ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.3K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ነጥብ ሁለት
“ዒባዳ”
“ዒባዳ” عبادة የሚለው ቃል “ዓበደ عَبَدَ “አመለከ” ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን “አምልኮ” ማለት ነው፤ አምልኮ የሚገባው አንዱ አምላክ አላህ ብቻ ነው፤ መልእክተኞችም የተላኩበት ጭብጥ ይህ ነው፦
16:36 በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ “አላህን #አምልኩ اعْبُدُوا፤ ጣዖትንም ራቁ” በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፤
21:25 ከአንተ በፊትም፣ እነሆ “ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና #አምልኩኝ فَاعْبُدُونِ ” በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢሆን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም።

ለናሙና ያክል እነዚህ መልእክተኞች፦
ኑሕ
23:23 ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ በእርግጥ ላክነው፡፡ ወዲያውም «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን #አምልኩ اعْبُدُوا፡፡ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ አትጠነቀቁምን» አላቸው፡፡

ሁድ
11:50 ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን ላክን አላቸው ፦ ወገኖቼ ሆይ አላህን #አምልኩ اعْبُدُوا ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፤ እናንተም ቀጣፊዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም።

ሷሊህ
7:73 ወደ ሠሙድም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን፤ አላቸው ፦ ወገኖቼ ሆይ! አላህን #አምልኩ اعْبُدُوا ፤ ከርሱ ሌላ ለናንተ ምንም አምላክ የላችሁም፤

ኢብራሂምን
29:16 ኢብራሂምንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፦ አላህን #አምልኩ اعْبُدُوا፤ ፍሩትም፤ ይሃችሁ የታውቁ ብትሆኑ ለናንተ በላጭ ነው።

ሹዐይብ
11:84 ወደ መድየንም ወንድማችውን ሹዐይብን፣ ላክን፤ አላቸው ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን #አምልኩ اعْبُدُوا፤ ከርሱ ሌላ ለናንተ አምላክ የላችሁም፤

ሙሳ
2:83 የእስራኤል ልጆችንም ጥብቅ ኪዳን አላህን እንጂ ሌላን #አታምልኩ لَا تَعْبُدُون ፤ … በማለት በያዝንባቸው ጊዜ አስታውሱ፡፡

ዒሳ
5:72 አልመሲሕም አለ፦ የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን #አምልኩ” اعْبُدُوا፤

ነብያችን
11:2 እንዲህ #በላቸው ፦ አላህን እንጂ ሌላን #አታምልኩ أَلَّا تَعْبُدُوا፤ እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላክሁ አስስጠንቂ እና አብሳሪ ነኝ።

ቁርአን ሲሶው የሚናገረው ስለ ኢባዳ ነው፣ ይህ የቁርአን አንድ ሶስተኛው የአምልኮ ጭብጥ በቀድሞዎቹ መጻሐፍት ውስጥ የተወሳ ነው፣ ለቀድሞቹ ነቢያት የመጣው የተውሂድ ትምህርት ነው በቁርአን ውስጥ የመጣው፣ በፊት ለነበሩት መልክተኞች የተባለው “አምልኩኝ” ሲሆን በነብያችን የተባለው ይህ ነው፤ ይህ ለእሳቸው እና ከእሳቸው በፊት የነበረው የተውሒድ መገሰጫ ነው፦
26:196 እርሱም ቁርኣን በቀድሞዎቹ መጻሐፍት ውስጥ “የተወሳ” ነው፡፡
23:68 የቁርኣንን ንግግሩንም አያስተነትኑምን ወይስ ለመጀመሪያዎቹ አባቶቻቸው ያልመጣ ነገር መጣባቸውን?
41:43 ከአንተ በፊት ለነበሩት መልክተኞች የተባለው “ቢጤ” እንጅ ለአንተ ሌላ አይባልም፤
21:24 ይልቁንም ከእርሱ ሌላ አማልክት ያዙን? አስረጃችሁን አምጡ፤ *ይህ እኔ ዘንድ ያለው መገሠጫ፣ ከኔ በፊትም የነበረው መገሠጫ ነው* በላቸው። በእውነቱ አብዛኞቻቸው እውነቱን አያውቁም፤ ስለዚህ እነርሱ እንቢተኞች ናቸው أَمِ ٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِهِۦٓ ءَالِهَةًۭ ۖ قُلْ هَاتُوا۟ بُرْهَٰنَكُمْ ۖ هَٰذَا ذِكْرُ مَن مَّعِىَ وَذِكْرُ مَن قَبْلِى ۗ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ ٱلْحَقَّ ۖ فَهُم مُّعْرِضُونَ ።
Or, have they taken gods besides Him? Say: Bring your proof; this is the reminder of those with me and the reminder of those before me. Nay! most of them do not know the truth, so they turn aside. Shakir translation