ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
69 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ነቢዩ ዙልኪፍል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

21፥85 ኢስማዒልን፣ ኢድሪስን፣ ዙልኪፍልን አስታውስ! ሁሉም ከታጋሾቹ ናቸው፡፡ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِدْرِيسَ وَذَا الْكِفْلِ ۖ كُلٌّ مِّنَ الصَّابِرِينَ

"ዙ" ذَا ማለት በአገዛዛቢ መደብ የመጣ ሲሆን "ባለቤት" ማለት ነው፥ "ኪፍል" كِفْل ማለት "ክፍል" ማለት ሲሆን "ዙልኪፍል" ذَا الْكِفْل ማለት "የክፍል ባለቤት" ማለት ነው። ይህ ነቢይ በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ዒራቅ ውስጥ ነበረ፥ እዛ የተወሰነ ክፍል ተሰቶት ይኖር ነበር። ያ የኖረበት ቦታ "ኪፍል" كِفْل ሲባል ነቢዩ ደግሞ "የክፍል ባለቤት" ተብሏል፥ ይህ ነቢይ በቁርኣን ውስጥ ልክ እንደ ኢድሪሥ በማዕረግ ስም ተጠርቷል። የተጸውዖ ስሙ "ሒዝቂያል" حِزْقِيَال ይባላል፥ አይሁዳውያን ኪፍል በሚባል ቦታ የሕዝቅኤልን መቃብር ይጎበኙ ነበር። አምላካችን አሏህ ዙልኪፍልን ከኢስማዒል እና ከኢድሪስ ጋር ያወሳዋል፦
21፥85 ኢስማዒልን፣ ኢድሪስን፣ ዙልኪፍልን አስታውስ! ሁሉም ከታጋሾቹ ናቸው፡፡ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِدْرِيسَ وَذَا الْكِفْلِ ۖ كُلٌّ مِّنَ الصَّابِرِينَ
21፥86 ከችሮታችንም ውስጥ አገባናቸው፡፡ እነርሱ ከመልካሞቹ ናቸውና፡፡ وَأَدْخَلْنَاهُمْ فِي رَحْمَتِنَا ۖ إِنَّهُم مِّنَ الصَّالِحِينَ

አሏህ ኢስማዒልን፣ ኢድሪስን፣ ዙልኪፍልን ከችሮታው ውስጥ አገባቸው፥ ይህም ችሮታ ወሕይ በማውረድ የሚሰጥ ነቢይነት ነው፦
3፥74 በችሮታው (በነቢይነት) የሚሻውን ይመርጣል፡፡ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡ يَخْتَصُّ بِرَحْمَتِهِ مَن يَشَاءُ ۗ وَاللَّهُ ذُو الْفَضْلِ الْعَظِيمِ
2፥90 አላህ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ከችሮታው (ራእይን) ማውረዱን በመመቅኘት አላህ ባወረደው ነገር መካዳቸው ነው፡፡ أَن يَكْفُرُوا بِمَا أَنزَلَ اللَّهُ بَغْيًا أَن يُنَزِّلَ اللَّهُ مِن فَضْلِهِ عَلَىٰ مَن يَشَاءُ مِنْ عِبَادِهِ

አሏህ "ባሪያችንን አዩብን፣ ባሮቻችንን ኢብራሂምን፣ ኢሥሐቅን፣ የዕቁብን አውሳ" ካለ በኃላ በማለት "ኢስማዒልን፣ አልየሰዕን፣ ዙልኪፍልን አውሳ! በማለት ከነቢያት ምድብ ውስጥ ይከታቸዋል፥ ኢስማዒል፣ አልየሰዕ፣ ዙልኪፍል ከበላጮቹ ናቸው። አሏህ መጽሐፍን፣ ጥበብን እና ነቢይነትን ሰቷቸዋል፦
38፥48 ኢስማዒልን፣ አልየሰዕን፣ ዙልኪፍልን አውሳ! ሁሉም ከበላጮቹ ናቸው፡፡ وَاذْكُرْ إِسْمَاعِيلَ وَالْيَسَعَ وَذَا الْكِفْلِ ۖ وَكُلٌّ مِّنَ الْأَخْيَارِ
6፥89 እነዚህ እነዚያ መጽሐፍን፣ ጥበብን እና ነቢይነትን የሰጠናቸው ናቸው፡፡ أُولَـٰئِكَ الَّذِينَ آتَيْنَاهُمُ الْكِتَابَ وَالْحُكْمَ وَالنُّبُوَّةَ

አምላካችን አሏህ በትንሳኤ ቀን በእነርሱ ላይ ከለገሳቸው ከነቢያት ጋር ያማረ ጓደኛ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የኤፍራጥስ ወንዝ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

53፥4 እርሱ ንግግሩ የሚወረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ إِنْ هُوَ إِلَّا وَحْيٌ يُوحَىٰ

"ሷሒብ" صَاحِب ማለት "ጓደኛ" "ሞክሼ" "ባልደረባ" ማለት ሲሆን ነቢያችን"ﷺ" ለመጡበት ሕዝብ ባልደረባ ነበሩ፥ የመጡበት ሕዝብ ነቢያችንን"ﷺ" እንደተሳሳቱ እና እንደጠመሙ ሰው አሊያም ዕብድ አርጎ ስላያቸው አምላካችን አሏህ፦ "ባልደረባችሁ አልተሳሳተም፤ አልጠመመም። በፍጹም ዕብድ አይደለም" በማለት ለተሳላቂዎች መልስ ይሰጥ ነበር፦
53፥2 ባልደረባችሁ አልተሳሳተም፤ አልጠመመም፡፡ مَا ضَلَّ صَاحِبُكُمْ وَمَا غَوَىٰ
81፥22 ባልደረባችሁ በፍጹም ዕብድ አይደለም፡፡ وَمَا صَاحِبُكُم بِمَجْنُونٍ

የመጡበት ሕዝብ ነቢያችንን"ﷺ" እንደተሳሳቱ እና እንደጠመሙ ሰው አሊያም ዕብድ አርጎ ያየበት ምክንያት ነቢያችን"ﷺ" ያዩት እና የሚናገሩት የሩቅ ነገር ወሬ ነው። ይህ የሩቅ ነገር ወሬ ምን ነበር? "ውኃን ከጥሩ ነገርን ከሥሩ" የሚለውን አገርኛ ብሒል ይዘን እንጀምር! ጂብሪል ወደ ነቢያችን”ﷺ” የሚመጣው በሚወዱት ባልደረባ በዲሕያህ ኢብኑ ኸሊፋህ በሚባል ሰው ተመስሎ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 66, ሐዲስ 2
አቡ ዑስማን እንደተረከው፦ “ጂብሪል ወደ ነቢዩ”ﷺ” ሲመጣ ኡሙ ሠላማህ ከእርሳቸው ጋር ነበረች፥ ጂብሪል መናገር ጀመረ። ነቢዩም”ﷺ”፦ “ኡሙ ሠላማህ ይህ ማን ነው? አሉ፥ እርሷም፦ “ይህ ዲሕያህ ነው” አለች። ጂብሪል በሄደ ጊዜ እርሷም፦ “ወሏሂ! በነቢዩ”ﷺ” ሑጥባህ ላይ ስለ ጂብሪል ዜና እስኪነግሩን ድረስ ከዲሕያህ በስተቀር ሌላ ማንንም አላሰብኩም ነበር”። عَنْ أَبِي عُثْمَانَ، قَالَ أُنْبِئْتُ أَنَّ جِبْرِيلَ، أَتَى النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم وَعِنْدَهُ أُمُّ سَلَمَةَ فَجَعَلَ يَتَحَدَّثُ فَقَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم لأُمِّ سَلَمَةَ ‏ “‏ مَنْ هَذَا ‏”‌‏.‏ أَوْ كَمَا قَالَ قَالَتْ هَذَا دِحْيَةُ‏.‏ فَلَمَّا قَامَ قَالَتْ وَاللَّهِ مَا حَسِبْتُهُ إِلاَّ إِيَّاهُ حَتَّى سَمِعْتُ خُطْبَةَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم يُخْبِرُ خَبَرَ جِبْرِيلَ أَوْ كَمَا قَالَ،

ነቢያችን"ﷺ" በመንገድ ጉዞ እያሉ ጂብሪል በተፈጥሮ ቅርጹ ግን ለመጀመሪያ ጊዜ ወርዶ በሰማይ እና በምድር መካከል ተቀምጦ አይተውታል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 78, ሐዲስ 238
ጃቢ ኢብኑ ዐብደሏህ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰማው ብሎ እንደተረከው፦ “እርሳቸውም እንዲህ አሉ፦ “ከዚያም ወሕይ ወደ እኔ ተቋረጦ ነበር፥ ድንገት እየተጓዝኩኝ እያለ ከሰማይ ድምፅ ሰማሁኝ። እራሴን ቀና አድርጌ ወደ ሰማይ ስመለከት በሒራእ ዋሻ የጎበኘኝ መልአክ በሰማይ እና በምድር መካከል በመንበር ላይ ተቀምጦ አየሁት”። عَنِ جَابِرُ بْنُ عَبْدِ اللَّهِ، أَنَّهُ سَمِعَ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ “‏ ثُمَّ فَتَرَ عَنِّي الْوَحْىُ، فَبَيْنَا أَنَا أَمْشِي سَمِعْتُ صَوْتًا مِنَ السَّمَاءِ، فَرَفَعْتُ بَصَرِي إِلَى السَّمَاءِ فَإِذَا الْمَلَكُ الَّذِي جَاءَنِي بِحِرَاءٍ قَاعِدٌ عَلَى كُرْسِيٍّ بَيْنَ السَّمَاءِ وَالأَرْضِ ‏”‌‏.‏

ነቢያችን"ﷺ" ጂብሪልን በተፈጥሮ ቅርጹ ለሁለተኛ ጊዜ ያዩት ደግሞ ሲድረቱል ሙንተሃ ላይ ነው፥ “ሲድረቱል ሙንተሃ” سِدْرَة الْمُنْتَهَى የሰባተኛው ሰማይ መጨረሻ ሊታለፍ የማይችል ድንበራዊ ዛፍ ነው፦
53፥14 “በሲድረቱል ሙንተሃ አጠገብ አይቶታል”። عِندَ سِدْرَةِ الْمُنتَهَىٰ
53፥15 “እርሷ ዘንድ መኖሪያይቱ ጀናህ ያለች ስትኾን”፡፡ عِندَهَا جَنَّةُ الْمَأْوَىٰ
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 53፥13-15 “በሌላይቱም መውረድ ጊዜ በእርግጥ አይቶታል፣ በሲድረቱል ሙንተሃ አጠገብ አይቶታል፣ እርሷ ዘንድ መኖሪያይቱ ጀናህ ያለች ስትኾን” የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “ጂብሪልን አይቼዋለው፥ ስድስት መቶ ክንፍ አለው”። وَلَقَدْ رَءَاهُ نَزْلَةً أُخْرَى – عِندَ سِدْرَةِ الْمُنتَهَى – عِندَهَا جَنَّةُ الْمَأْوَى قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله «رَأَيْتُ جِبْرِيلَ وَلَهُ سِتُّمِائَةِ جَنَاحٍ »

“ሙንተሃ” مُنتَهَىٰ የሚለው ቃል “ነሃ” نَهَىٰ ማለትም “ከለከለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ክልክል” ማለት ነው፥ የሰባተኛው ሰማይ ድንበሩ የሢድራህ ዛፍ ናት። የብርታት ባለቤት የኾነውን ጂብሪል በላይኛውና በግልጹ አድማስ በሲድረቱል ሙንተሃ ላይ ኾኖ ተደላድሎ ሲወርድ አዩት፦
53፥6 “የዕውቀት ባለቤት የኾነው ተደላደለም”፡፡ ذُو مِرَّةٍ فَاسْتَوَىٰ
53፥7 “እርሱ በላይኛው አድማስ ኾኖ”፡፡ وَهُوَ بِالْأُفُقِ الْأَعْلَىٰ
81፥23 “በግልጹ አድማስም በእርግጥ አይቶታል”፡፡ وَلَقَدْ رَآهُ بِالْأُفُقِ الْمُبِينِ

ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ወደ ሲድረቱል ሙንተሃ ሲወጡ አራት ወንዞችን አይተዋል፥ እነዚህም አራት ወንዞች ሠይሓን፣ ጀይሓን፣ ፉራት እና ኒል ናቸው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 74, ሐዲስ 36
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “አራቱን ወንዞች ባየሁ ጊዜ ወደ ሢድራን ወጣሁኝ”። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ رُفِعْتُ إِلَى السِّدْرَةِ فَإِذَا أَرْبَعَةُ أَنْهَارٍ،
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 53, ሐዲስ 30
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሠይሓን፣ ጀይሓን፣ፉራት እና ኒል ሁሉም ከጀናህ ወንዞች ናቸው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ سَيْحَانُ وَجَيْحَانُ وَالْفُرَاتُ وَالنِّيلُ كُلٌّ مِنْ أَنْهَارِ الْجَنَّةِ ‏"‏ ‏.‏

"ሠይሓን" سَيْحَان ማለት "ፊሶን" ማለት ሲሆን፣ "ጀይሓን" جَيْحَان ማለት "ጤግሮስ" ማለት ሲሆን፣ "ፉራት" فُرَات ማለት "ኤፍራስጥ" ማለት ሲሆን፣ "ኒል" نِّيل ማለት ደግሞ "ግዮን" ማለት ነው። አሏህ ሰማይ ላይ ያሉ ሥርዓት በምድር ላይም አርጓል፥ ለምሳሌ፦ በሰባተኛ ሰማይ ከዕባህ ንድፍ የሆነበት ሰባ ሺህ መላእክት አምልኮ የሚፈጽሙበት የደመቀው ቤት "በይቱል መዕሙር" بَيْت الْمَعْمُور ሲባል በተመሳሳይ ምድር ላይ መካህ የሚገኘው የአሏህ ቤት "በይቱል መዕሙር" بَيْت الْمَعْمُور ተብላል፦
52፥4 በደመቀው ቤት እምላለው፡፡ وَالْبَيْتِ الْمَعْمُورِ
በተመሳሳይ አሏህ በሰማይ ላይ እንዳሉት ወንዞች በምድር ላይ ወንዞች አድርጓል፥ ከዚያው ውስጥ በሐዲስ በስም የተጠቀሰ ወንዝ የኤፍራጥስ ወንዝ ነው። ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" መስጴጦምያ ስለሚገኘው ስለ ኤፍራጥስ ወንዝ እንዲህ በማለት ትንቢት ተናግረዋል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 54, ሐዲስ 38
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሰዓቲቱ የኤፍራጥስ ወንዝ የወርቅ ተራራ እስኪገልጥ ድረስ ቢደርቅና በእርሱ ጉዳይ ሰዎች ቢዋጉ እንጂ አትቆምም"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ لاَ تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى يَحْسِرَ الْفُرَاتُ عَنْ جَبَلٍ مِنْ ذَهَبٍ يَقْتَتِلُ النَّاسُ عَلَيْهِ
ሪያዱ አስ-ሷሊሒን መጽሐፍ 18, ሐዲስ 15
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሰዓቲቱ የኤፍራጥስ ወንዝ የወርቅ ተራራ እስኪገልጥ ድረስ ቢደርቅና ሰዎች በእርሱ ጉዳይ ቢዋጉ እንጂ አትቆምም"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ لاَ تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى يَحْسِرَ الْفُرَاتُ عَنْ جَبَلٍ مِنْ ذَهَبٍ فَيَقْتَتِلُ النَّاسُ عَلَيْهِ ‏"‏ ‏.‏

ከሰዓቲቱ ምልክት አንዱ የኤፍራጥስ ወንዝ መድረቅ ከሆነ ይህ ትንቢት በዘመናችን እየተፈጸመ ነው። የኤፍራጥስ ወንዝ እየደረቀ ነው፥ የወርቁ ተራራ ኢንሻሏህ ሲገለጥ ታላቁ ጦርነት ይመጣል። አምላካችን አሏህ ይህንን ገይብ ለነቢዩ"ﷺ" አሳውቋል፥ "ገይብ" غَيْب የሚለው ቃል "ጋበ" غَابَ ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "የሩቅ ወሬ" "የሩቅ ሚስጥር" ማለት ነው፦
81፥24 እርሱም በሩቁ ወሬ ላይ ንፉግ አይደለም፡፡ وَمَا هُوَ عَلَى الْغَيْبِ بِضَنِينٍ

"ዘኒን" ظَنِين ማለት "ሰሳች" "ንፉግ" ማለት ሲሆን ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ከአሏህ የተቀበሉትን ገይብ ሳይሰስቱ ነግረውናል። ይህንን ገይብ ከልብ ወለድም አልተናገሩም፥ ንግግራቸው የሚወርድ ግልጠተ መለኮት እንጂ ሌላ አይደለም፦
53፥3 ከልብ ወለድም አይናገርም፡፡ وَمَا يَنطِقُ عَنِ الْهَوَىٰ
53፥4 እርሱ ንግግሩ የሚወረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ إِنْ هُوَ إِلَّا وَحْيٌ يُوحَىٰ

አምላካችን አሏህ በነቢያችን"ﷺ" ሡናህ ከሚጠቀሙ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የእግር ኳስ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

49፥10 ምእመናን ወንድማማች ናቸው፡፡ إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ

"ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلٰهَ إِلَّا اللّٰه ጠንካራ ዘለበት ነው፥ በጣዖት ክደን በአሏህ ስናምን እራሳችንን ለአሏህ እንሰጣለን፦
2፥256 "በጣዖትም የሚክድ እና በአላህ የሚያምን ሰው ለእርሷ መበጠስ የሌላትን "ጠንካራ ዘለበት" በእርግጥ ጨበጠ"፡፡ فَمَن يَكْفُرْ بِالطَّاغُوتِ وَيُؤْمِن بِاللَّهِ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ لَا انفِصَامَ لَهَا
31፥22 "እርሱ መልካም ሠሪ ሆኖ ፊቱን ወደ አላህ የሚሰጥም ሰው "ጠንካራን ዘለበት" በእርግጥ ጨበጠ"፡፡ وَمَن يُسْلِمْ وَجْهَهُ إِلَى اللَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ

እዚህ አንቀጽ "የሚሰጥ" ለሚለው የገባው ቃል እራሱ "ዩሥሊም" يُسْلِمْ መሆኑ በራሱ "ሙሥሊም" مُسْلِم ማለት የላ ኢላሀ ኢለል ሏህ ዘለበት በትክክል ዐውቆ እራሱ ለአሏህ የሰጠ ማለት ነው፥ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" የሚለውን የአሏህን ገመድ የያዘ ሰው በዘር፣ በብሔር፣ በዘውግ፣ በቋንቋ፣ በባህል አይለያይም፦
3፥103 የአላህን ገመድ ሁላችሁም ያዙ! አትለያዩም። وَاعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللَّهِ جَمِيعًا وَلَا تَفَرَّقُوا ۚ

"ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" በዘር፣ በብሔር፣ በዘውግ፣ በቋንቋ፣ በባህል ጠበኞች የነበሩትን ሊያስተሳስር የሚችል የአሏህ ፀጋ ነው፦
3፥103 ጠበኞችም በነበራችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ የዋለውን የአላህን ጸጋ አስታውሱ! በልቦቻችሁም መካከል አስማማ፥ በጸጋውም ወንድማማቾች ኾናችሁ፡፡ በእሳት ጉድጓድ አፋፍም ላይ ነበራችሁ፥ ከእርስዋም አዳናችሁ፡፡ እንደዚሁ ትመሩ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾቹን ያብራራል፡፡ وَاذْكُرُوا نِعْمَتَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ كُنتُمْ أَعْدَاءً فَأَلَّفَ بَيْنَ قُلُوبِكُمْ فَأَصْبَحْتُم بِنِعْمَتِهِ إِخْوَانًا وَكُنتُمْ عَلَىٰ شَفَا حُفْرَةٍ مِّنَ النَّارِ فَأَنقَذَكُم مِّنْهَا ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمْ آيَاتِهِ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ

ከእሳት ጉድጓድ ተንጠልጥሎ ለመውጣት የሚያስችል ብቸኛው ገመድ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" የሚለው የአሏህ ገመድ ነው፥ በዘር፣ በብሔር፣ በዘውግ፣ በቋንቋ፣ በባህል ጥላቻ እና ቂም አጥፍቶ የሚያስማማ፣ የሚያስተሳስር፣ ወንድማማች የሚያረግ ይህ ገመድ ነው።

እግር ኳስ ደግሞ እራሱ የቻለ ጥበብ የያዘ የእስፓርት ክፍል ነው፥ እግር ኳስ ማየት ወይም አለማየት ሐራም እና መክሩሕ አሊያም ፈርድ እና ሙሥተሐብ ሳይሆን ሙባሕ ነው። ሰዎች ቡድን ሠርተው እየተቧደኑ ሙሥሊም ለሙሥሊም መሰዳደብ፣ መጠዛጠዝ፣ መናቆር ከዚያ አልፎ መመታታት የአሏህ ገመድ ከሁሉም በላይ ያለማስበለጥ ምልክት ነው፥ አንድን ኳስ ከሃይማኖት፣ ከብሔር፣ ከዘር ጋር አያይዞ መደገፍ ሆነ መቃወም ዲናዊ አይደለም።
አንድ አገር ሙሥሊም ስለሚበዛባት ልክ እንደ ክርስቲያን ቱዩብ ያለ ቻናል ጭፍን ጥላቻ በመያዝ መንዛት ጭፍንነት ነው፥ በኳስ ሙሥሊም የሚበዛበት አሊያም ክርስቲያን የሚበዛበት አገር ስላሸነፈ ሆነ ስለተሸነፈ ከእምነት ጋር አንዳች ትስስር የለውም። ኳስን ከእምነት ጋር የምታያይዙም ሰዎች የላ ኢላሀ ኢለል ሏህ ጠንካራ ዘለበት በቅጡ የተደረዳችሁ አይመስለኝም።
አምላካችን አሏህ በላ ኢላሀ ኢለል ሏህ ጠንካራ ዘለበት ወንድማማችነታችንን የምንጠብቅ ያርገን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ብቻውን ያለ ጌታ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

39፥45 አላህም ብቻውን በተወሳ ጊዜ የእነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ሰዎች ልቦች ይደነብራሉ፡፡ وَإِذَا ذُكِرَ اللَّهُ وَحْدَهُ اشْمَأَزَّتْ قُلُوبُ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِالْآخِرَةِ

"ሞኖስ" μόνος በባለቤት የሚገባ ቅጽል ነው፣ "ሞኖ" μόνῳ በርቱዕ ተሳቢ የሚገባ ቅጽል ነው፣ "ሞኖን" μόνον ደግሞ በኢርቱዕ ተሳቢ የሚገባ ቅጽል ሲሆን "ብቻ" ማለት ነው፥ ይህ ገላጭ ቅጽል ለአብ ብዙ ቦታ ገብቷል፦
ዮሐንስ 17፥3 እውነተኛ አምላክ ብቻህን የሆንህ አንተን እና የላክኸውን ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት። αὕτη δέ ἐστιν ἡ αἰώνιος ζωή, ἵνα γινώσκωσιν σὲ τὸν μόνον ἀληθινὸν θεὸν καὶ ὃν ἀπέστειλας Ἰησοῦν Χριστόν.
ሮሜ 16፥27 "ብቻውን" ጥበብ ላለው "ለ-"አምላክ" "በ-"ኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን! አሜን። μόνῳ σοφῷ Θεῷ, διὰ Ἰησοῦ Χριστοῦ, ᾧ ἡ δόξα εἰς τοὺς αἰῶνας τῶν αἰώνων· ἀμήν.

ኢየሱስ የላከው ብቻውን እውነተኛ አምላክ የሆነው እስከ ዘላለም ድረስ ክብር በኢየሱስ በኩል የሚቀርብለት ከሆነ የተላከውን ኢየሱስ እና ብቻውን ጥበብ ያለው አምላክ በማንነት ሆነ በምንነት ይለያያሉ፥ ብቻውን ለሆነ አምላክ ክብር፣ ግርማ፣ ኃይል እና ሥልጣን በኢየሱስ አማካኝነት ይቀርብለታል፦
ይሁዳ 1፥25 "ብቻውን "ለ-ሆነ አምላክ እና መድኃኒታችን  ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን "በ-"ኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን። μόνῳ Θεῷ Σωτῆρι ἡμῶν διὰ Ἰησοῦ Χριστοῦ τοῦ Κυρίου ἡμῶν δόξα μεγαλωσύνη κράτος καὶ ἐξουσία πρὸ παντὸς τοῦ αἰῶνος καὶ νῦν καὶ εἰς πάντας τοὺς αἰῶνας· ἀμήν.

ይህ ብቻውን እውነተኛ አምላክ የሆነው፣ ብቻውን ጥበብ ያለው የማይሞት እና አንድ ሰው እንኳ ያላየው ነው፦
1 ጢሞቴዎስ 1፥17 "ብቻውን" አምላክ ለሚሆን ለማይሞተው፣ ለማይታየው፣ ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን። Τῷ δὲ Βασιλεῖ τῶν αἰώνων, ἀφθάρτῳ ἀοράτῳ μόνῳ Θεῷ, τιμὴ καὶ δόξα εἰς τοὺς αἰῶνας τῶν αἰώνων· ἀμήν.
1 ጢሞቴዎስ 6፥16 እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን። ὁ μόνος ἔχων ἀθανασίαν, φῶς οἰκῶν ἀπρόσιτον, ὃν εἶδεν οὐδεὶς ἀνθρώπων οὐδὲ ἰδεῖν δύναται· ᾧ τιμὴ καὶ κράτος αἰώνιον· ἀμήν.
1 ጢሞቴዎስ 6፥15 ያንም መገለጡን በራሱ ጊዜ ብፁዕና "ብቻውን የሆነ ገዥ" የነገሥታት ንጉሥ እና የጌቶች ጌታ ያሳያል። ἣν καιροῖς ἰδίοις δείξει ὁ μακάριος καὶ μόνος Δυνάστης, ὁ Βασιλεὺς τῶν βασιλευόντων καὶ Κύριος τῶν κυριευόντων,

1 ጢሞቴዎስ 6፥16 ላይ "እርሱ" የሚለው ተውላጠ ስም 1 ጢሞቴዎስ 6፥15 ላይ "ብቻውን የሆነ ገዥ" የተባለውን ማንነት ተክቶ የመጣ ነው፥ ስለዚህ "እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም" የተባለው አብ ሲሆን ይህም "ብቻውን የሆነ ገዥ" ነው። "ብቻውን የሆነ ገዥ" የተባለው አብ ይሁዳ ላይ "ብቻውን ያለውን ጌታ" ተብሏል፦
ይሁዳ 1፥4 ብቻውን ያለውን ጌታ እና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ። καὶ τὸν μόνον Δεσπότην καὶ Κύριον ἡμῶν Ἰησοῦν Χριστὸν ἀρνούμενοι.

"ዴስፖቴስ" δεσπότης ማለት "ጌታ" ማለት ሲሆን በግሪክ ሰፕቱአጀንት "ያህዌህ" יְהוָ֣ה የሚለው ቴትራግራማቶን ተክቶ የመጣ ነው፦
ኢሳይያስ 1፥24 ስለዚህ የእስራኤል ኃያል የሠራዊት ያህዌህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ לָכֵ֗ן נְאֻ֤ם הָֽאָדֹון֙ יְהוָ֣ה צְבָאֹ֔ות אֲבִ֖יר יִשְׂרָאֵ֑ל
ኢሳይያስ 1፥24 ስለዚህ የእስራኤል ኃያል የሠራዊት ጌታ ጌታ እንዲህ ይላል፦ διὰ τοῦτο τάδε λέγει Κύριος ὁ δεσπότης σαβαώθ, ὁ δυνάστης τοῦ ᾿Ισραήλ·
ልብ ብላችሁ ከሆነ "አዶን" אָדוֹן֙ ለሚለው በግሪኩ ያስቀመጡት "ኩርዮስ" Κύριος ሲሆን "ያህዌህ" יְהוָ֣ה ለሚለው ደግሞ "ዴስፖቴስ" δεσπότης ነው፥ ለዚያ ነው "ብቻውን ያለውን ጌታ" የተባለው ኢየሱስ ስላልሆነ ኮዴክስ ቤዛይ ላይ፦ "ብቻውን ያለውን ጌታ አምላክ" በማለት አብ ለማመልከት የተቀመጠው፦
ይሁዳ 1፥4 ብቻውን ያለውን ጌታ አምላክ እና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ። καὶ τὸν μόνον δεσπότην θεὸν καὶ κύριον ἡμῶν Ἰησοῦν χριστὸν ἀρνούμενοι.

"ቴዎን" θεὸν የሚለውን ቃል አትለፉት! ለዚያ ነው በ 1611 ድኅረ ልደት በታተመው ቅጂ The King James Version (KJV) ላይ "and denying the only Lord God, and our Lord Jesus Christ" ብለው ያስቀመጡት። "ዴስፖቴን ቴዎን" δεσπότην θεὸν እና "ኩርዮን ቶን ቴዎን" ማለት "ጌታ አምላክ" ማለት ሲሆን "ያህዌህ ኤሎሂም" የሚለውን ተክቶ የመጣ ነው፦
ማቴዎስ 4፥10 "ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ" Κύριον τὸν θεόν σου προσκυνήσεις καὶ αὐτῷ μόνῳ λατρεύσεις.
ዘዳግም 6፥13 ያህዌህ አምላክህን ፍራ እርሱንም አምልክ በስሙም ማል። אֶת־יְהוָ֧ה אֱלֹהֶ֛יךָ תִּירָ֖א וְאֹתֹ֣ו תַעֲבֹ֑ד וּבִשְׁמֹ֖ו תִּשָּׁבֵֽעַ׃

ስለዚህ በቀላሉ "ብቻውን ያለውን ያህዌህ አምላክ እና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ" ማለት ነው። ይህን ከተረዳን ግራንቪል ሻርፕ የተሰኘ የግሪክ ስድስት ሰዋስው መርሕ መካከል አንደኛ መርሕ ላይ፦ "ሁለት ነጠላ የማዕረግ ስሞች "እና" በሚል መስተጻምር ተያይዘው ተመሳሳይ ሙያ ካላቸው እና የመጀመሪያው የማዕረግ ስም ከፊቱ ላይ ውስን መስተአምር ካለ በተቃራኒው ሁለተኛው የማዕረግ ስም ከፊቱ ላይ ውስን መስተአምር ከሌለ የሚያመለክተው አንድ ማንነትን ነው" የሚል ነው።

በዚህ ሕግ ይሁዳ 1፥4 የመጀመሪያው የማዕረግ ስም "ዴስፖቴን" δεσπότην ሲሆን ከፊቱ ላይ "ቶን" τὸν የሚል ውስን መስተአምር አለው፥ በተቃራኒው ሁለተኛው የማዕረግ ስም ደግሞ "ኩርዮን" Κύριον ሲሆን ከፊቱ ላይ "ቶን" τὸν የሚል ውስን መስተአምር የለውም። "ዴስፖቴን" እና "ኩርዮን" በሚል ሁለት የማዕረግ ስሞች መካከል "ካይ" καὶ የሚል መስጻምር አለ፥ ቅሉ ግን ከካይ በፊት ያለው "ዴስፖቴን" ሙያው ተሳቢ ሙያ ሲሆን ከካይ በኃላ ያለው "ኩርዮን" ደግሞ "ሄሞን" ἡμῶν ማለትም "የእኛ" የሚል አገናዛቢ ሙያ ስላለ ሁለት የተለያየ ሙያዎች ናቸው። ስለዚህ "ጌታ" እና "ጌታችን" ሁለት የተለያየ ሙያ ሆነው ስለመጡ "ብቻውን ያለውን ጌታ አምላክ" የተባለው አብ እና ጌታችን የተባለው ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ለየቅል የሆኑ ምንነት እና ማንነት ናቸው።

በአዲስ ኪዳን ተዛማች ጥቅስ "ዴስፖቴስ" δεσπότης የሚለው ቃል "ጌታ" በሚል ለአብ ብዙ ቦታ መጥቷል፥ አረጋዊ ስምዖን ሕፃኑን አቅፎ የሕፃኑን አምላክ አብን እየባረከ "ዴስፖቴስ" በማለት ተናግሯል፦
ሉቃስ 2፥28-29 እርሱ ደግሞ ተቀብሎ አቀፈው አምላክንም እየባረከ እንዲህ አለ፦ "ጌታ" ሆይ! አሁን እንደ ቃልህ ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ። καὶ αὐτὸς ἐδέξατο αὐτὸ εἰς τὰς ἀγκάλας καὶ εὐλόγησεν τὸν Θεὸν καὶ εἶπεν Νῦν ἀπολύεις τὸν δοῦλόν σου, Δέσποτα, κατὰ τὸ ῥῆμά σου ἐν εἰρήνῃ·

ሐዋርያት ወደ አንዱ አምላክ ወደ አብ ሲጸልዩ "ዴስፖቴስ" በማለት እና ኢየሱስ ደግሞ በዲስፓቴስ የተቀባ የዲስፓቴስ ባሪያ እንደሆነ ተናግረዋል፦
የሐዋርያት ሥራ 4፥24 እነርሱም በሰሙ ጊዜ በአንድ ልብ ሆነው ወደ አምላክ ድምፃቸውን ከፍ አደረጉ እንዲህም አሉ፦ "ጌታ" ሆይ! አንተ ሰማዩንና ምድሩን ባሕሩንም በእነርሱም የሚኖረውን ሁሉ የፈጠርህ። οἱ δὲ ἀκούσαντες ὁμοθυμαδὸν ἦραν φωνὴν πρὸς τὸν Θεὸν καὶ εἶπαν Δέσποτα, σὺ ὁ ποιήσας τὸν οὐρανὸν καὶ τὴν γῆν καὶ τὴν θάλασσαν καὶ πάντα τὰ ἐν αὐτοῖς,

"ብቻውን ያለው ጌታ" የተባለበት በጌትነቱ የሚጋራው የሌለው እንደሆነ ለመግለጽ ነው፥ ይህ በጌትነቱ እና በአምላክነቱ ማንም የማይመስለው ብቻውን ያለ ነው፦
ነህምያ 9፥6 አንተ ብቻ ያህዌህ ነህ። אַתָּה־ה֣וּא יְהוָה֮ לְבַדֶּךָ֒
ኢዮብ 23፥13 እርሱ ግን ብቻውን ነው፥ እርሱንስ የሚመስለው ማን ነው?

ብቻውን ያለውን ጌታ አምላክ እና ኢየሱስ ከመካድ ይልቅ ኢየሱስ "በአምላክ እመኑ" "በእኔም እመኑ" በማለት እርሱ እና አምላኩ ሁለት የተለያዩ ምንነት እና ማንነት እንደሆኑ አበክሮ እና አዘክሮ ተናግሯል፦
ዮሐንስ 14፥1 በአምላክ እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ። πιστεύετε εἰς τὸν Θεόν, καὶ εἰς ἐμὲ πιστεύετε.

"በእኔ" በሚለው ቃል ላይ “ም” የሚለው ጥገኛ ምዕላድ በዐማርኛ ተጨማሪ ነገርን ለማሳየት የገባው በግሪኩ "ካይ" καὶ ማለትም "እና" የሚለውን መስተጻምር ለማሳየት የገባ ነው፥ ይህም አምላክ እና መልእክተኛው ሁለት የተለያዩ ሃልዎት እና ኑባሬ እንደሆኑ ቁልጭ አርጎ ያሳያል።
አምላካችን አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፥ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ አሏህ ብቻውን በተወሳ ጊዜ የእነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ሰዎች ልቦች ይደነብራሉ፦
2፥163 አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፥ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ እርሱ እጅግ በጣም ርኅሩህ አዛኝ ነው፡፡ وَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الرَّحْمَـٰنُ الرَّحِيمُ
39፥45 አላህም ብቻውን በተወሳ ጊዜ የእነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ሰዎች ልቦች ይደነብራሉ፡፡ وَإِذَا ذُكِرَ اللَّهُ وَحْدَهُ اشْمَأَزَّتْ قُلُوبُ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِالْآخِرَةِ

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
Video
ይችላል ወይስ አይችልም?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

15፥45 አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ وَكَانَ اللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ مُّقْتَدِرًا

አምላካችን አሏህ ስለ እርሱ ኑባሬ በሦስተኛ መደብ ሲናገር፦ "አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው" በማለት አለመቻል በእርሱ ቻይነት ላይ እንደሌለበት ይናገራል፦
15፥45 አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ وَكَانَ اللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ مُّقْتَدِرًا

ነገር ግን ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ፦ "አምላክ ሁሉን ማድረግ ይችላል ወይስ አይችልም? በማለት ይጠይቅና መልሱ "ይችላል" ከሆነ "መውለድ እና መወለድ አይችልም ወይስ ይችላል? የሚል ስሑት ጥያቄ ይጠይቃል።
፨ሲጀመር "ማድረግ" "ማስሆን" እና "መደረግ" "መሆን" ልዩነት አላቸው። ለምሳሌ፦ "መላእክት ወንድ ናቸው ወይስ ሴት? ተብሎ ቢጠየቅ ከመነሻው ጥያቄው ስሑት ጥያቄ ነው፥ ምክንያቱም ሴት እና ወንድ ፆታ ላለው ተፈጥሮ እንጂ ፆታ ለሌላቸው ለመላክእት አይሆንም። "መውለድ" እና "መወለድ" ደግሞ "መሆን" እንጂ "ማስሆን" አይደለም፥ "መደረግ"  እንጂ "ማድረግ" አይደለም። በአሏህ ባሕርይ ውስጥ "ማስሆን" እንጂ "መሆን" ወይም "ማድረግ" እንጂ "መደረግ" የሚባል ባሕርይ የለም፥ እርሱ "ነው" እንጂ "ሆነ" አይባልም። እርሱ የሚያስሆን እና የሚያደርግ እንጂ የሚሆን እና የሚደረግ አይደለም፥ መውለድ ወላዲ መሆን መወለድ ተወላዲ መሆን ስለሆነ እርሱ የሚያስሆን እንጂ የሚሆን አይደለም።
አሏህ ከወለደ ከአንድ ወደ ሁለት ይባዛል፥ ከተወለደ በአጭር ቁመትና በጠባብ ደረት ተወስኖ ፍጡር፣ ሟች፣ ደካማ፣ እንቅልፋም፣ ባሪያ ይሆናል። ስለዚህ ከፍጥረት ውጪ ጊዜ እና ቦታን ያካበበ ፈጣሪ በአንድነቱ ሁለትነት የለውም፥ "አሏህ "መሆን" ይችላል ወይስ አይችልም?" ተብሎ የሚጠየቀው የዐላዋቂዎች ጥያቄ ሁለት ስሑት ቀጠና"false dichotomy" ነው። ይህም ሥነ-አመክኗዊ ሕፀፅ"logical fallacy" አለበት፥ ምክንያቱም "መሆን" እና "አለመሆን" የፍጡር ባሕርይ እንጂ የፈጣሪ ባሕርይ ስላልሆነ ሌላ "ማስሆን" የሚባል ሦስተኛ ቀጠና"trichotomy" አለ።
፨ሲቀጥል መውለድ መንስኤ ሲሆን መወለድ ውጤት ነው፥ አብ አስገኝ ወልድ ተገኚ ከሆነ በመካከላቸው ድብን አድጎ መሽቀዳደም አለ። ይህም የመንስኤ እና የውጤት መቀዳደም ነው፥ ወላዲ አስገኝ በመሆን አስጀማሪ ሲሆን ተወላዲ ተገኚ በመሆን ተጀማሪ ስለሚሆን በመካከላቸው የመንስኤ እና የውጤት መቀዳደም አለ።

በመቀጠል፦ "እግዚአብሔር የማይችለው አንድ ነገር ነው፥ እርሱም አለመቻልን ነው" ይለናል፥ እንደ እርሱ ስሑት ሙግት እግዚአብሔር አለመቻልን ካልቻለ ሁሉን ቻይ አይደለም ማለት ነው። "አምላክ ሁሉን ነገር ማድረግ ከቻለ አለመቻል መቻል እንዴት ያቅተዋል? ለምሳሌ፦ "ፈጣሪ ሁሉን ቻይ "አለመሆን" ይችላል ወይስ አይችልም?" ብንል "ይችላል" ካልን ሁሉን ቻይ አይደለም፥ ምክንያቱም ሁሉን ቻይ አለመሆን መቻሉ ሁሉን ቻይ አያስብለውም። "አይችልም" ካልን ሁሉን ቻይ አይደለም፥ ምክንያቱም ሁሉን ቻይ አለመሆን አለመቻሉ ነው።
ስለዚህ ጥያቄው ሥነ-አመክኗዊ ሕፀፅ አለበት፥ ሦስተኛ ቀጠና ግን ከመሆን እና ከአለመሆን ነጻ የወጣ "ማስሆን" የሚባል ባሕርይ ስላለ "አሏህ ሰው "ማስሆን" "ማድረግ" ይችላል ወይስ አይችልም?" ወይም "አሏህ ሰው እንዲወልድ እና እንዲወለድ "ማስሆን" "ማድረግ" ይችላል ወይስ አይችልም?" ተብሎ መጠየቅ አለበት! መልስ አሏህ ነገርን ሁሉ "በማድረግ" እና "በማስሆን" ቻይ ነው።

ክርስቲያኖች ሆይ! የሚገዳደረው ወደረኛ፣ የሚቀናቀነው ተቀናቃኝ፣ የሚተካከለው እኩያ፣ የሚፎካከረው አቻ፣ የሚመስለው አምሳያ የሌለውን አንዱን አምላክ አሏህን በብቸኝነት እንድታመልኩት ጥሪአችን ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የአሏህ መልእክተኛ ኢየሱስ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

4፥71 የመርየም ልጅ አል-መሲሕ ዒሣ የአላህ መልእክተኛ ብቻ ነው። إِنَّمَا الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ اللَّهِ

"ረሡል" رَسُول የሚለው ቃል "አርሠለ" أَرْسَلَ ማለትም "ላከ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መልእክተኛ" ማለት ነው፥ "ሪሣላህ" ማለት "መልእክት" ማለት ሲሆን "ሙርሢል” مُرْسِل ማለት ደግሞ "ላኪ" ማለት ነው። አምላካችን አሏህ "ሙርሢል" ሲሆን ዒሣ ኢብኑ መርየም ደግሞ "ረሡል" ነው፦
4፥71 የመርየም ልጅ አል-መሲሕ ዒሣ የአላህ መልእክተኛ ብቻ ነው። إِنَّمَا الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ اللَّهِ

አሏህ ለዒሣ እንዲያስተላልፍ የሰጠው "ሪሣላህ" ኢንጂል ነው፥ እርሱ ከበፊቱ መልእክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልእክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፦
5፥75 የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልእክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልእክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ

አምላካችን አሏህ ዒሣን የላከው ለእስራኤል ልጆች ነው፥ እርሱም በተልኮው፦ "ወደ እናንተ የተላክሁ የአላህ መልእክተኛ ነኝ" በማለት ተናግሮ እንደነበረ አሏህ ነግሮናል፦
3፥49 ወደ እስራኤልም ልጆች መልእክተኛ ያደርገዋል፡፡ وَرَسُولًا إِلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ
61፥6 የመርየም ልጅ ዒሳም፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! እኔ ከተውራት በፊቴ ያለውን የማረጋግጥና ከእኔ በኋላ በሚመጣው መልእክተኛ ስሙ አሕመድ በኾነው የማበስር ስኾን ወደ እናንተ የተላክሁ የአላህ መልክተኛ ነኝ» ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ قَالَ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ يَا بَنِي إِسْرَائِيلَ إِنِّي رَسُولُ اللَّهِ إِلَيْكُم مُّصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيَّ مِنَ التَّوْرَاةِ وَمُبَشِّرًا بِرَسُولٍ يَأْتِي مِن بَعْدِي اسْمُهُ أَحْمَدُ

በባይብል ባለው መለኮታዊ ቅሪት ኢየሱስ፦ "ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም" ብሏል፦
ማቴዎስ 15፥24 እርሱም መልሶ፦ "ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም" አለ።

ኢየሱስ የአምላክ መልእክተኛ እንደሆነ በጥልቀት እስቲ እንይ! "እነሆ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል" የተባለው መልእክተኛ ዮሐንስ ነው፦
ሚልክያስ 3፥1 እነሆ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል።
ማቴዎስ 11፥10 "እነሆ መንገድህን በፊትህ የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ" ተብሎ የተጻፈለት ይህ ነውና።

"እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል" የተባለው የመቅደሱ ባለቤት እና አይሁዳውያን የሚፈልጉት ያህዌህ ነው፥ አሞጽ5፥4 ዘሌዋውያን 19፥30 ሚልክያስ 4፥6 ተመልከት! "የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ እነሆ ይመጣል" የተባለው መልእክተኛ መሢሑ ነው፦
ሚልክያስ 3፥1 የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ እነሆ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌህ። וּמַלְאַ֨ךְ הַבְּרִ֜ית אֲשֶׁר־אַתֶּ֤ם חֲפֵצִים֙ הִנֵּה־בָ֔א אָמַ֖ר יְהוָ֥ה צְבָאֹֽות׃

እዚህ አንቀጽ ላይ ፈጣሪ ስለ መሢሑ መምጣት ከአባቶች ጋር ቃል ኪዳን ስለገባላቸው "የቃል ኪዳን መልእክተኛ" ተብሏል፥ በዕብራይስጥ ማሶሬት "ማላክ" מֲלְאָךְ ማለት "መልእክተኛ" ማለት ሲሆን የሚመጣው መሢሕ የአምላክ መልእክተኛ እንደሆነ በቀላሉ መረዳት ይቻላል። በአዲስ ኪዳን ይህ "ይመጣል" ተብሎ የተነገረለት መልእክተኛ ኢየሱስ ነው፦
ማቴዎስ 10፥40 እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።

"የላከኝን" የሚለው ቃል ይሰመርበት! ላኪ አምላክ ሲሆን ተላኪ መልእክተኛ ደግሞ ኢየሱስ ነው፥ ኢየሱስ "እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል" ሲል ጳውሎስ ደግሞ "እንደ የአምላክ መልእክተኛ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ተቀበላችሁኝ" በማለት ኢየሱስ "የአምላክ መልእክተኛ" መሆኑን አስረግጦ እና ረግጦ ተናግሯል፦
ገላትያ 4፥14 ነገር ግን እንደ አምላክ መልእክተኛ አዎን እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ ተቀበላችሁኝ። ἀλλὰ ὡς ἄγγελον Θεοῦ ἐδέξασθέ με, ὡς Χριστὸν Ἰησοῦν.

"አዎን" ማለት ማረጋገጫ ነው፥ "አዎን" ክርስቶስ ኢየሱስ "የአምላክ መልእክተኛ" መሆኑን ለማረጋገጥ የገባ ነው። እዚህ አንቀጽ ላይ በዐማርኛው "መልአክ" ቢለውም በግሪኩ "አንገሎን" ወይም "አገሎን" ἄγγελον በሚል ተሳቢ ሙያ አስቀምጦታል፥ "አንገሎስ" ወይም "አገሎስ" ἄγγελος ማለት በቀላሉ "መልእክተኛ" ማለት ሲሆን ለነቢዩ ዮሐንስ መልእክተኛነት ገብቷል፦
ማቴዎስ 11፥10 "እነሆ መንገድህን በፊትህ የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ" ተብሎ የተጻፈለት ይህ ነውና። οὗτός ἐστιν περὶ οὗ γέγραπται Ἰδοὺ ἐγὼ ἀποστέλλω τὸν ἄγγελόν μου πρὸ προσώπου σου, ὃς κατασκευάσει τὴν ὁδόν σου ἔμπροσθέν σου.
እዚህ አንቀጽ ላይ ዮሐንስ "መልእክተኛ" የተባለበት ቃል በተመሳሳይ "አንገሎስ" ἄγγελος ነው። "አፓስቶሎስ" ἀπόστολος ማለት እራሱ "መልእክተኛ" ማለት ሲሆን ኢየሱስ "አፓስቶሎስ" ተብሏል፦
ዕብራውያን 3፥1 የሃይማኖታችንን "መልእክተኛ" እና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ፤ κατανοήσατε τὸν Ἀπόστολον καὶ Ἀρχιερέα τῆς ὁμολογίας ἡμῶν Ἰησοῦν,
ዮሐንስ 13፥16 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም። "መልእክተኛም" ከላከው አይበልጥም። ἀμὴν ἀμὴν λέγω ὑμῖν, οὐκ ἔστιν δοῦλος μείζων τοῦ κυρίου αὐτοῦ, οὐδὲ ἀπόστολος μείζων τοῦ πέμψαντος αὐτόν.

ዕብራውያን 3፥1 ላይ "ሐዋርያ" የተባለበት እና ዮሐንስ 13፥16 ላይ "መልእክተኛ" የተባለበት "አፓስቶሎስ" ἀπόστολος ነው። እንግዲህ ኢየሱስ መልእክተኛ ከሆነ እርሱ ጋር የሌለ ግን ሌላ ማንነት ጋር ያለው ዕውቀት ለማስተላለፍ የተላከ ተላላኪ ነው፦
ዮሐንስ 12፥49 እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ።
ዮሐንስ 14፥10 እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም።
ዮሐንስ 12፥50 ስለዚህ እኔ የምናገረውን አብ እንደ ነገረኝ እንዲሁ እናገራለሁ።
ዮሐንስ 14፥24 የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም።

የሚለው እና የሚናገረው መልእክት፣ ዕውቀት፣ ትምህርት ከተሰጠው ያ የተሰጠው ዕውቀት፣ መልእክት፣ ትምህርት እርሱ ጋር አልነበረም ማለት ነው፥ ሰጪ ላኪ ሲሆን ተቀባይ ደግሞ መልእክተኛው ከሆነ ስጦታው መልእክቱ፣ ዕውቀት፣ ትምህርት ነው። አንድ ሁሉን ዐዋቂ አምላክ ሙሉ ዕውቀት ካለው ለሌላ ምንነት እና ማንነት እንዴት መልእክተኛ ይሆናል? ከሌላ ምንነት እና ማንነት ምን እንደሚናገር ትእዛዝ እየተቀበለ እንዴት ይናገራል? ከራሱ ምንም መናገር ካልቻለ እራሱ ጋር በቂ ትምህርት፣ ዕውቀት እና መልእክት የለውም ማለት ነው። ከራሱ የማይናገር እና የሚናገረው የላከው እንጂ የራሱ ካልሆነ እንዴት ሙሉ አምላክ ይሆናል? እውነት “እግዚአብሔር ወልድ” የሚባል ሙሉ አምላክነት ያለው ከሆነ ከሌላ ምንነት እና ማንነት መልእክት እየሰማ ለሕዝብ እንዴት ይናገራል? ይህ መልእክተኛ ግን ከላከው እየሰማ እና እየተማረ የሚናገር ነቢይ ነበር፦
ዮሐንስ 8፥26 ዳሩ ግን የላከኝ እውነተኛ ነው፥ እኔም ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለዓለም እናገራለሁ።
ዮሐንስ 7፥16 ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም።
ዮሐንስ 8፥28 አባቴም እንዳስተማረኝ እነዚህን እናገር ዘንድ እንጂ ከራሴ አንዳች እንዳላደርግ በዚያን ጊዜ ታውቃላችሁ።

ሙሉ ዕውቀት ያለው ሰው ከሌላ ማንነት አይማርም፥ ኢየሱስ ግን የሚናገረው የላከው ያስተማረውን እንጂ ከራሱ ምንም አልተናገረም። እውነት ግን አንድ እውነተኛ አምላክ ሙሉ ዕውቀት እያለው ከሌላ ምንነት እና ማንነት ይሰማልን? ከሌላ ኑባሬ ተምሮ ማስተላለፍ በምን ስሌት እና ቀመር ነው ሙሉ አምላክ የሚያስብለው? ኢየሱስ የራሱ ሙሉ ዕውቀት ቢኖረው ኖሮ ማንም ሳይልከው እራሱ በራሱ ከራሱ ይመጣ ነበር፥ ነገር ግን እርሱ ተልኮ እንጂ ከራሱ እና በራሱ አልመጣም፦
ዮሐንስ 8፥42 እርሱ ላከኝ እንጂ ከራሴ አልመጣሁምና።
ዮሐንስ 7፥28 እኔም በራሴ አልመጣሁም፡ ነገር ግን እናንተ የማታውቁት የላከኝ እውነተኛ ነው።

በእርግጥ እነርሱ እንደሚሉት ኢየሱስ “እግዚአብሔር ወልድ” የሚባል አምላክ ሆኖ “እግዚአብሔር አብ” ከሚባል አምላክ እየሰማ እና እያዳመጠ የሚናገር ሳይሆን ከአንዱ አምላክ እየሰማ ሲያስተላልፍ የነበረው ሰው ነው፦
ዮሐንስ 8፥40 ነገር ግን አሁን ከአምላክ የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ። νῦν δὲ ζητεῖτέ με ἀποκτεῖναι, ἄνθρωπον ὃς τὴν ἀλήθειαν ὑμῖν λελάληκα, ἣν ἤκουσα παρὰ τοῦ Θεοῦ·

እዚህ አንቀጽ ላይ "አምላክ" አሰሚ ባለቤት ሲሆን "ሰው" ሰሚ ተሳቢ ነው፥ በአምላክ እና በሰው መካከል "የሰማሁት" የሚል አጫፋሪ ግሥ"transitive verb" አለ። ስለዚህ ኢየሱስ የአምላክ መልእክተኛ ነው። ይህንን ሰው እና መልእክተኛ የምታመልኩ አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የተቀረጸ ምስል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ "እኔን ብቻ አምልኩኝ"፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ

"ኤዴሎን" εἴδωλον ማለት "ምስል" ማለት ሲሆን "ላትሬኦ" λατρεία ደግሞ "አምልኮ" ማለት ነው፦
1 ቆሮንቶስ 10፥14 ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ! "ጣዖትን ከማምለክ" ሽሹ። Διόπερ, ἀγαπητοί μου, φεύγετε ἀπὸ τῆς εἰδωλολατρείας.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ጣዖት ማምለክ" ለሚለው የገባው ቃል "ኤዶሎላትሬኦ" εἰδωλολατρεία ሲሆን "የተቀረጸ ምስል ማምለክ" ማለት ነው፦
ዘጸአት 20፥4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ "የተቀረጸውን ምስል" ለአንተ አታድርግ። οὐ ποιήσεις σεαυτῷ εἴδωλον, οὐδὲ παντὸς ὁμοίωμα, ὅσα ἐν τῷ οὐρανῷ ἄνω καὶ ὅσα ἐν τῇ γῇ κάτω καὶ ὅσα ἐν τοῖς ὕδασιν ὑποκάτω τῆς γῆς.

እዚህ አንቀጽ ላይ "የተቀረጸውን ምስል" ለሚለው የገባው ቃል "ኤዴሎን" εἴδωλον ሲሆን በላይ በሰማይ ካለው ለመልአክ ወይም በታች በምድር ካለው ለሰው ምስል መስገድ ወይም ማምለክ የተከለከለ ነው፦
ዘጸአት 20፥5 አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም። οὐ προσκυνήσεις αὐτοῖς, οὐδὲ μὴ λατρεύσεις αὐτοῖς·

"ፕሩስኩኔኦ" προσκυνέω ማለት "ስግደት" ማለት ሲሆን "ላትሬኦ" λατρεία ማለት ደግሞ "አምልኮ" ማለት ነው፥ ለተቀረጸ ምስል መስገድ ሆነ ማምለክ ክልክል እንደሆነ በአጽንሮት እና በአንክሮት ተቀምጧል። ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ ከንቱዎች ናቸው፦
ኢሳይያስ 44፥9 የተቀረጸውን ምስል የሚሠሩ ሁሉ ከንቱዎች ናቸው።
መዝሙር 97፥7 ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ። αἰσχυνθήτωσαν πάντες οἱ προσκυνοῦντες τοῖς γλυπτοῖς, οἱ ἐγκαυχώμενοι ἐν τοῖς εἰδώλοις αὐτῶν·

እዚህ አንቀጽ ላይ "ጣዖት" ለሚለው የገባ ቃል "ኤዴሎን" εἴδωλον ሲሆን "የተቀረጸ ምስል" ማለት ነው። "ስዕል" ማለት በሰሌዳ ላይ በቀለም፣ በጠመኔ፣ በእርሳስ አለዚያም በሌላ ነገር ተስርቶ በዓይን በማየት የሚገነዘቡት የአንድ ማንነት ወይም ምንነት "ምስል" ማለት ነው፥ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ላይ ሥዕልን እንዲህ ይገልጹታል፦
ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መጽሐፈ ሰዋሰው ወግሥ ወመዝገበ ቃላት 673
"ስዕል" ማለት በቁም መልክ፣ የመልክ ጥላ፣ ንድፍ፣ አምሳል፣ ንድፍ በውኃ፣ በመጽሔት፣ በጥልፍ፣ በስፌት ወይም በቀለም በወረቀት ገዝፎ ተጽፎ ከደብር፣ ከእብን፣ ከእጽ፣ ከማዕድን ታንጦ፣ ተቀርጦ፣ ተሸልሞ፣ አጊጦ የሚታይ የሚዳሰስ ነገር ነው"፡፡

ስለዚህ ስዕል የተቀረጸ ምስል እስከሆነ ድረስ ለሥላሴ ስዕል አምልኮ ለፍጡራን ስዕል የጸጋ ስግደት መስገድ ክልክል ነው። ከዚህ በተቃራኒው በተአምረ ማርያም ላይ "ለሥዕሏ ያልሰገደ ግን ከቆመበት ቦታ ይጥፋ" ይላል፦
ተአምረ ማርያም የዘወትር መቅድም ቁጥር 35-36 ገጽ 7
"በስዕሏ ፊት ስገዱ! ለሥዕሏ ያልሰገደ ግን ከቆመበት ቦታ ይጥፋ! ስም አጠራሩ አይታወቅ። በሰማይ ያሉ መላእክትም ይደረግ ይሁን ይበሉ።

"በስዕሏ ፊት ስገዱ" የሚለውን ትእዛዛዊ መመሪያ ተመልከት! ስዕል የተቀረጸ ምስል ነው፥ አይሰማ አይለማ አይናገር አይጋገር ለምን ይሆን የሚሰገድለት? መስቀል እራሱ የተቀረጸ ምስል ነው፥ ነገር ግን የዘወትር ጸሎት ላይ፦ "ለ-ተሰቀለበት መስቀል እሰግዳለው" ይላል፦
የዘወትር ፀሎት
"ለ-ተሰቀለበት መስቀል እሰግዳለው"።

"ዕፀ መስቀል" ማለት "የእንጨት መስቀል" ማለት ነው፥ እንጨት ደግሞ አይሰማ አይለማ አይናገር አይጋገር ለምን ይሆን የሚሰገድለት? ስዕል ወረቀት ሲሆን መስቀል እንጨት ነው፥ እነዚህ የተቀረጹ ምስሎች "የጸጋ ስግደት ይገባቸዋል" የሚል መመሪያ ባይብል ላይ ፈጽሞ የለም።
በክርስትና ታሪክ ውስጥ የተቀረጸ ምስል ለአምልኮ መጠቀም በ 754 ድኅረ ልደት ላይ በተካሄደው በሄሪያ ጉባኤ ተወግዞ ነበር፥ ነገር ግን በ 787 ድኅረ ልደት በንጉሥ 6ኛ ቆስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት 2ኛ የኒቂያ ጉባኤ ላይ 308 ኤጲጵ ቆጶሳት ከተለያየ ቦታ ተሰብስበው ውግዘቱት አንስተው የተቀረጸ ስምል ለአምልኮ መጠቀም እንደሚቻል አጽድቀዋል። የሚያጅበው ከ 787 ድኅረ ልደት በፊት በነቢያችን"ﷺ" ዘመን የነቢያችን"ﷺ" ባልደረቦቻቸውን ወደ ሐበሻህ ሲልኳቸው ከሔዱት መካከል በአክሱም ቤተክርስቲያን ውስጥ ስዕላትን አይተዋል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 77
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ ”ኡሙ ሐቢባህ እና ኡሙ ሠለማህ በሐበሻህ ስላዩአት በውስጧ ስዕሎች ስለነበሩባት ቤተክርስቲያን ዘክረዋል፥ ስለዚህ ለነቢዩም”ﷺ”ዘክረዋል። እርሳቸውም እንዲህ አሉ፦ “በእነዚያ ሰዎች መካከል የትኛውም ሷሊሕ ሰው ቢሞት በመቃብሩ ላይ የአምልኮ ስፍራ ቢገነቡ እና እነዚህን ስዕላት ቢያደርጉ፥ በትንሳኤ ቀን በአላህ ዘንድ እነርሱ ከፍጥረት ሁሉ ክፉ ናቸው፡፡ عَنْ عَائِشَةَ، أَنَّ أُمَّ حَبِيبَةَ، وَأُمَّ سَلَمَةَ ذَكَرَتَا كَنِيسَةً رَأَيْنَهَا بِالْحَبَشَةِ فِيهَا تَصَاوِيرُ، فَذَكَرَتَا لِلنَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ ‏ “‏ إِنَّ أُولَئِكَ إِذَا كَانَ فِيهِمُ الرَّجُلُ الصَّالِحُ فَمَاتَ بَنَوْا عَلَى قَبْرِهِ مَسْجِدًا، وَصَوَّرُوا فِيهِ تِلْكَ الصُّوَرَ، فَأُولَئِكَ شِرَارُ الْخَلْقِ عِنْدَ اللَّهِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ

“ተስዊራህ” تَصْوِيرَة ማለት “ስዕል” ማለት ነው፥ የተስዊራህ ብዙ ቁጥር “ተሷዊር” تَصَاوِير ማለት ሲሆን “ስዕላት” ማለት ነው። ስዕል በአምልኮ ውስጥ ምንም ሚና መኖር የለበትም፥ የሥላሴ፣ የኢየሱስ፣ የማርያም፣ የመላእክት እና የቅዱሳን ሰዎች ስዕል ስሎ በፊታቸው መለማመን ባዕድ አምልኮ ነው። በኢሥላም አስተምህሮት ሙሥሊሞች ለአምልኮ የምንጠቀምበት የተቀረጸ ምስል የለም፥ ከአሏህ ውጪ የምናመልከው እና የምንሰግድለት ምንነት ሆነ ማንነት የለም። አምላካችን አሏህ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለቱ እኛ ሙሥሊሞች የአምልኮ ሐቅ ለእርሱ ብቻ እናቀርባለን፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ "እኔን ብቻ አምልኩኝ"፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ
21፥92 ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ "እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ"፡፡ إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةًۭ وَٰحِدَةًۭ وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُونِ

የአምልኮ ገንዘብ እና ሐቅ የሚገባው አሏህ "እኔ" ብሎ የሚናገር ነባቢ መለኮት ሲሆን ለተቀረጸ ምስል ከመስገድ እና ከማምለክ የፈጠረንን አንዱን አምላክ አሏህን በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ብርሃን ማን ነው?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥15 ከአላህ ዘንድ ብርሃን እና ገላጭ መጽሐፍ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ قَدْ جَاءَكُم مِّنَ اللَّهِ نُورٌ وَكِتَابٌ مُّبِينٌ

ፈጣሪ ብርሃን ነው፥ የእርሱ ብርሃንነት መነሻና ጅማሬ የሌለው ቀዳማይ እና መዳረሻና ፍጻሜ የሌለው ደሓራይ ነው፦
1 ዮሐንስ 1፥5 ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት፦ "አምላክ ብርሃን ነው፥ ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም" የምትል ይህች ናት። Καὶ ἔστιν αὕτη ἡ ἀγγελία ἣν ἀκηκόαμεν ἀπ’ αὐτοῦ καὶ ἀναγγέλλομεν ὑμῖν, ὅτι ὁ Θεὸς φῶς ἐστιν καὶ σκοτία ἐν αὐτῷ οὐκ ἔστιν οὐδεμία.

ዮሐንስ ከኢየሱስ የሰማው መልእክት፦ "አምላክ ብርሃን ነው፥ ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም" የሚል ነው፥ "አምላክ ብርሃን ነው፥ ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም" የሚለው መልእክት በአራቱም ወንጌላት ውስጥ የለም። ኢየሱስ የአምላክ መልእክተኛ ሲሆን ዮሐንስ ከእርሱ የሰማው ይህ መልእክት በአራቱ ወንጌል ያልተካተሉ የወንጌል ክፍሎች "አግራፎን" ይባላሉ፥ "አግራፎን" ἄγραφον ማለት "በቃል የተላለፈ መልእክት" ማለት ነው።
አንዱ አምላክ ኢየሱስን ብርሃን ስላደረገው ኢየሱስ ብርሃንነቱ መነሻ እና ጅማሬ ያለው ነው፦
ኢሳይያስ 42፥6 ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌ እሰጥሃለሁ። καὶ ἔδωκά σε εἰς διαθήκην γένους, εἰς φῶς ἐθνῶν
ኢሳይያስ 49፥6 ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌ ሰጥቼሃለሁ። ἰδοὺ δέδωκά σε εἰς διαθήκην γένους, εἰς φῶς ἐθνῶν τοῦ εἶναί σε εἰς.

"አድርጌ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! ብርሃን አድራጊ አንዱ አምላክ ሲሆን ብርሃን ተደራጊ ደግሞ ኢየሱስ ነው፥ ለዚያ ነው ኢየሱስ፦ "እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ" ያለው፦
ዮሐንስ 8፥12 እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ። Ἐγώ εἰμι τὸ φῶς τοῦ κόσμου·

ኢሳይያስ 49፥6 ላይ "ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌ ሰጥቼሃለሁ" የሚለውን አንቀጽ የጥንት አበው ለኢየሱስ ቢጠቀሙበትም ሐዋርያት ለእነርሱ የተነገረ ትንቢት እንደሆነ አበክረው እና አዘክረው ተናግረዋል፦
የሐዋርያት ሥራ 13፥47 እንዲሁ ጌታ፦
"እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ለማዳን ትሆን ዘንድ "ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ" ብሎ አዞናልና" አሉ።

"አሕዛብ" የሕዝብ ብዙ ቁጥር ሲሆን "ሕዝቦች" ማለት ነው። ኢየሱስን ሆነ ሐዋርያትን ብርሃን ያደረገ አንድ አምላክ ሲሆን ኢየሱስ በመጀመርያ መደብ እራሱን፦ "እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ" ባለበት አፉ ሳያቅማማ ሐዋርያትን በሁለተኛ መደብ፦ "እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ" ብሏቸዋል፦
ማቴዎስ 5፥14 እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። Ὑμεῖς ἐστε τὸ φῶς τοῦ κόσμου.

ኢየሱስ ሆነ ሐዋርያት "ብርሃን" ለተባሉበት የገባው ቃል "ፎስ" φῶς መሆኑን ልብ አድርግ! ስለዚህ "አምላክ ብርሃን ነው" ስለተባለ እና ኢየሱስ "እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ" ስላለ "ኢየሱስ አምላክ ነው" ካላችሁ እንግዲያውስ ሐዋርያት "እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ" ተብለዋልና "ሐዋርያት አምላክ ናቸው" ብላችሁ እረፉት። ቅሉ እና ጥቅሉ ግን አምላክ ብርሃን የተባለበት እና ኢየሱስ ብርሃን የተባለበት በይዘትም ሆነ በዓይነት፥ በመንስኤም ሆነ በውጤት ይለያያል።
በቁርኣን ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ብርሃን ተብለዋል፥ ነገር ግን የእርሳቸው ብርሃንነት በመደረግ ላይ የተመሠረተ ነው፦
5፥15 ከአላህ ዘንድ ብርሃን እና ገላጭ መጽሐፍ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ قَدْ جَاءَكُم مِّنَ اللَّهِ نُورٌ وَكِتَابٌ مُّبِينٌ
33፥46 ወደ አላህም በፈቃዱ ጠሪ፣ አብሪ ብርሃንም አድርገን ላክንህ፡፡ وَدَاعِيًا إِلَى اللَّهِ بِإِذْنِهِ وَسِرَاجًا مُّنِيرًا

ከላይ ያለውን ሙግት በዚህ መልክ እና ልክ መረዳት ይቻላል። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ፍጡር ማምለክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ "እኔን ብቻ አምልኩኝ"፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ

የኦርቶዶክስ መምህራን ከእነጀሌዎቻቸው እሥልምናን በዐውደ ምሕረት ላይ ሲያበሻቅጡ፣ ሲያብጠለጥሉ፣ ሲያነውሩ እኛ ሙሥሊሞች አጸፌታ ብንመልስ "አገር፣ ጎረቤት፣ ባልንጀርነት፣ ቤተሰብ ይፈርሳል" በማለት ስሜታችንን ገታ አርገን ከአሏህ አጅር ማግኘቱን መርጠን ነበር፥ ባይሆን የተተቸውን አሳብ ብቻ ረብጣ በሆነ አሳብ ለማረቅ ሞክረናል እንጂ ገጀራ አላነሳንም። ከሊቅ እስከ ደቂቅ በማሕበራዊ ሚድያ ላይ እንደፈለጉ እሥልምናን ሲሳደቡ ሲኖዶስ ሆነ መንግሥት "ተዉ" ብለው አያውቁም፥ ዛሬ ፓስተር ዮናታን አክሊሉ ለኃየሰው ኂስ ምድሪቱ ሸብረብ እስክትል ድረስ ያዙኝ ልቀቁኝ እና አሸሼ ገዳዬ ሲሉ ገርሞናል።

ፓስተር ዮናታን አክሊሉ በራሱ መድረክ ላይ ስሜታዊ ሆኖ ተአምረ ማርያም መቅድም ላይ ያሉትን አናቅጽ እየተነተነ ከሞገተ በኃላ፦ "አንዱ ኢትዮጵያን ጨለማ ውስጥ እና ድንቁርና ውስጥ ወደ ኃላ ኃላቀርነት ውስጥ የከተተው በፈጣሪ ፋንታ ፍጡርን ለማምለክ የሚደረግ ጣዖት አምላኪነት ነው" በማለት ፓለቲካ ይዘት ያለው መልእክት አስተላልፏል፥ ይህ ንግግሩ "የሰው ስሜት የጠበቀ ነው" ብዬ አላምንም።
ነገር ግን ፓስተር ዮናታን አክሊሉ ከመጽሐፉ ጠቅሶ እና አጣቅሶ ፦ "በስዕሏ ፊት ስገዱ! ለሥዕሏ ያልሰገደ ግን ከቆመበት ቦታ ይጥፋ! ስም አጠራሩ አይታወቅ" ይህ ጣዖት አምላኪነት ነው" በማለት ተናግራል፦
ተአምረ ማርያም የዘወትር መቅድም ቁጥር 35-36 ገጽ 7
"በስዕሏ ፊት ስገዱ! ለሥዕሏ ያልሰገደ ግን ከቆመበት ቦታ ይጥፋ! ስም አጠራሩ አይታወቅ። በሰማይ ያሉ መላእክትም ይደረግ ይሁን ይበሉ።

ለማርያም መስገድ እና ለስዕሏ መስገድ ሁለት ለየቅል ነገር ነው፥ ስዕል እኮ የማይሰማ የማይለማ የማይናገር የማይጋገር ግዑዝ ነገር ነው። ለዚህ ግዑዝ ነገር መስገድ በምን አግባብ ነው ትክክል የሚሆነው? የኦርቶዶክስ መምህራን እስካሁን ድረስ "በስዕሏ ፊት ስገዱ! ለሥዕሏ ያልሰገደ ግን ከቆመበት ቦታ ይጥፋ" የሚለው ኃይለ-ቃል ባይብላዊ መሠረት አርገው መልስ ሲሰጡት በፍጹም አይታይም። ስለዚህ ስዕል የተቀረጸ ምስል እስከሆነ ድረስ ጣዖት አምልኮ ነው፥ "ኤዴሎን" εἴδωλον ማለት "ምስል" ማለት ሲሆን "ላትሬኦ" λατρεία ደግሞ "አምልኮ" ማለት ነው፦
1 ቆሮንቶስ 10፥14 ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ! "ጣዖትን ከማምለክ" ሽሹ። Διόπερ, ἀγαπητοί μου, φεύγετε ἀπὸ τῆς εἰδωλολατρείας.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ጣዖት ማምለክ" ለሚለው የገባው ቃል "ኤዶሎላትሬኦ" εἰδωλολατρεία ሲሆን "የተቀረጸ ምስል ማምለክ" ማለት ነው፦
ዘጸአት 20፥4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ "የተቀረጸውን ምስል" ለአንተ አታድርግ። οὐ ποιήσεις σεαυτῷ εἴδωλον, οὐδὲ παντὸς ὁμοίωμα, ὅσα ἐν τῷ οὐρανῷ ἄνω καὶ ὅσα ἐν τῇ γῇ κάτω καὶ ὅσα ἐν τοῖς ὕδασιν ὑποκάτω τῆς γῆς.

እዚህ አንቀጽ ላይ "የተቀረጸውን ምስል" ለሚለው የገባው ቃል "ኤዴሎን" εἴδωλον ሲሆን በላይ በሰማይ ካለው ለመልአክ ወይም በታች በምድር ካለው ለሰው ምስል መስገድ ወይም ማምለክ የተከለከለ ነው፦
ዘጸአት 20፥5 አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም። οὐ προσκυνήσεις αὐτοῖς, οὐδὲ μὴ λατρεύσεις αὐτοῖς·

"ፕሩስኩኔኦ" προσκυνέω ማለት "ስግደት" ማለት ሲሆን "ላትሬኦ" λατρεία ማለት ደግሞ "አምልኮ" ማለት ነው፥ ለተቀረጸ ምስል መስገድ ሆነ ማምለክ ክልክል እንደሆነ በአጽንሮት እና በአንክሮት ተቀምጧል።
በመቀጠል ፓስተሩ፦ "በፈጣሪ ፋንታ የተፈጠረውን ማምለክ ጣዖት አምላኪነት ነው" ብሏል፥ ይህ ሁሉም የሚስማማበት ነጥብ ነው። በዚህ መርሕ እነ ዮናታንም ከጣዖት አምላኪነት የማያመልጡበት ምክንያት የኢየሱስ ፈጣሪ በብቸኝነት ከማምለክ ይልቅ የተፈጠረውን ኢየሱስን እያመለኩ ነው።

ኦርቶዶክሳውያን፦ "እኛ ማርያምን እናከብራታለን እንጂ አናመልካትም" በማለት ፓስተሩን ከሰውታል፥ ምክንያቱም ሰዎች የማይሉትን እና የማያምኑትን እንደሚሉ እና እንደሚያምኑ አርጎ መሞገት ቁልመማዊ ሕፀፅ"strawman fallacy" ነው። ነገር ግን ፓስተሩ የማይሉትን እና የማያምኑትን እንደሚሉ እና እንደሚያምኑ አርጎ አልሞገተም፥ ምክንያቱም በኦርቶዶክስ ማርያም በግልጽ ትመለካለችና። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በሐሙስ እንዚራ ስብሐት ላይ፦ "የአምልኮ መሥዋዕትንም ለአንቺ እሠዋለሁ" በማለት ያመልካታል፦
እንዚራ ስብሐት ምዕራፍ 12 ቁጥር 98 "ለአንቺም የምስጋና እጅ መንሻን አቀርባለሁ፣ በመፍራት እገዛልሻለሁ፣ በመስገድም እጅ እነሣሻለሁ። "የአምልኮ መሥዋዕትንም ለአንቺ እሠዋለሁ"።

የአምልኮ መሥዋዕት የሚቀርብለት አንድ አምላክ ሆኖ ሳለ ለማርያም የአምልኮ መሥዋዕት ማቅረቡ ግልጽ ማሻረክ አይደለምን? "ዐማርኛ ትክክል አይደለም" እንዳንል ግዕዙ ላይ "ለኪ እሠውዕ መሥዋዕተ አምልኮ" ብሎ በግልጽ አስቀምጦታል፦
እንዚራ ስብሐት ምዕራፍ 4 ቁጥር 98
"እትቀነይ ለኪ በፍርሃት ወእኤምሐኪ በአስተብርኮ። ለኪ አቀርብ ቁርባነ አኮቴት ወ-"ለኪ እሠውዕ መሥዋዕተ አምልኮ"።

"ለኪ" ማለት "ለአንቺ" ማለት ነው፥ "ለ" የሚለው መስተዋድድ በማያፈናፍን መልኩ የሚጠጋው ወደ ማርያም ነው። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በዓርብ እንዚራ ስብሐት ላይ ይቀጥልና፦ "የሚጣፍጥ የአምልኮ መሥዋዕትን ለአንቺ አቀርብልሻለሁ" በማለት ያመልካታል፦
እንዚራ ስብሐት ምዕራፍ 13 ቁጥር 113
"ማርያም ሆይ! ያማረ ፍጹም ምስጋና አቀርብልሻለሁ። የሚጣፍጥ የአምልኮ መሥዋዕትን ለአንቺ አቀርብልሻለሁ።

አምልኮ የአንድ አምላክ ገንዘብ እና ሐቅ ከሆነ ለማርያም የአምልኮ መሥዋዕት ማቅረቡ ግልጽ ማሻረክ ነው። "ዐማርኛ ትክክል አይደለም" እንዳንል ግዕዙ ላይ "አርብ ለኪ መሥዋዕተ አምልኮ ምዑዘ" ብሎ በግልጽ አስቀምጦታል፦
እንዚራ ስብሐት ምዕራፍ 5 ቁጥር 113
"አበውእ ለኪ ኦ እግዚእትየ ማርያም መዝሙረ ማኅሌት ሐዋዘ። ወአርብ ለኪ መሥዋዕተ አምልኮ ምዑዘ"።

"አርብ" ማለት "አቀርባለው" ማለት ነው፥ የአምልኮ መሥዋዕት ሊሰዋለት የሚገባው አንድ አምላክ ሆኖ ሳለ ለማርያም መሠዋቱ በራሱ ዓይን ያስፈጠጠ እና ጥርስ ያስገጠጠ አምልኮ ነው።
በኢሥላም አስተምህሮት ሙሥሊሞች ለአምልኮ የምንጠቀምበት የተቀረጸ ምስል የለም፥ ከአሏህ ውጪ የምናመልከው እና የምንሰግድለት ምንነት ሆነ ማንነት የለም። አምላካችን አሏህ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለቱ እኛ ሙሥሊሞች የአምልኮ ሐቅ ለእርሱ ብቻ እናቀርባለን፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ "እኔን ብቻ አምልኩኝ"፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ
21፥92 ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ "እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ"፡፡ إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةًۭ وَٰحِدَةًۭ وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُونِ

የአምልኮ ገንዘብ እና ሐቅ የሚገባው አሏህ "እኔ" ብሎ የሚናገር ነባቢ መለኮት ሲሆን ለተቀረጸ ምስል ከመስገድ እና ከማምለክ የፈጠረንን አንዱን አምላክ አሏህን በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አማላጁ ኢየሱስ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥186 ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ “እኔ ቅርብ ነኝ፥ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡ وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ

“ዱዓእ” دُعَآء የሚለው ቃል “ደዓ” دَعَا ማለትም “ለመነ” “ጠራ” “ጸለየ” “ተማጸነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ልመና” “ጥሪ” “ጸሎት” “ተማጽንዖ” ማለት ነው። ዱዓእ የአንዱ አምላክ የአሏህ ሐቅና ገንዘብ ነው፦
2፥186 ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ “እኔ ቅርብ ነኝ፥ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡ وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِي عَنِّي فَإِنِّي قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ الدَّاعِ إِذَا دَعَانِ

አንዱ አምላክ "የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ" በማለት እርሱ ተለማኝ እንደሆነ አበክሮ ይናገራል፥ "ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና" በማለት ፍጡራን ለማኝ መሆናቸውን ያስረዳል፦
40፥60 ጌታችሁም አለ «ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና፡፡ እነዚያ እኔን ከማምለክ የሚኮሩት ተዋራጆች ኾነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ”፡፡ وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ ۚ إِنَّ الَّذِينَ يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِي سَيَدْخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 34, ሐዲስ 2
አን-ኑዕማን ኢብኑ በሺር እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ "ዱዓእ ዒባዳህ ነው፥ ከዚያም፦ “ጌታችሁም አለ «ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና” የሚለውን አንቀጽ ቀሩ”። عَنِ النُّعْمَانِ بْنِ بَشِيرٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏”‏ إِنَّ الدُّعَاءَ هُوَ الْعِبَادَةُ ‏”‏ ‏.‏ ثُمَّ قَرَأَ ‏{وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ}‏

"ዒባዳህ" عِبَادَة የሚለው ቃል "ዓበደ" عَبَدَ ማለትም "አመለከ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “አምልኮ” ማለት ነው። እዚህ ድረስ ከተግባባን ኢየሱስ ሲያስተምር፦ "አምናችሁም በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ" ብሏል፦
ማቴዎስ 21፥22 አምናችሁም በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ።

ኢየሱስ እራሱ አንዱን አምላክ ጠይቆ መልስ የሚጠብቅ ለማኝ ነበር፦
ዮሐንስ 11፥22 አሁንም ከአምላክ የምትለምነውን ሁሉ አምላክ እንዲሰጥህ አውቃለሁ አለችው። καὶ νῦν οἶδα ὅτι ὅσα ἂν αἰτήσῃ τὸν Θεὸν δώσει σοι ὁ Θεός.

ኢየሱስ አምላክን ለምኖ የሚሰጠው ከሆነ እርሱ ለማኝ ነቢይ እንጂ ተለማኝ አምላክ በፍጹም አይደለም፥ በጸሎት ብርቱ ስለነበር ሌሊቱን ሙሉ ወደ አምላክ ሲጸልይ ያድር ነበር፦
ሉቃስ 6፥12 በነዚህም ወራት ይጸልይ ዘንድ ወደ ተራራ ወጣ፥ ሌሊቱንም ሁሉ "ወደ" አምላክ ሲጸልይ አደረ። Ἐγένετο δὲ ἐν ταῖς ἡμέραις ταύταις ἐξελθεῖν αὐτὸν εἰς τὸ ὄρος προσεύξασθαι, καὶ ἦν διανυκτερεύων ἐν τῇ προσευχῇ τοῦ Θεοῦ.

"ወደ" የሚለው መስተዋድድ ጸላዩን ኢየሱስ ከሚጸለይለት አምላክ ለይቶ ያስቀምጠዋል። ኢየሱስ ካረገም በኃላ አብን በጸሎት ይለምናል፦
ዮሐንስ 14፥16 እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል።

ለዘላለምም ከሰዎች ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ እንዲሰጥ የጸለየበት ክፍል በምድር ላይ የለም። ነገር ግን ካረገ በኃላ የሚጸልየው ጸሎት ነው፥ ምክንያቱም ኢየሱስ በአምላክ ቀኝ ሆኖ እንደሚያማልድ በግልጽ ተቀምጧል፦
ሮሜ 8፥34 በአምላክ ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ὅς ἐστιν ἐν δεξιᾷ τοῦ Θεοῦ, ὃς καὶ ἐντυγχάνει ὑπὲρ ἡμῶν.

"ኢንቱካኖ" ἐντυγχάνω ማለት "ጠራ" "ማለደ" "አማለደ" ማለት ሲሆን ኢየሱስ ለማኝ መሆኑን አምላክ ተለማኝ መሆኑን ፍንትው አርጎ ያሳያል፥ ምክንያቱም ጳውሎስ በ 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥1 ላይ ስለ ሰዎች ምልጃ እንዲደረግ ሲናገር "ምልጃ" ለሚለው ቃል የተተጠቀመበት "ኢንቱኪስ" ἔντευξις ነው። በ 1879 እንደ ጽብሓውያን ኦርቶዶክስ አቆጣጠር የተዘጋጀው የአባ ሮሜ የቁም ጽሑፍ የሚባል የባይብል ዕትም ኢየሱስ አማላጅ እንደሆነ ይናገራል፦
1ኛ ዮሐንስ 2፥1 ከላንትም ማንም ኃጢአት ቢሰራ ከአብ ዘንድ "አማላጅ" አለን፥ የሱስ ክርስቶስ ጻድቅ። ሮሜ ፰፤፫፬ ዕብ ፯፤፪፭

ኢየሱስ ለምኖ መልስ የሚጠብቅ "አማላጅ" ከተባለ ፍጡር ነው ማለት ነው፥ ምክንያቱም አማላጅ ካለ ተማላጅ አለ። ተማላጁ አንዱ አምላክ ከሆነ አማላጁ ኢየሱስ ይሆናል ማለት ነው፥ የሚገርመው ሮሜ 8፥34 እና ዕብ 7፥25 ማጣቀሻ ያስቀምጣል። በሮሜ 8፥34 ላይ "የሚያስምር" ሲለው እና በዕብ 7፥25 ደግሞ "ጸሎትን የሚያሳርግ" ይለዋል፥ እርሱ የሚያስምር እና ጸሎትን የሚያሳርግ ከሆነ የሚምር እና ጸሎትን የሚቀበል አንድ አምላክ ከኢየሱስ በማንነት ሆነ በምንነት የሚለይ ኑባሬ አለ። "ማለደ" ማለት "ለመነ" "ደጅ ጠና" ማለት ነው፥ "አማላጅ" ማለት "በለማኙ ስም ተለማኙን የሚጠይቅ እና የሚለምን ሦስተኛ ወገን" ማለት ነው።
ዐማርኛ መዝገበ ቃላት፤ የኢትዮጵያ የቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል አ.አ.ዩ ፣ ገጽ 70፤ የካቲት 1993. ተመልከት!

ኢየሱስ አንዱን አምላክ ለምኖ አሕዛብን ለርስቱ የምድርንም ዳርቻ ለግዛቱ እንዲሰጠው አምላክ ኢየሱስን "ለምነኝ" ብሎታል፦
መዝሙር 2፥8 "ለምነኝ"! አሕዛብን ለርስትህ የምድርንም ዳርቻ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ።

ኢየሱስ በምድር ላይ እያለ አሕዛብን ለርስቱ የምድርንም ዳርቻ ለግዛቱ እንዲሰጠው አምላክን አለመነም፥ ቅሉ ግን አብ ኢየሱስን "ለምነኝ" ባለው መሠረት ይለምነዋል። የምድርንም ዳርቻ ለግዛቱ እንዲሰጠው ሲለምነው ዳግም ሲመጣ ሁሉን ከእግሩ በታች ያስገዛለታል፥ አሁን ግን ሁሉ እንደ ተገዛለት ገና አናይም። በምጽአቱ ጊዜ ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ግን ሁሉን ላስገዛለት ለአምላክ ይገዛል፦
ዕብራውያን 2፥8 አሁን ግን ሁሉ እንደ ተገዛለት ገና አናይም።
1 ቆሮንቶስ 15፥28 ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ግን አምላክ ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል። ὅταν δὲ ὑποταγῇ αὐτῷ τὰ πάντα, τότε καὶ αὐτὸς ὁ Υἱὸς ὑποταγήσεται τῷ ὑποτάξαντι αὐτῷ τὰ πάντα, ἵνα ᾖ ὁ Θεὸς πάντα ἐν πᾶσιν.

"በዚያን ጊዜ" የሚለው "ሁሉ ከተገዛለት በኋላ" ማለት ነው፥ "በዚያን ጊዜ" ኢየሱስ ሁሉን ላስገዛለት ለአምላክ ይገዛል። "በዚያን ቀን" ኢየሱስ ስለ ሰዎች መለመኑን ያቆማል፦
ዮሐንስ 16፥26 "በዚያን ቀን" በስሜ ትለምናላችሁ፤ "እኔም ስለ እናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም"።

"በዚያን ቀን" ዳግም ሲመጣ ነው፥ ያኔ ተልእኮውን በትክክል ያሟላል። በእርግጥ ኢየሱስ አማላጅ ፍጡር ከሆነ የላከው አምላክ ተማላጅ ፈጣሪ ነውና የፈጠረውን ተማላጅ በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው።

አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ስለ ሃሩት እና ማሩት በድምፅ ያዳምጡ፦ https://youtu.be/MPycDqNn7gg
ኃፍረተ ሥጋ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

23፥5 *"እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የሆኑት ፍላጎታቸው አገኙ"*፡፡ وَالَّذِينَ هُمْ لِفُرُوجِهِمْ حَافِظُونَ

"ፈርጅ" فَرْج የሚለው ቃል በቁርኣን 8 ጊዜ የመጣ ሲሆን "ኃፍረተ ሥጋ" ወይም "ብልት" ማለት ነው፥ ይህ ቃል የወንድን ኃፍረተ ሥጋ ወይም የሴትን ኃፍረተ ሥጋ ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል፦
24፥30 *"ለምእመናን ንገራቸው፦ ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ። ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ"*። قُل لِّلْمُؤْمِنِينَ يَغُضُّوا مِنْ أَبْصَارِهِمْ وَيَحْفَظُوا فُرُوجَهُمْ
24፥30 *"ለምእመናትም ንገራቸው፦ ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ፡፡ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ"*፡፡ وَقُل لِّلْمُؤْمِنَاتِ يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَارِهِنَّ وَيَحْفَظْنَ فُرُوجَهُنَّ
23፥5 *"እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የሆኑት ፍላጎታቸው አገኙ"*፡፡ وَالَّذِينَ هُمْ لِفُرُوجِهِمْ حَافِظُونَ

ሦስቱም አናቅጽ ላይ "ብልቶች" ለሚለው የገባው ቃል "ፉሩጅ" فُرُوج ሲሆን "ፈርጅ" فَرْج ለሚለው ብዙ ቁጥር እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። "ብልት" የሚለው የዐማርኛ ቃል የዋለው "ክፍል"part" ለሚል ቃል እንዲሁ "ኃፍረተ ሥጋ"private part" ለሚል ነው፥ በተመሳሳይ ለመርየም ኃፍረተ ሥጋ የገባው ቃል "ፈርጅ" فَرْج ነው፦
21፥91 *"ያችንም ብልቷን የጠበቀቺውን በእርሷም ውስጥ ከመንፈሳችን የነፋንባትን እርሷን እና ልጅዋን ለዓለማት ተአምር ያደረግናትን አስታውስ"*፡፡ وَالَّتِي أَحْصَنَتْ فَرْجَهَا فَنَفَخْنَا فِيهَا مِن رُّوحِنَا وَجَعَلْنَاهَا وَابْنَهَا آيَةً لِّلْعَالَمِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ብልት" የተባለው ለሁለቱም ፆታ አገልግሎት ላይ የሚለው "ፈርጅ" فَرْج መሆኑን ልብ አድርግ! በዓለማችን ላይ 58 የተለያዩ በእንግሊዝኛ የተዘጋጁ የቁርኣን ትርጉሞች አሉ፥ ሁሉም ሲያስቀምጡ "chastity" "private part" "virginity" እያሉ እንጂ "Vagina" ብለው አላስቀመጡም። "ከረቤዛ"Vagina" ለማለት በቀጥታ ትርጉሙ "መህበል" مَهْبَل እንጂ "ፈርጅ" فَرْج አይደለም። "ወሲብ" ወይም "ፍትወተ-ስጋ" ከማለት ይልቅ "ተራክቦ" የሚለውን የጨዋ ዐማርኛ ለመጠቀም እንደሚያስፈልገው የሴት ኃፍረተ ሥጋ በዘመናችን ያለውን ስም ከመጠቀም ይልቅ የጥንቱን "ከረቤዛ" የሚለውን ቃል መርጫለው። "ቁርኣን ላይ የብልግና ቃል አለ" ብላችሁ ስትደሶክሩ የነበራችሁ ምን ይውጣችሁ ይሆን? አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
Watch "አሏህ እና መላእክቱ ለነቢዩ ይሰግዳሉን? ሶለዋት ላይ የተነሳው ማምታቻ ይመልከቱ፦ on YouTube
https://youtu.be/hYhIo2ljJiA