ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.3K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ኤጲስ ቆጶስ ማር ማሪ ኢማኑኤል ማን ናቸው?
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኤጲስ ቆጶስ ማር ማሪ ኢማኑኤል "ኢየሱስ ብቸኛ እውነተኛ አምላክ ነው፥ ከኢየሱስ ውጪ አምላክ የለም" በማለት አብ እና መንፈስ ቅዱስን በማሽቀንጠር የሰባልዮስ ትምህርት እያራመዱ ነው። "ኢየሱስ ብቸኛ እውነተኛ አምላክ ነው፥ ከኢየሱስ ውጪ አምላክ የለም" የሚል ባይብል ላይ ሽታው የለም።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom
ሸፊዕ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

32፥4 ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም እናም አማላጅም ምንም የላችሁም። አትገሰጹምን?። مَا لَكُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا شَفِيعٍ ۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُون

“ሸፊዕ” شَفِيع ማለት “አማላጅ” ማለት ሲሆን በአሏህ ፈቃድ ለሙእሚን የሚያማልዱት መላእክት፣ ነቢያት እና ሰማዕታት ናቸው። ለምሳሌ መላእክት፦
53፥26 በሰማያት ውስጥ ካለ መልአክም ብዙዎች ሊማለዱለት ለሚሻው እና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢኾን እንጅ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም፡፡ وَكَم مِّن مَّلَكٍ فِي السَّمَاوَاتِ لَا تُغْنِي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئًا إِلَّا مِن بَعْدِ أَن يَأْذَنَ اللَّهُ لِمَن يَشَاءُ وَيَرْضَىٰ
21፥28 በፊታቸው ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ያውቃል፡፡ ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም፡፡ እነርሱም እርሱን ከመፍራታቸው የተነሳ ተጨናቂዎች ናቸው፡፡ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يَشْفَعُونَ إِلَّا لِمَنِ ارْتَضَىٰ وَهُم مِّنْ خَشْيَتِهِ مُشْفِقُونَ

“ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም” የሚለው ኃይለ ቃል መላእክት ለአማንያን እንደሚያማልዱ ያሳያል፥ ሌላው አማላጆች አሏህ ቃል ኪዳን የገባላቸው ነቢያት ናቸው፦
19፥87 አልረሕማን ዘንድ ቃል ኪዳንን የያዘ ሰው ቢኾን እንጂ ማማለድን አይችሉም፡፡ لَّا يَمْلِكُونَ الشَّفَاعَةَ إِلَّا مَنِ اتَّخَذَ عِندَ الرَّحْمَـٰنِ عَهْدًا
2፥255 ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው?። مَن ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِندَهُ إِلَّا بِإِذْنِهِ
33፥7 ከነቢያትም የጠበቀ ኪዳናቸውን ከአንተም፣ ከኑሕም፣ ከኢብራሒምም፣ ከሙሳም እና ከመርየም ልጅ ከዒሳም ጋር በያዝን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከእነርሱም የከበደን ቃል ኪዳን ያዝን፡፡ وَإِذْ أَخَذْنَا مِنَ النَّبِيِّينَ مِيثَاقَهُمْ وَمِنكَ وَمِن نُّوحٍ وَإِبْرَاهِيمَ وَمُوسَىٰ وَعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ ۖ وَأَخَذْنَا مِنْهُم مِّيثَاقًا غَلِيظًا

ከላይ በግልፅና በማያሻማ መልኩ አሏህ የፈቀደለት አማላጅ እና የሚማለድለት ተመላጅ ሰው እንዳለ ተቀምጧል፦
10፥3 ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፡፡ እነሆ! አሏህ ጌታችሁ ነውና አምልኩት! አትገሰጹምን?። مَا مِن شَفِيعٍ إِلَّا مِن بَعْدِ إِذْنِهِ ۚ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ ۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ

“ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም” የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! ነገር ግን ጣዖታውያን ቁሬሾች ከአሏህ ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ያመልካሉ፥ “እነዚህም አሏህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው” ይላሉ። እነዚህም በትንሳኤ ቀን፦ “እነዚያንም እነርሱ በእናንተ ውስጥ ለአሏህ ተጋሪዎች ናቸው" የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም” ይባላሉ፦
10፥18 ከአሏህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ያመልካሉ፤ “እነዚህም አሏህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው” ይላሉ፡፡ وَيَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنفَعُهُمْ وَيَقُولُونَ هَـٰؤُلَاءِ شُفَعَاؤُنَا عِندَ اللَّهِ
6፥94 እነዚያንም እነርሱ በእናንተ ውስጥ ለአሏህ ተጋሪዎች ናቸው የምትሉዋቸውን አማላጆቻችሁን ከእናንተ ጋር አናይም፤ ግንኙነታችሁ በእርግጥ ተቋረጠ፡፡ ከእናንተም ያ "ያማልደናል" የምትሉት ጠፋ ይባላሉ፡፡ وَمَا نَرَىٰ مَعَكُمْ شُفَعَاءَكُمُ الَّذِينَ زَعَمْتُمْ أَنَّهُمْ فِيكُمْ شُرَكَاءُ ۚ لَقَد تَّقَطَّعَ بَيْنَكُمْ وَضَلَّ عَنكُم مَّا كُنتُمْ تَزْعُمُونَ
እነዚያ ጣዖታውያን በአሏህ ሌላ የሚያጋሩትን ጣዖታት፦ “አማላጆቻችን ናቸው” ይበሉ እንጂ ለእነርሱ ወደ አሏህ የሚያማልድ አማላጅ የላቸው፦
6፥51 እነዚያንም ከእርሱ ሌላ ረዳት እና አማላጅም የሌላቸው ሲኾኑ ወደ ጌታቸው መስሰብሰብን የሚፈሩትን ይጠነቀቁ ዘንድ በእርሱ በቁርኣን አስጠንቅቅ፡፡ وَأَنذِرْ بِهِ الَّذِينَ يَخَافُونَ أَن يُحْشَرُوا إِلَىٰ رَبِّهِمْ ۙ لَيْسَ لَهُم مِّن دُونِهِ وَلِيٌّ وَلَا شَفِيعٌ لَّعَلَّهُمْ يَتَّقُونَ
40፥18 ለበዳዮች ምንም ወዳጅ እና ተሰሚ አማላጅ የላቸውም፡፡ مَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ حَمِيمٍ وَلَا شَفِيعٍ يُطَاع

"ወሊይ" وَلِيٍّ ማለት "ረዳት" "ወዳጅ" ማለት ሲሆን አሏህ ወሊይ ነው፥ ከእሳት ቅጣት የሚያድን ከአሏህ ሌላ ረዳት የለም። በተጨማሪ በአሏህ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም፦
32፥4 ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም እናም አማላጅም ምንም የላችሁም። አትገሰጹምን?። مَا لَكُم مِّن دُونِهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا شَفِيعٍ ۚ أَفَلَا تَتَذَكَّرُون

“ማ ለኩም ሚን ዱኒሂ ሚን ወሊይ” مَا لَكُمْ مِنْ دُونِهِ مِنْ وَلِيٍّ ማለትም “ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም” ማለት ሲሆን ከአሏህ ውጪ በጀነት ለመጥቀምና በጀሃነም ለመቅጣት የሚችል ማንም እረዳት የላቸውም፥ “ሚን ዱኒሂ” مِنْ دُونِهِ ማለትም “ከእርሱ ሌላ” የሚለው ተሳቢ ተውላጠ ስም ከሰዋስው አንጻር አሏህ ብቻ በመጥቀምና በመጉዳት ረዳት መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። አንቀጹ ላይ፦ “ወላ ሸፊዒን” وَلَا شَفِيعٍ ማለት “እና አማላጅም የላችሁም” ማለት ሲሆን ከመጀመሪያው ሐረግ ለመለየት “ወ” وَ የሚል መስተጻምር ይጠቀማል፥ ያ ማለት “በተጨማሪም አማላጅም የላችሁም” ማለት ነው። “ማ” مَا የሚለው "ሐርፉን ነፍይ" حَرْف النَفْي በመጀመሪያው ሐረግ ላይ ገብቶ በተጨማሪ በሁለተኛው ሐረግ ላይ “ላ” لَا የሚለው ሐርፉን ነፍይ መደገሙ ጣዖታውያን ጣዖቶቻቸውን "ወደ አሏህ በማማለድ ያቀርቡናል" ብለው የሚናገሩላቸውን ጣኦታት አማላጆች አለመሆናቸውን ለማሳየት ነው። በዚህ ምክንያት “አማላጅ የላችሁም” በማለት ዘግቶታል፦
30፥13 ለእነርሱም ከሚያጋሩዋቸው አማላጆች አይኖሯቸውም። وَلَمْ يَكُن لَّهُم مِّن شُرَكَائِهِمْ شُفَعَاءُ

ስለዚህ “አማላጅም ምንም የላችሁም” ማለት “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ካልሆነ በቀር እናንተ ከምታጋሯቸው የሚያማልድ አንድም አማላጅ የለም” ማለት ነው እንጂ በአሏህ ፈቃድ የሚያማልዱ አማላጆች የሉም ማለትን አሊያም አሏህ አማላጅ ነው ማለትን አያሲዝም። ከአሏህ ሌላ ከቅጣት ሊያድናቸው የሚችል ረዳት የላቸውም፥ እንዲሁ ቅጣት እንዳይቀጡ ወደ አሏህ የሚያማልዱ አማላጅ የላቸውም ማለት ነው። ሙፈሢሮችም የፈሠሩት በዚህ መልክ እና ልክ ነው፦
36፥23 ”ከእርሱ ሌላ አማልክትን እይዛለሁን? አልረህማን በጉዳት ቢሻኝ ምልጃቸው ከእኔ ለመመለስ ምንም አትጠቅመኝም፥ አያድኑኝምም፡፡ أَأَتَّخِذُ مِن دُونِهِ آلِهَةً إِن يُرِدْنِ الرَّحْمَـٰنُ بِضُرٍّ لَّا تُغْنِ عَنِّي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئًا وَلَا يُنقِذُونِ
ተፍሢር ኢብኑ ከሲር 32፥4 "ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ረዳት የላችሁም” ማለት “እርሱ ብቻ ሉአላዊ የሁሉንም ጉዳዮች ተቆጣጣሪ፣ የሁሉም ነገር ፈጣሪ፣ ሁሉን ነገር አድራጊ ነው፤ ከእርሱ ሌላ ፈጣሪ የለም” ማለት ነው። “እናም አማላጅም ምንም የላችሁም” ማለት “ከእርሱ ፈቃድ በኋላ ቢኾን እንጂ አንድም አማላጅ የለም” ማለት ነው።
( ما لكم من دونه من ولي ولا شفيع )
أي : بل هو المالك لأزمة الأمور ، الخالق لكل شيء ، المدبر لكل شيء ، القادر على كل شيء ، فلا ولي لخلقه سواه ، ولا شفيع إلا من بعد إذنه .

"መላእክት፣ ነቢያት እና ሰማዕታት ለሙእሚን ያማልዳሉ" ማለት እና "እኛ ወደ ፍጡራን በሌሉበት መለማመን፣ መጠየቅ እና መጸለይ" ይለያያል፥ ወደ ፍጡራን በሌሉበት መለማመን፣ መጠየቅ እና መጸለይ ምልጃ ሳይሆን ሺርክ ነው። የሁሉንም ፍጥረት ልመና፣ ጥያቄ እና ጸሎት ጊዜና ቦታ ሳይወስነው ሁሉን የሚሰማ፣ ሁሉን የሚያይ እና ሁሉን የሚያውቅ የዐለማቱ ጌታ አሏህ ብቻ እና ብቻ ነው።  "አሏህ አማላጅ ከሆነ ተማላጁ ማን ነው? የሚለው የሚሽነሪዎች ቅጥፈት ውኃ በላው፥ አሏህ ተማላጅ እንጂ አማላጅ አይደለም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ግርዶ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

42፥51 ለሰውም አሏህ በራእይ ወይም ከግርዶ ወዲያ ወይም መልእክተኛን መልአክን የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን ነገር የሚያወርድለት ቢኾን እንጅ በገሃድ ሊያናግረው ተገቢው አይደለም፡፡ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና፡፡ وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ اللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِن وَرَاءِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًا فَيُوحِيَ بِإِذْنِهِ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّهُ عَلِيٌّ حَكِيمٌ

ጭሮ አዳሪ ከመሆን ይልቅ ጸብ አጫሪ መሆንን ምርጫቸው ያረጉ ክርስቲያን ሚሽነሪዎች "ጸብ በደላላ ካልሆነልን" ብለው ለገላይ በማያመች "ያዙኝ ልቀቁኝ ደግፉኝ ጣሉኝ" በማለት መፎለሉን፣ ማቅራራቱን፣ መሸለሉን፣ መፎከሩን ተያይዘውታል። "አሏህ እንደ እንስት ሒጃብ ይለብሳል" በማለት የሌለ አሻሚ ሕፀፅ"Fallacy of equivocation" ያፅፃሉ። ምሁራን "ውኃን ከጥሩ ነገርን ከሥሩ" እንደሚሉ ስለ ሒጃብ ከሥር መሠረቱ ኢንሻላህ እንመልከት!
"ሒጃብ" حِجَاب የሚለው ቃል "ሐጀበ" حَجَبَ ማለትም "ሸፈነ" "ጋረደ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መሸፈኛ"cover" "መጋረጃ"curtain" "ግርዶ"screen" ማለት ነው፥ ለምሳሌ፦ መርየም ያደረገችው መጋረጃ "ሒጃብ" حِجَاب ተብሏል፦
19፥17 ከእነርሱም "መጋረጃን" አደረገች፡፡ فَاتَّخَذَتْ مِن دُونِهِمْ حِجَابًا

እዚህ አንቀጽ ላይ "መጋረጃ" ለሚለው የገባው ቃል "ሒጃብ" حِجَاب እንደሆነ ልብ አድርግ! በተጨማሪ የጀነት ሰዎች እና የእሳት ሰዎች እንዳይገናኙ በመካከል ያለው አዕራፍ "ሒጃብ" حِجَاب ተብሏል፦
7፥46 በመካከላቸውም ግርዶሽ አለ፡፡ وَبَيْنَهُمَا حِجَابٌ

ስለዚህ "ሒጃብ" حِجَاب የሚለው ቃል እንደ ዐውዱ የተለያየ ትርጉም አለው። ለተጨማሪ ግንዛቤ እነዚህ አናቅጽ ተመልከት፦ 17፥45 38፥32 41፥5
ሌላው ሴት ልጅ የምትሰተርበት ጉፍታ "ሒጃብ" حِجَاب ተብሏል፦
33፥59 አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶችህ፣ ለሴቶች ልጆችህ እና ለምእምናን ሚስቶች ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65 ሐዲስ 312
ዑመር"ረ.ዐ." እንደተናገረው፦ "እኔ የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! ሰናይ እና እኩይ ሰዎች ወደ እርሶ ይገባሉ፥ ለምእመናን እናቶች በሒጃብ እንድታሰትራቸው አስጤናለው" አልኩኝ፥ ከዚያም አሏህ የሒጃብ አንቀጽ አወረደ"። قَالَ قَالَ عُمَرُ ـ رضى الله عنه ـ قُلْتُ يَا رَسُولَ اللَّهِ، يَدْخُلُ عَلَيْكَ الْبَرُّ وَالْفَاجِرُ، فَلَوْ أَمَرْتَ أُمَّهَاتِ الْمُؤْمِنِينَ بِالْحِجَابِ، فَأَنْزَلَ اللَّهُ آيَةَ الْحِجَابِ‏.‏

እዚህ ድረስ ከተግባባን አምላካችን አሏህ አንድን ሰው ነቢይ አርድጎ ለማስነሳት በግልጠት ከሚያናግርበት መንገድ አንዱ ከግርዶ ወዲያ ነው፦
42፥51 ለሰውም አሏህ በራእይ ወይም ከግርዶ ወዲያ ወይም መልእክተኛን መልአክን የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን ነገር የሚያወርድለት ቢኾን እንጅ በገሃድ ሊያናግረው ተገቢው አይደለም፡፡ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና፡፡ وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ اللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِن وَرَاءِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًا فَيُوحِيَ بِإِذْنِهِ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّهُ عَلِيٌّ حَكِيمٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ግርዶ" ለሚለው የገባው ቃል "ሒጃብ" حِجَاب ሲሆን አሏህን ሳያዩ በድምፅ ብቻ መስማት ነው። ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" በለይለቱል ኢሥራእ ወል ሚራጅ ጊዜ አምስት ወቅት ሶላትን ሲቀበሉ ያዩት ይህ ሒጃብ ብርሃን ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 350
አቢ ዘር እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛን”ﷺ” ጌታህን አይተከዋልን? ብዬ ጠየኳቸው። እርሳቸው፦ "ያየሁት ብርሃን ነው፥ እንዴት እርሱን ማየት እችላለው? አሉ። عَنْ أَبِي ذَرٍّ، قَالَ سَأَلْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم هَلْ رَأَيْتَ رَبَّكَ قَالَ ‏ “‏ نُورٌ أَنَّى أَرَاهُ ‏”‏ ‏.‏
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 201
አቡ ሙሣ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “አሏህ አይተኛም፥ እርሱ መተኛት አይገባውም። እርሱ ሚዛኖችን ዝቅ ያረጋል ያነሳልም፥ የእርሱ ግርዶ ብርሃን ነው። أَبِي مُوسَى، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ لاَ يَنَامُ وَلاَ يَنْبَغِي لَهُ أَنْ يَنَامَ يَخْفِضُ الْقِسْطَ وَيَرْفَعُهُ حِجَابُهُ النُّورُ

"መንጦላዕት" የሚለው የግዕዙ ቃል "አንጦልዐ" ማለትም "ጋረደ" "ሸፈነ" ከሚል ሥረወ ቃል የመጣ ሲሆን "መጋረጃ" ማለት ነው። የፈጣሪ መጋረጃ ብርሃን ነው፥ ፈጣሪ ማንም ሊቀርበው በማይችል በብርሃን መጋረጃ ይኖራል፦
መዝሙር 31፥20 በፊትህ "መጋረጃ" ከሰው ክርክር ትጋርዳቸዋለህ። תסתירם בסתר פניך מרכסי איש
መዝሙር 4፥6 በጎውን ማን ያሳየናል? የሚሉ ብዙ ናቸው። ያህዌህ ሆይ! የፊትህ "ብርሃን" በላያችን ታወቀ። רַבִּ֥ים אֹמְרִים֮ מִֽי־יַרְאֵ֪נוּ֫ טֹ֥וב נְֽסָה־עָ֭לֵינוּ אֹ֨ור פָּנֶ֬יךָ יְהוָֽה׃
1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥16 እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፥ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል። አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም።

አንድ ሰው እንኳ ያለየው እና ሊያየው የማይቻለው በብርሃን መጋረጃ ስለሚኖር ነው። ከመስማት እና ከመስማማት ይልቅ የመደናቆር እና የመጻረር አባዜ ስለተጠናወታቸው እንጂ በትውፊት እና በአዋልድ መጻሕፍት ውስጥ "ሰባቱ መንጦላይት" የሚባሉት "ሰባቱ የእሳት መጋረጃ" ሲሆኑ አምላክ በእነዚህ ሰባት የእሳት መጋረጃ የተሰወረ ነው፦
ሰይፈ ሥላሴ ዘዓርብ ቁጥር 14
"ሥላሴ "በእሳት መጋረጃ" ውስጥ የተሰወረ ነው"።
መዓዛ ቅዳሴ ምዕራፍ 1 ቁጥር 51
"በሱራፌል መካከል "የእሳት መጋረጃ" በፊቱ ጋረደ፥ አሳቡን የሚያውቅ የለም። አኳኃኑን የሚረዳ የለም፥ ስውር በሆነ መሰወሪያው እራሱን ሰወረ"።

እንግዲህ ቅንፍጥፍ በማለት ከማዛግ ይልቅ ቅልጥፍጥፍ ብላችሁ በአርምሞ እና በጥሞና ብትመረምሩ እና ብትመራመሩ የአሏህ ምሪት ለማግኘት መደንርደሪያ ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የሰው ሥጋ በባይብል

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

7፥70 የአደምንም ልጆች በእርግጥ አከበርናቸው፡፡ وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِي آدَمَ

እስራኤላውያን በሚያጠፉት ጥፋት አምላክ ቅጣቱ የወንዶች ልጆቻቸውን እና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ እንደሚበሉ ማድረግ ነበር፦
ዘሌዋውያን 26፥29 የወንዶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ፥ የሴቶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ።

"ትበላላችሁ" የሚለው ይሰመርበት! እስራኤላውያንን ጠላቶቻቸው ባስጨነቋቸው እና መከራ ባሳይዋቸው ጊዜ የሆዳቸውን ፍሬ የሆኑትን የወንዶች እና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ እንደሚበሉ ነግሯቸዋል፦
ዘዳግም 28፥53 ጠላቶችህም ከብበው ባስጨነቁህ እና መከራ ባሳዩህ ጊዜ አምላክህ እግዚአብሔር የሚሰጥህን የሆድህን ፍሬ የወንዶች እና የሴቶች ልጆችህን ሥጋ ትበላለህ።

ለእስራኤላውያን የወንዶች እና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ የሚያበላው እራሱ አምላክ እንደሆነ ይናገራል፦
ኤርምያስ 19፥9 የወንዶች እና የሴቶች ልጆቻቸውንም ሥጋ "አበላቸዋለሁ"።

"አበላቸዋለሁ" የሚለው ይሰመርበት! አምላክ የሰውን ሥጋ ለዛውም የገዛ የአብራክ ክፋል ልጅ መብላት ከመፍቀዱ አልፎ ማስበላቱ ምን ዓይነት ቅጣት ይሆን? አስበይው አምላክ በይው እስራኤላውያንን ናቸው። በዚህ ምክንያት አባቶች ልጆቻቸውን ይበላሉ ልጆችም አባቶቻቸውን ይበላሉ፦
ሕዝቅኤል 5፥10 ስለዚህ በመካከልሽ አባቶች ልጆቻቸውን "ይበላሉ" ልጆችም አባቶቻቸውን "ይበላሉ"።

ምቾት ላይ የነበረ ሰው ረሃብ ላይ የምግብ እጦት ስለሚኖር በወንድሙ፣ አቅፋውም በምትተኛ በሚስቱ እና በቀሩትም ልጆች ይቀናል፥ ከመሰሰቱ የተነሳ ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ለአንዱ አይሰጥም፦
ዘዳግም 28፥54 በአንተ ዘንድ የተለሳለሰ እና በቅምጥልነት ሁልጊዜ ይኖር የነበረ ሰው በወንድሙ፣ አቅፋውም በምትተኛ በሚስቱ እና በቀሩትም ልጆች ይቀናል።
ዘዳግም 28፥55 በደጆችህ ሁሉ ውስጥ ጠላቶችህ ከብበው ባስጨነቁህ እና መከራ ባሳዩህ ጊዜ ሌላ ነገር የቀረው የለምና ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ለአንዱ አይሰጥም።

የሆዳቸውን ፍሬ የሆኑትን የወንዶች እና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ ከማጣትም አልፈው ሴት በእግርዋ መካከል በሚወጣው በእንግዴ ልጅ ትቀናለች፦
ዘዳግም 28፥57 በወንድ እና በሴት ልጅዋም፥ በእግርዋ መካከል በሚወጣው በእንግዴ ልጅ፥ በምትወልዳቸውም ልጆች ትቀናለች።

በተግባር ልጅን ቀቅሎ መብላት የተለመደ ነገር ነበር፥ ይህንን ተግባር ኤርሚያስ በሰቆቃ ነግሮናል፦
2ኛ ነገሥት 6፥28-29 ንጉሡም፦ ምን ሆነሻል? አላት፥ እርስዋም፦ ይህች ሴት፦ "ዛሬ እንድንበላው ልጅሽን አምጪ! ነገም ልጄን እንበላለን" አለችኝ። ልጄንም ቀቅለን በላነው፥ በማግሥቱም፦ "እንድንበላው ልጅሽን አምጪ" አልኋት፤ ልጅዋንም ሸሸገችው" ብላ መለሰችለት።
ሰቆ ኤርምያስ 4፥10 ዮድ። የርኅሩኆች ሴቶች እጆች ልጆቻችውን ቀቅለዋል፥ የወገኔ ሴት ልጅ በመቀጥቀጥዋ መብል ሆኑአቸው።
ሰቆ ኤርምያስ 2፥20 ሬስ።አቤቱ፥ እይ፤ በማን ላይ እንደዚህ እንዳደረግህ ተመልከት። በውኑ ሴቶች ፍሬያቸውን፥ ያቀማጠሉአቸውን ሕፃናት ይበላሉን?
ወደ አዲስ ኪዳን ስንመጣ የሰው ሥጋ መብላት እና ደም መጠጣት ሐላል ሆኗል፦
ዮሐንስ 6፥53-54 ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም። ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። ሥጋዬ እውነተኛ መብል፡ ደሜም እውነተኛ መጠጥ፡ ነውና።

የክርስቶስ ሥጋ እና ደም ምሳሌአዊ ሳይሆን እውነተኛ መብል እና መጠጥ ነው፥ የጌታ እራት የሚባለው "እንጀራው ወደ ሥጋ እዲሁ ወይኑ ወደ ደም ይለወጣል" የሚል እምነት በካቶሊክ እና በኦርቶዶክስ ትምህርት ውስጥ አለ፦
ማቴዎስ 26፥26-28 ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና፦ “እንካችሁ፥ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው፡” አለ። ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ፦ “ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው።

ካቶሊክ "እንጀራው ወደ ሥጋ እዲሁ ወይኑ ወደ ደም በኑባሬ ደረጃ ይለወጣል" የሚል ትምህርታቸው "ትራንስ ሰብስታንቴሽን"transubstantiation" ሲባል በኦርቶዶክስ ደግሞ "እንጀራው ወደ ሥጋ እዲሁ ወይኑ ወደ ደም በተማልሎአዊ ይለወጣል" ሲባል ተማልሎአዊ ለውጥ"mystical change" ነው፥ በሁለቱም እምነት "የበቃ ሰው በከለር፣ በጣዕም፣ በይዘት ተቀይሮ ያየዋል" የሚል እምነት አላቸው። በፕሮቴስታንት ደግሞ "ኅብስቱ ከሥጋው ጋር እንዲሁ ወይኑ ከደሙ ጋር ኅብረት ብቻ አለው እንጂ አይለወጥም" የሚል ትምህርት "ኮን ሰብስታንቴሽን"Consubstantiation" ይባላል።
ይህ ውስብስብ ትምህርት የሰው ሥጋ መብላት እና ደም መጠላት ሐላል ነው" የሚል ትምህርት ነው፥ ቅሉ ግን የሰውን ሥጋ መሥዋዕት መሠዋት ሐራም ነው። 1ኛ ነገሥት 13፥1-2 2ኛ ነገሥት 23:20 ዘዳግም 18፥9-12 ተመልከት!  የሰው መሥዋት መሰዋት የዐረማዊ አሕዛብ የሚያደርጉት ርኵሰት ነው።                                                                    

አምላካችን አሏህ የሰውን ልጅ ያከበረው ፍጡር ነው፥ ሐላል ምግብ ከየብስ እና ከባሕር እንዲመገቡት የአደምን ልጆች አሏህ በየብስ እና በባሕር አሳፈራቸው። ከፈጠርናቸውም ፍጡሮች ከማዕድናት፣ ከዕጽዋት፣ ከእንስሳት በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጣቸው፦
7፥70 የአደምንም ልጆች በእርግጥ አከበርናቸው፡፡ وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِي آدَمَ
7፥70 በየብስ እና በባሕር አሳፈርናቸው፥ ከመልካሞች ሲሳዮች ሰጠናቸው፡፡ وَحَمَلْنَاهُمْ فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ وَرَزَقْنَاهُم مِّنَ الطَّيِّبَاتِ
7፥70 ከፈጠርናቸውም ፍጡሮች በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጥናቸው፡፡ وَفَضَّلْنَاهُمْ عَلَىٰ كَثِيرٍ مِّمَّنْ خَلَقْنَا تَفْضِيلًا

አምላካችን አሏህ ሰው እርስ በእርስ ሥጋውን እንዲበላላ ሐላል አላደረግም፥ ከዚያ በተቃራኒ የሰው ሥጋ መብላት ሐራም ነው፦
49፥12 ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ! አንደኛችሁ የወንድሙን ሥጋ የሞተ ኾኖ ሊበላው ይወዳልን? መብላቱን ጠላችሁት ሐሜቱንም ጥሉት፡፡ አሏህን ፍሩ! አሏህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡ وَلَا يَغْتَب بَّعْضُكُم بَعْضًا ۚ أَيُحِبُّ أَحَدُكُمْ أَن يَأْكُلَ لَحْمَ أَخِيهِ مَيْتًا فَكَرِهْتُمُوهُ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ تَوَّابٌ رَّحِيمٌ
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 106
አነሥ ኢብኑ-ማሊክ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ወደ ሰማይ በተወሰድኩኝ ጊዜ ከነሐስ የሆነ ጥፍር ኖሯቸው ፊቶቻቸውን እና ደረቶቻቸውን የሚቧጥጡ በሆኑ ሰዎች በኩል አለፍኩ። እኔም፡- "ጂብሪል ሆይ! እነማናቸው እነዚህ? ስለው፥ እርሱም፦ "እነዚህ የሰዎችን ሥጋ የሚበሉ እና ክብራቸውን የሚነኩ ናቸው" አለኝ"። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لَمَّا عُرِجَ بِي مَرَرْتُ بِقَوْمٍ لَهُمْ أَظْفَارٌ مِنْ نُحَاسٍ يَخْمِشُونَ وُجُوهَهُمْ وَصُدُورَهُمْ فَقُلْتُ مَنْ هَؤُلاَءِ يَا جِبْرِيلُ قَالَ هَؤُلاَءِ الَّذِينَ يَأْكُلُونَ لُحُومَ النَّاسِ وَيَقَعُونَ فِي أَعْرَاضِهِمْ ‏"‏

አምላካችን አሏህ ሡናን ከሚተገብሩ ሙእሚን ያድርገን! አሚን።   

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ላብ አደር

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

43፥32 ከፊላቸውም ከፊሉን ሠራተኛ አድርጎ ይይዝ ዘንድ ከፊላቸውን ከከፊሉ በላይ በደረጃዎች (በሀብት) አበለጥን፡፡ وَرَفَعْنَا بَعْضَهُمْ فَوْقَ بَعْضٍ دَرَجَاتٍ لِّيَتَّخِذَ بَعْضُهُم بَعْضًا سُخْرِيًّا

"አደር" ማለት የዕለት ለዕለት የአኗኗርን ዘይቤን ለማመልከት የሚመጣ ፈሊጣዊ አነጋር እንጂ "አዳር" ከሚለው ቃል የሚሳለጥ አይደለም፥ ለምሳሌ፦ "ሠርቶ አደር" "ወጥቶ አደር" "አርሶ አደር" "አርብቶ አደር" "ወዝ አደር" "ላብ አደር" ሲባል ይህንን ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ነው። ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ስለ ላብ አደር የሠራተኛን ዋጋ ላቡ ሳይደርቅ ክፈሉ" ብለው ነግረውናል፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 16 ቁጥር 8
ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የሠራተኛን ዋጋ ላቡ ሳይደርቅ ክፈሉ"። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُمَرَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ أَعْطُوا الأَجِيرَ أَجْرَهُ قَبْلَ أَنْ يَجِفَّ عَرَقُهُ ‏"‏ ‏.‏

አንድ አሠሪ የሠራተኛውን ላብ የማይከፍል ከሆነ አሏህ በትንሣኤ ቀን ከሚጻረራቸው ሦስት ሰዎች አንዱ ይሆናል፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 16 ቁጥር 7
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አሏህ እንዲህ ይላል፦ "እኔ በትንሣኤ ቀን የሥስት ሰዎች ተጻራሪ ነኝ፥ እኔ የማንም ተጻራሪ ከሆንኩ በትንሣኤ ቀን አሸንፈዋለሁ። በስሜ ቃል የገባ ከዚያም የሚያታልል ሰው፣ ነጻ ሰው ሸጦ ዋጋውን የሚበላ ሰው እና ሠራተኛ የሚቀጥር እና ተጠቅሞበት ከዚያም ደመወዙን የማይሰጥ ሰው ነው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ ثَلاَثَةٌ أَنَا خَصْمُهُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَمَنْ كُنْتُ خَصْمَهُ خَصَمْتُهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ رَجُلٌ أَعْطَى بِي ثُمَّ غَدَرَ وَرَجُلٌ بَاعَ حُرًّا فَأَكَلَ ثَمَنَهُ وَرَجُلٌ اسْتَأْجَرَ أَجِيرًا فَاسْتَوْفَى مِنْهُ وَلَمْ يُوفِهِ أَجْرَهُ ‏"‏ ‏.‏

አምላካችን አሏህ በቅርቢቱ ሕይወት ኑሯችንን በመካከላችን አከፋሏል፥ ከፊላቸውም ከፊሉን ሠራተኛ አድርጎ ይይዝ ዘንድ ሀብትን ሰጥቶአል፦
43፥32 እነርሱ የጌታህን ችሮታ ያከፋፍላሉን? እኛ በቅርቢቱ ሕይወት ኑሯቸውን በመካከላቸው አከፋፍለናል፡፡ ከፊላቸውም ከፊሉን ሠራተኛ አድርጎ ይይዝ ዘንድ ከፊላቸውን ከከፊሉ በላይ በደረጃዎች (በሀብት) አበለጥን፡፡ የጌታህም ጸጋ ገነት ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ናት፡፡ أَهُمْ يَقْسِمُونَ رَحْمَتَ رَبِّكَ ۚ نَحْنُ قَسَمْنَا بَيْنَهُم مَّعِيشَتَهُمْ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا ۚ وَرَفَعْنَا بَعْضَهُمْ فَوْقَ بَعْضٍ دَرَجَاتٍ لِّيَتَّخِذَ بَعْضُهُم بَعْضًا سُخْرِيًّا ۗ وَرَحْمَتُ رَبِّكَ خَيْرٌ مِّمَّا يَجْمَعُونَ

የአሏህ ገነት ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ናትና ላብ አደርን በዙልም በመዞለም ጀነት ተነፍጎ አሏህ ከሚጻረረን አሏህን ፈርተን የላብ አደሩን ሐቅ መስጠት ትሩፋት አለው። ዲኒል ኢሥላም የሚያስከብረው ላብ አደርን እንጂ የላብ አደር ቀንን አይደለምና ላብ አደርን እናክብር! አምላካችን አሏህ የሰዎችን ሐቅ ከሚጠብቁ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አልሰማ አላችሁን

መምህር ዮሐንስ ጌታቸው፦ "እግዚአብሔር ዓይን፣ እጅ፣ እግር እንዳለው" በግልጽ ተናግረዋል። ይደመጥ!

እነዚህ የአካል ክፍሎች ትርጉም መስጠት ሠለስቱ ምዕት ከልክለዋል፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 19 ቁጥር 33
“ለእግዚአብሔር ዓይኖች እና ጆሮዎች እንዳሉት መጽሐፍት የተናገሩት እና የቀሩት እንዳሉት ስለ እግዚአብሔር የተነገረው ሁሉ የታመነ እውነተኛ እንደሆነ እናምናለን፥ ነገር ግን አይመረመርም አይታሰብም”።

"ሠለስቱ ምዕት" ማለት በ 325 ድኅረ ልደት በኒቂያ ጉባኤ የተሰበሰቡት 318 ሊቃውንት ናቸው፥ እነርሱ፦ "የቀሩት" ያሉት ከዓይኖች እና ከጆሮዎች ሌላ የተገለጹትን የአካል ክፍሎች ነው፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 28 ቁጥር 30
“ለእግዚአብሔር ዓይን፣ ጆሮ፣ እጅ፣ እግር እንዳለው የተነገረው ሁሉ ስለ እግዚአብሔር በከበሩ መጻሕፍት የተጻፈ ሁሉ የታመነ የተረዳ ነው፥ የተናገርነው ሁሉ አለው። ነገር ግን አይመረመርም አይታወቅም”።

እርማችሁን አውጡ! ጆሮ፣ እጅ፣ እግር እንዳለ እንቅጩን ፍርጥ አርገው ተናግረዋል። ለእግዚአብሔር እጅ፣ ጥፍር፣ እግር እንዳለው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ተናግሯል፦
መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 1 ቁጥር 62
“እግዚአብሔር እጆች እና ክንድ፣ ጥፍር እንዳለው ዕወቁ”።

በዚህ ዚሪያ ከዚህ በፊት የተጻፈ መጣጥፍ ያንብቡ፦ https://tttttt.me/Wahidcom/3501

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom
ኪርያ ላይሶን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥116 አላህም፡- «የመርየም ልጅ ዒሣ ሆይ! አንተ ለሰዎቹ፡- "እኔን እና እናቴን ከአሏህ ሌላ አማልክት አድርጋችሁ ያዙ ብለሃልን?» በሚለው ጊዜ አስታውስ ፡፡ وَإِذْ قَالَ اللَّهُ يَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ أَأَنتَ قُلْتَ لِلنَّاسِ اتَّخِذُونِي وَأُمِّيَ إِلَـٰهَيْنِ مِن دُونِ اللَّهِ

"ኩሪዮስ" κύριος ማለት "ወንድ ጌታ" "አባ ወራ" ማለት ሲሆን "ኩሪያ" κυρία ማለት ደግሞ "ሴት ጌታ" "እመቤት" ማለት ነው፥ ማርያም በኦርቶዶክስ፣ በካቶሊክ እና በአንግሊካን "ኩሪያ" κυρία ትባላለች። በአገራችን በግዕዝ "እግዚእ" ማለት "ወንድ ጌታ" "አባ ወራ" ማለት ሲሆን "እግዚእት" ማለት ደግሞ "ሴት ጌታ" "እመቤት" ማለት ነው፥ ኢየሱስን "ጌታችን" ለማለት "እግዚእነ" ሲሉ ማርያም ደግሞ "ጌታችን" ለማለት "እግዚእትነ" ይሏታል።

የአገራችን ኦርቶዶክስ ሰሙነ ሕማማት ላይ "ኪርያ ላይሶን" የሚሉት ማርያም እንጂ ኢየሱስ አይደለም።
"ኪርያ" የሚሉት "ኩሪያ" κυρία ለማለት ሲሆን "ላይሶን" የሚሉት የሚሉት ደግሞ "ኤልይሶን" ἐλέησον ነው፥ በጥቅሉ "ኩሪያ ኤልይሶን" κυρία ἐλέησον ወይም "ኪርያ ላይሶን" ማለት "ጌታችን ማሪን" ማለት ነው።
እውን ማርያምን በሌለችበት "ጌታችን ማሪን" ማለት አግባብ ነውን? ማርያምስ እንዲህ ያለ ሥልጣን እንደተሰጣት የሚያሳይ የባይብል ጥቅስ አለን? ቅሉ እና ጥቅሉ ግን ይህ ግልጽ ሺርክ ነው። ይህ አምልኮተ ማርያም ከልጇ የተገኘ ትምህርት ስላልሆነ አምላካችን አሏህ ኢየሱስን፦ "አንተ ለሰዎቹ፡- "እኔን እና እናቴን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጋችሁ ያዙ ብለሃልን? ብሎ ይጠይቀዋል፦
5፥116 አላህም፡- «የመርየም ልጅ ዒሣ ሆይ! አንተ ለሰዎቹ፡- "እኔን እና እናቴን ከአሏህ ሌላ አማልክት አድርጋችሁ ያዙ ብለሃልን?» በሚለው ጊዜ አስታውስ ፡፡ وَإِذْ قَالَ اللَّهُ يَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ أَأَنتَ قُلْتَ لِلنَّاسِ اتَّخِذُونِي وَأُمِّيَ إِلَـٰهَيْنِ مِن دُونِ اللَّهِ

እርሱም፦ "በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል ጌታዬን እና ጌታችሁን አሏህን አምልኩት ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም" በማለት መልስ ይሰጣል፦
5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል ጌታዬን እና ጌታችሁን አሏህን አምልኩት ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَا أَمَرْتَنِي بِهِ أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمْ

"አምላክ" የሚለውም ቃል "መለከ" ማለትም "አመለከ" ከሚል የግዕዝ ቃል የመጣ ሲሆን "የሚመለክ" ማለት ነው። ከሣቴ ብርሃን ተሰማ የዐማርኛ መዝገበ ቃላት (2005) ገጽ 708)

ከዚህ አንጻር ዐበይት ክርስትና ማርያምን አያመልኳትምን? እንዴታ! ድብን አርገው ያመልካሉ። አንድ ሰው ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ ያዘ ማለት ፍላጎቱን አምላኬ ብሎ ጠራ ማለት ሳይሆን ለአምላክ የሚሰጠውን የአምልኮ ክፍል ለፍላጎቱ ቅድሚያ ሰጠ ማለት ነው፦
25፥43 ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን? አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትሆናለህን? أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا

የማርያምን አምላክ አርጎ መያዝ በዚህ ሒሳብ መረዳት ይቻላል። በተመሳሳይ ጳውሎስ፦ "ሆዳቸው አምላካቸው ነው" ብሏል፦
ፊልጵስዩስ 3፥19 መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው።

ያ ማለት ማለት ሆዳቸውን "አምላኬ" ብለው ጠሩ ማለት ሳይሆን ለአምላክ የሚሰጠውን የአምልኮ ክፍል ለሆዳቸው ቅድሚያ ሰጡ ማለት ነው፥ የማርያምን አምላክ አርጎ መያዝ በዚህ ስሌት መረዳት ይቻላል።
"እግዚእ ኦ" ማለት "ጌታ ሆይ! ማለት ሲሆን "እግዚእ ኦ" ተብሎ እና "አቤቱ" ተብሎ ሁሉም አቤቱታ የሚቀርብለት አምላካችን አሏህ ብቻ እና ብቻ ነው፥ ሐጃህ የሚሞላ የምጀንበት መጀን የእርሱ ስም ብቻ ነው። በዐበይት ክርስትና አምልኮተ ማርያም የተዘፈቃችሁ ካላችሁ ሞት ሳይመጣባችሁ አሊያም የፍርዱ ቀን ከመምጣቱ በፊት ወደ አሏህ በንስሓ ተመለሱ!
አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አንዱ በኮሜንት መጥቶ፦ "ትክክለኛው "ኩሪዬ ኤልይሶን" Κύριε ἐλέησον ወይም "ኪርዬ ላይሶን" ነው፥ ትርጉሙ በወንድ አንቀጽ "ጌታችን ማረን" ማለት ስለሆነ ለኢየሱስ እንጂ ለማርያም አይደለም" በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል። ቅሉ ግን ከልጅነት እስከ ዕውቀት አብሮን ያደገው "ኪርያ ላይሶን" እየተባለ እንጂ "ኪርዬ ላይሶን" ሲባል አልሰማንም። ያያያዝኩትን ቪድዮ ስሙት!
ጠባቂዎች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

9፥116 ለእናንተም ከእርሱ በቀር ጠባቂም ረዳትም የላችሁም፡፡ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ

ማመናፈስ እና ማመቻመች የሚወዱ ሚሽነሪዎች ቀን ከሌሊት ወቃሽና ነቃሽ በመሆን ማኮሰስ እና ማራከስ ተያይዘውታል፥ የሃይማኖት ንጽጽር ላይ ያሉት ዐቃቢያነ እሥልምና ደግሞ የሚሽነሪዎችን የቆላ ሀሩር የደጋ ቁር ኢምንት እና ቀቢጽ ያክል ሳይቆጥሩ መልስ ይሰጣሉ። ከሚያንኳስሱትና ከሚያራክሱት ነገር መካከል፦ "ከአሏህ በቀር ጠባቂ የለም" ተብሎ በሌሎች አናቅጽ "መላእክት ጠባቂዎች ናቸው" መባላቸውን ነው። ይህንን የተውረግረገረገ መረዳት በሰከነ እና በሰላ አእምሮ እንየው፦
አምላካችን አሏህ ለአማንያን ጠባቂ ነው፥ ከእርሱ በቀር ጠባቂ የለም። ከእሳት ቅጣት የሚጠብቅ እርሱ ብቻ ነው፦
9፥116 ለእናንተም ከእርሱ በቀር ጠባቂም ረዳትም የላችሁም፡፡ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ
11፥113 ወደ እነዚያም ወደ በደሉት አትጠጉ፡፡ እሳት ትነካችኋለችና፡፡ ከአላህም ሌላ ጠባቂዎች የሏችሁም፡፡ ከዚያም አትረዱም፡፡ وَلَا تَرْكَنُوا إِلَى الَّذِينَ ظَلَمُوا فَتَمَسَّكُمُ النَّارُ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ اللَّهِ مِنْ أَوْلِيَاءَ ثُمَّ لَا تُنصَرُونَ

"ከአላህም ሌላ ጠባቂዎች የሏችሁም" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! እሳት እንዳይነካን ከአሏህ ሌላ ጠባቂዎች የሉም። ቅሉ ግን አምላካችን አሏህ ለሰው ከክፉ የሚጠብቁት ተተካኪዎች መላእክት አድርጓል፦
13፥11 *"ለሰው ከስተፊቱም ከኋላውም በአላህ ትዕዛዝ ከክፉ የሚጠብቁት ተተካኪዎች መላእክት አሉት"*፡፡ لَهُ مُعَقِّبَاتٌ مِّن بَيْنِ يَدَيْهِ وَمِنْ خَلْفِهِ يَحْفَظُونَهُ مِنْ أَمْرِ اللَّهِ
86፥4 *"ነፍስ ሁሉ በእርሷ ላይ ጠባቂ ያለባት እንጅ ሌላ አይደለችም"*፡፡ إِن كُلُّ نَفْسٍ لَّمَّا عَلَيْهَا حَافِظٌ
6፥61 እርሱም ከባሮቹ በላይ ሲኾን ሁሉን አሸናፊ ነው፥ በእናንተም ላይ ጠባቂዎችን ይልካል፡፡ وَهُوَ الْقَاهِرُ فَوْقَ عِبَادِهِ ۖ وَيُرْسِلُ عَلَيْكُمْ حَفَظَةً

መላእክት ጠባቂ የተባሉበት አሏህ ጠባቂ በተባለበት ሒሣብ እና ቀመር በፍጹም እንዳልሆነ እሙን እና ቅቡል ነው። ምክንያቱም “መልአክ” مَلْأَك የሚለው ቃል “ለአከ” لَأَكَ ማለትም “ላከ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ተላላኪ” ማለት ነው፥ የመለክ ብዙ ቁጥር ደግሞ “መላኢክ” مَلَائِك‎ ወይም “መላኢካህ” مَلَائِكَة‎ ነው። እነዚህ የአሏህ መላእክት የተለያየ የሥራ ድርሻ ተሰቷቸው ይጠብቃሉ፦
72፥8 ‹እኛም ሰማይን ለመድረስ ፈለግን፡፡ ብርቱ ጠባቂዎችን እና ችቦዎችንም ተሞልታ አገኘናት፡፡ وَأَنَّا لَمَسْنَا السَّمَاءَ فَوَجَدْنَاهَا مُلِئَتْ حَرَسًا شَدِيدًا وَشُهُبًا
72፥27 ከመልክተኛ ለወደደው ቢኾን እንጅ ለሌላ አይገልጽም፡፡ እርሱም ከስተፊቱም ከስተኋላውም ጠባቂዎችን ያደርግለታል፡፡ إِلَّا مَنِ ارْتَضَىٰ مِن رَّسُولٍ فَإِنَّهُ يَسْلُكُ مِن بَيْنِ يَدَيْهِ وَمِنْ خَلْفِهِ رَصَدًا
ስለዚህ አሏህ "ጠባቂ" የተባለው በራሱ የተብቃቃ እና የባሕርይ ገንዘቡ"ontological term" ሲሆን መላእክት "ጠባቂዎች" የተባሉት የጸጋ እና የሹመት ጉዳይ"functional term" ነው። አንድ ስም ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ አሳብ እና ትርጉም እንደሌለው ዕሙር እና ስሙር ነው፥ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጉም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ እሙን ነው። መታየት ያለበት ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው አሳብ፣ የአንቀጹን ምህዋር፣ አውታርና ምህዳር እንደሆነ ቅቡል ነው። ይህ እንዲገባችሁ ከባይብል አንድ ናሙና እንመልከት! ፈጣሪ ብዙ ቦታ፦ "ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም" ይላል፦
ኢሳይያስ 45፥22 እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ እኔ አምላክ ነኝና፥ "ከእኔም በቀር ሌላ የለም"። פְּנוּ־אֵלַ֥י וְהִוָּשְׁע֖וּ כָּל־אַפְסֵי־אָ֑רֶץ כִּ֥י אֲנִי־אֵ֖ל וְאֵ֥ין עֹֽוד
ዘዳግም 32፥39 አሁንም እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ፥ "ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ" እዩ!።  רְא֣וּ ׀ עַתָּ֗ה כִּ֣י אֲנִ֤י אֲנִי֙ ה֔וּא וְאֵ֥ין אֱלֹהִ֖ים עִמָּדִ֑י אֲנִ֧י אָמִ֣ית וַאֲחַיֶּ֗ה מָחַ֙צְתִּי֙ וַאֲנִ֣י אֶרְפָּ֔א וְאֵ֥ין מִיָּדִ֖י מַצִּֽיל
ኢሳይያስ 45፥5 እኔ ያህዌህ ነኝ፥ ከእኔም ሌላ ማንም የለም። "ከእኔም በቀር አምላክ የለም"። אֲנִ֤י יְהוָה֙ וְאֵ֣ין עֹ֔וד זוּלָתִ֖י אֵ֣ין אֱלֹהִ֑ים אֲאַזֶּרְךָ֖ וְלֹ֥א יְדַעְתָּֽנִי

ኢሳይያስ 45፥22 ላይ "አምላክ" ለሚለው በዕብራይስጡ የገባው ቃል "ኤል" אֵ֖ל ሲሆን "ኤሎሃ" אלוהּ ለሚለው ቃል ምጻረ-ቃል ነው፥ ዘዳግም 32፥39 እና ኢሳይያስ 45፥5 ላይ  "አምላክ" ለሚለው በዕብራይስጡ የገባው ቃል "ኤሎሂም" אלהים ሲሆን "ኤሎሃ" אלוהּ ለሚለው ቃል ብዜት ነው። ከእርሱ በቀር ኤሎሂም ከሌለ መላእክት "ኤሎሂም" אלהים ተብለዋል፦
መዝሙር 97፥7 "አማልክትም" ሁሉ ስገዱለት።  הִשְׁתַּחֲווּ־לֹ֝ו כָּל־אֱלֹהִֽים
መዝሙር 8፥5 "ከአማልክትን" እጅግ ጥቂት አሳነስኸው። וַתְּחַסְּרֵ֣הוּ מְּ֭עַט מֵאֱלֹהִ֑ים
መዝሙር 138፥1 በአማልክት" ፊት እዘምርልሃለሁ። נגד אלהים אזמרך

እነዚህ ሦስት አናቅጽ ላይ "ኤሎሂም" כֵּֽאלֹהִ֔ים የተባሉት መላክእት ስለሆኑ ግሪክ ሰፕቱጀንት እና የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ፦ "መላእክት" ብለው በግልጽ አስቀምጠዋል። ጥያቄአችን፦ "ያህዌህ ከእኔ ሌላ ኤሎሂም የለም" ካለ ዘንዳ በሌሎች ጥቅሶች መላእክት ለምን ኤሎሂም ተባሉ? አዎ መልሱ፦ "መላእክት "አማልክት" የተባሉት ፈጣሪ "አምላክ" በተባለበት ስሌት እና ቀመር አይደለም" ከሆነ እንግዲያውስ መላእክት ጠባቂ የተባሉበት አሏህ ጠባቂ በተባለበት ሒሣብ እና ቀመር በፍጹም አይደለም። ተግባባን? አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
በወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር ድረ ገጽ ላይ አዲስ የተለቀቁ 👇


1) ገደቢስነት
https://www.wahidislamicapologetics.org/ገደቢስነት/

2) የኤፍራጥስ ወንዝ
https://www.wahidislamicapologetics.org/የኤፍራጥስ-ወንዝ/

3) ሙሥሊም
https://www.wahidislamicapologetics.org/ሙሥሊም/

🌐 ወደ ድረ ገጹ ለመግባት
http://www.wahidislamicapologetics.org
ባወቀ ኖሮ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

8፥23 በውስጣቸውም ደግ መኖሩን አሏህ ባወቀ ኖሮ ባሰማቸው ነበር፡፡ ባሰማቸውም ኖሮ እነርሱ እውነትን የተው ኾነው በሸሹ ነበር፡፡ وَلَوْ عَلِمَ اللَّهُ فِيهِمْ خَيْرًا لَّأَسْمَعَهُمْ ۖ وَلَوْ أَسْمَعَهُمْ لَتَوَلَّوا وَّهُم مُّعْرِضُونَ

ኢሥላም እንደ ትቢያ በኖ እንደ ጢስ ተኖ እንዲጠፋላቸው የሚፈልጉ ሚሽነሪዎች እውነትን የመሸጥ እና የመሸቀጥ አባዜ የተጠናወታቸው ሰዎች እንጂ መስማት እና መስማማት ሞታቸው ነው። እነዚህ ባተሎ እና ዘባተሎ ሙግት የሚሟገቱ ተላላ እና ጽሉል ሰዎች "አሏህ ሁሉን ዐዋቂ አይደለም" ብለው ይህንን ጥቅስ ይጠቅሳሉ፦
8፥23 በውስጣቸውም ደግ መኖሩን አሏህ ባወቀ ኖሮ ባሰማቸው ነበር፡፡ ባሰማቸውም ኖሮ እነርሱ እውነትን የተው ኾነው በሸሹ ነበር፡፡ وَلَوْ عَلِمَ اللَّهُ فِيهِمْ خَيْرًا لَّأَسْمَعَهُمْ ۖ وَلَوْ أَسْمَعَهُمْ لَتَوَلَّوا وَّهُم مُّعْرِضُونَ

"በውስጣቸውም ደግ መኖሩን አሏህ ባወቀ ኖሮ" ማለት "አሏህ የሚያውቀው በውስጣቸው ክፉ መኖሩን ነው" ወይም "አሏህ የሚያውቀው በውስጣቸው ደግ አለመኖሩን ነው" ማለት ነው፥ ሙፈሢሮች ያስቀመጡልን "አሏህ ያላሰማቸው በውስጣቸውም ደግ አለመኖሩን ስለሚያውቅ ነው" በማለት ነው። "ለው" لَوْ የሚለው ሐርፉሽ ሸርጥ የመጣው በውስጣቸው ደግ አለመኖሩን ለማሳየት የገባ አጽንዖታዊ እና አንክሮታዊ ቃል ነው። ለምሳሌ፦ አንድ ነገርን አለመኖሩን ለማሳየት አጽንዖታዊ እና አንክሮታዊ ቃል መግባት በባይብልም የተለመደ ነው፦
ኢሳይያስ 44፥8 ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? አምባ የለም፥ ማንንም አላውቅም። הֲיֵ֤שׁ אֱלֹ֙והַּ֙ מִבַּלְעָדַ֔י וְאֵ֥ין צ֖וּר בַּל־יָדָֽעְתִּי׃

"ማንንም አላውቅም" የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! "ያዳአቲ" יָדָֽעְתִּי የሚለው ቃል "ያዳ" יָדַע ማለትም "አወቀ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "አውቃለው" ማለት ነው፥ "በል" בַּל־ የሚለው አፍራሽ ቃል ሲሆን "በል ያዳአቲ" בַּל־ יָדָֽעְתִּי ማለት "አላውቅም" ማለት ነው። "ማንንም አላውቅም" ሲል "ሁሉን ዐዋቂ" ከሚል ማንነቱ ጋር ይጋጫል? ወይስ "ማንንም አላውቅም" ሲል "አምልኮ የሚገባው አምላክ ከእኔ ውጪ የለም" ለማለት ፈልጎ ነው? አዎ! "አላውቅም" ሲል "የለም" ለማለት ከሆነ እንግዲያውስ አሏህ የሚያውቀው በውስጣቸው ክፉ መኖሩን ስለሆነ "ደግ በውስጣቸው የለም" ማለት ነው። ሌላ ምሳሌ፦
ሆሴዕ 8፥4 ለራሳቸው ነገሥታትን አነገሡ፥ ከእኔም ዘንድ አይደለም። አለቆችንም አደረጉ፥ እኔም አላወቅሁም። ለጥፋታቸውም ከብራቸውና ከወርቃቸው፤ ጣዖታትን ለራሳቸው አደረጉ። הֵ֤ם הִמְלִיכוּ֙ וְלֹ֣א מִמֶּ֔נִּי הֵשִׂ֖ירוּ וְלֹ֣א יָדָ֑עְתִּי כַּסְפָּ֣ם וּזְהָבָ֗ם עָשׂ֤וּ לָהֶם֙ עֲצַבִּ֔ים לְמַ֖עַן יִכָּרֵֽת׃

እስራኤላውያን ለራሳቸው አለቆች ሲያደርጉ ያህዌህ ስለማያውቅ "እኔም አላወቅሁም" ብሏል። "አላወቅሁም" ለሚለው የገባው ቃል "ቨሎ ያዳአቲ" וְלֹ֣א יָדָֽעְתִּי ሲሆን እርሱ ሳያውቅ እንዴት አንድ ድርጊት ይከናወናል? ሰካራም ሰው በስካር ውስጥ እያለ ሲጎስሙት ስለማይታወቀው የገባው ቃል በተመሳሳይ "በል ያዳአቲ" בַּל־ יָדָֽעְתִּי ነው፦
ምሳሌ 23፥35 መቱኝ፥ ያውም አልተሰማኝም፤
ጐሰሙኝ፥ "አላወቅሁምም"። መቼ እነሣለሁ? ደግሞ ጨምሬ እሻታለሁ ትላለህ። הִכּ֥וּנִי בַל־חָלִיתִי֮ הֲלָמ֗וּנִי בַּל־יָ֫דָ֥עְתִּי מָתַ֥י אָקִ֑יץ אֹ֝וסִ֗יף אֲבַקְשֶׁ֥נּוּ עֹֽוד׃

እንዲህ ዓይን ያስፈጠጠ እና ጥርስ ያገጠጠ ሐቅ ሲመጣ ሞንሟና እና ሸሞንሟና ከመሆን ይልቅ ተረጋግቶ የራስን መጽሐፍ መፈተሽ ይገባል! አየክ ጥቂት ኩርማ መረዳት በጥሪኝ እና በእፍኝ ቀድቶ እና ዘግኖ ማቅረብ ዕቅበተ ኢሥላም ላይ ለሚሠራ ሰው ኢምነት ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
በወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር ድረ ገጽ ላይ አዲስ የተለቀቁ 👇


1) የባሕርይ እናት
https://www.wahidislamicapologetics.org/የባሕርይ-እናት/

2)ታላቁ ገደል/

https://www.wahidislamicapologetics.org/ታላቁ-ገደል/

3) ተዋዱዕ

https://www.wahidislamicapologetics.org/ተዋዱዕ/

🌐 ወደ ድረ ገጹ ለመግባት
http://www.wahidislamicapologetics.org
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለስዕል አትሰግዱምን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

41፥37 ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ ለፀሐይና ለጨረቃ “አትስገዱ”፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው ለአሏህ “ስገዱ” ፡፡ እርሱን ብቻ “የምታመልኩ” እንደ ኾናችሁ ”ለሌላ አትስገዱ”፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُون

በግሪክ "ኢኮን" εἰκών በዕብራይስጥ “ኤሊል” אֱלִיל ማለት "ስዕል"image" ማለት ሲሆን በሰሌዳ ላይ በቀለም፣ በጠመኔ፣ በእርሳስ አለዚያም በሌላ ነገር ተስርቶ በዓይን በማየት የሚገነዘቡት የአንድ ማንነት ወይም ምንነት ምስል ነው። አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ላይ ሥዕልን እንዲህ ይገልጹታል፦
ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መጽሐፈ ሰዋሰው ወግሥ ወመዝገበ ቃላት 673
"ስዕል ማለት በቁም መልክ፣ የመልክ ጥላ፣ ንድፍ፣ አምሳል፣ ንድፍ በውኃ፣ በመጽሔት፣ በጥልፍ፣ በስፌት ወይም በቀለም በወረቀት ገዝፎ ተጽፎ ከደብር፣ ከእብን፣ ከእጽ፣ ከማዕድን ታንጦ፣ ተቀርጦ፣ ተሸልሞ፣ አጊጦ የሚታይ የሚዳሰስ ነገር ነው፡፡"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ በአንድ ትምህርቱ ላይ ዓይኑን በጨው አጥቦ "እኛ ለስዕል አንሰግድም" ብሎ ሽምጥጥ አርጎ ክዷል፥ በተግባር ለስዕል እየሰገዱ እና በትምህርታቸው ውስጥ ለስዕል መሰገድ እንዳለበት እያስተማሩ "አሞኛችሁ ዘንድ ዓይናችሁን ጨፍኑ"በማለት ተከታዩን ያሞኛል፦
ተአምረ ማርያም የዘወትር መቅድም ቁጥር 35-36 ገጽ 7
ግዕዙ፦
"ወቅድመ ስዕላ ስግዱ! ዘኢሰገደ ላቲ ይደምስስ እምቅዋሙ ወኢይትዐወቅ ዝግረ ስሙ። ወይበሉ መላእክተ ሰማይ ኲሎሙ አሜን"።

ትርጉም፦
"በስዕሏ ፊት ስገዱ! ለሥዕሏ ያልሰገደ ግን ከቆመበት ቦታ ይጥፋ! ስም አጠራሩ አይታወቅ። በሰማይ ያሉ መላእክትም ይደረግ ይሁን ይበሉ"።

"በስዕሏ ፊት ስገዱ! ለሥዕሏ ያልሰገደ ግን ከቆመበት ቦታ ይጥፋ" የሚል እያለ "እኛ ለስዕል አንሰግድም" ብሎ ማቄሉን እዛው የማያነቡትን ያቂል! በኦርቶዶክስ መምህራን "እኛ ለስዕል አንሰግድም" የሚል እንዲህ ዓይነት ለውጥ እንዴት ሊመጣ ቻለ? ሲባል መልሱ የሙሴ አምላክ ለሙሴ፦ "የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ፣ የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፣ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም” ብሎ አዞልታ፤ እንደውም መዝሙረኛው፦ "ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ ይፈሩ" ስለሚል ነው፦
ዘሌዋውያን 26፥1 እኔ ያህዌህ አምላካችሁ ነኝና ለእናንተ ”ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ”፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ።
ዘጸአት 20፥4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር ”የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፤ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም”*፤
መዝሙር 97፥7 ”ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ፥ በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ፤ መላእክቱ ሁሉ ስገዱለት።

ሰው ለሠራው የእጅ ሥራ እንዴት ይሰገዳል? በኦርቶዶክስ፣ በካቶሊክ እና በአንግሊካን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለስዕል የጸጋ ስግደት ይሰገዳል፤ ልብ አድርግ የጸጋ ስግደት ስገዱ የሚል ትእዛዝ የለም። በተቃራኒው ለተቀረጸ ምስል "አትስገድላቸው" የሚል ትእዛዝ ቢኖር እንጂ። ይህንን አስፈሪ ወንጀል እያየ ወደ ክርስትና የሚገባ ሰው ቂል ካልሆነ ወይም በጥቅማ ጥቅም አሊያም በተቃራኒ ፆታ ፍቅር መነደፍ ካልሆነ በስተቀር አይሞክረውም። ይህንን ፍርድ እያወቀ ወደ ኢሥላም የማይመጣ በእሳት የሚጫወት ነው፦
41፥37 ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ ለፀሐይና ለጨረቃ “አትስገዱ”፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው ለአሏህ “ስገዱ” ፡፡ እርሱን ብቻ “የምታመልኩ” እንደ ኾናችሁ ”ለሌላ አትስገዱ”፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُون

" እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ" የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! በኢሥላም ፈጣሪ ከሆነው ከአንዱ አምላክ ከአሏህ ውጪ የሚሰገድለት ማንነት ሆነ ምንነት የለም። ስዕል የሰው እጅ ሥራ ነው፤ ለዚህ ግዑዝ ነገር የምትሰግዱ ካላችሁ ጊዜው ሳይረፍድ ወደ አሏህ በንስሓ ተመለሱ! ከአሏህ በቀር የምትጠሯቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፤ እራሳቸውንም አይረዱምና፦
7፥197 እነዚያም ከእርሱ በቀር የምትጠሯቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፤ እራሳቸውንም አይረዱም። وَٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِهِۦ لَا يَسْتَطِيعُونَ نَصْرَكُمْ وَلَآ أَنفُسَهُمْ يَنصُرُونَ

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የሃይማኖት ንጽጽር ኮርስ

በወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር"Wahid islamic apologetics society" 13ኛ ዙር የሙቃረናህ ደርሥ!

"ሙቃረናህ" مُقَارَنَة የሚለው ቃል "ቃረነ" قَارَنَ ማለትም "አነጻጸረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ንጽጽር" ማለት ነው፥ ሙቃረናህ የሃይማኖት ንጽጽር"Comparative Religion" ሲሆን በዱኑል ኢሥላም እና እና በክርስትና መካከል ያለው የሥነ መለኮት አንድነት እና ልዩነት እየተነጻጸረ የሚቀርብበት ጥናት ነው። ደርሡ (ትምህርቱ) የሚፈጀው 7 ወር ኢንሻሏህ ሲሆን ሁለት ተርም አለው።

፨ የመጀመሪያው ተርም ዐጽመ አሳብ በፈጣሪ እሳቦት ላይ የሚያውጠነጥነው፦
1.በነገረ ሥላሴ ጥናት"Triadogy"
2.በነገረ ክርስቶስ ጥናት"Christology"
3.በነገረ ማርያም ጥናት"Mariology"
4. በነገረ መላእክት ጥናት"angelology"
5. በነገረ ምስል ጥናት"Iconlogy" ላይ ነው።

፨ የሁለተኛው ተርም ዐጽመ-አሳብ በቅዱሳን መጽሐፍት ላይ የሚያውጠነጥነው፦
1.በአህሉል ኪታብ"People of the Book"
2.በመጽሐፍት"scriptures"
3. በመጽሐፍ አጠባበቅ"preservation"
4.በመጽሐፍት ልኬት"Standardization"
5. በባይብል ግጭት"Contradiction"
6. በኦሪት"Torah"
7. በወንጌል"Gospel" ላይ ነው።

አባሪ ኮርሶች፦
1. ዐቂዳህ"creed"
2. ሥነ ምግባር"ethics"
3. ሥነ አመክንዮ"logic"
4. ሥነ ልቦና"psychology"
5. ሥነ ቋንቋ"linguistics" ናቸው።

ለመመዝገብ ከታች የተዘረዘሩት አድሚናት በውስጥ ያናግሩ!
እኅት ጀሙቲ፦ http://tttttt.me/myprophet34
ወንድም አቡ ኑዓይም፦https://tttttt.me/arhmanu
እኅት ሰላም፦ http://tttttt.me/SeuweSe
አኅት ዘሃራ፦ https://tttttt.me/Zhara_mustefa
እኅት አበባ፦ http://tttttt.me/selemtewa

ቦታ ሳይያዝ ይመዝገቡ! መልካም የትምህርት ጊዜ ይሁንልዎ!
ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!