ነጥብ ሁለት
“አምልኮ”
“አምልኮ” የሚለው ቃል በእብራይስጥ “አቫድ” עָבַד ሲሆን በግሪክ ደግሞ “ላትሬኦ” λατρεύω ነው፤ ይህም ለአንዱ አምላክ ብቻ በሙሉ ሁለንተና የሚቀርብ ልመና፣ ስእለት፣ማጎብደድ፣ መተናነስ፣ ስግደት፣ መገዛት ፣ አገልግሎት Adoration ነው፤ ይህም አምልኮ ለአንድ አምላክ ብቻ እንደሚገባ የመለኮታዊ ትምህርት ቅሪት ባለበት ባይብል ላይ ሰፍሯል፦
ዘዳግም 6፥13 አምላክህን ያህዌህን ፍራ እርሱንም #አምልክ תַעֲבֹ֑ד በስሙም ማል።
ዘዳግም 10፥20 አምላክህን ያህዌህን ፍራ፥ እርሱንም #አምልክ תַעֲבֹ֑ד ከእርሱም ተጣበቅ፥ በስሙም ማል።
ዘዳግም 13፥4 አምላካችሁን ያህዌህን ተከተሉ፥ እርሱንም ፍሩ፥ ትእዛዙንም ጠብቁ፥ ቃሉንም ስሙ፥ እርሱንም תַעֲבֹ֑ד፥ ከእርሱም ጋር ተጣበቁ።
ኢያሱ 24፥14 አሁንም ያህዌህን ፍሩ፥ በፍጹምም በእውነተኛም ልብ #አምልኩት תַעֲבֹ֑ד አባቶቻችሁም በወንዝ ማዶ በግብፅም ውስጥ ያመለኩአቸውን አማልክት ከእናንተ አርቁ፥ ያህዌህንም አምልኩ תַעֲבֹ֑ד ።
ሳሙኤል ቀዳማዊ 12፥20 ሳሙኤልም ሕዝቡን አለ። አትፍሩ በእውነት ይህን ክፋት ሁሉ አደረጋችሁ ነገር ግን ያህዌህን በፍጹም ልባችሁ #አምልኩት תַעֲבֹ֑ד እንጂ ያህዌህን ከመከተል ፈቀቅ አትበሉ።
ሳሙኤል ቀዳማዊ 7፥3 ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ። በሙሉ ልባችሁ ወደ ያህዌህ ከተመለሳችሁ እንግዶችን አማልክትና አስታሮትን ከመካከላችሁ አርቁ፥ ልባችሁንም ወደ ያህዌህ አቅኑ፥ እርሱንም ብቻ #አምልኩ תַעֲבֹ֑ד… ብሎ ተናገራቸው።
ማቴዎስ 4፥10 ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ #አምልክ λατρεύσεις ተብሎ ተጽፎአልና አለው።
ልብ አድርግ አንድ ማንነት ብቻ ያለው አንድ አምላክ መሆኑን ለማመልከት “እርሱን” ብቻ አምልክ በሚል በገላጭ”adjective” የተጠፈነገ ነጠላ ተውላጠ ስም እንጂ “እነርሱ” የሚል የለም፤ ታዲያ ሶስት ማንነቶች ያሉባቸውን ምስልና ሃውልት አበይት በሚባሉት በኦርቶዶክስ፣ በካቶሊክ እና በአንግሊካን አብያተ-ክርስቲያናት ለምን ይሰገዳል፣ እጣን ይጨሳት፣ ይሸረገዳል፣ ይጎባደዳል? ይህ የጣኦት አምልኮ ካልሆነ ምን እንበለው? ወገኖቻችን፦ “ለስእልና ለሃውልት የአምልኮ ስግደት ሳይሆን የፀጋ ስግደት ነው የምናደርሰው” ይላሉ፤ እርግጥ ነው የአክብሮት ስግደት ባይብል ላይ ለመላእክትና ለሰዎች አይተናል፤ ግን የት ቦታ ነው ለማይሰማና ለማይለማ ምስልና ሃውልት ስገዱ የተባለው? ከዚያ ይልቅ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፤ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም ተብሏል፦
ዘጸአት 20፥4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፤ #አትስገድላቸው፥ #አታምልካቸውምም፤
የሚገርመ የአገራችን ሰዎች እንዲህ ይፀልያሉ፦ “ዓለምን ለማዳን ሲል ኢየሱስ ክርስቶስ “ለ”ተሰቀለበት መስቀልም እስገዳለው” የዘወትር ጸሎት
“መስቀል” እንጨት፣ ብር፣ ወርቅ ወይም ብረት አይደለምን? ይህንን ቀርፆ ለእርሱ መስገድ የጣኦት ክፍል አይደለምን? ሥላሴን በጀሶ ቀርፆ ወደ እነርሱ አምላኬ እያሉ መለማመን ባእድ አምልኮ አይደለምን?
ኢሳይያስ 44፥17 #የቀረውንም #እንጨት አምላክ አድርጎ ምስል ይቀርጽበታል፤ በፊቱም ተጐንብሶ #ይሰግዳል ወደ እርሱም #እየጸለየ፦ አምላኬ ነህና አድነኝ ይላል።
ኢሳይያስ 45፥20 እናንተ ከአሕዛብ ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ፥ ተሰብስባችሁ ኑ በአንድነትም ቅረቡ፤ #የተቀረጸውን #የምስላቸውን #እንጨት የሚሸከሙና ያድን ዘንድ ወደማይችል አምላክ #የሚጸልዩ እውቀት የላቸውም።
ኤርምያስ 10፥2-5 ያህዌህ እንዲህ ይላል፦ “የአሕዛብን መንገድ አትማሩ ከሰማይ ምልክትም አትፍሩ፤ አሕዛብ ይፈሩታልና። “የአሕዛብ ልማድ” ከንቱ ነውና፤ ዛፍ ከዱር ይቈረጣል፥ በሠራተኛም እጅ በመጥረቢያ ይሠራል። በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፥ እንዳይናወጥም በችንካርና በመዶሻ ይቸነክሩታል። እንደ #ተቀረጸ ዓምድ ናቸው እነርሱም አይናገሩም፤ መራመድም አይቻላቸውማን ይሸከሙአቸዋል። ክፉ መሥራትም አይቻላቸውምና፥ ደግምም መልካም ይሠሩ ዘንድ አይችሉምና አትፍሩአቸው።
የሥላሴ፣ የመላእክት፣ የቅዱሳን ምስልና ሃውልት ክፉ መሥራትም አይቻላቸውም፤ ደግምም መልካም ይሠሩ ዘንድ አይችሉም፤ ካልቻሉ ለምን ይሰገድላቸዋል? ይህ የእኛ የሙስሊሞች ጥያቄአችን ብቻ ነው እንጂ ነቀፌታ ወይም መዘርጠጥ አይደለም፤ አላህ ከእርሱ ሌላ ሰዎች የሚያመልኩአቸውን ጣዖታት አትስደቡ ብሎናል፤ ምክንያቱም ድንበርን በማለፍ ያለእውቀት አላህን ይሰድባሉና፦
6፥108 እነዚያንም ከአላህ ሌላ “የሚጠሩዋቸውን” يَدْعُونَ ጣዖታት አትስደቡ፤ ድንበርን በማለፍ ያለእውቀት አላህን ይሰድባሉና። وَلَا تَسُبُّوا۟ ٱلَّذِينَ يَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ فَيَسُبُّوا۟ ٱللَّهَ عَدْوًۢا بِغَيْرِ عِلْمٍۢ
እኛ ሙሊለሞች የምናመልከው በአንድነቱ ሁለትነትና ሶስትነት የሌለበትን፣ በአምላክነቱ ሰውነት የሌለበትን፣ በህያውነቱ ሞት የሌለበትን፣ በሃያልነቱ ድካም የሌለበትን፣ በጥበቃ እንቅልፍ የሌለበትን የዓለማቱን ጌታ አላህ ብቻ ነው፤ ይህንን አምላክ እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው።
✍ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ወሰላሙ አለይኩም