ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ሥርጸት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

3፥49 ወደ እስራኤልም ልጆች መልእክተኛ ያደርገዋል፡፡ ይላልም፡- "እኔ ከጌታችሁ በተአምር ወደ እናንተ መጣሁላችሁ"፡፡ وَرَسُولًا إِلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنِّي قَدْ جِئْتُكُم بِآيَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ

"ሥርጸት" የሚለው የግዕዙ ቃል "ሠረጸ" ማለትም "ወጣ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መውጣት"procession" ማለት ነው፥ "ወጣ" የሚለው ቃል በግዕዝ "ወጽአ" "ሠረቀ" "ሠረጸ" ነው። በቁርኣን ውስጥ አሏህ አፍ እንዳለው ያልተገለጸ ሲሆን በባይብል ውስጥ ግን አምላክ አፍ ኖሮት ከአፉ ጥበብ፣ ማስተዋል፣ ዕውቀት፣ ቃል፣ እስትንፋስ ይወጣሉ፦
ሲራክ 24፥3 እኔ(ጥበብ) ከልዑል "አፍ ወጣሁ" ምድርንም እንደ ጉም ሽፈንኋት።
ምሳሌ 2፥6 "ከ-"አፉም" ዕውቀት እና ማስተዋል "ይወጣሉ"።
ኢሳይያስ 55፥11 "ከ-"አፌ" የሚወጣ "ቃሌ" እንዲሁ ይሆናል።
ኢዮብ 15፥30 "በ-"አፉ እስትንፋስ" አበባዎቹም ይረግፋሉ። וְ֝יָס֗וּר בְּר֣וּחַ פִּֽיו׃

ከአፉ የሚወጡት ጥበብ፣ ማስተዋል፣ ዕውቀት፣ ቃል፣ እስትንፋስ ሸንሽነን ማንነት ካበጀንላቸው ሥላሴ ሦስት መሆኑ ቀርቶ ስድስት ይሆናሉ፥ ቅሉ ግን በባይብል ጥበብ፣ ማስተዋል፣ ዕውቀት፣ ቃል፣ እስትንፋስ ባሕዮት እንጂ አካላት አይደሉም። ኢየሱስ፦ "ከአብ ወጥቼ" ሲል "ከአፉ ወጥቼ" ማለቱ ሳይሆን "ከአብ መጥቼ" "ከአብ ተልኬ" ማለቱ ነው፦
ዮሐንስ 16፥28 ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ።

ምክንያቱም ሰይጣን እራሱ "ወጥቼ" የሚለውን ቃል ሲጠቀም ጌታም የእርሱን ንግግር ተቀብሎ "ውጣ" አለው፦
1ኛ ነገሥት 22፥22 ጌታም፦ በምን? አለው እርሱም፦ "ወጥቼ" በነቢያቶቹ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ እሆናለሁ አለ። ጌታም፦ ማሳሳትስ ታሳስተዋለህ፥ ይሆንልሃልም "ውጣ"፥ እንዲሁም አድርግ አለ።” καὶ εἶπε πρὸς αὐτὸν Κύριος· ἐν τίνι; καὶ εἶπεν· ἐξελεύσομαι καὶ ἔσομαι πνεῦμα ψευδὲς εἰς τὸ στόμα πάντων τῶν προφητῶν αὐτοῦ. καὶ εἶπεν· ἀπατήσεις καί γε δυνήσῃ, ἔξελθε καὶ ποίησον οὕτως.

ሰይጣን ከአብ ወጥቶ ሲያሳስት ከአብ መላኩን እና መምጣቱን እንጂ ከአብ አፍ ወይም ከአብ አካል ተወልዶ መምጣቱን አያሳይም። በተጨማሪም ሐሰተኛ ነቢያት ወጥተው ወደ ዓለም ገብተዋል፦
1ኛ ዮሐንስ 4፥1 ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም "ወጥተዋልና"።
2ኛ ዮሐንስ 1፥7 ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም "ገብተዋል"።

ወደ ዓለም የገቡት ከየት ነው? የወጡትስ? የወጡት ከሰዎች መካከል እንጂ ከሰዎች አፍ ወይም አብራክ ተከፍለው አይደለም፦
1ኛ ዮሐንስ 2፥19 "ከ-"እኛ ዘንድ "ወጡ"።

"ወጡ" ማለት "መጡ" ማለት ከሆነ ኢየሱስ "ወጥቼ" ሲል "ተልኬ" "መጥቼ" ማለቱ ነው። "መውጣት" ተብሎ የተቀመጠው የግሪኩ ቃል "አክ ኤርኮማይ" ἐξέρχομαι ሲሆን "ኤክ" ἐκ እና "ኤርኮማይ" ἔρχομαι ከሚሉ ሁለት ቃላት የተዋቀረ ነው፥ "ኤክ" ἐκ የሚለው መስተዋድድ "ከ" ማለት ሲሆን "ኤርኮማይ" ἔρχομαι ማለት "መምጣት" ማለት ነው፦
ዮሐንስ 5፥43 እኔ በአባቴ ስም መጥቻለሁ አልተቀበላችሁኝምም፥ ሌላው በራሱ ስም ቢመጣ እርሱን ትቀበሉታላችሁ። ἐγὼ ἐλήλυθα ἐν τῷ ὀνόματι τοῦ Πατρός μου, καὶ οὐ λαμβάνετέ με· ἐὰν ἄλλος ἔλθῃ ἐν τῷ ὀνόματι τῷ ἰδίῳ, ἐκεῖνον λήμψεσθε.

እዚህ አንቀጽ ላይ "መምጣት" ለሚል የግሥ መደብ የገባው ቃል "ኤርኮማይ" ἔρχομαι እንደሆነ 2064 ጠንካራ ቁጥር ተመልከት! "በራሱ ስም መምጣት" ማለት "ሳይላክ ተልኬአለው" ማለትን ከገለጸ "በአብ ስም መምጣት" ማለት "አብ ልኮት መምጣት" ማለት ነው፦
ዮሐንስ 8፥42 እርሱ ላከኝ እንጂ "ከራሴ አልመጣሁምና"።
ዮሐንስ 7፥28 እኔም "በራሴ አልመጣሁም"፥ ነገር ግን እናንተ የማታውቁት "የላከኝ" እውነተኛ ነው።

ስለዚህ "ወጥቼ" የሚለው ቃል "እምቅድመ ዓለም ያለ እናት አብን አህሎ እና መስሎ እንዲሁ ከአካል አካልን ወስዶ ከባሕርይ ባሕርይ ወስዶ ተወለደ" ለሚል ትምህርት መሠረት በፍጹም አይሆንም፥ "መወለድ" ማለት "መውጣት" ማለት ከሆነ መንፈስ ቅዱስ "ከአብ የሚወጣ" ስተለባለ ለምንስ "ተወለደ" "ልጅ" ነው አይባልም?

በ 381 ድኅረ ልደት የተሰበሰበው የቁስጥንጥንያ ጉባኤ መንፈስ ቅዱስ "ከአብ የሠረጸ" የሚል ትውፊት ከጽባሓውያን ኦርቶዶክስ እና ከመለካውያን ኦርቶዶክስ የመጣ ሲሆን "ከአብ እና ከወልድ የሠረጸ" የሚል ትውፊት ከካቶሊክ እና ከፕሮቴስታንት ትውፊት መጥቷል፥ የቁስጥንጥንያ ጉባኤ የቱን በትክክል እንዳሉ አሻሚ ስለነበር በሁለት ባሕርይ የሚያምኑት ካቶሊክ እና መለካውያን ኦርቶዶክስ በ 1053 ድኅረ ልደት በጉባኤ ተሰብስበው ባለመግባባት ተወጋግዘው ተለያይተዋል። ይህም ክፍፍል ቤተክርስቲያንን የምሥራቅ እና የምዕራብ ቤተክርስቲያን አርጎ ስለከፈለ ታላቁ ክፍፍል"great Schism" ይባላል፥ በ 1517 ከካቶሊክ የተገነለጠለው የፕሮቴስታንት አንጃም በሥርጸት ጉዳይ የካቶሊክን ትውፊት የያዘ ነው።

ወደ ቁርኣን ስንመጣ ዒሣ ኢብኑ መርየም ከአሏህ በተአምር የመጣ መልእክተኛ ነው፦
3፥49 ወደ እስራኤልም ልጆች መልእክተኛ ያደርገዋል፡፡ ይላልም፡- "እኔ ከጌታችሁ በተአምር ወደ እናንተ መጣሁላችሁ"፡፡ وَرَسُولًا إِلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنِّي قَدْ جِئْتُكُم بِآيَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ

ይህም ተአምር ዕውር ማብራት፣ ለምጻም ማንጻት፣ ሙት ማስነሳት ወዘተ ነው። በተመሳሳይ ነቢዩሏህ ሙሣ ከአሏህ በተአምር የመጣ መልእክተኛ ነው፦
7፥105 «በአላህ ላይ ከእውነት በቀር አለመናገር ተገቢዬ ነው፡፡ "ከጌታችሁ በተአምር በእርግጥ መጣሁላችሁ"፡፡ حَقِيقٌ عَلَىٰ أَن لَّا أَقُولَ عَلَى اللَّهِ إِلَّا الْحَقَّ ۚ قَدْ جِئْتُكُم بِبَيِّنَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ

ዒሣ እና ሙሣ፦ "ከጌታችሁ በተአምር በእርግጥ መጣሁላችሁ" ብለው ያሉት ጣምራ ንግግር "ኢየሱስ ከአምላክ ዘንድ መጥቷል" ስንል "ሙሴ ከአምላክ ዘንድ መጥቷል" በተባለበት ሒሣብ እንደሆነ ያስረዳል፥ ኒቆዲሞስም የተረዳው በዚህ ስሌት ነው፦
ዮሐንስ 3፥2 "መምህር ሆነህ ከአምላክ ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን" አለው። καὶ εἶπεν αὐτῷ Ῥαββεί, οἴδαμεν ὅτι ἀπὸ Θεοῦ ἐλήλυθας διδάσκαλος·

ኢየሱስን ከዳዊት ዘር ወደ ዓለም ያመጣው አምላክ ነው፥ የተወለደውም ወደ ዓለም ከመጣ በኃላ ሳይሆን ከተወለደ በኃላ ነው ወደ ዓለም የመጣው፥ ከተወለደ በኃላ የተላከ ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 13፥23 "ከዚህም ሰው ዘር" አምላክ እንደ ተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኃኒትን እርሱም ኢየሱስን "አመጣ"።
ዮሐንስ 18፥37 እኔ ለእውነት ልመሰክር ስለዚህ ተወልጃለሁ፥ ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ።
ገላትያ 4፥4 አምላክ "ከሴት የተወለደውን" ከሕግም በታች የተወለደውን "ልጁን ላከ"።

ስለዚህ ታሪክን ከነገረ-መለኮት ጋር ግጣም አርጎ ማጎላበት እና ማጎልበት ክብረት እንጂ ክስረት የለውም። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሚካኤል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥98 ለአላህ እና ለመላእክቱ፣ ለመልእክተኞቹ፣ ለጂብሪል፣ ለሚካኤል ጠላት የኾነ ሰው አላህ ለከሓዲዎች ጠላት ነው፡፡ مَن كَانَ عَدُوًّا لِّلَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَرُسُلِهِ وَجِبْرِيلَ وَمِيكَالَ فَإِنَّ اللَّهَ عَدُوٌّ لِّلْكَافِرِينَ

"ሚካኢል" مِيكَائِيل የሚለው የዐረቢኛው ቃል ከሦስት ቃላት የተዋቀረ ነው፥ "ሚ" مِي ወይም "መን" مَن ማለት "ማን" ማለት ሲሆን መጠይቅ ተውላጠ ስም ነው፣ "ካ" كَا ወይም "ከ" كَ ማለት "እንደ" ማለት ሲሆን መስተዋድድ ነው፣ "ኢል"  ئِيل ወይም "ኢላህ" إِلَـٰه  ማለት "አምላክ" ማለት ሲሆን ስም ነው። በጥቅሉ "ሚካኢል" مِيكَائِيل ማለት "ማን እንደ አምላክ" "መኑ ከመ አምላክ" ማለት ነው፦
2፥98 ለአላህ እና ለመላእክቱ፣ ለመልእክተኞቹ፣ ለጂብሪል፣ ለሚካኤል ጠላት የኾነ ሰው አላህ ለከሓዲዎች ጠላት ነው፡፡ مَن كَانَ عَدُوًّا لِّلَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَرُسُلِهِ وَجِبْرِيلَ وَمِيكَالَ فَإِنَّ اللَّهَ عَدُوٌّ لِّلْكَافِرِينَ
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 59 , ሐዲስ 47
ሠሙራህ እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “በሌሊት ላይ ሁለት ሰዎች ወደ እኔ ሲመጡ አየሁኝ፥ ከእነርሱ አንዱ እንዲህ አለ፦ “ያ እሳት የሚያይዝ “ማሊክ” ሲሆን የእሳት ዘበኛ ነው፥ “እኔ ጂብሪል ነኝ”። ይህ ሚካኢል ነው”። عَنْ سَمُرَةَ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ رَأَيْتُ اللَّيْلَةَ رَجُلَيْنِ أَتَيَانِي قَالاَ الَّذِي يُوقِدُ النَّارَ مَالِكٌ خَازِنُ النَّارِ، وَأَنَا جِبْرِيلُ، وَهَذَا مِيكَائِيلُ ‏”‌‏.‏

በኢሥላም አስተምህሮት ሚካኢል ከመላእክት ሊቃውንት(አለቆች) አንዱ ሊቀ መላእክት እና እራሱ በምንነቱ መልአክ ነው። በባይብል "ሚካኤል" מִיכָאֵל የሚለው የዕብራይስጥ ቃል ከሦስት ቃላት የተዋቀረ ነው፥ "ሚ" מִי ማለት "ማን" ማለት ሲሆን መጠይቅ ተውላጠ ስም ነው፣ "ካ" כָ ማለት "እንደ" ማለት ሲሆን መስተዋድድ ነው፣ "ኤል" אֵל ማለት "አምላክ" ማለት ሲሆን ስም ነው። በጥቅሉ "ሚካኤል" מִיכָאֵל ማለት "ማን እንደ አምላክ" ማለት ነው፦
ዘዳግም 33፥26 እንደ አምላክ ማንም የለም። אֵ֥ין כָּאֵ֖ל

እዚህ አንቀጽ ላይ "እንደ አምላክ" ለሚለው ቃላት የገባው ቃላት "ካኤል" כָּאֵ֖ל እንደሆነ ልብ አድርግ! "ሚካኤል" מִיכָאֵל የሚለው ስም ለሰዎች የተጸውዖ ስም ሆኖ መጥቷል፦
ዘኍልቍ 13፥13 ከአሴር ነገድ የ-"ሚካኤል" ልጅ ሰቱር።
ዕዝራ 8፥8 የሰፋጥያስ ልጆች የ-"ሚካኤል" ልጅ ዝባድያ፥ ከእርሱም ጋር ሰማንያ ወንዶች።

ነገር ግን ይህ ስም ለመላእክት አለቃ ለመልአኩ የተጸውዖ ስም ነው፥ ሚካኤል ከመላእክት አለቆች አንዱ ነው፦
ይሁዳ 1፥9 የመላእክት አለቃ ሚካኤል..።
ዳንኤል 10፥13 ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፤
ዳንኤል 12፥1 በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል።
ኢያሱ 5፥14 እኔ የያህዌህ ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቼአለሁ።

በኢያሱ ፊት የተመዘዘ ሰይፉን የያዘው የያዘው የመላእክት አለቃ ሚካኤል እንደሆነ ድርሳነ ሚካኤል ይናገራል፦
ድርሳነ ሚካኤል ዘወርኃ ኅዳር 3፥148
"የነዌ ልጅ ኢያሱ በንጉሡ የጦር ቢትወደድ አምሳል ክቡር ገናና ሀኖ ያየው ይህ ሚካኤል ነው"

ይህ ከመሆኑ ጋር ከ 1695 እስከ 1758 ይኖር የነበረው የአይሪሽ ፕሮቴስታንት መሪ ሮበርት ክላይቶን"Robert Clayton፣ የአድቬንቲስት ቤተክርስቲያን እና የይሆዋ ምስክሮች፦ "ኢየሱስ ብሉይ ኪዳን ላይ ሲላክ የነበረ መልአክ ወይም የመላእክት አለቃ ሚካኤል ነው" ብለው ያምናሉ፥ ምክንያታቸው ደግሞ የጥንት የቤተክርስቲያን አባቶች፦ "ኢየሱስ ብሉይ ኪዳን ላይ ሲላላክ የነበረ የመላእክት አለቃ እና መልአክ ነው" ብለው ስለተናገሩ ነው።

ሰማዕቱ ዮስጦስ፦
"ክርስቶስ ንጉሥ፣ ካህን፣ አምላክ፣ ጌታ፣ መልአክ፣ ሰው እና አለቃ ነው፥ ኢያሱ 5፥13-15"
Justin Martyr’s Dialogue w/ Trypho Ch. 34

የልዮኑ ኢራኒዮስ፦
፨"እርሱ(ክርስቶስ) ሁሉ በሁሉ ነው፥ ከአባቶች መካከል አባት ነው፣ በሕግጋት መካከል ሕግ ነው፣ በካህናት መካከል ሊቀ ካህናት ነው፣ በነገሥታት መካከል ገዥ ነው፣ በነቢያት መካከል ነቢይ ነው፣ በመላእክት መካከል መልአክ ነው፣ በሰዎች መካከል ሰው ነው"
Fragments of Irenaeus Ch. 53

፨"እርሱ በካህናት መካከል ካህን ነው፣ በነገሥታት መካከል ጠቅላይ ገዥ ነው፣ በነቢያት መካከል ነቢይ ነው፣ በመላእክት መካከል መልአክ ነው፣ በሰዎች መካከል ሰው ነው፣ በአብ ደግሞ ልጅ ነው"
Fragments of Irenaeus Ch. 54

የሰርዴሱ ሚልጦን፦
"እርሱ በሕግ ሕግ ነው፣ በካህናት መካከል ሊቀ ካህናት ነው፣ በነገሥታት መካከል ገዥ ነው፣ በነቢያት መካከል ነቢይ ነው፣ በመላእክት መካከል የመላእክት አለቃ ነው"
Melito of Sardis’ Fragments Ch. 4

የቂሳርያው አውሳቢዮስ፦
፨"እርሱ አምላክ እና የቅዱሳን ጌታ ተብሎ ቢጠራም ነገር ግን የልዑል አባቱ መልአክ ነው"
Eusebius’ The Proof of the Gospel Book 1 Ch. 5

፨"እርሱ(ክርስቶስ) የሰማይ ሰራዊት አለቃ ነው፥ የጌታ ሠራዊት አለቃ ኢያሱ 5፥13-15።"
Eusebius’ The Proof of the Gospel Book 4 Ch. 10
የሚያጅበት በኢሳይያስ 9፥6 ላይ ከማሶሬት በተቃራኒው ከ 330–360 ድኅረ ልደት በክርስቲያኖች እጅ በተዘጋጀው በኮዴክስ ሲናቲከስ ኮድ በፊደል S በቁጥር 01ውስጥ የግሪክ ሰፕቱአጀንት ቅጂ፦ "የታላቁ ጉባኤ መልአክ" ይለዋል፦
ኢሳይያስ 9፥6 ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል። ስሙም፦ "የታላቁ ጉባኤ መልአክ" ይባላል፥ በአለቆች ላይ ሰላምን እና በእርሱ ላይ ጤናን አመጣለው። ὅτι παιδίον ἐγεννήθη ἡμῖν, υἱὸς ἐδόθη ἡμῖν, οὗ ἡ ἀρχὴ ἐγενήθη ἐπὶ τοῦ ὤμου αὐτοῦ, καὶ καλεῖται τὸ ὄνομα αὐτοῦ Μεγάλης βουλῆς ἄγγελος· ἄξω γὰρ εἰρήνην ἐπὶ τοὺς ἄρχοντας καὶ ὑγείαν αὐτῷ.
For a child is born to us, and a son is given to us, whose government is upon his shoulder, and his name is called the angel of great counsel, for I will bring peace upon the princes, and health to him.

"ሜጋሌስ ቡሌስ አንጌሎስ" Μεγάλης βουλῆς ἄγγελος ማለት "የታላቁ ጉባኤ መልአክ"the angel of great counsel" ማለት ነው፥ በማሶሬት ላይ፦ "ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ" የሚለውን አሽቀንጥረው ጥለው "የታላቁ ጉባኤ መልአክ" ብለውታል። ይህም ጉባኤ የቅዱሳን መላእክት ጉባኤ ነው፦
መዝሙር 88(89)፥6 ጌታ ሆይ! ሰማያት ተኣምራትህን እውነትህንም ደግሞ በቅዱሳን ጉባኤ ያመሰግናሉ፥ ἐξομολογήσονται οἱ οὐρανοὶ τὰ θαυμάσιά σου, Κύριε, καὶ τὴν ἀλήθειάν σου ἐν ἐκκλησίᾳ ἁγίων.
መዝሙር 88(89)፥7 ጌታን በሰማይ የሚተካከለው ማን ነው? ከአምላክ ልጆች ጌታን ማን ይመስለዋል? ὅτι τίς ἐν νεφέλαις ἰσωθήσεται τῷ Κυρίῳ; καὶ τίς ὁμοιωθήσεται τῷ Κυρίῳ ἐν υἱοῖς Θεοῦ;
መዝሙር 88(89)፥8 በቅዱሳን ጉባኤ አምላክ ክቡር ነው፥ በዙሪያው ባሉት ሁሉ ላይ ታላቅና ግሩም ነው። ὁ Θεὸς ἐνδοξαζόμενος ἐν βουλῇ ἁγίων, μέγας καὶ φοβερὸς ἐπὶ πάντας τοὺς περικύκλῳ αὐτοῦ.

ኢየሱስን የዚህ ጉባኤ መልእክተኛ ማድረግ የመላእክት አለቃ ከሚለው ማዕረግ ዝቅ ማድረግ ነው። በእርግጥ "መልአከ ምክር(የጉባኤ መልአክ) ሚካኤል ነው፦
ድርሳነ ሚካኤል ዘወርኃ መጋቢት 7፥184
"ተአምሪሁ ለመልአክ ክቡር ሚካኤል ሊቀ መላእክት "መልአክ ምክሩ" ለአብ"
ቅዳሴ ዮሐንስ አፈ ወርቅ 15፥17
"ፈነወ ለነ ወልዶ መድኅነ ወመቤዝወ "መልአከ ምክሩ" የማኑ እደ መዝራዕቱ ኃይሉ ወጥበቡ ለአቡሁ"

ለአብ የጉባኤ መልአክ ማን ነው ሚካኤል ወይስ ኢየሱስ? በእርግጥ ዐበይት ክርስትና ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ፣ አንግሊካን እና ፕሮቴስታንት በሥነ-መለኮት ትምህርታቸው "ኢየሱስ ሚካኤል ነው" ባይሉም "ኢየሱስ ብሉይ ኪዳን ላይ ሲላክ የነበረ መልአክ ነው" ብለው ያምናሉ፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 83 ቁጥር 12
"-"የእግዚአብሔር ልጅ፣ መልአክ፣ ክንድ፣ ነቢይ" ተባለ።"
ሰይፈ ሥላሴ ምዕራፍ 4 ቁጥር 48
"መልአክ የተባለውም የእግዚአብሔር ልጅ ነው"

እውን መልአክ ይመለካልን? "መልአክ" የሚለው የግዕዝ ቃል "ለአከ" ማለትም "ላከ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ተላላኪ" "መልእክተኛ" ማለት ነው፥ እንግዲህ ኢየሱስ መልእክተኛ ከሆነ እርሱ ጋር የሌለ ግን ሌላ ማንነት ጋር ያለው ዕውቀት ለማስተላለፍ የተላከ ተላላኪ ነው ማለት ነው። አንድ ሁሉን ዐዋቂ አምላክ ሙሉ ዕውቀት ካለው ለሌላ ምንነት እና ማንነት እንዴት መልእክተኛ ይሆናል? ከሌላ ምንነት እና ማንነት ምን እንደሚናገር መልእክት እየተቀበለ እንዴት ይናገራል? መልእክተኛ የሌላ መልእክት እንጁ የራሱን አይናገርም፥ ከራሱ ምንም መናገር ካልቻለ እራሱ ጋር በቂ ትምህርት፣ ዕውቀት እና መልእክት የለውም ማለት ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መሢሑ ሰሎሞን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

38፥30 ለዳውድም ሡለይማንን ሰጠነው፡፡ ምን ያምር ባሪያ! እርሱ ተመላሽ ነው፡፡ وَوَهَبْنَا لِدَاوُودَ سُلَيْمَانَ ۚ نِعْمَ الْعَبْدُ ۖ إِنَّهُ أَوَّابٌ

አምላካችን አሏህ ለዳውድ ሡለይማንን ልጅ አርጎ ሰቶታል፥ እርሱም ወደ አሏህ በንስሓ ተመላሽ ነው፦
38፥30 ለዳውድም ሡለይማንን ሰጠነው፡፡ ምን ያምር ባሪያ! እርሱ ተመላሽ ነው፡፡ وَوَهَبْنَا لِدَاوُودَ سُلَيْمَانَ ۚ نِعْمَ الْعَبْدُ ۖ إِنَّهُ أَوَّابٌ

"ተውባህ" تَوْبَة የሚለው ቃል "ታበ" تَابَ ማለትም "ተመለሰ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ከነበሩበት ስህተት በንስሐ ወደ አሏህ መመለስ” ማለት ነው፥ አሏህ ወደ እርሱ የሚመለሱት ንስሐን የሚቀበል ስለሆነ “አት-ተዋብ” التَّوَّاب ሲሆን ወደ እርሱ "ተመላሽ" ባሪያ ደግሞ "አዋብ" أَوَّاب ይባላል።
ስለ ሡለይማን በቁርኣን ጥቂት ካልን ዘንዳ በባይብል ደግሞ ይህ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን መሢሕ ተብሏል፦
1ኛ ሳሙኤል 2፥35 የታመነም ካህን ለእኔ አስነሣለሁ፥ በልቤም በነፍሴም እንዳለ እንዲሁ ያደርጋል፤ እኔም የታመነ ቤት እሠራለታለሁ፥ ዘመኑን ሁሉ "በ"-መሢሔ" ሰው ፊት ይሄዳል። וַהֲקִימֹתִ֥י לִי֙ כֹּהֵ֣ן נֶאֱמָ֔ן כַּאֲשֶׁ֛ר בִּלְבָבִ֥י וּבְנַפְשִׁ֖י יַעֲשֶׂ֑ה וּבָנִ֤יתִי לֹו֙ בַּ֣יִת נֶאֱמָ֔ן וְהתְהַלֵּ֥ךְ לִפְנֵֽי־מְשִׁיחִ֖י כָּל־הַיָּמִֽים׃

በዕብራይስጥ ማሶሬት ላይ "ማሺያኽ" מָשִׁיחַ‎ የሚለው የማዕረግ ስም ትርጉሙ "የተቀባ" "ቅቡዕ" "መሢሕ" "ክርስቶስ" ማለት ነው፥ ይህ የማዕረግ ስም ለነገሥታት፣ ለነቢያት እና ለካህናት የሚውል ስም ነው። ይህ ጥቅስ ትንቢት ሲሆን ትንቢቱም ስለ ካህን እና ካህኑ ስለሚሄድበት መሢሑ ነው፥ ካህኑ ሳዶቅ ሲሆን መሢሑ ደግሞ ቤት የሠራው ሰለሞን ነው። ካህኑም ሳዶቅ ከድንኳኑ የቅብዓቱን ቀንድ ወስዶ ሰሎሞንን ቀባ፦
1ኛ ነገሥት 1፥39 ካህኑም ሳዶቅ ከድንኳኑ የቅብዓቱን ቀንድ ወስዶ ሰሎሞንን "ቀባ"።

ንጉሥ ዳዊት ስለ ልጁ ስለ ሰሎሞን በተናገረበት አንቀጽ ላይ ንጉሡ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን መሢሕ እንደሆነ የዐረማይክ ታርገም በዚህ መልኩ አስቀምጦቷል፦
መዝሙር 72፥1 አምላክ ሆይ! ፍርድህን ለንጉሡ መሢሕ ስጥ፥ ጽድቅህንም ለንጉሥ ዳዊት ልጅ። אֱלָהָא הִילְכוֹת דִינָךְ לְמַלְכָּא מְשִׁיחָא הַב וְצִדְקָתָךְ לִבְרֵיהּ דְדָוִד מַלְכָּא

"ታርገም" תרגום‎ ማለት "ትርጉም"translation ማለት ነው፥ ከ 35 እስከ 120 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረው አኪላስ(አቂላስ) ያዘጋጀው ቶራህን መሠረት ያደረገ ማብራሪያ ታርገም አኪላስ"Targum Onkelos" ሲባል ከ 110 ቅድመ ልደት እስከ 10 ድኅረ ልደት ይኖር ነበር ተብሎ በሚገመተው ዮናታን ቤን ዑዚኤል ያዘጋጀው ነቢምን መሠረት ያደረገ ማብራሪያ ደግሞ ታርገም ዮናታን"Targum Jonathan" ይባላል። ዳዊት ለልጁ የምድረ በዳ ዘላኖች እንደሚንበረከኩለት ተናግሯል፦
መዝሙር 72፥9 የምድረ በዳ ዘላኖች በፊቱ ይንበረከካሉ። לְ֭פָנָיו יִכְרְע֣וּ צִיִּ֑ים

"ጺዪ" צִיִּי ማለት "የምድረ በዳ ዘላን" ማለት ሲሆን የጺዪ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ጺዪም" צִיִּ֑ים ነው፥ ይህም ቃል የበረሃ ሰውን ወይም የዱር አውሬን ለማመልከት ይመጣል። እዚህ አንቀጽ ላይ "ይንበረከካሉ" ለሚለው የገባው ቃል "ይክራዩ" יִכְרְע֣וּ ሲሆን "ካራ" כָּרַע ማለትም "ተንበረከከ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ነው፥ በተመሳሳይም አምሳ አለቃው በኤልያስ ፊት በጒልበቱ ተንበርክኮለታል፦
2ኛ ነገሥት 1፥13 በኤልያስ ፊት በጒልበቱ "ተንበረከከ"። וַיִּכְרַ֥ע עַל־ בִּרְכָּ֣יו לְנֶ֣גֶד אֵלִיָּ֗הוּ

"ዪክራ" כְרַ֥ע የሚለው የግሥ መደብ "ካራ" כָּרַע ለሚለው አሁናዊ ግሥ ነው። ታዲያ አምሳ አለቃው ለኤልያስ በጒልበቱ ስለተንበረከከ ኤልያስን እያመለከው ነበርን? እረ በፍጹም። በመቀጠል ንጉሥ ዳዊት ለልጁ ለሰሎሞን ነገሥታት እንደሚሰግዱ እና ሕዝቦች እንደሚገዙ ተናግሯል፦
መዝሙር 72፥11 ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል፥ አሕዛብም ሁሉ ይገዙለታል። וְיִשְׁתַּחֲווּ־לֹ֥ו כָל־מְלָכִ֑ים כָּל־גֹּויִ֥ם יַֽעַבְדֽוּהוּ׃
እዚህ አንቀጽ ላይ "ይሰግዳሉ" ለሚለው የገባው ቃል "ዪስታሀዉ" יִשְׁתַּחֲווּ ሲሆን "ሻኻህ" שָׁחָה ማለትም "ሰገደ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ነው፥ "ይገዙለታል" ለሚለው የገባው ቃል ደግሞ "የዐብዱ-ሁ" יַֽעַבְדֽוּהוּ ሲሆን "ዐበድ" עָבַד ማለትም "ተገዛ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ነው። ይስሐቅ ልጁን ያዕቆብን ሲባርከው የተጠቀመው ቃል ተመሳሳይ ነው፦
ዘፍጥረት 27፥29 አሕዛብ ይገዙልህ ሕዝብም ይስገዱልህ። יַֽעַבְד֣וּךָ עַמִּ֗ים [וְיִשְׁתַּחוּ כ] (וְיִֽשְׁתַּחֲו֤וּ ק) לְךָ֙ לְאֻמִּ֔ים 

እዚህ አንቀጽ ላይ "ይገዙልህ" ለሚለው የገባው ቃል "የዐብዱ-ከ" יַֽעַבְד֣וּךָ ሲሆን "ይስገዱ" ለሚለው የገባው ቃል ደግሞ "ዪስታሀዉ" יִֽשְׁתַּחֲו֤וּ ነው፥ ታዲያ ያዕቆብ አሕዛብ ስለተገዙለት እና ስለሰገዱለት እንደሚመለክ ያሳያልን? እረ በፍጹም። ስለዚህ "አይነኬ" ብለው ያሉት የሚሽነሪዎች ሙግት እንዲህ ዶግ አመድ እና አፈር ደቼ ይገባል፥ ዳዊት ከልጁ ባሻገር በድርብ መልእክት ለሚመጣው መሢሕ ትንቢት ከተናገረ ያ የሚመጣው መሢሕ ኢየሱስ ነው። ሚሽነሪዎች፦ "መሢሑ ይሰገድለታል፥ ይመለካል" ብለው መዝሙር 72፥11 ላይ ያለውን "ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል፥ አሕዛብም ሁሉ ይገዙለታል" የሚለውን ኃይለ-ቃል ይጠቀማሉ፥ ቅሉ ግን "መስገድ" እና "መገዛት" ለያዕቆብ እና ለንጉሡ ሰሎሞን ስለገባ እነዚህ ሰዎች ይመለካሉን? "እረ በፍጹም" ከተባለ እንግዲያውስ "የሚመጣው መሢሕ ይመለካል" ማለት በምንም አግባብ አንዳች ቊብ እና ረብ የለውም። ሚሽነሪዎች ኢየሱስ እንደሚመለክ ለማስመሰል የማይቆፍሩት ጉድጓድ፣ የማይፈነቅሉት ድንጋይ እና የማይደረምሱት መሬት የለም፥ ዐረብ ክርስቲያኖች በ 867 ድኅረ ልደት ከዕብራይስጥ ወደ ዐረቢኛ ባዘጋጁት በኮዴክስ ዐረቢከስ ላይ "ይገዙለታል" ለሚለው "ሊ-ተኽዲም-ሁ" لِتَخْدِمْهُ አሉት እንጂ "ሊ-ተዕቡዱ-ሁ" لِيَعْبُدُوهُ በፍጹም አላሉትም፦
لِيَنْحَنِ خُضُوعًا لَهُ كُلُّ المُلُوكِ، وَلِتَخْدِمْهُ كُلُّ الشُّعُوبِ.

"ኺድማህ" خِدْمَة የሚለው ቃል "ኸደመ" خَدَمَ ማለትም "አስተናገደ" "አገለገለ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መስተንግዶ" "አገልግሎት" ማለት ነው፥ "ኻዲም" خَادِمْ ማለት "አስተናጋጅ" "አገልጋይ" ማለት ሲሆን ለምሳሌ፦ አነሥ "ረ.ዐ." ነቢዩን"ﷺ" በአላፊ ግሥ "አገለገልኩኝ" ለማለት የተጠቀመበት ቃል በተመሳሳይ "ኸደምቱ" خَدَمْتُ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 78, ሐዲስ 68
አነሥ "ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "እንዲህ አለ፦ "ነቢዩን"ﷺ" አሥር ዓመት አስተናገድኩኝ(አገለገልኩኝ)"። يَقُولُ حَدَّثَنَا أَنَسٌ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ خَدَمْتُ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم عَشْرَ سِنِينَ،

ስለዚህ "ኢየሱስ ይመለካል" ብሎ ኲታ ገጠም ርእስ አርጎ በደምሳሳው መሞገት ወትሮም ቢሆን ዘንድሮም የሚያዋጣ ሙግት አይደለም። አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ንጉሡ ዳዊት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

4፥172 አልመሢሕ ለአላህ ባሪያ ከመኾን ፈጽሞ አይጠየፍም፡፡ لَّن يَسْتَنكِفَ الْمَسِيحُ أَن يَكُونَ عَبْدًا لِّلَّهِ

መሢሑ ከዳዊት ዘር የሚመጣ ነቢይ ስለሆነ "ዳዊት" ተብሏል፥ "ደውድ" דָּוִד ማለት "የተወደደ" ማለት ነው፦
ሕዝቅኤል 37፥24 ባሪያዬም ዳዊት ንጉሥ ይሆናቸዋል፥ ለሁሉም አንድ እረኛ ይሆንላቸዋል። በፍርዴም ይሄዳሉ፥ ትእዛዜንም ይጠብቃሉ ያደርጓትማል። וְעַבְדִּ֤י דָוִד֙ מֶ֣לֶךְ עֲלֵיהֶ֔ם וְרֹועֶ֥ה אֶחָ֖ד יִהְיֶ֣ה לְכֻלָּ֑ם וּבְמִשְׁפָּטַ֣י יֵלֵ֔כוּ וְחֻקֹּתַ֥י יִשְׁמְר֖וּ וְעָשׂ֥וּ אֹותָֽם׃

መሢሑ ኢየሱስ ሲሆን ኢየሱስ ዳግም ሲመጣ ሰዎች በአምላክ ፍርድ ይሄዳሉ፣ ትእዛዙንም ይጠብቃሉ ያደርጉታል፥ ፈጣሪ የሚመጣውን መሢሕ፦ "ዐብዲ" עַבְדִּ֔י ማለትም "ባሪያዬ" ይለዋል። ይህ የፈጣሪ ባሪያ ንጉሥ፣ እረኛ፣ አለቃ ነው፦
ሕዝቅኤል 37፥25 ባሪያዬም ዳዊት ለዘላለም አለቃ ይሆናቸዋል። וְדָוִ֣ד עַבְדִּ֔י נָשִׂ֥יא לָהֶ֖ם לְעֹולָֽם׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "ዘላለም" ለሚለው የገባው ቃል "ዖላም" עוֹלָ֗ם ሲሆን አላፊ ወይም መጻኢ ውስን ጊዜን ለማመልከት ይውላል፥ ለምሳሌ፦ እዚህ ጥቅስ ላይ መጻኢ ውስን ጊዜን ለማመልከት መጥቷል፦
ዘጸአት 21፥6 ወደ ደጁም ወደ መቃኑ አቅርቦ ጆሮውን በወስፌ ይብሳው፤ “ለዘላለምም” ባሪያው ይሁን። וְהִגִּישֹׁ֤ו אֲדֹנָיו֙ אֶל־הָ֣אֱלֹהִ֔ים וְהִגִּישֹׁו֙ אֶל־הַדֶּ֔לֶת אֹ֖ו אֶל־הַמְּזוּזָ֑ה וְרָצַ֨ע אֲדֹנָ֤יו אֶת־אָזְנֹו֙ בַּמַּרְצֵ֔עַ וַעֲבָדֹ֖ו לְעֹלָֽם׃ ס

ስለዚህ "ለዘላለም አለቃ ይሆናቸዋል" ሲባል መጻኢ ውስን ጊዜን ለማመልከት ነው። የሚያጅበው ነገር አንዱ አምላክ ያህዌህ እና ንጉሥ፣ እረኛ፣ አለቃ የተባለው መሢሑ "ወ" וְ ማለትም "እና" በሚል መስተጻምር ተለይተዋል፦
ሆሴዕ 3፥5 ከዚያም በኋላ የእስራኤል ልጆች ተመልሰው አምላካቸውን ያህዌህን እና ንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ። אַחַ֗ר יָשֻׁ֙בוּ֙ בְּנֵ֣י יִשְׂרָאֵ֔ל וּבִקְשׁוּ֙ אֶת־יְהוָ֣ה אֱלֹהֵיהֶ֔ם וְאֵ֖ת דָּוִ֣ד מַלְכָּ֑ם
ኤርሚያስ 30፥9 ለአምላካቸው ለያህዌህ እና ለማስነሣላቸው ለንጉሣቸው ለዳዊትም ይገዛሉ። וְעָ֣בְד֔וּ אֵ֖ת יְהוָ֣ה אֱלֹֽהֵיהֶ֑ם וְאֵת֙ דָּוִ֣ד מַלְכָּ֔ם אֲשֶׁ֥ר אָקִ֖ים לָהֶֽם׃ ס

እዚህ አንቀጽ ላይ "ይገዛሉ" ለሚለው የገባው የግሥ መደብ "ዓቤዱ" עָ֣בְד֔וּ ሲሆን ቅሉ ግን ሚሽነሪዎች በአንድ ቃለ ማሠሪያ አንቀጽ ላይ ያለውን ይህንን ግሥ "ያመልካሉ" በማለት ይረዱታል፥ ይህ ያረጀ እና ያፈጀ፤ የተመታ እና የተምታታ መደዴ ሙግት ነው። ምክንያቱም ከአምላክ ጋር "እና" በሚል መስተጻምር በአንድ ግሥ ተጫፍሮ እና ተዛርፎ የተቀመጠ ፍጡር በፍጹም ፈጣሪ ስላልሆነ አይመለክም፦
2ኛ ዜና 35፥3 አሁንም አምላካችሁን ያህዌህን እና ሕዝቡን እስራኤልን አገልግሉ። עִבְדוּ֙ אֶת־יְהוָ֣ה אֱלֹֽהֵיכֶ֔ם וְאֵ֖ת עַמֹּ֥ו יִשְׂרָאֵֽל׃

“ዒብዱ” עִבְדוּ֙ ማለት “አገልግሉ” “ተገዙ” “አምልኩ” ማለት ነው፥ እና የእስራኤል ሕዝብ ከያህዌህ ጋር ይመለካል ማለት ነውን? “አይ የእስራኤል ሕዝብ ይገለገላል የተባለው ያህዌህ በሚገለገልበት ሒሣብ አይደለም” ካላችሁ እንግዲያውስ "ለአምላካቸው ለያህዌህ እና ለማስነሣላቸው ለንጉሣቸው ለዳዊትም ይገዛሉ" ማለትን በዚህ ስሌት ተረዱት! ንጉሡ ዳዊት ከአምላክ ጋር "እና" በሚል መስተጻምር በአንድ ግሥ ተጫፍሮ እና ተዛርፎ ተሰግዶለታል፦
1ኛ ዜና 29፥20 ራሳቸውንም አዘንብለው ለያህዌህ እና ለንጉሡ ሰገዱ። וַיִּקְּד֧וּ וַיִּֽשְׁתַּחֲו֛וּ לַיהוָ֖ה וְלַמֶּֽלֶךְ׃

እዚህ ዐውድ ላይ "ንጉሡ" የተባለውን ንጉሡ ዳዊት እንደሆነ እሙን እና ቅቡል ነው፥ ለያህዌህ እና ለዳዊት "ሰገዱ" ተብሎ የገባው የግሥ መደብ "ዪስታሃዉ" יִּֽשְׁתַּחֲו֛וּ ሲሆን ሥርወ-ቃሉ "ሻኻህ" שָׁחָה ነው። እና ዳዊት ከያህዌህ ጋር ይመለካል ማለት ነውን? እንቀጥል፦
መሣፍንት 7፥18 እኔ ከእኔም ጋር ያሉት ሁሉ ቀንደ መለከት ስንነፋ፥ እናንተ ደግሞ በሰፈሩ ዙሪያ ሁሉ ቀንደ መለከታችሁን ንፉ፦ "ለያህዌህ እና ለጌዴዎን" በሉ፡ አላቸው። וְתָקַעְתִּי֙ בַּשֹּׁופָ֔ר אָנֹכִ֖י וְכָל־אֲשֶׁ֣ר אִתִּ֑י וּתְקַעְתֶּ֨ם בַּשֹּׁופָרֹ֜ות גַּם־אַתֶּ֗ם סְבִיבֹות֙ כָּל־הַֽמַּחֲנֶ֔ה וַאֲמַרְתֶּ֖ם לַיהוָ֥ה וּלְגִדְעֹֽון׃ פ

እዚህ አንቀጽ ላይ ጌዴዎን "እና" በሚል መስተጻምር ከያህዌህ ጋር ስለተጫፈ እና ስለተዛረፈ እኩል ክብር እና ሥልጣን አላቸውን? እንቀጥል፦
ምሳሌ 24፥21 ልጄ ሆይ! ያህዌህን እና ንጉሥን ፍራ። יְרָֽא אֶת־ יְהוָ֣ה בְּנִ֣י וָמֶ֑לֶךְ

እዚህ ዐውድ ላይ "ንጉሥ" የተባለው በፍርድ ወንበር የሚቀመጥ ማንኛውም ንጉሥ ያመለክታል፥ ምሳሌ 20፥8 ተመልከት! ያህዌህ እና ንጉሥን "ፍሩ" ተብሎ የገባው የግሥ መደብ "ዩራ" יְרָֽא־ ሲሆን ሥርወ-ቃሉ "ያረ" יָרֵא ነው። እና በፍርድ ወንበር የሚቀመጥ ማንኛውም ንጉሥ ከያህዌህ ጋር ይመለካል ማለት ነውን?
ስለዚህ ከላይ ፈጣሪ "ባሪያዬ" የሚለው መሢሑ አይመለክም። ከዚያ በተቃራኒው ይህ መሢሕ ለአሏህ ባሪያ ከመኾን ፈጽሞ አይጠየፍም፦
4፥172 አልመሢሕ ለአላህ ባሪያ ከመኾን ፈጽሞ አይጠየፍም፡፡ لَّن يَسْتَنكِفَ الْمَسِيحُ أَن يَكُونَ عَبْدًا لِّلَّهِ

አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሥላሴ በታርገም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ

180 ድኅረ ልደት የአንጾኪያው ቴዎፍሎስ "ሦስት" የሚለውን ቃል ተጠቅሞ ነበር፦
"ሊቃውንት ከመፈጠራቸው በፊት ያሉት ሦስት ቀናት የሦስቱ ማለትም የአምላክ፣ የቃሉ እና የጥበቡ ምሳሌዎች ናቸው"(Letter to Autolycus, Book II, Chapter XV(15)

የአንጾኪያው ቴዎፍሎስ ጽሑፍ ላይ "ሦስት" ለሚለው የገባው ቃል "ትሪያስ" τρῐᾰ‌ς ሲሆን አምላክን፣ ቃሉን እና ጥበቡን ለማመላከት እና ለማመልከት እንጂ የሥላሴ እሳቤ ለመግለጽ በፍጹም አልተጠቀመበትም። ባይሆን በ 220 ድኅረ ልደት የካርቴጁ(ቱኒዚያ) ጠርጡሊያኖስ የሥላሴን እሳቤ አርቅቋል፥ ጠርጡሊያኖስ የሞንታኖስ ተማሪ የነበረ ነበር። "ታርገም" תרגום‎ ማለት ደግሞ "ትርጉም"translation" ማለት ነው፦
ዕዝራ 4፥7 በዐረማይስጥ ቋንቋ "ተተርጉሞ" ነበር። ומתרגם ארמית׃ פ

"ተተርጉሞ" ለሚለው የገባው ቃል "መቱርጋም" מְתֻרְגָּ֥ם ነው፥ ከ 35 እስከ 120 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረው አኪላስ(አቂላስ) ያዘጋጀው ቶራህን መሠረት ያደረገ ማብራሪያ ታርገም አኪላስ"Targum Onkelos" ሲባል ከ 110 ቅድመ ልደት እስከ 10 ድኅረ ልደት ይኖር ነበር ተብሎ በሚገመተው ዮናታን ቤን ዑዚኤል ያዘጋጀው ነቢምን መሠረት ያደረገ ማብራሪያ ደግሞ ታርገም ዮናታን"Targum Jonathan" ይባላል።
እንደእነ አንቶኒ ሮጀርስ ያሉ ሥላሴአውያን"trinitarian" ታርገም ውስጥ ለሥላሴ ትምህርት ድምዳሜ ላይ ያደርሳል ብለው በግድ ሲላላጡ እና ሲጋጋጡ ማየት እየተለመደ ቢመጣም ቅሉ ግን የሥላሴን እሳቤ እንኩትኩት የሚያደርጉ ማስረጃዎች በቁና እየተገኙ ነው። እስቲ እንይ፦
ታርገም ዮናታን ዘፍጥረት 1፥26 "ጌታ በፊቱ ለሚያገለግሉት መላእክት፦ "ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር" አለ። וּבְרָא יְיָ יַת אָדָם בִּדְיוּקְנֵיהּ בְּצַלְמָא יְיָ בְּרָא יָתֵיהּ בְּמָאתָן וְאַרְבְּעִין וּתְמַנֵי אֵיבָרִין בִּתְלַת מְאָה וְשִׁיתִּין וְחַמְשָׁא גִידִין וּקְרַם עֲלוֹי מוֹשְׁכָא וּמְלֵי יָתֵיהּ בִּסְרָא

"ልብላ" ብል አዳማጬን እንደማያካትት ሁሉ በግነት "እንብላ" ብል አዳማጬን ላያካትት ይችላል፥ ለምሳሌ፦ አምላክ፦ "ልፍጠር" ብሎ ለመላእክት ተናግሯል፦
ዘፍጥረት 2፥18 ያህዌህ ኤሎሂምም አለ፦ "ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት "ልፍጠርለት"። וַיֹּאמֶר יְהוָה אֱלֹהִים, לֹא-טוֹב הֱיוֹת הָאָדָם.ֹלְבַדּוֹ; אֶעֱשֶׂה-לּוֹ עֵזֶר, כְּנֶגְדּו

እዚህ አንቀጽ ላይ ዕብራይስጡ "አዔሳህ" ּאֶֽעֱשֶׂה ማለትም “ልፍጠር” አለ እንጂ "ናዓሳህ" נַעֲשֶׂה እንፍጠር” አላለም፥ እንግሊዘኞቹም፦ "I will make" ብሎ አስቀምጦታል። ነገር ግን "እንፍጠር" የሚለው "ልፍጠር" የሚለውን ለማግነን መጥቷል፦
ኩፋሌ 4፥4 ወይቤለነ እግዚአብሔር ለነ፤ አኮ ሰናይ የሀሉ ብእሲ ባሕቲቱ፤ አላ "ንግበር" ሎቱ መርድአ ዘከማሁ፤ መወየደ እግዚአብሔር አምላክነ ሕድመተ ላዕሌሁ ወኖመ”

ትርጉም፦ "ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ለእኛ እንዲህ አለን፦ "ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት "እንፍጠርለት"።
ዐውዱ ላይ "ፈጣሪያችን" የሚሉት መላእክት ሲሆኑ "እንዲህ አለን" በማለት "እንፍጠርለት" እንዳላቸው ያሳያል። "ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ" ሲልም "እኛ" የሚለው መላእክትን እንደሆነ ታርገም ዮናታን ይናገራል፦
ታርገም ዮናታን ዘፍጥረት 3፥22 "ጌታ አምላክም በፊቱ ለሚያገለግሉት መላእክት፦ "እነሆ እኔ በሰማያት በላይ ብቸኛ እንደሆንኩኝ አዳምም በምድር ላይ ብቸኛ ነው፥ ከእርሱ የተነሳ መልካሙን እና ክፉውን ለይተው የሚያውቁ ይሆናሉ" አለ። וַאֲמַר יְיָ אֱלהִים לְמַלְאָכַיָא דִי מְשַׁמְשִׁין קֳדָמוֹי הָא אָדָם הֲוָה יְחִידִי בְּאַרְעָא הֵיכְמָא דַאֲנָא יְחִידִי בִּשְׁמֵי מְרוֹמָא וַעֲתִידִין לְמֵיקוּם מִינֵהּ דְיַדְעוּן לְמַפְרְשָׁא בֵּין טַב לְבִישׁ אִלוּ נָטַר מִצְוָותָא דִפְקִידְתֵּיהּ אִית הוּא

"ኑ! እንውረድ" የሚለውም በፊቱ ቆመው ለሚያገለግሉት ሰባ መላእክት እንደሆነ ታርገም ዮናታን ይናገራል፦
ታርገም ዮናታን ዘፍጥረት 11፥7 " ጌታም በፊቱ ለሚቆሙት ሰባ መላእክት፦ "ኑ! እንውረድ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው" አለ። וַאֲמַר יְיָ לְשַׁבְעִין מַלְאָכַיָא דְקַיְימִין קוֹמוֹי אִיתוּן כְּדֵין וְנָחִית וּנְעַרְבְּבָא תַּמָן לִישַׁנְהוֹן דְלָא יִשְׁמְעוּן אֱינַשׁ לִישָׁן חַבְרֵיהּ

እንቀጥል? አብርሃም ቤት የገቡት ሦስት ሰዎች ሦስት መላእክት እንደሆኑ የኢየሩሳሌም ታርገም ይናገራል፦
ታርገም ኢየሩሳሌም ዘፍጥረት 18፥1 "ሦስት መላእክት ወደ አባታችን አብርሃም ተላኩ፥ ሦስቱም ለሦስት ጉዳይ ተላኩ። ምክንያቱም ከከፍተኛ መላእክት አንዱ ከአንድ በላይ ለሆነ ጉዳይ መላክ አይቻልምና፥ የመጀመሪያው መልአክ አባታችን አብርሃምን ሳራ ይስሐቅን እንደምትወልድ ሊያበስረው ተላከ፣ ሁለተኛው መልአክ ሎጥን ከሚገለበጡት ከተሞች ለማውጣት ተላከ፣ ሦስተኛው መልአክ ደግሞ ሰዶምን፣ ገሞራን፣ አዳማን እና ሰቦይምን ለመገለባበጥ ተላከ። תְּלָתָא מַלְאָכַיָא אִשְׁתַּלְחוּ לְוַת אֲבוּנָן אַבְרָהָם וּתְלָתֵיהוֹן אִשְׁתַּלְחִין לִתְלַת מִילִין אֲרוּם לֵית אֶפְשָׁר לְחָד מִן מַלְאֲכֵי מְרוֹמָא דְיִשְׁתַּלַח בִּידֵיהּ יַתִּיר מִן מִילָה חֲדָא מַלְאָכָא קַדְמָאָה אִשְׁתַּלַח לְבַשְרָא לְאָבוּנָא אַבְרָהָם דְהָא שָרָה יָלְדָה לְיִצְחָק מַלְאָכָא תִּינְיָנָא אִישְׁתַּלַח לְשֵׁיזְבָא יַת לוֹט מִגוֹ הֲפֵיכָתָא מַלְאָכָא תְּלִתָאָה אִשְׁתַּלַח לְמֶהְפַךְ לִסְדוֹם וַעֲמוֹרָה אַדְמָה וּצְבוֹיִם בְּגִין כֵּן הֲוָה פִּתְגָם נְבוּאָה מִן קָדָם

ክርስቲያኖች ሆይ! ነቢያት ስለ ሥላሴ በፍጹም አላስተማሩም። አምላክን አንድ ባላችሁበት አፋችሁ «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አሏህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፦
4፥171 «ሦስት ነው» አትበሉ! ተከልከሉ! ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ وَلَا تَقُولُوا ثَلَاثَةٌ ۚ انتَهُوا خَيْرًا لَّكُمْ ۚ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ

አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አልፋ እና ዖሜጋ

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

57፥3 እርሱ ፊትም ያለ፣ ኋላም ቀሪ፣ ግልጽም፣ ስውርም ነው፡፡ እርሱም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ هُوَ الْأَوَّلُ وَالْآخِرُ وَالظَّاهِرُ وَالْبَاطِنُ ۖ وَهُوَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

"አፓካሊፕሲስ" ἀποκάλυψις ማለት "ቀለምሲስ" "ራእይ" "መገለጥ"revelation" ማለት ሲሆን ፈጣሪ ለኢየሱስ እንዲናገር የሰጠው "ራእይ" ነው፥ ይህም ራእይ ከአምላክ ወደ ኢየሱስ፣ ከኢየሱስ ወደ መልአኩ፣ ከመልአኩ ወደ ዮሐንስ የመጣ ነው፦
ራእይ 1፥1 ቶሎ መሆን የሚገባውን ነገር ለአገልጋዮቹ እንዲያሳይ አምላክ የሰጠው የኢየሱስ ክርስቶስ ራእይ ይህ ነው፥ ኢየሱስም መልአኩን ልኮ ለአገልጋዩ ለዮሐንስ ገለጠለት። Ἀποκάλυψις Ἰησοῦ Χριστοῦ, ἣν ἔδωκεν αὐτῷ ὁ Θεός, δεῖξαι τοῖς δούλοις αὐτοῦ ἃ δεῖ γενέσθαι ἐν τάχει, καὶ ἐσήμανεν ἀποστείλας διὰ τοῦ ἀγγέλου αὐτοῦ, τῷ δούλῳ αὐτοῦ Ἰωάνῃ,

የተጠቀምኩት ከግሪኩ ጋር ተቀራራቢነት ያለውን አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነው። ይህ ለኢየሱስ የተሰጠ ራእይ የአምላክ ንግግር እና የኢየሱስ ምስክርነት ነው፦
ራእይ 1፥2 እርሱም ስለ የአምላክ ቃል እና የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት ያየውን ሁሉ መሰከረ። ὃς ἐμαρτύρησεν τὸν λόγον τοῦ Θεοῦ καὶ τὴν μαρτυρίαν Ἰησοῦ Χριστοῦ, ὅσα εἶδεν.

ይህ ለኢየሱስ የተሰጠው ኦርጅናል ራእይ በ 286 ድኅረ ልደት በተነሱት የሮም አላውያን ነገሥታት በሆኑት በዲዮቅልጥያኖስ እና በመክስምያኖስ ከጠፋ በኃላ ከ 347 እስከ 407 ይኖር የነበረ ዮሐንስ አፈ ወርቅ"John Chrysostom" የሚባል የቁስጥንጥንያ ኤጲጵ ቆጶስ "የኢየሱስ ራእይ ድጋሚ ተገለጠልኝ" ብሎ ከራእይ 22፥18-21 የእርሱ ንግግር እንደጨረ አንድምታው ላይ ተቀምጧል፦
ሊቀ ሊቃውንት መሐሪ ትርፌ፤ መጻሕፍተ ሐዲሳት ሠለስቱ፤ ራእየ ዮሐንስ አንድምታ ትርጓሜ መቅድም፤ ገጽ 351- 353.

ሆነም ቀረ ራእዩ አምላክ ለኢየሱስ የሰጠው ሲሆን የራእዩ ባለቤት አንዱ አምላክ ነው፥ ይህ አንዱ አምላክ ከኢየሱስ በሰዋስው ተለይቶ ተቀምጧል፦
ራእይ 1፥4 ካለውና ከነበረው "ከ-"ሚመጣውም፥ በዙፋኑም ፊት ካሉት "ከ-"ሰባቱ መናፍስት፥ ከታመነውም ምስክር ከሙታንም በኵር የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነ "ከ-ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና ሰላም ለእናንተ ይሁን። χάρις ὑμῖν καὶ εἰρήνη ἀπὸ ὁ ὢν καὶ ὁ ἦν καὶ ὁ ἐρχόμενος, καὶ ἀπὸ τῶν ἑπτὰ Πνευμάτων ἃ ἐνώπιον τοῦ θρόνου αὐτοῦ, καὶ ἀπὸ Ἰησοῦ Χριστοῦ, ὁ μάρτυς ὁ πιστός, ὁ πρωτότοκος τῶν νεκρῶν καὶ ὁ ἄρχων τῶν βασιλέων τῆς γῆς.

ጸጋ እና ሰላም ከሦስት ምንነቶች እንደመጣ ይህ ጥቅስ ያስረዳል፥ አንደኛ "ያለው፣ የነበረው እና የሚመጣው" ከተባለው፣ ሁለተኛ "ሰባቱ መናፍስት" ከተባሉት እና ሥስተኛ "ታማኝ ምስክር" ከሆነው ከኢየሱስ ነው። "አፖ" ἀπὸ ማለት "ከ" ማለት ሲሆን ይህ መስተዋድድ "ያለው፣ የነበረው እና የሚመጣው" ከሚለው ቃል በፊት፣ "ሰባቱ መናፍስት" ከሚለው ቃል በፊት እና "ከታማኙ ምስክር" በፊት መግባቱ ኢየሱስን "ያለው፣ የነበረው እና የሚመጣው" ከተባለው ይነጥለዋል፥ "ያለው፣ የነበረው እና የሚመጣው" የተባለውን ምንነት ከሰባቱ መናፍስት እና ከኢየሱስ "ካይ" καὶ ማለት "እና" በሚል መስተጻምር ተለይቷል። ያለው፣ የነበረው እና የሚመጣው ሁሉን የሚችል ጌታ አምላክ፦ "አልፋ እና ዖሜጋ እኔ ነኝ" ብሏል፦
ራእይ 1፥8 ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ "አልፋ እና ዖሜጋ እኔ ነኝ" ይላል። Ἐγώ εἰμι τὸ Ἄλφα καὶ τὸ Ὦ, λέγει Κύριος ὁ Θεός, ὁ ὢν καὶ ὁ ἦν καὶ ὁ ἐρχόμενος, ὁ Παντοκράτωρ.

ዮሐንስ "አልፋ እና ዖሜጋ እኔ ነኝ" ያለው ማን እንደሆነ ለማመልከት ሲናገር "ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚችል ጌታ አምላክ" በማለት "አልፋ እና ዖሜጋ እኔ ነኝ" ባዩ ለኢየሱስ ራእይ የሰጠው እና "ከ" "እና" በሚል ሰዋስው የተለየው አንዱ አምላክ ነው። ሁሉንም የሚችል ጌታ አምላክ ከኢየሱስ ተለይቶ የተቀመጠ ምንነት ነው፦
ራእይ 21፥22 ሁሉንም የሚችል ጌታ አምላክ እና በጉ መቅደስዋ ናቸው። ὁ γὰρ Κύριος ὁ Θεὸς ὁ Παντοκράτωρ ναὸς αὐτῆς ἐστιν, καὶ τὸ Ἀρνίον.

"ናቸው" የሚለው አያያዥ ግሥ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክን እና ኢየሱስን በቅጡ ለይቷቸዋል። "ሁሉንም የሚገዛ" ተብሎ በዐማርኛ የተቀመጠው ቃል ግሪኩ "ፓንቶክራቶስ" Παντοκράτωρ ሲሆን "ሁሉን ቻይ"the Almighty" ማለት ነው፥ በዕብራይስጥ "ሻዳይ" שַׁדַּ֔י ሲሆን ራእይ ላይ ያለ የነበረ ፓንቶክራቶስ አብ ነው፦
ራእይ 11፥17 እንዲህ አሉ፦ "ያለህ እና የነበርህ "ሁሉን የምትችል" Παντοκράτωρ ጌታ አምላክ ሆይ፥ ትልቁን ኃይልህን ስለ ያዝህ ስለ ነገሥህም እናመሰግንሃለን።
ራእይ 15፥3 "ሁሉን የምትችል" Παντοκράτωρ ጌታ አምላክ ሆይ፥ ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው።
ራእይ 16፥7 "ሁሉን የምትችል" Παντοκράτωρ ጌታ አምላክ ሆይ፥ ፍርዶችህ እውነትና ጽድቅ ናቸው።
2 ቆሮንቶስ 6፥18 ለእናንተም "አባት" እሆናለሁ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆች እና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ፤ ይላል፤ ሁሉን ቻይ ጌታ። καὶ ἔσομαι ὑμῖν εἰς Πατέρα, καὶ ὑμεῖς ἔσεσθέ μοι εἰς υἱοὺς καὶ θυγατέρας, λέγει Κύριος Παντοκράτωρ.
"አባት" አብ ከሆነ ሁሉን ቻይ ጌታ እርሱ ነው፥ ኢየሱስ ደግሞ ወልድ እንጂ አብ አይደለም። ሲጀመር ኢየሱስ ሁሉን ነገር በማድረግ ሁሉን ቻይ ሳይሆን ከራሱ ምንም ማድረግ የማይችል ነው፥ ሲቀጥል በባይብል "ጌታ አምላክ" የተባለው ለኢየሱስ ዙፋንን የሰጠው እና ብቻውን የሚመለከው ነው፦
ሉቃስ 10፥22 ሁሉ ከአባቴ ዘንድ "ተሰጥቶኛል"።
ሉቃስ 1፥32 ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን "ይሰጠዋል"።
ማቴዎስ 4፥10 "ለጌታህ ለአምላክህ" ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ"።

ሰጪ ጌታ አምላክ አብ ከሆነ ተሰጪ ኢየሱስ ነው። "ጌታ አምላክ" ተብሎ የተቀመጠው "ያህዌህ አምላክ" ነው፥ ኢየሱስ፦ "ተብሎ ተጽፏል" ብሎ የጠቀሰው ላይ ጥቅሱ "ያህዌህ አምላክህን" የሚል ነው፦
ዘዳግም 6፥13 ያህዌህ አምላክህን ፍራ፣ አምልክ፣ በስሙም ማል። אֶת־יְהוָ֧ה אֱלֹהֶ֛יךָ תִּירָ֖א וְאֹתֹ֣ו תַעֲבֹ֑ד וּבִשְׁמֹ֖ו תִּשָּׁבֵֽעַ׃

"የሐዋሐ" י‎ה‎ו‎ה በሚለው ቴትራግራማቶን ፋንታ በግሪኩ ላይ "ኩርዮስ" κύριος እያሉ ስለተኩት "ጌታ አምላክ" የሚለው ንግግር ትንሽ አምታቷል። ስለዚህ "አልፋ እና ዖሜጋ እኔ ነኝ" ያለው ኤልሻዳዩ ያህዌህ አምላክ ነው፥ ይህም አብ ነው። "የሚመጣው" የሚለው በዘመናት የሸመገለውን አብን ነው፦
ዳንኤል 7፥22 በዘመናት የሸመገለው "እስኪመጣ" ድረስ፥ ፍርድም ለልዑሉ ቅዱሳን እስኪሰጥ ድረስ።

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ላይ የዳንኤልን ንግግር ይዘው ስለ አብ መምጣት እንደሆነ ተናግረዋል፦
መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 10 ቁጥር 13
“ወበእንተ ምጽአተ አብ ይቤ ነቢይ ዳንኤል ወአምጹ መናብርተ ለብሉየ መዋዕል”።

ትርጉም፦ “ነቢዩ ዳንኤል ስለ አብ ማምጣት፦ “በዘመናት ለሸመገለው መናብርት አመጡለት” አለ”።

"አብ" ማለት "ባለቤት" ማለት ሲሆን "አቡ ቀለምሲስ" ማለት "የራእይ ባለቤት" "ባለ ራእይ" ማለት ነው፥ ይህም ለዮሐንስ የተሰጠ ማዕረግ ነው። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ላይ የዮሐንስ አቡ ቀለምሲስ ንግግር ይዘው "ያለ የነበረ እና የሚመጣው" ስለ አብ መምጣት እንደሆነ ተናግረዋል፦
መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 10 ቁጥር 18
“ወካዕበመ ነገረ ዮሐንስ አቡ ቀለምሲስ በእንተ ምጽአተ አብ ወወልድ”።

ትርጉም፦ “ሁለተኛም ዮሐንስ አቡ ቀለምሲስ ስለ አብ እና ወልድ መምጣት ተናገረ”።

ዮሐንስ በራእይ ላይ ስለ አብ መምጣት የተናገረበት ቦታዎች ራእይ 1፥4 ራእይ 1፥8 ራእይ 4፥8 ራእይ 22፥7 ራእይ 22፥12 ናቸው። ኢንሻሏህ ይቀጥላል....

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አልፋ እና ዖሜጋ

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

57፥3 እርሱ ፊትም ያለ፣ ኋላም ቀሪ፣ ግልጽም፣ ስውርም ነው፡፡ እርሱም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ هُوَ الْأَوَّلُ وَالْآخِرُ وَالظَّاهِرُ وَالْبَاطِنُ ۖ وَهُوَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

ራእይ ላይ በዙፋኑ ላይ አንድ ተቀምጭ ነበረ፥ ይህም ተቀማጭ በቀኝ እጁ ላይ በውስጥና በኋላ የተጻፈበት እና በሰባት ማኅተም የተዘጋ መጽሐፍ ነበረው፦
ራእይ 4፥2 እነሆ ዙፋን በሰማይ ቆሞአል፥ በዙፋኑም ላይ ተቀማጭ ነበረ።
ራእይ 5፥1 በዙፋኑ ላይም በተቀመጠው በቀኝ እጁ ላይ በውስጥና በኋላ የተጻፈበት እና በሰባት ማኅተም የተዘጋ መጽሐፍን አየሁ።

እንደሚታወቀው "በግ" ማለት "የሚታረድ ሥጋ" እንጂ መለኮት አይደለም፥ እንደ ባይብሉ "በግ" የተባለው በተምሳሌታዊ "ሰው" ነው። ይህም ሰው ኢየሱስ ሲሆን ኢየሱስ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠ ከዚያ ከቀኝ እጁ መጽሐፉን ወሰደው፦
ራእይ 5፥7 (በጉ) መጥቶም በዙፋን ላይ ከተቀመጠ ከዚያ ከቀኝ እጁ መጽሐፉን ወሰደው።

ወሳጁ ኢየሱስ የወሰደው በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ነው፥ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው ደግሞ አንዱ አምላክ "በዘመናት የሸመገለው" አብ ነው፦
ዳንኤል 7፥9 ዙፋኖችም እስኪዘረጉ ድረስ አየሁ፥ "በዘመናት የሸመገለውም ተቀመጠ"።
ራእ 19፥4 ሀያ አራቱም ሽማግሌዎችና አራቱ እንስሶች በፊታቸው ተደፍተው "በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለ-አምላክ"፦ "አሜን፥ ሃሌ ሉያ" እያሉ ሰገዱለት። καὶ ἔπεσαν οἱ πρεσβύτεροι οἱ εἴκοσι τέσσαρες καὶ τὰ τέσσερα ζῷα, καὶ προσεκύνησαν τῷ Θεῷ τῷ καθημένῳ ἐπὶ τῷ θρόνῳ λέγοντες Ἀμήν, Ἁλληλουϊά.

"ሃሌሉ ያህ" הַלְלוּ-יָהּ ማለት "ያህን አመስግኑት" ማለት ነው፥ መዝሙር 106፥1 ተመልከት! ያህ የያህዌህ ምጻረ ቃል ሲሆን በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው አንዱ አምላክ ያህዌህ እና በጉ "እና" በሚል መስተጻምር ተለይተዋል፦
ራእይ 5፥13 በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው እና ለበጉ ይሁን። Τῷ καθημένῳ ἐπὶ τῷ θρόνῳ καὶ τῷ Ἀρνίῳ
ራእይ 6፥16 ተራራዎችንና ዓለቶችንም፦ በላያችን ውደቁ፡ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት እና ከበጉ ቍጣ ሰውሩን" አሉአቸው። καὶ λέγουσιν τοῖς ὄρεσιν καὶ ταῖς πέτραις Πέσετε ἐφ’ ἡμᾶς καὶ κρύψατε ἡμᾶς ἀπὸ προσώπου τοῦ καθημένου ἐπὶ τοῦ θρόνου καὶ ἀπὸ τῆς ὀργῆς τοῦ Ἀρνίου,
ራእይ 7፥10 በታላቅም ድምፅ እየጮሁ አሉ፦ በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለአምላካችን እና ለበጉ ማዳን ነው። καὶ κράζουσιν φωνῇ μεγάλῃ λέγοντες Ἡ σωτηρία τῷ Θεῷ ἡμῶν τῷ καθημένῳ ἐπὶ τῷ θρόνῳ καὶ τῷ Ἀρνίῳ.

ዐማርኛ ላይ "በጉ" በሚለው መድረሻ ቅጥያ ላይ ያለው "ም" የሚለው ጥገኛ ምዕላድ "እና" የሚለውን መስተጻምር ለመተካት የመጣ ነው፥ በግሪኩ "ካይ" καὶ ስለሚል የእንግሊዝኛ መተርጉማን "and" በማለት አስቀምጠውታል። በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው አንዱ አምላክ ከበጉ የተለየው አብ፦ "አልፋ እና ዖሜጋ፥ መጀመሪያው እና መጨረሻው እኔ ነኝ" ብሏል፦
ራእይ 21፥5 በዙፋንም የተቀመጠው፦ እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ አለ። ለእኔም፦ እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ አለኝ።
ራእይ 21፥6 አለኝም፦ "ተፈጽሞአል። አልፋ እና ዖሜጋ፥ መጀመሪያው እና መጨረሻው እኔ ነኝ"። καὶ εἶπέν μοι Γέγοναν. ἐγὼ τὸ Ἄλφα καὶ τὸ Ὦ, ἡ ἀρχὴ καὶ τὸ τέλος.

በባይብል "አልፋ እና ዖሜጋ" የሚለው ቃል ሦስት ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን ከሦስቱ አንዱ ይህ ጥቅስ ነው፥ የኮይኔ ግሪክ ፊደላት 24 ሲሆኑ "ዐቢብ ፊደል"uppercase" እና "ንዑስ ፊደል"lowercase" ጉልኅ ሚና አላቸው። የመጀመሪያው ፊደል "አልፋ" άλφα ነው፥ "አልፋ" ማለት "መጀመሪያ" "ቀዳማይ" "ጥንታዊ" ማለት ነው። ዐቢብ አልፋ ፊደሉ Α ሲሆን ንዑስ አልፋ ፊደሉ α ነው፥ በድምጽ ሲነበብ "ኣ" ነው።
የመጨረሻው ፊደል "ዖሜጋ" ωμέγα ነው፥ "ዖሜጋ" ማለት "መጨረሻ" "ደኃራይ" "ኃላዊ" ማለት ነው። ዐቢብ ኦሜጋ ፊደሉ Ω ሲሆን ንዑስ ኦሜጋ ፊደሉ ω ነው፥ በድምጽ ሲነበብ "ዖ" ነው።
በኢየሱስ ራእይ ውስጥ "አልፋ እና ዖሜጋ" የተባለው አንዱ አምላክ ሆኖ ሳለ ወደ ኢየሱስ ለማስጠጋት ይህንን ጭማሬ አስገብተዋል፦
ራእይ 1፥11 እንዲህም ሲል፦ "አልፋ እና ዖሜጋ፥ ፊተኛው እና ኃለኛው እኔ ነኝ"። {Ἐγώ ἐιμι τὸ Α καὶ τὸ Ω, ὁ πρῶτος καὶ ὁ ἔσχατος καὶ}
የግሪኩ እደ ክታባታት ላይ ስለሌለ Greek Interlinear በቅንፍ አስቀምጦታል፥ ራእይ 1፥11 ላይ "አልፋ እና ዖሜጋ፥ ፊተኛው እና ኃለኛው እኔ ነኝ" ብለው የጨመሩት በ 1611 ድኅረ ልደት በታተመው ቅጂ The King James Version (KJV) ላይ ነው። በአገራችን ደግሞ በ 1879 እንደ ኢትዮ ኦርቶዶክስ አቆጣጠር በቁም ጽሑፍ በሚባል እትም ላይ ከኪንግ ጀምስ በመተርጎም አስገብተውታል፥ ይህንን ዓይን ያፈጠጠ ቅጥፈት በሌሎች ዐማርኛ እትም እና በሎሎች እንግሊዝኛ እትም ላይ አሽቀንጥረው ጥለውታል።
ለማንኛውም ኢየሱስ ጅማሮ እና መነሻ ያለው ፍጡር ስለሆነ አልፋ እና ዖሜጋ አይደለም፦
ዮሐንስ 5፥26 አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ ለወልድ በራሱ "ሕይወት" እንዲኖረው "ሰጥቶታልና"።

ወልድ ሕይወትን በስጦታ ያገኘ ሃልዎት ከሆነ ሕይወት ከመሰጠቱ በፊት ሕይወት አልባ ስለሆነ በባዶነት የተቀደመ ነው፥ ሕይወት የተሰጠው ማንነት እና ምንነት መነሻ እና ጅማሮ አለው። የሂፓው አውግስጢኖስ"Augustine of Hippo" ደግሞ ሕይወት ሰጠው ማለት “እርሱ(አብ) ወልድን ወልዶታል” ማለት ነው በማለት ይናገራል፦
፨ እንዲህ አለ፦ ለወልድ በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልን? በአጭሩም እላለሁኝ፦ “እርሱ(አብ) ወልድን ወልዶታል”
Augustine on the Gospel of John. Tractates (Lectures) 19 number 13
፨አብ በራሱ ሕይወት ያለው እንጂ ከወልድ አይደለም፥ ወልድ ግን በራሱ ሕይወት ያለው ከአብ ነው። ወልድ በራሱ እንዲኖር ከአብ የተወለደ ነው፥ ነገር ግን አብ በራሱ እንዲኖር አልተወለደም።
Augustine on the Gospel of John. Tractates (Lectures) 19 number 13
፨ ልክ እርሱ እንደሚለው፦ “አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው ወልድ በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ወልዶታል” ማለቱ ነው።
Augustine on the Gospel of John. Tractates (Lectures) 19 number 13

"ዛሬ” በሚባል ጊዜ ውስጥ ለተፈጠረው ሰው ፈጣሪ “አባት” ሲባል ለፈጠረው ፈጣሪ ደግሞ ያ ፍጡር “ልጅ” ተብሏል፥ በጊዜ ውስጥ የተወለደ ነገር መነሻ አለው፦
ዕብራውያን 1፥5 “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፥ ደግሞም፦ እኔ አባት እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል”።

የዘፍጥረት መጽሐፍ ስሙ በዕብራይስጥ "ረሺት" רֵאשִׁית ሲሆን በዘፍጥረት 1፥1 ላይ መሠረት በማድረግ ትርጉሙ "መጀመሪያ" ነው፦
ዘፍጥረት 1፥1 በመጀመሪያ ኤሎሂም ሰማይን እና ምድርን ፈጠረ። בְּרֵאשִׁ֖ית בָּרָ֣א אֱלֹהִ֑ים אֵ֥ת הַשָּׁמַ֖יִם וְאֵ֥ת הָאָֽרֶץ׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "መጀመሪያ" ለሚለው የገባው ቃል "ረሺት" רֵאשִׁית እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። የዘፍጥረት መጽሐፍ ስሙ በግሪክ ሰፕቱአጀንት"LXX" ደግሞ "ገኔሲስ" γένεσις ሲሆን በዘፍጥረት 2፥4 ላይ መሠረት በማድረግ ትርጉሙ "ልደት" ነው፦
ዘፍጥረት 2፥4 የሰማይ እና የምድር "ልደት" ይህ ነው። Αὕτη ἡ βίβλος γενέσεως οὐρανοῦ καὶ γῆς,

ዘፍጥረት በግዕዝ ኦሪት "ዘልደት" ይባላል፥ "ፍጥረት" እና "ልደት" በሚል ቃል ላይ ያለው መነሻ ቅጥያ "ዘ" አገናዛቢ ዘርፍ "የ" ማለት ሲሆን "የ-ፍጥረት" ወይም "የ-ልደት" ማለት ነው። ሰማይ እና ምድር ልደት አላቸው ማለት ጅማሬ እና መነሻ አላቸው ማለት ከሆነ ኢየሱስ ልደት ስላለው ጅማሮ እና መነሾ አለው፦
ማቴዎስ 1፥18 የኢየሱስ ክርስቶስም "ልደት" እንዲህ ነበረ። Τοῦ δὲ Ἰησοῦ Χριστοῦ ἡ γένεσις οὕτως ἦν.
ሉቃስ 3፥23 ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር።

ልደት ኖሮት ሠላሳ ዓመት ዕድሜ የተቆጠረለት ይህ መነሻ እና ጅማሬ ያለው ማንነት እና ምንነት አልፋ እና ዖሜጋ በፍጹም አይሆንም። ኢንሻሏህ ይቀጥላል....

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አልፋ እና ዖሜጋ

ክፍል ሦስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

57፥3 እርሱ ፊትም ያለ፣ ኋላም ቀሪ፣ ግልጽም፣ ስውርም ነው፡፡ እርሱም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ هُوَ الْأَوَّلُ وَالْآخِرُ وَالظَّاهِرُ وَالْبَاطِنُ ۖ وَهُوَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

በራእይ ውስጥ ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክ አብ እንደሆነ ቁልጭ ባለ መልኩ አይተናል፥ ይህ አንዱ ጌታ አምላክ በቶሎ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ እንዲያሳይ መልአኩን ላከ፦
ራእይ 22፥6 የነቢያትም መናፍስት "ጌታ አምላክ" ቶሎ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ እንዲያሳይ መልአኩን ላከ። καὶ ὁ Κύριος ὁ Θεὸς τῶν πνευμάτων τῶν προφητῶν ἀπέστειλεν τὸν ἄγγελον αὐτοῦ δεῖξαι τοῖς δούλοις αὐτοῦ ἃ δεῖ γενέσθαι ἐν τάχει.
ራእይ 1፥1 ቶሎ መሆን የሚገባውን ነገር ለአገልጋዮቹ እንዲያሳይ አምላክ የሰጠው የኢየሱስ ክርስቶስ ራእይ ይህ ነው። Ἀποκάλυψις Ἰησοῦ Χριστοῦ, ἣν ἔδωκεν αὐτῷ ὁ Θεός, δεῖξαι τοῖς δούλοις αὐτοῦ ἃ δεῖ γενέσθαι ἐν τάχει,

ቶሎ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ እንዲያሳይ መልአኩን በኢየሱስ የላከው ለኢየሱስ ራእይ የሰጠው ጌታ አምላክ ነው፥ ጌታ አምላክ "እነሆም በቶሎ እመጣለሁ" በማለት ይናገራል፦
ራእይ 22፥7 እነሆም በቶሎ እመጣለሁ። የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል የሚጠብቅ ብፁዕ ነው" አለኝ።
ሚልክያስ 4፥6 "መጥቼም" ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።
ማቴዎስ 21፥40 እንግዲህ የወይኑ አትክልት ጌታ "በሚመጣ" ጊዜ በእነዚህ ገበሬዎች ምን ያደርግባቸዋል?

የሚመጣው የወይኑ አትክልት ጌታ ልጁን የላከው እንደሆነ ዐውዱን ተመልከት፦ ማቴዎስ 21፥33-37
በተመሳሳይ ዳዊት፦ “ያህዌህ ግልጥ ሆኖ ይመጣል” በማለት ስለ አብ መምጣት ተናግሯል፦
መዝሙር 50፥2 ከክብሩ ውበት ከጽዮን ያህዌህ ግልጥ ሆኖ “ይመጣል”።

የዳዊትን ንግግር ይዘው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ላይ፦ “ዳዊት፦ “እግዚአብሔር በግልጽ ይመጣል” ብሎ ስለ አብ ተናገረ” በማለት ተናግረዋል፦
መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 10 ቁጥር 6
“ዳዊት እግዚአብሔር ገሀደ ይመጽእ አብ ዘበእንቲአሁ ይቤ በእንተ አብ”።

ትርጉም፦ “ዳዊት፦ “እግዚአብሔር በግልጽ ይመጣል” ብሎ ስለ አብ ተናገረ”።

አብ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ሲፈርድ ኢየሱስ በእርሱ ፊት ለሚያምኑት ይመሰክርላቸዋል ለካዱት ደግሞ ይመሰክርባቸዋል፦
ዳንኤል 7፥9 ዙፋኖችም እስኪዘረጉ ድረስ አየሁ፥ በዘመናት የሸመገለውም ተቀመጠ።
ማቴዎስ 10፥32-33 ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።

የኢየሱስን ንግግር ይዘው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ላይ፦ “የአብ መምጣት ባይኖር ኖሮ፦ “በሰው ፊት ያመነብኝ እኔም በአባቴ ፊት አምነዋለው፥ በሰው ፊት የካደኝ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ” በአላለም ነበር” በማለት ተናግረዋል፦
መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 10 ቁጥር 17
“እመሰ ኢሀሎ ምጽአተ አብ እምኢይቤ ለዘአምነኒ በገጸ ሰብእ አእምኖ በገጸ አቡዬ፥ ወለዘክህደኒ በገጸ ሰብእ እክህዶ በገጸ አቡዬ ዘበሰማያት”

ትርጉም፦ “የአብ መምጣት ባይኖር ኖሮ፦ “በሰው ፊት ያመነብኝ እኔም በአባቴ ፊት አምነዋለው፥ በሰው ፊት የካደኝ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ” በአላለም ነበር”

ስለ አብ ለፍርድ መምጣት በቁና ጥቅስ ማቅረብ ይቻል ነበር፥ ቅሉ ግን አንባቢያንን ማሰልቸት ነው። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ላይ ይህንን ሐቅ ተናግረዋል፦
መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 10 ቁጥር 22
“ወአነሂ እብሎሙ እመሰኬ ቦቱ እምቃለ መጻሕፍት ዘይነግር በእንተ ኢመጺአ አብ”

ትርጉም፦ “እኔም ከመጻሕፍት ቃል ስለ አብ አለመምጣት የሚናገር ካለ በሽንገላ ቃል ስለምን አሰናከለኝ?”
"መልአክ" ማለት "መልእክተኛ" ማለት ነው፥ ጌታ አምላክ መልአኩን ልኮ በመልአኩ፦ "እነሆም በቶሎ እመጣለሁ" ብሎ ሲናገር ራእዩን ያየው እና የሰማው ዮሐንስ ነው፥ ዮሐንስም ላሳማው እና ላሳየው መልአክ ይሰግድ ዘንድ ተደፋ፦
ራእይ 22፥8 ይህንም ያየሁት እና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ። በሰማሁት እና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ።

መልአኩም፦ "እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ" አለው፦
ራእይ 22፥9 እርሱም፦ እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፡ አለኝ።

መልአኩም ለዮሐንስ በመቀጠል እንዲህ አለው፦
ራእይ 22፥10-11 ለእኔም፦ "ዘመኑ ቀርቦአልና የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል በማኅተም አትዝጋው። ዓመፀኛው ወደ ፊት ያምፅ፥ ርኵሱም ወደ ፊት ይርከስ፥ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፥ ቅዱሱም ወደፊት ይቀደስ" "አለ"።

ዮሐንስ ዐውዱ ላይ "አለ" የሚለው መልአኩን ነው፥ በመቀጠል መልአኩ፦ "እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ። አልፋ እና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ" አለ፦
ራእይ 22፥12 እነሆ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ። አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።

"ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ" የሚለው ይሰመርበት! ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋን የሚከፍል አብ ነው፦
1 ጴጥሮስ 1፥17 ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን "አባት" ብላችሁ ብትጠሩ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።
መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 10 ቁጥር 9
"ሐዋርያው፦ "ፊትን ሳያይ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው የሚፈርድ አብን ብትጠሩት" እንዳለው።

ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ ሰው እግዚአብሔር አብ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና፦
ዕብራውያን 11፥6 ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና።

መልአኩ መልእክተኛ ከሆነ መልእክቱ የጌታ አምላክ ነው፥ መልአኩ ለዮሐንስ የሚነግረው የአምላክ ንግግር እና የኢየሱስ ምስክርነት ነው፦
ራእይ 1፥2 እርሱም ስለ የአምላክ ቃል እና የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት ያየውን ሁሉ መሰከረ። ὃς ἐμαρτύρησεν τὸν λόγον τοῦ Θεοῦ καὶ τὴν μαρτυρίαν Ἰησοῦ Χριστοῦ, ὅσα εἶδεν.

የአምላክ ንግግርን ከላይ "እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ አልፋ እና ዖሜጋ እኔ ነኝ" የሚል ንግግር ካየን በኃላ ዐውዱ የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት ይቀጥላል፦
ራእይ 22፥16 እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥር እና ዘር ነኝ፥ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።

ኢየሱስ ከእሴይ ሥር ያቆጠቆጠ የዳዊት ሥር እና ዘር ነው፥ የሚያበራም ብርሃን ነው። "ይህን እንዲመሰክርላችሁ" ይላል፥ የቱን? ስንል ኢየሱስ ከእሴይ ሥር ያቆጠቆጠ የዳዊት ሥር እና ዘር መሆኑን እና የሚያበራም ብርሃን መሆኑን ነው። ኢየሱስ የአንዱ አምላክ ታማኝ ምስክር ነው፦
ራእይ 3፥14 የታመነው እና እውነተኛው ምስክር፥
ራእይ 1፥5 "ከታመነውም ምስክር" ከሙታንም በኵር የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
1 ጢሞቴዎስ 6፥13 በጴንጤናዊውም በጲላጦስ ዘንድ መልካሙን "መታመን በመሰከረ" በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት አዝሃለሁ፤
ዮሐንስ 18፥37 እኔ ለእውነት "ልመሰክር" ስለዚህ ተወልጃለሁ፡ ስለዚህም ወደ ዓለም መጥቻለሁ።

ኢየሱስ የአንዱን አምላክ መልአክ ወደ ራሱ በማስጠጋት "መልአኬ" ስላለ ኢየሱስን አምላክ አያረገውም፥ ምክንያቱም የሰማይ መላእክት ለሚካኤል መላእክት ናቸው፦
ራእይ 22፥7 በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤል እና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። Καὶ ἐγένετο πόλεμος ἐν τῷ οὐρανῷ, ὁ Μιχαὴλ καὶ οἱ ἄγγελοι αὐτοῦ τοῦ πολεμῆσαι μετὰ τοῦ δράκοντος.

"መላእክቱ" የሚለው ቃል "አንጌሎይ አውቱ" ἄγγελοι αὐτοῦ ሲሆን "የእርሱ መላእክት"his angels" ማለት ነው፥ ሚካኤል ፍጡር ሆኖ መልአክ ካለው ኢየሱስ ፍጡር ሆኖ መልአክ ቢኖረው አይደንቅም። ኢንሻሏህ ይቀጥላል.....

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አልፋ እና ዖሜጋ

ክፍል አራት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

57፥3 እርሱ ፊትም ያለ፣ ኋላም ቀሪ፣ ግልጽም፣ ስውርም ነው፡፡ እርሱም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ هُوَ الْأَوَّلُ وَالْآخِرُ وَالظَّاهِرُ وَالْبَاطِنُ ۖ وَهُوَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

ኢየሱስ፦ "እኔ አልፋ እና ዖሜጋ ነኝ፥ ስለዚህ አምልኩኝ" ቢል ኢየሱስ ፍጡር፣ ነቢይ፣ መልእክተኛ እና አምላክን የሚያመልክ ባሪያ መሆኑ ስለተነገረን አንዱ አምላክ በእርሱ በኩል፦ "አልፋ እና ዖሜጋ ነኝ፥ ስለዚህ አምልኩኝ" በማለት እየተናገረ እንደሆነ በቅጡ እንረዳለን ማለት ነው፥ ምክንያቱም አፓካሊፕሲስ አንዱ አምላክ ለኢየሱስ እንዲናገር የሰጠው "ራእይ" ነው፦
ራእይ 1፥1 ቶሎ መሆን የሚገባውን ነገር ለአገልጋዮቹ እንዲያሳይ አምላክ የሰጠው የኢየሱስ ክርስቶስ ራእይ ይህ ነው። Ἀποκάλυψις Ἰησοῦ Χριστοῦ, ἣν ἔδωκεν αὐτῷ ὁ Θεός, δεῖξαι τοῖς δούλοις αὐτοῦ ἃ δεῖ γενέσθαι ἐν τάχει,

"የሰጠው" ስለሚል "ሰጪ" ላኪው አንድ አምላክ፣ "ተሰጪው" ነቢዩ ኢየሱስ፣ "ስጦታው" ደግሞ የሚለው እና የሚናገረው ትእዛዝ ነው፦
ዮሐንስ 12፥49 እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ።

"ከራሴ አልተናገርሁም" ካለ የሚናገረው የራሱን ሳይሆን የላከውን መልእክት ብቻ ነው፥ ስለዚህ ከኢየሱስ የሚሰሙት ራእይ እና ትምህርት አብ ሲናገር ሰምቶ የሚያስተላልፈው መልእክት ነው፦
ዮሐንስ 14፥10 እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም።
ዮሐንስ 12፥50 ስለዚህ እኔ የምናገረውን አብ እንደ ነገረኝ እንዲሁ እናገራለሁ።
ዮሐንስ 14፥24 የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም።
ዮሐንስ 8፥26 ዳሩ ግን የላከኝ እውነተኛ ነው፥ እኔም ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለዓለም እናገራለሁ።
ዮሐንስ 7፥16 ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም።

"ከእኔ አይደለም" "የእኔ አይደለም" የሚል ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! መልእክተኛው የሚናገረው መልእክት የላኪው ከሆነ በወልድ ሲናገር የነበረው አብ ነው፦
ዕብራውያን 1፥2 በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤

አንዱ አምላክ ለኢየሱስ የሰጠው ራእይ በ 286 ድኅረ ልደት በተነሱት የሮም አላውያን ነገሥታት በሆኑት በዲዮቅልጥያኖስ እና በመክስምያኖስ ከጠፋ በኃላ ከ 347 እስከ 407 ይኖር የነበረ ዮሐንስ አፈ ወርቅ "የኢየሱስ ራእይ ድጋሚ ተገለጠልኝ" ብሎ ቅሰጣ እና ቅየጣ ጨምሯል፥ ከራእይ 22፥18 እስከ ራእይ 22፥21 ያለው የራሱ የዮሐንስ አፈ ወርቅ ቅየጣ እና ቅሰጣ ነውና። በዚህ አስተማማኝ ባልሆነ መጽሐፍ ላይ ኢየሱስ፦ "ፊተኛው እና ኃለኛው እኔ ነኝ" እንዳለ ተገልጿል፦
ራእይ 1፥17 እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ! ፊተኛው እና ኃለኛው"። λέγων Μὴ φοβοῦ· ἐγώ εἰμι ὁ πρῶτος καὶ ὁ ἔσχατος
ራእይ 1፥18 ሕያው ነኝ፥ ሞቼም ነበር"። καὶ ὁ Ζῶν, καὶ ἐγενόμην νεκρὸς
ራእይ 2፥8 ሞቶ የነበረው እና ሕያውም የሆነው ፊተኛው እና ኃለኛው። ὁ πρῶτος καὶ ὁ ἔσχατος, ὃς ἐγένετο νεκρὸς καὶ ἔζησεν

ሞቶ ሕያው መሆኑ ይቆየንና መሞቱ እና ከሞት ሕያው መሆኑ በራሱ አልፋ እና ዖሜጋ ከሚለው ቃል ጋር ተቃራኒ ነው፥ ምክንያቱም መሞት ህልውና አልባ መሆን ነው። ባይሆን የሙታን "ፊተኛው" እና መንፈስ በመሆን "ኃለኛው" አዳም ነው። "ፊተኛው" የሚለው የግሪኩ ቃል "ፕሮቶስ" πρῶτος ሲሆን እንደ ባይብሉ እርሱ የሙታን "ፊተኛ" ነው፦
ቆላስይስ 1፥18 እርሱም በሁሉ ፊተኛ ይሆን ዘንድ፥ መጀመሪያ ከሙታንም "በኵር" ነው። ὅς ἐστιν ἀρχή, πρωτότοκος ἐκ τῶν νεκρῶν,

እዚህ አንቀጽ ላይ "በኵር" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ፕሮቶቶኮስ" πρωτότοκος ሲሆን የሁለት ቃላት ውቅር ነው፥ "ፕሮቶስ" πρῶτος እና "ቲክቶ" τίκτω ነው። "ፕሮቶስ" πρῶτος ማለት "ፊተኛ" ማለት ሲሆን "ቲክቶ" τίκτω ማለት ደግሞ "መወለድ" "መምጣት" "መውጣት" ማለት ነው። ከሙታን በመውጣት ፊተኛ ስለሆነ ፊተኛ ነው፦
ዕብራውያን 13፥20 ኢየሱስን ከሙታን "ያወጣው" የሰላም አምላክ።
"ኃለኛው" የሚለው የግሪኩ ቃል "ኤስካቶስ" ἔσχατος ሲሆን እንደ ባይብሉ ኢየሱስ በሥጋ ሞቶ "በመንፈስ ሕያው ሆነ" ይለናል፥ በሕያውነት መንፈስ ሲሆን "ኃለኛው" አዳም ሆነ፦
1 ጴጥሮስ 3፥18 በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ። θανατωθεὶς μὲν σαρκὶ ζωοποιηθεὶς δὲ πνεύματι·
1 ቆሮንቶስ 15፥45 "ኋለኛው" አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ። ὁ ἔσχατος Ἀδὰμ εἰς πνεῦμα ζωοποιοῦν.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ኋለኛው" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ኤስካቶስ" ἔσχατος ሲሆን "ሕያው ሆነ" "መንፈስ ሆነ" ከሚል ጋር ተዛምዶ የመጣ ነው፥ ስለዚህ እርሱ የሙታን ፊተኛ እና ሕያው በመሆን ኃለኛ ነው። ፊተኛ እና ኃለኛ አንጻራዊ እንጂ ፍጹማዊ አይደለም፥ አንድ ናሙና አንድ ጥቅስ እንይ፦
ማቴዎስ 19፥30 ነገር ግን ብዙዎቹ "ፊተኞች" ኋለኞች፥ "ኋለኞች" ፊተኞች ይሆናሉ። Πολλοὶ δὲ ἔσονται πρῶτοι ἔσχατοι καὶ ἔσχατοι πρῶτοι.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ፕሮቶኢ" πρῶτοι የሚለው ቃል "ፕሮቶስ" πρῶτος ለሚለው ቃል ብዜት ሲሆን "ፊተኞች" ማለት ነው፥ "ኤስካቶኢ" ἔσχατοι የሚለው ቃል "ኤስካቶስ" ἔσχατος ለሚለው ቃል ብዜት ሲሆን "ኋለኞች" ማለት ነው። ሰዎች "ፊተኞች" እና "ኋለኞች" ስለተባሉ መነሻ የሌላቸው አልፋ መዳረሻ የሌላቸው ዖሜጋ ማለት ነውን? እረ በፍጹም። በቁርኣንም ቢሆን ዒሣ ከተከታዮቹ ጋር በአንጻራዊ ደረጃ፦ "ለመጀመሪያዎቻችን እና ለመጨረሻዎቻችን" ብሏል፦
5፥114 የመርየም ልጅ ዒሳ አለ፡- «ጌታችን አላህ ሆይ! ለእኛ ለመጀመሪያዎቻችን እና ለመጨረሻዎቻችን ባዕል መደሰቻ የምትኾንን ከአንተም ተአምር የኾነችን ማእድ ከሰማይ በእኛ ላይ አውርድ፡፡ ስጠንም፡፡ አንተ ከሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነህና፡፡» قَالَ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ اللَّهُمَّ رَبَّنَا أَنزِلْ عَلَيْنَا مَائِدَةً مِّنَ السَّمَاءِ تَكُونُ لَنَا عِيدًا لِّأَوَّلِنَا وَآخِرِنَا وَآيَةً مِّنكَ ۖ وَارْزُقْنَا وَأَنتَ خَيْرُ الرَّازِقِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "አወል" لِّأَوَّل እና "አኺር" آخِر በአንጻራዊ ደረጃ የመጣ ሲሆን አምላካችን አሏህ ግን ከፍጥረት በፊት የነበረ መነሻ የሌለው ቀዳማይ እና ከፍጥረት በኃላ የሚኖር መዳረሻ የሌለው ደኃራይ ነው። "አዘል" أَزَل ማለት መጀመሪያ የሌለው"beginningless" ቀዳማይ ማለት ሲሆን "አዘሊይ" أَزَلِيّ ደግሞ ገላጭ ግጽል ነው፥ አሏህ መነሻ የሌለው ቀዳማይ ስለሆለ "አል-አወል" الْأَوَّل ነው። "አበድ" أَبَد ማለት "መጨረሻ የሌለው"endless" ደኃራይ ማለት ሲሆን "አበዲይ" أَبَدِيّ ደግሞ ገላጭ ግጽል ነው፥ አሏህ መዳረሻ የሌለው ደኃራይ ስለሆለ "አል-አኺር" الْآخِر ነው፦
57፥3 እርሱ ፊትም ያለ፣ ኋላም ቀሪ፣ ግልጽም፣ ስውርም ነው፡፡ እርሱም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ هُوَ الْأَوَّلُ وَالْآخِرُ وَالظَّاهِرُ وَالْبَاطِنُ ۖ وَهُوَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 48, ሐዲስ 82
"አሏህ ሆይ! አንተ ቀዳማይ ነህ፥ ከአንተ በፊት ምንም ነገር የለም። አንተ ደኃራይ ነህ፥ ከአንተ በኃላ ምንም ነገር የለም። اللَّهُمَّ أَنْتَ الأَوَّلُ فَلَيْسَ قَبْلَكَ شَىْءٌ وَأَنْتَ الآخِرُ فَلَيْسَ بَعْدَكَ شَىْءٌ

አሏህ ከነገር ውጪ ስለሆነ የእርሱ ቀዳማይነት እና ደኃራነት ዛቲይ ነው፥ "ዛት" ذَات ማለት "ህላዌ" "ኑባሬ" ምንነት" ማለት ሲሆን "ዛቲይ" ذَاتِيّ ማለት ደግሞ "ህላዌአዊ" "ኑባሬአዊ" "ምንነታዊ" ማለት ነው።
ክርስቲያኖች ሆይ! ልደት እና ሞት ያካበበው ፍጡር በማምለክ "አንዴ መነሻ የለውም፥ አንዴ በመፈጠር መነሻ አለው። አንድ መዳረሻ የለውም፥ አንዴ በመሞት መዳረሻ አለው" ከሚል ውዝግብ ወጥታችሁ መነሻ የሌለው ቀዳማይ እና መዳረሻ የሌለው ደኃራይ አንዱን አምላክ አሏህ እንድታመልኩ ጥሪአችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የፈጣሪ እግር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

42፥11 የሚመስለው ምንም "ነገር" የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ

አምላካችን አሏህ ከፍጡራኑ ጋር የማይመሳሰል የራሱ ባሕርያት አሉት፥ እርሱን የሚመስል ምንም ነገር የለም፦
42፥11 የሚመስለው ምንም "ነገር" የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሚስል" مِثْل በሚለው ቃል ላይ መነሻ ቅጥያ ሆኖ የገባው "ከ" كَ የሚል መስተዋድድ "በጭራሽ" ማለት ነው፥ "ነገር" በሚለው ቃል ውስጥ ሁሉም ፍጡራን የሚካተቱ ሲሆኑ ከፍጡራን መካከል እርሱን የሚመስል ብጤ በጭራሽ የለም። እዚሁ አንቀጽ ላይ አሏህ "ሰሚ እና ተመልካች" እንደሆነ ተገልጿል፥ ሰውም "ሰሚ እና ተመልካች" እንደሆነ ተገልጿል፦
76፥2 እኛ ሰውን በሕግ ግዳጅ የምንፈትነው ስንኾን ቅልቅሎች ከኾኑ የፍትወት ጠብታ ፈጠርነው፡፡ ሰሚ ተመልካችም አደረግነው*፡፡ إِنَّا خَلَقْنَا الْإِنسَانَ مِن نُّطْفَةٍ أَمْشَاجٍ نَّبْتَلِيهِ فَجَعَلْنَاهُ سَمِيعًا بَصِيرًا

የአሏህ መስማት እና ማየት ከፍጡራን ጋር እንደማይመሳሰል እና እንደማይነጻጸር ሁሉ የፈጣሪ እግር ከፍጡራን እግር ጋር አይመሳሰለም አይነጻጸርም፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 369
አነሥ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሰዎች ወደ እሳት ይጣላሉ፥ እሳትም አሏህ እግሩን በእርሷ ላይ እስኪያኖር እና በቃኝ በቃኝ እስክትል ድረስ "ጭማሬ አለን? ትላለች። عَنْ أَنَسٍ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ يُلْقَى فِي النَّارِ وَتَقُولُ هَلْ مِنْ مَزِيدٍ‏.‏ حَتَّى يَضَعَ قَدَمَهُ فَتَقُولُ قَطِ قَطِ ‏"‌‏.‏

እዚህ ሐዲስ ላይ አሏህ እግር እንዳለው መጠቀሱ በስላቅ ሚሽነሪዎች፦ "ፈጣሪ እንዴት እግር ይኖረዋል? ብለው ይሳለቃሉ፥ አንዳንዶች የራሳቸውን መጽሐፍ በቅጡ እና በጥሞና ካለማንበብ ሲሆን ሌሎች ደግሞ እያወቁ እሥልምናን በምን እናጠልሸው? የሚል ከንቱ ልፋት ነው። እስቲ ከባይብል ፈጣሪ እግር እንዳለው እንመልከት፦
ኢሳይያስ 66፥1 ያህዌህ እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም "የእግሬ" መረገጫ ናት።
መዝሙር 18፥9 ሰማዮችን ዝቅ ዝቅ አደረገ ወረደም፥ ጨለማ "ከእግሩ" በታች ነበረ።
መዝሙር 99፥5 አምላካችንን ያህዌን ከፍ ከፍ አድርጉት፥ ቅዱስ ነውና ወደ "እግሩ" መረገጫ ስገዱ።
ናሆም 1፥3 ያህዌህ በወጀብና በዐውሎ ነፋስ ውስጥ መንገድ አለው፥ ደመናም "የእግሩ" ትቢያ ነው።

ፈጣሪ፦ "እግሬ" ሲል ነቢያት "እግሩ" ይሉናል፥ ምድር የእግሩ መረገጫ ናት። "ወደ "እግሩ" መረገጫ ስገዱ" ይለናል፥ እግር ብቻ ሳይሆን እግሮች እንዳሉትም ተገልጿል፦
መዝሙር 132፥7 "እግሮቹ" በሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን።

“ዓይን” ጆሮ” እና የቀሩት “እግር” “እጅ” ሲባል ትርጉም መስጠት ክልክል እንደሆነ ሠለስቱ ምዕት ተናግረዋል፥ “ሠለስቱ ምዕት” ማለት በኒቂያ ጉባኤ የተሰበሰቡት “ሦስት መቶ አሥራ ስምንት ሊቃውንት” ናቸው፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 19 ቁጥር 33
“ለእግዚአብሔር ዓይኖች፣ ጆሮዎች እንዳሉት መጽሐፍት የተናገሩት እና የቀሩት እንዳሉት ስለ እግዚአብሔር የተነገረው ሁሉ የታመነ እውነተኛ እንደሆነ እናምናለን፥ ነገር ግን አይመረመርም አይታሰብም”።

“የቀሩት እንዳሉት ስለ እግዚአብሔር የተነገረው ሁሉ” ከተባሉት እጅ እና እግር ይጨምራል፥ ሊቃውንቱ “አይመረመርም አይታሰብም” አሉ እንጂ ትርጉም ሰጥተው አላራቆቱትም። ይህንን አትናቴዎስ እንቅጩን ተናግሯል፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 28 ቁጥር 30
“ለእግዚአብሔር ዓይን፣ ጆሮ፣ እጅ፣ እግር እንዳለው የተነገረው ሁሉ ስለ እግዚአብሔር በከበሩ መጻሕፍት የተጻፈ ሁሉ የታመነ የተረዳ ነው፥ የተናገርነው ሁሉ አለው። ነገር ግን አይመረመርም አይታወቅም”።

ለእግዚአብሔር እጅ፣ ጥፍር፣ እግር እንዳለው አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ምሥጢር ተናግሯል፦
፨መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 1 ቁጥር 62
“እግዚአብሔር እጆች እና ክንድ፣ ጥፍር እንዳለው ዕወቁ”።
፨መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 1 ቁጥር 64
“ስለ እግሮችም የከበረች ኦሪት፦ “የእግዚአብሔር እግሮች በዚህ እና በዚያ የቆሙበትን ዓለት ምታ” እንዳለው ተናገረች”።
፨መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 1 ቁጥር 65
“ዳዊትም፦ “የእግዚአብሔር እግር በቆሙበት ሥፍራ እንሰግዳለን” አለ”።

አሏህ እግሩን በእሳት ላይ ማኖሩ ስትሳለቁ እግዚአብሔር ሲኦል ውስጥም እንደሚኖር ስትሰሙ ምን ይውጣችሁ ይሆን? እግዚአብሔር፦ በጨለማው ውስጥ እኖራለሁ" ብሎአል፦
መዝሙር 139፥8 ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ "በዚያ አለህ"።
1 ነገሥት 8፥12 ሰሎሞንም፦ እግዚአብሔር፦ በጨለማው ውስጥ እኖራለሁ" ብሎአል፤

አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
በእርሱ ተፈጥረዋል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

7፥191 ምንንም የማይፈጥሩትን እና እነርሱም የሚፈጠሩትን በአላህ ላይ ያጋራሉን? أَيُشْرِكُونَ مَا لَا يَخْلُقُ شَيْئًا وَهُمْ يُخْلَقُونَ

ክርስቲያኖች እራሳቸውን የሚያስጠጉበት ጳውሎስ የፈጣሪ ነቢይ ወይም ከአሥራ ሁለቱ የኢየሱስ ሐዋርያት መካከል አይደለም፥ እርሱ ያስተላለፈው ትምህርት እስር ቤት ሆኖ የደረሰው ደብዳቤ እንጂ የፈጣሪ ንግግር ወይም "በል" ተብሎ የተላከው መልእክት አይደለም። "አንገሊያ" ἀγγελία ማለት "መልእክት"message" ማለት ሲሆን "ኢፕስቶሌን" ἐπιστολὴν ማለት ደግሞ "ደብዳቤ"letter" ማለት ነው፥ የጳውሎስ ትምህርት ከራሱ የፈለቀ ደብዳቤ"letter" ነው። እንደዛም ሆኖ ግን ጳውሎስ፦ "ኢየሱስ ፈጣሪ ነው" ብሎ በፍጹም አላስተማረም፥ ክርስቲያኖች "አስተምሯል" ብለው ድምዳሜ ላይ የደረሱበትን ጥቅስ ኢንሻሏህ ጥርስ እና ምላሱን እየነቀስንና እያደማን እንመልከት፦
ቆላስይስ 1፥15 እርሱም የማይታይ አምላክ መልክ እና የፍጥረት ሁሉ በኵር ነው። ὅς ἐστιν εἰκὼν τοῦ Θεοῦ τοῦ ἀοράτου, πρωτότοκος πάσης κτίσεως,

እዚህ ጥቅስ ላይ "የማይታየው አምላክ" ብቻውን አምላክ የሆነ አብን ቁልጭ እና ፍንትው አርጎ አስቀምጦታል፥ ይህ የማይታየው አምላክ ኢየሱስ ሳይሆን ያልሞተ ብቻውን አምላክ የሚሆን እንደሆነ እንቅጩን ፍርጥ አርጎ ነግሮናል፦
1 ጢሞቴዎስ 1፥17 ብቻውን አምላክ ለሚሆን፣ ለማይሞተው፣ ለማይታየውም፣ ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።
1 ጢሞቴዎስ 6፥16 እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን።

ይህ ብቻውን አምላክ የሆነ፣ የማይታይ እና የማይሞት ማንነት ከኢየሱስ ተነጥሎ ተቀምጧል፥ ኢየሱስ የዚያ የማይሞት፣ የማይታይ፣ የብቸኛ አምላክ መልክ ነው፥ "ኢኮን" εἰκὼν ማለት "መልክ" ማለት ሲሆን ኢየሱስ ብቻ ሳይሆን ወንድ እራሱ የአምላክ መልክ ነው፦
1ኛ ቆሮንቶስ 11፥7 ወንድ የአምላክ መልክ እና ክብር ስለ ሆነ ራሱን መከናነብ አይገባውም። εἰκὼν καὶ δόξα Θεοῦ ὑπάρχων· ἡ γυνὴ δὲ δόξα ἀνδρός ἐστιν.

ወንድ የአምላክ መልክ ሆኖ እንደተፈጠረ ሁሉ ኢየሱስም የአምላክ መልክ ሆኖ ተፈጥሯል፦
ቆላስይስ 3፥10 የፈጠረውንም "መልክ" እንዲመስል እውቀትን ለማግኘት የሚታደሰውን አዲሱን ሰው ለብሳችሁታል። καὶ ἐνδυσάμενοι τὸν νέον τὸν ἀνακαινούμενον εἰς ἐπίγνωσιν κατ’ εἰκόνα τοῦ κτίσαντος αὐτόν,

"the image of him that created him" የሚለው ይሰመርበት! ዕውቀትን ለማግኘት የሚታደሰውን አዲሱን ሰው የሚመስለው "የፈጠረውንም መልክ" ኢየሱስን ነው፥ አዲሱ ሰው የተፈጠረው እንደ ኢየሱስ ነው፦
ኤፌሶን 4፥24 ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ። καὶ ἐνδύσασθαι τὸν καινὸν ἄνθρωπον τὸν κατὰ Θεὸν κτισθέντα ἐν δικαιοσύνῃ καὶ ὁσιότητι τῆς ἀληθείας.

ኢየሱስ የፍጥረት ሁሉ በኵር ነው፥ "ፓንታ" πάντα ወይም "ፓስ" πᾶς ማለት "ሁሉ" ማለት ሲሆን "ሁሉ" የሚለው ገላጭ ቅጽል አንጻራዊ ንግግር ነው፥ "በኵር" ማለት "መጀመሪያ" ማለት ሲሆን ኢየሱስ መጀመሪያነቱ ዘፍጥረት ላይ ላለው ፍጥረት ሳይሆን የአዲስ ፍጥረት ሁሉ መጀመሪያ ነው። የዘፍጥረት ፍጥረት መጀመሪያ እኮ ሰማይ እና ምድር ነው፦
ዘፍጥረት 1፥1 በመጀመሪያ ኤሎሂም ሰማይንና ምድርን ፈጠረ። בְּרֵאשִׁ֖ית בָּרָ֣א אֱלֹהִ֑ים אֵ֥ת הַשָּׁמַ֖יִם וְאֵ֥ת הָאָֽרֶץ

እዚህ አንቀጽ ላይ "መጀመሪያ" ለሚለው የገባው ቃል "ረሺት" רֵאשִׁית ሲሆን ቤሕሞት "የአምላክ ፍጥረት መጀመሪያ" ለተባለበት የገባውም ቃል በተመሳሳይ "ረሺት" רֵאשִׁית ነው፥ ቤሕሞት "የአምላክ ፍጥረት መጀመሪያ" በተባለበት ሒሣብ ኢየሱስም "የአምላክ ፍጥረት መጀመሪያ" ተብሏል፦
ኢዮብ 40፥19 እርሱ የአምላክ ፍጥረት መጀመሪያ ነው። ה֖וּא רֵאשִׁ֣ית דַּרְכֵי־אֵ֑ל
τοῦτ᾿ ἔστιν ἀρχὴ πλάσματος Κυρίου,
ራእይ 3፥14 "የአምላክ ፍጥረት መጀመሪያ" ἡ ἀρχὴ τῆς κτίσεως τοῦ θεοῦ, የነበረው

ግሪክ ሰፕቱአጀንት ላይ ቤሕሞት "መጀመሪያ" የተባለበት እና ራእይ ላይ ኢየሱስ "መጀመርያ" የተባለት "አርኬ" ἀρχὴ መሆኑን ልብ አርግ! ስለዚህ ቤሕሞት የአራዊት መጀመሪያ እንጂ የዘፍጥረት ፍጥረት መጀመሪያ እንዳልሆነ ሁሉ ኢየሱስም የአዲስ ፍጥረት ሁሉ መጀመሪያ እንጂ የዘፍጥረት ፍጥረት መጀመሪያ አይደለም። ቅሉን ግን በአዲስ ፍጥረት ውስጥ ዙፋናት፣ ጌትነት፣ አለቅነት፣ ሥልጣናት "በ"-ክርስቶስ ተፈጥረዋል፦
ቆላስይስ 1፥16 የሚታዩት እና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት።

1. ዙፋናት የአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አገልግሎት ነው፦ ማቴዎስ 19፥28 ራእይ 20፥4
2. ጌትነት የጉባኤ ሽማግሌዎች አገልግሎት ነው፦ 2 ጴጥሮስ 2፥9 ይሁዳ 1፥8 1 ጴጥሮስ 5፥5 ዕብራውያን 13፥7 13፥17
3. አለቅነት የኤጲስ ቆጶሳት አገልግሎት ነው፦ ቆላስይስ 2፥15 ሉቃስ 12፥11 ኤፌሶን 3፥10
4. ሥልጣናት የአስተማሪዎች አገልግሎት ነው፦ 2 ጴጥሮስ 2፥10 ይሁዳ 1፥8

የቤተ ክርስቲያን ራስ ማለት የዙፋናት፣ የጌትነት፣ የአለቅነት፣ የሥልጣናት ራስ ማለት ነው፦
ቆላስይስ 1፥18 እርሱም የአካሉ ማለት የቤተ ክርስቲያን "ራስ" ነው።
ቆላስይስ 2፥10 ለአለቅነት እና ለሥልጣንም ሁሉ "ራስ" በሆነ በእርሱ ሆናችሁ ተሞልታችኋል።

የሚታዩት በምድር ያሉት እና የማይታዩት በሰማይ ያሉት የተባሉት አዲስ ፍጥረት ናቸው፥ "በሰማይ እና በምድር ያሉት ሁሉ" የሚለው ይሰመርበት! እስቲ፦
ቆላስይስ 1፥16 በሰማይ እና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ነው። ὅτι ἐν αὐτῷ ἐκτίσθη τὰ πάντα ἐν τοῖς οὐρανοῖς καὶ ἐπὶ τῆς γῆς,

ልብ አርጋችሁ ከሆነ የሚለው "ሰማይ እና ምድር" ሳይሆን "በሰማይ እና በምድር ያሉት" ነው፥ "በሰማይ እና በምድር ያሉት ሁሉ" የተባሉት እዛው ዐውደ ንባቡ ላይ በክርስቶስ ከእግዚአብሔር ጋር የታረቁትን የሚያመለክት እንደሆነ አስረግጦ እና ረግጦ አስቀምጦታል፦
ቆላስይስ 1፥20 "በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ" ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና።

"በምድር ያሉት ሁሉ" ሲባል እንስሳት፣ እጽዋት፣ ማዕድናት በአዳም ከእግዚአብሔር ጋር ተጣልተው በክርስቶስ ታርቀዋልን? "በሰማያት ያሉት ሁሉ" ሲባል መላእክት፣ ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት በአዳም ከእግዚአብሔር ጋር ተጣልተው በክርስቶስ ታርቀዋልን? በሰማያት ያሉት በሚበልጥ መሥዋዕት እንደነጹ ይናገራል፦
ዕብራውያን 9፥23 "በሰማያት ያሉቱ" ራሳቸው ከእርሱ ይልቅ በሚበልጥ መሥዋዕት ሊነጹ የግድ ነበረ።
መቼም "በሚበልጥ መሥዋዕት የነጹት መላእክት፣ ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት ናቸው" የሚል ቂል ያለ አይመስለኝም። ስለዚህ በሰማይ እና በምድር ያሉት "ሁሉ" የሚለው አጻራዊ ንግግር እንጂ ፍጹማዊ ንግግር አይደለም፥ በሰማያት የተጻፉት የበኵራት ማኅበር እና በምድር ያሉት አማኞች በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት ሆነዋል እንጂ ስለ ዘፍጥረት ፍጥረት በፍጹም አያወራም፦
ዕብራውያን 12፥23 በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር።
2 ቆሮንቶስ 5፥17 ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ "ሁሉም" አዲስ ሆኖአል። ὥστε εἴ τις ἐν Χριστῷ, καινὴ κτίσις· τὰ ἀρχαῖα παρῆλθεν, ἰδοὺ γέγονεν καινά.

አጠቃላይ ሥነ-ፍጥረት አዲስ ሆኗልን? እረ በፍጹም። ስለዚህ "ሁሉ" አንጻራዊ እንጂ ፍጹማዊ ስላልሆነ "ሁሉ አዲስ ሆኖአል" የተባለው አማኞችን ብቻ የሚመለከት ከሆነ "አዲስ ፍጥረት" የተባሉት አማንያን ብቻ ናቸው፦
ገላትያ 6፥15 በክርስቶስ ኢየሱስ "አዲስ ፍጥረት" መሆን ይጠቅማል እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና።
ኤፌሶን 2፥10 እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።

እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ የተፈጠሩት በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት እንጂ መላው ፍጥረት እግዚአብሔር አስቀድሞ ባዘጋጀውን ውስጥ አይካተቱም። ደግሞም "በ-"እርሱ ተፈጥረዋል" ማለት ክርስቶስን ፈጣሪ አያደርገውም፦
ቆላስይስ 1፥16 "በ-"እርሱ ተፈጥረዋልና ὅτι ἐν αὐτῷ ἐκτίσθη

"በ" ለሚለው የገባው መስተዋድድ "ኤን" ἐν ሲሆን መሣሪያ"instrument" እንጂ እራሱ የድርጊቱ ፈጻሚ አይደለም፥ ለምሳሌ፦ ነገርን ሀሉ "በ" ጊዜ ውብ አድርጌ ሠራው" ይላል፦
መክብብ 3፥11 ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው። σύμπαντα, ἃ ἐποίησε, καλὰ ἐν καιρῷ αὐτοῦ,

"ጊዜ" ፍጡር ነው፥ "ነገርን ሁሉ" "በ"-ጊዜ ሠራው ማለት "ጊዜ" ፈጣሪ ነውን? "እርሱ" በሚለው መነሻ ላይ "ኤን" ἐν መስተዋድድ የሚል ስላለ "ኢየሱስ" ፈጣሪ ከሆነ "ጊዜ" በሚለው መነሻ ላይ "ኤን" ἐν የሚል መስተዋድድ ስላለ "ጊዜ" ፈጣሪ ነውን? ወንድ እኮ የተፈጠረው በሴት ነው፦
1 ቆሮንቶስ 11፥12 ሴት ከወንድ እንደ ሆነች እንዲሁ ወንድ ደግሞ "በ"-ሴት ነውና። ὥσπερ γὰρ ἡ γυνὴ ἐκ τοῦ ἀνδρός, οὕτως καὶ ὁ ἀνὴρ διὰ τῆς γυναικός·

እዚህ ጥቅስ ላይ "ሴት" በሚለው ቃል ላይ ለገባው "በ" ለሚለው መስተዋድድ የገባው "ዲያ" διὰ ሲሆን ወንድ በሴት በኩል መሆኑን እንጂ ሴት ፈጣሪ መሆኗን እንደማያሳይ ሁሉ "በ-"እርሱ ተፈጥረዋል ማለት እርሱ ፈጣሪ ነው ማለት አይደለም፦
ቆላስይስ 1፥16 ሁሉ በእርሱ እና "ለ"እርሱ ተፈጥሮአል። all things have been created through him and for him.(NIV)

"ለ-እርሱ"for him" የሚለው አዲስ ፍጥረት "ለ"-ኢየሱስ መፈጠሩን ያሳያል፥ "ለ"for" የሚለው መስተዋድድ ፍጡር ለፍጡር ይገባል። ለምሳሌ ሴት "ለ"-ወንድ ተፈጠረች፥ ሰንበት "ለ"ሰው ተፈጥሮአል፦
1 ቆሮንቶስ 11፥9 ሴት "ለ"-ወንድ ተፈጠረች እንጂ ወንድ "ለ"-ሴት አልተፈጠረምና። neither was man created "for" woman, but woman "for" man.(NIV)
ማርቆስ 2፥27 ደግሞ አላቸው፦ ሰንበት "ለ"ሰው ተፈጥሮአል እንጂ ሰው "ለ"-ሰንበት አልተፈጠረም። Then he said to them, “The Sabbath was made "for" man, not man for the Sabbath.(NIV)

ሴት ለወንድ ተፈጠረች ማለት ሴት አምላኪ ወንድ ተመላኪ ማለት ነውን? ሰንበት ለሰው ተፈጥሮአል ማለት ሰንበት አምላኪ ሰው ተመላኪ ማለት ነውን? ይህ ሙግት አያዋጣችሁም። "ተፈጥረዋል" የሚለው የግሪኩ ቃል "ኤክቲስቴ" ἐκτίσθη ሲሆን እድሳትን ወይም ከመንፈዊ ጨለማ ወደ መንፈሳዊ ብርሃን በመምጣት የሚገኝ ለውጥ"transformation" የሚያሳይ ነው፦
መዝሙር 51፥10 አቤቱ ንጹሕ ልብን "ፍጠርልኝ"፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ "አድስ"።

"ፍጠርልኝ" ሲል "አድስልኝ" ለማለት እንደሆነ ከተረዳን ዘንዳ "ተፈጥረዋል" ሲል "ታድሰዋል" ማለቱ ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 3፥21 "ነገር ሁሉ እስከሚታደስበት ዘመን" ድረስ ሰማይ ይቀበለው ዘንድ ይገባልና።

"ነገር ሁሉ" ታድሷል እንዴ? አይ አማንያን መታደሳቸውን የሚያሳይ ነው። እሩቅ ሳንሄድ "አዲስ ፍጥረት" የሚለው ቃል "አዲስ ልደት" በሚል እኮ መጥቷል፦
ቲቶ 3፥5 እንደ ምሕረቱ መጠን "ለአዲስ ልደት" በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን።

"አዲስ" በሚል ገላጽ ቅጽል ተስታኮ የመጣውን "ልደት" የሚለውን ቃል ከእናት እና አባት ውልደትን እንደማያመለክት ሁሉ "አዲስ" በሚል ገላጽ ቅጽል ተስታኮ የመጣውን "ፍጥረት" የሚለውን ቃል ሥነ-ፍጥረትን አያመለክትም። ሰማይ እና ምድርን ብቻውን የፈጠረ አንድ ማንነት ነው፥ ይህ አንድ ማንነት "እኔ" በሚል ነጠላ ተውላጠ ስም በመጠቀም አንድ ማንነት ብቻውን እንደፈጠረ ይናገራል፦
ኢሳይያስ 44፥24 ከማኅፀን የሠራህ፥ የሚቤዥህ ያህዌህ እንዲህ ይላል፦ ሁሉን የፈጠርሁ፥ ሰማያትን ለብቻዬ የዘረጋሁ ምድርንም ያጸናሁ ያህዌህ እኔ ነኝ፤ ከእኔ ጋር ማን ነበረ?

"እኔ" ለአንድ ማንነት"person" የምንጠቀምበት እንጂ "እኔ" ተብሎ ሁለት እና ከአንድ በላይ ማንነቶች አይባልም። "ማን ነበረ" ለሚለው ጥያቄ "ማንም" ከሆነ "ማን" የሚለውን "ማንነትን" ያሳያል፥ ከአንዱ እኔነት ጋር አብሮ የፈጠረ ማንነት ማንም የለም። ክርስቲያኖች ሆይ! የማይፈጥርን ይልቁንስ የሚፈጠርን አካል በአሏህ ላይ አታጋሩ! የጳውሎስ ደብዳቤ አሏህ ማስረጃን ያላወረደበት የራሱ የጳውሎስ ንግግር ነው፦
7፥191 ምንንም የማይፈጥሩትንና እነርሱም የሚፈጠሩትን በአላህ ላይ ያጋራሉን? أَيُشْرِكُونَ مَا لَا يَخْلُقُ شَيْئًا وَهُمْ يُخْلَقُونَ
22፥7 ከአላህ ሌላም በእርሱ ማስረጃን ያላወረደበትን ለእነርሱም በእርሱ ዕውቀት የሌላቸውን ነገር ያመልካሉ፡፡ ለባዳዮችም ምንም ረዳት የላቸውም፡፡ وَيَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ مَا لَمْ يُنَزِّلْ بِهِ سُلْطَانًا وَمَا لَيْسَ لَهُم بِهِ عِلْمٌ ۗ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِن نَّصِيرٍ
3፥151 በእነዚያ በካዱት ሰዎች ልቦች ውስጥ አላህ በእርሱ ማስረጃን ያላወረደበትን ነገር በአላህ ላይ በማጋራታቸው ምክንያት ፍርሃትን እንጥላለን፡፡ መኖሪያቸውም እሳት ናት፡፡ የበዳዮችም መኖሪያ ምን ትከፋ! سَنُلْقِي فِي قُلُوبِ الَّذِينَ كَفَرُوا الرُّعْبَ بِمَا أَشْرَكُوا بِاللَّهِ مَا لَمْ يُنَزِّلْ بِهِ سُلْطَانًا ۖ وَمَأْوَاهُمُ النَّارُ ۚ وَبِئْسَ مَثْوَى الظَّالِمِينَ

ሕዝበ ክርስትናው በውስጡ ሰላም የሌለው እና ፍርሃት ያለው አሏህ በእርሱ አስረጅ ያላወረደበትን ነገር በአሏህ ላይ በማጋራታቸው ምክንያት ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም