ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.3K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
የማይሞት አምላክ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

25፥58 በዚያም በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ፡፡ وَتَوَكَّلْ عَلَى الْحَيِّ الَّذِي لَا يَمُوتُ

አምላካችን አሏህ ስለ እርሱ ኑባሬ በሦስተኛ መደብ ሲናገር፦ "የማይሞተው ሕያው አምላክ" በማለት መዋቲነት በእርሱ ሕያውነት ላይ እንደሌለበት ይናገራል፦
25፥58 በዚያም በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ፡፡ وَتَوَكَّلْ عَلَى الْحَيِّ الَّذِي لَا يَمُوتُ

በባይብልም ቢሆን አንድ ሰው እንኳ ያላየው አንዱ አምላክ ብቻ የማይሞት ነው፥ ይህም የማይሞት ብቻውን አምላክ የሚሆን ነው፦
1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥16 እርሱ ብቻ "የማይሞት ነው"፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም።
1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥17 ብቻውን አምላክ ለሚሆን "ለማይሞተው" ለማይታየውም ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን። Τῷ δὲ Βασιλεῖ τῶν αἰώνων, ἀφθάρτῳ ἀοράτῳ μόνῳ Θεῷ, τιμὴ καὶ δόξα εἰς τοὺς αἰῶνας τῶν αἰώνων· ἀμήν.

የማይታየው ይህ ብቻውን ያለ አምላክ የማይሞት"immortal" ከሆነ ኢየሱስ ከእርሱ በተቃራኒው ሟች ነው። እንደ ጳውሎስ ትምህርት "አንዱ" ሞተ ሲባል "አንዱ አምላክ" ማለቱ ሳይሆን "አንዱ ሰው" ሞተ ማለቱ ነው፦
2ኛ ቆሮንቶስ 5፥14 "አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ"።
ሮሜ 5፥15 "በአንዱ ሰው" በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የሆነው ስጦታ ከዚያ ይልቅ ለብዙዎች በዛ። and the gift by grace, which is by one man, Jesus Christ, hath abounded unto many.

የሚያሞት አንድ አምላክ ከሞተ ፍጥረትን ማን ሊቆጣጠራት ነው? እርሱስ ሲሞት ማን ሊያሞተው ነው? ፈጣሪ በፍጥረቱ ተገደለ ማለትስ ስሜት ይሰጣልን? የሚያሞት እና ሕያው የሚያደርግ አሏህ ከሚሉት ነገር ጥራት ይገባው! ኢየሱስ ሟች ከሆነ አንዱ አምላክ የማይሞት ከሆነ የሚሞተው ኢየሱስ የማይሞተውን አንዱን አምላክ በምን ዓይነት መልኩ እንዴት አድርጎ ሊሆን ይችላል? ከአንዱ በቀር ማንም አምላክ የለም፥ ይህ አንዱ አምላክ አይሞትም፦
1ኛ ቆሮንቶስ 8፥4 ከአንዱም በቀር ማንም አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።
ዕንባቆም 1፥12 የተቀደስህ አምላኬ ያህዌህ ሆይ! አንተ ከዘላለም ጀምሮ አልነበርህምን? አንተ አትሞትም"። הֲלֹ֧וא אַתָּ֣ה מִקֶּ֗דֶם יְהוָ֧ה אֱלֹהַ֛י קְדֹשִׁ֖י לֹ֣א נָמ֑וּת

"አታህ" אַתָּ֣ה ማለት "አንተ" ማለት ሲሆን "ሎ ናሙት" לֹ֣א נָמ֑וּת ማለት "አትሞትም"not die" ማለት ነው፥ "አትሞትም"you will not die" በሚል ብዙ መተርጉማን አስቀምጠዋል፦
1.Christian Standard Bible
Are you not from eternity, LORD my God? My Holy One, you will not die.

2. New International Version
LORD, are you not from everlasting? My God, my Holy One, you will never die.

3. Holman Christian Standard Bible
Are You not from eternity, Yahweh my God? My Holy One, You will not die.

4. NET Bible
LORD, you have been active from ancient times; my sovereign God, you are immortal.

5. New Revised Standard Version
Are you not from of old, O LORD my God, my Holy One? You shall not die.

በተቃራኒው "እኛ አንሞትም"We shall not die" በማለት ያስቀመጡ መተርጉማን ቢኖሩም ሰው ሆኖ የማይሞት እንደሌለ ከሚታወቀው ሥነ ኑባሬአዊ እውነታ ጋር ይጣረሳል። የማይሞት አንድ አምላክ አለ፥ በአንድ አምላክ እና በሰዎች መካከል መልእክት የሚያስተላልፍ መካከለኛ ሟች ሰው አለ፦
1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥5 አንድ አምላክ አለና፥ በአምላክ እና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። εἷς γὰρ Θεός, εἷς καὶ μεσίτης Θεοῦ καὶ ἀνθρώπων, ἄνθρωπος Χριστὸς Ἰησοῦς,

መሢሑ የማይሞት ሕያው አምላክ ሳይሆን የማይሞት ሕያው አምላክ ከሞት የሚያስነሳው ሟች ፍጡር ነው። ዮስጦስ ሰማዕቱ አምላክ ብቻ ያልተወለደ እና የማይሞት እንዲሁ ከእርሱ በኋላ ያሉት ነገሮች ሁሉ የተፈጠሩ እና የሚሞቱ መሆናቸውን ተናግሯል፦
"አምላክ ብቻ ያልተወለደ እና የማይሞት ነውና፥ ስለዚህም እርሱ አምላክ ነው። ነገር ግን ከእርሱ በኋላ ያሉት ነገሮች ሁሉ የተፈጠሩ እና የሚሞቱ ናቸው"።
Dialogue with Trypho (Justin Martyr) > Chapter 5

ክርስቲያኖች ሆይ! የሚሞት ፍጡር ማምለክ ትታችሁ የማይሞተውን ሕያው አምላክ እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። በሕያውነቱ ሞት የሌለበት አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የማይመገብ አምላክ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

6፥14 «ሰማያትን እና ምድርን ፈጣሪ ከኾነው አሏህ እርሱ የሚመግብ እና የማይመገብ ሲኾን ሌላን አምላክ እይዛለሁን?» በላቸው፡፡ قُلْ أَغَيْرَ اللَّهِ أَتَّخِذُ وَلِيًّا فَاطِرِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَهُوَ يُطْعِمُ وَلَا يُطْعَمُ

አምላካችን አሏህ ጂንን እና ሰውን የፈጠረበት ዓላማ እርሱን በብቸኝነት እንዲያመልኩት ነው፦
51፥56 ጂንን እና ሰውን ሊያመልኩኝ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

አሏህ ከፈጠራቸው ከጂን ሆነ ከሰው ምንም ሲሳይ አይፈልግም፥ ሊመግቡትን አይሻም። በእርሱ መጋቢነት መመገብ የሚባል ባሕርይ የለውም፦
51፥57 ከእነርሱም ምንም ሲሳይ አልፈልግም፡፡ ሊመግቡኝም አልሻም፡፡ مَا أُرِيدُ مِنْهُم مِّن رِّزْقٍ وَمَا أُرِيدُ أَن يُطْعِمُونِ
6፥14 «ሰማያትን እና ምድርን ፈጣሪ ከኾነው አሏህ እርሱ የሚመግብ እና የማይመገብ ሲኾን ሌላን አምላክ እይዛለሁን?» በላቸው፡፡ قُلْ أَغَيْرَ اللَّهِ أَتَّخِذُ وَلِيًّا فَاطِرِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَهُوَ يُطْعِمُ وَلَا يُطْعَمُ

"አሏህ እርሱ የሚመግብ እና የማይመገብ ሲኾን" የሚለው ይሰመርበት! ከአሏህ በተቃራኒው መሢሑ ኢየሱስ የእርሱ መልእክተኛ ሲሆን የተገኘባት እናቱ መርየም ደግሞ ጻዲቅ ሴት ናት፦
5፥75 የመርየም ልጅ አል መሢሕ ከበፊቱ መልእክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልእክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ እናቱም በጣም እውነተኛ ናት፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ وَأُمُّهُ صِدِّيقَةٌ

መርየም ሆነ ልጇ መሢሑ ሁለቱም ምግብን የሚመገቡ ነበሩ፦
5፥75 ሁለቱም ምግብን የሚመገቡ ነበሩ፥ አንቀጾችን ለእነርሱ (ለከሓዲዎች) እንዴት እንደምናብራራ ተመልከት! ከዚያም ከእውነት እንዴት እንደሚመለሱ ተመልከት፡፡ كَانَا يَأْكُلَانِ الطَّعَامَ ۗ انظُرْ كَيْفَ نُبَيِّنُ لَهُمُ الْآيَاتِ ثُمَّ انظُرْ أَنَّىٰ يُؤْفَكُونَ

መሢሑ ምግብ የሚመገብ ከሆነ የመሢሑ ፈጣሪ አሏህ ምግብ የማይመገብ ከሆነ የሚመገብ ፍጡር መሢሑ የማይመገበውን አንዱን አምላክ አሏህን በምን ዓይነት መልኩ እንዴት አድርጎ ሊሆን ይችላል?
በባይብልም ቢሆን ፍጥረትን የሚመግብ አንዱ አምላክ የሚበላ እና የሚጠጣ ምንነት በፍጹም አይደለም፦
መዝሙር 50፥13 የፍሪዳውን ሥጋ እበላለሁን? የፍየሉንስ ደም እጠጣለሁን?

የፍሪዳውን ሥጋ እበላለሁን? የፍየሉንስ ደም እጠጣለሁን? የሚለው መጠይቅ ምጸት "አልበላም አልጠጣም" የሚል መልእክት አለው። ይህ የማይበላ እና የማይጠጣ አንድ አምላክ ከሚበላ እና ከሚጠጣ ሰው በሰዋስው ተነጥሎ ተቀምጧል፦
ዮሐንስ 13፥31 ከወጣም በኋላ ኢየሱስ እንዲ አለ፦ “አሁን የሰው ልጅ ከበረ አምላክም ሰለ እርሱ ከበረ። Ὅτε οὖν ἐξῆλθεν, λέγει Ἰησοῦς Νῦν ἐδοξάσθη ὁ Υἱὸς τοῦ ἀνθρώπου, καὶ ὁ Θεὸς ἐδοξάσθη ἐν αὐτῷ·

"የሰው ልጅ" እና "አምላክ" ሁለት የተለያዩ ምንነት እና ማንነት ስለ ሆኑ አምላክ አክባሪ ባለቤት የሰው ልጅ ኢየሱስ ተከባሪ ተሳቢ ነው፦
ዮሐንስ 13፥32 አምላክ ስለ እርሱ የከበረ ከሆነ፥ አምላክ ደግሞ እርሱን ራሱን ያከብረዋል። ወዲያውም ያከብረዋል። εἰ ὁ Θεὸς ἐδοξάσθη ἐν αὐτῷ, καὶ ὁ Θεὸς δοξάσει αὐτὸν ἐν αὑτῷ, καὶ εὐθὺς δοξάσει αὐτόν.

"የሰው ልጅ" በሚል ቃል ውስጥ "ሰው" የተባለችው ድንግል ማርያም ስትሆን የእርሷ ልጅ ፍጡር ስለሆነ የመራብ እና የመጠማት እንዲሁ የመብላት እና የመጠጣት ባሕርይ አለው፥ ኢየሱስ ምግብ እየበላ እና መጠጥ እየጠጣ የመጣ ነው፦
ማቴዎስ 11፥19 "የሰው ልጅ” እየበላ እና እየጠጣ መጣ።

የመብላት እና የመጠጣት ባሕርይ ያለው ሰው የመጸዳዳት እና የመሽናት ባሕርይ አለው፥ ወደ አፉ የበላውን እና የጠጣውን ደግሞ በሌላ መልኩ ከሰውነት ያስወግዳል፦
ማቴዎስ 15፥17 ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ ወደ ሆድ አልፎ ወደ እዳሪ እንዲጣል አትመለከቱምን?

ኢየሱስ መጸዳጃ ቤት ሲጸዳዳ ሰው መጥቶ ቢያንኳኳበት "ሰው አለ" እንጂ "አምላክ አለ" ወይም "ሰውም አምላክ" አለ አይልም። እንግዲህ መሢሑ የማይመገብ አምላክ ሳይሆን በፈጣሪ ሲሳይ ተመጋቢ ፍጡር ነው። ክርስቲያኖች ሆይ! እንደ እናንተ የሚመገብ ፍጡር ማምለክ ትታችሁ የማይመገበውን መጋቢ አምላክ እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። በመጋቢነት ላይ ተመጋቢነት የሌለበት አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የገደለ ይገደል!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

42፥40 የመጥፎም ነገር ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ናት፡፡ وَجَزَاءُ سَيِّئَةٍ سَيِّئَةٌ مِّثْلُهَا

“ዘንብ” ذَنب ማለት “ኃጢአት” ማለት ነው፥ በሥነ ኃጢአት ጥናት”hamartiology” ውስጥ "ኃጢአት” ማለት "አሏህ ያዘዘውን መልካም ነገር አለማድረግ፥ የከለከለውን ክፉ ነገር ማድረግ" ማለት ነው። ኃጢአት “ከባኢሩ አዝ ዘንብ” كَبَائِر الْذَنب እና “ሶጋኢሩ አዝ ዘንብ” صَغَائِر الْذَنب ተብለው ለሁለት ይከፈላሉ፥ “ከባኢር” كَبَائِر ማለት “ዐብይ” “ታላቅ” ማለት ሲሆን “ሶጋኢር” صَغَائِر ማለት ደግሞ “ንዑስ” “ትንሽ” ማለት ነው። ከዐበይት ኃጢአቶች መካከል አንዱ ነፍስን ያለ ሕግ መግደል ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 83, ሐዲስ 53
ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምሪው እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ ”ዐበይት ኃጢአቶች በአሏህ ላይ ማሻረክ፣ ወላጆችን አለማክበር፣ ነፍስን መግደል እና የውሸት መሓላ ናቸው”። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الْكَبَائِرُ الإِشْرَاكُ بِاللَّهِ، وَعُقُوقُ الْوَالِدَيْنِ، وَقَتْلُ النَّفْسِ، وَالْيَمِينُ الْغَمُوسُ ‏”‌‏.‏

"ቀትሉ አን-ነፍሥ" قَتْلُ النَّفْس የሚለው ቃል ይሰመርበት! አምላካችን አሏህ ነፍስን መግደል ሐራም አርጓል፦
17፥33 ”ያቺንም አላህ እርም ያረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ”፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ

“እርም ያረጋት” ለሚለው የገባው ቃል “ሐረመ” حَرَّمَ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። “ሐራም” حَرَام የሚለው ቃል እራሱ “ሐረመ” حَرَّمَ ማለትም “ከለከለ” ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “የተከለከለ” ማለት ነው። እንደውም ያለጥፋት አንድን ሰው መግደል ሰዎችን ሁሉ እንደገደለ ነው፦
5፥32 ”በዚህ ምክንያት በእስራኤል ልጆች ላይ እነሆ ያለ ነፍስ መግደል ወይም በምድር ላይ ያለማጥፋት ካልሆነ በስተቀር ነፍስን የገደለ ሰው ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው፥ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው” ማለትን ጻፍን፡፡ مِنْ أَجْلِ ذَٰلِكَ كَتَبْنَا عَلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنَّهُ مَن قَتَلَ نَفْسًا بِغَيْرِ نَفْسٍ أَوْ فَسَادٍ فِي الْأَرْضِ فَكَأَنَّمَا قَتَلَ النَّاسَ جَمِيعًا وَمَنْ أَحْيَاهَا فَكَأَنَّمَا أَحْيَا النَّاسَ جَمِيعًا

አንድን ነፍስ ያለ ሕግ መግደል እርሱ አግብቶ ቤተሰብ፣ ነገድ፣ ጎሳ፣ አገር እያለ ሕዝብ የሚሆንበትን የተፈጥሮ ዐላማና ዒላማ መቅጨት ስለሆነ ነፍስ ያለ ሕግ የገደለ ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው። ቅሉ ግን ወሰን አልፈው የሚገሉትን ሰዎች መግደል ቂሷስ ነው፥ "ቂሷስ" قِصَاص የሚለው ቃል "ቋሶ" قَاصَّ ማለትም "አመሳሰለ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ማመሳሰል" ማለት ነው፦
2፥179 ባለ አእምሮዎች ሆይ! ለእናንተም በማመሳሰል ሕግ ውስጥ ሕይወት አለላችሁ፡፡ ትጠነቀቁ ዘንድ ገዳይን መግደል ተደነገገላችሁ፡፡ وَلَكُمْ فِي الْقِصَاصِ حَيَاةٌ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ማመሳሰል" ለሚለው ቃል የገባው "ቂሷስ" قِصَاص መሆኑ ልብ አድርግ! ሰው ጤናማ ሕይወት ይኖር ዘንድ አምላካችን አሏህ ቂሷስን ደንግጓል፥ በቂሷስ ነፍስ ያጠፋ ነፍሱ ይጠፋል። "ያለ ሕግ አትግደሉ" ሲል በሕግ መሠረት የገደለ ይገደላል፥ መጥፎ ለሠሩ ሠዎች መጥፎ ቅጣት መቅጣት ቂሷስ ነው። የአሏህ መጽሐፍ ጭብጡ ቂሷስ ነው፦
42፥40 የመጥፎም ነገር ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ናት፡፡ وَجَزَاءُ سَيِّئَةٍ سَيِّئَةٌ مِّثْلُهَا
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 26
አነሥ እንደተረከው፦ “ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የአሏህ መጽሐፍ ቂሷስ ነው"። أَنَّ أَنَسًا، حَدَّثَهُمْ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ كِتَابُ اللَّهِ الْقِصَاصُ ‏”‌‏.‏

በባይብልስ? ነቁ እና በቁ የተባሉ መምህራን "መጽሐፋችን ይቅርባይነት እንጂ ግደሉ አይልም" እያሉ ይቀጥፋሉ። እኛም እንደ ፍጥርጥራቸው እና እንደ ፍጥምጥማቸው ሳንል በባይብል የገደለ እንደሚገደል እንሞግታለን፦
ዘሌዋውያን 24፥17 ሰውንም እስኪሞት ድረስ የሚመታ ፈጽሞ ይገደል።

"ይህ ብሉይ ኪዳን ላይ ነው" ብለው ማንቃረሩን ሲያያዙት ቀፍድደን ወደ አዲስ ኪዳን በማምጣት ኢየሱስ ሲመጣ ደግሞ ሕጉ ጠብቆ እና አጥብቆ የሞት ፍርድ የሚገባው የገደለ ብቻ ሳይሆን በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ የሞት ፍርድ እንደሚገባው አበክሮ እና አዘክሮ መናገሩን እናስረዳለን፦
ማቴዎስ 5፥21-22 ለቀደሙት፦ አትግደል እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል።

"የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል" ማለት በዘሌዋውያን 24፥17 "ፈጽሞ ይገደል" የሚለው ከሆነ "በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል" ሲል "ፍርድ ይገባዋል" ማለት "ፈጽሞ ይገደላል" ማለት ነው። አጥር እና ቅጥር በማድረግ "ብሉይ ኪዳን ላይ ነው" ለሚሉን ኢየሱስ እንቅጩን ፍርጥ አርጎ፦ "በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል" ማለቱን እናረዳቸዋለን፦
ራእይ 13፥10 "በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል"።

"በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ራሱ በሰይፍ እንዲገደል ይገባዋል" የሚለው መልእክት በዮሐንስ፣ በመልአኩ፣ በኢየሱስ ከአምላክ የመጣ መልእክት ነው። ራእይ 1፥1 ተመልከት! በአዲስ ኪዳን ባለ ሥልጣኖች በአምላክ የተሾሙ እና በመልካም ነገር ለሕዝብ የቆሙ የአምላክ አገልጋዮች ናቸው፥ ሰይፍ የሚታጠቁት አምባሻ ሊቆርጡበት ሳይሆን ሕገ ወጥን አንገቱን እንዲቀሉበት ነው፦
ሮሜ 13፥1 ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በአምላክ የተሾሙ ናቸው።
ሮሜ 13፥4 ለመልካም ነገር ለአንተ የአምላክ አገልጋይ ነውና። በከንቱ ግን ሰይፍ አይታጠቅምና ክፉ ብታደርግ ፍራ፤ ቍጣውን ለማሳየት ክፉ አድራጊውን የሚበቀል የአምላክ አገልጋይ ነውና።

የምን ከዘፋኙ በላይ መወዛወዝ ነው? ባለ ሥልጣኖች ክፉ አድራጊውን የሚበቀሉ የአምላክ አገልጋዮች ከሆኑ እንግዲያውስ የገደለውን በታጠቀው ሰይፍ መቅጣት አዲስ ኪዳናዊ ትምህርት መሆኑን ስናራውጣቸው እና ስናቆራጥጣቸው መግቢያቸው ምን ይሆን? አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
Video
ስቅለተ ዐርብ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥157 ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም፡፡ مَا لَهُم بِهِ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا اتِّبَاعَ الظَّنِّ ۚ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًا

ክርቲያኖች እራሳቸውን የሚያስጠጉበት ጳውሎስ ኢየሱስ በተቀበረ "በሦስተኛው ቀን ተነሣ" ይለናል፦
1ኛ ቆሮንቶስ 15፥3 መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥ that he was buried and that he was raised on the third day according to the Scriptures.

ሦስቱ ቀን የሚጀምረው ከተቀበረበት ከሆነ በምድር ልብ ማለትም በመቃብር ውስጥ ሦስት ቀን እና ሦስት ሌሊት እንደሚሆን ይናገራል፦
ማቴዎስ ወንጌል 12፥40 ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፥ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።

ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በመቃብር ያለውን ጊዜ የሚሸፍን መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያሳያል። ያ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ወደ መቃብር የገባው ደግሞ በምሽት ነው፦
ማርቆስ 15፥42-46 አሁንም "በመሸ ጊዜ" የሰንበት ዋዜማ የሆነ የማዘጋጀት ቀን ስለ ነበረ።

"በመሸ ጊዜ" የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! አይሁድ የሚያከብሩት በዓል ከ 12 ሰዓት በኃላ የነገው ነው፥ ያ በዓል የሚጀመረውም ሌሊቱ ከምሽቱ 12 ነው። ምሽት የሌሊት መጀመሪያ ነው፦
ዘጸአት 12፥18 በመጀመሪያውም ወር በአሥራ አራተኛው ቀን "በመሸ ጊዜ" ከወሩም እስከ ሀያ አንድ ቀን በመሸ ጊዜ የቂጣ እንጀራ ትበላላችሁ።
ማቴዎስ 26፥20 "በመሸም ጊዜ" ከአሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርቱ ጋር በማዕድ ተቀመጠ።
ማርቆስ 1፥32 "ፀሐይም ገብቶ በመሸ ጊዜ"፥ የታመሙትንና አጋንንት ያደረባቸውን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤

"ፀሐይም ገብቶ በመሸ ጊዜ" የሚለው ይሰመርበት! ምሽት ማለት የፀሐይ መግባት ነው። እንግዲህ ከዚህ ከሰንበት ማለት ከቅዳሜ ዋዜማ ምሽቱ የቅዳሜ ከሆነ ከዚያ ጀምራችሁ ቁጠሩት! ሰኞ ማታ ለማክሰኞ ዋዜማ ላይ ይመጣል፥ ያ ማለት ሥስት ቀን እና ሦስት ሌሊት አይሞላም። አንድ የቅዳሜ ሌሊት እና አንድ የእሑድ ሌሊት ሲሆን ሁለት ሌሊት ይሆናል፥ አንድ የቅዳሜ መዓልት(ቀን) ብቻ ይተርፋል። በጥቅሉ ሁለት ሌሊት እና አንድ መዓልት እንጂ ሦስት ሌሊት እና ሦስት መዓልት አይሞላም፦
ዮሐንስ 20፥1 ከሳምንቱም በፊተኛው ቀን መግደላዊት ማርያም ገና ጨለማ ሳለ ማለዳ ወደ መቃብር መጣች ድንጋዩም ከመቃብሩ ተፈንቅሎ አየች።

በአይሁድ የሳምንቱም ፊተኛው ቀን እሑድ ሲሆን እሑድ እጅግ በማለዳ ፀሐይ ሳትወጣ ጨለማ ሳለ ከመቃብር ተነሳ ካለ ሦስት ሌሊት እና ሦስት መዓልት አይሞላም። ይህ የገባው የፕሮቴስታንት መምህር ሀብታሙ ታደሰ "ኢየሱስ የሞተው ረቡዕ ነው" በማለት ከእሑድ ወደ ኃላ በመቁጠር ሦስት ሌሊት እና ሦስት መዓልት የሚለውን ለማስታረቅ ሞክሯል። ቅሉ እና ጥቅሉ ግን ቤተክርስቲያን ሆነች የቤተክርስቲያን አበው "ረቡዕ" የሚለውን ሳይሆን "ዓርብ" የሚለውን ስላስቀመጡ ስቅለት የሚባል በዓል በዓመት አንድ ጊዜ ዓርብ ቀን ያከብራሉ፦
ዲድስቅልያ 30፥25 ዓርብ ቀን ሰቀሉት፥ ተሰቅሎ በሞተ በሦስተኛው ቀን ተነሣ።

ዲድስቅልያ"didache" የጥንት ጽሑፍ ነው። እሩቅ ሳንሄድ የ 1980 አዲስ ትርጉም ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ እና ፕሮቴስታንት የተሳተፉበት የትርጉም ሥራ ሲሆን የሸንጎ አማካሪ የሆነ ዮሴፍ በዓለት በተዋቀረ መቃብር የቀበረው ዓርብ ማታ እንደሆነ ተጽፏል፦
ሉቃስ 23፥54 ይህንንም ያደረገው "ዓርብ" ማታ ለሰንበት ዝግጅት በሚደረግበት ጊዜ ነው።

የ 1993 አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሉቃስ 23፥54 ጥቅስን በሚያብራራበት የግርጌ ማብራሪያ ላይ "የመዘጋጀት ቀን ለሰንበት ቀን የሚያስፈልግ ማንኛውም ነገር የሚሰናዳበት ቀን ሲሆን ቀኑም ዓርብ ነው" በማለት እንቅጩን አስቀምጧል። ከመነሻው ሰንበት ቅዳሜ ከሆነ የሰንበት ዋዜማ ዐርብ ነው፦
ማርቆስ 15፥42 አሁንም በመሸ ጊዜ የሰንበት ዋዜማ የሆነ የማዘጋጀት ቀን ስለ ነበረ፥ የከበረ አማካሪ የሆነ የአርማትያስ ዮሴፍ መጣ።

"የሰንበት ዋዜማ" የሚለው ይሰመርበት! የማርቆስ 15፥42 የትርጓሜ መጽሐፍ አንድምታው፦ "ዓርብ ሲመሽ ያን ጊዜም የሰንበት መግቢያ ነበር" በማለት ፍርጥ አርጎ አስቀምጦታል። ገና ለገና ከሙሥሊም ሙግት ለማምለጥ ታሪክን እና ትውፊትን ጥሶ እና በርጥሶ "የተሰቀለው ረቡዕ ነው" ብሎ መጨነቅ እና መጨናነቅ ለምን አስፈለገ? ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በኢየሱስ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም፦
4፥157 ጥርጣሬን ከመከተል በስተቀር በእርሱ ነገር ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ በእርግጥም አልገደሉትም፡፡ مَا لَهُم بِهِ مِنْ عِلْمٍ إِلَّا اتِّبَاعَ الظَّنِّ ۚ وَمَا قَتَلُوهُ يَقِينًا

አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሞናርኪያውያን

ክፍል አንድ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

28፥53 በእነርሱ ላይ በሚነበብላቸውም ጊዜ «በእርሱ አምነናል፡፡ እርሱ ከጌታችን የኾነ እውነት ነው፡፡ "እኛ ከእርሱ በፊት ሙሥሊሞች ነበርን» ይላሉ፡፡ وَإِذَا يُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ قَالُوا آمَنَّا بِهِ إِنَّهُ الْحَقُّ مِن رَّبِّنَا إِنَّا كُنَّا مِن قَبْلِهِ مُسْلِمِينَ

"ሞናርኪያ" የሚለው ቃል "ሞናርኺያ" μοναρχίᾱ ከሚል ግሪክ ኮይኔ ቃል የመጣ ነው፥ "ሞናርኺያ" μοναρχίᾱ የሚለው ቃል "ሞኖስ" μόνος እና "አርኾስ" ἀρχός ከሚል ሁለት ቃላት ውቅር ነው። "ሞኖስ" μόνος ማለት "ብቻ" ማለት ሲሆን "አርኾስ" ἀρχός ማለት ደግሞ "ገዥ" ማለት ነው፥ በጥቅሉ "ሞናርኺያ" μοναρχίᾱ ማለት "ብቸኛ ገዥነት" ማለት ነው። "አንድ አምላክ አብ ብቻ ነው" የሚል አቋም ያላቸው የጥንት አሐዳውያን "ሞናርኪያውያን" ሲባሉ "የኢየሱስ አምላክ አንዱ አምላክ ነው" የሚል ይህ አቋም የኢየሱስም አቋም ነው፦
ዮሐንስ 17፥3 እውነተኛ አምላክ ብቻህን የሆንህ አንተን እና የላክኸውን ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት። αὕτη δέ ἐστιν ἡ αἰώνιος ζωή, ἵνα γινώσκωσιν σὲ τὸν μόνον ἀληθινὸν θεὸν καὶ ὃν ἀπέστειλας Ἰησοῦν Χριστόν.

"ሴ ቶን ሞኖን አሌቲኖን ቴዎን" σὲ τὸν μόνον ἀληθινὸν θεὸν ማለት "እውነተኛ አምላክ ብቻህን የሆንህ አንተን" ማለት ነው፥ ለዚያ ነው የኦርቶዶክስ፣ የካቶሊክ እና የፕሮቴስታንት ሊቃውንት የተሳተፉበት የ 1980 አዲስ ትርጉም፦ "ብቻህን እውነተኛ አምላክ የሆንከው አንተን" ብሎ በቅጡ ያስቀመጠው። "ሞኖን" μόνον" ማለት "ብቻ" ማለት ሲሆን ይህም ቅጽል እየገለጸ ያለው ከፊቱ "ሴ" σὲ ማለትም "አንተ" የተባለውን ማንነት ነው፥ ይህም ማንነት አብ ሲሆን አብ ብቻውን እውነተኛ አምላክ ነው።

"ሞኖቴይዝም"monotheism" የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል እራሱ "ሞኖስ" μόνος እና "ቴዎስ" θεός ከሚሉ ሁለት ቃላት የተዋቀረ ነው፥ "ሞኖስ" μόνος ማለት "ብቸኛ" ማለት ሲሆን "ቴዎስ" θεός ደግሞ "አምላክ" ማለት ነው። በጥቅሉ "ሞኖ ቴዎስ" μόνο θεός ማለት "አንድ ብቸኛ አምላክ" ማለት ሲሆን ይህም አንድ አምላክ ኢየሱስን የላከ ነው። ጳውሎስም ብዙ ቦታ አብን ብቸኛ አምላክ አርጎ ያስቀምጣል፦
ሮሜ 16፥27 "ብቻውን" ጥበብ ላለው "ለ-"አምላክ" "በ-"ኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን! አሜን። μόνῳ σοφῷ Θεῷ, διὰ Ἰησοῦ Χριστοῦ, ᾧ ἡ δόξα εἰς τοὺς αἰῶνας τῶν αἰώνων· ἀμήν.
1 ጢሞቴዎስ 1፥17 "ብቻውን" አምላክ ለሚሆን ለማይሞተው፣ ለማይታየው፣ ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን። Τῷ δὲ Βασιλεῖ τῶν αἰώνων, ἀφθάρτῳ ἀοράτῳ μόνῳ Θεῷ, τιμὴ καὶ δόξα εἰς τοὺς αἰῶνας τῶν αἰώνων· ἀμήν.
1 ጢሞቴዎስ 6፥16 እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን። ὁ μόνος ἔχων ἀθανασίαν, φῶς οἰκῶν ἀπρόσιτον, ὃν εἶδεν οὐδεὶς ἀνθρώπων οὐδὲ ἰδεῖν δύναται· ᾧ τιμὴ καὶ κράτος αἰώνιον· ἀμήν.
1 ጢሞቴዎስ 6፥15 ያንም መገለጡን በራሱ ጊዜ ብፁዕና "ብቻውን የሆነ ገዥ" የነገሥታት ንጉሥ እና የጌቶች ጌታ ያሳያል። ἣν καιροῖς ἰδίοις δείξει ὁ μακάριος καὶ μόνος Δυνάστης, ὁ Βασιλεὺς τῶν βασιλευόντων καὶ Κύριος τῶν κυριευόντων,

1 ጢሞቴዎስ 6፥16 ላይ "እርሱ" የሚለው ተውላጠ ስም 1 ጢሞቴዎስ 6፥15 ላይ "ብቻውን የሆነ ገዥ" የተባለውን ማንነት ተክቶ የመጣ ነው፥ ስለዚህ "እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም" የተባለው አብ ሲሆን ይህም "ብቻውን የሆነ ገዥ" ነው። ብቻውን ለሆነ አምላክ ክብር፣ ግርማ፣ ኃይል እና ሥልጣን በኢየሱስ አማካኝነት ይቀርብለታል፦
ይሁዳ 1፥25 "ብቻውን "ለ-ሆነ አምላክ እና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን "በ-"ኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን። μόνῳ Θεῷ Σωτῆρι ἡμῶν διὰ Ἰησοῦ Χριστοῦ τοῦ Κυρίου ἡμῶν δόξα μεγαλωσύνη κράτος καὶ ἐξουσία πρὸ παντὸς τοῦ αἰῶνος καὶ νῦν καὶ εἰς πάντας τοὺς αἰῶνας· ἀμήν.
አምላካችን አሏህ በዒሣ ቀዳማይ ተከታዮች ልቦች ውሰጥ መለዘብን እና እዝነትን አድርጎ ሳለ የአሏህን ውዴታ ለመፈለግ ምንኩስና ፈጠሩ፥ ነገር ግን አዲስ የፈጠሩዋትንም ምንኩስናን በእነርሱ ላይ አልደነገገም። ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ሲሆኑ ጥቂት አሓዳውያን በቁርኣን ላመኑት ምንዳቸውን ሰጣቸው፦
57፥27 ከእነርሱም ለእነዚያ ላመኑት ምንዳቸውን ሰጠናቸው፥ ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፡፡ فَـَٔاتَيْنَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مِنْهُمْ أَجْرَهُمْ ۖ وَكَثِيرٌۭ مِّنْهُمْ فَٰسِقُونَ

እነዛ ጥቂት አሓዳውያን ቁርኣን በወረደበት ጊዛ በቁርኣን አምነዋል፥ ቁርኣን በእነርሱ ላይ በሚነበብላቸውም ጊዜ «በቁርኣን አምነናል፡፡ ቁርኣን ከጌታችን የኾነ እውነት ነው፡፡ "እኛ ከቁርኣን በፊት ሙሥሊሞች ነበርን» ይላሉ፦
28፥52 እነዚያ ከእርሱ በፊት መጽሐፍን የሰጠናቸው እነርሱ "በእርሱ ያምናሉ"፡፡ الَّذِينَ آتَيْنَاهُمُ الْكِتَابَ مِن قَبْلِهِ هُم بِهِ يُؤْمِنُونَ
28፥53 በእነርሱ ላይ በሚነበብላቸውም ጊዜ «በእርሱ አምነናል፡፡ እርሱ ከጌታችን የኾነ እውነት ነው፡፡ "እኛ ከእርሱ በፊት ሙሥሊሞች ነበርን» ይላሉ፡፡ وَإِذَا يُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ قَالُوا آمَنَّا بِهِ إِنَّهُ الْحَقُّ مِن رَّبِّنَا إِنَّا كُنَّا مِن قَبْلِهِ مُسْلِمِينَ

"እኛ ከእርሱ በፊት ሙሥሊሞች ነበርን" የሚለው ይሰመርበት! "ሙሥሊም” مُسْلِم ማለት "አንዱን አምላክ በብቸኝነት አምላኪ፣ ተገዢ፣ ታዛዥ" ማለት ነው፥ እዚህ አንቀጽ ላይ "ሙሥሊሞች" ለሚል የገባው ቃል "ሙሥሊሚን" مُسْلِمِين ሲሆን "ሙሥሊም" مُسْلِم ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው። ወደ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" የመጣው ወሕይ ጭብጡ እና አንኳር መልእክቱ "አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው" የሚል ነው፦
6፥19 «እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ እኔም ከምታጋሩት ነገር ንጹሕ ነኝ» በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ وَإِنَّنِى بَرِىٓءٌۭ مِّمَّا تُشْرِكُونَ
21፤108 «ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ "አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው" ማለት ነው፥ ታዲያ እናንተ ፍጹም “ታዛዦች” ናችሁን?» በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ታዛዦች” ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ሙሥሊሚን" مُسْلِمِين እንደሆነ ልብ አድርግ! "አንድ" ለሚለው ቃል የገባው ቃል “ዋሒድ” وَٰحِد ነው፥ "አሏህ አንድ ነው" ብሎ የሚያምን አማኝ “ሙዋሒድ” مُوَٰحِد ሲባል የአንድ አምላክ አስተምህሮቱ ደግሞ "ተውሒድ" تَوْحِيد ይባላል። ከእነርሱም ብዙዎቹ ከቀጥተኛው መንገድ ከተውሒድ ወጥተው በሥላሴ በማመን የተሳሳቱ ናቸው፥ ቅሉ ግን ጥቂት ያልተሳሳቱ የኢየሱስ ተከታዮች ነበሩ፦
1፥7 የእነዚያን በእነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን፥ በእነርሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውን እና ያልተሳሳቱትን ሰዎች መንገድ ምራን" በሉ፡፡ صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا الضَّالِّينَ
ጃምዒ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47 ሐዲስ 3212
ዐዲይ ኢብኑ ሓቲም እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ "አይሁዳውያን የተቆጣባቸው ናቸው፥ ክርስቲያኖች የተሳቱተት ናቸው"። عَنْ عَدِيِّ بْنِ حَاتِمٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الْيَهُودُ مَغْضُوبٌ عَلَيْهِمْ وَالنَّصَارَى ضُلاَّلٌ ‏”‏ ‏.‏

ከክርስቲያኖች ጥቂት ያልተሳሳቱ ሙዋሒዲን የሄዱበትን መንገድ "ምራን" ብለን እንቀራለን። ታዲያ ሞናርኪያውያን በታሪክ ውስጥ ምን ሆኑ? አሁን ላይ የት አሉ? ኢንሻላህ ይቀጥላል.....

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
قَالَ إِنِّي عَبْدُ اللَّهِ آتَانِيَ الْكِتَابَ وَجَعَلَنِي نَبِيًّا
وَجَعَلَنِي مُبَارَكًا أَيْنَ مَا كُنتُ وَأَوْصَانِي بِالصَّلَاةِ وَالزَّكَاةِ مَا دُمْتُ حَيًّا
وَبَرًّا بِوَالِدَتِي وَلَمْ يَجْعَلْنِي جَبَّارًا شَقِيًّا
وَالسَّلَامُ عَلَيَّ يَوْمَ وُلِدتُّ وَيَوْمَ أَمُوتُ وَيَوْمَ أُبْعَثُ حَيًّا
ሞናርኪያውያን

ክፍል ሁለት

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥14 ከእነዚያም "እኛ ነሷራ ነን" ካሉት የጠበቀ ቃል ኪዳናቸውን ያዝን፡፡ በእርሱም ከታዘዙበት ነገር ፈንታን ተውት፡፡ وَمِنَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّا نَصَارَىٰ أَخَذْنَا مِيثَاقَهُمْ فَنَسُوا حَظًّا مِّمَّا ذُكِّرُوا بِهِ فَأَغْرَيْنَا

የኢየሱስ ቀዳማይ ተከታዮች ሐዋርያት ሙሥሊሞች ነበሩ፦
3፥52 ዒሣ ከእነርሱ ክህደት በተሰማውም ጊዜ፡- «ወደ አሏህ ረዳቶቼ እነማን ናቸው?» አለ፥ ሐዋርያትም፡- «እኛ የአሏህ ረዳቶች ነን፤ በአሏህ አምነናል፥ እኛም ትክክለኛ ታዛዦች መኾናችንን መስክር» አሉ፡፡ فَلَمَّآ أَحَسَّ عِيسَىٰ مِنْهُمُ ٱلْكُفْرَ قَالَ مَنْ أَنصَارِىٓ إِلَى ٱللَّهِ ۖ قَالَ ٱلْحَوَارِيُّونَ نَحْنُ أَنصَارُ ٱللَّهِ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَٱشْهَدْ بِأَنَّا مُسْلِمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዛዦች" ለሚል የገባው ቃል "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون ሲሆን "ሙሥሊም" مُسْلِم ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ "ነሲር" نَصِير ማለት "ረዳት" ማለት ሲሆን የነሲር ብዙ ቁጥር ደግሞ "አንሷር" أَنصَار ነው። "ነስራኒይ" نَصْرَانِيّ ገላጭ ቅጽል ሲሆን "ረዳት" ማለት ነው፥ የነስራኒይ ብዙ ቁጥር "ነሷራ" نَصَارَىٰ ሲሆን "ረዳቶች" ማለት ነው፦
5፥14 ከእነዚያም "እኛ ነሷራ ነን" ካሉት የጠበቀ ቃል ኪዳናቸውን ያዝን፡፡ በእርሱም ከታዘዙበት ነገር ፈንታን ተውት፡፡ وَمِنَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّا نَصَارَىٰ أَخَذْنَا مِيثَاقَهُمْ فَنَسُوا حَظًّا مِّمَّا ذُكِّرُوا بِهِ فَأَغْرَيْنَا

አምላካችን አሏህ "እኛ የአሏህ ረዳቶች ነን" ካሉት ከሐዋርያት ጋር የያዘው የጠበቀ ቃል ኪዳን «በእኔ እና በመልእክተኛዬ እመኑ» የሚል ነው፥ እነርሱም "አመንን፥ እኛ ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክር" አሉ፦
5፥111 ወደ ሐዋርያትም «በእኔ እና በመልእክተኛዬ እመኑ» በማለት ባዘዝኩ ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ أَوْحَيْتُ إِلَى الْحَوَارِيِّينَ أَنْ آمِنُوا بِي وَبِرَسُولِي
5፥111 «አመንን፥ እኛ ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክር» አሉ፡፡ قَالُوا آمَنَّا وَاشْهَدْ بِأَنَّنَا مُسْلِمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሙሥሊሞች" ለሚል የገባው ቃል "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون መሆኑን ልብ አድርግ! ነገር ግን ከሐዋርያት ኅልፈት በኃላ የተነሱት ሰዎች የታዘዙበትን ተውሒድ ተውት፥ በአሏህ ላይ ወሰን አልፈው አምላክን "አንድም ሦስትም ነው" በማለት አስተማሩ።
ከ 180 እስከ 313 ድኅረ ልደት በዓለም ዐቀፍ ደረጃ "ታላቂቱ ቤተክርስቲያን"Great Church" ተብላ በሮም መንግሥት መቀመጫ ያደረገች ታላቂቱ ቤተክርስቲያን በአበው ተዋቅራ ተደራጀች፥ ይህቺ ሴት በሮም መንግሥት ላይ ተቀምጣ በቅዱሳን ደም እና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ ታይታለች፦
ራእይ 17፥6 ሴቲቱም በቅዱሳን ደም እና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ አየኋት።

በታሪክ ውስጥ "ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው" የሚለውን ታላቁን እና ፊተኛውን የአምላክ ትእዛዝ የሚጠብቁትን የኢየሱስ ምስክር ያላቸው አሐዳውያንን ቤተ ክርስቲያን ደማቸውን በማፍሰስ ገላለች።
በ 200 እስከ 275 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረውን ጳውሎስ ዘሳምሳጢ"Paul of Samosata" የሳምሳጢ ኤጲስቆጶስ በግዝት እና በግዞት አሰቃይታለች። ሞናርኪያውያን "ኢየሱስ በምንነት ሰው ብቻ ነው፣ ምንነቱ ከማርያም ይጀምራል፣ ከማርያም በፊት በቃል ደረጃ እንጂ በህልውና የለም። በማንነቱ ነቢይ፣ መልእክተኛ፣ መሢሕ ነው፥ የአብ ልጅ የተባለው በግብር እንጂ በባሕርይ ስላልሆነ ልጅነቱ የማደጎ ልጅነት"Adoption" ነው" የሚል አቋም ነበራቸው፦
2ኛ ሳሙኤል 7፥12 ከወገብህ የሚወጣውን ዘርህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ፥
2ኛ ሳሙኤል 7፥14 እኔም አባት እሆነዋለሁ፥ እርሱም ልጅ ይሆነኛል።

ከወገብ የሚወጣ ዘር ፍጡር ነው፥ ከወገብ ለሚወጣ ዘር አምላክ "አባት እሆነዋለሁ" ሲል የሚወጣው ዘር ደግሞ "ልጅ ይሆነኛል" ስላለ ልጅነቱ የማደጎ ልጅነት የሚል አቋም አላቸው። እነዚህ ሞናርኪያውያን "ጠንካራ ሞናርኪያውያን"dynamic monarchian" ሲባሉ ነገር ግን በ 260 ድኅረ ልደት ሰባልስዮስ ዘሊቢያ"Sabellius of Libya" ሞናርኪያ የነበረ ሲሆን ሮም ሄዶ ከተማረ በኃላ "ኩነት"mode of existence" የተባለውን ትምህርት አስተማረ፦
መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 5 ቁጥር 4
"ሰብልያኖስ "አብ እንደ ሰው፣ ወልድ እንደ አንደበቱ ንግግር፣ መንፈስ ቅዱስ እንደ አፉ እስትንፋስ ናቸው" አለ። ስለዚህ አንድ ገጽ ናቸው" አለ።

"አንድ ሰው አንድ ገጽ(ማንነት) ኖሮት ዋናው ልብ ሲኖረው ከልቡ ቃል እና ከአፉ እስትንፋስ እንደሚወጣ አንድ አምላክ አብ ከራሱ የሚወጣ ቃል ወልድ እስትንፋሱ መንፈስ ቅዱስ ይባላል" የሚል አቋም ያላቸው የሰባልዮስ ተከታዮች "ኩነታዊ ሞናርኪያውያን"Modalistic monarchian" ይባላሉ። ሰባልዮስ ይህንን አቋም ሊያራምድ የቻለው ሮም ውስጥ "አማልክት ከአንዱ አምላክ "ብናኝ"Aeon" እየሆኑ ይወጣሉ" የሚል የኤዎን እሳቤ አዙሮት ነው። ይህ የመኳኳን ኩነት አብን ካርዲያስ ምንጭ፣ ወልድን ሎጎስ፣ መንፈስ ቅዱስን ኑውማቶስ በማድረግ ተኳኩነት"Modalism" ነው፥ "ካርዲያስ" καρδίας ማለት "ልብ" ማለት ነው፣ "ሎጎስ" λόγος ማለት "ቃል" ማለት ነው፣ "ኑውማቶስ" ማለት "እስትንፋስ" ማለት ነው።
ሰባልዮስ በማመስጠር እና በማመናፈስ "የኢየሱስ መለኮት አብ፣ ቃሉ ወልድ፣ እስትንፋሱ መንፈስ ቅዱስ" ብሎ ይሁዳ 1፥4 በተሳሳተ መልኩ በመጥቀስ "ኢየሱስ ብቻ"only Jesus" በማለት ይናገር ነበር፦
ይሁዳ 1፥4 ብቻውን ያለውን ጌታ እና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ። καὶ τὸν μόνον Δεσπότην καὶ Κύριον ἡμῶν Ἰησοῦν Χριστὸν ἀρνούμενοι.

"ዴስፖቴስ" δεσπότης ማለት "ጌታ" ማለት ሲሆን በግሪክ ሰፕቱአጀንት "ያህዌህ" יְהוָ֣ה የሚለው ቴትራግራማቶን ተክቶ የመጣ ነው፥ ለዚያ ነው "ብቻውን ያለውን ጌታ" የተባለው ኢየሱስ ስላልሆነ ኮዴክስ ቤዛይ ላይ፦ "ብቻውን ያለውን ጌታ አምላክ" በማለት አብ ለማመልከት የተቀመጠው፦
ይሁዳ 1፥4 ብቻውን ያለውን ጌታ አምላክ እና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ። καὶ τὸν μόνον δεσπότην θεὸν καὶ κύριον ἡμῶν Ἰησοῦν χριστὸν ἀρνούμενοι.

"ቴዎን" θεὸν የሚለውን ቃል አትለፉት! ለዚያ ነው በ 1611 ድኅረ ልደት በታተመው ቅጂ The King James Version (KJV) ላይ "and denying the only Lord God, and our Lord Jesus Christ" ብለው ያስቀመጡት። "ዴስፖቴን ቴዎን" δεσπότην θεὸν እና "ኩርዮን ቶን ቴዎን" ማለት "ጌታ አምላክ" ማለት ሲሆን "ያህዌህ ኤሎሂም" የሚለውን ተክቶ የመጣ ነው።
ለሥላሴ ትምህርት መሠረት የጣለው የሰባልዮስ የኩነት ትምህርት ነው፥ ሥላሴ ማለት "አምላክ በአካል ሦስት ሲሆን በኑባሬ አንድ ነው" ማለት ሲሆን ይህ ትምህርት የግሪኩ ፈላስፋ የአፍላጦን"plato" ትምህርት ነው፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 97 ቁጥር 7
"ዳግመኛም አፍአዊ አፍላጦን ስለ መለኮት የመለኮትን ምሥጢር ወደ ጢሞቴዎስ ጻፈ፦ "እግዚአብሔር በሦስት ስም በሦስት አካላት እንዳለ ይታወቃል፥ የጌትነት ሥልጣን በሦስቱ ያለ ነው፥ መጀመሪያ ጥንት ለሁሉ የሚራራ (አብ) ነው፣ ሁለተኛ ጥንት ሁሉን የፈጠረ ዕውቀት (ወልድ) ነው፣ ሦስተኛ ጥንት ለሁሉ ሕይወትን የሚያድል ነፍሳትን የሚያድን (መንፈስ ቅዱስ) ነው። ለእነዚህ (ለሦስቱ) የሚታወቁበት የአምላክነት ኃይል አላቸው"።

በቅንፍ ያስቀመጥኩት በግዕዙ ላይ ስለሌለ ነው። "አፍአዊ" ማለት "አንደበተ ርቱዕ" ማለት ሲሆን አፍላጦን የኖረው ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ 427 እስከ 348 ነው፥ ለዚህ ነው "ሥላሴ ሐዋርያት እና ነቢያት ያላስተማሩት አፍላጦአዊ ፍልስፍና ነው" የምንለው። ከታዘዙት ፈንታ በመተዋቸው እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ በመካከላቸው ጠብ እና ጥላቻ መኖሩ የአሏህ ቅጣት ነው፦
5፥14 ስለዚህ እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ በመካከላቸው ጠብን እና ጥላቻን ጣልንባቸው፡፡ አሏህም ይሠሩት የነበሩትን ሁሉ በእርግጥ ይነግራቸዋል፡፡ بَيْنَهُمُ الْعَدَاوَةَ وَالْبَغْضَاءَ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ ۚ وَسَوْفَ يُنَبِّئُهُمُ اللَّهُ بِمَا كَانُوا يَصْنَعُونَ

አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
እንቁጣጣሽ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

57፥3 ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ። اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ

“ጳጉሜ” የሚለው ቃል “ኤፓጎሜኖይ” ἐπαγόμενοι ከሚለው ከግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ “ተጨማሪ” ወይም “የተጨመረ” ማለት ነው፥ ጳጉሜ የወር ስም ሲሆን በነባሮች 12 ወራት ላይ የተጨመረ 13ኛ ወር ነው። ይህም ወር በነሐሴ እና በመስከረም መካከል የሚገኝ የመጨረሻው ወር ነው፥ ጳጉሜ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር በዘመነ ሉቃስ ስድስት ቀናት ሲኖሩር በዘመነ ዮሐንስ፣ በዘመነ ማቴዎስ እና በዘመነ ማርቆስ አምስት ቀናት ይሆናል። ልብ በሉ! ይህ ወር ከግሪክ ሄለኒዝም የተጀመረ እና ከአሌክሳንድርያ ወደ ኢትዮጵያ የገባ እንጂ በዕብራውያን አቆጣጠር ላይ ወራት 12 ብቻ ናቸው። አምላካችን አሏህ የወሮች ቁጥር በእርሱ መጽሐፍ ሰማያትን እና ምድርን በፈጠረበት ቀን አሥራ ሁለት ወር እንደሆነ ነግሮናል፦
9፥36 አላህ ዘንድ የወሮች ቁጥር በአሏህ መጽሐፍ ዉስጥ ሰማያትን እና ምድርን በፈጠረበት ቀን አሥራ ሁለት ወር ነው። إِنَّ عِدَّةَ ٱلشُّهُورِ عِندَ ٱللَّهِ ٱثْنَا عَشَرَ شَهْرًۭا فِى كِتَٰبِ ٱللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ

ይህ የሚያሳየው የኢትዮጵያው ዘመን መለወጫ በልምድ ከግሪክ የመጣ ሰርጎገብ እንጂ አገር በቀል አይደለም፥ ከዚያም ባሻገር መለኮታዊ ትእዛዝ ያለው ሳይሆን ሰው ሠራሽ ቢድዓህ ነው። ዓመተ ምሕረትን ያማከለ ዘመነ ሉቃስ፣ ዘመነ ዮሐንስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ሰው ሠራሽ ሃይማኖታዊ አስተምህሮት ነው፥ በዛ ላይ የባዕድ አምልኮ የሚፈፀምበት ቀን ነው። በጳጉሜ ቀናት ማልዶ የወጣ ሰው እንዲራመዳቸው ታስቦ በጎረቤት መተላለፊያ እና ህዝብ በሚያዘወትራቸው መንገዶች ላይ ፍየሎች፣ ዶሮዎች፣ ድመቶች፣ ጥንቸሎች ወዘተ ታርደው ይጣላሉ፥ በደም የተነከሩ ሳንቲሞች፣ ብሮች፣ ጌጣ ጌጦች እና የተለያዩ ቁሳቁሶች እዚህም እዚያም ወድቀው ይታያሉ።

ይህ ቀን ሲያልቅ የቀኑ መጨረሻ ተጓግቶ ስለሚመጣ “እንቁ” ተባለ፥ የሚያመጣው ጣጣና መዘዝ ደግሞ “ጣጣሽ” ተባለ። በጥቅሉ “እንቁ ጣጣሽ” ተባለ፥ ጥንቆላና ድግምት ከትልቁ ሽርክ የሚመደቡ የአሏህን ሐቅ የሚነካ ትልቅ በደል ነው። እንቁጣጣሽን ማክበር አቆጣጠሩ አገራዊ ሳይሆን እምነታዊ መሠረት ያለው ሲሆን ከእርሱ ጋር የተያያዙት ባዕድ አምልኮ አስበን ከዚህ ሰው ሠራሽ በዓል እራሳችንን እንጠብቅ! እንግዲህ እንቁጣጣሽ ዓመታዊ በዓል ዓረማዊ እና ክርስትናን ቀላቅሎ የያዘ በዓል ነው፥ በዚህ ጊዜ "እንኳን አደረስን" ወይም "እንኳን አደረሳችሁ" ሲባል ይህንን በዓል ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ነው። ሙሥሊም ያሉት ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻ እና ብቻ ናቸው፥ እነርሱም ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው ዐወቁ። እርሳቸውም፦ "እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፥ "ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ ”አሏህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፥ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን አሏቸው”። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ‏”‏ مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ‏”‏ ‏.‏
ጃሚዕ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፥ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው”። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
ጃሚዕ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 91
አቡ ሰዒደል ኹድሪይ እንደተረከው፥ የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” ”በሁለቱ በዓል በዒደል አደሐ እና ዒደል ፈጥር መጾም ከልክለዋል”። عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ، قَالَ نَهَى رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم عَنْ صِيَامَيْنِ يَوْمِ الأَضْحَى وَيَوْمِ الْفِطْرِ ‏.

“ዒድ” عِيد የሚለው ቃል “ዓደ” عَادَ ማለትም “ተመላለሰ” ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “ምልሰት” ማለት ነው፥ ይህ “መደሰቻ” ወይም “በዓል” በየዓመቱ ስለሚመላለስ ይህንን ስያሜ አግኝቷል። ስለዚህ ከአላህ የወረዱትን ቁርኣን እና ሐዲስ ብቻ ከተከተልን ሁለት በዓል ብቻ እና ብቻ አለን፦
7፥3 ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ። اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ

“ተከተሉ” የሚለው ቃል “ኢተቢዑ” اتَّبِعُوا ሲሆን “ኢትባዕ” إِتْبَاع‎ ማለት እራሱ የቢድዓህ ተቃራኒ "ከአሏህ ወደ ነቢያችን”ﷺ” የተወረደውን ብቻ መከተል" ማለት ነው። "ቢድዓህ" بِدْعَة የሚለው ቃል "በደዐ" بَدَعَ ማለትም "ፈጠረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ፈጠራ” ማለት ነው፥ ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ የሌለ ነገር በዲን ላይ መጨመር "ቢድዓህ" ሲሆን ሙሥሊም ግን የተወረደውን ብቻ ሲከተል ሁለት ዒድ ብቻ እና ብቻ ያከብራል። ስለዚህ "እንቁጣጣሽ" ስንባል "እንኳን ደህና መጣሽ" ከማለት ይልቅ "ማን አመጣሽ?" ብለህ በታሪካዊ ዳራ እና ፍሰት እንሞግታለን። በዓሉን ባለማወቅ ለሚያከብሩ አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
እንቁጣጣሽ
በኦሮሚኛ
https://tttttt.me/Wahidomar1/81

በትግሪኛ
https://tttttt.me/wahidtigriga/40

ጉራጊኛ
https://tttttt.me/wahidcomguragiga/50

በሲዳምኛ
https://tttttt.me/wahidcomsidamo/58

በስልጢኛ
https://tttttt.me/wahidcomselitiy/33

ተለቋል። የቋንቋው ባለቤቶች አንብቡ አስነብቡ!
አረጋግጡ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

49፥6 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነገረኛ ወሬን ቢያመጣላችሁ በስህተት ላይ ኾናችሁ ሕዝቦችን እንዳትጎዱ እና በሠራችሁት ነገር ላይ ተጸጻቾች እንዳትኾኑ አረጋግጡ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِن جَاءَكُمْ فَاسِقٌ بِنَبَإٍ فَتَبَيَّنُوا أَن تُصِيبُوا قَوْمًا بِجَهَالَةٍ فَتُصْبِحُوا عَلَىٰ مَا فَعَلْتُمْ نَادِمِينَ

ለፍቶ አዳሪ እና ሠርቶ አዳሪ ከመሆን ይልቅ ነጥቆ አዳሪ እና አውርቶ አዳሪ የሆኑት የሚድያ ጡረተኞች ወሬን ሳያረጋግጡ ሾላ በድፍኑ ሊቦተረፉ ማየት የተለመደ ጉዳይ እየሆነ መጥቶአል፥ አበው "እፍ ብለህ ታነዳለህ እፍ ብለህ ታጠፋለህ" በሚል አገርኛ ብሒላቸው ሚድያን ለአሉታዊ ነገር የሚጠቀሙ ተንኮለኛ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ በተቃራኒው ለአውንታዊ ነገር የሚጠቀሙ ቅን ሰዎች አሉ። የሚድያ ጡረተኞች የሚያመጡትን ወሬ ባተሎ እና ተላላ ሆኖ ከማራገብ ይልቅ ማረጋገጡ አምላካዊ ትእዛዝ ነው፦
49፥6 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነገረኛ ወሬን ቢያመጣላችሁ በስህተት ላይ ኾናችሁ ሕዝቦችን እንዳትጎዱ እና በሠራችሁት ነገር ላይ ተጸጻቾች እንዳትኾኑ አረጋግጡ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِن جَاءَكُمْ فَاسِقٌ بِنَبَإٍ فَتَبَيَّنُوا أَن تُصِيبُوا قَوْمًا بِجَهَالَةٍ فَتُصْبِحُوا عَلَىٰ مَا فَعَلْتُمْ نَادِمِينَ

"ነበእ" نَبَأ ማለት "መረጃ"information" ሲሆን የሚመጣልንን መረጃ ከማረጋገጥ ይልቅ ቸኩለን ያለ ዕውቀት እና ያለ ማስረጃ መናገር ትርፉ ሰውን መጉዳት እና የሕሊና ጸጸት ነው። እውነተኛ ሰው በማስረጃ ያረጋግጣል፦
2፥111 «እውነተኞች እንደኾናችሁ ማስረጃችሁን አምጡ» በላቸው፡፡ قُلْ هَاتُوا بُرْهَانَكُمْ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ

"ቡርሃን" بُرْهَان ማለት "ማስረጃ"evidence" ማለት ሲሆን አንድን መረጃ እውነት ወይም ሐሰት መሆኑን ለማረጋገጥ "ማስረጃ" ጉልህ እማኝ እና ዋቢ ነው። እውነተኛ ሰው በተጨማሪ በዕውቀት ያረጋግጣል፦
6፥143 «እውነተኞች እንደሆናችሁ በዕውቀት ንገሩኝ» በላቸው፡፡ نَبِّئُونِي بِعِلْمٍ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 229
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ ”ዕውቀት መፈለግ በሁሉም ሙሥሊም ላይ ግዴታ ነው”። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ طَلَبُ الْعِلْمِ فَرِيضَةٌ عَلَى كُلِّ مُسْلِمٍ

ያለ ዕውቀት አንድን ነገር በነሲብ፣ በጭፍን እና በደንዳናነት መከተል አይፈቀድም። ያለዚያ የፍርዱ ቀን ጭፍኑ ሰው ከጆሮ፣ ከዓይን እና ከልብ ተጠያቂ ነው፦
17፥36 ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር አትከተል! መስሚያ፣ ማያም፣ ልብም እነዚህ ሁሉ ባለቤታቸው ከእነርሱ ተጠያቂ ነውና፡፡ وَلَا تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ ۚ إِنَّ السَّمْعَ وَالْبَصَرَ وَالْفُؤَادَ كُلُّ أُولَـٰئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْئُولًا

ቅጥፈታዊ መረጃ እንደ ትቢያ በኖ እንደ ጢስ ተኖ የሚጠፋው እውነተኛ ሰው በማስረጃ እና በዕውቀት ሲያረጋግጥ ነው። ስለዚህ አንድ ነገር ከሚድያ ጡረተኞች ስንሰማ በመቸኮል አጀንዳ አርገን ከማራገብ ይልቅ ተረጋግተን በማስረጃ እና በዕውቀት መፈተሽ አለብን! መረጋጋት ከአሏህ ነው፥ ችኮላ ከሸይጧን ነው፦
ጃሚዕ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 27 ሐዲስ 118
ጀዳህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "መረጋጋት ከአሏህ ነው፥ ችኮላ ከሸይጧን ነው"። عَنْ جَدِّهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ الأَنَاةُ مِنَ اللَّهِ وَالْعَجَلَةُ مِنَ الشَّيْطَانِ ‏"‏

ኢማም አሥ ሡዩጢይ ሠነዱን ሐሠን ብለውታል። መቸኮላችን ዋጋ እያስከፈለን ነው፥ ሰው እስከ ማስገደል ድረስ ወንጀል የሚያሠራው ይህ ችኮላ ነው። በዕውቀት እና በማስረጃ እስከምናረጋግጥ ድረስ ዝም ማለቱ ነጻ ያወጣል፦
ጃሚዕ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 37 ሐዲስ 87
ዐብደላህ ኢብኑ ዐምር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ዝም ያለ ነጻ ሆነ"። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم "‏ مَنْ صَمَتَ نَجَا ‏"‏
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1 ሐዲስ 80
አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "በአሏህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን መልካም ይናገር ወይም ዝም ይበል"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ مَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ فَلْيَقُلْ خَيْرًا أَوْ لِيَصْمُتْ

የምእመናን አርአያ እና የሥነ ምግባር ባለቤት የሆኑት ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" "በአሏህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምን መልካም ይናገር ወይም ዝም ይበል" ብለው በአጽንዖት እና በአንክሮት ዘክረውናል። አምላካችን አሏህ ሰውን ከመጉዳት እና ከሕሊና ጸጸት ይጠብቀን! ተረጋግተው በማስረጃ እና በዕውቀት ከሚያረጋግጡት ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ተጸጸተ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

65፥11 አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

አምላካችን አሏህ ሁሉንም "ነገር" ዐዋቂ ነው፥ "ሸይእ" شَيْء ማለት "ነገር" ማለት ሲሆን ይህም ነገር አጠቃላይ ፍጥረትን ሁሉ ያጠቃልላል፦
65፥11 አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

አሏህ አንድ ነገር ከመከሰቱ፣ ከመሆኑ፣ ከመደረጉ፣ ከመከናወኑ በፊት ያለውን ሩቅ ነገር እና አንድ ነገር ከተከሰተ፣ ከሆነ፣ ከተደረገ፣ ከተከናወነ በኃላ ያለውን ግልጹን ነገር ሁሉ ዐዋቂ ነው፦
64፥18 ሩቁን ነገር ግልጹንም ሁሉ ዐዋቂው አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ عَالِمُ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ

"አማሬ ኲሉ" ማለት "ሁሉን ዐዋቂ" ማለት ነው፥ መለኮት "ሁሉን ዐዋቂ" ነው። በባይብል አንዱ አምላክ "ሁሉን ዐዋቂ" ነው፦
1 ዮሐንስ 3፥20 አምላክ ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና "ሁሉንም ያውቃል"። ὅτι μείζων ἐστὶν ὁ Θεὸς τῆς καρδίας ἡμῶν καὶ γινώσκει πάντα.

ቅሉ ግን አንድ ማንነት በሠራው ሥራ ከተጸጸተ ያንን ሥራ ከመሥራቱ በፊት ስለማያውቅ ሁሉን ዐዋቂ አይደለም። ለምሳሌ፦ ሰው በሚሠራው ሥራ ይጸጸታል፦
ዘጸአት 13፥17 አምላክ፦ "ሕዝቡ ሰልፉን ባየ ጊዜ እንዳይጸጽተው እና ወደ ግብፅ እንዳይመለስ" ብሎአልና። אָמַ֣ר אֱלֹהִ֗ים פֶּֽן־יִנָּחֵ֥ם הָעָ֛ם בִּרְאֹתָ֥ם מִלְחָמָ֖ה וְשָׁ֥בוּ מִצְרָֽיְמָה׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "እንዳይጸጽተው" ለሚለው የገባው ግሥ " ፐን ዪንናኼም" פֶּֽן־ יִנָּחֵ֥ם ሲሆን ሥርወ-ቃሉ "ናኻም" נָחַם ነው። የእስራኤል ሕዝብን የፈርዖንን ሠራዊት ሰልፍ ባየ ጊዜ ከግብፅ መውጣቱ ጸጽቶት ወደ ግብፅ መመለስ ከከጀለ በመውጣቱ ይጸጸት ነበር፥ የእስራኤል ሕዝብን ሰው ስለሆነ የወደፊቱን ሰማያውቅ በሠራው ሥራ ሊጸጸት ስለሚችል ፈጣሪ እንዳይጸጸቱ መክሯቸዋል። ሰው የወደፊቱን ሁሉን ዐዋቂ ስላልሆነ በሚሠራው ሥራ ይጸጸታል፥ የሰው ተቃራኒ አምላክ ደግሞ የወደፊቱን ሁሉን ዐዋቂ ስለሆነ በሚሠራው ሥራ አይጸጸትም፦
ዘኍልቍ 23፥19 ሐሰትን ይናገር ዘንድ አምላክ ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። לֹ֣א אִ֥ישׁ אֵל֙ וִֽיכַזֵּ֔ב וּבֶן־אָדָ֖ם וְיִתְנֶחָ֑ם
1 ሳሙኤል 15፥29 የእስራኤል ኃይል አይዋሽም አይጸጸትምም፤ እርሱ ይጸጸት ዘንድ ሰው አይደለምና። וְגַם֙ נֵ֣צַח יִשְׂרָאֵ֔ל לֹ֥א יְשַׁקֵּ֖ר וְלֹ֣א יִנָּחֵ֑ם כִּ֣י לֹ֥א אָדָ֛ם ה֖וּא לְהִנָּחֵֽם׃

ሁለቱም አናቅጽ ላይ "መጸጸት" ለሚለው የገባው የግሥ መደብ ሥርወ-ቃሉ "ናኻም" נָחַם እንደሆነ ልብ አድርግ! ነገር ግን ከዚያ በተቃራኒው ያህዌህ በሠራው ሥራ እንደተጸጸተ ባይብሉ ይናገራል፦
ዘፍጥረት 6፥6 ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፤ በልቡም እጅግ አዘነ። וַיִּנָּ֣חֶם יְהוָ֔ה כִּֽי־עָשָׂ֥ה אֶת־הָֽאָדָ֖ם בָּאָ֑רֶץ וַיִּתְעַצֵּ֖ב אֶל־לִבֹּֽו׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "ተጸጸተ" ለሚለው የገባው ግሥ "ይዪንናኼም" פֶּֽן־ יִנָּחֵ֥ם ሲሆን ሥርወ-ቃሉ "ናኻም" נָחַם ነው፥ ያህዌህ የተጸጸተ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ነው። የሠሩትን ወንጀል ዓይቶ "ከመነሻው ሰው መፍጠር አልነበረብኝም" ብሎ በሠራው ሥራ ተጸጸተ፥ መጸጸት ለሁሉን ዐዋቂ አምላክ የተገባ ባሕርይ አይደለም።
በእርግጥ "ናኻም" נָחַם የሚለው ቃል "ተጸጸተ" ብቻ ሳይሆን "አዘነ" "ራራ" "አጽናና" "ረዳ" "ተቆጣ" የሚል ፍቺ ይኖረዋል፥ ይህንን ይዘን፦
፨"ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ "አዘነ"
፨ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ "ራራ"
፨ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ "አጽናና"
፨ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ "ረዳ"
፨ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ "ተቆጣ"
ትርጉም ይሰጣልን? እራሱ በሠራው ሥራ ማዘን፣ መራራት፣ መጽናናት፣ መርዳት፣ መቆጣት ትርጉም አይሰጥም፥ ነገር ግን እራሱ በሠራው ሥራ ተጸጽቷል። ይህ የፈጣሪ ባሕርይ በፍጹም አይደለም፥ "አምላክ ይጸጸት ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም" "እርሱ ይጸጸት ዘንድ ሰው አይደለም" ከሚሉት አናቅጽ ጋር ከመጋጨት አልፎ በመላተም ይፋጫል። የሚያሳዝነው "ያህዌህ ሰውን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ" ብሎ የሚነግረው ያህዌህ ወይም ሙሴ ሳይሆን ማንነቱ በውል የማይታወቅ ሰው ነው፦
ዘፍጥረት 6፥7 ያህዌህ፦ “የፈጠርሁትን ሰው ከምድር ላይ አጠፋለሁ፥ ከሰው እስከ እንስሳ እስከ ተንቀሳቃሽም እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ፤ ስለ ፈጠርኋቸው ተጸጽቼአለሁና” አለ።

እሺ ሰውስ ስላጠፋ አምላክ ሰውን በመፍጠሩ ጸጸተ እንስሳ፣ ተንቀሳቃሽ እና የሰማይ ወፍ ምን አድርገው ነው እነርሱ ስለ መፍጠሩ የተጸጸተው? ይህ ውሉ የማይታወቅ ሰው ንግግር ይዘን እንደ አምላክ ቃል መሞገት አግባብ አይደም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መውሊድ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

7፥3 ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ። اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ

“መውሊድ” مَوْلِد‎ የሚለው ቃል "ወለደ" وَلَدَ ማለትም "ወለደ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “ልደት” ማለት ነው፥ "የልደት ቀን፣ ቦታ እና በዓል እራሱ "መውሊድ" مَوْلِد‎ ይሉታል። በተለይ ነቢያችን”ﷺ” ተወለዱት ተብሎ የሚከበርበት ቀን "መውሊድ" مَوْلِد‎ ይባላል፥ ይህንን የመውሊድ እሳቤ ለማወቅ ከዝንባሌ ነጻ ሆነን ስለ ሸሪዓችን ጠንቅቀህ ማወቅ ይጠበቅብናል። መፍረድ ያለብንም ከአሏህ በወረደው ሸሪዓህ ብቻ ነው፦
5፥48 በመካከላቸውም አሏህ ባወረደው ሕግ ፍረድ። فَٱحْكُم بَيْنَهُم بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ

“ሑክም” حُكْم የሚለው ቃል”ሐከመ” حَكَمَ ማለትም “ፈረደ” ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን ፍርድ” ወይም “ሕግ” ማለት ነው፥ “አሕካም” أَحْكَام‎ ማለት ደግሞ የሑክም ብዙ ቁጥር ሲሆን “ሕግጋት” ማለት ነው። በኢሥላም አሕካም በአምስት ዋና ዋና ክፍል ይከፈላል፥ እነርሱም፦ “ፈርድ” فَرْد‎ “ሙስተሐብ” مُسْتَحَبّ‎ “ሙባሕ” مُبَاح‌‌‎ “መክሩህ” مَكْرُوه‎ እና “ሐራም” حَرَام ናቸው። አምላካችን አሏህ ሐላል ያላደረገውን ነገር ሐላል ማድረግ ዝንባሌን መከተል ነው፦
5፥48 እውነቱም ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን አትከተል፡፡ ከእናንተ ለሁሉም ሕግን እና መንገድን አደረግን፡፡ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَآءَهُمْ عَمَّا جَآءَكَ مِنَ ٱلْحَقِّ ۚ لِكُلٍّۢ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةًۭ وَمِنْهَاجًۭا

እዚህ አንቀጽ ላይ “ሕግ” ለሚለው ቃል የገባው “ሺርዓህ” شِرْعَة ሲሆን “ሸሪዓህ” شَرِيعَة ማለት እራሱ “ትክክለኛ ሕግ” ማለት ነው። “ዒባዳህ” عِبَادَة ማለት “አምልኮ” ማለት ሲሆን ዒባዳህ አሏህ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኝባቸው ሥስት ሸርጦች አሉት፥ እነርሱም፦ ኢማን፣ ኢኽላስ እና ኢትባዕ ናቸው። “ኢትባዕ” إِتْبَاع‎ የሚለው ቃል “አትበዐ” أَتْبَعَ ማለትም “ተከተለ” ከሚለው ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን የተወረደውን “መከተል” ማለት ነው፥ ያለ ኢትባዕ ማንኛውም ዒባዳህ ተቀባይነት የለውም። ኢትባዕ ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ በተቀመጠው ብቻ ዒባዳህን መፈጸም ነው፦
6፥106 ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን ተከተል፡፡ اتَّبِعْ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ
7፥3 ከጌታችሁ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ። اتَّبِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ

“ተከተሉ” የሚለው ቃል “ኢተቢዑ” اتَّبِعُوا ሲሆን “ኢትባዕ” ማለት ከአሏህ ወደ ነቢያችን”ﷺ” የተወረደውን ብቻ መከተል ማለት ነው፥ ሙሥሊም የተወረደውን ብቻ ሲከተል ሁለት ዒድ ብቻ ያከብራል። “ዒድ” عِيد የሚለው ቃል “ዓደ” عَادَ ማለትም “ተመላለሰ” ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “ምልሰት” ማለት ነው፥ ይህ “መደሰቻ” ወይም “በዓል” በየዓመቱ ስለሚመላለስ ይህንን ስያሜ አግኝቷል። ነቢያችን”ﷺ” የነገሩን ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻ እና ብቻ ናቸው፥ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ጃሚዕ አት ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው"። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
አሥ ሠለፉ አስ ሷሊሑን የሚያከብሩት እነዚህን ሁለቱን በዓላት ብቻ ነበር። እነዚህ ሦስት ትውልድ፦
፨፦ የመጀመሪያው ትውልድ “ሰሓቢይ” صَحَابِيّ ሲባሉ የነቢያችን”ﷺ” ውድ “ባልደረባ”companion” ናቸው፣
፨፦ ሁለተኛው ትውልድ “ታቢዒይ” تَابِعِيّ ሲባሉ ለጥቆ ያሉ ናቸው፣
፨፦ ሦስተኛው ትውልድ “ታቢዑ አት-ታቢዒን” تَابِع التَابِعِين ሲባሉ ሠልሶ ያሉ ናቸው። እነዚህ ሦስት ትውልድ “አሥ-ሠለፉ አስ-ሷሊሑን” ٱلسَلَف ٱلصَالِحُون ማለትም “መልካሞቹ ቀደምት” ይባላሉ፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 83, ሐዲስ 72
ዒምራን ኢብኑ ሑሰይን እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ ”ከእናንተ ምርጡ የእኔ ትውልድ ነው፥ ቀጥሎ ያሉት እነርሱን የሚከተሉት ነው፥ ለጥቆ ያሉት የሚከተሉትን የሚከተሉ ናቸው”። قَالَ سَمِعْتُ عِمْرَانَ بْنَ حُصَيْنٍ، يُحَدِّثُ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ خَيْرُكُمْ قَرْنِي، ثُمَّ الَّذِينَ يَلُونَهُمْ، ثُمَّ الَّذِينَ يَلُونَهُم

አሥ-ሠለፉ አስ-ሷሊሑን በመንሀጃቸው ውስጥ ስለ መውሊድ  አላስተማሩም፥ መውሊድን አልተገበሩትም። “መንሀጅ” مَنْهَج ማለት “ፍኖት” “ፋና” “መንገድ” ማለት ነው። በታሪክ እንደሚታወቀው ለመጀመርያ ጊዜ "የነቢያችን”ﷺ”  የልደት ቀን" ተብሎ መከበር የተጀመረው ግብፅ ውስጥ በፋጢሚዩን በአራተኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ላይ ነው፥ የጀመሩትም ክርስቲያኖች ከሚያከብሩት "ልደት" ኮርጀው ነው። ክርስቲያኖች ደግሞ የሚያክብሩት ከመጽሓፋቸው ተፈቅዶላቸው ወይም ታዘው ሳይሆን ከፓጋን ኮርጀው ነው። ስለ ገና ይህንን ጽሑፍ ይመልከቱ፦ https://tttttt.me/Wahidcom/3665

ስለዚህ ሦስተኛ በዓል መውሊድ መጤ እና ቢድዓ ነው፥ “ቢድዓህ” بِدْعَة የሚለው ቃል “በደዐ” بَدَعَ ማለትም “ፈጠረ” ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “ፈጠራ” ማለት ነው። ቢድዓህ የኢትባዕ ተቃራኒ ነው፥ “ቢድዓህ” ማለት አላህ ሳያዘን እና ሳይፈቅድልን ዝንባሌአችንን ተከትለን የምናደርገው አዲስ አምልኮ ማለት ነው። ያለ ኢትባዕ የአሏህን ውዴታ ለመፈለግ ተብሎ የሚደረግ ማንኛውም አዲስ አምልኮ ቢድዓህ ነው፦
ሡነን ነሣኢ መጽሐፍ 19, ሐዲስ 23
ጃቢር ኢብኑ ዐብደላህ እንደተረከው፦ የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” ኹጥባቸው ላይ እንደተናገሩት፦ “አሏህ የመራውን ማንም አያጠመውም፥ አሏህ ያጠመመውን ማንም አያቀናውም። ከንግግር ሁሉ በላጩ የአሏህ መጽሐፍ ነው፥ ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነው። ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓህ ነው፥ ቢድዓህ ሁሉ ጥመት ነው። ጥመት ሁሉ የእሳት ነው"። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ قَالَ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ فِي خُطْبَتِهِ يَحْمَدُ اللَّهَ وَيُثْنِي عَلَيْهِ بِمَا هُوَ أَهْلُهُ ثُمَّ يَقُولُ مَنْ يَهْدِهِ اللَّهُ فَلَا مُضِلَّ لَهُ وَمَنْ يُضْلِلْهُ فَلَا هَادِيَ لَهُ إِنَّ أَصْدَقَ الْحَدِيثِ كِتَابُ اللَّهِ وَأَحْسَنَ الْهَدْيِ هَدْيُ مُحَمَّدٍ وَشَرُّ الْأُمُورِ مُحْدَثَاتُهَا وَكُلُّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ وَكُلُّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ وَكُلُّ ضَلَالَةٍ فِي النَّارِ

ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓህ ነው፥ ቢድዓህ ሁሉ ጥመት ነው። ጥመት ሁሉ የእሳት ከሆነ ካየን ዘንዳ ቢድዓህ የሚያራምድ ማንኛውም ሰው "ተብዲዕ" تَبْدِيع ከተደረገበት “ሙብተዲዕ” مُبْتَدِع ይባላል። ቢድዓህ ደግሞ ምንጩ ዝንባሌን መከተል ነው፥ በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፦
79፥40 በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ፥ وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَى
79፥41 ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፡፡ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ

አምላካችን አሏህ ዝንባሌ ከመከተል ይጠብቀን! ከቢድዓህ እርቀን በኢትባዕ ብቻ እርሱን የምናመልክ ያርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዲኑል ኢሥላም

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥19 አሏህ ዘንድ ሃይማኖት ኢሥላም ነው፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ

አምላካች አሏህ በተለያየ ዘመነ መግቦት"dispensation" መልእክተኛ ልኳል፥ ያ የሚላከው ማንንም መልእክተኛ በአሏህ ፈቃድ አማኞች ሊታዘዙት እንጂ አልተላከም፦
4፥64 ማንንም መልእክተኛ በአሏህ ፈቃድ ሊታዘዙት እንጂ አልላክንም፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن رَّسُولٍ إِلَّا لِيُطَاعَ بِإِذْنِ اللَّهِ

"ኢዝን" بِإِذْن ማለት "ፈቃድ" ማለት ሲሆን አንድ አማኝ የተላከው መልእክተኛ መታዘዝ የአሏህ ፈቃድ ነው፥ በዚህም ኑሕ፣ ሁድ፣ ሷሊሕ፣ ሉጥ፣ ሹዕይብ፣ ዒሣ ወዘተ "ታዘዙኝ" በማለት ይናገራሉ፦
26፥108 26፥126 26፥144 26፥163 26፥169 3፥50 አሏህንም ፍሩ! ታዘዙኝም፡፡ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ

እነዚህ አናቅጽ ላይ "ታዘዙኝ" ለሚለው የገባው ቃል "አጢዑኒ" أَطِيعُونِ ነው፥ አምላካችን አሏህ ተወዳጁ ነቢያችንን"ﷺ" መታዘዝ እንዳለብን ሲናገር "መልእክተኛውን ታዘዙ" በማለት ነው፦
24፥56 ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ፣ ምጽዋትንም ስጡ፣ መልእክተኛውን ታዘዙ! ለእናንተ ሊታዘንላችሁ ይከጀላልና፡፡ وَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዘዙ" ለሚለው የገባው ቃል "አጢዑ" أَطِيعُوا እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። ቅሉ እና ጥቅሉ ግን ሰዎች ለአሏህ "ታዘዙ" የተባሉበት ትእዛዝ ግን ለእርሱ ብቻ አምልኮታዊ መታዘዝ ነው፦
22፥34 አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱም ብቻ ታዘዙ! ለአሏህ ተዋራጆችንም አብስራቸው፡፡ فَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ فَلَهُ أَسْلِمُوا ۗ وَبَشِّرِ الْمُخْبِتِينَ

"አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው" ካለ በኃላ "ለእርሱም ብቻ ታዘዙ" በማለት ያስቀምጣል፥ እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዘዙ" ለሚለው የገባው ቃል "አሥሊሙ" أَسْلِمُوا ሲሆን ለእርሱ በብቸኝነት የሚቀርብ አምልኮ ነው፦
39፥54 «ቅጣቱም ወደእናንተ ከመምጣቱ እና ከዚያም የማትረዱ ከመኾናችሁ በፊት ወደ ጌታችሁ በመጸጸት ተመለሱ፡፡ ለእርሱም ታዘዙ!፡፡ وَأَنِيبُوا إِلَىٰ رَبِّكُمْ وَأَسْلِمُوا لَهُ مِن قَبْلِ أَن يَأْتِيَكُمُ الْعَذَابُ ثُمَّ لَا تُنصَرُونَ

አሁንም እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዘዙ" ለሚለው የገባው ቃል "አሥሊሙ" أَسْلِمُوا ነው፥ "ኢሥላም" إِسْلَام ማለት እራሱ "መታዘዝ" ማለት ነው፦
3፥19 አሏህ ዘንድ ሃይማኖት ኢሥላም ነው፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ

ለአሏህ ብቻ በውጥን የሚደረግ መታዘዝ "ኢሥላም" إِسْلَام ይባላል፥ "ኢሥላም" إِسْلَام የሚለው ቃል "አሥለመ" أَسْلَمَ‎ ማለትም "ታዘዘ" "ተገዛ" "አመለከ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መታዘዝ" "መገዛት" "ማምለክ" ማለት ነው።
"ዲን" دِين የሚለው ቃል "ዳነ" دَانَ ማለትም "ሃይመነ" "ደነገገ"  "ፈረደ" "በየነ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ሃይማኖት" "ፍትሕ" "ፍርድ" "ሕግ" "መርሕ"doctrine" ማለት ነው፥ አሏህ ዘንድ ያለው ሃይማኖት ኢሥላም ነው። አንድ ማንነት ለአሏህ ብቻ በአምልኮ ሲታዘዝ "ሙሥሊም" مُسْلِم ይባላል፦
3፥84 «እኛ ለእርሱ ታዛዦች ነን» በል፡፡ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ
2፥136 «እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን» በሉ፡፡ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ
29፥46 በሉም «በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ወደ እናንተም በተወረደው አመንን፡፡ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፡፡ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን» وَقُولُوا آمَنَّا بِالَّذِي أُنزِلَ إِلَيْنَا وَأُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَإِلَـٰهُنَا وَإِلَـٰهُكُمْ وَاحِدٌ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ

እነዚህ አናቅጽ ላይ "ታዛዦች" ለሚለው የገባው ቃል "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون ነው፥ "ሙሥሊም" مُسْلِم ማለት በነጠላ "ታዛዥ" ማለት ሲሆን ብዙ ቁጥሩ "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون ነው። ታዲያ ቀደምት ነቢያት ሙሥሊሞች አይደሉምን? ዲናቸውስ "ፈጣሪ አንድ አምላክ ነው" ተብሎ ፈጣሪን ብቻ በአምልኮ መታዘዝ አይደለምን? እንዴታ።
ወደ እኛም የተወረደው እና ወደ መጽሐፉ ሰዎች የተወረደው ግልጠተ መለኮት ጭብጡ የአንድ አምላክ አስተምህሮት ነው፦
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልእክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ

አሏህ ከጥንት ጀምሮ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" ብሎ ለሚልከው ነቢይ የሚገልጠው ይህ ግልጠት ነው፥ "የምናወርድ" ለሚለው የገባው ቃል "ኑሒ" نُوحِي ሲሆን የሚወርድለት "ወሕይ" وَحْي ነው። ስለዚህ የቀደሙት ነቢያት ሙሥሊም ነበሩ፦
5፥44 እነዚያ "ትእዛዝን የተቀበሉት" ነቢያት በእነዚያ አይሁዳውያን በኾኑት ላይ በእርሷ ይፈርዳሉ፡፡ يَحْكُمُ بِهَا النَّبِيُّونَ الَّذِينَ أَسْلَمُوا لِلَّذِينَ هَادُوا

በግሥ መደብ "ትእዛዝን የተቀበሉት" ለሚለው የገባው ቃል "አሥለሙ" أَسْلَمُوا ሲሆን በስም መደብ "ሙሥሊም" مُسْلِم ነው። የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፦
3፥64 በል፦ "የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ تَعَالَوْا إِلَىٰ كَلِمَةٍ سَوَاءٍ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ

ይህቺ የጋራ ትክክለኛ ቃል አሏህን እንጂ ሌላን ላናመልክ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአሏህ ሌላ ጌቶች አድርጎ ላይዝ ነው፦
3፥64 እርሷም፦ "አሏህን እንጂ ሌላን ላናመልክ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአሏህ ሌላ ጌቶች አድርጎ ላይዝ ነው"። أَلَّا نَعْبُدَ إِلَّا اللَّهَ وَلَا نُشْرِكَ بِهِ شَيْئًا وَلَا يَتَّخِذَ بَعْضُنَا بَعْضًا أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ

"ረብ" رَبّ ማለት "ጌታ" ማለት ነው፥ የረብ ብዙ ቁጥር "አርባብ" أَرْبَابً ሲሆን "ጌቶች" ማለት ነው። አሏህን በአምልኮቱ እና በጌትነቱ መታዘዝ ኢሥላም ሲሆን ይህንን ሐቅ ካስተባበሉ ሑጃህ እንዲቆምባቸው እኛ ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፦
3፥64 ምቢ ቢሉም፡- "እኛ ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክሩ" በሏቸው፡፡ فَإِن تَوَلَّوْا فَقُولُوا اشْهَدُوا بِأَنَّا مُسْلِمُونَ

አምላካችን አሏህ በዲኑል ኢሥላም ያጽናን! ሙሥሊም አድርጎ ወደ እርሱ ይውሰደን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ወንድ እና ሴት

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

53፥45 እርሱም ሁለቱን ዓይነቶች ወንድን እና ሴትን ፈጠረ፡፡ وَأَنَّهُ خَلَقَ الزَّوْجَيْنِ الذَّكَرَ وَالْأُنثَىٰ

ሐቅን መሸጥ፣ መሸቀጥ እና መሸቃቀጥ የለመዱ ሚሽነሪዎች "ቁርኣን ወንድን እንጂ ሴትን ሰው አይላትም" በማለት ዓይነ መጭማጫ ሆነው ጥቅስን በቅጡ እና በአግባቡ ሳያነቡ እና ሳይረዱ ያንሸዋርራሉ። ቁርኣንን ሳያጠኑ ከላይ ከላይ እያንኮበከቡ ለሚያጠናብሩ ደግነታችን መሬት ስለማይነጥፍ መልስ እንሰጣለን።
"ኑጥፋህ” نُّطْفَة ማለት "የፍትወት ፈሳሽ"sexual fluid" ማለት ነው፥ ይህምም የፍትወት ፈሳሽ የወንዱ የዘር ሕዋስ"sperm cell" እና የሴቷ የእንቁላል ሕዋስ"egg cell" ነው። አምላካችን አሏህ ሰውን ቅልቅሎች ከኾኑ የፍትወት ሕዋስ እንደፈጠረ ይናገራል፦
76፥2 እኛ ሰውን በሕግ ግዳጅ የምንፈትነው ስንኾን ቅልቅሎች ከኾኑ የፍትወት ሕዋስ ፈጠርነው፡፡ إِنَّا خَلَقْنَا الْإِنسَانَ مِن نُّطْفَةٍ أَمْشَاجٍ نَّبْتَلِيهِ

የወንዱ 23 ነጠላ ሕዋስ"haploid" እና የሴቷ 23 ነጠላ ሕዋስ"haploid" በተራክቦ ጊዜ አምሻጅ ይሆናል፥ “አምሻጅ” أَمْشَاج ማለት “ቅልቅል"diploid" ማለት ነው። ከዚህ ቅልቅል የፍትወት ሕዋስ ድቅለት"fertilization" ፅንስ ይፈጠራል፥ "ሚን" مِن ማለት "ከ" ማለት ሲሆን "ሚን" የሚለው መስተዋድድ "ኑጥፋህ" ከሚለው መነሻ ላይ መምጣቱ በራሱ የሁለቱን ተቃራኒ ጾታ የሚያመለክት ነው። እዚህ አንቀጽ ላይ "ሰው" ለሚለው የገባው ቃል "አል ኢንሣን" الْإِنسَان ሲሆን ከሁለቱንም የፍትወት ሕዋስ ማለትም ከወንድ የፍትወት ሕዋስ እና ከሴት የፍትወት ሕዋስ የተፈጠረውን ሰው አመላካች ነው፥ ከወንድ የፍትወት ሕዋስ እና ከሴት የፍትወት ሕዋስ የተፈጠረውን ሰው ሌላ ቦታ ላይ ወንድ እና ሴት ይለዋል፦
53፥45 እርሱም ሁለቱን ዓይነቶች ወንድን እና ሴትን ፈጠረ፡፡ وَأَنَّهُ خَلَقَ الزَّوْجَيْنِ الذَّكَرَ وَالْأُنثَىٰ
53፥46 ከፍትወት ሕዋስ በምትፈሰስ ጊዜ፡፡ مِن نُّطْفَةٍ إِذَا تُمْنَىٰ

"ኢዛ" إِذَا ማለት "ጊዜ" ማለት ነው፥ ይህም የተራክቦን ጊዜ ያሳያል። "ቱምና" تُمْنَىٰ ወይም "ዩምና" يُمْنَىٰ የግሥ መደብ ሲሆን "የምትፈሰስ" ማለት ነው፥ የስም መደቡ ደግሞ "መኒይ" مَّنِىّ ማለትም "የፍትወት ሕዋስ" ማለት ነው። ከፍትወት ሕዋስ የተፈጠረው ሰው ወንድ እና ሴት ነው፦
75፥36 "ሰው" ልቅ ኾኖ መትተውን ይጠረጥራልን? أَيَحْسَبُ الْإِنسَانُ أَن يُتْرَكَ سُدًى
75፥37 የሚፈሰስ ከኾነ የፍትወት ሕዋስ አልነበረምን? أَلَمْ يَكُ نُطْفَةً مِّن مَّنِيٍّ يُمْنَىٰ
75፥38 ከዚያም "የረጋ ደም" ሆነ፥ ፈጠረውም፡፡ አስተካከለውም፡፡ ثُمَّ كَانَ عَلَقَةً فَخَلَقَ فَسَوَّىٰ
75፥39 "ከእርሱም ሁለት ዓይነቶችን ወንድ እና ሴትን አደረገ"፡፡ فَجَعَلَ مِنْهُ الزَّوْجَيْنِ الذَّكَرَ وَالْأُنثَىٰ

"ሚን-ሁ" مِنْهُ ማለት "ከእርሱ" ማለት ሲሆን "ከ" የሚል መስተዋድ ያለበት ተሳቢ ስለሆነ "እርሱ" የተባለው ዐውደ ንባቡ ላይ ያለው "መኒይ" مَّنِىّ የሚለውን ተክቶ የመጣ ነው፥ እዚህ አንቀጽ ላይ አሏህ "ሁለት ዓይነቶችን ወንድ እና ሴትን" የሆነን ሰው ከመኒይ እንደፈጠረ ሲናገር ከላይ ደግሞ ሰውን "ቅልቅሎች ከኾኑ የፍትወት ሕዋስ ፈጠርነው" ማለቱ "ሰው" የሚባሉት ወንድ እና ሴት መሆናቸውን ፍንትው አርጎ ያሳያል። የአባት ሀብለ በራሂ"paternal chromosome" ግማሽ 23% የእናት ሀብለ በራሂ"maternal chromosome" 23% ተገናኛተው 46% ሀብለ በራሂ ሕዋስ"diploid" ሆነው ይዋሐዳሉ፦
49፥13 እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድ እና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَاكُم مِّن ذَكَرٍ وَأُنثَىٰ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሰዎች" ለሚለው የገባው ቃል "አን ናሥ" النَّاس ሲሆን ከወንድ እና ከሴት የተፈጠሩትን ወንድ እና ሴት ያመለክታል፥ ሰዎች ከሴት ተፈጥረው ሳለ "ሰው ካሆነች ሴት ሰዎች ተፈጠሩ" ማለት ቂልነት ነው። አሏህ ከወንድ አደም እና ከሴት ሐዋ ብዙ ወንዶችን እና ሴቶችን የፈጠረ ነው፦
4፥1 እናንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ የፈጠራችሁን፣ ከእርስዋም መቀናጆዋን የፈጠረውን፣ ከእነርሱም ብዙ ወንዶችን እና ሴቶችን የበተነውን ጌታችሁን ፍሩ፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ اتَّقُوا رَبَّكُمُ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَاحِدَةٍ وَخَلَقَ مِنْهَا زَوْجَهَا وَبَثَّ مِنْهُمَا رِجَالًا كَثِيرًا وَنِسَاءً

"እናንተ ሰዎች ሆይ" የሚለው ይሰመርበት! “ከእነርሱም” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሚንሁማ” مِنْهُمَا ሲሆን “ሙሰና” مُثَنًّى ነው። “ሚንሁማ” مِنْهُمَا ሁለቱን ጥንድ የሚያሳይ ሲሆን ከእነርሱ ማለትም ከአደም እና ከሐዋ ብዙ ወንዶችን እና ሴቶችን ፈጠረ፥ አሏህ እነዚህ ወንዶችን እና ሴቶችን "እናንተ ሰዎች ሆይ" ይላቸዋል። "አዝዋጅ أَزْوَاج ማለት "ጥንዶች"pairs" ማለት ነው፦
78፥8 ጥንዶች አድርገን ፈጠርናችሁ፡፡ وَخَلَقْنَاكُمْ أَزْوَاجًا

እነዚህ ጥንዶች ወንድ እና ሴት እንደሆኑ ተፍሢር ኢብኑ ዐባሥ፣ ተፍሢር ኢብኑ ከሲር እና ተፍሢር ጀላለይን ገልጸውታል፥ ሴት ከወንድ ሰው ተፈጥራ ሳለ "ሰው አይደለችም" ማለት ጅላንፎነት ነው። ስለዚህ "በቁርኣን "ሴት ሰው ናት" የሚል የለም" የሚል ሙግት ዕውር ድንብር የሆነ ጸለምተኛ ሙግት"Pessimistic Approach" ነው።
በአሁን ሰዓት የሙሥሊም ዐቃቢያን ዕቅበተ ሥራ ብዙ ክርስቲያኖችን እየናጠ ስለሆነ ቆፍጠን ብለን ኢንሻላህ እናስተምራለን። ሚሽነሪዎች ሆይ! ዛሬ ብዙ ወደ ኢሥላም የመጡ ሺ በክንፉ ሺ በአክናፉ የተባለላቸው ኅሩያን እና ንዑዳን የከፍታቸው ምሥጢር በመተናነስ መጠየቃቸው ነውና በቅንነት ጠይቁ እንጂ እልህ አትጋቡ! ሙግት ማለት በእንካ ሰላንቲያ መጎናተል እና መጋፈር ሳይሆን ኩታ ገጠም በሆኑ አርስት ላይ አንጡራ ሙግት"metropolitan argument" ማንሸራሸር ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይወፍቃችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አምላከ አበው

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልእክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ

"አብ" ማለት "አባት" ማለት ነው፥ "አበው" የአብ ብዙ ቁጥር ሲሆን "አባቶች"ማለት ነው። እዚህ ጽሑፍ ላይ "አበው" ስል ጥንት የነበሩትን ነቢያት አብርሃምን፣ ይስሓቅን እና ያዕቆብ ወዘተ ለማመልከት ነው፥ "አምላከ አበው" ማለት "የአባቶች አምላክ" ማለት ነው።
አምላካችን አሏህ የጥንት አባቶች አምላክ ነው፥ ቁርኣን የአሏህ ንግግር ነው። አምላካችን አሏህ በሡረቱ አጥ ጧሀ ላይ "ቁርኣንን በአንተ ላይ እንድትቸገር አላወረድንም" በማለት ዐውዱ ይጀምራል፦
20፥2 ቁርኣንን በአንተ ላይ እንድትቸገር አላወረድንም፡፡ مَا أَنزَلْنَا عَلَيْكَ الْقُرْآنَ لِتَشْقَىٰ

እዚህ ዐውድ ላይ አሏህ በሁለተኝም መደብ "አንተ" የሚላቸው ተወዳጁ ነብያችንን”ﷺ” ነው፥ በመቀጠል አሏህ ለተወዳጁ ነቢያችን”ﷺ” "የሙሣም ወሬ በእርግጥ መጥቶሃል" በማለት ይናገራል፦
20፥9 የሙሣም ወሬ በእርግጥ መጥቶሃል፡፡ وَهَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ مُوسَىٰ

አሏህም ሙሣን ጠራውና "የሚወረድልህንም ነገር አዳምጥ" አለው፥ ይህ የወረደለት የአሏህ ንግግር ሲሆን ይህም የወረደው ንግግር፦ "እኔ አሏህ እኔ ነኝ፥ ከእኔ በቀር አምላክ የለምና አምልከኝ" የሚል ነው፦
20፥11 በመጣም ጊዜ «ሙሣ ሆይ» በማለት ተጠራ፡፡ فَلَمَّآ أَتَىٰهَا نُودِىَ يَٰمُوسَىٰٓ
20፥13 «እኔም መረጥኩህ፤ የሚወረድልህን አዳምጥ፡፡ وَأَنَا اخْتَرْتُكَ فَاسْتَمِعْ لِمَا يُوحَىٰ
20፥14 እኔ አሏህ እኔ ነኝ፥ ከእኔ በቀር አምላክ የለምና አምልከኝ፡፡ ሶላትንም እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡ إِنَّنِي أَنَا اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدْنِي وَأَقِمِ الصَّلَاةَ لِذِكْرِي

ሙሣን ጠርቶ "እኔ አሏህ እኔ ነኝ፥ ከእኔ በቀር አምላክ የለምና አምልከኝ" ብሎት እንደነበር ለተወዳጁ ነቢያችንን”ﷺ” በሁለተኛ መደብ የሚነግራቸው አሏህ እራሱ ስለሆነ "ከጡር ቀኝ ጎን በኩልም ጠራነው፤ ያነጋገርነውም ሲኾን አቀረብነው" በማለት ይናገራል፦
19፥52 ከጡር ቀኝ ጎን በኩልም ጠራነው፤ ያነጋገርነውም ሲኾን አቀረብነው፡፡ وَنَٰدَيْنَٰهُ مِن جَانِبِ ٱلطُّورِ ٱلْأَيْمَنِ وَقَرَّبْنَٰهُ نَجِيًّۭا

"ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" የሚለው መገሰጫ ወደ ተወዳጁ ነቢያችን”ﷺ” የወረደ እና ከእርሳቸው በፊት በነበሩት አበው የወረደ መገሰጫ ነው፦
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልእክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ

አንዱ አምላክ የጥንት አበው አሏህ እያሉ ይጠሩ እንደነበር የዐረቢኛ ባይብል ላይ ብዙ ቦታ ተጠቅሷል። ለምሳሌ፦ አሏህ ለኢብራሂም፦ "አሏህ እኔ ነኝ" እንዳለው ተቀምጧል፦
ዘፍጥረት 5፥7 ይህችን ምድር ትወርሳት ዘንድ እንድሰጥህ ከከለዳውያን ዑር ያወጣሁህ አሏህ እኔ ነኝ" አለው።
وَقَالَ لَهُ: «أنَا هُوَ اللهُ الَّذِي أخْرَجَكَ مِنْ أُورِ الكِلْدَانِيِّينَ لِيُعْطِيكَ هَذِهِ الأرْضَ مِلْكًا.»

አሏህ ፈጣሪ ካልሆነ ለምን በዐረቢኛ ላይ "አሏህ እኔ ነኝ" እንዳለ ሰፈረ? ዐረብ ክርስቲያኖች "አሏህ" ሲሉ እውነት አሏህ የሚለው ቃል ፈጣሪን ለማመልከት ሳይገባቸው ቀርተው ነው? ለይስሐቅም አሏህ ተገለጠለት ይለናል፦
ዘፍጥረት 26፥2 አሏህ ተገለጠለት እና እንዲህ አለው፦ “ወደ ግብፅ አትውረድ፥ እኔ በምልህ ምድር ተቀመጥ እንጂ።
فَظَهَرَ اللهُ لِإسْحَاقَ وَقَالَ لَهُ: «لَا تَنْزِلْ إلَى مِصْرٍ. بَلِ امْكُثْ فِي الأرْضِ الَّتِي سَأقُولُ لَكَ عَنْهَا.

"መገለጥ" ማለት "መታወቅ" ማለት ነው፥ ለይስሐቅ "እኔ በምልህ ምድር ተቀመጥ እንጂ" እያለው የሚያናግረው አሏህ እንደሆነ መገለጹ ስህተት ነውን? አሏህ ለያዕቆብ "የአባትህ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ እኔ ነኝ" አለው፦
ዘፍጥረት 28፥13 አሏህም፦ "የአባትህ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ እኔ ነኝ" አለው።
فَقَالَ اللهُ: «أنَا إلَهُ أبِيكَ إبْرَاهِيمَ، وَإلَهُ إسْحَاقَ.

ከተወዳጁ ነቢያችን”ﷺ” በፊት አሏህ የሰበከ ከሌለ ለምን "አሏህ አለ" "እኔ አሏህ ነኝ" የሚል ቃል ባይብል ላይ ሰፈረ? አሏህ ሙሴን፦ እኔ አሏህ ነኝ" ብሎታል፦
ዘጸአት 6፥29 እርሱም ሙሴን፦ እኔ አሏህ ነኝ፤ እኔ የምነግርህን ሁሉ ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን ንገር" ብሎ ተናገረው።
قَالَ لَهُ: «أنَا اللهُ. قُلْ لِفِرعَونَ مَلِكِ مِصْرٍ كُلَّ مَا أقُولُهُ لَكَ.»

በዚህ ሙግት ስናቆራጥጣቸው "የእኛ አሏህ እና የእናንተ አሏህ ይለያያል፥ የእኛ አሏህ አንድም ሦስት ነው፤ የእናንተ አሏህ አንድ ብቻ ነው" ይሉናል። ጥሩ!
፨ አንደኛ ሁለት አሏህ በህልውና የለም፥ ስለ አሏህ ሁለት ሰዎች የተለያየ መረዳት ቢኖራቸው አሏህ ሁለት ሆኖ ሳይሆን መረዳታቸው ብቻ ይለያያል።
፨ ሁለተኛ ከክርስቲያኖች በፊት ያሉ አይሁዳውያን ወጥ በሆነ አቋም አሏህ ጥንት የነበረው የአባቶች አምላክ መሆኑን ይቀበላሉ፥ በተጨማሪም "አሏህ አንድ ብቻ ነው" ብለው ሲያምኑ በተቃራኒው "አንድም ሦስት ነው" የሚለውን ክፉኛ ይቃወማሉ።
፨ ሦስተኛ አሏህ ፈጣሪ መሆኑን ከተቀበላችሁ እና ከጥንት ነቢያት ማስተማራቸውን መቀበላችሁ "ይበል" የሚያስብል ንግግር ነው፥ አሏህ የሚለው ስም ለጣዖት አገልግሎት የዋለበት አንድም የሐራዊ ሆነ የወጋዊ ዘገባ የሌለ ሲሆን ከዚህ ጋር ተያይዞ የባዕድ አምላክ ስም ቢሆን ኖሮ ባይብል ላይ ለነቢያት አምላክ ስም አርገው አይጠቀሙም ነበር።

አምላከ አበው አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
በወንድም ተውፊቅ አል ሐበሺይ
ሡረቱል አንቢያ 21፥21-35