ወግ ብቻ
17.9K subscribers
513 photos
11 videos
21 files
51 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch
@zefenbicha

Creator @leul_mekonnen1
Download Telegram
ለምን 'ለምን' ሞተች??
    (ገብርኤላ ይመር)

First we mourn the grief we bear, and then later we mourn the grief we've caused"

-Meron Hadero, Kind stranger

አንዲት ከሰዓት አንድ የእስራኤል መስፍን ያስጨነቁት ጠላቶቹን ሊገጥም ከመውጣቱ በፊት ጠላቶቹን በእጁ የጣለለት እንደሆን ወደ ቤቱ ሲመለስ ሊቀበለው የወጣ ማንኛውም ነገር ሊሰዋለት ከአምላኩ ጋር ቃል ተገባባ። መስፍኑም ድል አደረጎ ወደ ቤቱ በደስታ ሲመለስ ወንድምም እሀትም ያልተወለደላት አንድያ ሴት ልጁ ልትቀበለው ወጣችና ደስ የተሰኘች ነፍሱን ስለ ገባው ቃል አዉከቸው። እርሷም አለች "አንዴ ከአምላከሀ ጋር ቃል ይዘሃልና እሰዋለሁ ግን ከዚያ በፊት ግን ከእስራኤል ልጆች ጋር ያስቆጥረኛል ላልኩት ለድንግልናዬ ላልቅስለት!"

አሸንዳ: የመስፍኑ ዮፍታሔና የልጁ ታሪክ መጽሐፈ መሣፍንት 11:34) አንደኛው የአሸንዳ በዓል አጀማመርምክንያት ሲሆን የእስራኤል ልጃገረዶች በዓመት አራቴ ስለ ዮፍታሔ ልጅ የማልቀስ ልማድ ነበራቸው። ይህም ባህል ወደ ሀገራችን ከታቦተ ጽዮን መምጣት ጋር ተያይዞ ከገቡ ትውፊቶች አንዱ ሆኖ በየዓመቱ ልጃገረዶች አሸንዳ፣ ሻደይና ሶለል ብለው የሚያዘክሩት በዓል ሆኗል።)

#ያለቀን

"ራስ ጉግሳ ወሌ ጣሉህ እንደምንም እንዳላለቅስልህ ያለቀን አይሆንም" - አዝማሪ

ነሐሴ 2014 ዓ.ም

በአንድ ነሐሴ ከሰዓት አንድ ሰውዬን ከበው የሚጨፍሩ አሸንዳ ልጃገረዶችን አልፌ ከፊታቸው ካለው ዳቦቤት ልገባ ስል ስልኬ ተንጨረጨረ። በስንት ጊዜ አንዴ የሚደውለው አጎቴ ነውና ጥሪው ሁሉ ለሆነ የቤተሰብ ጉዳይ ምልክት ስለሆነ በምን ይሆን አነሳሁለት።
ሄሎ!
"ሄሎ!"
"የት ነሽ"
ያለሁበትን ቦታ እስከ ረቂቁ ልተነትንለት አይገባምና
“መንገድ ላይ ነኝ" አልኩት
"እ! አቫዬ ስላረፈች ልንገርሽ ብዬ ነው! "

ምን ሆንኩ? ምን አለኝ?

እንደ ወጉ "ልንገርሽ ብዬ" ተብሎ የምረዳው ሞት አልነበረም ግን ሀዘን የተደጋገመበት ቤት ነውና እንደ አቫዬ ያለ ሰው ሞት እንደ ምንም በአንድ ስልክ ጥሪ የምሰማው ሆነ። ከእርሷ ሶስት ቀን በፊት መቀሌ ዶን ቦስኮ አብራኝ ከአንድ ወንበር ስትማር የነበረች የጓደኛዬን ተደፍራ ሆስፒታል መግባት የሰማው ጆሮዬ፣ ከሳምንት በፊት የኔ ዕድሜ እኩዮች የሆኑትን የአክስቶቼን ልጆች ሞት የተረዳ ጎኔ፣ እኔ ብቻ የቀረሁ እስኪመስለኝ ያለፉት ጓደኞቹን ሀዘን የተሸከመ አንጀቴ ላይ አሻዬ መጠች። መንገዴን ያወረዛ ምርቃቷ፣ ቤቷ ያላትን ሁሉ አቅርባ በልቼ ስጠረቃ የምታቀርበውን እርጎ አልጠጣም ስላት ያለቀሰቸው፣ እርሷ ብቻ የምትጠራኝ "ተምኒተይ" የሚለው ስሜ ፣ እንደ አያት በወግ እንዳንቀብራት አዲግራት መሄጃ መንገድ የሌለ መሆኑ ሁሉም እንጀቴን አላውሶ ሊያስነባኝ ሲል ወደ ዳቦ ቤቱ የዞረ ፊቱን ወደ ልጃገረዶቹ መለስኩ። ደረታቸውን እየደቁ
ይዘላሉ። ትውፊት ላወረሳቸው የአንዲት የመስፍን ሴት ልጅ ድንግልና ሳይሆን ለዓመታት አባቶቻቸው ደም ለሚቃቡትና ድል ላልነሱት ጦርነት የሚሰዋ ድንግልናቸውና ሴትነታቸው ደረታቸውን የሚደቁ መሰለኝ፣ የተቆነደደ ጸጉራቸው የልጃገረድ ውበታቸውን ከማድመቅ በላይ ሲሾረብ የተሰማቸው ህመም እኩል በቅያቸው ውድመት የቆሰለ አንጀታቸው ታየኝ። እንዳያለቅሱለት ቀን ላልተሰጣቸውና ያለቀን መጥቶ ግራ ላጋባቸው ሀዘናቸው ቀን አውጥተው ሙሾ የሚወርዱ።
ምናልባትም የቀደሙት አያቶቻቸው ተነስተው የሞቱለት ምድርን ቢያዩ እንደ ምንም ለተረሳች ለማትመለስ ህይወታቸው፣ እንደ ማንም ለወደቀ እነሱነታቸው እንዲያለቅሱ እግዜሩን በተለማመኑት ነበር። እንደ ልጃገረዶቹም የሚከሰከሱ አጥንቶቻቸውን እንደ ሻደይ

ቄጤማ በሽንጣቸው አገልድመው፣ የሚያርር አንጀታቸውን እንደ መቀነት በወገባቸው ቋጥረው፣ የፈሰሰ ደማቸውን እንደ ሥርኩል በዓይኖቻቸው ቀብተው ለሚዘነጋ መስዋእትነታቸውና ላለተረፏት ሀገራቸው ባለቀሱላትም ነበር።

ብገዛውም ከአንጀቴ የማይጠጋ ዳቦውን ትቼ፣ በመንገድ መርዶ የደነበረ በድን ሰውነቴን ይዤ ወደ ቤቱ ተመልስኩ።.

:

#ደንባራ

“ያልተገራ ፈረስ ጠቅል እያላችሁ ከማይጨው ደንብሮ ለንደን ገባላችሁ" - አዝማሪ

በአንድ ሀይስኩል ከሰዓት እንደለመድነው ቀጣዩ መምህርከመግባቱ በፊት የራፕ እና ሬጌ ሙዚቃ የምንሰማ ልጆች ተቧድነን እንበሻሸቃለን።እኛ የሬጌ ሙዚቃ ወዳድ ልጆች ግርማዊነታቸውን በማሞገስና ራሳችንን The emperors ምናምን ብለን በመጥራት የራፕ ወገኖችን ስናኳስስ የታሪክ መምህራችን ከተፍ አለ። ትላንትና ታሪኩን ካቆመበት የማይጨው ጦርነት መቀጠል ሲጀምር የሰማነው ትርክት ግን ስማችንን ከemperor ወደ ደንባራ የቀየረው ሆነ። ይሄም ግርማዊነታቸው በማይጨው ጦርነት ሽንፈት ኋላ ከቤተሰባቸው ጋር ሀገር ለቀው ለንደን መግባታቸውና የሀገር አዝማሪም በተረብ ያዜመውን ታሪኩን አስታኮ በመንገሩ ነበር።

" ያልተገራ ፈረስ ጠቅል እያላችሁ ከማይጨው ደንብሮ ለንደን ገባላችሁ"

ከዚያ ጊዜ በኋላ ለንደንን ሳስብ የደንባራ ጥርቅም ትመስለኛለች። አልተሳሳትኩም!

በዚያ ሆነው ባልኖሩበትና ባልተነኩበት ነገር የደነበረ ሀሳብ እየነዙ ራሳቸው ደንብረው የሀገር ሰውን በጦርነት የሚያደናብሩ ሰዎች በለንደንና ዘመዶቿ ጉያ ውስጥ ነው ያሉት። ደንባሮች። ከማይጨው ኋላ እንደተነሱ አባ ጠቅልን ሳይሆን የሀገርፍቅር በአንድ ጠቅልሎ ያጋመዳቸውን የእነ አባ ኮስትር ወኔ፣ ሀሳብና ብርታት የሌለብን እኛ ደግሞ አካሄዱን ለምን ብለን ለማንጠይቅበት የለንደን ደንባሮች መጫወቻ ሆነን።

#አካሄድ

"ለምን ለምን ሞተ"?

(በ1966 የአዲስአበባ ዩኒቨርht ተማሪዎች የንቅናቄ መሪያቸው የነበረውን የተማሪ ጥላሁን ግዛውን ግድያ ለመቃወም በወጡት የተማሪዎች ሰልፍ የተዜመ: “ጥላሁን ለምን ለምን ሞተ"

)

ላጠፋሁት ሁሉ ቶሎ ቀበቶ ፈተው ከሚጋረፉት አባቶች ወገን አይደለም። ለምን እንዳጠፋሁ ከእርምጃው በፊት ይጠይቀኛል። ከመልሴ ተነስቶ ለማጥፋት ሰበብ የማይሆን አመክንዮዬን ያርመኛል።

"ለምን" የምክንያትና የመፍትሔ ቋጠሮ እንደሆነች ያውቃልና ከቀበቶ በፊት ለምን? ይለኛል። ለምን?

በአንዲት የመስሪያ ቀን ከሰዓት ከተጠራሁበት ስብሰባ ተሰይሜ "አካሄድ" በሚል ቃል የታጀበውን ንግግራቸውን አደምጣለሁ። ከተሰበሰብንበት አጀንዳ ይልቅ የበዛው አካሄድ የተባለው ነገር መሆኑ አሳስቦኛል።
አስባለሁ በአንድ ትንሽዬ መስሪያ ቤት ለሚካሄድ ስብሰባ "አካሄድ" ብሎ ለመጋደል የሚቀናው ሰው ለሚኖርባት ሀገር አካሄዷን ለምን ብሎ አለመጠየቁ ያሳስበኛል። ሀገር የሚያህል የለምን ጥያቄዎችን ታቅፈን ለምን ማለትን ማን እንደቀበረብን?

ለምን ተጋደልን

ለምን ሰላም ጠፋን

ለምን ፍቅር ራቀን

ብዙ የተዋጡ ለምንኖች

ከሁሉም ደግሞ እኛ እንደ 1960 ተማሪዎች "ለምን ሞተ" ብለን የምንጠይቀው ስለ አንድ ግለሰብ ሳይሆን ሀገር ነው ያለችን። እሷስ ለምን ለምን ሞተች??

#ይፋፋምብኝ

"አብዮት ያላስነሳንባቸው ልጉም ዘመኖች ታሪካችን ከመሆን ማን ያስቀራቸዋል?"

-ጽዮን ልሳኑ, ጉራማይሌ
41👍3🔥2