YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የሰላም ፌስቲቫል ዛሬ በጅጅጋ ይጀመራል

ሀገር አቀፍ የሰላም ፌስቲቫል ዛሬ በጅግጅጋ ከተማ ይጀመራል ተብሎ እየተጠበቀ ነው ።

የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት እንደገለፀው ፌስቲቫሉ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚዘልቅ ነው ።

የርእሰ መስተዳደሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሡልጣን አብዲ አሊ ሸገሕ እንደገለፁት በከተማው የሚካሔደው የሰላም ፌስቲቫል ሀገራዊ የሰላም እሴቶችን ለማጠናከር የሚረዱ የፓናል ውይይቶች ፣ ስፖርታዊ ውድድሮችና የሙዚቃ ኮንሰርት ያካተተ ነው ።

በኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስትርና የሶማሌ ክልላዊ መንግስት በጋራ ባዘጋጁት በዚሁ ፌስቲቫል ላይ የሚሳተፉ ከአራት ሺህ በላይ እንግዶችና ታዋቂ የሙዚቃ ባለሙያዎች ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል።

በፌስቲቫሉ ላይ የፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት ፣ የማህበረሰብ ተወካዮችና ከክልሎች እና ከከተማ አስተዳደር የተወጣጡ አመራሮች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪው ገልፀዋል።

ምንጭ፡-ኢዜአ
@YeneTube @FikerAssefa
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም የሕክምና ኮሌጅ የሕክምና ባለሙያዎችን እያስመረቀ ነው።

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም የሕክምና ኮሌጅ የሕክምና ባለሙያዎችን በስካይ ላይት ሆቴል እያስመረቀ ነው፡፡ኮሌጁ በቅድመ- እና ድህረ-ምረቃ መርሃ-ግብር ያሰለጠናቸውን የሕክምና ባለሙያዎችን ነው በማስመረቅ ላይ ያለው፡፡በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴና የጤና ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን ተገኝተው ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ላበረከቱም የክብር ዶክትሬቶች ይሰጣሉም ተብሏል፡፡

ምንጭ፡-ኢቢሲ
@YeneTube @FikerAssefa
የሰላም ሚኒስቴር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ዛሬ የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቪዥን አባላትን አግኝተው የልጆችን ጥያቄዎች መልሰዋል።ቆይታቸውን ከኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቪዥን መከታተል ይችላሉ።

@YeneTube @FikerAssefa
ከህዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጫ ጀኔሬተሮች ውስጥ አምስቱ ግድቡ ተጠናቆ ውኃ ከተሞላ በኋላ እንዲተከሉ ተወሰነ።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት አካል ከሚሆኑት 16 የኃይል ማመንጫ ጀኔሬተሮች መካከል አምስቱ ጀኔሬተሮች፣ የግድቡ ግንባታ ተጠናቆ የሚፈለገው ውኃ ከተሞላ በኋላ እንዲገጠሙ ተወሰነ፡፡ከፍተኛ ሀብት የሚወጣባቸው እነዚህ ውስን ጀኔሬተሮች ግድቡ ሙሉ በሙሉ በውኃ ሳይሞላ ኃይል ማመንጨት እንደማይችሉ እየታወቀ እንዲደረደሩ ማድረግ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ የሌለው፣ ይልቁንም ለእነዚህ ጀኔሬተሮች የሚወጣውን ሀብት ለሌላ ፍላጎት በማዋል ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ማስገኘት የውሳኔው ምክንያትነት እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል፡፡

ምንጭ: ሪፖርተር
@YeneTube @FikerAssefa
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፈፎች ያስተማራቸውን 774 ተማሪዎችን አስመረቀ፡፡

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፈፎች ያስተማራቸውን 774 ተማሪዎችን በ11ኛ ዙር አስመረቀ፡፡በምረቃ ስነ-ስርዓቱ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት የመሰረተ ልማትና ከተማ ልማት አማካሪና የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ዣንጥራር አባይ ለተመራቂ ተማሪዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

Via SRTN
@YeneTube @FikerAssefa
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና የእስራኤሉ አቻቸው ቤኒያሚን ኔታኒያሁ በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ በጋራ ማብራሪያ ሰጡ።

👇👇👇
https://bit.ly/2NLAGOD

@YeneTube @FikerAssefa
ሰባተኛው አመታዊው "የበጎ ሰው" የእውቅናና ሽልማት ፕሮግራም በፋና ቲቪ በቀጥታ እየተላለፈ ይገኛል። እንዲከታተሉት ጋብዘንዎታል።

@YeneTube @FikerAssefa
ቤተ ክርስቲያን ህግ እንዲከበር ለጠየቀችው ጥያቄ "መንግስት" ምላሽ ነፈጋት !!


" አስፈላጊውን ቀኖናዊና እርምጃ ቤተክርስቲያን እንደምትወስድ " ገልፃለች !!!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ! #በአቶ_በላይ_መኮንን የተጠራው የዕወጃ መርሐ ግብር ቤተ ክርስቲያን እንደማታወቀውና ድርጊቱም ሕገ ወጥ መሆኑን በመግለጽ ፤ ከቤተክርስቲያኒቱ ዕውቅናና ይሁንታ ውጭ የሚካሄደው ድርጊት "መንግሥት" እንዲያስቆም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በመግለጫ ጠይቃ ነበር።

ይሁን እንጂ ፤ የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫና ማሳሰቢያ እንዲሁም ውግዘት ወደጎን በመተው #አቶ_በላይ_መኮንን በዛሬው ዕለት መግለጫ የሰጠ ሲሆን ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሕገ-ወጥ ነው ያለችው ድርጊት "መንግሥት" እንዲያስቆም ብትጠይቅም በ"መንግሥት" በኩል ምላሽ ተነፍጎታል።

ቋሚ ሲኖዶሱ ከ2 ቀናት በፊት ፤ ከመዋቅር አፈንግጠው በወጡ ፓለቲከኞች የተጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ቤተክርስቲያን የማታውቀውና ሕገ ወጥ የሆነ ፣ ቤተክርስቲያንን ከስሯ ለመናድ የሚደረግ እንደሆነ በመግለጽ ፤ ሕዝበ ክርስቲያን በተጠንቀቅ እንዲጠብቅ ቤተክርስቲያኒቱ ያሳሰበች ሲሆን ፤ "መንግስት" ሕገ-ወጥ ድርጊቱን እንዲያስቆም በመጠየቅ ይህ የማይሆን ከሆነ አስፈላጊውን ቀኖናዊና እርምጃ ቤተክርስቲያን እንደምትወስድ መግለጿ የሚታወቅ ነው።


ምንጭ:- mereja.com
@YeneTube @FikerAssefa
የሕገ ወጥ ደላሎች ሰንሰለት የሽንኩርት ዋጋን አባብሷል

የሕገ ወጥ ደላሎች ሰንሰለት መርዘም የሽንኩርት ዋጋ ከምንጊዜውም በላይ እንዲወጣ እና ሸማቹ እንዲማረር እያደረገ ነው።

የሽንኩርት ምርት ከአምራቹ እስከ ሕጋዊ ነጋዴዎች ለመድረስ ቢያንስ ሦስት ደላሎችን ማለፍ ግድ እየሆነ መምጣቱን እና እያንዳንዳቸው ደላሎች በመኪና (በቢያጆ) ከአራት እስከ ስድስት ሺህ ብር ጭማሪ እንደሚያደርጉ በምሥራቅ ሸዋ ቦራ ወረዳ በማሊማ ቀበሌ ነዋሪ እና ሽንኩርት አምራች የሆነው ወጣት አማኑኤል ለማ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ገልጿል።

ምንጭ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
@YeneTube @FikerAssefa
ኢትዮጵያና እስራኤል በቀጣይ በግብርና: መስኖ: አይሲቲና በሌሎችም ዘርፎች የሚኖረውን ትብብር ለማጎልበት ተፈራረሙ ።

በዚሁም መሰረት:
1. በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ኢኮኖሚያዊ ትብብር በሀገራቱ ሕግና መመሪያ መሰረት በጋራ የበለጠ ለማጎልበት ተስማምተዋል፡፡

2. በግብርና ፣ በውሃ ፣ በመስኖ ልማት ፣ በጤና እና በሳይንስና በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተፈረሙ ስምምነቶችን ተግባራዊ ለማድረግ ትብብራቸውን ይበልጥ አጠናክሮ ለመቀጠል ተስማምተዋል፡፡

3. ሁለቱ ወገኖች የሳይበር ደህንነት ፣ ቴሌኮሙኒኬሽን እና የጠፈር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂን ጨምሮ በሌሎች የትብብር መስኮች ላይ ተጨማሪ ስምምነት (ቶች) ለመፈራርም የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ለመመርመር ተስማምተዋል፡፡

4. የተፈረሙ ስምምነቶችን ተፈፃሚነት ለመቆጣጠር እና በአፈፃፀም ወቅት ሊከሰቱ ለሚችሉ ችግሮች መፍትሄ ለመስጠት እንደአስፈላጊነቱ ተጨማሪ ስልቶችን ለመቀየስ ተስማምተዋል፡፡

5. በተቀመጠው ውስን የሀብት አቅም በሁለቱ አገራት መካከል የተደረጉ ስምምነቶችን አፈፃፀም ለመከለስና ለመከታተል ተስማምተዋል፡፡

ምንጭ:- ዋልታ ቲቪ
@YeneTube @FikerAssefa
'የመገናኛ ብዙሀን የህዝብ ድምፅና ስሜት ከማስተጋባት ይልቅ የግለሰብን ተክለ ስብዕና ማስተጋቢያ እንዲሆን እየተደረገ ያለው አሰራር ለማንም የማይበጅ ህዝበኝነትን የሚያነግስ' ነው ሲል የአዲስ አበባ አዴፓ ኮሚቴ ገለጸ።

@YeneTube @FikerAssefa
የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት በክልል ደረጃ እንዲዋቀር የቀረበው ጥያቄ ምላሽ በ30 ቀናት ውስጥ ቅዱስ ሲኖዶሱ እንዲያሳውቃቸው ይህ ካልተፈፀመ ግን አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ፅህፈት ቤት አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ቀሲስ በላይ መኮንን አስታውቀዋል። ይህንን ያሳወቁት ዛሬ በሰጡት መግለጫ ነው።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በበጎ ሰው ሽልማት በዘጠኝ ዘርፎች ለመጨረሻ ዕጩ ከቀረቡት ሶስት ሶስት ዕጩዎች ውስጥ የመጨረሻ አሸናፊዎች ይፋ እየተደረገ ይገኛል።


በዚህ መሰረትም እስካሁን ፦
📌 በመምህርነት ዘርፍ -ወይዘሮ ህይወት ወልደመስቀል፣
📌 በቅርስና ባህል ጥበቃ ዘርፍ- አቶ አብደልፈታህ አብደላ
📌 በሳይንስ ዘርፍ -ፕሮፌሰር ሰብስቤ ደምሰው
📌 በንግድ ስራ ፈጠራ ዘርፍ - አቶ ነጋ ቦንገር
📌 በመንግስታዊ የስራ ተቋማት ሃላፊነት ዘርፍ- አቶ ግርማ ወንዳፍራሽ
📌 በበጎ አድራጎት ዘርፍ -ዶክተር አብዱላዚዝ ኢብራሂም አሸናፊ መሆናቸው ይፋ ተደርጓል።

የበጎ ሰው ሽልማት ዋና አላማ በኢትዮጵያ በጎ የሰሩ እና ለሌሎች አራያ ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎችን ማበረታታት እና እውቅና መስጠት ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
For one chilled charity
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ካምፓስ እና ህክማናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ( ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ) ሰራተኞች እንዲሁም ሌሎች በበጎ አድራጎት ሥራ ላይ የተሰማራችሁ ግለሰቦች ድርጅቶች!!
እኛ በአመት ሁለት ጊዜ ያለፉትን ተከታታይ ስድስት አመታት ህፃናት በትምህርት መርጃ መሳሪያ እጦት ከትምህር ገበታ መቅረት የለባቸውም በሚል በራሳችን ተነሳሽነት ለህፃናቱ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች እና አልባሳትን ከተለያዩ ግለሰቦች በማሰባሰብ ድጋፍ ስናደርግ ቆይተናል የ2012 ዓ/ም ትምህርት ዘመን ሳይጀመር ደብተር ' እስኪቢርቶ' እርሳስ ' ላጲስ 'መቅረጫ እና የህፃናት አልባሳትን መለገስ ለምትፈልጉ
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ጊቢ
አቶ አየለ አዳቶ (0911851045)
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህጤሳኮ
ዶ/ር በላይሁን ክብረት (0916138486)
ዶ/ር ሰለሞን አስናቀ (0912088346)
አቶ ፍሬዘር ታደለ (0913372998)
በመደወል ድጋፋችሁን እንድታደርጉ ጥሪ እናቀርባለን
ትውልድን በማስተማር የነገ የሀገር ተስፋዎችን ለመፍጠር በጋራ እንነሳ!!!!
ዓይነ ስውራን ሰላማዊ ሰልፍ ወጡ..

" ፍትህ ለ ድረሱ ! "

ዓይነ ስውራንን ከግንዛቤ ያልከተተ የሚሰሩ ግንባታዎች እና የሚቆፈር ጉድጓዶች፤ ዓይነ ስውራንን ከሞት እስከ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ በመሆኑ ፤ እነኚህ ችግሮች እንዲቀረፉ የሚጠይቅ አይነ ስውራን ሰላማዊ አደርገዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ፤ መምህር ድረሱ የተባለ አይነ ስውር ፤ ክፍት በተተው ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ህይወቱ ያለፈ በመሆኑ ፤ ሰለፍኞች ፦ " ፍትህ ለ ድረሱ ! " በማለት ጥያቄያቸውን አሰምተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
በ7ኛው የበጎ ሰው ሽልማት በዘጠኝ ዘርፎች ለመጨረሻ ዕጩ ከቀረቡት ሶስት ሶስት ዕጩዎች ውስጥ የመጨረሻ ተሸላሚዎች ይፋ ተደርገዋል።
በዚህ መሰረትም ፦

📌 በመምህርነት ዘርፍ -ወይዘሮ ህይወት ወልደመስቀል፣
📌 በቅርስና ባህል ጥበቃ ዘርፍ- አቶ አብደልፈታህ አብደላ፣
📌 በሳይንስ ዘርፍ -ፕሮፌሰር ሰብስቤ ደምሰው፣
📌 በንግድ ስራ ፈጠራ ዘርፍ - አቶ ነጋ ቦንገር፣
📌 በመንግስታዊ የስራ ተቋማት ሃላፊነት ዘርፍ- አቶ ግርማ ወንዳፍራሽ፣
📌 በበጎ አድራጎት ዘርፍ -ዶክተር አብዱላዚዝ ኢብራሂም፣
📌 በኪነ ጥበብ ዘርፍ (በፎቶ ግራፍ ጥበብ)-አቶ በዛብህ አብተው፣
📌በሚዲያና ጋዜጠኝነት ዘርፍ -አቶ አማረ አረጋዊ ፣
📌በዳያስፖራዎች ዘርፍ - አቶ ኦባንግ ሜቶ ተሸላሚ መሆናቸው ይፋ ተደርጓል።

📌በተጨማሪም የጋሞ ሽማግሌዎች የ7ኛው የበጎ ሰው ሽልማት ልዩ ተሸላሚዎች ሆነዋል።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
እንኳዕ ንበዓል ኣሸንዳ ኣብፀሐኩም!

በአዲስ አበባ ደረጃ የአሸንዳ በዓል የማጠቃለያ ፕሮግራም በሚሊኒየም አዳራሽ በድምቀት ተከብሯል፡፡

በበዓሉ ላይ ኢ/ር ታከለ ኡማን ጨምሮ የኢፌዲሪ ፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ፣ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሄር ፣ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር ወ/ሮ ያለም ፀጋዬን ጨምሮ በአዲስ አበባ የሚኖሩ በርካታ የትግራይ ተወላጆች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከእስራኤሉ ፕሬዚዳንት ሬቬን ሪቭሊን ጋር ተወያይተዋል።

በእስራኤል ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና ልዑካቸው ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሬቬን ሪቭሊን ጋር በሁለትዮሽና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በዛሬው ዕለት ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ጋር እየሩሳሌም በሚገኘው ፅህፈት ቤታቸው ሀገራቱ ያላቸውን ግንኙነት ማጠናከር በሚችሉባቸው መንገዶች ዙሪያ ተወያይተዋል።

Via Fana
@YeneTube @FikerAssefa
The average cost of 1GB of mobile data, 2019.

India: $0.2
Russia: $0.9
Malaysia: $1.1
Pakistan: $1.8
Nigeria: $2.2
#Ethiopia :around $3.0 /100br
Brazil: $3.5
Spain: $3.7
UK: $6.6
Germany: $6.9
China: $9.8
Canada: $12
US: $12.3
South Korea: $15.1
Switzerland: $20.2

(Cablecouk)
@YeneTube @FikerAssefa
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የኦሮሚያ ቤተ-ክሕነት ፅህፈት ቤት ለማቋቋም ለቀረበው ጥያቄ ቅዱስ ሲኖዱስ በ30 ቀናት ውስጥ መልስ እንዲሰጥ አደራጅ ኮሚቴው ጠየቀ።

በሊቀ-አዕላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን የሚመራው ኮሚቴ በዛሬው ዕለት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የቤተ-ክርስቲያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ በኦሮሚያ ክልል ቤተ-ክህነት እንዲቋቋም ከፈቀደ «የሰው ሐይል አመዳደቡ እና አፈፃጸሙ አደራጅ ኮሚቴ እና ጠቅላይ ቤተክህነት በጋራ» ያከናውኑታል ብሏል።
አደራጅ ኮሚቴው በዛሬው ዕለት ባለ ስድስት ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።

አደራጅ ኮሚቴው «አንድ ቅዱስ ሲኖዶስ፤ አንድ ፓትርያርክ፤ አንዲት ቤተ-ክርስቲያን» የሚል ዕምነት እንዳለው የገለጸው በሊቀ-አዕላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን የተነበበው የአቋም መግለጫ «ሌላ ሕገ ቤተ-ክርስቲያን ወይም ሌላ ቃለ-አዋዲ» ማውጣት አያስፈልግም ብሏል። ኮሚቴው ለቀረበው ጥያቄ በ30 ቀናት ውስጥ ምላሽ ካልተሰጠ «አስፈላጊውን እርምጃ» እንደሚወስድ ገልጿል።

ሥ«ከላይ በተጠየቀው መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ-ጉባኤው ተሰብስቦ የማይወስን ከሆነ የቤተ-ክርስቲያኒቱን ችግር ለመፍታት፣ የተበተኑ ምዕምናን ወደ እናት ቤተ-ክርስቲያናቸው ለመመለስ እንዲሁም በጉጉት የሚጠበቀውን በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አማኞችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ አስፈላጊውን እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን» ብሏል።

አደራጅ ኮሚቴው ሊወስድ የሚችለው «አስፈላጊ እርምጃ» ምን እንደሆነ ያለው ነገር የለም። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን በኦሮሚያ ክልል የቤተ-ክሕነት ፅህፈት ቤት ለማቋቋም ጥያቄ ያቀረበውን አደራጅ ኮሚቴ እንቅስቃሴን ተቃውማለች።

ቤተ-ክርስቲያኒቱ በጠቅላይ ቤተ-ክሕነት ምክትል ሥራ-አስኪያጅ ርዕሰ ደብር መኃሪ ኃይሉ በኩል ከዚህ ቀደም አደራጅ ኮሚቴው የኦሮሚያ ቤተክሕነት ፅህፈት ቤት ስለማቋቋም የሰጠው መግለጫ «ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን እውቅና ያልተሰጠው በመሆኑ የሚመለከተው የመንግሥት አካል ድርጊቱን እንዲያቆምልን» ስትል ጠይቃለች።

አደራጅ ኮሚቴው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን በክልል የተደራጀ ቤተ-ክሕነት ስለሌላት የምዕምናን ቁጥር ቀንሷል፤ «በክልል ደረጃ መብቷን የሚያስከብርላት አላገኘችም፤ ክብሯንም አጥታለች» ብሏል።

Via:- DW
@YeneTube @FikerAssefa