ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.3K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.73K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ወንድማማችነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

49፥10 *ምእመናኖች ወንድማመቾች ናቸው፡፡ በሁለት ወንድሞቻችሁም መካከል አስታርቁ*፡፡ ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህን ፍሩ፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ فَأَصْلِحُوا بَيْنَ أَخَوَيْكُمْ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ

በአማርኛችን ላይ "ወንድማማችነት"brotherhood" እና "እህትማማችነት"sisterhood" የሚሉትን የሚያቅፍ አንድ ቃል የለም። ነገር ግን ቁርኣኑ ላይ ሁለቱንም የሚያቅፍ "ኢኽወቱን" إِخْوَةٌ የሚል ቃል አለ። እንግዲህ እኔ ሆነ አማርኛው የቁርኣን ትርጉም በዚህ አርስት ላይ "ወንድማማችነት" ስል ሁለቱንም ጾታ ያቀፈ መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። አምላካችን አላህ በቁርኣን ወንድማማች የሚላቸው በሦስት ዋና ዋና ክፍል ይከፈላሉ፦

ነጥብ አንድ
"ሰብአዊ ወንድማማችነት"
የሰው ልጆች ባጠቃላይ ኑባሪያችን ሰው ነን፤ ሰብአዊነት ያገኘነው ከአባታችን አደም እና ከእናታችን ሐዋ ነው፤ ሁላችንንም የአዳም ልጆች ነን፤ አላህ ሰዎችን ሁሉ ከአንድ የአደም ስብዕና እና ከመቀናጃው ከሐዋ ብዙ ወንዶችንና ሴቶች የበተነውን ነው፦
7፥27 *የአዳም ልጆች ሆይ! ሰይጣን አባትና እናታችሁን* ኀፍረተ ገላቸውን ሊያሳያቸው ልብሶቻቸውን ከነሱ የገፈፋቸው ሲኾን ከገነት እንዳወጣቸው ሁሉ እናንተን አይሞክራችሁ፡፡ يَا بَنِي آدَمَ لَا يَفْتِنَنَّكُمُ الشَّيْطَانُ كَمَا أَخْرَجَ أَبَوَيْكُم مِّنَ الْجَنَّةِ يَنزِعُ عَنْهُمَا لِبَاسَهُمَا لِيُرِيَهُمَا سَوْآتِهِمَا ۗ إِنَّهُ يَرَاكُمْ هُوَ وَقَبِيلُهُ مِنْ حَيْثُ لَا تَرَوْنَهُمْ ۗ إِنَّا جَعَلْنَا الشَّيَاطِينَ أَوْلِيَاءَ لِلَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ
4፥1 *እናንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ የፈጠራችሁን ከእርስዋም መቀናጆዋን የፈጠረውን ከእነርሱም ብዙ ወንዶችንና ሴቶች የበተነውን ጌታችሁን ፍሩ*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ اتَّقُوا رَبَّكُمُ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَاحِدَةٍ وَخَلَقَ مِنْهَا زَوْجَهَا وَبَثَّ مِنْهُمَا رِجَالًا كَثِيرًا وَنِسَاءً ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ الَّذِي تَسَاءَلُونَ بِهِ وَالْأَرْحَامَ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلَيْكُمْ رَقِيبًا

በዚህ ወንድማማችነት ከሃድያንም ወንድምና እህት ናቸው፤ ምክንያቱም እነርሱ ድመት፣ ውሻ፣ ዝንጀሮ ሳይሆኑ ሰው ስለሆኑ፤ አምላካችን አላህ ከሃድያንን በወገን ደረጃ ለአማንያን "ወንድማቸው" በማለት ይናገራል፦
26፥106 *ወንድማቸው ኑሕ* ለእነርሱ ባላቸው ጊዜ «አትጠነቀቁምን? إِذْ قَالَ لَهُمْ أَخُوهُمْ نُوحٌ أَلَا تَتَّقُونَ
7፥56 ወደ ዓድም *ወንድማቸውን ሁድን ላክን*፡፡ «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ የአላህን ቅጣት አትፈሩምን» አላቸው፡፡ وَإِلَىٰ عَادٍ أَخَاهُمْ هُودًا ۗ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَـٰهٍ غَيْرُهُ ۚ أَفَلَا تَتَّقُونَ
11፥61 *ወደ ሰሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን*፡፡ «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ለእናንተ አምላክ የላችሁም፡፡ وَإِلَىٰ ثَمُودَ أَخَاهُمْ صَالِحًا ۚ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَـٰهٍ غَيْرُهُ ۖ هُوَ أَنشَأَكُم مِّنَ الْأَرْضِ وَاسْتَعْمَرَكُمْ فِيهَا فَاسْتَغْفِرُوهُ ثُمَّ تُوبُوا إِلَيْهِ ۚ إِنَّ رَبِّي قَرِيبٌ مُّجِيبٌ
26፥161 *ወንድማቸው ሉጥ ለእነርሱ ባለ ጊዜ «አትጠነቀቁምን?* إِذْ قَالَ لَهُمْ أَخُوهُمْ لُوطٌ أَلَا تَتَّقُونَ
11፥84 *ወደ መድየንም ወንድማቸውን ሹዐይብን ላክን*፡፡ አላቸው «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ለናንተ አምላክ የላችሁም፡፡ وَإِلَىٰ مَدْيَنَ أَخَاهُمْ شُعَيْبًا ۚ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَـٰهٍ غَيْرُهُ ۖ وَلَا تَنقُصُوا الْمِكْيَالَ وَالْمِيزَانَ ۚ إِنِّي أَرَاكُم بِخَيْرٍ وَإِنِّي أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ مُّحِيطٍ
ነጥብ ሁለት
"አብራካዊ ወንድማማችነት"
በአንድ ማህጸን የተኙ ወንድምና እህት ወይም ከአንድ አባት የሚወለዱ የአብራክ ክፋይ ወንድምና እህት ይባላሉ፦
12፥5 አባቱም አለ «ልጄ ሆይ! ሕልምህን *ለወንድሞችህ* አታውራ፡፡ ላንተ ተንኮልን ይሰሩብሃልና፡፡ ሰይጣን ለሰው ግልጽ ጠላት ነውና፡፡» قَالَ يَا بُنَيَّ لَا تَقْصُصْ رُؤْيَاكَ عَلَىٰ إِخْوَتِكَ فَيَكِيدُوا لَكَ كَيْدًا ۖ إِنَّ الشَّيْطَانَ لِلْإِنسَانِ عَدُوٌّ مُّبِينٌ
7፥151 ሙሳም፡- «ጌታዬ ሆይ! *ለእኔም ለወንድሜም ማር*፡፡ በእዝነትህም ውስጥ አግባን፡፡ አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ» አለ፡፡ قَالَ رَبِّ اغْفِرْ لِي وَلِأَخِي وَأَدْخِلْنَا فِي رَحْمَتِكَ ۖ وَأَنتَ أَرْحَمُ الرَّاحِمِينَ

ነጥብ ሦስት
"መንፈሳዊ ወንድማማችነት"
በሊላሂ መንገድ የአላህን ገመድ የያዝን አማንያን በጸጋው የሃይማኖት ወንድማማች ነን፦
11፥11 ቢጸጸቱም፣ ሶላትንም ቢሰግዱ፣ ዘካንም ቢሰጡ *የሃይማኖት ወንድሞቻችሁ ናቸው*፡፡ ለሚያውቁ ሕዝቦችም አንቀጾችን እናብራራለን፡፡ فَإِن تَابُوا وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَآتَوُا الزَّكَاةَ فَإِخْوَانُكُمْ فِي الدِّينِ ۗ وَنُفَصِّلُ الْآيَاتِ لِقَوْمٍ يَعْلَمُونَ
3፥103 *የአላህንም ገመድ ሁላችሁም ያዙ፡፡ አትለያዩም፡፡ ጠበኞችም በነበራችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ የዋለውን የአላህን ጸጋ አስታውሱ፡፡ በልቦቻችሁም መካከል አስማማ፡፡ በጸጋውም ወንድማማቾች ኾናችሁ*፡፡ وَاعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللَّهِ جَمِيعًا وَلَا تَفَرَّقُوا ۚ وَاذْكُرُوا نِعْمَتَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ كُنتُمْ أَعْدَاءً فَأَلَّفَ بَيْنَ قُلُوبِكُمْ فَأَصْبَحْتُم بِنِعْمَتِهِ إِخْوَانًا وَكُنتُمْ عَلَىٰ شَفَا حُفْرَةٍ مِّنَ النَّارِ فَأَنقَذَكُم مِّنْهَا ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمْ آيَاتِهِ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ
33፥5 ለአባቶቻቸው በማስጠጋት ጥሯቸው፡፡ እርሱ አላህ ዘንድ ትክክለኛ ነው፡፡ አባቶቻቸውንም ባታውቁ *በሃይማኖት ወንድሞቻችሁና ዘመዶቻችሁ ናቸው*፡፡ ادْعُوهُمْ لِآبَائِهِمْ هُوَ أَقْسَطُ عِندَ اللَّهِ ۚ فَإِن لَّمْ تَعْلَمُوا آبَاءَهُمْ فَإِخْوَانُكُمْ فِي الدِّينِ وَمَوَالِيكُمْ ۚ وَلَيْسَ عَلَيْكُمْ جُنَاحٌ فِيمَا أَخْطَأْتُم بِهِ وَلَـٰكِن مَّا تَعَمَّدَتْ قُلُوبُكُمْ ۚ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا
49፥10 *ምእመናኖች ወንድማመቾች ናቸው፡፡ በሁለት ወንድሞቻችሁም መካከል አስታርቁ*፡፡ ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህን ፍሩ፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ فَأَصْلِحُوا بَيْنَ أَخَوَيْكُمْ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ

ይህ የባህርይ መመሳሰል ለምሳሌ አባካኞች የሰይጣናት ወንድሞች ናቸውና፦
17፥27 *አባካኞች የሰይጣናት ወንድሞች ናቸውና*፡፡ ሰይጣንም ለጌታው ብርቱ ከሓዲ ነው፡፡ إِنَّ الْمُبَذِّرِينَ كَانُوا إِخْوَانَ الشَّيَاطِينِ ۖ وَكَانَ الشَّيْطَانُ لِرَبِّهِ كَفُورًا

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሲራጥ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

19፥71 *ከእናንተም ወደ እርሷ ወራጅ እንጂ አንድም የለም፡፡ መውረዱም ጌታህ የፈረደው ግዴታ ነው*፡፡ ከዚያም *እነዚያን የተጠነቀቁትን እናድናለን፡፡ በደለኞችንም የተንበረከኩ ኾነው በውስጧ እንተዋቸዋለን*፡፡ وَإِن مِّنكُمْ إِلَّا وَارِدُهَا ۚ كَانَ عَلَىٰ رَبِّكَ حَتْمًا مَّقْضِيًّا ثُمَّ نُنَجِّي الَّذِينَ اتَّقَوا وَّنَذَرُ الظَّالِمِينَ فِيهَا جِثِيًّا

"ዒሊዪን" عِلِّيِّين "ማለት "ከፍተኛ" ወይም "አርያም" ማለት ሲሆን "ዐሊየት" عَالِيَة ማለት ደግሞ "ከፍተኛይቱ" ማለት ነው፤ የምእምናን መጽሐፍ በእርግጥ በዒሊዮን ውስጥ ነው፦
88፥10 *በከፍተኛ ገነት* ውስጥ ናቸው፡፡ فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٍ
69፥22 *በከፍተኛይቱ ገነት* ውስጥ፡፡ فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٍ
83፥18 በእውነቱ *የእውነተኞቹ ምእምናን መጽሐፍ በዒሊዮን ውስጥ ነው*፡፡ كَلَّا إِنَّ كِتَابَ الْأَبْرَارِ لَفِي عِلِّيِّينَ

"ሢጂን" سِجِّين የሚለው ቃል "ዩሥጀነ" يُسْجَنَ ማለትም "ታሰረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "እስር" ወይም "እንጦሮጦስ" ማለት ነው፤ "ሠጅን" سِّجْن ማለት "መታሰር" ማለት ሲሆን "መሥጁኒን" مَسْجُونِين ደግሞ "እስረኞች" ማለት ነው፤ የከሓዲዎቹ መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው፦
83፥7 በእውነት *የከሓዲዎቹ መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው*፡፡ كَلَّا إِنَّ كِتَابَ الْفُجَّارِ لَفِي سِجِّينٍ

"ሲራጥ” صِرَٰط በጀነት እና በጀሀነም መካከል ያለ “ድልድይ” ነው፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 81 , ሐዲስ 124
አቢ ሠዒድ አል-ኹድሪይ"ረ.ዐ." እንደተተከው የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" አሉ፦ "ምእመናን ከእሳት ይድናሉ፤ በጀነትን እና በጀሃነም መካከል ድልድይ ይቆማል። قَالَ حَدَّثَنَا سَعِيدٌ عَنْ قَتَادَةَ عَنْ أَبِي الْمُتَوَكِّلِ النَّاجِيِّ أَنَّ أَبَا سَعِيدٍ الْخُدْرِيَّ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ يَخْلُصُ الْمُؤْمِنُونَ مِنَ النَّارِ، فَيُحْبَسُونَ عَلَى قَنْطَرَةٍ بَيْنَ الْجَنَّةِ وَالنَّارِ،

ሁሉም የሰው ልጆች ወደዚያ ድልድይ ወራጅ እንጂ አንድም የለም፤ መውረዱም ጌታህ የፈረደው ግዴታ ነው፤ ከዚያም እነዚያን የተጠነቀቁትን ይድናሉ፤ በደለኞችንም ግን የተንበረከኩ ኾነው ተንሸራተው በጀሃነም ይተዋሉ፦
19፥71 *ከእናንተም ወደ እርሷ ወራጅ እንጂ አንድም የለም፡፡ መውረዱም ጌታህ የፈረደው ግዴታ ነው*፡፡ ከዚያም *እነዚያን የተጠነቀቁትን እናድናለን፡፡ በደለኞችንም የተንበረከኩ ኾነው በውስጧ እንተዋቸዋለን*፡፡ وَإِن مِّنكُمْ إِلَّا وَارِدُهَا ۚ كَانَ عَلَىٰ رَبِّكَ حَتْمًا مَّقْضِيًّا ثُمَّ نُنَجِّي الَّذِينَ اتَّقَوا وَّنَذَرُ الظَّالِمِينَ فِيهَا جِثِيًّا
ነጥብ አንድ
"ሲራጥ"
በሱረቱል መርየም 19፥71 ላይ "ሃ" ُهَا ማለትም "እርሷ" የሚለው ሦስተኛ መደብ ተሳቢ ተውላጠ-ስም ”ሲራጥ” መሆኗን ነብያችን"ﷺ" ነግረውናል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 44, ሐዲስ 235
በሃፍሳ ፊት ከነብዩ"ﷺ" ሰምታ ኡሙ ሙበሽር እንደተረከችው፦ "በአላህ ፈቃድ የጀነት ባለቤቶች በዚያው መሠረት ታማኝነታቸውን ከሚቀበሉት መካከል ወደ እሳት አይገቡም። ሃፍሳም የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" ሆይ! ለምን?
ብላ ጠየቀቻቸው፤ እርሳቸውም ገሰጿት፤ እርሷም፦ "ከእናንተም ወደ ድልድይ ወራጅ እንጂ አንድም የለም" አለች፤ ነብዩን"ﷺ"፦ "የላቀውና ክብራማው አላህ፦ "ከዚያም እነዚያን የተጠነቀቁትን እናድናለን፡፡ በደለኞችንም የተንበረከኩ ኾነው በውስጧ እንተዋቸዋለን" ብሏል፤ አሉ። يَقُولُ أَخْبَرَتْنِي أُمُّ مُبَشِّرٍ، أَنَّهَا سَمِعَتِ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ عِنْدَ حَفْصَةَ ‏"‏ لاَ يَدْخُلُ النَّارَ إِنْ شَاءَ اللَّهُ مِنْ أَصْحَابِ الشَّجَرَةِ أَحَدٌ ‏.‏ الَّذِينَ بَايَعُوا تَحْتَهَا ‏"‏ ‏.‏ قَالَتْ بَلَى يَا رَسُولَ اللَّهِ ‏.‏ فَانْتَهَرَهَا فَقَالَتْ حَفْصَةُ ‏{‏ وَإِنْ مِنْكُمْ إِلاَّ وَارِدُهَا‏}‏ فَقَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ قَدْ قَالَ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ ‏{‏ ثُمَّ نُنَجِّي الَّذِينَ اتَّقَوْا وَنَذَرُ الظَّالِمِينَ فِيهَا جِثِيًّا‏}‏
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 17, ቁጥር 1475
ዐብደላህ ኢብኑ መሱድ እንደተረከው፤ የአላህ መልክተኛ”ﷺ” አሉ፦ "ሰዎች ወደ ድልድል ይወርዳሉ፤ ከዚያም ከርሷ በሥራቸው ይወጣሉ። Narrated Abdullah ibn Mas’ud
Allah’s Messenger (peace be upon him) said, “mankind will go down to bridge and then come up from it because of their deeds.
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ Book 37, ሐዲስ 4420
"ዓኢሻ"ረ.ዐ." ስትናገር እንደተረከችው፦ እኔ የአላህን መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ ስል ጠየኲቸው፦ "ምድር በሌላ ምድር የምትለወጥበትን ሰማያትም እንደዚሁ አንድ አሸናፊ ለኾነው አላህም ፍጡራን ሁሉ የሚገለጹበት ቀን አስታውሱ" የሚል አለ፤ ታዲያ የዚያ ቀን ሰዎች የት ይሆናሉ? እርሳቸውም፦ "በድልድይ ላይ" ሲሉ መለሱ። حَدَّثَنَا أَبُو بَكْرِ بْنُ أَبِي شَيْبَةَ، حَدَّثَنَا عَلِيُّ بْنُ مُسْهِرٍ، عَنْ دَاوُدَ، عَنِ الشَّعْبِيِّ، عَنْ مَسْرُوقٍ، عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ سَأَلْتُ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ عَنْ قَوْلِهِ ‏{يَوْمَ تُبَدَّلُ الأَرْضُ غَيْرَ الأَرْضِ وَالسَّمَوَاتُ ‏}‏ فَأَيْنَ تَكُونُ النَّاسُ يَوْمَئِذٍ قَالَ ‏"‏ عَلَى الصِّرَاطِ ‏"‏

“ዐላ” ﻋَﻠَﻰٰ ማለት “ላይ”over” ማለት ነው፤ እንጂ ውስጥ ማለት አይደለም፤ ሲቀጥል
“መውረድስ” ማለት “መግባት” ብቻ ነው ያለው ማን ነው? ውሃ ቀጂዎች ወደ ውሃ ኩሬ “ወረዱ” ማለት ውሃ ውስጥ ገቡ ማለት ነውን? አይደለም፦
12:19 *መንገደኞችም መጡ፡፡ ውሃ ቀጂያቸውንም ላኩ*፡፡ አኮሊውንም ወደ ጉድጓዱ ሰደደ «የምስራች! ይህ ወጣት ልጅ ነው» አለ፡፡ ሸቀጥ አድርገውም ደበቁት፡፡ አላህም የሚሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ وَجَاءَتْ سَيَّارَةٌ فَأَرْسَلُوا وَارِدَهُمْ فَأَدْلَىٰ دَلْوَهُ ۖ قَالَ يَا بُشْرَىٰ هَـٰذَا غُلَامٌ ۚ وَأَسَرُّوهُ بِضَاعَةً ۚ وَاللَّهُ عَلِيمٌ بِمَا يَعْمَلُونَ
28:23 *ወደ መድየንም ውሃ በወረደ* ጊዜ በእርሱ ላይ ከሰዎች ጭፍሮችን መንጋዎቻቸውን የሚያጠጡ ሆነው አገኘ፡፡ وَلَمَّا وَرَدَ مَاءَ مَدْيَنَ وَجَدَ عَلَيْهِ أُمَّةً مِّنَ النَّاسِ يَسْقُونَ وَوَجَدَ مِن دُونِهِمُ امْرَأَتَيْنِ تَذُودَانِ ۖ قَالَ مَا خَطْبُكُمَا ۖ قَالَتَا لَا نَسْقِي حَتَّىٰ يُصْدِرَ الرِّعَاءُ ۖ وَأَبُونَا شَيْخٌ كَبِيرٌ

በተመሳሳይ ሰዎች ወደ ድልድዩ ወረዱ ማለት ጀሃነም ገቡ ማለት አይደለም።
ነጥብ ሁለት
"ሙተቂን"
“ሙተቂን” ﻣُﺘَّﻘِﻴﻦ ማለት አላህን የሚፈራ "ፈሪሃ" ነው፤ አላህ ሁሉን ያየናል ብለው ከመጥፎ ድርጊት፣ ሁሉን ይሰማናል ብለው ከመጥፎ ንግግር፣ ሁሉን ያውቃል ብለው ከመጥፎ ሃሳብ የሚጠነቀቁ ሲሆን አላህ ከጀሃነም ያድናቸዋል፦
78:31 *ለጥንቁቆቹ መዳኛ ስፍራ አላቸው*። إِنَّ لِلْمُتَّقِينَ مَفَازًا
19፥72 ከዚያም *እነዚያን የተጠነቀቁትን እናድናለን*፡፡ በደለኞችንም የተንበረከኩ ኾነው በውስጧ እንተዋቸዋለን፡፡ ثُمَّ نُنَجِّي الَّذِينَ اتَّقَوا وَّنَذَرُ الظَّالِمِينَ فِيهَا جِثِيًّا

አላህ ጀነትን ያዘጋጀው ሙተቂን ለሚባሉት ባሮቹ ነው፦
3፥133 *ከጌታችሁ ወደ ኾነችም ምሕረትና ስፋትዋ እንደ ሰማያትና ምድር ወደ ኾነች ገነት ለጥንቁቆቹ የተዘጋጀች ስትኾን ተቻኮሉ*፡፡ وَسَارِعُوا إِلَىٰ مَغْفِرَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ وَجَنَّةٍ عَرْضُهَا السَّمَاوَاتُ وَالْأَرْضُ أُعِدَّتْ لِلْمُتَّقِينَ
68:34 “ለጥንቁቆቹ” በጌታቸው ዘንድ መጠቀሚያ ገነቶች አሏቸው። إِنَّ لِلْمُتَّقِينَ عِندَ رَبِّهِمْ جَنَّاتِ النَّعِيمِ
44፥51 ጥንቁቆቹ በእርግጥ በጸጥተኛ መኖሪያ ውስጥ ናቸው፡፡ إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي مَقَامٍ أَمِينٍ
77:41 ጥንቁቆቹ በጥላዎችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡ إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي ظِلَالٍ وَعُيُونٍ
38፥49 ይህ መልካም ዝና ነው፡፡ *ለጥንቁቆቹ በእርግጥ ውብ የኾነ መመለሻ አላቸው*፡፡ هَـٰذَا ذِكْرٌ ۚ وَإِنَّ لِلْمُتَّقِينَ لَحُسْنَ مَآبٍ

ስለዚህ ሙስሊሞች ሁሉ ገሃነም ይገባሉ የሚለው ፕሮፓጋንዳ ከጥራዝ-ነጠቅ ዕውቀት የሚመጣ ጥያቄ ነው፤ የሙስሊሞችማ እጣ
ፈንታ ጀነት እንደሆነ በግልፅና በማያሻማ መልኩ ተቀምጧል፦
4:124 *ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ ከበጎ ሥራዎች አንዳችን የሚሠራም ሰው እነዚያ ገነትን ይገባሉ፡፡ በተምር ፍሬ ላይ ያለችን ነጥብ ያክል እንኳ አይበደሉም*፡፡ وَمَن يَعْمَلْ مِنَ الصَّالِحَاتِ مِن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُولَـٰئِكَ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ وَلَا يُظْلَمُونَ نَقِيرًا
40:40 *እርሱ አማኝ ሆኖ ከወንድ ወይም ከሴት በጎን የሠራም ሰው እነዚያ ገነትን ይገባሉ፤ በእርሷ ውስጥ ያለ ቁጥጥር ይመገባሉ*። مَنْ عَمِلَ سَيِّئَةً فَلَا يُجْزَىٰ إِلَّا مِثْلَهَا ۖ وَمَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُولَـٰئِكَ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ يُرْزَقُونَ فِيهَا بِغَيْرِ حِسَابٍ
ነጥብ ሦስት
"ዛሊም"
"ዛሊም” ﻇَﺎﻟِﻢ ማለት “በዳይ” ማለት ሲሆን በአላህ ላይ ሌላ ሃልዎትንና ኑባሬን ማጋራት ትልቁ በደል ነው፤ አላህ በደለኞቹንም የተንበረከኩ ኾነው በውስጧ ይተዋቸዋል፦
31፥13 ሉቅማንም ለልጁ እርሱ የሚገስጸው ሲሆን፦ ልጄ ሆይ! *በአላህ አታጋራ፤ ማጋራት ታላቅ በደል ነውና* ያለውን አስታውስ። وَإِذْ قَالَ لُقْمَانُ لِابْنِهِ وَهُوَ يَعِظُهُ يَا بُنَيَّ لَا تُشْرِكْ بِاللَّهِ ۖ إِنَّ الشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ
4፥30 ወሰን በማለፍ እና *በመበደልም ይህንን የሠራ ሰው እሳትን እናገባዋለን*። ይኸም በአላህ ላይ ገር ነው፡፡ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ عُدْوَانًا وَظُلْمًا فَسَوْفَ نُصْلِيهِ نَارًا ۚ وَكَانَ ذَٰلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرًا
19፥72 ከዚያም እነዚያን የተጠነቀቁትን እናድናለን፡፡ *በደለኞችንም የተንበረከኩ ኾነው በውስጧ እንተዋቸዋለን*፡፡ ثُمَّ نُنَجِّي الَّذِينَ اتَّقَوا وَّنَذَرُ الظَّالِمِينَ فِيهَا جِثِيًّا

አላህ በደለኞቹንም የተንበረከኩ ኾነው በእሳት ውስጥ ይተዋቸዋል፤ “ፊሃ” ﻓِﻴﻬَﺎ ማለት “በእርሷ ውስጥ” የሚለው መስተዋድድ አገልግሎት ላይ የዋለው ለበደለኞች እንጂ ለሙተቂን በፍጹም አይደለም። “አምን” أَمْن ማለት “ጸጥታ” ማለት ሲሆን አላህን በማንነት ሆነ በምንነት አንድ ነው ብሎ በማመንና በብቸኝነት በማምለክ በቀልብ ላይ የሚመጣ “ጸጥታ” “መረጋጋት” እና “ሰላም” ነው፦
6፥82 *እነዚያ ያመኑ እና እምነታቸውን “በበደል” ያልቀላቀሉ እነዚያ ለእነርሱ “ጸጥታ” አላቸው*፤ እነርሱም የተመሩ ናቸው ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَلَمْ يَلْبِسُوٓا۟ إِيمَٰنَهُم بِظُلْمٍ أُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمُ ٱلْأَمْنُ وَهُم مُّهْتَدُونَ ።

የአላህ ሃቅ የሆነውን አምልኮ ለሌላ ማንነት ሆነ ምንነት መስጠት በእርሱ ላይ የሚፈፀም ዙልም ነው፤ “ዙልም” ظُلْم ማለት “በደል” ማለት ሲሆን በአላህ ላይ ማጋራት ታላቁ በደል ነው፤ ሱረቱል አንዓም 6፥82 አንቀጽ በወረደ እና በተነበበ ጊዜ “ዙልም” የተባለው ሺርክን መሆኑን በዚህ ሐዲስ ላይ ተገልጿል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 65 , ሐዲስ 4776:
“እነዚያ ያመኑ እና እምነታቸውን “በበደል” ያልቀላቀሉ እነዚያ ለእነርሱ “ጸጥታ” አላቸው፤ እነርሱም የተመሩ ናቸው” የሚለው አንቀፅ በወረደ ጊዜ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ባልደረቦች የሆኑት ቃሉ ከባድ ስለነበር እነርሱም፦ “ከእኛ ውስጥ በደለኛ ያልሆነ ማን አለ?” ብለው ሲጠይቁ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሉቅማን ለልጁ፡- በአላህ አታጋራ፤ ማጋራት “ታላቅ በደል” ያለውን አልሰማችሁምን? ብለው ተናገሩ። حَدَّثَنَا قُتَيْبَةُ بْنُ سَعِيدٍ، حَدَّثَنَا جَرِيرٌ، عَنِ الأَعْمَشِ، عَنْ إِبْرَاهِيمَ، عَنْ عَلْقَمَةَ، عَنْ عَبْدِ اللَّهِ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ لَمَّا نَزَلَتْ هَذِهِ الآيَةُ ‏{‏الَّذِينَ آمَنُوا وَلَمْ يَلْبِسُوا إِيمَانَهُمْ بِظُلْمٍ‏}‏ شَقَّ ذَلِكَ عَلَى أَصْحَابِ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَقَالُوا أَيُّنَا لَمْ يَلْبِسْ إِيمَانَهُ بِظُلْمٍ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّهُ لَيْسَ بِذَاكَ، أَلاَ تَسْمَعُ إِلَى قَوْلِ لُقْمَانَ لاِبْنِهِ ‏{‏إِنَّ الشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ‏}‌‏”‏

ከወንድም ወሒድ ዑመር

https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የተቀረጸ ምስል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

በዕብራይስጥ “ኤሊል” אֱלִיל ማለት “ምስል”፣ “ቅርፅ”፣ “ጣዖት” ማለት ሲሆን በግሪክ ደግሞ “ኤዶሎን” εἴδωλον ነው፤ ትርጉሙ ተመሳሳይ ነው። የሙሴ አምላክ ለሙሴ “”ለእናንተ ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ፣ የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፣ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም”” ብሎ ተናግሯል፤ እንደውም ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ ይፈሩ ይላል፦
ዘሌዋውያን 26፥1 እኔ ያህዌህ አምላካችሁ ነኝና ለእናንተ *”ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ”*፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ።
ዘጸአት 20፥4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር *”የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፤ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም”*፤
መዝሙር 97፥7 *”ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ፥ በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ*”፤ መላእክቱ ሁሉ ስገዱለት።

“ለ”ተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ ይፈሩ እየተባለ ለምንድን ነው ለግኡዝ ነገር የፀጋ ስግደት የሚሰገድለት? ምስጋናስ የሚቅብለት የሚሰማበት ዐቅል የት አለውና ነው? እኔስ ኢሳይያስ የተናገረው ትንቢት ትዝ አለኝ፦
ኢሳይያስ 44፥15-19 ለሰውም ማገዶ ይሆናል፤ ከእርሱም ወስዶ ይሞቃል፥ አንድዶም እንጀራ ይጋግርበታል፤ ከእርሱም አምላክ አበጅቶ ይሰግድለታል፥ የተቀረጸውንም ምስል ሠርቶ በእርሱ ፊት ይንበረከካል። ግማሹን በእሳት ያቃጥላል፥ በዚያ በግማሹ ሥጋ ይበላል፥ ሥጋም ይጠብስበትና ይጠግባል፤ ይሞቃልና፦ እሰይ ሞቅሁ፥ እሳቱን አይቻለሁ ይላል። የቀረውንም እንጨት አምላክ አድርጎ ምስል ይቀርጽበታል፤ በፊቱም ተጐንብሶ ይሰግዳል ወደ እርሱም እየጸለየ፦ አምላኬ ነህና አድነኝ ይላል። አያውቁም፥ አያስቡም፤ እንዳያዩ ዓይኖቻቸውን፥ እንዳያስተውሉ ልቦቻቸውን ጨፍነዋል። በልቡም ማንም አያስብም፦ ግማሽዋን በእሳት አቃጥያለሁ፥ በፍምዋም ላይ እንጀራን ጋግሬአለሁ፥ ሥጋም ጠብሼ በልቻለሁ፤ የቀረውንም አስጸያፊ ነገር አደርጋለሁን? ለዛፍስ ግንድ እሰግዳለሁን? እንዲልም እውቀትና ማስተዋል የለውም።

ከአላህ በቀር የምትጠሯቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፤ እራሳቸውንም አይረዱምና ወደ አላህ በንስሃ ተመለሱ፦
7፥197 እነዚያም ከእርሱ በቀር የምትጠሯቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፤ እራሳቸውንም አይረዱም وَٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِهِۦ لَا يَسْتَطِيعُونَ نَصْرَكُمْ وَلَآ أَنفُسَهُمْ يَنصُرُونَ ፡፡

ከወንድም ወሒድ ዑመር

https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የዓኢሻ”ረ.ዓ.” ቤት



በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

9፥33 የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ለማጥፋት ይፈልጋሉ፤ አላህም ከሓዲዎች ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን መሙላትን እንጅ ሌላን አይሻም፡፡

መግቢያ
መቼም ሚሽነሪዎች የኢስላም ብርሃን በምን እናጠልሸው ብለው ከተነሱ ጊዜያት አለፉ፤ የኢስላምን መሰረትና ውቅር፣ ዋልታና ማገር፣ ጥልቀትና ስፋት፣ ድርና ማግ በቅጡ ያልተረዱ ስለሆኑ መደበኛ በሆነ መርሃ-ግብርና መዋቅር ከመማር ይልቅ ጎግል ላይ በሰፈረው የተለቃቀመ ጥራዝ-ነጠቅ መረጃ ድምዳሜ ላይ ሲደርሱ ማየት እጅጉን ያማል፣ አንዱ ሚሽነሪ፦ ነብያችንን”ﷺ” የዓኢሻ”ረ.ዓ.” ልብስ ሲለብሱ እና ከእርሷ ጋር ተራክቦ ሲያደርጉ ብቻ ነው ወህይ የሚወርድላቸው ብሎ በትክክል እንኳን ማንበብ የማይችለውን ጩቤ ጥቅስ ጠቅሶ የጨባራ ለቅሶ እና ተስካር የሆነው ውሃ የማይቋጥ ሙግት ሲሟገተኝ ነበር፤ ይህ ስሁት የሆነ ሙግት ሳይርቅ በቅርቡ ሳይደርቅ በእጥቡ ሳይቃጠል በቅጠል እንደሚባለው ከመነሻው አከርካሪውን መመታት አለበት፤ እስቲ ሐዲሱን እንመልከት፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 51 , ሐዲስ 16:
ሂሻም ኢብኑ ኡርዋህ ከዓኢሻ”ረ.ዓ.” እንደተረከው….የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ለኡሙ ሰላማ”ረ.ዓ.” በአይሻ ጉዳይ አታስቸግሪኝ፤ ወላሂ ከማናቸውም ሴቶች ልብስ ውስጥ ወህይ አይመጣልኝም “ከአይሻ ልብስ በስተቀር አሏት”፤ فَقَالَ لَهَا ‏”‏ لاَ تُؤْذِينِي فِي عَائِشَةَ، فَإِنَّ الْوَحْىَ لَمْ يَأْتِنِي، وَأَنَا فِي ثَوْبِ امْرَأَةٍ إِلاَّ عَائِشَةَ ‏”‌‏ ።

ምን ያህት ቅጥፈት እንዳለ ተመልከቱ፤ እዚህ ሐዲስ ላይ የዓኢሻ”ረ.ዓ.” ልብስ ለበሱ የሚል የት አለ? ከዓኢሻ”ረ.ዓ.” ጋር ተራክቦ ሳደርግ የሚል የት አለ? ወህይ የሚመጣልኝ ከአይሻ ልብስ ውስጥ ብቻ ነው የሚል የት አለ? ይህ ሁሉ ገለባ ሂስ ነው፤ ነብያችን ወህይ የሚመጣላቸው በተለያየ ሁኔታ ቢሆንም ከሌሎች ባለቤቶታቸው ይልቅ የዓኢሻ”ረ.ዓ.” ቤት እያሉ ብቻ ነው ወህይ የሚመጣላቸው ማለት “ይልቅ” የሚለው ማነፃፀሪያ ከሴቶቹ ጋር እንጂ አጠቃላይ አይደለም፤ “ሠውብ” ثَوْب የሚለው ቃል በብዙ ይመጣል፦
“ሂጃብ” حِجَاب “መጋረጃ”፣
“ፊራሽ” فِرَٰش ምንጣፍ”፣
“ሊሃፍ” لِحَاف “ፍራሽ”
“በይት” بَيْت “ቤት”
“ሊባሥ” لِبَاس “ልብስ” በሚል ይመጣል፤ ይህንን በተለያዩ ነጥቦች ማየት ይቻላል፦
ነጥብ አንድ
“ሊሃፍ”
“ሊሃፍ” لِحَاف የሚለው ቃል “ፍራሽ” ማለት ሲሆን “ከአይሻ ልብስ በስተቀር” የሚለው “ከአይሻ ፍራሽ በስተቀር” በሚለው መጥቷል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 62 , ሐዲስ 122:
ኡሙ ሰላማ ሆይ በአይሻ ጉዳይ አታስቸግሪኝ፤ ወላሂ ከማናቸውም ሴቶች ፍራሽ ውስጥ ወህይ አይመጣልኝም “ከአይሻ ፍራሽ በስተቀር” “‏ يَا أُمَّ سَلَمَةَ لاَ تُؤْذِينِي فِي عَائِشَةَ، فَإِنَّهُ وَاللَّهِ مَا نَزَلَ عَلَىَّ الْوَحْىُ وَأَنَا فِي لِحَافِ امْرَأَةٍ مِنْكُنَّ غَيْرِهَا ‏”‌‏.‏ ፤

ነጥብ ሁለት
“በይት”
“በይት” بَيْت ማለት “ቤት” ሲሆን “ከአይሻ ልብስ በስተቀር” የሚለው “ከአይሻ ቤት” በሚለው መጥቷል፤ ቤት የሚከፋፈለው በመጋረኛ ስለሆነ “ሠውብ” የሚለው በሌላ ሪዋያ ላይ “በይት” بَيْت “ቤት” በሚል መጥቷል፦
ኢማሙ አህመድ መጽሐፍ 6 ሐዲስ 293
የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ ኡሙ ሰላማ ሆይ በአይሻ ጉዳይ አታስቸግሪኝ፤ ወላሂ ከማናቸውም ሴቶች ቤት ውስጥ ወህይ አይመጣልኝም ከአይሻ ቤት በስተቀር፤ رسول الله صلى الله عليه و سلم ثم قال يا أم سلمة لا تؤذيني في عائشة فإنه والله ما نزل على الوحي وأنا في بيت امرأة من نسائي غير عائشة ።
ነጥብ ሶስት
“ሊባሥ”
“ሊባሥ” لِبَاس ማለት ትርጉሙ “ልብስ” ማለት ሲሆን “ሠውብ” ማለት “ሊባሥ” ነው ብንል እንኳን “ልብስ” የሚለው ቃል ሁልጊዜ ሱሪን፣ ቀሚስን፣ ጃኬትን ብቻ ሳይሆን የሚያመለክተው መጠለያን፣ መከለያ፣ መሸሸጊያ ለማመልከት ይመጣል፤ አምላካችም አላህ ለምሳሌ ሴት የወንድ ልብስ ናት ወንድ የሴት ልብስ ነው ይለናል፦
2፥187 በጾም ሌሊት ወደ ሴቶቻችሁ መድረስ ለእናንተ ተፈቀደላችሁ፡፡ እነርሱ ለእናንተ “ልብሶች” ናቸው፤ እናንተም ለእነርሱ “ልብሶች” ናችሁ أُحِلَّ لَكُمْ لَيْلَةَ ٱلصِّيَامِ ٱلرَّفَثُ إِلَىٰ نِسَآئِكُمْ ۚ هُنَّ لِبَاسٌۭ لَّكُمْ وَأَنتُمْ لِبَاسٌۭ لَّهُن ፡፡

መቼም ልብስ የሚለውን አንዱ የአንዱ መሸሸጊያ ማለት እንጂ አንዱ የአንዱ ጃኬት ወይም ቀሚስ አሊያም ሱሪ ማለት ነው የሚል ቂል የለም፤ አላህ ሌሊትን ልብስ አደረገ፤ ያ ማለት “መጠለያ” ማለት ነው፦
25:47 እርሱም ያ ለእናንተ “ሌሊትን” ልብስ፣ እንቅልፍንም ማረፊያ ያደረገ፤ ቀንንም መበተኛ ያደረገላችሁ ነው وَهُوَ ٱلَّذِى جَعَلَ لَكُمُ ٱلَّيْلَ لِبَاسًۭا وَٱلنَّوْمَ سُبَاتًۭا وَجَعَلَ ٱلنَّهَارَ نُشُورًۭا ።
78:10 ሌሊቱንም ልብስ አደረግን وَجَعَلْنَا ٱلَّيْلَ لِبَاسًۭا ።

ይህንን ካየን ነብያችን”ﷺ”፦ “ከማናቸውም ሴቶች ልብስ ውስጥ ወህይ አይመጣልኝም ከዓኢሻ”ረ.ዓ.” ልብስ በስተቀር” ሲሉ ከዓኢሻ”ረ.ዓ.” ፍራሽ ወይም ቤት ማለታቸው እንደሆነ እሙንና ቅቡል ነው እንጂ ቃላትን ማንሸዋረር እና ማውረግረግ አይቻልም። እንዴት የአንድ ሴት ልብስ ውስጥ አንድ ወንድ ቃል በቃል ሊገባስ ይችላል? ይህ ሆን ተብሎ ድርቅና አላህ በትንሣኤ ቀን በዚያ በእርሱ ትወዛገቡበት በነበራችሁት ሁሉ በመካከላችሁ ይፈርዳል፦
18፥68-69 ቢከራከሩህም «አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው» በላቸው፡፡ አላህ በትንሣኤ ቀን በዚያ በእርሱ ትወዛገቡበት በነበራችሁት ሁሉ በመካከላችሁ ይፈርዳል፡፡

ከወንድም ወሒድ ዑመር

https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የነብያችን”ﷺ” አሟሟት


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3:144 ሙሐመድም ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የሆነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፤ ታድያ “”ቢሞት፥ ወይም ቢገደል”” ወደኋላችሁ ትገለበጣላችሁን? ወደኋላዉ የሚገለበጥም ሰዉ አላህን ምንም አይጐዳም። አላህም አመስጋኞቹን በእርግጥ ይመነዳል።

ብዙ ሚሽነሪዎች በተለይ የክርስትናው አቃቤ እምነት ዴቪፍ ሁድ እና ሳም ሻሙስ የነብያችንን”ﷺ” አሟሟት አጣመው ነብያችንን”ﷺ” እንደ ኃሳዌ ነብይ ለማድረግ ሲቃጣቸው በተደጋጋሚ ጊዜ ይሰማል፤ በነገራችን ላይ አንድ ነብይ ይቅርና አንድ አማኝ በአላህ ሃይማኖት የተሰደደ፣ የተገደለ ወይም የሞተ አላህ መልካምን ሲሳይ በእርግጥ ይሰጠዋል፦
22:58 እነዚያም በአላህ ሃይማኖት የተሰደዱ፣ ከዚያም የተገደሉ፣ ወይም የሞቱ፣ አላህ መልካምን ሲሳይ በእርግጥ ይስጣቸዋል፣ አላህም እርሱ ከሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነው።

ነብያችን ከመላካቸው በፊት የእስራኤል ልጆች ነብያትን ያለ አግባብ ገድለዋል፦
2:91 «አማኞች ከኾናችሁ ከአሁን በፊት የአላህን ነቢያት ለምን ገደላችሁ?» በላቸው፡፡
4:155 ቃል ኪዳናቸውንም በማፍረሳቸው፣ በአላህም አንቀጾች በመካዳቸው፣ “ነቢያትንም ያለ አግባብ በመግደላቸው” እና ልቦቻችን ሽፍኖች ናቸው በማለታቸው ምክንያት ረገምናቸው፤

አንድ ነብይ በሰው እጅ መገደሉ እና አላህ ያንን ነብይ እንዲገደል መፍቀዱ ያ ነብይ ኃሳዌ ነብይ ለመሆኑ መስፈርት ነው ያለው ማን ነው? የእስራኤል ልጆች ነብያትን ያለ አግባብ ገድለዋል፤ ታዲያ የተገደሉት ነብያት ሰማዕታት ናቸው ወይስ ኃሳውያን? አይ የነብያት መገደል ቁርአን ላይ ብቻ ነው ያለው እዳትሉ ባይብሉ ላይ ፍንትውና ቁልጭ ብሎ ተቀምጧል፦
ሉቃስ 11፥47 አባቶቻችሁ የገደሉአቸውን የነቢያትን መቃብር ስለምትሠሩ፥ ወዮላችሁ።
ሉቃስ 11፥49-51 ስለዚህ ደግሞ የእግዚአብሔር ጥበብ እንዲህ አለች፦ ወደ እነርሱ “”ነቢያትንና ሐዋርያትን እልካለሁ፥ ከእነርሱም ይገድላሉ”” ያሳድዱማል፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የፈሰሰው “”የነቢያት ሁሉ ደም””፥ ከአቤል ደም ጀምሮ በመሠዊያውና በቤተ መቅደስ መካከል እስከ ጠፋው እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ፥ ከዚህ ትውልድ እንዲፈለግ አዎን እላችኋለሁ፥ ከዚህ ትውልድ ይፈለጋል።

ታዲያ የተገደሉት ነብያት ሰማዕታት ናቸው ወይስ ኃሳውያን? አንድ ነብይ የሚደርስበት ስደት፣ እንግልት፣ እስራት እና ሞት የአላህ ነብይ እንዳልሆነ መስፈርት ሊሆን አይችልም። ነብያችን”ﷺ” ላይ ከሃድያን ሊያስሯቸው፣ ሊያሳድዷቸው እና ሊገሏቸው እንደነበረ እና አላህ ይህንን ምክር እንዳከሸፈ ይናገራል፦
8:30 እነዚያም የካዱት “ሊያስሩህ ወይንም “ሊገድሉህ” ወይም ከመካ ሊያወጡህ” በአንተ ላይ በመከሩብህ ጊዜ አስታውስ፤ ይመክራሉም አላህም ተንኮላችውን ይመልስባቸዋል፤ አላህም ከመካሪዎች ሁሉ በላይ ነው።

ስለዚህ ነብያችን”ﷺ” ከበፊታቸው መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የሆኑ መልክተኛ አይነት እንጂ ሌላ አይነት አይደሉም፤ መሞት ወይም መገደል የአንድ ነብይ እጣ ፋንታ ነው፦
3:144 ሙሐመድም ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የሆነ መልክተኛ እንጂ ሌላ አይደለም፤ ታድያ “”ቢሞት፥ ወይም ቢገደል”” ወደኋላችሁ ትገለበጣላችሁን? ወደኋላዉ የሚገለበጥም ሰዉ አላህን ምንም አይጐዳም። አላህም አመስጋኞቹን በእርግጥ ይመነዳል።

ነብያችን”ﷺ” በ 628 AD በኸይበር ዘመቻ ጊዜ አይሁዳዊ ሴት ዘይነብ ቢንት ሀረስ የምትባል በበግ ወርች ስጋ ምግብ አመጣችላቸውና በሉ፤ ያ ምግብ የተመረዘ ነበር እና ከባልደረዎች አንዱ ሞተ፤ ከዚያም ጅብሪል መጥቶ የተመረዘ መሆኑን ለነብያችን”ﷺ” ነገራቸው፤ ከዚያም ማንም እንዳይመገቡ አዘዙ፤ ነገር ግን ያ መርዝ በደም ስራቸው ውስጥ እስኪሞቱ ድረስ አሉታዊ ተፅእኖ አድርጎባቸዋል፤ ይህንን እሳቸው እንዲህ በማለት ይገልፃሉ፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 64 , ሐዲስ 450:
ዓኢሻ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ ነብዩ”ﷺ” ሊሞቱ በህመማቸው ሳሉ እንዲህ ይሉ ነበር፦ “ዓኢሻ ሆይ በኸይበር የበላሁት ምግብ እስካሁን ይሰማኛል፤ አሁንም በዚያ መርዝ “የደም ስሬ” እንደተቆረጠ ይሰማኛል قَالَ عُرْوَةُ قَالَتْ عَائِشَةُ ـ رضى الله عنها ـ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ فِي مَرَضِهِ الَّذِي مَاتَ فِيهِ ‏ “‏ يَا عَائِشَةُ مَا أَزَالُ أَجِدُ أَلَمَ الطَّعَامِ الَّذِي أَكَلْتُ بِخَيْبَرَ، فَهَذَا أَوَانُ وَجَدْتُ انْقِطَاعَ أَبْهَرِي مِنْ ذَلِكَ السَّمِّ ‏”‌‏

“አብሀር” أَبْهَر ማለት “የደም ስር” ማለት ነው፤ ልብ አድርጉ አንዳንድ ሚሽነሪዎች ይህንን ሐዲስ ተንተርሰው፦ “”ነብያችሁ ከቀጠፉ አላህ የልባቸውን ደም ስር እንደሚቆርጥ ተናግሮ ነበር፤ ስለዚህ ነብያችሁ የደም ስራቸው መቆረጥ መሰማቱ መቅጠፋቸውን ወሊአዑዙቢላህ ያሳያል”” ይላሉ፤ ሲጀመር “ደም ስሬ ተቆረጠ” እና “እንደ-ተቆረጠ” የሚሉት ቃላት ለየቅል ናቸው፤ ሲቀጥል ቁርአኑ የሚለውን እና ገለባው ትችት እስቲ እንየው፦
69፥44-46 በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት ያላልነውን “በቀጠፈ” ኖሮ وَلَوْ تَقَوَّلَ عَلَيْنَا بَعْضَ ٱلْأَقَاوِيلِ ፤ በኀይል በያዝነው ነበር لَأَخَذْنَا مِنْهُ بِٱلْيَمِينِ ፡፡ ከዚያም ከእርሱ የልቡን ሥር በቆረጥን ነበር ثُمَّ لَقَطَعْنَا مِنْهُ ٱلْوَتِينَ ፡፡
ነጥብ አንድ
“ቀጠፈ”
“ቀጠፈ” ለሚለው ቃል የመጣው “ተቀውወለ” تَقَوَّلَ ሲሆን አላፊ ግን እንጂ ወደፊት ከቀጠፈ የሚል ፍቺ የለውም፤ ስለዚህ ከአለፈ ድርጊት ጋር እንጂ ከወደፊት ሞታቸው ጋር እንዳይያያዝ ሰዋሰዉ አይፈቅድላችሁም። ይህንን “ተቀውወለ” የሚለው ቃል በሌላ አንቀፅ አላፊ ግን መሆኑን መረዳት ይቻላል፦
52፥33 ወይም «”ቀጠፈው” ይላሉን?» አይደለም፤ በእውነቱ አያምኑም أَمْ يَقُولُونَ تَقَوَّلَهُۥ ۚ بَل لَّا يُؤْمِنُونَ ፡፡

ስለዚህ አላህ ይህንን አንቀፅ ያወረደበት ምክንያት ከሃድያን ነብያችንን ከልብ ወለድ፣ ከቀድሞ ሰዎች ወይም ከባለቅኔ ወይም ከጠንቋይ አሊያም ከሸይጣን ቀጥፏል ላሉበት መሳለቂያ መልስ ነው፦
69፥41-43 እርሱም የባለቅኔ ቃል አይደለም ጥቂትን ብቻ ታምናላችሁ። የጠንቋይም ቃል አይደለም ጥቂቱን ብቻ ታስታዉሳላችሁ። ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው።
53፥3-4 ከልብ ወለድም አይናገርም وَمَا يَنطِقُ عَنِ ٱلْهَوَىٰٓ ፡፡
እርሱ ንግግሩ የሚወርረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም إِنْ هُوَ إِلَّا وَحْىٌۭ يُوحَىٰ ፡፡
25፥5-6 አሉም «የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ተረቶች ናት፡፡ አስጻፋት፡፡ እርሷም በእርሱ ላይ ጧትና ማታ ትነበብለታለች፡፡» «ያ በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለን ምስጢር የሚያውቀው አወረደው፡፡ እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና» በላቸው፡፡
81:25 እርሱም ቁርአን የርጉም ሰይጣን ቃል አይደለም።
41:42 ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም፤ ጥበበኛ ምስጉን ከሆነው ጌታ የተወረደ ነው።

ነጥብ ሁለት
“የልብ ስር”
“ወቲን” وَتِين ማለት “የልብ ስር” ማለት ሲሆን ይህ የልብ ስር ከተቆረጠ አንድ ሰው ይሞታል፤ አላህ ምንም አልቀጠፈም፤ ከዚህ በፊት ቢቀጥፍ ኖሮ የልቡን ስር እንቆርጠው ነበር እያለን ነው፤ ነገር ግን ነብያችን”ﷺ” በ 628 AD መርዙን በልተው ከእርሳቸው ጋር የነበረው ሰሃባ ሲሞት እርሳቸው ግን 4 ዓመት ቆይተው በ 632 AD አርፈዋል፤ ሐዲሱ የሚለው “አብሀር” أَبْهَر ማለትም “የደም ስር” እንጂ “ወቲን” وَتِين ማለትም “የልብ ስር” አይደለም።
ሲጀመር እንደው መርዝ እኮ ከገደለም ገደለ ነው ወይም ከማረም ማረ ነው እንጂ 4 ዓመት አቆይቶ ይገላልን?
ሲቀጥል ነብያችን”ﷺ” የተሰማቸው ነው እንጂ መርዙ ደም ስሬን ቆረጠው መች አሉ? እንደ ተቆረጠ ማለት ተቆረጠ ማለት ነውን?
ሲሰልስ “አብሀር” ማለት እና “ወቲን” ማለት በየትኛው ቀመር እና ስሌት ነው አንድ ቃላት የሚሆነው?
ሲያረብብ እውነቱ መርዙ የደም ስራቸውን ቆርጦት ከገደላቸውም የመርዙ መንስኤ ዘይነብ ቢንት ሀረስ ስለሆነች በሰው እጅ ከተገደሉ እንደማንኛው ነብይ ሰማዕት ይሆናሉ። ነብያችን”ﷺ” ቢሞቱ ወይም ቢገደሉ በክህደት ወደኋላችሁ ትገለበጣላችሁን? ወደኋላዉ ብትገለበጡ አላህን ምንም አትጎዱም፦
3:144 ሙሐመድም ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የሆነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፤ ታድያ “”ቢሞት፥ ወይም ቢገደል”” ወደኋላችሁ ትገለበጣላችሁን? ወደኋላዉ የሚገለበጥም ሰዉ አላህን ምንም አይጐዳም። አላህም አመስጋኞቹን በእርግጥ ይመነዳል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር

https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም።
ቂሰቱል ገራኒቅ


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

69፥44-46 በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት ያላልነውን “በቀጠፈ” ኖሮ وَلَوْ تَقَوَّلَ عَلَيْنَا بَعْضَ ٱلْأَقَاوِيلِ ፤ በኀይል በያዝነው ነበር لَأَخَذْنَا مِنْهُ بِٱلْيَمِينِ ፡፡ ከዚያም ከእርሱ የልቡን ሥር በቆረጥን ነበር ثُمَّ لَقَطَعْنَا مِنْهُ ٱلْوَتِينَ ፡፡

ዊሊያም ሙኢር በ 1819 AD ተወልዶ በ 1905 AD ያለፈ “ሙስተሽሪቅ” مستشرق ማለትም “የመካከለኛው ምስራቅ ጥንተ-ነገር አጥኚ”Orientalist” ሲሆን እርሱ ለመጀመሪያ ጊዜ በ 1858 AD በመጽሐፉ ሽፋን ላይ “ሰይጣናዊ አንቀፅ”Satanic Verse” ብሎ ጻፈ፤ በመቀጠል የእርሱን ፈለግ የተከተለው ሳልማን ሩሽዲ 1988 AD በመጽሐፉ ሽፋን ላይ “ሰይጣናዊ አንቀፅ” ብሎ ጻፈ፤ ይህ መጽሐፍ በምዕራባዊያና በሚሽነሪዎች እገዛ በዓለማችን ላይ ትልቅ የህትመት ሽፋን ተሰቶት ተሰራጭቶ ነበር፤ ሳልማን ሩሽዲን ብዙዎች ከሊቅ እስከ ደቂቅ እጹብ ድንቅ በማለት አሞካሽተውት ነበር፤ ቂሰቱል ገራኒክ በቅጡ በማይታወቅበት በዚያ ጊዜ አለማወቅን ተገን አድርጎ የተነሣው ይህ ሰው ብዥታው አላንዳች ከልካይ እንደ ተዛማጅ በሽታ በዓለማችም ላይ ተዛምቶ ነበር፤ ከመነሻው የብዙዎችን ልብ የሳበው ይህ መጽሐፍ ከእርሱ በኋላ ለመጡት መሰል የሚሽነሪዎች ትችት ትልቅ የማደላደል ሥራ ሠርቷል። “ሰይጣናዊ አንቀፅ” ከትችት የመነጨ ሲሆን ይህ ስያሜ በኢስላም ጽሑፎች ውስጥ የለም። “ሰይጣናዊ አንቀፅ” በኢስላማዊ ጥናት ውስጥ ግን “ቂሰቱል ገራኒቅ” قصة الغرانيق ይባላል፤ “ገራኒቅ” غرانيق ማለት “የውሃ ወፍ”crane” ማለት ነው።
“ቂሰቱል ገራኒቅ” ማለት ይህ ነው፦
“ቲልከል ገራኒቁል ዑልያ፤ ወኢንነ ሸፋዐተሁንነ ለቱርጃ” تِلْكَ الْغَرَانِيقُ الْعُلْيَ وَ إِنَّ شَفاَعَتَهُنَّ لَتُرْجَى.
‹እነዚህ የተከበሩ ናቸው ምልጃቸው ተቀባይነት ያገኘው ናቸው›These are the high-flying ones, verily their intercession is to be hoped for!

ይህንን ከማየታችን በፊት ሙሉ ታሪካዊ ዳራውን እንመልከት፤ የረመዷን ወር ነብያችን”ﷺ” ወደ ተከበረው የሐረም መስጊድ ሄዱ፤ ቁረይሾች ተሰባስበው ባሉበት በድንገት ከመካከላቸው ቆሙና ሱረቱል ነጅም የተሰኘውን የቁርዓን ክፍል አነበቡ፤ ይህንን ሱራ አንብበው ሲጨርሱ “ለአላህም ስገዱ አምልኩትም” አንቀፅ ስለነበር ሁሉም ሙስሊሞች ሰገዱ፤ ከኃላ ሲሰሙ የነበሩት ቁረይሾች አብረው ሰገዱ፦
53፥62 ለአላህም ስገዱ አምልኩትም فَٱسْجُدُوا۟ لِلَّهِ وَٱعْبُدُوا۟ ۩ ፡፡
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 17 , ሐዲስ 5:
ኢብኑ ዐባስ”ረ.ዓ.” እንደተረከው፦ ነቢዩ”ﷺ” ሱረቱል ነጅምን በቀሩ ጊዜ ሰገድኩ፣ ከእርሳቸው ጋር ሙስሊሞች፣ ሙሽሪኮች፣ ጂኒዎችና ሰዎችም ሰገዱ عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم سَجَدَ بِالنَّجْمِ وَسَجَدَ مَعَهُ الْمُسْلِمُونَ وَالْمُشْرِكُونَ وَالْجِنُّ وَالإِنْسُ‏.‏ ።

አረብ ሙሽሪኮች የሰገዱበት ምክንያት “”አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን? ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን?”” የሚለውን አንቀጽ ነብያችን”ﷺ” ስላነበቡ እንደሆነ ሰሒህ የሆነው ሐዲስ ላይ ከላይ ተቀምጧል።
ይህ የመጀመሪያው እይታ ሲሆን ነገር ግን ሁለተኛው እይታ ከዚህ በኃላ ያለው ታሪክ ኢብኑ ሃጅር አል አስቃላኒ እና ሼኽ አልባኒ ደኢፍ ነው ብለው አስቀምጠውታል፤ ራዚም፦ “በሙናፊቃን የተቀጠፈ መውዱዕ ነው” ብሏል(ተፍሲሩል ራዚ 11/134)። በተጨማሪም ኢብኑ ከሲር ሲናገር ይህ ታሪክ ደኢፍ ነው ብሎ ከደኢፍ ሁለተኛውን ክፍል ሙርሰል እንደሆነና በእርሱ አስተሳሰብ ሳሒህ እንዳልሆነ ተናግሯል። ይህንን ደኢፍ ታሪክ ኢብኑ ሂሻም፣ አል-ፈይሩዝ አባዲ፣ ተፍሲሩል ጀላለይን እና ኢብኑ ጀሪር አጥ-ጣባሪ ዘግበውታል፤ እንደውም ኢብኑ ጀሪር አጥ-ጣባሪ መግቢያው ላይ እንዲህ ይላል፦
“በዚህ መጽሐፍ ትረካ አንባቢ ተቃራኒ ወይም ተገቢ ሆኖ በሚያገኝበት ጊዜ ይህ የእኛ ባህርይ እንዳልሆነ ማወቅ አለበት፤ ነገር ግን ካለፉት ሰዎች ወደ እኛ የተላለፈ ትረካ ነው” (ታሪኩር ረሱል ወል ሙልክ ቅፅ 1, ገፅ 3)

ስለዚህ ከዚህ በታች ያለው የኢብኑ ጀሪር አጥ-ጣባሪ ትረካ ደኢፍ የሆሃንበት አጋጣሚ አለ ማለት ነው፤ አንዳንድ ሙፈሲሪን መሰረት ያደረጉበትን የኢብኑ ጀሪር አጥ-ጣባሪ ትረካ እስቲ እንየው፦
“አላህ፦ “በኮከብ እምላለሁ በገባ ጊዜ፡፡ ባልደረባችሁ አልተሳሳተም፤ አልጠመመምም፡፡ ከልብ ወለድም አይናገርም፡” የሚለውን አንቀጽ አወረደ፤ በመቀጠል፦
“አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን? ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን?”
ይህንን በአነበቡ ጊዜ ሸይጣን “”በንባቡ ላይ””፦
“ቲልከል ገራኒቁል ዑልያ፤ ወኢንነ ሸፋዐተሁንነ ለቱርጃ” تِلْكَ الْغَرَانِيقُ الْعُلْيَ وَ إِنَّ شَفاَعَتَهُنَّ لَتُرْجَى.
‹እነዚህ የተከበሩ ናቸው ምልጃቸው ተቀባይነት ያገኘው ናቸው› የሚለውን ቃል ጣለ።
አላህም፦ “ከመልክተኛና ከነቢይም ከአንተ በፊት አንድንም አላክንም ባነበበ ጊዜ ሰይጣን በንባቡ ላይ የሚጥል ቢሆን እንጅ፡፡ ወዲያውም አላህ ሰይጣን የሚጥለውን ያስወግዳል” የሚለውን አንቀፅ አወረደ።
(ታሪኩር ረሱል ወል ሙልክ ቅፅ 1, ገፅ 108)

“በንባቡ ላይ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ፊ ዑምኒይየቲሂ” فِي أُمْنِيَّتِهِ ሲሆን በነብያችን”ﷺ” ንባብ ማለትም “አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን? ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን?” ብለው ባሉ ጊዜ ጎን ለጎን ሸይጣን፦ ‹እነዚህ የተከበሩ ናቸው ምልጃቸው ተቀባይነት ያገኘው ናቸው› የሚለውን ቃል ጣለ። እንግዲህ ይህ ነው “ቂሰቱል ገራኒቅ” የሚባለው፤ ሙሽሪክ ከሃድያን ይህ ሱራ ሲነበብ «ይህንን ቁርኣን አታዳምጡ፡፡ ታሸንፉም ዘንድ ሲነበብ በእርሱ ውሰጥ ተንጫጩ» አሉ፦
41፥26 እነዚያም የካዱት «ይህንን ቁርኣን አታዳምጡ፡፡ ታሸንፉም ዘንድ “ሲነበብ” በእርሱ ውሰጥ ተንጫጩ» አሉ وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَا تَسْمَعُوا۟ لِهَٰذَا ٱلْقُرْءَانِ وَٱلْغَوْا۟ فِيهِ لَعَلَّكُمْ تَغْلِبُونَ ፡፡
በዚህ ሰአት ከእውነት “በራቀ ጭቅጭቅ ውስጥ” ሆነው “አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን? ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን?” የሚለው አንቀፅ ሲነበብ በሚንጫጩት ልብ ውስጥ ፈተና ሊያደርግ ሸይጣን ልብስብስን ቃልን ጣለ፤ ሁልጊዜ በእያንዳንዱ ነብይ ዘመን ነብዩ ባነበበ ጊዜ ሰይጣን ልቦቻቸውም ደረቆች በሆኑት ውስጥ ልብስብስን ቃልን ይጥላል፤ ይህን የሚያደርገው የቀጠፈውን እንዲቀጣጥፉ ነው፦
22፥53 ሰይጣን የሚጥለውን ነገር ለእነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ላለባቸው ልቦቻቸውም ደረቆች ለሆኑት ፈተና ሊያደርግ ይጥላል፡፡ በዳዮችም ከእውነት “በራቀ ጭቅጭቅ ውስጥ” ናቸው لِّيَجْعَلَ مَا يُلْقِى ٱلشَّيْطَٰنُ فِتْنَةًۭ لِّلَّذِينَ فِى قُلُوبِهِم مَّرَضٌۭ وَٱلْقَاسِيَةِ قُلُوبُهُمْ ۗ وَإِنَّ ٱلظَّٰلِمِينَ لَفِى شِقَاقٍۭ بَعِيدٍۢ ፡፡
6:112-113 እንደዚሁም *ለነቢያት ሁሉ ከሰውና ከጋኔን የኾኑን ሰይጣናት ጠላት አደረግን*፡፡ ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ለማታለል *ልብስብስን ቃል ይጥላሉ*፡፡ ጌታህም በሻ ኖሮ ባልሠሩት ነበር፡፡ *ከቅጥፈታቸውም ጋር ተዋቸው*፡፡ *የሚጥሉትም ሊያታልሉ* እና የእነዚያም በመጨረሻይቱ ሕይወት የማያምኑት ሰዎች ልቦች ወደእርሱ እንዲያዘነብሉ እንዲወዱትም እነርሱ *ይቀጥፉ የነበሩትንም እንዲቀጣጥፉ* ነው፡፡
22፥52 ከመልክተኛና ከነቢይም ከአንተ በፊት አንድንም አላክንም ባነበበ ጊዜ ሰይጣን በንባቡ ላይ የሚጥል ቢሆን እንጅ፡፡ ወዲያውም አላህ ሰይጣን የሚጥለውን ያስወግዳል፡፡ ከዚያም አላህ አንቀጾቹን ያጠነክራል፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍۢ وَلَا نَبِىٍّ إِلَّآ إِذَا تَمَنَّىٰٓ أَلْقَى ٱلشَّيْطَٰنُ فِىٓ أُمْنِيَّتِهِۦ فَيَنسَخُ ٱللَّهُ مَا يُلْقِى ٱلشَّيْطَٰنُ ثُمَّ يُحْكِمُ ٱللَّهُ ءَايَٰتِهِۦ ۗ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌۭ ፡፡

ይህ አንቀፅ ሙጅመል ማለትም ጥቅላዊ ነው፤ ምክንያቱም *”ከአንተ በፊት”* የሚለው ገለጻ ከነብያችን በፊት በነበሩት ነብያትና መልእክተኞችም ላይም ከሰውና ከጋኔን የኾኑን ሰይጣናት ለማታለል *ልብስብስን ቃል* ይጥላሉ፤ ወዲያውም አላህ ሰይጣን የሚጥለውን ያስወግዳል፡፡ ከዚያም አላህ አንቀጾቹን ያጠነክራል፤ ሸኹል ኢስላም ኢብኑ ተምያህ ይህንን እይታ ይጋራሉ። ነገር ግን በወቅቱ ነብያችን”ﷺ” “አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን? ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን?” የሚለው አንቀጽ በአሉታዊ መልኩ አንብበው ሲጨርሱ በንባቡ ላይ ሸይጣን፦ “እነዚህ የተከበሩ ናቸው ምልጃቸው ተቀባይነት ያገኘው ናቸው” የሚለውን ለሙሽሪኮች ሲያነብ ሙሽሪኮች ይህን ቃል ሲሰሙ፦ “ነቢዩ”ﷺ” አማልክቶቻችንን አወድሷል” ሲሉ ዋሹ፤ የዚህ ቅጥፈት ዜና ወደ ሐበሻ ከተሰደዱ ሰሐቦች ዘንድ ከእውነታው እጅግ በተለየና በራቀ መልኩ ተሰማ፤ አላህም ነብያችንን”ﷺ” “ከዚያም ወደ አንተ ካወረድነው ሌላን በእኛ ላይ ትዋሽ ዘንድ ሊፈትኑህ በእርግጥ ተቃረቡ፡፡ ያን ጊዜም ወዳጅ አድርገው በያዙህ ነበር” በማለት ይህ ቅጥፈት ለማስዋሸት ፈተና መሆኑን እና ቢዋሹ ወዳጆች አድርገው ይይዧቸው እንደነበር ተናገረ፦
17፥73 እነሆ ከዚያም ወደ አንተ ካወረድነው ሌላን በእኛ ላይ ትዋሽ ዘንድ ሊፈትኑህ በእርግጥ ተቃረቡ፡፡ ያን ጊዜም ወዳጅ አድርገው በያዙህ ነበር وَإِن كَادُوا۟ لَيَفْتِنُونَكَ عَنِ ٱلَّذِىٓ أَوْحَيْنَآ إِلَيْكَ لِتَفْتَرِىَ عَلَيْنَا غَيْرَهُۥ ۖ وَإِذًۭا لَّٱتَّخَذُوكَ خَلِيلًۭا ፡፡

ሙሽሪኮች ጠላት መሆናቸው በራሱ ከአላህ ቃል ሌላ ቃልን እንዳልተናገሩ በቂ ማስረጃ ነው፤ ምክንያቱም ነብያችንን”ﷺ” ወዳጅ አድርገው አለመያዛቸው ነው፤ በተጨማሪም በመቀጠል ከአላህ ውጪ ከሌላ ማንነት ሆነ ምንነት ከፊል ቃልን አምጥቶ ቢቀጥፉ የልብ ስራቸውን እንደሚቆርጥ በመናገር ከሌላ ህልውና ምንም እንዳላሉ መስክሮላቸዋል፤ ፦
69፥44-46 በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት ያላልነውን “በቀጠፈ” ኖሮ وَلَوْ تَقَوَّلَ عَلَيْنَا بَعْضَ ٱلْأَقَاوِيلِ ፤ በኀይል በያዝነው ነበር لَأَخَذْنَا مِنْهُ بِٱلْيَمِينِ ፡፡ ከዚያም ከእርሱ የልቡን ሥር በቆረጥን ነበር ثُمَّ لَقَطَعْنَا مِنْهُ ٱلْوَتِينَ ፡፡

“”የልቡን ሥር በቆረጥን ነበር “”ብሎ ማለት የቱን ያህል በግህደተ-መለኮት ቀልድ እንደሌለ የሚያሳይ ሃይለ-ቃል ነው። ከአላህ ወዲህ የትኛው ንግግር ማስረጃ ሊሆን ይችላል? ቁርአንን አላህ ነው ያወረደው፤ አላህ ከሰው ሆነ ከሸይጣን ቃላት ጠብቆታል፣ ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም፦
15:9 እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡
41:42 ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም፤ ጥበበኛ ምስጉን ከሆነውጌታ የተወረደ ነው።
መደምደሚያ
ይህንን የተመታ እና የተመምታታ ውሃ የማያነሳ ሙግት ሳልማን ሩሽዲ በ 1988 AD “ሰይጣናዊ አንቀፅ” የሚል መጽሐፉን ሲያራግቡ ከነበሩት መካከል ሚሽነሪዎች አንዶቹ ናቸው፤ እስቲ በዚህ ሂስ ባይብል ላይ ያለውን ዳዊት እንመልከተው፤ ይህን ሙግት የዳዊትን ነብይነት ለማስተባበል ሳይሆን እሾህክን በእሾክ እንዴት እንደሆነ ለማሳየት ነው፤ ዳዊት እስራኤልን ቁጠር ሳይባል ቆጥሮ ዳዊት በሰራው ስህተት እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ቸነፈርን ልኮ ከእስራኤልም ሰባ ሺህ ሰዎች በመቅሰፍት ገደለ፦
2ኛ ሳሙኤል 24.14 እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ቸነፈርን ሰደደ፤ ከእስራኤልም ሰባ ሺህ ሰዎች ወደቁ።

ይህ ስህተት የራሱ የዳዊት እንደሆነ አምኗል፣ ይቅርታም ጠይቋል፣ ከዚያም ባሻገር ይህ የእኔ ስህተት ነው ህዝቡን አትንካ ብሎ ጸለየ፣ ነገር ግን የዳዊት ልመናም አልሰራም፦
1ኛ ዜና መዋዕል 21፥8 ዳዊትም እግዚአብሔርን፦ ይህን በማድረግ እጅግ በድያለሁ፤ አሁን ግን ታላቅ ስንፍና አድርጌአለሁና የባሪያህን ኃጢአት ታስወግድ ዘንድ እለምንሃለሁ አለው።
1ኛ ዜና መዋዕል 21፥17 ዳዊትም እግዚአብሔርን፦ ሕዝቡ ይቈጠር ዘንድ ያዘዝሁ እኔ አይደለሁምን? የበደልሁና ክፉ የሠራሁ እኔ ነኝ፤ እነዚህ በጎች ግን ምን አድርገዋል? አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ትሁን፥ ነገር ግን ይቀሠፍ ዘንድ በሕዝብህ ላይ አትሁን አለው።

ታዲያ ዳዊት ማን ቁጠር ብሎት ነው የቆጠረው? ስንል
ዳዊት እስራኤልን የቆጠረው ሰይጣን “ቁጠር” ብሎት ነው ይለናል፦
2ኛ ሳሙኤል 24.1 ደግሞም የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ ዳዊትንም፦ *ሂድ፥ እስራኤልንና ይሁዳን ቍጠር* ብሎ በላያቸው አስነሣው።

ሂድ፥ እስራኤልንና ይሁዳን ቍጠር ያለው ሰይጣን ነው፥ እርሱ የተባለው ህቡዕ ተውላጠ-ስም ሰይጣን መሆኑን ሌላ ጥቅስ ይነግረናል፦
1ኛ ዜና መዋዕል 21፥1 ሰይጣንም በእስራኤል ላይ ተነሣ፥ እስራኤልንም ይቈጥር ዘንድ ዳዊትን “አንቀሳቀሰው”።

“አንቀሳቀሰው” ብለው ያስቀመጡት የዕብራይስጡ ቃል “የሰት” תְּסִיתֵ֥נִי ሲሆን “ሱት” סוּת ማለትም “አሳሳተ” ከሚል ግስ የመጣ ነው ፣ ለሃሰተኛ ነብይ ማሳሳት “የስቲአከ” יְסִֽיתְךָ֡ ማለትም “ቢያስትህ” በሚል መጥቷል፦
ዘዳግም 13.6 አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ ብሎ ቢያስትህ יְסִֽיתְךָ֡፥

ዳዊትም ከሰይጣን መልዕክት የተቀበለውን ለኢዮአብንና ለሕዝቡ አለቆች ቍጠሩ ብሎ አስተላልፏል፦
ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 21.8 ዳዊትም ኢዮአብንና የሕዝቡን አለቆች፦ ሂዱ፥ ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ዳን ድረስ እስራኤልን ቍጠሩ፥ ድምራቸውንም አውቅ ዘንድ አስታውቁኝ አላቸው።

አንዱ ይህንን ሙግት ሳቀርብለት ዳዊት ነብይ አይደለም ብሎ ሽምጥጥ አድርጎ ሊክደኝ ሞክሯል፤ በባይብል የተብራራው ዳዊት የፈጣሪ ነብይ እንደሆነ ይናገራል፦
የሐዋርያት ስራ 2፡29-30 ወንድሞች ሆይ፥ ስለ አባቶች አለቃ ስለ ዳዊት እንደ ሞተም እንደ ተቀበረም ለእናንተ በግልጥ እናገር ዘንድ ፍቀዱልኝ፤ መቃብሩም እስከ ዛሬ በእኛ ዘንድ ነው። *ነቢይ ስለ ሆነ*፥

አዎ ዳዊት ነብይ ነበረ ከተባለ፤ የነብይ መስፈርቱ ከፈጣሪ መልዕክት መቀበል ወይስ ከሰይጣን መልዕክት መቀበል ? ፍርዱን ለህሊና።

ከወንድም ወሒድ ዑመር

https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም።
ብዙ ሚስት


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

መግቢያ
ስለ ጋብቻ የሚያጠናው የትምህርት ዘርፍ በምሁራን ዘንድ ማትሪሞኒ”matrimony” ይባላል፤ ይህም ስነ-ጋብቻ ጥናት የሚያጠኑ ምሁራን በዋነኝነት ለሁለት ይከፍሉታል፦
1. ተመሳሳይ ፃታ ግንኙነት ሆሞ-ሴክሹአል”homosexual”
2. ተቃራኒ ፃታ ሄትሮ-ሴክሹአል”Heterosexual” ይባላሉ። መቼም ተመሳሳይ ፃታ ግንኙነት ለጊዜው አርስታችን ስላልሆነ ወደ ተቃራኒ ፃታ ጋብቻ እንሂድ፤ ተቃራኒ ፆታ ጋብቻ እራሱ በአራት ይከፈላል፤ እነርሱም፦
1ኛ. አንድ ወንድ ለአንድ ሴት አንዲት ሴት ለአንድ ወንድ ሲሆን ሞኖጋሚ”Monogamy” ይባላል፤ “Monogamy” የግሪክ ቃል ነው፥ “mono” ማለት “ብቻ” ማለት ሲሆን “gamy” ደግሞ “ጋብቻ” ማለት ነው።
2ኛ. አንድ ወንድ ለብዙ ሴት አንዲት ሴት ለብዙ ወንድ ሲሆን ፓሊጋሚ”Polygamy” ይባላል፤ “polygamy” የግሪክ ቃል ነው፥ “poly” ማለት “ብዙ” ማለት ሲሆን “gamy” ደግሞ “ጋብቻ” ማለት ነው።
3ኛ. አንድ ወንድ ለብዙ ሴት ሲሆን ፓሊአንድሪ”Polyandry” ይባላል፤ “Polyandry” የግሪክ ቃል ነው፥ “poly” ማለት “ብዙ” ማለት ሲሆን “andry” ደግሞ “ወንድ” ማለት ነው።
4ኛ. አንዲት ሴት ለብዙ ወንድ ሲሆን ፓሊጂኒ”Polygyny” ይባላል፤ “Polygyny” የግሪክ ቃል ነው፥ “poly” ማለት “ብዙ” ማለት ሲሆን “gyny” ደግሞ “ሴት” ማለት ነው፤ ይህኛው ጋብቻ በማህበራዊ ጥናት”sociology” ላይ የተቀመጠ መረጃ እንጂ ስነ-መለኮታዊ ጥናት”theology” ላይ አልተቀመጠም።
ይህን በግርድፉ እና በሌጣ ካየን ዘንዳ ደርዝና ፈርጅ ባለው መልኩ ስለ አንድ ወንድ ለብዙ ሴት”Polyandry” ከቁርአን እና ከባይብል እናያለን፦

ነጥብ አንድ
“ብዙ ሚስት በቁርአን”
“አሕካም” أحكام “የሑክም” حُكْم ብዙ ቁጥር ሲሆን “ፍርድ” ወይም “ህግ” ማለት ነው፤ በኢስላም “ህጎች” በአምስት ይከፈላሉ፤ እነርሱም፦ 1ኛ. “ፈርድ” فرض ማለትም “የታዘዘ”
2ኛ. “ሙስተሐብ” مستحب” ማለትም “የተወደደ”
3ኛ. “ሙባሕ” مباح ማለትም “የተፈቀደ”
4ኛ. “መክሩህ” مكروه” ማለትም “የተጠላ”
5ኛ. “ሐራም” حرام” ማለትም “የተከለከለ ናቸው።
ይህ “ፊቅህ” فقه የተባለውን የስነ-ህግ ጥናት ዋቢና ታሳቢ ያደረገ ነው፤ “ፊቅህ” ስነ-ህግ ጥናት”the study of law” ሲሆን ህግ አዋቂ ደግሞ “ፈቂህ” فقيه ይባላል፤ ይህንን ነጥብ ያነሳሁት ስለ አሕካም ለመዳሰስ ሳይሆን አንድ ወንድ ለብዙ ሴት”Polyandry” የተባለው የጋብቻ አይነት በኢስላም በኒያ ሙስተሐብ ሲሆን በፍትህ ሙባሕ ነው፤ ነገር ግን ፈርድ አይደለም፦
4:3 በየቲሞችም ማግባት አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ፣ ዝሙትንና ከተወሰነላችሁ በላይ ማግባትንም ፍሩ፤ ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት፣ ሦስት ሦስትም፣ አራት አራትም አግቡ። አለማስተካከልንም ብትፈሩ፣ “”አንዲትን ብቻ””፣ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፤ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው።

በኢስላም በፍትህ ማስተካከል ከተቻለ እስከ አራት ማግባት ይቻላል፤ ነገር ግን ያ ካልሆነ አንዲት ብቻ ነው ማግባት ያለበት፤ እዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሳ ጥያቄ አላህ የጋብቻን ገደብ እስከ አራት ካለ ለምንድን ነው ነብያችን እስከ ዘጠኝ ያገቡት? የሚል ነው፤ አንደኛ ምላሽ የሚሆነው አምላካችን አላህ ስለፈቀደ ነው፤ ሁለተኛ እንደሚታወቀው ቁርአን በአንድ ጊዜና ቦታ የወረደ ግህደተ-መለኮት ሳይሆን በሒደት የወረደ ግህደተ-መለኮት ነው፤ መካ ላይ ለአስር ዓመታትን ሲወርድ መዲና ላይ ደግሞ ለአስራ ሶስት ዓመታትን ወርዷል፤ የዓለማቱ ጌታ አላህ ጋብቻን የመጨረሻ ገደብ አራት ብቻ መሆኑን የሚያበስረው አንቀፅ ሲያወርድ ነብያችን ቀደም ብለው ዘጠኝ ሚስቶች ነበሯቸው፤ ይህ የቁርአን ታሪካዊ ዳራ ከአለመረዳት የሚመጣ ጥያቄ ነው።
ነጥብ ሁለት
“ብዙ ሚስት በባይብል”
ከአንድ በላይ ማግባት በባይባል የተከለከለበት አንድ ጥቅስ የለም፤ ከዚያ ይልቅ ከአንድ በላይ ያገቡ ነቢያት በቁና ሰፍሯል፦
ዘፍጥረት 31፥17 ያዕቆብም ተነሣ፥ ልጆቹንና “ሚስቶቹንም” በግመሎች ላይ አስቀመጠ፤
መሣፍንት 8፥30 ለጌዴዎንም “ብዙ ሚስቶች” ነበሩትና ከወገቡ የወጡ ሰባ ልጆች ነበሩት።
1ኛ ሳሙኤል 1፥2 ሕልቃ…””ሁለትም ሚስቶች” ነበሩት፤ የአንዲቱ ስም ሐና የሁለተኛይቱም ስም ፍናና ነበረ፤
1ኛ ሳሙኤል 25፥43 ዳዊትም ደግሞ ኢይዝራኤላዊቱን አኪናሆምን ወሰደ፤ “”ሁለቱም ሚስቶች” ሆኑለት።
1ኛ ነገሥት 11፥3 ለእርሱም ወይዛዝር የሆኑ “”ሰባት መቶ ሚስቶች”” ሦስት መቶም ቁባቶች ነበሩት፤
1ኛ ዜና መዋዕል 4፥5 ለቴቁሔም አባት ለአሽሑር ሔላና ነዕራ “”የተባሉ ሁለት ሚስቶች”” ነበሩት።
1ኛ ዜና መዋዕል 14፥3 ዳዊትም በኢየሩሳሌም “”ሚስቶችን”” ጨምሮ ሌሎችን ወንዶችንና ሴቶችን ልጆች ወለደ።

አይ እነርሱ አደረጉት እንጂ ፈጣሪ አልፈቀደላቸውም ከተባለ ፈጣሪ አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ካሉት እንዴት መንከባከብ እንዳለበት የተናገረው ሳይፈቅድ ነውን? እስቲ እንይ፦
ዘዳግም 21፥15-17 ለአንድ ሰው አንዲቱ የተወደደች አንዲቱም የተጠላች “”ሁለት ሚስቶች”” ቢኖሩት፥ ለእርሱም የተወደደችው ደግሞም የተጠላችው ልጆችን ቢወልዱ፥ በኵሩም ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ ቢሆን፥ ለልጆቹ ከብቱን በሚያወርስበት ቀን ከተጠላችው ሚስት በተወለደው በበኵሩ ፊት ከተወደደችው ሚስት የተወለደውን ልጅ በኵር ያደርገው ዘንድ አይገባውም፤ ነገር ግን ከከብቱ ሁለት እጥፍ ለእርሱ በመስጠት ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ በኵር እንደ ሆነ ያስታውቅ። የኃይሉ መጀመሪያ ነውና በኵርነቱ የእርሱ ነው።

እግዚአብሔር ከአንድ በላይ ማግባት ቢከለክል ኖሮ ለዳዊት ለዛውን  የሰውን ሚስቶችን ይሰጠው ነበርን? የጌታው  የሳኦን ሚስቶች ሰቶት ነበር፤ ከዚያ የበለጠም ካስፈለገ እንደሚጨምርለት ቃል ገብቶለታል፦
               2ኛ ሳሙኤል 12 : 8 የጌታህንም ቤት ሰጠሁህ፥ “”የጌታህንም ሚስቶች” በብብትህ “”ጣልሁልህ””፤ የእስራኤልንና የይሁዳን ቤት ሰጠሁህ፤ “”ይህም አንሶ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበለጠ እጨምርልህ ነበር””።”

ሌላው የአዲስ ኪዳን ነብይ ኢየሱስ ነው፤ ኢየሱስ ከአንድ በላይ ማግባት ክልክል ነው አላለም፤ በብሉይ የነበረውን ህግ አልሻረም። ሌላው እራሳቸውን የሚያስጠጉበት ጳውሎስ ነው፤ ሲጀመር ጳውሎስ ነብይ አይደለም፤ ሲቀጥል የሚናገረው በሞኝነት እንጂ ጌታ አዞት አይደለም፤ ንግግሩ የራሱ እንጂ የጌታ አይደለም፦
1ኛ ቆሮ 7፥12 ሌሎችንም “””እኔ እላለሁ፥ ጌታም አይደለም””፤ ከወንድሞች ወገን ያላመነች ሚስት ያለችው ቢኖር እርስዋም ከእርሱ ጋር ልትቀመጥ ብትስማማ፥ አይተዋት፤”
2ኛ ቆሮ 11፥17እንደዚህ ታምኜ ስመካ “”የምናገረው፥ በሞኝነት እንጂ ጌታ እንዳዘዘኝ አልናገርም””።”

ሲሰልስ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ባል ይኑራት አለ እንጂ ለእያንዳንዱ ለራሱ አንድ ሚስት ትኑረው አንድ ባል ይኑራት አላለም፦
1ኛ ቆሮ 7፥2 ነገር ግን ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራስዋ ባል ይኑራት።”

ከአንድ በላይ ማግባት ክልክል ነው ያሉት ምዕራባውያን እንጂ ባይብል አይደለም፤ ምዕራባውያን ከአንድ በላይ ማግባት ቢከለክሉም ከአንድ በላይ ዝሙት ማድረግ የአንድ ሰው መብቱና ነፃነቱ ነው የሚል መርህ አላቸው፤ ምዕራባውያን በ 17ኛው ክፍለ-ዘመን ሰው እንዲዋለድና እንዲባዛ ስላልፈለጉ እንጂ የመጡበትን ዳራ መሰረት አድርገው አይደለም፤ ለዛ ነው ግብረ-ሰዶም እንዲስፋፋ የተፈለገው፤ ይህንን እንደ ሥልጣኔ ቤተ-ክርስቲያን ግብረ-ሰዶም ታጋባለች፤ ይህ ደግሞ መሠልጠን ሳይሆን መሰይጠን ነው፤ ሥልጣኔ በምጣኔ ካልሆነ ጥፋት ነው፤ ምዕራባውያን ከአንድ በላይ ዝሙት ሲፈቅዱ ኢስላም ደግሞ ከአንድ በላይ በሃላል ኒካ ማድረግ ይፈቅዳል፦
24:32 ከእናንተም ትዳር የሌላቸውን አጋቡ፤ “ከወንዶች ባሮቻችሁ” عِبَادِكُمْ እና “ከሴቶች ባሮቻቹሁም” وَإِمَائِكُمْ ለጋብቻ ብቁ የሆኑትን “አጋቡ” وَأَنْكِحُوا፤ ድሆች ቢሆኑ፤ አላህም ከችሮታው ያከብራቸዋል፤ አላህም ስጦታ ሰፊ ዓዋቂ ነው።
2:221አጋሪ የሆኑ ሴቶች እስከሚያምኑ ድረስ “አታግቡዋቸው” وَلَا تَنْكِحُوا ፡፡ ከአጋሪይቱ ምንም ብትደንቃችሁም እንኳ “ያመነችው ባሪያ” وَلَأَمَةٌ مُؤْمِنَةٌ በእርግጥ በላጭ ናት፡፡ ለአጋሪዎቹም እስከሚያምኑ ድረስ “አትዳሩላቸው” وَلَا تُنْكِحُوا ፡፡ ከአጋሪው ምንም ቢደንቃችሁ “ምእምኑ ባሪያ” وَلَعَبْدٌ مُؤْمِنٌ በላጭ ነው፡፡
4:25 ከእናንተም ውስጥ “ጥብቆች” ምእምናት” الْمُحْصَنَاتِ الْمُؤْمِنَاتِ የሆኑትን “ለማግባት” يَنْكِحَ ሀብትን ያልቻለ ሰው፣ “እጆቻችሁ ካደረጓቸው” مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ከምእመናት “ባሪያን” فَتَيَاتِكُمُ الْمُؤْمِنَاتِ “ያግባ”፤

በወንድም ወሒድ ዑመር

https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ተሕሪም


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

66:1 አንተ ነቢዩ ሆይ አላህ ለአንተ የፈቀደልህን ነገር ሚስቶችህን ማስወደድን የምትፈልግ ስትሆን በአንተ ላይ ለምን “እርም” ታደርጋለህ?፤ አላህ እጅግ መሐሪ አዛኝ ነው يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ لِمَ تُحَرِّمُ مَآ أَحَلَّ ٱللَّهُ لَكَ ۖ تَبْتَغِى مَرْضَاتَ أَزْوَٰجِكَ ۚ وَٱللَّهُ غَفُورٌۭ رَّحِيمٌۭ ።

መግቢያ
ሚሽነሪዎች ኢስላምን ለማጠልሸት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የማይደረምሱት መሬት የለም ብዬ ብናገር ግነት፣ እብለት ወይም ቅጥፈት አይሆንብኝም፤ በባይብል ላይ ስለ ነብያት የተዘገበው ለሰሚም ለተመልካችም ግራ የሆነው ትረካ በዋል ፈሰስ አስቀርተው የነብያት መደምደሚያ የሆኑትን ነብያችንን”ﷺ” ሊወርፉ ሲነሱ ማየት የሚያጅብ ነው፤ ለማንኛውም እግር እራስን አያክምና ቅድሚያ የራሳችሁን ባይብል ፈትሹት፤ ወደ አርስታችን ስንገባ ሱረቱ አተሕሪም የተባለው ሱራህ የወረደበት ሰበብ ሪዋያህ ነጥብ በነጥብ እንመለከታለን፦

ነጥብ አንድ
“እርም”
“ተሕሪም” تَحريم የሚለው ቃል “ሐርረመ” حَرَّمَ ማለትም “ከለከለ” ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን “እርም” ወይም “ክልክል” ማለት ነው፤ “ሐራም” حَرَام “የተከለከለ” የረባበት ግስ እና ተሕሪም አንድ ሥርወ-ግንድ ነው፤ አንድ ጊዜ ነብያችን”ﷺ” ከባለቤታቸው ከዘይነብ ቢንት ጀህሽ”ረ.ዓ.” ቤት ሄደው ማር አጠጥታቸው፤ ሌሎች የነብያችን”ﷺ” ባልተቤቶች ይህንን ሲያውቁ ቅናት ተሰምቷቸው በመመካከር፦ ምንድን ነው የበላኸው? የአፍህ ጠረን “መጋፊር” مَغَافِيرَ ይሸታል፤ መጋፊር በልተሃል ወይ? በማለት ጠየቁ፤ “መጋፊር” ማለት የአበባ አይነት ሲሆን ጠረኑ መጥፎ ሲሆን ይህንን በልተው የአፋቸው ሽታ እንደተቀየረ ለማስመሰል ተናገሩ፤ ከዚያ ነብያችንም”ﷺ” ከዛሬ በኃላ ማር አልጠጣም ብለው ባለቤቶቻቸውን ለማስደሰት እርም አሉ፤ አላህም፦ ሚስቶችን ለማስወደድ ብለህ ለምን አላህ ለአንተ የፈቀደልህን ነገር በአንተ ላይ ለምን እርም ታደርጋለህ? የሚለውን አንቀፅ አወረደ፦
66:1-4 አንተ ነቢዩ ሆይ አላህ ለአንተ “የፈቀደልህን” ነገር “ሚስቶችህን ማስወደድን” የምትፈልግ ስትሆን በአንተ ላይ ለምን “እርም” ታደርጋለህ?፤ አላህ እጅግ መሐሪ አዛኝ ነው يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ لِمَ تُحَرِّمُ مَآ أَحَلَّ ٱللَّهُ لَكَ ۖ تَبْتَغِى مَرْضَاتَ أَزْوَٰجِكَ ۚ وَٱللَّهُ غَفُورٌۭ رَّحِيمٌۭ ።

ነጥብ ሁለት
“መሓላ”
የነብያችን”ﷺ” ባልተቤቶች መጋፊር በልተው የአፋቸው ሽታ እንደተቀየረ ለማስመሰል ስለነገሯቸው ነብያችን”ﷺ”፦ “በፍፁም ከዘይነብ ቢንት ጀህሽ”ረ.ዓ.” ቤት ማር ጠጥቻለው ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ ግን አልጠጣም” ብለው ምለው ተገዝተው ነበር፤ ለማሃላቸው ማካካሻ ካደረጉ አላህ እጅግ መሐሪ አዛኝ ነው፤ “የመሓሎቻችሁን መፍቻ” ማድረጉ እርሱም ዐዋቂው ጥበበኛው ነው፦
66፥2 አላህ ለእናንተ የመሓሎቻችሁን መፍቻ ደነገገላችሁ፤ አላህም እረዳታችሁ ነው፤ እርሱም ዐዋቂው ጥበበኛው ነው قَدْ فَرَضَ ٱللَّهُ لَكُمْ تَحِلَّةَ أَيْمَٰنِكُمْ ۚ وَٱللَّهُ مَوْلَىٰكُمْ ۖ وَهُوَ ٱلْعَلِيمُ ٱلْحَكِيمُ ፡፡

የማለ ሰው መሃላውን ቢፈታ ዐስርን ምስኪኖች ማብላት፣ ወይም እነርሱን ማልበስ ወይንም ጫንቃን ነጻ ማውጣት ነው፤ ከተባሉት አንዱን ያላገኘም ሰው ሦስት ቀኖችን መጾም ነው፤ ይህ የመሐላዎቻችሁ ማካካሻ ነው፦
5፥89 አላህ በመሐላዎቻችሁ በውድቁ አይዛችሁም፤ ነገር ግን መሐላዎችን ባሰባችሁት ይይዛችኋል፡፡ ማስተሰሪያውም ቤተሰቦቻችሁን ከምትመግቡት ከመካከለኛው ምግብ ዐስርን ምስኪኖች ማብላት ወይም እነርሱን ማልበስ ወይንም ጫንቃን ነጻ ማውጣት ነው፤ ከተባሉት አንዱን ያላገኘም ሰው ሦስት ቀኖችን መጾም ነው፤ ይህ በማላችሁ ጊዜ የመሐላዎቻችሁ ማካካሻ ነው፡፡ መሐላዎቻችሁንም ጠብቁ፡፡ እንደዚሁ አላህ ለናንተ አንቀጾችን ያብራራል፡፡ እናንተ ልታመሰግኑ ይከጀላልና لَا يُؤَاخِذُكُمُ ٱللَّهُ بِٱللَّغْوِ فِىٓ أَيْمَٰنِكُمْ وَلَٰكِن يُؤَاخِذُكُم بِمَا عَقَّدتُّمُ ٱلْأَيْمَٰنَ ۖ فَكَفَّٰرَتُهُۥٓ إِطْعَامُ عَشَرَةِ مَسَٰكِينَ مِنْ أَوْسَطِ مَا تُطْعِمُونَ أَهْلِيكُمْ أَوْ كِسْوَتُهُمْ أَوْ تَحْرِيرُ رَقَبَةٍۢ ۖ فَمَن لَّمْ يَجِدْ فَصِيَامُ ثَلَٰثَةِ أَيَّامٍۢ ۚ ذَٰلِكَ كَفَّٰرَةُ أَيْمَٰنِكُمْ إِذَا حَلَفْتُمْ ۚ وَٱحْفَظُوٓا۟ أَيْمَٰنَكُمْ ۚ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ ٱللَّهُ لَكُمْ ءَايَٰتِهِۦ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ ፡፡
ነጥብ ሶስት
“ሚስጥር”
ነብያችን”ﷺ” ከባለቤታቸው አንዷ ለሆነችው ለሃፍሳ”ረ.ዓ.” “በፍፁም ከዘይነብ ቢንት ጀህሽ”ረ.ዓ.” ቤት ማር ጠጥቻለው ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ ግን አልጠጣም” ብለው ይህ ወሬ በሚስጥር በመሰጠሯት ጊዜ ሄዳ ለዓኢሻ”ረ.ዓ.” ተናገረች፤ ነብይ ማለት የሩቅ እውቀት የሚገለጥለት ነውና ለዓኢሻ”ረ.ዓ.” በተናገረች ጊዜ የተናገረችውን ከፊሉን አሳውቀዋት ከፊሉን ችላ ብለው ሲተዉት፤ በዚያ በነገሯት ነገር ሃፍሳ”ረ.ዓ.”፦ ይህን ማን ነገረህ? ብላ አለቻቸው፤ ነብያችንም”ﷺ”፦ «ዐዋቂው ውስጠ ዐዋቂው ነገረኝ» አሏት፤ ይህንን ጉዳይ አምላካችን አላህ እንዲህ ይነግረናል፦
66፥3 ነቢዩ ከሚስቶቹ ወደ አንዷ ወሬን በመሰጠረ ጊዜ አስታውስ፡፡ እርሱንም በነገረች እና አላህ እርሱን ማውራትዋን ባሳወቀው ጊዜ ከፊሉን አስታወቀ፤ ከፊሉንም ተወ፡፡ በእርሱም ባወራት ጊዜ «ይህን ማን ነገረህ?» አለች፡፡ «ዐዋቂው ውስጠ ዐዋቂው ነገረኝ» አላት وَإِذْ أَسَرَّ ٱلنَّبِىُّ إِلَىٰ بَعْضِ أَزْوَٰجِهِۦ حَدِيثًۭا فَلَمَّا نَبَّأَتْ بِهِۦ وَأَظْهَرَهُ ٱللَّهُ عَلَيْهِ عَرَّفَ بَعْضَهُۥ وَأَعْرَضَ عَنۢ بَعْضٍۢ ۖ فَلَمَّا نَبَّأَهَا بِهِۦ قَالَتْ مَنْ أَنۢبَأَكَ هَٰذَا ۖ قَالَ نَبَّأَنِىَ ٱلْعَلِيمُ ٱلْخَبِيرُ ፤

ነጥብ አራት
“ተውበት”
አላህ በተከበረው ንግግሩ፦ ለነብያችን”ﷺ” ሁለቱ ባለቤቶቻቸው ለዓኢሻ”ረ.ዓ.” እና ለሃፍሳ”ረ.ዓ.”፦ ወደ አላህ በተውበት ብትመለሱ ልቦቻው ተዘንብለዋልና፤ አይ ካላችሁ ብትረዳዱ አላህ እርሱ ረዳቱ ነው፣ ጂብሪልም፣ ከምእምናንም መልካሙ ከዚህም በኋላ መላእክቱ ረዳቶቹ ናቸው። ከዚያም ባሻገር ቢፈታችሁ አላህ ከእናንተ የበለጡ ሚስቶችን ሙስሊሞች፣ አማኞች፣ ታዛዦች፣ ተጸጻቾች፣ አምላኪዎች፣ ጾመኞች፣ ፈቶች፣ ደናግልም የኾኑትን ሊያመጣለት ይችላል በማለት መለሰ፦
66፥4-5 ወደ አላህ ብትመለሱ ልቦቻችሁ በእርግጥ ተዘንብለዋልና ትስማማላችሁ፡፡ በእርሱም ላይ ብትረዳዱ አላህ እርሱ ረዳቱ ነው፣ ጂብሪልም፣ ከምእምናንም መልካሙ ከዚህም በኋላ መላእክቱ ረዳቶቹ ናቸው إِن تَتُوبَآ إِلَى ٱللَّهِ فَقَدْ صَغَتْ قُلُوبُكُمَا ۖ وَإِن تَظَٰهَرَا عَلَيْهِ فَإِنَّ ٱللَّهَ هُوَ مَوْلَىٰهُ وَجِبْرِيلُ وَصَٰلِحُ ٱلْمُؤْمِنِينَ ۖ وَٱلْمَلَٰٓئِكَةُ بَعْدَ ذَٰلِكَ ظَهِيرٌ ። ቢፈታችሁ ከእናንተ የበለጡ ሚስቶችን ሙስሊሞች፣ አማኞች፣ ታዛዦች፣ ተጸጻቾች፣ አምላኪዎች፣ ጾመኞች፣ ፈቶች፣ ደናግልም የኾኑትን ጌታው ሊለውጠው ይከጀላል عَسَىٰ رَبُّهُۥٓ إِن طَلَّقَكُنَّ أَن يُبْدِلَهُۥٓ أَزْوَٰجًا خَيْرًۭا مِّنكُنَّ مُسْلِمَٰتٍۢ مُّؤْمِنَٰتٍۢ قَٰنِتَٰتٍۢ تَٰٓئِبَٰتٍ عَٰبِدَٰتٍۢ سَٰٓئِحَٰتٍۢ ثَيِّبَٰتٍۢ وَأَبْكَارًۭا ፡፡


መደምሚያ
ተፍሲሩል ኢብኑ ከሲር ኢማም ቡኻሪይ መሰረት አድገው እና ተፍሲሩል ቁርጡቢ ኢማም ሙስሊም መሰረት አድርገው ይህን ሱራህ ፈስረውቷል፤ ይህንን ወህይ መውረድ ምክንያት አራት ሙሐዲሲን አስቀምጠውታል፤ እነርሱም ኢማን ቡኻሪይ፣ ኢማም ሙስሊም፣ ኢማም አቢ ዳውድ እና ኢማም ነሳኢ ናቸው፦
1ኛ. ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 68 , ሐዲስ 17:
ዓኢሻ”ረ.ዓ.” እንደተናገረችው፦ ነብዩ”ﷺ” ከዘይነብ ቢንት ጀህሽ”ረ.ዓ.” ጋር ትንሽ ጊዜ በመቆየት እና ከእርሷ ቤት ማር ይጠጡ ነበር፤ ስለዚህ ሃፍሳ”ረ.ዓ.” እና እኔ ፦”ነብዩ”ﷺ”
ወደ እኛ ከመጡ እርሷ፦ የመጋፊር ሽታ ሸተኸኛል እንድትል ወሰንን፤ መጋፊር በልተሃልን? ከዚያም ነብዩ”ﷺ” ከእነርሱ አንዷን ሲዘይሩ እንዲሁ በተመሳሳይ አለቻቸው፤ ነብዩም”ﷺ” ፦ “በፍፁም ከዘይነብ ቢንት ጀህሽ”ረ.ዓ.” ቤት ማር ጠጥቻለው ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ ግን አልጠጣም” አሉ፤ ስለዚህ ይህ አንቀፅ ወረደ፦
66:1 አንተ ነቢዩ ሆይ አላህ ለአንተ የፈቀደልህን ነገር ሚስቶችህን ማስወደድን የምትፈልግ ስትሆን በአንተ ላይ ለምን እርም ታደርጋለህ?
66፥4 “ወደ አላህ ሁለታችሁ ብትመለሱ” ይህ የሚያመለክተው ዓኢሻ”ረ.ዓ.” እና ሃፍሳን”ረ.ዓ.” ነው፤
66፥3 ነቢዩ ከሚስቶቹ ወደ አንዷ ወሬን በመሠጠረ ጊዜ አስታውስ”
ማለትም “እኔ ግን ጥቂት ማር ጠጥቻለው” አሉ።
يَقُولُ سَمِعْتُ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَمْكُثُ عِنْدَ زَيْنَبَ ابْنَةِ جَحْشٍ، وَيَشْرَبُ عِنْدَهَا عَسَلاً، فَتَوَاصَيْتُ أَنَا وَحَفْصَةُ أَنَّ أَيَّتَنَا دَخَلَ عَلَيْهَا النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم فَلْتَقُلْ إِنِّي أَجِدُ مِنْكَ رِيحَ مَغَافِيرَ، أَكَلْتَ مَغَافِيرَ فَدَخَلَ عَلَى إِحْدَاهُمَا فَقَالَتْ لَهُ ذَلِكَ، فَقَالَ ‏”‏ لاَ بَلْ شَرِبْتُ عَسَلاً عِنْدَ زَيْنَبَ ابْنَةِ جَحْشٍ وَلَنْ أَعُودَ لَهُ ‏”‌‏.‏ فَنَزَلَتْ ‏{‏يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ لِمَ تُحَرِّمُ مَا أَحَلَّ اللَّهُ لَكَ‏}‏ إِلَى ‏{‏إِنْ تَتُوبَا إِلَى اللَّهِ‏}‏ لِعَائِشَةَ وَحَفْصَةَ ‏{‏وَإِذْ أَسَرَّ النَّبِيُّ إِلَى بَعْضِ أَزْوَاجِهِ‏}‏ لِقَوْلِهِ ‏”‏ بَلْ شَرِبْتُ عَسَلاً ‏”‌‏
2ኛ. ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 18, ሐዲስ 27:
وَحَدَّثَنِي مُحَمَّدُ بْنُ حَاتِمٍ، حَدَّثَنَا حَجَّاجُ بْنُ مُحَمَّدٍ، أَخْبَرَنَا ابْنُ جُرَيْجٍ، أَخْبَرَنِي عَطَاءٌ، أَنَّهُ سَمِعَ عُبَيْدَ بْنَ عُمَيْرٍ، يُخْبِرُ أَنَّهُ سَمِعَ عَائِشَةَ، تُخْبِرُ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَمْكُثُ عِنْدَ زَيْنَبَ بِنْتِ جَحْشٍ فَيَشْرَبُ عِنْدَهَا عَسَلاً قَالَتْ فَتَوَاطَأْتُ أَنَا وَحَفْصَةُ أَنَّ أَيَّتَنَا مَا دَخَلَ عَلَيْهَا النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم فَلْتَقُلْ إِنِّي أَجِدُ مِنْكَ رِيحَ مَغَافِيرَ أَكَلْتَ مَغَافِيرَ فَدَخَلَ عَلَى إِحْدَاهُمَا فَقَالَتْ ذَلِكَ لَهُ ‏.‏ فَقَالَ ‏”‏ بَلْ شَرِبْتُ عَسَلاً عِنْدَ زَيْنَبَ بِنْتِ جَحْشٍ وَلَنْ أَعُودَ لَهُ ‏”‏ ‏.‏ فَنَزَلَ ‏{‏ لِمَ تُحَرِّمُ مَا أَحَلَّ اللَّهُ لَكَ‏}‏ إِلَى قَوْلِهِ ‏{‏ إِنْ تَتُوبَا‏}‏ لِعَائِشَةَ وَحَفْصَةَ ‏{‏ وَإِذْ أَسَرَّ النَّبِيُّ إِلَى بَعْضِ أَزْوَاجِهِ حَدِيثًا‏}‏ لِقَوْلِهِ ‏”‏ بَلْ شَرِبْتُ عَسَلاً ‏”‏ ‏.‏
3ኛ. ሱነን ነሳኢ መጽሐፍ 27 , ሐዲስ 33:
أَخْبَرَنَا قُتَيْبَةُ، عَنْ حَجَّاجٍ، عَنِ ابْنِ جُرَيْجٍ، عَنْ عَطَاءٍ، أَنَّهُ سَمِعَ عُبَيْدَ بْنَ عُمَيْرٍ، قَالَ سَمِعْتُ عَائِشَةَ، زَوْجَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَمْكُثُ عِنْدَ زَيْنَبَ وَيَشْرَبُ عِنْدَهَا عَسَلاً فَتَوَاصَيْتُ وَحَفْصَةَ أَيَّتُنَا مَا دَخَلَ عَلَيْهَا النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم فَلْتَقُلْ إِنِّي أَجِدُ مِنْكَ رِيحَ مَغَافِيرَ فَدَخَلَ عَلَى إِحْدَاهُمَا فَقَالَتْ ذَلِكَ لَهُ فَقَالَ ‏”‏ بَلْ شَرِبْتُ عَسَلاً عِنْدَ زَيْنَبَ – وَقَالَ – لَنْ أَعُودَ لَهُ ‏”‏ ‏.‏ فَنَزَلَ ‏{‏ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ لِمَ تُحَرِّمُ مَا أَحَلَّ اللَّهُ لَكَ ‏}‏ ‏{‏ إِنْ تَتُوبَا إِلَى اللَّهِ ‏}‏ لِعَائِشَةَ وَحَفْصَةَ ‏{‏ وَإِذْ أَسَرَّ النَّبِيُّ إِلَى بَعْضِ أَزْوَاجِهِ حَدِيثًا ‏}‏ لِقَوْلِهِ ‏”‏ بَلْ شَرِبْتُ عَسَلاَ ‏”‏ ‏.‏ كُلُّهُ فِي حَدِيثِ عَطَاءٍ ‏.‏
4ኛ. ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 27 , ሐዲስ 46:
حَدَّثَنَا أَحْمَدُ بْنُ مُحَمَّدِ بْنِ حَنْبَلٍ، حَدَّثَنَا حَجَّاجُ بْنُ مُحَمَّدٍ، قَالَ قَالَ ابْنُ جُرَيْجٍ عَنْ عَطَاءٍ، أَنَّهُ سَمِعَ عُبَيْدَ بْنَ عُمَيْرٍ، قَالَ سَمِعْتُ عَائِشَةَ، – رضى الله عنها – زَوْجَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم تُخْبِرُ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَمْكُثُ عِنْدَ زَيْنَبَ بِنْتِ جَحْشٍ فَيَشْرَبُ عِنْدَهَا عَسَلاً فَتَوَاصَيْتُ أَنَا وَحَفْصَةُ أَيَّتُنَا مَا دَخَلَ عَلَيْهَا النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم فَلْتَقُلْ إِنِّي أَجِدُ مِنْكَ رِيحَ مَغَافِيرَ فَدَخَلَ عَلَى إِحْدَاهُنَّ فَقَالَتْ لَهُ ذَلِكَ فَقَالَ ‏”‏ بَلْ شَرِبْتُ عَسَلاً عِنْدَ زَيْنَبَ بِنْتِ جَحْشٍ وَلَنْ أَعُودَ لَهُ ‏”‏ ‏.‏ فَنَزَلَتْ ‏{‏ لِمَ تُحَرِّمُ مَا أَحَلَّ اللَّهُ لَكَ تَبْتَغِي ‏}‏ إِلَى ‏{‏ إِنْ تَتُوبَا إِلَى اللَّهِ ‏}‏ لِعَائِشَةَ وَحَفْصَةَ رضى الله عنهما ‏{‏ وَإِذْ أَسَرَّ النَّبِيُّ إِلَى بَعْضِ أَزْوَاجِهِ حَدِيثًا ‏}‏ لِقَوْلِهِ ‏”‏ بَلْ شَرِبْتُ عَسَلاً ‏”‏ ‏.‏

እንዲህ በሰሒሕ እና በሐሠን ሪዋያህ መረዳት ነው እንጂ ሪዋያህ በሌላቸው ከሼኽ ጎግል በሚለቃቀመው ደኢፍ እና መውዱዕ ጥንቅሮች መፎተት እራስን ማታለል ነው፤ አላህ በእርሱ መንገድ ላይ እርሱን ለማግኘት እሾት ያላቸውን ሰዎች ሂዳያ ይስጣቸው ለእኛም ፅናቱን ይስጠን አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር

https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም