ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
69 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ኃይል እና ጥበብ በአምላክ ዘንድ ያሉ የእርሱ ባሕርዮት ሲሆኑ እርሱ ምድርን በኃይሉ የፈጠረ፥ ዓለሙን በጥበቡ የመሠረተ ነው፦
ኢዮብ 12፥16 ኃይል እና ጥበብ በእርሱ ዘንድ ናቸው።
ኢዮብ 12፥13 በያህዌህ ዘንድ ጥበብና ኃይል አለ።
ኤርምያስ 10፥12 ምድርን በኃይሉ የፈጠረ፥ ዓለሙን በጥበቡ የመሠረተ ሰማያትንም በማስተዋሉ የዘረጋ እርሱ ነው።

ኃይል፣ ጥበብ፣ ማስተዋል ባሕርያት ናቸው። ኢየሱስ ቃል በቃል የአምላክ ጥበብ የማይሆንበት ምክንያት የጥበብ መንፈስ አርፎበታል፥ ጥበብ ሞልቶበት በጥበብ ያድግ ነበር፦
ኢሳይያስ 11፥2 የያህዌህ መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኃይል መንፈስ፥ የእውቀትና ያህዌህን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።
ሉቃስ 2፥40 ሕፃኑም አደገ፥ ጥበብም ሞልቶበት በመንፈስ ጠነከረ፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ በእርሱ ላይ ነበረ።
ሉቃስ 2፥52 ኢየሱስም ደግሞ በጥበብ እና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር።

ታዲያ ምሳሌ ላይ በጥበብ ንግግር ውስጥ ፦ "ጌታ ከሁሉ አስቀድሞ ፈጠረኝ" ለምን አለ? ሲባል አንድ ጥቅስ ለሁለት ነገር መዋሉ በባይብል አዲስ አይደለም። ለምሳሌ፦
ሆሴዕ 11፥1 እስራኤል ሕፃን በነበረ ጊዜ ወደድሁት፥ ልጄንም ከግብፅ ጠራሁት። አብዝቼ ብጠራቸው አጥብቀው ከፊቴ ራቁ፤ ለበኣሊምም ይሠዉ ነበር፥ ለተቀረጹ ምስሎችም ያጥኑ ነበር።
ዘጸአት 4፥22 ፈርዖንንም፦ ያህዌህ እንዲህ ይላል፦ "እስራኤል" የበኵር ልጄ ነው፤ ይገዛልኝ ዘንድ ልጄን ልቀቅ፡ አልሁህ፤ አንተም ትለቅቀው ዘንድ እንቢ አልህ፤ እነሆ እኔ የበኵር ልጅህን እገድላለሁ፡ ትለዋለህ።

ከግብፅ ተጠርቶ ለበኣሊም ይሠዋ የነበረ እና ለተቀረጹ ምስሎች ያጥን የነበረ የእስራኤል ሕዝብ ነው፥ "ልጄን ከግብፅ ጠራሁት" የሚለው ለእስራኤል የተነገረ ሲሆን ግን በውስጥ ታዋቂነት ለኢየሱስ ተጠቅመውበታል፦
ማቴዎስ 2፥14 እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በሌሊት ያዘና ከጌታ ዘንድ በነቢይ፦ "ልጄን ከግብፅ ጠራሁት" የተባለው እንዲፈጸም ወደ ግብፅ ሄደ፥ ሄሮድስም እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ።

"ልጄንም ከግብፅ ጠራሁት" ከሚለው በፊት እና በኃላ ያለውን ለኢየሱስ እንደማንጠቀምበት ሁሉ ከምሳሌ 8፥21-25 ካለው በፊት እና በኃላ ያለውን ለኢየሱስ አንጠቀምበትም። ኢየሱስ አሏህ ለእስራኤለም ልጆች ተአምር ያደረገው የኾነ ባሪያ እንጅ ሌላ አይደለም፦
43፥59 እርሱ በርሱ ላይ የለገስንለት ለእስራኤለም ልጆች ተአምር ያደረግነው የኾነ ባሪያ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ إِنْ هُوَ إِلَّا عَبْدٌ أَنْعَمْنَا عَلَيْهِ وَجَعَلْنَاهُ مَثَلًا لِّبَنِي إِسْرَائِيلَ

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መንፈስ "ፈጣሪ" ነውን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

40፥62 ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው፤ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፤ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ ታዲያ ከእምነት ወዴት ትመለሳላችሁ?፡፡ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ فَأَنَّىٰ تُؤْفَكُونَ

በባይብል ሁሉንም ሰው የፈጠረ አንድ አምላክ አለ፥ ይህ አንድ አምላክ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው፦
ሚልክያስ 2፥10 ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን?
ኤርምያስ 51፥19 የያዕቆብ እድል ፈንታ እንደ እነዚህ አይደለም፥ እርሱ የሁሉ ፈጣሪ ነውና፤ እስራኤልም የርስቱ ነገድ ነው፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ "ያህዌህ" ነው።

ያህዌህ አምላክ ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፥ ይህ አንድ አምላክ ሰው ያበጀውም በእጆቹ ነው፦
ዘፍጥረት 2፥7 ያህዌህ አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው።
መዝሙር 119፥73 እጆችህ ሠሩኝ አበጃጁኝም።

የያህዌህ እጆች ልክ እንደ ያህዌህ እራሳቸውን የቻሉ ማንነት ሳይሆኑ የምንነቱ መገለጫ ባሕርያት ናቸው፥ እነርሱ "ሠሩ" ስለተባሉ በስም መደብ "ሠሪዎች" እንደማይባሉ ሁሉ በተመሳሳይ ያህዌህ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስ እፍ ስላለበት እና በአፉ እስትንፋስ ስለፈጠረ የአፉ እስትንፋስ "ፈጣሪ" አይደለችም፦
ዘፍጥረት 2፥7 በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት።
ኢዮብ 33፥4 የያህዌህ መንፈስ ፈጠረችኝ፥ የሁሉን ቻዩ እስትንፋስ ሕይወት ሰጠችኝ። רֽוּחַ־אֵ֥ל עָשָׂ֑תְנִי וְנִשְׁמַ֖ת שַׁדַּ֣י תְּחַיֵּֽנִי׃

በሴት አንቀጽ "ዓሳቴኒይ" עָשָׂתְנִי ተብሎ የተቀመጠው የግሥ መደብ "ፈጠረችኝ" ማለት ነው፥ "የያህዌህ መንፈስ" ማለት "የሁሉን ቻዩ እስትንፋስ" ማለት ነው፥ እስትንፋሱ "ፈጠረች" ስለተባለ "ፈጣሪ" ከተባለች እጆቹ "ሠሩ" ስለተባሉ በስም መደብ "ፈጣሪዎች" ይባሉ ነበር። ቅሉ ግን እስትንፋስ ሆነ እጆቹ መፍጠሪያ እንጂ ፈጣሪዎች አይደሉም። ሌላ ናሙና እንመልከት፦
መዝሙር 8፥3 የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ።
መዝሙር 102፥25 ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው። וּֽמַעֲשֵׂ֖ה יָדֶ֣יךָ שָׁמָֽיִם׃

የያህዌህ ጣቶች እና እጆች ሰማያትን ስለሠሩ በስም መደብ "ፈጣሪዎች" እንደማይባሉ ሁሉ በተመሳሳይ የያህዌህ መንፈስ ስለፈጠረች "ፈጣሪ" አትባልም። ተጨማሪ ናሙና እንመልከት፦
ኢሳይያስ 48:13 እጄም ምድርን መሥርታለች ቀኜም ሰማያትን ዘርግታለች።

የያህዌህ እጅ ምድርን ስለመሠረት እና ቀኙ ሰማያትን ስለዘረጋች በስም መደብ "መሥራቾች" "ዘርጊዎች" ወይም "ፈጣሪዎች" እንደማይባሉ ሁሉ በተመሳሳይ የያህዌህ መንፈስ ስለፈጠረች "ፈጣሪ" አትባልም።
እንግዲህ የያህዌህ መንፈስ ልክ እንደ ያህዌህ ማንነት ካለው የያህዌህ እጆች፣ ጣቶች፣ ቀኙ ብዙ ማንነቶች ሊሆኑ ነው፥ ያ ደግሞ ሥላሴን ከሦስት በላይ ሊያደርግ ነው። ነገር ግን በግሥ መደብ የሚመጣ ድርጊት ባለቤቱ ያህዌህ ስለሆነ "ሠሪ" "ፈጣሪ" "መሥራች" "ዘርጊ" እርሱ ብቻ ነው እንጂ የእርሱን ባሕርይን እየሸነሸንን ማንነት አበጅተን ፈጣሪ አናረጋቸው። ለምሳሌ፦
ኢሳይያስ 1፥20 እምቢ ብትሉ ግን ብታምፁም፥ ሰይፍ ይበላችኋል፤ የያህዌህ አፍ ይህን ተናግሮአልና።
"የያህዌህ አፍ ይህን ተናግሮአል" የሚለው ይሰመርበት! የያህዌህ አፍ ስለተናገረ "ተናጋሪ" የሚለው የስም መደብ የምንጠቀመው ለያህዌህ እንጂ ለአፉ አይደለም፥ የያህዌህ ቅንዓት ያደርጋል፦
ኢሳይያስ 9፥7 የያህዌህ ቅንዓት ይህን ያደርጋል።

"የያህዌህ ቅንዓት ይህን ያደርጋል" የሚለው ይሰመርበት! የያህዌህ ቅንዓት ስላደረገ "አድራጊ" የሚለው የስም መደብ የምንጠቀመው ለያህዌህ እንጂ ለቅንዓት አይደለም፥ ሩቅ ሳንሄድ አንድ ሰው በአንደበቱ ስለሚያስተምር አስተማሪ ይባላል እንጂ አፉ "አስተማሪ" አይደለም፦
መዝሙር 37፥30 የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል፥ አንደበቱም ፍርድን ይናገራል።

አፍ ስላስተማረ "አስተማሪ" እንደማይባል እና አንደበት ስለተናገረ "ተናጋሪ" እንደማይባል ሁሉ እስትንፋስም ስለፈጠረች "ፈጣሪ" በፍጹም አትባልም፥ የሰው አፍ እና አንደበት እንደ ሰው ራሳቸውን የቻሉ ማንነቶች እንዳልሆኑ ሁሉ እስትንፋስም እንደ አምላክ ራሷን የቻለች ማንነት አይደለችም። የመጨረሻ ናሙና እንመልከት፦
ሉቃስ 11፥49 ስለዚህ ደግሞ የአምላክ ጥበብ እንዲህ አለች፦ ወደ እነርሱ ነቢያትንና ሐዋርያትን እልካለሁ፥ ከእነርሱም ይገድላሉ ያሳድዱማል።
ሲራክ 24፥3 እኔ(ጥበብ) ከልዑል "አፍ ወጣሁ" ምድርንም እንደ ጉም ሽፈንኋት።

ከአምላክ አፍ የምትወጣ የአምላክ ጥበብ ስለምትልክ "ላኪ" እንደማትባል ሁሉ እስትንፋስም ስለፈጠረች "ፈጣሪ" በፍጹም አትባልም። ዕውቀት እና ማስተዋል ከአምላክ አፍ የሚወጡ ባሕርያት ናቸው፥ በማስተዋሉ ሰማያትን አጸና እንዲሁ በእውቀቱ ቀላያት ተቀደዱ፦
ምሳሌ 2፥6 "ከ-"አፉም" ዕውቀት እና ማስተዋል "ይወጣሉ"።
ምሳሌ 3፥19 ያህዌህ በጥበብ ምድርን መሠረተ፥ በማስተዋልም ሰማያትን አጸና። በእውቀቱ ቀላያት ተቀደዱ፥ ደመናትም ጠልን ያንጠባጥባሉ።
ኤርምያስ 10፥12 ምድርን በኃይሉ የፈጠረ፥ ዓለሙን በጥበቡ የመሠረተ ሰማያትንም በማስተዋሉ የዘረጋ እርሱ ነው።

እንግዲህ እስትንፋስ ማንነት ከሆነች እጆች፣ ጣቶች፣ ቀኝ፣ አፍ፣ ጥበብ፣ ማስተዋል፣ እውቀት፣ ኃይል ስንት ማንነቶች አሉ? መፍጠሪያውን ፈጣሪ ካረግን ስንት ፈጣሪዎች አሉ? ስለዚህ እንደባይብሉ የአምላክ እስትንፋስ ልክ እንደ ዕውቀት፣ ማስተዋል፣ ጥበብ ከአፉ የምትወጣ ባሕርይ ናት፦
መዝሙር 33፥6 ሠራዊታቸውም ሁሉ "በ-"አፉ እስትንፋስ" ጸኑ። וּבְר֥וּחַ פִּ֝֗יו כָּל־צְבָאָֽם׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "እስትንፋስ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ሩሓህ" רוּחַ ሲሆን "መንፈስ" ማለት ነው፥ መንፈስ በተለያየ ጊዜ ለተለያየ ሥራ ከአፉ ወይም ከአፍንጫው የሚወጣ እስትንፋስ ከሆነ እራሱን የቻለ ማንነት እና ፈጣሪ በፍጹም አይደለም፦
ዘጸአት 15፥8 በአፍንጫህ እስትንፋስ ውኆች ተከመሩ። וּבְר֤וּחַ אַפֶּ֙יךָ֙ נֶ֣עֶרְמוּ מַ֔יִם

እዚህ አንቀጽ ላይ "እስትንፋስ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል በተመሳሳይ "ሩሓህ" רוּחַ ነው፥ አፍ እና አፍንጫ ሁለት የተለያዩ ከሆኑ ከሁለቱ የሚወጡትን እስትንፋሶች እየሸነሸንን አካላት የምንሰጥ እና "ፈጣሪዎች" የምንል ከሆነ ሥንት አካሎች እና ፈጣሪዎች ሊኖሩ ነው?
ወደ ቁርኣን ስንመጣ አምላካችን አሏህ አንድ ማንነት እና ምንነት ሲሆን የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፥ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፦
40፥62 ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው፤ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፥ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም። ታዲያ ከእምነት ወዴት ትመለሳላችሁ?፡፡ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ فَأَنَّىٰ تُؤْفَكُونَ

ክርስቲያኖች ሆይ! እንዲህ ተወሳስቦ ከሚያወዛግብ ትምህርት ወጥታችሁ አንዱን አምላክ አሏህን እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሁለት ልደት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

5፥75 የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልእክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ እናቱም በጣም እውነተኛ ናት፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ وَأُمُّهُ صِدِّيقَةٌ

"ልደት" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ጌነሲስ" γένεσις ሲሆን ሰማይ እና ምድር ምንም እንኳን የተፈጠሩ ቢሆኑም "ልደት" እንዳላቸው ተገልጿል፦
ዘፍጥረት 2፥4 የሰማይ እና የምድር “ልደት” ይህ ነው። Αὕτη ἡ βίβλος γενέσεως οὐρανοῦ καὶ γῆς,

እዚህ አንቀጽ ላይ "ልደት" ለሚለው በሰፕቱአጀንት”LXX” ላይ የገባው ቃል "ጌኔሲስ” γένεσις ሲሆን "ኦሪት ዘፍጥረት" በግዕዙ "ኦሪት ዘልደት" ይባላል፥ “ፍጥረት” እና “ልደት” በሚል ቃል ላይ ያለው መነሻ ቅጥያ “ዘ” የሚለው አገናዛቢ ዘርፍ “የ” ማለት ሲሆን “የ-ፍጥረት” ወይም “የ-ልደት” ማለት ነው። ሰማይ እና ምድር ልደት አላቸው ማለት ጅማሬ እና መነሻ አላቸው ማለት ከሆነ ኢየሱስ ልደት ስላለው ጅማሮ እና መነሾ አለው፦
ማቴዎስ 1፥18 የኢየሱስ ክርስቶስም “ልደት” እንዲህ ነበረ። Τοῦ δὲ Ἰησοῦ Χριστοῦ ἡ γένεσις οὕτως ἦν.
ሉቃስ 3፥23 ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር።

ዕድሜው ሠላሳ ዓመት የሆነው ጅማሬ እና መነሻ ስላለው ነው፥ ከዚህ ልደት ውጪ ኢየሱስ ሌላ ልደት የለውም። ነገር ግን 381 ድኅረ ልደት የተሰበሰበው የቁስጥንጥንያ ጉባኤ "ልደት ዘኢየኃልቅ" የሚባል እሳቤ አጽድቀዋል፥ "ልደት ዘኢየኃልቅ" ማለት "ዘላለማዊ ውልደት"eternal generation" ማለት ነው። ለዚህ እሳቤ ድምዳሜ ያደረሷቸውን ጥቅሳት እስቲ እንመልከት፦
ምሳሌ 8፥25 "ወዘንበለ አድባር ይተከሉ፥ ወእምቅድመ አውግር "ወለደኒ"።
ትርጉም፦ “ተራሮች ገና ሳይመሠረቱ፥ ከኮረብቶች በፊት "ወለደኝ"።

በግዕዝ "ወለደኒ" ማለት "ወለደኝ" ማለት ነው፥ አንዱ አምላክ ፆታ ስለሌለው፣ ወንድም ሴትም ስላልሆነ እና የባሕርይ መውለድ እና መወለድ ስለሌለው "ወለደኝ" ማለት "ፈጠረኝ" ማለት እንደሆነ አንድምታው እና ሃይማኖተ-አበው እንቅጩን ፍርጥ አርገው ነግረውናል፦
ምሳሌ 8፥25 አንድምታ፦ “ወለደኒ” ስለ ሥጋ “ፈጠረኝ” አልሁ።
ሃይማኖተ-አበው ዘባስልዮስ ምዕራፍ 32 ቁጥር 18
ግዕዙ፦ “ወለደኒ” ይተረጎም በወልደ እግዚአብሔር ወብሂለ “ፈጠረኒ” በእንተ ትስብእቱ።
ትርጉም፦ “ወለደኝ” ማለት የእግዚአብሔር ልጅ ስለመሆኑ “ፈጠረኝ” ማለት ሰው ስለ መሆኑ ይተረጎማል።

“ወለደኝ” ማለት “ፈጠረኝ” ማለት ከሆነ ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠ አብን አህሎ እና መስሎ ከአብ ያለ እናት መወለድን ሳይሆን ከድንግል ማርያም ተፈጥሮ መወለዱን ቁልጭ አርጎ የሚያሳይ ነው፥ የካርቴጁ ጡርጡሊያኖስ “ወለደኝ” ማለት “ፈጠረኝ” ማለት እንደሆነ ተናግሯል፦
"በመጀመሪያ ምድርን ከመፍጠሩ፣ ተራሮች ሳይሠሩ በፊት እኔን የመንገዱ መጀመሪያ አድርጎ ፈጠረኝ፤ ደግሞም እርሱ ከኮረብታዎች ሁሉ በፊት እኔን "ወለደኝ" ማለትም እርሱ "ፈጠረኝ" ማለት ነው"። Tertullian of Carthage (220 AD) on proverb 8:22: The Writings of Tertullian Volume II page 421]

ቀጣዩ ጥቅስ ደግሞ የዕብራይስጡ ማሶሬት፣ አብዛኛው እና አብላጫው እንግሊዝኛ ቅጂዎች እና በዐማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላይ ግን “ከንጋት ማኅፀን በቅዱስ ግርማህ ደምቀህ የጎልማሳነትህን ልምላሜ እንደ ጠል ትቀበላለህ”Arrayed in holy splendor, your youth will come to you like dew from the morning’s womb” ብለው ያስቀመጡት ሲሆን ግሪክ ሰፕቱጀንት፣ ግዕዙ እና ጥቂት የእንግሊዝኛ ትርጉም፦ "ከማኅፀን ወለድኩህ”I have begotten thee from the womb" ብለው አስቀምጠውታል፦
መዝሙር 119(110)፥3 ἐκ γαστρὸς πρὸ ἑωσφόρου ἐγέννησά σε.
ግዕዙ፦ “ወለድኩከ እም ከርሥ እምቅድመ ኮከበ ጽባሕ”
ትርጉም፦ “ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከማኅፀን ወለድኩህ”

“ከርሥ” ማለት “ማኅፀን”the womb” ማለት ሲሆን ይህ ማኅፀን የድንግል ማርያም ማኅፀን ነው፥ ስለዚህ እምድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት የተወለደበት የመጀመሪያ "ልደት" የሚባል ትምህርት የለም። በአገራችን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፣ ኦርቶዶክስ ቅብዓት፣ ኦርቶዶክስ ጸጋ፣ ኦርቶዶክስ ካራ የሚባሉ ሲኖሩ ኦርቶዶክስ ካራ "የክርስቶስ ሰዋዊ ምንነት የአብ ልጅነት ያገኘው በራሱ ቀቢነት በመቀባት ልጅነቱ ሦስተኛ ልደት ነው" ይላሉ።
የሚገርመው ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ "ማርያም አምላክን ወለደች" ከማለት አልፈው "አምላክ ለማርያም የባሕርይ ልጇ ነው፥ ማርያም ለአምላክ የባሕርይ እናቱ ናት" ይላሉ፥ የአምላክነት ባሕርይ ከሌላት ከባሕርይዋ የአምላክነት ባሕርይን ካልወሰደ የባሕርይ እናቱ እንዴት ትሆናለች?
አንድ ሰው ከወላጆቹ ዘርን ስለሚካፈል ለወላጆቹ የባሕርይ ልጅ ነው፥ ማርያም ሰው ናትና ከእርሷ የተካፈለው የሰው ባሕርይ ብቻ ስለሆነ ማርያም የሰው እናት ብቻና ብቻ ናት።

ወደ ቁርኣን ስንመጣ አምላካችን አሏህ መሢሑን ኢየሱስን በ 23 ቦታ “ኢብኑ መርየም” ابْن مَرْيَم ማለትም “የመርየም ልጅ” ይለዋል፥ ለናሙና ያክል አንድ አንቀጽ እንመልከት፦
5፥75 የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልእክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ "እናቱም" በጣም እውነተኛ ናት፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ وَأُمُّهُ صِدِّيقَةٌ

“እናቱ” የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! ልጅ የሚጠራው በአባቱ ስም "የእከሊት ልጅ" ሳይሆን "የእከሌ ልጅ" ነው፥ ነገር ግን ዒሣ አባት ስለሌለው በእናቱ ስም “የመርየም ልጅ” ይባላል። "አምላክ አምላክን ወለደ" ብላችሁ ለምታባዙ አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የጌታችን ክብር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

72፥3 ‹እነሆም የጌታችን ክብር ላቀ፡፡ ሚስትንም ልጅንም አልያዘም፡፡› وَأَنَّهُ تَعَالَىٰ جَدُّ رَبِّنَا مَا اتَّخَذَ صَاحِبَةً وَلَا وَلَدًا

ከጂን የኾኑ ጭፈሮች ቁርኣንን አዳምጠው "እኛ አስደናቂ የኾነን ቁርኣን ሰማንም" ማለታቸው ወደ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ተወርዷል፦
72፥1 በል «እነሆ ከጂን የኾኑ ጭፈሮች ቁርኣንን አዳመጡ፡፡‹እኛ አስደናቂ የኾነን ቁርኣን ሰማንም› አሉ ማለት ወደ እኔ ተወረደ፡፡ قُلْ أُوحِيَ إِلَيَّ أَنَّهُ اسْتَمَعَ نَفَرٌ مِّنَ الْجِنِّ فَقَالُوا إِنَّا سَمِعْنَا قُرْآنًا عَجَبًا

ከጂን የኾኑ ጭፈሮች ወደ ቀጥታ መንገድ የሚመራውን ቁርኣንን መስማት ብቻ ሳይሆን በቁርኣኑ አምነው በአሏህ ላይ ማንንም እንደማያጋሩ ተናግረዋል፦
72፥2 ‹ወደ ቀጥታ መንገድ የሚመራን ቁርአን ሰማን፥ በእርሱም አመንን፡፡ በጌታችንም አንድንም አናጋራም፡፡› يَهْدِي إِلَى الرُّشْدِ فَآمَنَّا بِهِ ۖ وَلَن نُّشْرِكَ بِرَبِّنَا أَحَدًا

በጌታችን አሏህ አንድነት አምነው ማንንም ሳያጋሩ ተጋሪዎች እና ልጅ ያልያዘውን ጌታቸውን አልቀዋል፦
72፥3 ‹እነሆም የጌታችን ክብር ላቀ፡፡ ሚስትንም ልጅንም አልያዘም፡፡› وَأَنَّهُ تَعَالَىٰ جَدُّ رَبِّنَا مَا اتَّخَذَ صَاحِبَةً وَلَا وَلَدًا

እዚህ አንቀጽ ላይ "ክብር" ለሚለው የገባው ቃል "ጀድ" جَدّ ሲሆን ክርስቲያን ፕሪንስ لَعْنَتَ اللَّهِ عَلَيْه ግን፦ "ጀድ" جَدّ ማለት "አያት"Grand Father" ማለት ነውና ከጂን የኾኑ ጭፈሮች "የጌታችን አያት" ብለዋል፥ ስለዚህ አሏህ አያት አለው" በማለት ያለ ዐውዱ በመቆልመም ሲቀጥፍ ይሰማል፥ ከዐውደ ንባቡ አንጻር "የጌታችን አያት ላቀ" ትርጉም አይሰጥም። በሥነ አፈታት ጥናት"hermeneutics" አንድ ዐውደ ንባብ የሚፈታው በሰጊጎት"eisegesis" ሳይሆን በፈቲሆት"exegesis" ነው፥ "ላቀ" ለሚለው የገባው የግሥ መደብ "ተዓላ" تَعَالَىٰ ሲሆን የአሏህ ዑሉው ለማሳየት ብዙ ቦታ መጥቷል፦
7፥190 አላህም ከሚያጋሩት ሁሉ "ላቀ"፡፡ فَتَعَالَى اللَّهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ
27፥63 አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ "ላቀ"፡፡ تَعَالَى اللَّهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ

"ላቀ" ለሚለው የገባው የግሥ መደብ "ተዓላ" تَعَالَىٰ እንደሆነ ልብ አድርግ! "ዑሉው" عُلُوّ ማለት "ልዕልና"transcendence" ማለት ሲሆን ከሁሉ ነገር በላይ የላቀው አሏህ ብቻ ስለሆነ የላቀው የአሏህ ክብር እንጂ ከመነሾ አንድ ብቻ የሆነ አሏህ አባት፣ አያት"Grand Father" የለውም፦
112፥1 በል «እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡ قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ
112፥2 «አላህ የሁሉ መጠጊያ ነው፡፡ اللَّهُ الصَّمَدُ
112፥3 «አልወለደም፤ አልተወለደምም፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ
112፥4 «ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም፡፡» وَلَمْ يَكُن لَّهُ كُفُوًا أَحَدٌ

"አልተወለደም" ከተባለ አባት፣ አያት፣ ቅድመ አያት የለውም፥ ይህ የሁሉ መጠጊያ አምላክ የሚመስለው ቢጤ ማንም ከሌለው አባት፣ አያት፣ ቅድመ አያት የለውም።
፨ሲቀጥል አንድ ቃል ቋንቋዊ ፍቺው "መዕና ሉገዊይ" مَعْنًى لُغَوِيّ ሲባል ሸሪዓዊ ፍቺው ደግሞ "መዕና ሸርዒይ" مَعْنًى شَرْعِيّ ይባላል፥ አንድ ቃል ቋንቋዊ ፍቺው ሆነ ሸሪዓዊ ፍቺው ብዙ ትርጉም ይይዛል። ለምሳሌ፦ "ተእዊል" تَأْوِيل ማለት "መጨረሻ" ማለት ነው፦
4፥59 ይህ የተሻለ "መጨረሻውም" ያማረ ነው*፡፡ ذَٰلِكَ خَيْرٌ وَأَحْسَنُ تَأْوِيلًا
7፥53 የዛቻውን "መጨረሻ" እንጂ ሌላ አይጠባበቁም፡፡ هَلْ يَنظُرُونَ إِلَّا تَأْوِيلَهُ

እነዚህ አናቅጽ ላይ "መጨረሻ" ለሚለው ቃል የገባው ቃል "ተእዊል" تَأْوِيل መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። "ተእዊል" تَأْوِيل በሌላ ፍቺው "ትርጉም"interpretation" ማለት ነው፦
12፥6 ከንግግሮችም "ትርጉምን" ያስተምርሃል፡፡ وَيُعَلِّمُكَ مِن تَأْوِيلِ الْأَحَادِيثِ
12፥101 ጌታዬ ሆይ! ከንግሥና በእርግጥ ሰጠኸኝ፡፡ ከሕልሞችም "ትርጉም" አስተማርከኝ፡፡ رَبِّ قَدْ آتَيْتَنِي مِنَ الْمُلْكِ وَعَلَّمْتَنِي مِن تَأْوِيلِ الْأَحَادِيثِ
እነዚህ አናቅጽ ላይ "ትርጉም" ለሚለው ቃል የገባው ቃል "ተእዊል" تَأْوِيل መሆኑን ልብ አድርግ! አንድ ቃል ብዙ ትርጉም እንዳለው እዚህ ድረስ ከተግባባን ዘንዳ ይህ በነሕው ደርሥ "ኢሥሙል ሙሽተሪክ" ይባላል፥ "ኢሥሙል ሙሽተሪክ" اِسْم المُشْتَرِك ማለት "ተመሳሳይ ቃል ግን የተለያየ ትርጉም ያለው አሳብ"Homonym" ነው። ስለዚህ "ጀድ" جَدّ ማለት "ቀዳማይ" "ጥንታዊ" "ክብር" "ግርማ" "ሞገስ" "ገናናነት" "አያት" እና "የምር"serious" " ማለት ነው፥ ለምሳሌ፦ "ጀድ" جَدّ የሚለው ቃል "የምር"serious" በሚል ፍቺ በሐዲስ ላይ መጥቷል፦
ሚሽካቱል መሷሒብ መጽሐፍ 13, ሐዲስ 200
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ሦስቱ ነገራት የምር ይሁን የምር፥ የቀልድም ይሁን የምር ናቸው። እነርሱም ትዳር፣ ፍች እና መማለስ ናቸው"። وَعَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ: " ثَلَاثٌ جَدُّهُنَّ جَدٌّ وَهَزْلُهُنَّ جَدُّ: النِّكَاحُ وَالطَّلَاقُ وَالرِّجْعَةُ ".

እዚህ ሐዲስ ላይ "የምር" ለሚለው የገባው ቃል "ጀድ" جَدّ ሆኖ ሳለ "አያት" ብንለው ትርጉም እንደማይሰጥ ሁሉ "የጌታችን ክብር" የሚለውን "የጌታችን አያት" ብንለው ትርጉሙ አይሰጥም። ለዛ ነው በለዘብተኛ(ሐራዊ) እና በጽንፈኛ(ወጋዊ) ምሁራን የተዘጋጁ የእንግሊዝኛ የቁርኣን ትርጉም "የጌታችን ክብር" "የጌታችን ግርማ" "የጌታችን ሞገስ" "የጌታችን ገናናነት" እንጂ "የጌታችን አያት" ያላሉት።
፨ሢሠልስ ተመሳሳይ ሙግት ባይብል ላይ እንይ! በዕብራይስጥ "ሚዒን" מֵעֶה ማለት "ወገብ" ነው፦
2ኛ ሳሙኤል 7፥12 "ከወገብህ" የሚወጣውን ዘርህን ከአንተ በኋላ አስነሣለሁ። וַהֲקִימֹתִ֤י אֶֽת־זַרְעֲךָ֙ אַחֲרֶ֔יךָ אֲשֶׁ֥ר יֵצֵ֖א מִמֵּעֶ֑יךָ וַהֲכִינֹתִ֖י אֶת־מַמְלַכְתֹּֽו׃

"ወገብ" ማለት "ልብ" ማለት እንዳልሆነ ቅቡል ቢሆን ቅሉ ግን "ሚዒን" מֵעֶה የሚለው ቃል “ልብ” ማለት ነው፦
መዝሙር 40፥8 ሕግህም “በልቤ” ውስጥ ነው። חָפָ֑צְתִּי וְ֝תֹ֥ורָתְךָ֗ בְּתֹ֣וךְ מֵעָֽי׃

እዚህ አንቀጽ ላይ “ልብ” ለሚለው የገባው ቃል “ሚዒን” מֵעֶה መሆኑን ልብ አድርግ! ሌላ ምሳሌ፦ “በተን” בֶּטֶן ማለት እኮ “ሆድ” ማለት ነው፦
ዘፍጥረት 30፥2 ያዕቆብም ራሔልን ተቆጥቶ፦ በውኑ እኔ የሆድን ፍሬ በነሣሽ በእግዚአብሔር ቦታ ነኝን? አላት። וַיִּֽחַר־אַ֥ף יַעֲקֹ֖ב בְּרָחֵ֑ל וַיֹּ֗אמֶר הֲתַ֤חַת אֱלֹהִים֙ אָנֹ֔כִי אֲשֶׁר־מָנַ֥ע מִמֵּ֖ךְ פְּרִי־בָֽטֶן׃

እዚህ አንቀጽ ላይ “ሆድ” ለሚለው የገባው ቃል “በተን” בֶּטֶן ቢሆንም ሆድ ልብ ባይሆንም “በተን” בֶּטֶן "ልብ" ማለት ነው፦
ምሳሌ 22፥18 እነርሱን “በልብህ” ብትጠብቅ፥ በከንፈሮችህም ላይ የተዘጋጁ ቢሆኑ፥ የተወደደ ነገር ይሆንልሃልና። כִּֽי־נָ֭עִים כִּֽי־תִשְׁמְרֵ֣ם בְּבִטְנֶ֑ךָ יִכֹּ֥נוּ יַ֝חְדָּ֗ו עַל־שְׂפָתֶֽיךָ׃

በግሪክ ኮይኔ “ኪሊአስ” κοιλίας ማለት "ማኅፀን" ማለት ነው፦
ሉቃስ 1፥42 የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። καὶ εὐλογημένος ὁ καρπὸς τῆς κοιλίας σου.

እዚህ አንቀጽ ላይ “ማኅፀን” ለሚለው የገባው ቃል “ኪሊአስ” κοιλίας ሲሆን የሚገርመው “ልብ” ለሚለው ቃል በግሪኩ ሰፕቱአጀንት ገብቷል፦
ዕንባቆም 3፥16 እኔ ሰምቻለሁ፥ “ልቤም” ደነገጠብኝ። ἐφυλαξάμην, καὶ ἐπτοήθη ἡ κοιλία μου

እዚህ አንቀጽ ላይ “ልብ” ለሚለው የገባው ቃል “ኪሊአስ” κοιλίας ነው፥ ግን ልብ ማኅፀን አይደለም። ስለዚህ አንድ ቃል ብዙ ትርጉም ካለው እንግዲያውስ ከላይ ያለውንም ሙግት በዚህ ስሌት ተረዱት! ለመበሻሸቅ ተብሎ ቃላት መቆልመም በእሳት መጫወት ነው፥ ዋጋ ያስከፍላል። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ለምን ተፈጠርን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

51፥56 ጂኒን እና ሰውን ሊያመልኩኝ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

ጂን እና ሰው የተፈጠሩበት ዓላማ ሁሉንም የፈጠረውን አንዱን አምላክ አሏህን በብቸኝነት እንዲያመልኩት ነው፦
51፥56 ጂኒን እና ሰውን "ሊ"ያመልኩኝ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "የዕቡዱኒ" يَعْبُدُونِ በሚለው ግሥ መነሻ ቅጥያ ላይ "ሊ" لِ የምትል መስተዋድድ አለች፥ ይህቺ "ላም" ل በነሕው ሕግ "ላሙ-አት-ታዕሊል" لَام الْتَاعْلِل ትባላለች። "ታዕሊል" تَاعْلِل ማለት "ግልጽ ዓላማ" ማለት ሲሆን አሏህ ጂንን እና ሰውን የፈጠረበት ዓላማ እርሱን በብቸኝነት እንዲያመልኩት ነው፥ እያንዳንዱ ሙሐከማት ሁሉ ደግሞ ዒባዳህ ነው። "ላሙ-አት-ታዕሊል" ለመረዳት በነሕው አወቃቀር አንድ ናሙና እስቲ እንመልከት፦
28፥9 የፈርዖንም ሚስት፦ "ለ"እኔ እና "ለ"አንተ የዓይኔ መርጊያ ነው፡፡ አትግደሉት! ሊጠቅመን ወይም ልጅ አድርገን ልንይዘው ይከጀላልና» አለች፡፡ وَقَالَتِ امْرَأَتُ فِرْعَوْنَ قُرَّتُ عَيْنٍ لِّي وَلَكَ ۖ لَا تَقْتُلُوهُ عَسَىٰ أَن يَنفَعَنَا أَوْ نَتَّخِذَهُ وَلَدًا

"እኔ" እና "አንተ" ከሚለው በፊት ያለችው "ላም" ل ላሙ-አት-ታዕሊል ስትሆን ፈርዖን እና ሚስቱ ሙሣን ያነሱበት ዓላማቸው ይጠቅመናል ብለው ሊያሳድጉት እንደሆነ ታሳያለች፥ ነገር ግን አድጎ ምን እንደሚያደርግ ፍጻሜውን ዐያውቁትም፦
28፥9 እነርሱም ፍጻሜውን የማያውቁ ሆነው አነሱት፡፡ وَقَالَتِ امْرَأَتُ فِرْعَوْنَ قُرَّتُ عَيْنٍ لِّي وَلَكَ ۖ لَا تَقْتُلُوهُ عَسَىٰ أَن يَنفَعَنَا أَوْ نَتَّخِذَهُ وَلَدًا وَهُمْ لَا يَشْعُرُونَ

አምላካችን አሏህ ሁሉን ዐዋቂ በመሆኑ ፍጻሜውን ስለሚያውቅ "ለእነርሱ ጠላት እና ሐዘን ይሆን ዘንድ አነሱት" ብሎ ነገረን፦
28፥8 የፈርዖን ቤተሰቦችም መጨረሻው "ለ"እነርሱ ጠላት እና ሐዘን "ይሆን ዘንድ" አነሱት፡፡ فَٱلْتَقَطَهُۥٓ ءَالُ فِرْعَوْنَ لِيَكُونَ لَهُمْ عَدُوًّۭا وَحَزَنًا

"የኩነ" يَكُونَ በሚለው ግሥ መነሻ ቅጥያ ላይ "ሊ" لِ የምትል መስተዋድድ አለች፥ ይህቺ "ላም" ل በነሕው ሕግ "ላሙል-ዓቂባህ" لَام الْعَاقِبَة ትባላለች። "ዓቂባህ" عَاقِبَة ማለት "ፍጻሜ" ማለት ሲሆን አሏህ ፍጻሜውን በማወቁ የነገረን ንግግር ነው። በተመሳሳይ አምላካችን አሏህ ጂን እና ሰው የፈጠረበት ዓላማ እርሱን እንዲያመልኩ ሲሆን ቅሉ ግን ጂን እና ሰው በነጻ ፈቃዳቸው አሏህን መታዘዝ ሲችሉ ጀነትን በተቃራኒው ሲያምጹ ጀሃነም ይገባሉ፥ ከጂን እና ከሰው በአሏህ ላይ ስለሚያምጹት አሏህ እንዲህ ይለናል፦
7፥179 "ከ"ጂኒ እና "ከ"ሰው ብዙዎችን "ለ"ገሀነም በእርግጥ ፈጠርን፡፡ وَلَقَدْ ذَرَأْنَا لِجَهَنَّمَ كَثِيرًا مِّنَ الْجِنِّ وَالْإِنسِ
"ጀሀነም" جَهَنَّمَ በሚለው ቃል መነሻ ላይ ያለችው "ላም" ل  ላሙል-ዓቂባህ ስትሆን አሏህ ፍጻሜውን በማወቁ የነገረን ንግግር ለማመልከት የመጣች ናት። አሏህ "ሊያመልኩኝ" በሚልበት ጊዜ "ጂኒ እና ሰው" ሲል ለገሃነም በሚልበት ጊዜ ግን "ከ"ጂኒ" እና "ከ"ሰው" በማለት "ሚን" مِّن ማለትም "ከ" የሚል መስተዋድድ አስገብቷል። አንቀጹ ላይ ከጂኒ እና ከሰው ለገሃነም የዳረጋቸው ልብ እያላቸው አለማወቃቸው፣ ዓይን እያላቸው ዓለማየታቸው፣ ጆሮ እያላቸው አለመስማታቸው ነው፦
7፥179 ለእነርሱ በእርሳቸው የማያውቁባቸው ልቦች አሏቸው፣ ለእነርሱም በሳቸው የማያዩባቸው ዓይኖች አሉዋቸው፣ ለእነርሱም በሳቸው የማይሰሙባቸው ጆሮዎች አሉዋቸው፡፡ እነዚያ እንደ እንስሳዎች ናቸው፡፡ ይልቁንም እነርሱ በጣም የተሳሳቱ ናቸው፡፡ እነዚያ ዘንጊዎቹ እነርሱ ናቸው። لَهُمْ قُلُوبٌ لَّا يَفْقَهُونَ بِهَا وَلَهُمْ أَعْيُنٌ لَّا يُبْصِرُونَ بِهَا وَلَهُمْ آذَانٌ لَّا يَسْمَعُونَ بِهَا ۚ أُولَـٰئِكَ كَالْأَنْعَامِ بَلْ هُمْ أَضَلُّ ۚ أُولَـٰئِكَ هُمُ الْغَافِلُونَ

እንስሳ ውሳጣዊ ልብ፣ ዓይን፣ ጆሮ የለውም፥ እነዚህ ግን ውሳጣዊ ማመዛዘኛ እያላቸው ባለመጠቀም እንደ እንስሳ ናቸው። ሆን ብለው በመሳሳት ዘንጊዎች ናቸው፥ ከጂኒ እና ከሰው በአሏህ ላይ ያመጹትን አሏህ በጀሀነም እንደሚቀጣ ሁሉ ከጂኒ እና ከሰው አሏህን የሚፈሩት ጀነትን ይመነዳል፦
55፥45 ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? فَبِأَيِّ آلَاءِ رَبِّكُمَا تُكَذِّبَانِ
55፥46 በጌታውም ፊት መቆምን ለፈራ ሁለት ገነቶች አሉት፡፡ وَلِمَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ جَنَّتَانِ
4፥124 "ከ"ወንድ ወይም "ከ"ሴት እርሱ አማኝ ኾኖ ከበጎ ሥራዎች አንዳችን የሚሠራ እነዚያ ገነትን ይገባሉ፡፡ وَمَن يَعْمَلْ مِنَ الصَّالِحَاتِ مِن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ

ለገሃነም "ፈጠርን" የሚለው ቃል "ዘረእና" ذَرَأْنَا ሲሆን "ጀዐልና" جَعَلْنَا ማለትም "አደረግን" በሚል ይመጣል፥ ለምሳሌ፦ ሞት የሕይወት ተቃራኒ ነው። አሏህን ግን ሞትን እንደፈጠረ ይናገራል፦
67፥2 ያ የትኛችሁ ሥራው ይበልጥ ያማረ መኾኑን ሊፈትናችሁ ሞትን እና ሕይወትን የፈጠረ ነው፡፡ الَّذِي خَلَقَ الْمَوْتَ وَالْحَيَاةَ لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًا

ሰው ያልነበረበት ሁኔታ ሕይወት አልባ ሲሆን "ሙታን" ተብሏል፥ ከአለመኖር ሁኔታ ወደ መኖር መምጣትን "ሕያውን ከሙት ያወጣል" ይለዋል፦
30፥19 ሕያውን ከሙት ያወጣል፥ ሙታንም ከሕያው ያወጣል፡፡ يُخْرِجُ الْحَيَّ مِنَ الْمَيِّتِ وَيُخْرِجُ الْمَيِّتَ مِنَ الْحَيِّ
2፥28 ሙታን የነበራችሁ ስትኾኑ ሕያው ያደረጋችሁ፣ ከዚያም የሚያሞታችሁ፣ ከዚያም ሕያው የሚያደርጋችሁ ሲኾን፣ ከዚያም ወደ እርሱ የምትመለሱ ስትኾኑ በአላህ እንዴት ትክዳለችሁ? كَيْفَ تَكْفُرُونَ بِاللَّهِ وَكُنتُمْ أَمْوَاتًا فَأَحْيَاكُمْ ۖ ثُمَّ يُمِيتُكُمْ ثُمَّ يُحْيِيكُمْ ثُمَّ إِلَيْهِ تُرْجَعُونَ

ስለዚህ አሏህ "ከ"ጂኒ እና "ከ"ሰው "ለ"ገሀነም በእርግጥ አደረግን" ቢል ለገሃነም ማድረጉ ፍትሐዊ ቅጣቱ አይደለምን? በእርግጥ ከጂን እና ከሰው ዲያብሎስን የተከተለ ጀሀነም ይገባል፦
38፥85 ከአንተ እና ከእነርሱ ውስጥ ከተከተሉህ በአንድ ላይ ገሀነምን በእርግጥ እሞላታለሁ፡፡ لَأَمْلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنكَ وَمِمَّن تَبِعَكَ مِنْهُمْ أَجْمَعِينَ
32፥13 ግን ገሀነምን ከጂን እና ከሰው የተሰበሰቡ ሆነው በእርግጥ እሞላለሁ ማለት ቃሉ ከእኔ ተረጋግጧል፡፡ وَلَـٰكِنْ حَقَّ الْقَوْلُ مِنِّي لَأَمْلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنَ الْجِنَّةِ وَالنَّاسِ أَجْمَعِينَ

አሏህ ለተፈጠርንበት ዓላማ እርሱን ብቻ ለማምለክ ይርዳን! ከጀሀነም ቅጣት ይጠብቀን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ለምን ተፈጠሩ?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

51፥56 ጂኒን እና ሰውን ሊያመልኩኝ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

ጂን እና ሰው የተፈጠሩበት ዓላማ ሁሉንም የፈጠረውን አንዱን አምላክ አሏህን በብቸኝነት እንዲያመልኩት ነው። ወደ ባይብሉ ከመጣን ግን ኃጢአተኛ የተፈጠረው ለገሃነም ነው፦
ምሳሌ 16፥4 ያህዌህ ሁሉን ለእርሱ ለራሱ እንዲሁ ኅጥኣንን ደግሞ ”ለክፉ ቀን ፈጠረ። כֹּ֤ל פָּעַ֣ל יְ֭הוָה לַֽמַּעֲנֵ֑הוּ וְגַם־רָ֝שָׁ֗ע לְיֹ֣ום רָעָֽה׃

"ክፉ ቀን" ለሚለው የገባው ቃል "ዩውም ራህ" יֹ֣ום רָעָֽה ሲሆን "ዩውም" י֣וֹם በሚለው መነሻ ቅጥያ ላይ "ለ" לְ የሚል መስተዋድድ መግባቱ በራሱ ኃጥአን የተፈጠረው ለክፉ ቀን"doomsday" እንደሆነ ያሳያል፥ ይህ ክፉ ቀን የጥፋት ቀን ሲሆን ፈጣሪ ኅጥኣንን በገሃነም የሚያጠፋበት ክፉ ቀን ነው፦
ኤርምያስ 17፥18 "ክፉንም ቀን" አምጣባቸው፥ በሁለት እጥፍ ጥፋት "አጥፋቸው"።
ማቴዎስ 10፥28 ይልቁንስ ነፍስን እና አካልን በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ። φοβεῖσθε δὲ μᾶλλον τὸν δυνάμενον καὶ ψυχὴν καὶ σῶμα ἀπολέσαι ἐν γεέννῃ.

"ኅጥኣን" ማለት "ኃጢአተኛ" ማለት ነው፥ የፍርዱ ቀን ለጻድቃን መልካም ቀን ሲሆን ለኃጥአን ክፉ ቀን ነው። የሚያፈርስን ኃጢአተኛ እንዲያጠፋ የፈጠረው እራሱ ያህዌህ ነው፥ ይህንን ያደረገው ገና እናታቸው ማኅፀን ውስጥ ሲፈጥራቸው ነው፦
ኢሳይያስ 54፥16 የሚያፈርሰውንም እንዲያጠፋ ፈጥሬአለሁ። וְאָנֹכִ֛י בָּרָ֥אתִי מַשְׁחִ֖ית לְחַבֵּֽל
መዝሙር 58፥3 ኅጥኣን ከማኅፀን ጀምረው ተለዩ፤ ከሆድም ጀምረው ሳቱ፥ ሐሰትንም ተናገሩ።

ኅጥኣን እናታቸው ማኅፀን ውስጥ ምን አንደበት ኖሯቸው ነው ሐሰትን የተናገሩት? ያኔስ ማን አሳስታቸው ነው የሳቱት? መልሳቸው ወሒድ ሆይ! ሸክላ ሠሪ ከአንዱ ጭቃ ክፍል አንዱን ዕቃ "ለ"ክብር አንዱንም "ለ"ውርደት ሊሠራ በጭቃ ላይ ሥልጣን የለውምን? የሚል ነው፦
ሮሜ 9፥21 ሸክላ ሠሪ ከአንዱ ጭቃ ክፍል አንዱን ዕቃ "ለ"ክብር አንዱንም "ለ"ውርደት ሊሠራ በጭቃ ላይ ሥልጣን የለውምን?

ስለዚህ አምላክ ሰውን ከጭቃ ሢሠራ አንዱን ለክብር ሌላውን ለውርደት ሊሠራ ሥልጣን ካለው በምን ሒሳብ ይሆን የአሏህን ንግግር ለመተቸት ሞራሉ ያላችሁ? የክርስትና አንጃ"sect" ፕሮቴስታንት ሲሆን ከፕሮቴስታንት ጎጥ"denomination" ደግሞ የካልቪኒዝም ጎጥ ለሕዱስ ሥነ-መለኮት"reformed theology" ፈር ቀዳጅ እና ፋና ወጊ ነው፥ የካልቪኒዝም መሥራች ዮሐንስ ካልቪን እንደ ጎርጎርዮሳውያን አቆጣጠር በ 1539 ድኅረ ልደት "የክርስትና ሃይማኖት ተቋማት" በሚል በጻፈው መጽሐፉ፦ "ሰዎች አንዳንዶቹ ለመዳን ሌሎች ደግሞ ለጥፋት አስቀድሞ መወሰን ተገብቷቸዋል" ብሏል፦
"ሰዎች አንዳንዶቹ ለመዳን ሌሎች ደግሞ ለጥፋት አስቀድሞ መወሰን ተገብቷቸዋል" Mankind some should be predestined to salvation and others to destruction.
The institutes of the christian religion Book 3 Chapter 21 Page 766

ግርድፍ እና ሽርክት ትርጉም ስለሆነብኝ እንግሊዝኛውን እዩት! "የሚድኑት እና የሚጠፉትን አስቀድ ወስኗል" የሚለው የካልቪን እሳቤ "ድርብ ቅድመ ውሳኔ"double predestination " ይባላል። ከካልቪን በፊት የሂፓ አውግስጢኖስ በድርብ ቅድመ ውሳኔ ያምናል፦
"ለምን እንግዲህ በምህረት ከሚያስተምረው በቀር ሁሉንም ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ አብ ሁሉንም አላስተማረም? በዚያው ልክ የማያስተምራቸውን በፍርድ አያስተምራቸውም? "እንግዲህ የሚወደውን ይምረዋል፥ የሚወደውንም ደንዳና ያደርገዋል" ሮሜ 9፥18። ነገር ግን መልካም ነገር በመስጠት ይምራል፥ ምን ያህን እንደሚገባ በሚክስ ጊዜ ያደነድናል።
On the Predestination of the Saints (Augustine) Book 1 Chapter 14

ካልቪን ሆነ አውግስጢኖስ ይህንን እሳቤ ያገኙት ከጳውሎስ ትምህርት ነው። ባይብል ላይ በመደረግ ሊጠፉ የተወሰኑ ሰዎች እንዳሉ እና እነዚህ ሰዎች "ከብዙ ጊዜ በፊት" ማለትም "ምንም ነገር ሳይፈጠር" ለፍርድ እንደተጻፉ ይናገራል፦
ቆላስይስ 2፥22 እነዚህ ሁሉ በመደረግ ሊጠፉ ተወስነዋልና።
ይሁዳ 1፥4 ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ "የተጻፉ" አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና።
መዝሙር 139፥16 ለእኔ የተወሰኑልኝ ዘመናት ገና አንዳቸውም ወደ መኖር ሳይመጡ በመጽሐፍህ ተመዘገቡ። (አዲሱ መደበኛ ትርጉም) גלמי ראו עיניך ועל ספרך כלם יכתבו ימים יצרו ולא אחד בהם׃

እዚህ አንቀጽ ላይ የአዲሱ መደበኛ ትርጉም ላይ "መጽሐፍ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል በዕብራይስጡ "ሰፈር" סֵפֶר ሲሆን ይህም መጽሐፍ ሰው ወደ መኖር ከመምጣቱ በፊት ተወስኖ የተጻፈበት መጽሐፍ ነው፥ ይህንን የአዲሱ መደበኛ ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ፦ "የሰው የሕይወት ዘመን በእግዚአብሔር የተወሰነ ነው፥ "በመጽሐፍህ" የእግዚአብሔር ውሳኔዎች ሁሉ የተጻፉበት የሰማይ መዝገብ ነው" በማለት ያትታል። የ 1954 እትም ደግሞ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ ሳይፈጠሩ በመጽሐፍ እንደተጻፉ ይናገራል፦
መዝሙር 139፥16 የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ
አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ። καὶ ἐπὶ τὸ βιβλίον σου πάντες γραφήσονται· ἡμέρας πλασθήσονται καὶ οὐθεὶς ἐν αὐτοῖς.

እዚህ አንቀጽ ላይ በግሪክ ሰፕቱአጀንት ላይ "መጽሐፍ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ቢብሊዮን" βιβλίον ነው፥ "አንድ ስንኳ ሳይኖር" ማለት "ምንም ነገር ሳይኖር" ማለት ሲሆን ምንም ነገር ሳይፈጠር የሰዎች ሁኔታ በአምላክ መጽሐፍ ተጽፏል። ይህንን ኤጲፋንዮስ በቅዳሴ ላይ፦ "ሁሉ በመጽሐፉ የተጻፈ ነው" በማለት ይናገራል፦
የኤጲፋንዮስ ቅዳሴ 14፥15 "ከእርሱ የሚሰወር የለም፣ ሁሉ በእርሱ ዘንድ የተገለጠ ነው፣ በዓይኖቹ ፊት ሁሉ የተዘረጋ ነው፣ ሁሉ በመጽሐፉ የተጻፈ ነው"።

ስለዚህ ሰዎች ለመካድ ሾልከው የገቡት ምንም ነገር ሳይፈጠር በፊት ለፍርድ የተጻፉ ስለሆኑ ነው። ክርስቲያኖች ሆይ! ውልፍጥ ዝልፍጥ ወለም ዘለም ሳትሉ ሰጥ እረጥ ለጥ ብላችሁ አንዱን አምላክ አሏህን እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አስ-ሶመድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

112፥2 አላህ የሁሉ መጠጊያ ነው፡፡ اللَّهُ الصَّمَدُ

ነቢያችን"ﷺ" ለሰዎች የሚሉትን አምላካችን አሏህ በትእዛዛዊ ግሥ "ቁል" قُلْ ማለትም "በል" በማለት ያዛቸዋል፦
112፥1 በል «እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡ قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ

አምላካችን አሏህ ስለራሱ "እርሱ" እያለ በሦስተኛ መደብ የሚናገረው አብዛኛውን ነቢያችን"ﷺ" እዲናገሩበት በሚያዝበት ጊዜ ነው፥ በመቀጠል "አላህ የሁሉ መጠጊያ ነው" በማለት ይናገራል፦
112፥2 አላህ የሁሉ መጠጊያ ነው፡፡ اللَّهُ الصَّمَدُ

"አስ-ሶመድ" الصَّمَد በቁርኣን ከተጠቀሱ የአሏህ ስሞች መካከል አንዱ ሲሆን አሏህ "የሁሉ መጠጊያ" መሆኑን የተወሰፈበት ስም ነው፥ "ሶመድ" صَّمَد የሚለው ቃል "ሶመደ" صَّمَدَ ማለትም "አስጠጋ" "አብቃቃ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የሁሉ መጠጊያ" "ተብቃቂ" ማለት ነው። ይህ ሆኖ ሳለ በአንድ ቋት ውስጥ የመፈረጅ አባዜ ያለባቸው ኩልኩሊያውያን ሚሽነሪዎች "አስ-ሶመድ" الصَّمَد የሚለውን የአሏህን ስም "ሶሙድ" صَمُود ከሚለው የጣጉት ስም ጋር ሲቀስጡ ይታያል፥ ለዚህ ቀሽም ስሑት ሙግት ይህንን ጥቅስ ይጠቅሳሉ፦
7፥70 «አላህን ብቻውን እንድናመልከው እና አባቶቻችንም ያመልኩት የነበረውን እንድንተው መጣህብን? ከእውነተኞች ከኾንክ የምታስጠነቅብንን ቅጣት አምጣብን» አሉ፡፡ قَالُوا أَجِئْتَنَا لِنَعْبُدَ اللَّهَ وَحْدَهُ وَنَذَرَ مَا كَانَ يَعْبُدُ آبَاؤُنَا ۖ فَأْتِنَا بِمَا تَعِدُنَا إِن كُنتَ مِنَ الصَّادِقِينَ
ተፍሢር ኢብኑ ከሲር 7፥70 "ሙሐመድ ኢብኑ ኢሥሐቅ እንደዘገበው፦ "የሁድ ሕዝቦች ሱዳእ፤ ሶሙድ እና ሀባእ የተባሉ የተለያዩ ጣዖታትን ያመልኩ ነበር"።

"ሶሙድ" صَمُود የሚለውን ቃል ጎትቶ እና ወትውቶ "ሶመድ" صَّمَد ከሚል ቃል ጋር እያወናበዱ መወስለት ኅሊናስ ይቀበለዋልን? እነዚህ ኮልኮሌ እና ኮበሌ ሚሽነሪዎች ሲጠቅሱ "ያረገኛል" የሚለውን ሳያስቡ "ያረግልኛል" በሚል ፈሊጥ ኢሥላምን አፈር ድሜ እና ዶግ አመድ ለማድረግ የሚቀጥፉት መቼም አይሳካላቸው፥ ስለዚህ "ሶሙድ" የተባለ ሁሉ "ሶመድ" ነው ብሎ ማሰብ አሻሚ ሕፀፅ"Fallacy of equivocation" ነው። ይህንን ተመሳሳይ ሙግት ከባይብል እንይ! "ሞለክ" מֹלֶךְ ከነዓናውያን እና አሞናውያን የሚያመልኩት ጣዖት ነው፦
አሞጽ 5፥26 ለራሳችሁም የሠራችኋቸውን ምስሎች፥ የእናንተ "ሞሎክን" ድንኳን እና የአምላካችሁን የሬፋን ኮከብ አነሣችሁ። וּנְשָׂאתֶ֗ם אֵ֚ת סִכּ֣וּת מַלְכְּכֶ֔ם וְאֵ֖ת כִּיּ֣וּן צַלְמֵיכֶ֑ם כֹּוכַב֙ אֱלֹ֣הֵיכֶ֔ם אֲשֶׁ֥ר עֲשִׂיתֶ֖ם לָכֶֽם׃
ኢሳይያስ 30፥33 ከቀድሞም ጀምሮ ቶፌት ተዘጋጅታለች፥ "ለሞለክም" ተበጅታለች"። כִּֽי־עָר֤וּךְ מֵֽאֶתְמוּל֙ תָּפְתֶּ֔ה גַּם־ הוּא כ הִ֛יא ק לַמֶּ֥לֶךְ הוּכָ֖ן הֶעְמִ֣יק

እዚህ አንቀጽ ላይ በዐማርኛ "ንጉሥ" ለሚለው የገባው ቃል “መለክ” מֶלֶךְ ሲሆን ለሞሎክ የገባ ቃል እንደሆነ ልብ አድርግ! "ሞለክ" מֹלֶךְ ሆነ “መለክ” מֶלֶךְ ትርጉማቸው አንድ ነው። ያህዌህ ደግሞ "መለክ" מֶלֶךְ ተብሏል፦
መዝሙር 74፥12 አምላክ አስቀድሞ የእኔ "መለክ” ነው። וֵ֭אלֹהִים מַלְכִּ֣י מִקֶּ֑דֶם

እናማ ያህዌህ “መለክ” מֶ֖לֶךְ ስለተባለ እና ጣዖቱ “መለክ” מֶ֖לֶךְ ስለተባለ ያህዌህ ጣዖቱ ነውን? መውጫ ቀዳዳ የላችሁም። "በኣል" בַּעַל ከነዓናውያን የመራባት አምላክ ብለው የሚያመልኩት የጣዖት ስም ነው፦
መሣፍንት 2፥13 ያህዌህን ትተው "በኣልን" እና አስታሮትን አመለኩ። וַיַּעַזְב֖וּ אֶת־יְהוָ֑ה וַיַּעַבְד֥וּ לַבַּ֖עַל וְלָעַשְׁתָּרֹֽות׃
1 ነገሥት 16፥32 በሰማርያም በሠራው በ-"በኣል" ቤት ውስጥ ለ-"በኣል" መሠዊያ አቆመ።  וַיָּ֥קֶם מִזְבֵּ֖חַ לַבָּ֑עַל בֵּ֣ית הַבַּ֔עַל אֲשֶׁ֥ר בָּנָ֖ה בְּשֹׁמְרֹֽון

ነገር ግን አሻሚ ሕፀፅ በመሥራት "በኣል" בַּעַל የሚለው ቃል ለፈጣሪ አገልግሎት ላይ ውሏል፦
ኢሳይያስ 54፥5 ፈጣሪሽ ባልሽ ነው። כִּ֤י בֹעֲלַ֙יִךְ֙ עֹשַׂ֔יִךְ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ባል" ለሚለው የገባው ቃል "በኣል" בַּעַל ነው። ስለዚህ ፈጣሪ ጣዖቱ በኣል ነው? አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ነገረ ድኅነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥103 በእሳት ጉድጓድ አፋፍም ላይ ነበራችሁ፥ ከእርስዋም አዳናችሁ፡፡ እንደዚሁ ትመሩ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾቹን ያብራራል፡፡ وَكُنتُمْ عَلَىٰ شَفَا حُفْرَةٍ مِّنَ النَّارِ فَأَنقَذَكُم مِّنْهَا ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمْ آيَاتِهِ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ

በቋንቋ ሊሒቃን ዘንድ "ድህነት" የሚለው ቃል በሃሌታው "ሀ" ሲጻፍ "ማጣት"poverty" የሚለውን ቃል የሚያሳይ ሲሆን "ድኅነት" ተብሎ በብዙኃኑ "ኀ" ሲጻፍ ደግሞ "መዳን"salvation" የሚለውን ቃል ያሳያል፥ በግሪክ ኮይኔ ደኅንነት "ሶቴሪያ" σωτηρία ይባላል። ነገረ ድኅነት"soteriology" በኢሥላም "ነጃህ" ወይም "ፈላሕ" ይባላል፥ "ነጃህ" نَّجَاة የሚለው ቃል "ነጀሐ" نَجَحَ ማለትም "ዳነ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መዳን" "ደኅነት" ማለት ነው፦
40፥41 ወገኖቼም ሆይ! ወደ "መዳን" የምጠራችሁ ስኾን ወደ እሳት የምትጠሩኝ ስትኾኑ ለእኔ ምን አለኝ? وَيَا قَوْمِ مَا لِي أَدْعُوكُمْ إِلَى النَّجَاةِ وَتَدْعُونَنِي إِلَى النَّارِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "መዳን" ለሚለው የገባው ቃል "ነጃህ" نَّجَاة እንደሆነ ልብ አድርግ! ሰው የሚድነው ከእሳት ሲሆን የአሏህን ጠሪ በመቀበል አምላካችን አሏህ ከእሳት ቅጣት ያድነናል፦
46፥31 ወገኖቻችን ሆይ! የአላህን ጠሪ ተቀበሉ፡፡ በእርሱም እመኑ፡፡ አላህ ከኀጢአቶቻችሁ ለእናንተ ይምራልና፡፡ ከአሳማሚ ቅጣትም ያድናችኋልና፡፡ يَا قَوْمَنَا أَجِيبُوا دَاعِيَ اللَّهِ وَآمِنُوا بِهِ يَغْفِرْ لَكُم مِّن ذُنُوبِكُمْ وَيُجِرْكُم مِّنْ عَذَابٍ أَلِيمٍ

"ፈላሕ" فَلَاح የሚለው ቃል "ፈለሐ" فَلَحَ ማለትም "ዳነ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መዳን" "ደኅነት" ማለት ነው፦
24፥31 ምእመናን ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ በመመለስ ተጸጸቱ። وَتُوبُوا إِلَى اللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ الْمُؤْمِنُونَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ትድኑ" ለሚለው የግሥ መደብ የገባው ቃል "ቱፍሊሑን" تُفْلِحُون ሲሆን የሥም መደቡ "ፈላሕ" فَلَاح ነው፥ ሰው ከእሳት ቅጣት የሚድነው ወደ አሏህን ንስሐ በመግባት ነው። "ተጸጸቱ" ለሚለው የገባው ቃል "ቱቡ" تُوبُوا ነው፥ "ተውባህ" تَوْبَة የሚለው ቃል "ታበ" تَابَ ማለትም "ተመለሰ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ከነበሩበት ስህተት በንስሐ ወደ አሏህ መመለስ” ማለት ነው። “ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ” لَا إِلٰهَ إِلَّا اللّٰه የሚለው ገመድ ምእመናንን በጸጋ ወንድማማቾች የሚያደርግ የአሏህ ገመድ ነው፦
3፥103 የአላህን ገመድ ሁላችሁም ያዙ፡፡ አትለያዩም፡፡ ጠበኞችም በነበራችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ የዋለውን የአላህን ጸጋ አስታውሱ! በልቦቻችሁም መካከል አስማማ፡፡ በጸጋውም ወንድማማቾች ኾናችሁ፡፡ وَاعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللَّهِ جَمِيعًا وَلَا تَفَرَّقُوا ۚ وَاذْكُرُوا نِعْمَتَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ كُنتُمْ أَعْدَاءً فَأَلَّفَ بَيْنَ قُلُوبِكُمْ فَأَصْبَحْتُم بِنِعْمَتِهِ إِخْوَانًا

ጥርት ያለው “ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ” لَا إِلٰهَ إِلَّا اللّٰه የሚለው የአሏህ ገመድ ሰዎችን በልቦቻቸው የሚያስተሳስር ነው፥ ኩፍር እና ሺርክ በእሳቱ ጉድጓድ አፋፍ ላይ ለእሳት የሚዳርጉ ሲሆኑ የአሏህ ገመድ ግን ከዚህ ከእሳት ጉድጓድ አፋፍ ተንጠልጥለን የምንድንበት ገመድ ነው፦
3፥103 በእሳት ጉድጓድ አፋፍም ላይ ነበራችሁ፥ ከእርስዋም አዳናችሁ፡፡ እንደዚሁ ትመሩ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾቹን ያብራራል፡፡ وَكُنتُمْ عَلَىٰ شَفَا حُفْرَةٍ مِّنَ النَّارِ فَأَنقَذَكُم مِّنْهَا ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمْ آيَاتِهِ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ

አንድ ሙሥሊም ይህንን ገመድ ከያዘ ከእሳት ጉድጓድ አፋፍ ተንጠልጥሎ ድኗል፥ በእርግጥ ምእመናን በዚህ ገመድ ዳኑ፦
23፥1 ምእምናን በእርግጥም "ዳኑ"። قَدْ أَفْلَحَ الْمُؤْمِنُونَ
እዚህ አንቀጽ ላይ "ዳኑ" ለሚለው የግሥ መደብ የገባው ቃል "አፍለሐ" أَفْلَحَ ሲሆን ሥርወ-ቃሉ "ፈለሐ" فَلَحَ ነው፥ ንቁ! የአላህ ሕዝቦች እነርሱ “የሚድኑት” ናቸው፦
58፥22 ንቁ! የአላህ ሕዝቦች እነርሱ “የሚድኑት” ናቸው፡፡ أَلَا إِنَّ حِزْبَ اللَّهِ هُمُ الْمُفْلِحُونَ
7፥8 ትክክለኛውም ሚዛን የዚያን ቀን ነው፡፡ ሚዛኖቻቸው የከበዱላቸው ሰዎችም እነዚያ እነርሱ “የሚድኑት” ናቸው፡፡ وَالْوَزْنُ يَوْمَئِذٍ الْحَقُّ ۚ فَمَن ثَقُلَتْ مَوَازِينُهُ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الْمُفْلِحُونَ

"የሚድኑት" ለሚለው የገባው ቃል "ሙፍሊሑን" مُفْلِحُون ሲሆን ሙፍሊሑን መልካም ሥራዎቻቸው የሚመዘንላቸው በጀነት ውስጥ ያለውን የተለያየ ደረጃ ሊመነዱ ነው፥ በተቃራኒው ኩፋሮች የሚሠሩት መልካም ሥራ ያለ ኢማን ስለሆነ ሥራዎቻቸው የሚመዘንበት ሚዛን አይቆምላቸውም፥ እነርሱም ከእሳት አይድኑም፦
18፥105 እነዚያ እነርሱ በጌታቸው ማስረጃዎችና በመገናኘቱ የካዱት ናቸው፡፡ ሥራዎቻቸውም ተበላሹ፡፡ ለእነርሱ በትንሣኤ ቀን ሚዛንን አናቆምላቸውም፡፡ أُولَـٰئِكَ الَّذِينَ كَفَرُوا بِآيَاتِ رَبِّهِمْ وَلِقَائِهِ فَحَبِطَتْ أَعْمَالُهُمْ فَلَا نُقِيمُ لَهُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَزْنًا
6፥135 እነሆ በደለኞች አይድኑም፡፡ إِنَّهُ لَا يُفْلِحُ الظَّالِمُونَ

በኢሥላም ሥነ-መለኮት ለመዳን የሰውዬው ነጻ ፈቃድና ምርጫ፣ እምነት፣ ንስሐ፣ መልካም ሥራ፣ ጽናት እና እንዲሁ የአሏህ ይቅርታ፣ ምሕረት፣ ሉዓላዊነት ስለሚያስፈልግ ደኅንነቱ የመተባበር ድኅነት"synergistic salvation" ነው፥ አንድ ሙሥሊም የአሏህን ገመድ እስከመጨረሻው በጽናት መያዝ ሲኖርበት ከለቀቀው ድኅነቱን ሊያጣ ስለሚችል ድኅነቱ ሁኔታዊ ደኅንነት"conditional salvation" ነው። “ኢሥቲቃማህ” اِسْتِقَامَة የሚለው ቃል “ኢሥቲቃመ اِسْتَقَامَ ማለትም “ቆመ” ወይም “ጸና” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ጽናት"perseverance" ማለት ነው፦
41፥30 እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉ ከዚያም "ቀጥ ያሉ" «አትፍሩ፤ አትዘኑም፤ በዚያችም ተስፋ ቃል ትደረግላችሁ በነበራችሁት ገነት ተበሰሩ» በማለት በእነርሱ ላይ መላእክት ይወርዳሉ፡፡ إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا تَتَنَزَّلُ عَلَيْهِمُ الْمَلَائِكَةُ أَلَّا تَخَافُوا وَلَا تَحْزَنُوا وَأَبْشِرُوا بِالْجَنَّةِ الَّتِي كُنتُمْ تُوعَدُون

እነዚህ አናቅጽ ላይ “ቀጥ ያሉ” ለሚለው ቃል የገባው “ኢሥተቃሙ” اسْتَقَامُوا ሲሆን "የጸኑ" ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ ጀነትን በተስፋ ዋስትና የሰጠው በዲኑል ኢሥላም ለሚጸኑ አማንያን ነው። አምላካችን አላህ ስለ ፈላሕ ተረድተው ሙፍሊሑን ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ቅጥፈት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

22፥30 ከጣዖታትም ርክሰት ተጠንቀቁ፡፡ ሐሰትንም ቃል ራቁ፡፡ فَٱجْتَنِبُوا۟ ٱلرِّجْسَ مِنَ ٱلْأَوْثَٰنِ وَٱجْتَنِبُوا۟ قَوْلَ ٱلزُّورِ

ከሥነ-ምግባር እሴት አንዱ ትክክለኛ ንግግር መናገር ነው፥ አንድ አማኝ ትክክለኛውንም ንግግር መናገር እና የሐሰትን ቃል መራቅ አለበት፦
33፥70 እናንተ ያመናችሁ ሆይ አላህን ፍሩ፤ ትክክለኛውንም ንግግር” ተናገሩ። يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَقُولُوا۟ قَوْلًۭا سَدِيدًۭا
22፥30 ከጣዖታትም ርክሰት ተጠንቀቁ፡፡ ሐሰትንም ቃል ራቁ፡፡ فَٱجْتَنِبُوا۟ ٱلرِّجْسَ مِنَ ٱلْأَوْثَٰنِ وَٱجْتَنِبُوا۟ قَوْلَ ٱلزُّورِ

“ባጢል” ْبَاطِل ማለት “ሐሰት” “ውሸት” “ቅጥፈት” ማለት ነው። እውነተኛ ሰው በማስረጃ እና በዕውቀት ይናገራል፥ ከእውነተኞችም ጎን ይቆማል፦
2፥111 እውነተኞች እንደኾናችሁ ማስረጃችሁን አምጡ በላቸው፡፡ قُلْ هَاتُوا۟ بُرْهَٰنَكُمْ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
6፥143 "እውነተኞች እንደሆናችሁ በዕውቀት ንገሩኝ" በላቸው፡፡ نَبِّـُٔونِى بِعِلْمٍ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
9፥119 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፤ ከእውነተኞቹም ጋር ኹኑ፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَكُونُوا۟ مَعَ ٱلصَّٰدِقِينَ

ሰሞኑን ዶዒፍ ሐዲስ ሳይሆን ለሚድያ ማሞቂያ ረሡል"ﷺ" ያላሉትን እንዳሉ እየተደረገ እየተቀጠፈ ይገኛል፥ ምንጭ አልባ እና ሰነድ አልባ ሐዲስ ሲነገራችሁ ፈትሹት! ማንም ሆን ብሎ በተወዳጁ ነቢይ "ﷺ" ላይ የሚቀጥፍ መቀመጫው እሳት ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 41, ሐዲስ 15
ዐብደሏህ ኢብኑ መሥዑድ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ማንም ሆን ብሎ በእኔ ላይ የሚቀጥፍ መቀመጫው እሳት ነው"። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ مَسْعُودٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ مَنْ كَذَبَ عَلَىَّ مُتَعَمِّدًا فَلْيَتَبَوَّأْ مَقْعَدَهُ مِنَ النَّارِ ‏"‏ ‏.‏

አሏህ ፈሣድ ከሚያስፋፉ ሙፍሢዲን ይጠብቀን! አሚን።

ከዐቃቢ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የተበደለው ማን ነው?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

49፥6 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነገረኛ ወሬን ቢያመጣላችሁ በስህተት ላይ ኾናችሁ ሕዝቦችን እንዳትጎዱና በሠራችሁት ነገር ላይ ተጸጸቾች እንዳትኾኑ አረጋግጡ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِن جَاءَكُمْ فَاسِقٌ بِنَبَإٍ فَتَبَيَّنُوا أَن تُصِيبُوا قَوْمًا بِجَهَالَةٍ فَتُصْبِحُوا عَلَىٰ مَا فَعَلْتُمْ نَادِمِينَ

“ዙልም” ظُلْم የሚለው ቃል “ዞለመ” ظَلَمَ ማለትም “በደለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “በደል” ማለት ነው፥ "ዙልማህ" ظُلْمَة ማለት "ጨለማ" ማለት ሲሆን በደል በፍርዱ ቀን ጨለማ ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 45, ሐዲስ 74
ጃቢር ኢብኑ ዐብደሏህ እንዳስተላለፈው፦ "የአሏህም መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "በደልን ተጠንቀቁ! በደል በትንሳኤ ቀን ጨለማ ነው"። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ اتَّقُوا الظُّلْمَ فَإِنَّ الظُّلْمَ ظُلُمَاتٌ يَوْمَ الْقِيَامَةِ

"ዙሉማት" ظُلُمَات የዙልማህ ብዙ ቁጥር ሲሆን "ጨለማዎች" ማለት ነው። አንዳንዴም አሏህ በደለኞች እዚሁ ዱንያህ ላይ ሲቀጣቸውም እናያለን፥ ይህ የሆነበት የተበዳዮች እንባ ወደ አሏህ በመረጨቱ ነው። የተበዳይ ዱዓእ ደግሞ መቅቡል ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 48, ሐዲስ 229
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሦስት ሰዎች ልመናቸው ተመላሽ አሆንም፥ እነርሱም፦ "እስኪያፈጥር ድረስ ያለ ፆመኛ፣ ፍትሐዊ መሪ እና የተበዳይ ልመና ናቸው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ ثَلاَثَةٌ لاَ تُرَدُّ دَعْوَتُهُمُ الصَّائِمُ حَتَّى يُفْطِرَ وَالإِمَامُ الْعَادِلُ وَدَعْوَةُ الْمَظْلُومِ "‏

"መዝሉም" مَظْلُوم ማለት "ተበዳይ" ማለት ሲሆን “ዟሊም” ﻇَﺎﻟِﻢ ማለት ደግሞ “በዳይ” ማለት ነው፥ አንድ ሙሥሊም መርዳት ያለበት ለተበደለው ተበዳይ በሐቅ ቆሞ ገፈትና አበሳን መታገል ሲሆን ለበደለው በዳይ ደግሞ በፍትሕ ቆሞ ጡርና ግፍ መታገል ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 46, ሐዲስ 5
አነሥ ኢብኑ”ረ.ዐ” እንደሚተረከው፦ “የአላህ መልክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ወንድምህን ተበዳይ ይሁን በዳይም እርዳው! ሶሓባዎችም፦ "የአላህ መልክተኛም”ﷺ” ሆይ! ተበዳዩን መርዳትስ ይሁን፥ በዳዩን እንዴት አድርገን ነው የምንረዳው? አሉ። እርሳቸውም፦ "ሌሎችን እንዳይጨቁን በመከላከል ነው" አሉ"። عَنْ أَنَسٍ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ انْصُرْ أَخَاكَ ظَالِمًا أَوْ مَظْلُومًا ‏"‌‏.‏ قَالُوا يَا رَسُولَ اللَّهِ هَذَا نَنْصُرُهُ مَظْلُومًا، فَكَيْفَ نَنْصُرُهُ ظَالِمًا قَالَ ‏"‏ تَأْخُذُ فَوْقَ يَدَيْهِ ‏"‌‏

ለተበደሉ ሰዎች መፍረድ ሐቀኝነት ሲሆን ለሚበድሉ ሰዎች ማልጎምጎም ብቻ ሳይሆን ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ መፋረድ ደግሞ ፍትሐዊነት ነው፥ ሰውን የሚበድሉ ሰዎች እራሳቸው የተጎዱ እና የሥነ-ልቦናቸው ዘይቤ የተዛባ ስለሆነ ሌሎችን እንዳይጨቁን ለመከላከል ምክር መስጠት፣ ተዉ ማለት፣ መገሰጽ አለብን!
ወደ ኦርቶዶክስ ጉዳይ ጉዳዩን ስመልሰው ኦርቶዶስ ተወልደን ያደግንበት ስለሆነ ውስጡን እናውቀዋለን፥ ውስጡ ያለው የዘረኝነት ክርፋት ውስጡ ያለ ወይም የነበረ ሰው ከማንም በላይ ያውቀዋል። በሁለት ጽንፎች ኃይለኛ ዋልታ ረገጥ ዘረኝነት አለ፥ "ማነው በትክክል የተበደለው" ለማለት፦
፨አንደኛ አንድ ሙሥሊም እውነቱን ለማወቅ ማረጋገጥ ይጠበቅበታል፦
49፥6 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነገረኛ ወሬን ቢያመጣላችሁ በስህተት ላይ ኾናችሁ ሕዝቦችን እንዳትጎዱና በሠራችሁት ነገር ላይ ተጸጸቾች እንዳትኾኑ አረጋግጡ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِن جَاءَكُمْ فَاسِقٌ بِنَبَإٍ فَتَبَيَّنُوا أَن تُصِيبُوا قَوْمًا بِجَهَالَةٍ فَتُصْبِحُوا عَلَىٰ مَا فَعَلْتُمْ نَادِمِينَ

የሚድያ ፓለቲከኞች እና ብሔርተኞች በሚያራግቡት አንዱ ሌላውን የማጥላላት እና ቆዳን የማዋደድ ነገር ስላለ ሙሥሊሙ እንዲህ ዓይነት ውዝግብ ውስጥ ከመግባት መቆጠብ አለበት፥ ጭራሽ ሙሥሊሙ አንዱን ጽንፍ በመደገፍ ጥቁር ፕሮፋይል ማድረግ እና ከኢቲባዕ በመውጣት "አብሬ እጦማለው" እስከማለት መድረሱ እንዲሁ ሌላውን ጽንፍ በመደገፍ ደግሞ "ሽርክ እና ኩፍር በቋንቋዬ ይሰበክልኝ" እስከማለት መድረሱ ሁለቱም ከዲን ጋር የሚላተሙ ዘረኝነት እና ሺርክ ናቸው። የአንድ ሰው እሥልምናው ማማሩ ምልክት የማይመለከተውን ነገር መተዉ ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 36, ሐዲስ 51
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የአንድ ሰው እሥልምናው ማማሩ ምልክት የማይመለከተውን ነገር መተዉ ነው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ مِنْ حُسْنِ إِسْلاَمِ الْمَرْءِ تَرْكُهُ مَا لاَ يَعْنِيهِ

የኦርቶዶክስን ችግር ለባለቤቶችን ትተን ከመንቀፍም ከመደገፍም መቆጠባችን ለእነርሱም ሆነ ለእኛ ጤናማ መፍትሄ ነው።
፨ሁለተኛ የክርስትና ግዝትና ግዞት አሊያም መከፍልፈል ዛሬ አልተጀመረም፥ በ 451 ድኅረ ልደት፣ በ 1054 ድኅረ ልደት፣ በ1517 ድኅረ ልደት በዶግማ ተከፋፍለዋል። በአገራችን እራሱ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፣ ኦርቶዶክስ ጸጋ፣ ኦርቶዶክስ፣ ቅባት፣ ኦርቶዶክስ ካራ እየተባለ በዶግማ ተከፋፍለዋል፥ ዘርን መሠረት ያደረገ የቀኖና ክፍፍል ዛሬ አዲስ ነገር አይደለም። እደውም የክርስትና እርስ በእርስ መበላላት እና መነካከስ የአሏህ ቅጣት ነው፦
5፥14 ስለዚህ እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ በመካከላቸው ጠብንና ጥላቻን ጣልንባቸው፡፡ አላህም ይሠሩት የነበሩትን ሁሉ በእርግጥ ይነግራቸዋል፡፡ فَأَغْرَيْنَا بَيْنَهُمُ الْعَدَاوَةَ وَالْبَغْضَاءَ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ ۚ وَسَوْفَ يُنَبِّئُهُمُ اللَّهُ بِمَا كَانُوا يَصْنَعُونَ

"ስለዚህ" የሚለው ተውሳከ ግሥ አንቀጸ ንባቡ ላይ መቀመጡ "እኛ ነሷራ ነን” ያሉት ከታዘዙበት ነገር ፈንታን የመተዋቸው ምክንያት ለመግለጽ የመጣ ነው፦
5፥14 ከእነዚያም “እኛ “ነሷራ” ነን” ካሉት የጠበቀ ቃል ኪዳናቸውን ያዝን፡፡ በእርሱም ከታዘዙበት ነገር ፈንታን ተውት፡፡ وَمِنَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّا نَصَارَىٰ أَخَذْنَا مِيثَاقَهُمْ فَنَسُوا حَظًّا مِّمَّا ذُكِّرُوا بِهِ

ከሐዋርያት ሕልፈት በኃላ ግን በእነርሱ እግር ሥር ተተካን የሚሉት ነሷራዎች ከታዘዙበት ከተውሒድ ፈታን ተሥሊሥ በመጨመር እንዲሁ ተሠግዎት፣ ምንኩስና ወዘተ… የሚባል የፓጋን ትምህርት በመጨመር ወሰን አለፉ፦
4፥171 እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ፡፡ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لَا تَغْلُوا فِي دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا عَلَى اللَّهِ إِلَّا الْحَقَّ
4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ
57፥27 “የፈጠሩዋትንም ምንኩስና በእነርሱ ላይ አልጻፍናትም” وَرَهْبَانِيَّةً ابْتَدَعُوهَا مَا كَتَبْنَاهَا عَلَيْهِمْ

እነዚህ አበው የዒሣን ትምህርት ከግሪክ እና ከሮም ፍልስፍና፣ ወግ፣ ዐረማዊነት ጋር ቀይጠዋል፥ ወራት እና ሳምንት በጣዖታት ስም መሆናቸው በራሱ ይህ የቅሰጣ ውጤት ነው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ በመካከላቸው ጠብ እና ጥላቻ መኖሩ የአሏህ ቅጣት ነው።

፨ሦስተኛ አይሁዶች እና ክርስቲያኖች ዲናቸውን እስካልተከተልን ድረስ እንደማይወዱን አሏህ ነግሮናል፥ ከእነርሱ ጋር በዲን ረገድ መመሳጠር አይቻልም። ዲናችንን ከማበላሸት አይቦዝኑም፥ ጥላቻቸው ከአፎቻቸው በእርግጥ ተገለጸች። እኛን ለማጥፋት በልባቸው የሚዶልቱት ይበልጥ ትልቅ ነው፦
2፥120 አይሁዶች እና ክርስቲያኖች ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ከአንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ
3፥118 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእናንተ ሌላ ምስጢረኛን አትያዙ፡፡ ማበላሸትን አይገቱላችሁም፡፡ ጉዳታችሁን ይወዳሉ፡፡ ጥላቻይቱ ከአፎቻቸው በእርግጥ ተገለጸች፡፡ ልቦቻቸውም የሚደብቁት ይበልጥ ትልቅ ነው፡፡ ልብ የምታደርጉ እንደኾናችሁ ለእናንተ ማብራሪያዎችን በእርግጥ ገለጽን፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا بِطَانَةً مِّن دُونِكُمْ لَا يَأْلُونَكُمْ خَبَالًا وَدُّوا مَا عَنِتُّمْ قَدْ بَدَتِ الْبَغْضَاءُ مِنْ أَفْوَاهِهِمْ وَمَا تُخْفِي صُدُورُهُمْ أَكْبَرُ ۚ قَدْ بَيَّنَّا لَكُمُ الْآيَاتِ ۖ إِن كُنتُمْ تَعْقِلُونَ

ዕቅበተ እምነት ውስጥ የነገረ መለኮት ንጽጽር"comparative theology" ስላለ እና ስለሚፈቀድ እንጂ ችግራቸው ውስጥ ገብተን በመደገፍ ሆነ በመቃወም በፍጹም መፈትፈት እና በኢሥላም ጠላቶች ልወደድ ባይ መሆን የለብንም። ኢሥላም ሰም እና ወርቅ የያዘ ቅኔ ነው፥ ሰሙ ሐቅ ሲሆን ወርቁ ፍትሕ ነው። አሏህ ለሁላችንም ሂያዳህ ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አል ወላእ ወል በራእ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

60፥1 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጠላቶቼን እና ጠላቶቻችሁን ወዳጆች አድርገችሁ አትያዙ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا عَدُوِّي وَعَدُوَّكُمْ أَوْلِيَاءَ

የተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ተከታዮች በኢብራሂም እና በእነዚያ ከእርሱ ጋር በነበሩት ምእምናን መልካም መከተል አለን፦
60፥4 በኢብራሂም እና በእነዚያ ከእርሱ ጋር በነበሩት ምእምናን መልካም መከተል አለቻችሁ፡፡ قَدْ كَانَتْ لَكُمْ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ فِي إِبْرَاهِيمَ وَالَّذِينَ مَعَهُ

ኢብራሂም እና ተከታዮቹ ለሕዝቦቻቸው ያስተላለፉት መልእክት አላህ አንድ ብቻ የሚለውን የተውሒድ እሳቤ እስኪያምኑ ድረስ በእነርሱ እና በሕዝቦቻቸው መካከል በራእ ማድረግን ነው፦
60፥4 ለሕዝቦቻቸው «እኛ ከእናንተ እና ከአላህ ሌላ ከምታመልኩት ንጹሓን ነን፡፡ በእናንተ ካድን፡፡ በአላህ አንድ ብቻ ሲኾን እስከምታምኑ ድረስ በእኛ እና በእናንተ መካከል ጠብና ጥላቻ ዘወትር ተገለጸ፡፡» ባሉ ጊዜ መልካም መከተል አለቻችሁ፡፡ إِذْ قَالُوا لِقَوْمِهِمْ إِنَّا بُرَآءُ مِنكُمْ وَمِمَّا تَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ كَفَرْنَا بِكُمْ وَبَدَا بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمُ الْعَدَاوَةُ وَالْبَغْضَاءُ أَبَدًا حَتَّىٰ تُؤْمِنُوا بِاللَّهِ وَحْدَهُ

"ንጹሓን" ለሚለው የገባው ቃል "ቡራእ" بُرَآء ሲሆን "በሪእ" بَرِيء ማለትም "ንጹሕ" ለሚለው ብዜት ነው፥ "በራእ" بَرَاء የሚለው ቃል እራሱ "በሪአ" بَرِئَ ማለትም "ጠላ" "ራቀ" "ተወ" "ነጻ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መጥላት" "መራቅ" "መተው" "ንጹሕ" ማለት ነው፦
43፥26 ኢብራሂምም ለአባቱ እና ለሕዝቦቹ፦ «እኔ ከምታመልኩት ሁሉ ንጹሕ ነኝ፡» ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ قَالَ إِبْرَاهِيمُ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِ إِنَّنِي بَرَاءٌ مِّمَّا تَعْبُدُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ንጹሕ" ለሚለው የገባው ቃል "በራእ" بَرَاء ሲሆን የአሏህን ጠላቶችን በዲን ነጥብ እና ጉዳይ ላይ በራእ አለማድረግ በአሏህ ላይ ማመጽ ነው፥ ከኢሥላም ውጪ ያሉት አላህ አንድ ብቻ የሚለውን የተውሒድ እሳቤ እስኪያምኑ ድረስ በእኛ እና በእነርሱ መካከል ጠብና ጥላቻ ዘወትር አለ። ቤተሰቦቻችንን ከአሏህ ቅጣት ምንም የማናስመልጥ ስንሆን ለእነርሱ በእርግጥ ምሕረትን እንለምናለን፦
60፥4 ኢብራሂም ለአባቱ «እኔ ለአንተ ከአላህ ቅጣት ምንም የማልጠቅም ስኾን ለአንተ በእርግጥ ምሕረትን እለምንልኻለሁ» ማለቱ ብቻ ሲቀር፡፡ «ጌታችን ሆይ! በአንተ ላይ ተመካን፡፡ ወደ አንተም ተመለስን መመለሻም ወደ አንተ ብቻ ነው፤» ባለው ተከተሉት፡፡ إِلَّا قَوْلَ إِبْرَاهِيمَ لِأَبِيهِ لَأَسْتَغْفِرَنَّ لَكَ وَمَا أَمْلِكُ لَكَ مِنَ اللَّهِ مِن شَيْءٍ ۖ رَّبَّنَا عَلَيْكَ تَوَكَّلْنَا وَإِلَيْكَ أَنَبْنَا وَإِلَيْكَ الْمَصِيرُ

የአሏህ ብቻ ሐቅ እና ገንዘብ የሆነው አምልኮ ለሌላ ምንነት እና ማንነት የሚያጋሩ ሰዎች የአሏህ ጠላቶች ናቸው፥ በዚህ ወንጀል የተዘፈቁ እስከ ዝንተ ዓለም ለእሳት ይዳረጋሉ። ከሓዲያን የአሏህ ጠላቶች ስለሆኑ ለአማንያንም በእርግጥ ግልጽ ጠላቶች ናቸው፦
41፥19 የአላህ ጠላቶች ወደ እሳት የሚሰበሰቡበትን ቀን አስታውስ፡፡ وَيَوْمَ يُحْشَرُ أَعْدَاءُ اللَّهِ إِلَى النَّارِ
4፥101 ከሓዲዎች ለእናንተ በእርግጥ ግልጽ ጠላቶች ናቸውና፡፡ إِنَّ الْكَافِرِينَ كَانُوا لَكُمْ عَدُوًّا مُّبِينًا
60፥1 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጠላቶቼን እና ጠላቶቻችሁን ወዳጆች አድርገችሁ አትያዙ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا عَدُوِّي وَعَدُوَّكُمْ أَوْلِيَاءَ

"ወሊይ" وَلِىّ ማለት "ወዳጅ" "ረዳት" "ጓደኛ" ማለት ሲሆን "አውሊያእ" أَوْلِيَاء ደግሞ "ወዳጆች" "ረዳቶች" "ጓደኞች" ማለት ነው፥ "ወላእ" وَلَاء የሚለው ቃል እራሱ "ወሊየ" وَلِيَ ማለትም "ረዳ" "ወደደ" "ቀረበ" "ተጎዳኘ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መርዳት" "መውደድ" "መቅረብ" "መጎዳኘት" ማለት ነው፦
9፥71 ምእመናን እና ምእመናት ከፊሎቻቸው ለከፊሉ "ረዳቶች" ናቸው፡፡ وَالْمُؤْمِنُونَ وَالْمُؤْمِنَاتُ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ረዳቶች" ለሚለው የገባው ቃል "አውሊያእ" أَوْلِيَاء እንደሆነ ልብ አድርግ! ለአማኝ ወንድሞች እና ለአማኝ እኅቶች "ወዳጆች" "ረዳቶች" "ጓደኞች" ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ነው። በአሏህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑ አማንያን አሏህን እና መልእክተኛው የሚዘልፉ ከቤተሰባቸው ቢሆኑ እንኳን አይወዳጁም፦
58፥22 በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑትን ሕዝቦች አላህን እና መልእክተኛው የሚከራከሩትን ሰዎች፤ አባቶቻቸው፣ ወይም ልጆቻቸው፣ ወይም ወንድሞቻቸው፣ ወይም ዘመዶቻቸው ቢኾኑም እንኳ የሚወዳጁ ኾነው አታገኛቸውም፡፡ لَّا تَجِدُ قَوْمًا يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ يُوَادُّونَ مَنْ حَادَّ اللَّهَ وَرَسُولَهُ وَلَوْ كَانُوا آبَاءَهُمْ أَوْ أَبْنَاءَهُمْ أَوْ إِخْوَانَهُمْ أَوْ عَشِيرَتَهُمْ

እንግዲህ "አል ወላእ ወል በራእ" الْوَلَاء وَالْبَرَاء የሚለው የተውሒድ መርሕ "ለአሏህ ብሎ መወደድ እና መጥላት" ማለት ነው፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 42 ሐዲስ 86
አቢ ኡማማህ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ማንም ለአሏህ ብሎ የወደደ እና የጠላ እንዲሁ ለአሏህ ብሎ የሰጠ እና የነፈገ የተሟላ ኢማን ይኖረዋል"። عَنْ أَبِي أُمَامَةَ، عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم أَنَّهُ قَالَ ‏ “‏ مَنْ أَحَبَّ لِلَّهِ وَأَبْغَضَ لِلَّهِ وَأَعْطَى لِلَّهِ وَمَنَعَ لِلَّهِ فَقَدِ اسْتَكْمَلَ الإِيمَان

ለአሏህ ብሎ መስጠት ከእዩልኝ እና ከስሙልኝ ነጻ የሆነ ልግስና ሲሆን ለአሏህ ብሎ ለአልባሌ ነገር ከመስጠት የነፈገ ከጥፋት መታደግ ነው፥ በተመሳሳይ ለዘሩ፣ ለብሔሩ፣ ለዘውጉ እና ለነፍሥያው ብሎ ሳይሆን ለአሏህ ብሎ አሏህ የሚጠላውን ነገር የሚጠላ እና አሏህ የሚወደውን የሚወድ የተሟላ ኢማን አለው።
አምላካችን አሏህ ሐቅን በማንገስ ባጢልን በማርከስ ወላእ እና በራእ የምናደርግ ያድርገን! ከሙገሳ እና ከወቀሳ ነጻ የሆነ ኢኽላሱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የአሏህ ጠላቶች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

41፥19 የአላህ ጠላቶች ወደ እሳት የሚሰበሰቡበትን ቀን አስታውስ፡፡ وَيَوْمَ يُحْشَرُ أَعْدَاءُ اللَّهِ إِلَى النَّارِ

"አል ወላእ ወል በራእ" الْوَلَاء وَالْبَرَاء የሚለው የተውሒድ መርሕ "ለአሏህ ብሎ መወደድ እና መጥላት" ቢሆንም በማኅበራዊ እሴት ውስጥ በሚኖረን ጉልኅ ሚና ለሰዎች መልካምን ሥራ እንድንሠራ አምላካችን አሏህ ያዘናል፦
4፥36 አላህንም አምልኩ፡፡ በእርሱም ምንንም አታጋሩ፡፡ ”በወላጆችና በቅርብ ዝምድና ባለቤትም፣ በየቲሞችም፣ በምስኪኖችም፣ በቅርብ ጎረቤትም፣ በሩቅ ጎረቤትም፣ በጎን ባልደረባም፣ በመንገደኛም፣ እጆቻችሁም ንብረት ባደረጓቸው፣ መልካምን ሥሩ”። አላህ ኩራተኛ ጉረኛ የኾነን ሰው አይወድም፡፡ وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا ۖ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا وَبِذِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَالْجَارِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَالْجَارِ الْجُنُبِ وَالصَّاحِبِ بِالْجَنبِ وَابْنِ السَّبِيلِ وَمَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخْتَالًا فَخُورًا

የወላጆች ሐቅ፣ የዝምድና ሐቅ፣ የጉርብትና ሐቅ መወጣት ግዴታ ነው፥ አንድ አማኝ ለራሱ የሚወደውን ለሌላው እስካልወደደ ድረስ አላመነም፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 77
አነሥ ኢብኑ ማሊክ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ ”ከእናንተ አንድም አላመነም ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ ወይም ለራሱ የሚወደውን ለጎረቤቱ እስካልወደደ ድረስ”፡፡ يُحَدِّثُ عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ لاَ يُؤْمِنُ أَحَدُكُمْ حَتَّى يُحِبَّ لأَخِيهِ – أَوْ قَالَ لِجَارِهِ – مَا يُحِبُّ لِنَفْسِه

ለሰዎች መልካምን መዋል፣ በፍትሕ ማስተካከል፣ ለአሏህ ብሎ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች መሆን ሸሪዓችን የሚያዘን ነው፦
60፥8 ከእነዚያ በሃይማኖት ካልተጋደሏችሁ ከአገሮቻችሁም ካላወጡዋችሁ መልካም ብትውሉላቸው እና ወደእነርሱ ብታስተካክሉ አላህ አይከለክላችሁም፡፡ አላህ ትክክለኞችን ይወዳልና፡፡ لَّا يَنْهَاكُمُ اللَّهُ عَنِ الَّذِينَ لَمْ يُقَاتِلُوكُمْ فِي الدِّينِ وَلَمْ يُخْرِجُوكُم مِّن دِيَارِكُمْ أَن تَبَرُّوهُمْ وَتُقْسِطُوا إِلَيْهِمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ
5፥8 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሕዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ لِلَّهِ شُهَدَاءَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ عَلَىٰ أَلَّا تَعْدِلُوا

ሰውን በቀለሙ፣ በቋንቋው፣ በብሔሩ፣ በዘውጉ መጥላት የፍሕት መጓደል ነው፥ ከዚህ ረገድ አንድ ሙሥሊም ሁሉንም ሰዎች በፍትሕ መያዙ ውዴታን ያሳያል። አንድን ድርጊት ከአድራጊው እንዲሁ አንድን ሥራ ከሠሪው ስለማይነጠል የድርጊቱ እና የሥራው ባለቤት በሚያደርገው ድርጊት እና በሚሠራው ሥራ አሏህ እንደሚወድ እና እንደሚጠላ ሁሉ እኛም አሏህ የደደደውን እንወዳለን የጠላውን እንጠላለን፥ ይህ ፍትሓዊ ብይን ነው። በበጎ ነገር እና አሏህን በመፍራት መረዳዳት የታዘዘ ነው፦
5፥2 በበጎ ነገር እና አላህን በመፍራት ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአት እና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ ۖ وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ
ነገር ግን በኃጢአት እና ወሰንን በማለፍ መረዳዳት ክልክል ነው፥ ለምሳሌ፦ በሐራም ሥራ መረዳዳት በኃጢአት መረዳዳት ሲሆን በሺርክ ወይም በኩፍር ሥራ መረዳዳት ወሰንን በማለፍ መረዳዳት ነው።
እዚህ ድረስ ከተግባባ ስለ አል ወላእ ወል በራእ በባይብል እንመልከት! ኢየሱስ፦ "ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ" ብሎ አስተምሯል፦
ዮሐንስ 15፥18 ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ። Εἰ ὁ κόσμος ὑμᾶς μισεῖ, γινώσκετε ὅτι ἐμὲ πρῶτον ὑμῶν μεμίσηκεν.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ዓለም" ለሚለው የገባው ቃል "ኮስሞስ" κόσμος ሲሆን ሰዎችን ያመለክታል፥ ኢየሱስ ሆነ ሐዋርያትን የጠሉት ሰዎች እንጂ ግዑዙ ጽንፈ ዓለም አይደለም። ኢየሱስ ሆነ ሐዋርያትን የጠሉት ሰዎች መውደድ ደግሞ ለአምላክ ጥል ነው፥ የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የአምላክ ጠላት ሆኖአል፦
ያዕቆብ 4፥4 አመንዝሮች ሆይ! ዓለምን መውደድ ለአምላክ ጥል እንዲሆን አታውቁምን? እንግዲህ የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የአምላክ ጠላት ሆኖአል። μοιχαλίδες, οὐκ οἴδατε ὅτι ἡ φιλία τοῦ κόσμου ἔχθρα τοῦ Θεοῦ ἐστιν; ὃς ἐὰν οὖν βουληθῇ φίλος εἶναι τοῦ κόσμου, ἐχθρὸς τοῦ Θεοῦ καθίσταται.

"ሰዎች እንዴት የአሏህ ጠላቶች ይሆናሉ? አሏህ እንዴት ሰዎችን ይጠላል" ብላችሁ ለጠየቃችሁ እንኳን ያሻረከ እና የከፈረ ይቅርና የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የአምላክ ጠላት ነው፥ አስማተኛ፣ መተተኛ፣ በድግምት የሚጠነቍል ድግምተኛ፣ መናፍስትን የሚጠራ፣ ጠንቋይም፣ ሙታን ሳቢም በአምላክ ፊት የተጠላ ነው፦
ዘዳግም 18፥11-12 አስማተኛም፥ መተተኛም፥ በድግምት የሚጠነቍልም፥ መናፍስትንም የሚጠራ፥ ጠንቋይም፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ። ይህንም የሚያደርግ ሁሉ በያህዌህ ፊት "የተጠላ" ነው።

በባይብል ፈጣሪ ኃጢአተኞችን ከመጥላትም ባሻገር በገሃነም ይቀጣ የለ? አንድ ሰው የፈጣሪን መልእክተኛ ለመከተል ሲመጣ ቤተሰቡ እና የራሱን ሕይወት ሊጠላ ይገባዋል፦
ሉቃስ 14፥26 ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱን እና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እኅቶቹንም የራሱን ሕይወት ስንኳ ሳይቀር ባይጠላ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።

"መጥላት" ማለት "ከራሱ እና ከቤተሰቡ ይልቅ አስበልጦ መውደድ" ማለት ከሆነ እኛም ሙሥሊሞችም ለዲናችን ብለን የማያምኑትን እንጠላለን ማለት ከማያምኑት ይልቅ አስበልጠን ሙሥሊም ወንድማችንን እና እኅታችንን እንወዳለን ማለት ነው። ሰዎች ከአሏህ ሌላ ባለንጣዎችን አሏህን እንደሚወዱ ሊወዱ ቢችሉም አማኞች ግን አሏህን በመውደድ ከከሓድያን የበረቱ ናቸው፦
2፥165 ከሰዎችም ከአላህ ሌላ ባለንጣዎችን አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ኾነው የሚይዙ አሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ ከእነርሱ ይበልጥ የበረቱ ናቸው፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يَتَّخِذُ مِن دُونِ اللَّهِ أَندَادًا يُحِبُّونَهُمْ كَحُبِّ اللَّهِ ۖ وَالَّذِينَ آمَنُوا أَشَدُّ حُبًّا لِّلَّهِ ۗ

አሏህ ሂያዳህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የቫላንታይን ቀን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

3፥31 በላቸው፡- «አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና፡፡ ኀጢኣቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡» قُلْ إِن كُنتُمْ تُحِبُّونَ اللَّهَ فَاتَّبِعُونِي يُحْبِبْكُمُ اللَّهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ ۗ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

በክርስትና ታሪክ ውስጥ ቫለንቲኑስ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ሰዎች ሲሆኑ ከሁለቱ የመጀመሪያው በ 100 ድኅረ ልደት ግብፅ ተወልዶ በ 160 ድኅረ ልደት ቆጵሮስ የሞተው ቫለንቲኑስ የኖስቲስ መሪ የነበረው የቴዎዳስ ተማሪ ነው፥ ቫለንቲኑስ “ኢየሱስ የማርያም ዘር አይደለም” የሚል አቋም ያለው ሲሆን የእርሱ ተማሪዎች ቫለንቱሳውያን ይህንን አቋም በጥንት ጊዜ ያራምዱ ነበር።
ሁለተኛው ደግሞ በ 226 ልደት ተወልዶ በ 269 ድኅረ ልደት በሮሙ ንጉሥ በክላውዲዮስ ዘመን የተሠዋው ሰማዕት ነው፥ ይህ ሰው በዘመነ ሰማዕታት ጊዜ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር የካቲት 14 ቀን 269 ድኅረ ልደት ሰማዕት ሆኗል። እርሱ የሞተበትን ቀን በምዕራባውያን ካቶሊክ የካቲት 14 ቀን ሲዘከር በምሥራቃውያን ኦርቶዶክስ ደግሞ ሰኔ 6 ይዘከራል፥ ሰማዕቱ ቫለንቲኑስ በሕይወት ዘመኑ ወቅት የሮም መንግሥት ወታደሮች እንዳያገቡ ሲከለክል እርሱ ግን የሚፋቀሩትን ይድር ነበር፥ በዚህም ንጉሡ ክላውዲዮስ አቂሞበት ነበርና በወቅቱ "ጣዖት አላመልክም" በማለት ሰማዕት ሆኗል።

በዘመናችን ያሉ ሰዎች የቫላንታይን ቀን እያሉ በዓመት አንዴ የካቲት 14 ቀን የሚያከብሩት የፍቅረኛሞች ቀን መሠረቱ ይህ ነው፥ "ቫላንታይን"Valentine" የሚለው ቃል እራሱ "ቫለንቲኑስ" ከሚባለው የክርስትና ሰማዕት እንደመጣ አንባቢ ልብ ይለዋል። እንደ ኢሥላም አስተምህሮት የምናከብረው ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻ እና ብቻ ነው፥ እነርሱም ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ዒዱል ፊጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፥ ዒዱል አድሓ ደግሞ መሥዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው”። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏

“ዒድ” عِيد የሚለው ቃል “ዓደ” عَادَ ማለትም “ተመላለሰ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ምልሰት” ማለት ነው፥ ይህ “መደሰቻ” ወይም “በዓል” በየዓመቱ ስለሚመላለስ ይህንን ስያሜ አግኝቷል። አሏህን የምንወድ እንደሆንን ተወዳጁ ነቢያችንን"ﷺ" እንከተል፦
3፥31 በላቸው፡- «አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና፡፡ ኀጢኣቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡» قُلْ إِن كُنتُمْ تُحِبُّونَ اللَّهَ فَاتَّبِعُونِي يُحْبِبْكُمُ اللَّهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ ۗ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

በተረፈ ከክርስትና ሾልኮ የመጣውን የቫላንታይን ቀን ከማክበር ሆነ ከማስከበር እንጠንቀቅ! የቫላንታይን ቀን ማክበር እና ማስከበር ግልጽ ፈሣድ ነው። አሏህ በኢሥላም ስም ፈሣድ ከሚያስፋፉ ሙፍሢዲን ይጠብቀን! አሚን።

ከዐቃቢ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የአሏህ ሉዓላዊነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥117 ነገርን ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፡፡ وَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

"ዑሉው" عُلُوّ የሚለው ቃል "ዐላ" عَلَا‎ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ሉዓላዊነት" ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ ከሁሉ በላይ "ልዑል" ስለሆነ "አል-ዓሊይ" العَلِيّ ነው፦
2፥255 እርሱም የሁሉ በላይ ታላቅ ነው፡፡ وَهُوَ الْعَلِيُّ الْعَظِيمُ

እዚህ አንቀጽ ላይ "የሁሉ በላይ" ለሚለው የገባው ቃል "አል-ዓሊይ" العَلِيّ ሲሆን "የበላይ" "ምጡቅ" "ልዑል" ማለት ነው፥ "ልዑል" የሚለው የግዕዝ ቃል እራሱ "የሁሉ በላይ" ማለት ነው። "ልዕልና" ወይም "ሉዓላዊነት" ማለት "የበላይነት" "ምጥቀት" ማለት ነው፥ በጥቅሉ "ዑሉዉል ሏህ" عُلُوّ اللَّه ማለት "የአሏህ ሉዓላዊነት"sovereignty of Allah" ማለት ነው። የአሏህ ሉዓላዊነት ሙጅመል ነው፥ "ሙጅመል" مُجّمَل ማለት "ጥቅል"general" ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ በጥቅሉ ፍጥረትን እርሱ ሽቶ እና ፈቅዶ ኹን በሚል ቃሉ ወስኖ ማስገኘቱ የአሏህ ሉዓላዊነት ነው፦
2፥117 ነገርን ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፡፡ وَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
3፥47 ነገርን ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፡፡ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
19፥35 ነገርን ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፡፡ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
40፥68 ነገርን ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፡፡ فَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

እነዚህ አናቅጽ ላይ "በሻ" ለሚለው የገባው ቃል "ቀዷ" قَضَىٰ ሲሆን "አራደ" أَرَادَ ማለት ነው፥ "አራደ" أَرَادَ ማለት "ፈለገ" "ፈቀደ" "አሻ" ማለት ነው፦
36፥82 ነገሩም አንዳችን ማስገኘት በሻ ጊዜ ኹን ማለት ነው፡፡ ወዲያው ይኾናልም፡፡ إِنَّمَا أَمْرُهُ إِذَا أَرَادَ شَيْئًا أَن يَقُولَ لَهُ كُن فَيَكُونُ

እዚህ አንቀጽ ላይ "በሻ" ለሚለው የገባው ቃል "አራደ" أَرَادَ ሲሆን በመጀመሪያ መደብ "አረድና" أَرَدْنَا በማለት ተናግራል፦
16፥40 ለማንኛውም ነገር መኾኑን "በሻነው" ጊዜ ቃላችን ለእርሱ “ኹን” ማለት ብቻ ነው፥ ወዲውም ይኾናል፡፡ إِنَّمَا قَوْلُنَا لِشَيْءٍ إِذَا أَرَدْنَاهُ أَن نَّقُولَ لَهُ كُن فَيَكُونُ

"አረድና-ሁ" أَرَدْنَاهُ ማለት "በወሰነው" "በፈለግነው" "በፈቀድነው" በሻነው" ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ ሽቶ እና ፈቅዶ ኹን በሚል ቃሉ ወስኖ ማስገኘቱ ጥቅላዊ የአሏህ ሉዓላዊነት ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 40, ሐዲስ 19
አቡ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "አሏህ ፍጥረትን ባሻ ጊዜ እራሱ በመጽሐፉ ጻፈ። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لَمَّا قَضَى اللَّهُ الْخَلْقَ كَتَبَ فِي كِتَابِهِ عَلَى نَفْسِهِ

እነዚህ ሐዲስ ላይ "በሻ" ለሚለው የገባው ቃል "ቀዷ" قَضَىٰ ሲሆን ፍጥረትን ከመፍጠሩ በፊት የፍጥረትን ሂደት ቀድሞ ስለሚያውቀው ጽፎታል።