣቸዋል፤የመጀመሪያ ዓመት ለሆኑት ተማሪዎች ስለሚወስዱአቸው የትምህርት አይነቶችና ፋይዳቸው፣ ስለተማሪዎች ሥነ-ምግባር መመሪያና ስለተቋማችን ሥነ-ስርአት፣ህግና ዲሲፕሊን ጉዳዮች ማብራሪያ እንዲያገኙ ይደረጋል” በሚል ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ የምጣኔ ሃብት መምህርና በአሁን ጊዜ የተቋሙ የቦርድ አባል ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተቋሙ በሚሻሻልበት ጉዳይ ላይ ሃሳባቸውን ሲሰጡ ተቋሙን በከፍተኛ ደረጃ ለማዘመንና ከሌሎች ታዋቂና ስመ-ጥር ዩኒቨርሲቲዎች ተርታ እንዲመደብ ለማስቻል የመምህራን፣የአስተዳደር፣የማህበረሰቡና የመንግስት ርብርብ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ በመድረኩ ላይ ተናግረዋል፡፡

ፕሮፌሰር ብርሃኑ እንደሃገር እንድንቀጥል ሲናገሩ፡- “የሃገሪቱ የትምህርት አወቃቀር የሚሻሻልበትን አቅጣጫ እንቀይስ፤ፈጣሪና አምራች ዜጋ እንድናገኝ ተማሪዎቻችንን በጥልቀት የሚያስቡና የሚያስተውሉ እናድርጋቸው፤ለዚህም ዩኒቨርሲቲው ጠቃሚ ሃሳቦች በነጻነት የሚንሸራሸሩበትና ልቆ የተገኘው ሃሳብ ተደማጭነትን አግኝቶ የሚተገበርበት ቁልፍ ቦታ እናድርገው” በሚል ገለጻቸውን ሰጥተዋል፡፡

Via'- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
@YeneTube @Fikerassefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሸገር 102.1 በቅዳሜ ጨዋታ እንግዳ ናቸው።

ይህን ውይይት ቅዳሜ መስከረም 3፣2012 ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት እንዲሁም በድጋሚ እሁድ መስከረም 4፣2012 ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እንድትከታተሉ ጋብዘንዋታል።

@YeneTube @FikerAssefa
ከቡራዩ ጥቃት ጋር ተያይዞ 22 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።በቡራዩ ጥቃት ጋር ተያይዞ የሸኔ ሽፍታ አባላትና ሌሎች ከእነሱ ጋር ትስስር ያላቸው 22 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ምንጭ:ETV
@YeneTube @FikerAssefa
የጅማ አባ ጅፋር ቤተ መንግስት የእደሳት ስራ ተጀምሯል፡፡

የጅማ አባ ጅፋር ቤተ መንግስት የእድሳት ስራ በሀገር ውስጥ እና በአሜሪካ ባለሙያዎች መከናወን ጀምሯል፡፡የእድሳት ስራውን የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ መኪዩ መሀመድ ተዘዋውረው ያዩ ሲሆን አስፈላጊው ድጋፍ ና ክክትል እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡ለቤተ መንግስቱ እድሳት አሜሪካ ድጋፍ እንደምታደርግ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ራይና ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር ጅማ ከተማንና ቤተ መንግስቱን በጎበኙበት ወቅት መግለፃቸው ይታወሳል፡፡የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን፣የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና የአሜሪካ ኢምባሲ 7.9 ሚሊዮን ብር ወጪ በማውጣት የቤተ መንግስቱን የእደሳት ስራውን በማከናወን ላይ መሆናቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የ10ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ውጤት ከሰዓታት በኋላ ይፋ ይሆናል።

በአገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠው የኹለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ውጤት ዛሬ መስከረም 2/2012 ከ10 ሠዓት ጀምሮ እንደሚለቀቅ ተገለፀ፡፡የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የዐስረኛ ክፍል ውጤት ዛሬ መስከረም 02/2012 ዓ.ም ከ10 ሰዓት ጀምሮ እንደሚለቀቅ ገልጾ ተማሪዎች በኤጀንሲው ድህረ ገጽ
www.neaea.gov.et/app . neaea.gov.et ወይም በአጭር የጽሁፍ መልእክት 8181 ላይ ID- በማለት አድሚሽን ቁጥራቸውን በማስገባት መመልከት እንደሚችሉ አሳውቋል፡፡

Via Addis Maleda
@YeneTube @FikerAssefa
ሊባኖሳዊው ግለሰብ ከቦሌ አየር ማረፊያ ”ታግተው” ተወሰዱ።

ሐሰን ጃበር የተባሉ ሊባኖሳዊ የንግድ ሰው በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀናት ትራንዚት በሚያደርጉበት አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ታግተው እንደተወሰዱ እና የደረሱበት እንዳልታወቀ ቤተሰባቸው አስታውቋል።

ምንጭ: አዲስ ማለዳ
@YeneTube @FikerAssefa