ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.1K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
መጅኑን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

89፥22 *"ነቢያችሁም በፍጹም ዕብድ አይደለም"*፡፡ وَمَا صَاحِبُكُم بِمَجْنُونٍ

"ጁኑን" جُنُون የሚለው ቃል "ጁነ" جُنَّ‎ ማለትም "ዐበደ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ዕብደት" ማለት ነው፥ ዕብደት ያለበት ዕብድ ደግሞ "መጅኑን" مَجْنُون‎ ይባላል። "መጅኑን" مَجْنُون‎ በቋንቋ ደረጃ "ጀነ" جَنَّ‎ ማለትም "ሰወረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን ዐቅሉ "የተሰወረ" "የተደበቀ" ማለት ነው፥ እሩቅ ሳንሄድ ማኅፀን ውስጥ ያለውን “ሽል” ለዓይናችን የተደበቀ ስለሆነ “አጂናህ” أَجِنَّة ማለትም “ስውር” ወይም “ድብቅ” ተብሏል፦
53፥32 *ከምድር በፈጠራችሁ ጊዜ እናንተም በእናቶቻችሁ ማኅፀኖች ውስጥ “ሽሎች” በኾናችሁ ጊዜ እርሱ በእናንተ ሁኔታ ዐዋቂ ነው*፡፡ هُوَ أَعْلَمُ بِكُمْ إِذْ أَنشَأَكُم مِّنَ الْأَرْضِ وَإِذْ أَنتُمْ أَجِنَّةٌ فِي بُطُونِ أُمَّهَاتِكُمْ ۖ فَلَا تُزَكُّوا أَنفُسَكُمْ

እዚህ ድረስ ከተግባባን አንድ የአሏህ መልእክተኛ ሲመጣ የመጣበት ማኅበረሰብ፦ "መጅኑን" ነው" ይሉታል፦
51፥52 ነገሩ እንደዚሁ ነው፡፡ *እነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ከመልክተኛ ማንም አልመጣቸውም፥ እርሱን «ድግምተኛ ወይም ዕብድ ነው» ያሉ ቢኾኑ እንጂ*፡፡ كَذَٰلِكَ مَا أَتَى الَّذِينَ مِن قَبْلِهِم مِّن رَّسُولٍ إِلَّا قَالُوا سَاحِرٌ أَوْ مَجْنُونٌ

አምላካችን አላህ ከተረከን የሩቅ ነገር ወሬ አንዱ ኑሕ፣ ሙሣ ወዘተ በማኅበረሰቡ "ዕብድ" መባላቸውን ነው፦
54፥9 *ከእነርሱ በፊት የኑሕ ነገድ አስተባበለች፥ ባሪያችን ኑሕንም አስተባበሉ፡፡ «ዕብድ ነውም» አሉ*፡፡ ተገላመጠም፡፡ كَذَّبَتْ قَبْلَهُمْ قَوْمُ نُوحٍ فَكَذَّبُوا عَبْدَنَا وَقَالُوا مَجْنُونٌ وَازْدُجِرَ
26፥27 *ፈርዖንም፦ «ያ ወደ እናንተ የተላከው መልክተኛችሁ በእርግጥ ዕብድ ነው» አለ*፡፡ قَالَ إِنَّ رَسُولَكُمُ الَّذِي أُرْسِلَ إِلَيْكُمْ لَمَجْنُونٌ

ነቢያችን”ﷺ” ሲመጡ በዛ ጊዜ የነበሩት ሕዝቦች፦ "ዕብድ" ብሏቸዋል፥ አምላካችን አላህም፦ "ነቢያችሁም በፍጹም ዕብድ አይደለም" በማለት እና ለራቸውም በሁለተኛ መደብ፦ "አንተ በጌታህ ጸጋ የተጎናጸፍክ ስትኾን ዕብድ አይደለህም" ብሎ መልሶ ሰጥቷል፦
15፥6 «አንተ ያ በእርሱ ላይ ቁርኣን የተወረደለት ሆይ! አንተ በእርግጥ ዕብድ ነህ» አሉም፡፡ وَقَالُوا يَا أَيُّهَا الَّذِي نُزِّلَ عَلَيْهِ الذِّكْرُ إِنَّكَ لَمَجْنُونٌ
89፥22 *"ነቢያችሁም በፍጹም ዕብድ አይደለም"*፡፡ وَمَا صَاحِبُكُم بِمَجْنُونٍ
68፥2 *"አንተ በጌታህ ጸጋ የተጎናጸፍክ ስትኾን ዕብድ አይደለህም"*፡፡ مَا أَنتَ بِنِعْمَةِ رَبِّكَ بِمَجْنُونٍ

አንድ ሕዝብ አንድን ነቢይ "መጅኑን" ነው" ስላለ ያ ነቢይ መጅኑን የሚሆን ከሆነ እንግዲያውስ መጅኑን መሆን የነበረበት ኢየሱስ ነበር፥ ምክንያቱም ዘመዶቹም ሰምተው፦ "አበደ" ብለዋልና ሊይዙት ወደነበረበት ተራራ ወጡ፦
ማርቆስ 3፥21 *"ዘመዶቹም ሰምተው፦ "አበደ" ብለዋልና ሊይዙት ወጡ"*። وَلَمّا سَمِعَتْ عائِلَةُ يَسُوعَ عَنْ مَجيئِهِ، جاءُوا لِيَأخُذُوهُ مَعَهُمْ، لِأنَّ النّاسَ كانُوا يَقُولُونَ إنَّهُ مَجنُونٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ "አበደ" ለሚለው የገባው ቃል "መጅኑን" مَجنُون መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ዘመዶቹ "አበደ" ብለው ሊይዙት ስለ ወጡ ኢየሱስ አብዶ ነበር እንዴ? አይ "አንድ ሕዝብ አንድን ነቢይ "መጅኑን" ነው" ስላለ ያ ነቢይ መጅኑን ነው ማለት አይደለም" ካላችሁን እንግዲያውስ በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርምና ነቢያችን”ﷺ” ሲመጡ በዛ ጊዜ የነበሩት ሕዝቦች፦ "ዕብድ" ስላላቸው እርሳቸው ዕብድ ነበሩ አይሰኝም ማለት ነው። የነቢያችንን”ﷺ” ነቢይነት ለማስተባበል ያመጣችሁት መስፈርት ስሑት ሙግት ስለሆነ ፉርሽ ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አሥራ ሁለቱ ነገዶች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥20 ሙሳም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፦ *«ሕዝቦቼ ሆይ የአላህን ጸጋ *በውስጣችሁ ነቢያትን ባደረገ* እና መንግሥትም ባደረጋችሁ ከዓለማትም ለአንድም ያልሰጠውን ችሮታ በሰጣችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ ያደረገውን ጸጋ አስታውሱ፡፡»* وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِ يَا قَوْمِ اذْكُرُوا نِعْمَةَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ جَعَلَ فِيكُمْ أَنبِيَاءَ وَجَعَلَكُم مُّلُوكًا وَآتَاكُم مَّا لَمْ يُؤْتِ أَحَدًا مِّنَ الْعَالَمِينَ

“ነቢይ” نبي የሚለው ቃል “ነበአ” نَبَّأَ ማለትም “አወራ” ወይም “ተናገረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን “አውሪ” ወይም “ነጋሪ” ማለት ነው፤ ይህንን እስቲ ከቁርአን እንመልከት፦
66፡3 ነቢዩ ከሚስቶቹ ወደ አንዷ ወሬን በመሠጠረ ጊዜ አስታውስ እርሱንም በነገረችና አላህ እርሱን ማውራትዋን ባሳወቀው ጊዜ ከፊሉን አስታወቀ ከፊሉንም ተወ፤ በእርሱም ባወራት ጊዜ *ይህን ማን “ነገረህ”? አለች፤ ዐዋቂው ውስጠ አዋቂው “ነገረኝ” አላት*። وَإِذْ أَسَرَّ النَّبِيُّ إِلَى بَعْضِ أَزْوَاجِهِ حَدِيثًا فَلَمَّا نَبَّأَتْ بِهِ وَأَظْهَرَهُ اللَّهُ عَلَيْهِ عَرَّفَ بَعْضَهُ وَأَعْرَضَ عَنْ بَعْضٍ فَلَمَّا نَبَّأَهَا بِهِ قَالَتْ مَنْ أَنْبَأَكَ هَذَا قَالَ نَبَّأَنِيَ الْعَلِيمُ الْخَبِيرُ ፤

በዚህ አንቀጽ ውስጥ “ማን ነገረህ” ለሚለው ቃል የገባው “መን አንበአከ” مَنْ أَنْبَأَكَْ ሲሆን “ነገረኝ” ለሚለው ደግሞ “ነበአኒየ” نَبَّأَنِيَ ነው፤ የሁለቱም ግስ ርቢ “ነበአ” نَبَّأَ የሚለው ቃል ነው፤ ስለዚህ ነቢይ ማለት ሁሉን ዐዋቂውና ውስጠ ዐዋቂው አላህ የሚያናግረው እና የሚነግረው ማለት ነው፤ በዚህ ስሌት አሥራ ሁለቱ ነገዶች በሙሳ ዘመን በኢስራኢል ልጆች የተነሱ ነቢያት ናቸው፦
5፥20 ሙሳም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፦ *«ሕዝቦቼ ሆይ የአላህን ጸጋ *በውስጣችሁ ነቢያትን ባደረገ* እና መንግሥትም ባደረጋችሁ ከዓለማትም ለአንድም ያልሰጠውን ችሮታ በሰጣችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ ያደረገውን ጸጋ አስታውሱ፡፡»* وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِ يَا قَوْمِ اذْكُرُوا نِعْمَةَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ جَعَلَ فِيكُمْ أَنبِيَاءَ وَجَعَلَكُم مُّلُوكًا وَآتَاكُم مَّا لَمْ يُؤْتِ أَحَدًا مِّنَ الْعَالَمِينَ

“በውስጣችሁ ነቢያትን ባደረገ ጊዜ” የሚለው ይሰመርበት፤ እነዚህ ነብያት ነገዶቹ ናቸው፤ አላህ ወደ ነገዶቹ ወሕይ አውርዷል፦
4፥163 እኛ ወደ ኑሕና ከርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት እንዳወረድን ወደ አንተም አወረድን፡፡ ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልም፣ ወደ ኢስሓቅም፣ ወደ ያዕቆብም፣ *ወደ ነገዶቹም፣ ወደ ዒሳም፣ ወደ አዩብም፣ ወደ ዩኑስም፣ ወደ ሃሩንና፣ ወደ ሱለይማንም አወረድን*፡፡ ለዳውድም ዘቡርን ሰጠነው፡፡ إِنَّا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ كَمَا أَوْحَيْنَا إِلَىٰ نُوحٍ وَالنَّبِيِّينَ مِن بَعْدِهِ ۚ وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَعِيسَىٰ وَأَيُّوبَ وَيُونُسَ وَهَارُونَ وَسُلَيْمَانَ ۚ وَآتَيْنَا دَاوُودَ زَبُورًا
3፥84 «በአላህ አመንን፡፡ በእኛ ላይ በተወረደውም፣ በኢብራሂምና በኢስማዒልም፣ በኢስሓቅም፣ በያዕቆብም፣ *በነገዶችም ላይ በተወረደው*፤ ለሙሳና ለዒሳም ለነቢያትም ሁሉ ከጌታቸው በተሰጠው አመንን፡፡ ከእነርሱ መካከል አንድንም አንለይም፡፡ እኛ ለእርሱ ታዛዦች ነን» በል፡፡ قُلْ آمَنَّا بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ عَلَيْنَا وَمَا أُنزِلَ عَلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَمَا أُوتِيَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَالنَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمْ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّنْهُمْ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ
2፥136 «በአላህና ወደኛ በተወረደው፣ ወደ ኢብራሂምም ወደ ኢስማዒልና ወደ ኢስሐቅም ወደ ያዕቁብ እና *ወደ ነገዶቹም በተወረደው* በዚያም ሙሳና ዒሳ በተሰጡት በዚያም ነቢያት ሁሉ ከጌታቸው በተሰጡት ከነርሱ በአንድም መካከል የማንለይ ስንኾን አመንን፤ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን» በሉ፡፡ قُولُوا آمَنَّا بِاللَّهِ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْنَا وَمَا أُنزِلَ إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَمَا أُوتِيَ مُوسَىٰ وَعِيسَىٰ وَمَا أُوتِيَ النَّبِيُّونَ مِن رَّبِّهِمْ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِّنْهُمْ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ
አላህ ወሕይ የሚወርድላቸውን እነዚህን ነገዶች አሥራ ሁለት አለቆች አድርጎ አስነሳቸው፤ ለአሥራ ሁለትም ሕዝቦች ከፋፈላቸው፦
5፥12 *አላህም የእስራኤልን ልጆች የጠበቀ ቃል ኪዳን በእርግጥ ያዘባቸው፡፡ ከእነርሱም አሥራ ሁለትን አለቆች አስነሳን*፡፡ وَلَقَدْ أَخَذَ اللَّهُ مِيثَاقَ بَنِي إِسْرَائِيلَ وَبَعَثْنَا مِنْهُمُ اثْنَيْ عَشَرَ نَقِيبًا
7፥160 *አሥራ ሁለት ነገዶች ሕዝቦች አድርገንም ከፋፈልናቸው*፡፡ ወደ ሙሳም ወገኖቹ መጠጣትን በፈለጉበት ጊዜ «ድንጋዩን በበትርህ ምታው» ስንል ላክን፡፡ መታውም *ከእርሱ አሥራ ሁለት ምንጮችም ፈለቁ*፡፡ وَقَطَّعْنَاهُمُ اثْنَتَيْ عَشْرَةَ أَسْبَاطًا أُمَمًا ۚ وَأَوْحَيْنَا إِلَىٰ مُوسَىٰ إِذِ اسْتَسْقَاهُ قَوْمُهُ أَنِ اضْرِب بِّعَصَاكَ الْحَجَرَ ۖ فَانبَجَسَتْ مِنْهُ اثْنَتَا عَشْرَةَ عَيْنًا

ጥንት የአሥራ ሁለቱ አበው የቃልኪዳን መጽሐፍ የነበረ ሲሆን አይሁዳውን በ 90 ድህረ-ልደት”AD” በጀሚኒያ ጉባኤ ውሳኔ የአፓክራፋ መጽሐፍ ብለው ቀንሰውታል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አምላካችን አላህ የመጽሐፉ ባለቤቶች ከመጽሐፉ ይሸሽጉት ከነበሩት ብዙውን የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛውን በእርግጥ ልኳል፦
5፥15 *የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን በእርግጥ መጣላችሁ*፡፡ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ قَدْ جَاءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًا مِّمَّا كُنتُمْ تُخْفُونَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَعْفُو عَن كَثِيرٍ

“አፓክራፋ” የሚለው ቃል “አፓክራፈስ” ἀπόκρυφος ከሚለው ግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን “ድብቅ” ማለት ነው፤ ከደበቁት መጽሐፍት ውስጥ ካሉት መለኮታዊ ቅሪት አስፈላጊውን አላህ የገለጸ ሲሆን ከደበቁት መጽሐፍት ውስጥ ካሉት መለኮታዊ ቅሪት ብዙውን ትቶታል፤ ወደ ነብያት ምን ተወርዶ እንደነበረ መልእክተኛው እንዲገልጹ ቁርኣንን አውርዷል፦
16፥44 በግልጽ ማስረጃዎችና በመጻሕፍት ላክናቸው፡፡ *ወደ አንተም ለሰዎች ወደ እነርሱ የተወረደውን ልትገልጽላቸው እና ያስተነትኑም ዘንድ ቁርኣንን አወረድን*፡፡ بِالْبَيِّنَاتِ وَالزُّبُرِ ۗ وَأَنزَلْنَا إِلَيْكَ الذِّكْرَ لِتُبَيِّنَ لِلنَّاسِ مَا نُزِّلَ إِلَيْهِمْ وَلَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُونَ

ይህ ቁርኣን ከበፊቱ ከአላህ የተወረዱትን የአላህ ንግግሮች የሚያረጋግጥ እና በእነዚያ ንግግሮች ውስጥ ያለውን ጭብጥ የሚዘረዝር ነው፦
10፥37 ይህም ቁርኣን ከአላህ ሌላ ከሆነ ፍጡር የተቀጠፈ ሊሆን አይገባውም፤ *ግን ያንን ከእርሱ በፊት ያለውን የሚያረጋግጥ እና በመጽሐፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው*፡፡ وَمَا كَانَ هَـٰذَا الْقُرْآنُ أَن يُفْتَرَىٰ مِن دُونِ اللَّهِ وَلَـٰكِن تَصْدِيقَ الَّذِي بَيْنَ يَدَيْهِ وَتَفْصِيلَ الْكِتَابِ لَا رَيْبَ فِيهِ مِن رَّبِّ الْعَالَمِينَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የእግዚአብሔር ባሕርያት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

እግዚአብሔር ክፉን መንፈስን፣ የስሕተትን አሠራር፣ ጨለማን እና ክሳትን እንደሚልክ ባይብል ይናገራል፦
2ኛ ተሰሎንቄ 2፥12 ስለዚህም ምክንያት፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ፥ *ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል*።
መሣፍንት 9፥23 *እግዚአብሔር በአቤሜሌክና በሴኬም ሰዎች መካከል ክፉን መንፈስ ሰደደ*፤
መዝሙር 105፥28 *ጨለማን ላከ* ጨለመባቸውም፤ በቃሉም ዐመፁ።
መዝሙር 106፥15 የለመኑትንም ሰጣቸው፤ ለነፍሳቸው ግን *ክሳትን ላከ*።

ይሄ ክፉም መንፈስ እንደ ኡቃቤ ከእግዚአብሔር ዘንድ እየተላከ ሳኦልን አሠቃየው፦
1ኛ ሳሙኤል 16፥14 የእግዚአብሔርም መንፈስ ከሳኦል ራቀ፥ *ክፉም መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ አሠቃየው*።
1ኛ ሳሙኤል 18፥10 በነጋውም ሳኦልን *ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያዘው*፥

ክፉም መንፈስ ከእግዚአብሔር ጋር ሹራ እያደረገ ለእግዚአብሔር ያሳስትለታል፦
1ኛ ነገሥት 22 20-23 እግዚአብሔርም፦ ወጥቶ በሬማት ዘገለዓድ ይወድቅ ዘንድ *አክዓብን የሚያሳስት ማን ነው?* አለ። አንዱም እንዲህ ያለ ነገር፥ ሌላውም እንዲያ የለ ነገር ተናገረ። *መንፈስም ወጣ በእግዚአብሔርም ፊት ቆሞ፦ እኔ አሳስተዋለሁ አለ*። እግዚአብሔርም፦ በምን? አለው እርሱም፦ *ወጥቼ በነቢያቶቹ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ እሆናለሁ አለ*። እግዚአብሔርም፦ *ማሳሳትስ ታሳስተዋለህ፥ ይሆንልሃልም ውጣ፥ እንዲሁም አድርግ አለ*። አሁንም፦ እነሆ፥ እግዚአብሔር በእነዚህ *በነቢያትህ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ አድርጎአል*፤ እግዚአብሔርም በላይህ ክፉ ተናግሮብሃል።

እግዚአብሔር ሰዎች የሰማይንም ጭፍራ ያመልኩ ዘንድ አሳልፎ ይሰጣል፦
የሐዋርያት ሥራ 7፥42 እግዚአብሔር ግን ዘወር አለ *የሰማይንም ጭፍራ ያመልኩ ዘንድ አሳልፎ ሰጣቸው*፥

እግዚአብሔር ሰዎች በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ይሰጣል፦
ሮሜ 1፥24 ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ *እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው*፤

እግዚአብሔር ሰዎች ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ይሰጣል፦
ሮሜ 1፥26 ስለዚህ *እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው*፤

እግዚአብሔር ሰዎች የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ይሰጣል፦
ሮሜ 1፥28 እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን *እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው*፤

እግዚአብሔር ሰዎች ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ የእንቅልፍ መንፈስን ይሰጣል፦
ሮሜ 11፥8 ሌሎቹም ደነዘዙ፤ እንዲሁም፦ ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ *እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስን እስከ ዛሬ ድረስ ሰጣቸው* ተብሎ ተጽፎአል።

እግዚአብሔር ሰዎች ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ የእንቅልፍ መንፈስን ያፈሳል፦
ኢሳይያስ 29፥10 *እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስ አፍስሶባችኋል ዓይኖቻችሁን ነቢያትንም ጨፍኖባችኋል ራሶቻችሁን ባለ ራእዮችን ሸፍኖባችኋል*።

እግዚአብሔር የጠማምነትን መንፈስ በውስጣቸው በመደባለቅ ያጠማቸዋል፦
ኢሳይያስ 19፥14 *እግዚአብሔር የጠማምነትን መንፈስ በውስጥዋ ደባልቆአል*፤
መክብብ 7:13 የእግዚአብሔርን ሥራ ተመልከት እርሱ *ጠማማ ያደረገውን ማን ሊያቀናው* ይችላል?

እግዚአብሔር ለጳውሎስ በመገለጥ ታላቅነት እንዳይታበይ የሥጋው መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመው የሰይጣን መልእክተኛ ሰቶታል፦
2 ቆሮንቶስ 12፥7 ስለዚህም በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመኝ *የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ*፤ ይኸውም እንዳልታበይ ነው።ባይብል ላይ ግን እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ ያደነደነው ኃይሉ ይገልጥበት ዘንድ እና ስሙ በምድር ሁሉ ላይ ይነገር ዘንድ ነው፦
ዘጸአት 9፥16 ነገር ግን *ኃይሌን እገልጥብህ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ላይ ይነገር ዘንድ ስለዚህ አስነሥቼሃለሁ*።
ሮሜ 9፥17 መጽሐፍ ፈርዖንን፦ ኃይሌን በአንተ አሳይ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ይነገር ዘንድ ለዚህ አስነሣሁህ ይላልና።

“ቃሻህ” קָשָׁה ማለት “ማደንደን” ማለት ሲሆን እግዚአብሔር ፈርዖን የእስራኤል ልጆችን እንዳይለቅ እና ሙሴን እንዳይሰማ የፈርዖንን ልብ አደንድኖታል፦
ዘጸአት 7፥3 እኔም *የፈርዖንን ልብ አደነድናለሁ אַקְשֶׁ֖ה * ፥ በግብፅ ምድርም ድንቄንና ተአምራቴን አበዛለሁ።
ዘጸአት 14፥4 እኔም *የፈርዖንን ልብ አደነድናለሁ וְחִזַּקְתִּ֣י * ፥ እርሱም ያባርራቸዋል፤
ዘጸአት 9፥12 እግዚአብሔርም *የፈርዖንን ልብ አደነደነ וַיְחַזֵּ֤ק *፤ እግዚአብሔር ለሙሴ እንደተናገረው አልሰማቸውም።
ዘጸአት 14፥8 እግዚአብሔርም የግብፅን ንጉሥ *የፈርዖንን ልብ አደነደነ* וַיְחַזֵּ֣ק ፥

እግዚአብሔር ቀደም ብሎ ልብን ስላደነደነው የፈርዖን ልብ ደነደነ፦
ዘጸአት 7፥13 *እግዚአብሔር እንደ ተናገረ፥ የፈርዖን ልብ ደነደነ וַיֶּחֱזַק֙:*፥ አልሰማቸውምም።
ዘጸአት 7፥14 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ *የፈርዖን ልብ ደነደነ*፥ ሕዝቡንም ለመልቀቅ እንቢ አለ።
ዘጸአት 9፥7 ፈርዖንም ላከ፥ እነሆም ከእስራኤል ልጆች ከብት አንድ ስንኳ አልሞተም። *የፈርዖን ልብ ግን ደነደነ*፥ ሕዝቡንም አልለቀቀም።
እውን ፈርዖን ተጠያቂ ነውን? ልቡንስ ካደነደነው ህዝቤን ልቀቅ ብሎ ሙሴና አሮንን መላክ ለምን አስፈለገ? ሕዝቡንም ለመልቀቅ እንቢ አለ ብሎ ፈርዖንን መውቀስ ለምንችአስፈለገ? በዚህ አላበቃም፤ እግዚአብሔር የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎንን መንፈሱን አደንድኖታል፦
ዘዳግም 2፥30 የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳልፈን ዘንድ አልፈቀደም፤ እንደ ዛሬው ሁሉ በእጅህ አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ አምላክህ *እግዚአብሔር መንፈሱን አደንድኖታልና*፥ ልቡንም አጽንቶታልና።

ለነገሩ ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር የሆነውን ክፉን መንፈስ ይልካል፦
2ኛ ተሰሎንቄ 2፥12 ስለዚህም ምክንያት፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ፥ *ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል*።
መሣፍንት 9፥23 *እግዚአብሔር በአቤሜሌክና በሴኬም ሰዎች መካከል ክፉን መንፈስ ሰደደ*፤

እግዚአብሔር ሰዎች ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ የእንቅልፍ መንፈስን ይሰጣል፦
ሮሜ 11፥8 ሌሎቹም ደነዘዙ፤ እንዲሁም፦ ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ *እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስን እስከ ዛሬ ድረስ ሰጣቸው* ተብሎ ተጽፎአል።

እግዚአብሔር ሰዎች ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ የእንቅልፍ መንፈስን ያፈሳል፦
ኢሳይያስ 29፥10 *እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስ አፍስሶባችኋል ዓይኖቻችሁን ነቢያትንም ጨፍኖባችኋል ራሶቻችሁን ባለ ራእዮችን ሸፍኖባችኋል*።

እግዚአብሔር የጠማምነትን መንፈስ በውስጣቸው በመደባለቅ ያጠማቸዋል፦
ኢሳይያስ 19፥14 *እግዚአብሔር የጠማምነትን መንፈስ በውስጥዋ ደባልቆአል*፤
መክብብ 7:13 የእግዚአብሔርን ሥራ ተመልከት እርሱ *ጠማማ ያደረገውን ማን ሊያቀናው* ይችላል?

እግዚአብሔር ለጳውሎስ በመገለጥ ታላቅነት እንዳይታበይ የሥጋው መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመው የሰይጣን መልእክተኛ ሰቶታል፦
2 ቆሮንቶስ 12፥7 ስለዚህም በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመኝ *የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ*፤ ይኸውም እንዳልታበይ ነው።

ነቢዩም ቢታለል ያንን ነቢይ ያታለለው እግዚአብሔር ነው ይላል፤ ሕዝቅኤልን፣ ኤርሚያስን እና ኢሳይያስን ያታለለው እርሱ እንደሆነ እራሳቸው ይናገራሉ፦
ሕዝቅኤል 14:9፤ ነቢዩም ቢታለል ቃልንም ቢናገር፥ ያንን ነቢይ *ያታለልሁ* እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥
ኤርሚያስ 20:7 አቤቱ፥ *አታለልኸኝ* እኔም ተታለልሁ፥
ኤርሚያስ 4:10 እኔም። ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ፥ አንተ ሰይፍ እስከ ነፍስ ድረስ በደረሰ ጊዜ። ሰላም ይሆንላችኋል ብለህ ይህን ሕዝብና ኢየሩሳሌምን እጅግ *አታለልህ* አልሁ።
ኢሳይያስ 63:17 አቤቱ፥ ከመንገድህ ለምን “አሳትኸን”? እንዳንፈራህም ልባችንን ለምን አጸናህብን? ስለ ባሪያዎችህ ስለ ርስትህ ነገዶች ተመለስ።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የኢየሱስ አምላክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

14፥52 ይህ ቁርኣን ለሰዎች ገላጭ ነው፡፡ ሊመከሩበት፣ በእርሱም ሊያስጠነቅቁበት፣ እርሱም አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት፣ የአዕምሮ ባለቤቶችም ሊገሰፁበት የተወረደ ነው፡፡ هَذَا بَلَاغٌ لِلنَّاسِ وَلِيُنْذَرُوا بِهِ وَلِيَعْلَمُوا أَنَّمَا هُوَ إِلَهٌ وَاحِدٌ وَلِيَذَّكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ ” سورة إبراهيم

ቁርኣን ከወረደበት ምክንያት አንዱ የአዕምሮ ባለቤቶችም አላህ አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት ነው፦
14፥52 ይህ ቁርኣን ለሰዎች ገላጭ ነው፡፡ ሊመከሩበት፣ በእርሱም ሊያስጠነቅቁበት፣ እርሱም አንድ አምላክ ብቻ መኾኑን ሊያውቁበት፣ የአዕምሮ ባለቤቶችም ሊገሰፁበት የተወረደ ነው፡፡ هَذَا بَلَاغٌ لِلنَّاسِ وَلِيُنْذَرُوا بِهِ وَلِيَعْلَمُوا أَنَّمَا هُوَ إِلَهٌ وَاحِدٌ وَلِيَذَّكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ ” سورة إبراهيم

ነገር ግን ይህንን አንድ አምላክ አንዴ በማንነት ሶስት ነው፣ አንዴ ሰው ሆነ፣ አንዴ ለሰው ኀጢአት ሞተ እያሉ በነውርና በጎዶሎ ባህርይ ያሻርኩታል፤ ይህ አንድ አምላክ በመለኮታዊ ቅሪት ሲናገር እንዲህ ይላል፦
ሆሴዕ 11፥9 እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁምና፥
ኢሳይያስ 44:6 ከእኔ ሌላም አምላክ የለም።

አንዱ አምላክ እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁም፣ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም እያለን ተመልሰው “ሰውም አምላክ ነህ” ማለት እኛ ፍጡራን፦ ፈጣሪን “ስለ አንተ ከአንተ ይልቅ እኛ እናውቅልሃለን” እያልነው ነው፤ ነገር ግን ኢየሱስ በአንዱ አምላክ እና በሰዎች መካከል መካከለኛ ሆኖ ከአምላክ ሰምቶ የሚናገር ሰው ነው፤ በድንቆች በምልክቶችም ከአንዱ አምላክ ዘንድ ለእስራኤል ሰዎች የተላከ ሰው ነበረ፦
1ኛ ጢሞቴዎስ 2:5 አንድ አምላክ Θεοῦ አለና፥ በአምላክ Θεοῦ እና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም *ሰው* የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤
ዮሐንስ 8፥40 ነገር ግን አሁን ከአምላክ Θεοῦ የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፤
የሐዋርያት ሥራ 2:22 የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ አምላክ Θεοῦ በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከአምላክ Θεοῦ ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ፤

እንግዲህ ኢየሱስ ሰው ከሆነ እና አንዱ አምላክ የላከው ከሆነ ሰው የሆነው ኢየሱስ እና አንዱ አምላክ ሁለት የተለያዩ ማንነት እና ምንነት ናቸው ማለት ነው፤ ኢየሱስ የሚያመልከው የራሱ አምላክ አለው፦

ነጥብ አንድ
“አምላኬ”
“አምላኬ” ማለት “የእኔ” አምላክ ማለት ነው፤ “አምላኬ” በሚል የመጀመሪያ መደብ “እኔ” የሚል አገናዛቢ ተውላጠ ስም አለ፤ “የእኔ አምላክ”my God” የሚለው የኢየሱስ ሙሉ እኔነት አምላክ አለው፦
ማቴዎስ 27:46 በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፡- ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም፡- የእኔ አምላክ የእኔ አምላክ ፥ አንተ እኔን ስለ ምን ተውኸኝ? ማለት ነው። “”My God, my God, why have you forsaken me””.
ዮሐንስ 20:17 ኢየሱስም። ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ። እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ “አምላኬ” እና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት።

በተለይ ኢየሱስ አንዱን አምላክ “አንተ” እራሱን ደግሞ “እኔ” በማለት “አምላኬ” ማለቱ ሰው የሆነው ኢየሱስ እና አንዱ አምላክ ሁለት ህልውናዎች መሆናቸው ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፤ “ተውከኝ” ስላለም በተወው ባለቤት እና በተተው ተሳቢ መካከል “ተውከኝ” የሚል ተሻጋሪ ግስ”transitive verb” መኖሩ ኢየሱስን ከአምላኩ ይለየዋል፤ በተጨማሪም “ወደ” የሚለው መስተዋድድ*preposition* መጠቀሙ በሁለት ማንነት መካከል ለመለየት የሚመጣ ነው፣ ኢየሱስ ማርያምን *ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ* ማለቱ ወንድሞቹና ማርያም የተለያየ ማንነት እንዳላቸው እንደሚያሳይ ሁሉ “ወደ አምላኬ አርጋለው” ማለቱ አምላኩና ኢየሱስ ሁለት የተለያዩ ህላዌዎች መሆናቸውን ፍንትው አድርጎ ያሳያል። ኢየሱስ ካረገም በኃላ አብን አምላኬ ይላል፦
ራእይ 3፥2፤ ሥራህን #በአምላኬ ፊት ፍጹም ሆኖ አላገኘሁትምና የነቃህ ሁን፥ ሊሞቱም ያላቸውን የቀሩትን ነገሮች አጽና።
ራእይ 3፥12 ድል የነሣው #በአምላኬ መቅደስ ዓምድ እንዲሆን አደርገዋለሁ፥ ወደ ፊትም ከዚያ ከቶ አይወጣም፤ #የአምላኬን ስምና የአምላኬን ከተማ ስም፥ ማለት ከሰማይ #ከአምላኬ ዘንድ የምትወርደውን አዲሲቱን ኢየሩሳሌምን፥ አዲሱንም ስሜን በእርሱ ላይ እጽፋለሁ።
ነጥብ ሁለት
“አምላካችን”
ኢየሱስ “ወደ አምላኬ እና ወደ አምላካችሁ” አለ እንጂ “ወደ አምላካችን” ስላላለ አንዱ አምላክ ለኢየሱስ አምላክ የሆነበትና ለሃዋርያት አምላክ የሆነበት መደብ ይለያያል ይላሉ፤ ይህ ውሃ የማያነሳ ሙግት ነው፤ አንደኛ ይህ አነጋገር የተለመደ ነው፦
ዘፍጥረት 43፥23 እርሱም አላቸው፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን፥ አትፍሩ፤ *አምላካችሁ እና የአባታችሁ አምላክ* በዓይበታችሁ የተሰወረ ገንዘብ ሰጣችሁ፤ ብራችሁስ ደርሶኛል።

“አምላካችሁ እና የአባታችሁ አምላክ” ስለተባለ አንዱ አምላክ ለአባታቸው ለያእቆብ እና ለልጆቹ አምላክነቱ ይለያያልን? ሁለተኛ ኢየሱስ “አምላካችን” በሚል አንደኛ መደብ ብዜት ተናግሯል፦
ኢሳይያስ61:1-2 የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል። የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት “”አምላካችንም”” የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ፥ የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ ልኮኛል፤
ማርቆስ 12:29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ። እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ጌታ “”አምላካችን”” አንድ ጌታ ነው፥

ነጥብ ሶስት
“አምላክህ”
መዝሙረኛ እግዚአብሔር ለኢየሱስ አምላክ መሆኑን ለማሳየት ” አምላክህ” በማለት በሁለተኛ መደብ ተናግሯል፦
መዝሙር 45:7 ጽድቅን ወደድህ ዓመፃንም ጠላህ፤ ስለዚህ ከባልንጀሮችህ ይልቅ እግዚአብሔር “አምላክህ” የደስታ ዘይትን ቀባህ።
ዕብራውያን 1:9 ጽድቅን ወደድህ ዓመፅንም ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር “አምላክህ” ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ።

ለኢየሱስ ባለንጀሮቹ ሲቀቡ የነበሩት ነብያት ናቸው፤ ክርስቶስ ማለት “የተቀባ” ማለት ሲሆን አምላኩ እግዚአብሔር ኢየሱስን የደስታ ዘይት በሆነው በመንፈስ ቅዱስ ቀብቶታል፤ ቀቢው አንዱ አምላክ ከሆነ ተቀቢው ሰው ብቻ ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 10:38 እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤

ነጥብ አራት
“አምላኩ”
ኢየሱስ አምላክ እንዳለው ለማሳየት “አምላኩ” በማለት በሶስተኛ መደብ ተናግረዋል፦
ራእይ 1:6 መንግሥትም “”ለአምላኩ”” እና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥
ሚክያስ 5:4፤ እርሱም ይቆማል፥ በእግዚአብሔርም ኃይል “”በአምላኩ”” በእግዚአብሔር ስም ግርማ መንጋውን ይጠብቃል፤ እነርሱም ይኖራሉ፤ እርሱ አሁን እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ታላቅ ይሆናልና።

በተጨማሪም “የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ” በማለት ኢየሱስ አምላክ እንዳለው ተናግረዋል፦
ኤፌሶን 1:17 የክብር አባት የጌታችን “”የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ”” እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ።
2ኛ ቆሮንጦስ1:3 የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።
2ኛ ቆሮንጦስ 11:31 ለዘላለም የተባረከ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት እንዳልዋሽ ያውቃል።

መደምደሚያ
ኢየሱስ በንግግሩ እራሱን ሁለተኛው የአንዱ አምላክ አባል አድርጎ አስተምሮ አያውቅም። ከዚያ ይልቅ እራሱ ከአንዱ አምላክ ውጪ ያደርግ ነበር፦
ማርቆስ 10:18 ኢየሱስም። ስለ ምን ቸር እኔን ትለኛለህ? ከአንዱ አምላክ በቀር ቸር ማንም የለም።Why callest you me good? there is none good but one, that is , God.
ዮሐንስ 17፥3 እውነተኛ አምላክ ብቻህን የሆንህ አንተን እና የላከውን ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህቺ የዘላለም ህይወት ናት። (1980 አዲስ ትርጉም)
ዮሐንስ 14:1 ልባችሁ አይታወክ፤ በአምላክ Θεοῦ እመኑ፥ በእኔም ደግሞ እመኑ።
ዮሐ7፥16-17 ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው። ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ*myself አይደለም፤ ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ ይህ ትምህርት ከአምላክ Θεοῦ ቢሆን ወይም እኔ ከራሴ*myself የምናገር ብሆን ያውቃል።

አንዳንድ ቂሎች “ኢየሱስ አምላክ አለው ግን ለስጋው ነው” ይሉናል፤ ስጋው ፍጡር እና የራሱ ማንነት ከሆነ በስጋው የሚያመልከው አምላክ ካለው ኢየሱስ አምላኪም ተመላኪም ከሆነ ሁለት አይሆንም ወይ? ሲቀጥል “ስጋ” ብቻውን “እኔ” ይላል ወይ? የሰው ሁለተንተና መንፈሱ፣ ነፍሱ እና ስጋው ናቸው፦
1ኛ ተሰሎንቄ 5:23 የሰላምም አምላክ ራሱ “”ሁለንተናችሁን”” ይቀድስ፤ “መንፈሳችሁም፣ ነፍሳችሁም፣ ፣ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።”

ኢየሱስ የራሱ መንፈስ ካለው፣ የራሱን መንፈስ ለአንዱ አምላክ ከሰጠ የራሱ መንፈስ ከአንዱ አምላክ ይለያል፦
ዮሐንስ13:21 ኢየሱስ ይህን ብሎ “በመንፈሱ” ታወከ መስክሮም።
ሉቃስ 23:46 ኢየሱስም በታላቅ ድምፅ ጮኾ። አባት ሆይ፥ “መንፈሴን” በእጅህ አደራ እሰጣለሁ አለ። ይህንም ብሎ “መንፈሱን” ሰጠ። NIV

አንዱ አምላክ ደግሞ የመንፈስ ሁሉ አምላክ ከሆነ አንዱ አምላክ የኢየሱስ ሁለንተና አምላክ ነው፦
ዘኊልቅ 16:22 እነርሱም በግምባራቸው ወድቀው። አምላክ ሆይ፥ አንተ የሰው ሁሉ መንፈስ አምላክ(the God of the spirits of all flesh,)፥ አንድ ሰው ኃጢአት ቢሠራ አንተ በማኅበሩ ሁሉ ላይ ትቈጣለህን? አሉ።
ዘኊልቅ 27:16፤17፤ የእግዚአብሔር ማኅበር እረኛ እንደሌለው መንጋ እንዳይሆን፥ በፊታቸው የሚወጣውን በፊታቸውም የሚገባውን የሚያስወጣቸውንም የሚያስገባቸውንም ሰው የሥጋ ሁሉ መንፈስ አምላክ (the God of the spirits of all flesh) እግዚአብሔር በማኅበሩ ላይ ይሹመው።

ስለዚህ አንዱ ኣምላክ አምላክነቱ ለመንፈሱም ጭምር ከሆነ እና ባይብል ላይ 17 ቦታ ኢየሱስ አምላክ እንዳለው ከተገለፀ እውነትም ኢየሱስ አምላኪ ፍጡር ነው፤ በእውነት ሊመለክ የሚገባው የኢየሱስ አምላክ ብቻ ነው። አምላካችን አላህም ኢየሱስ ተናገር ብሎ ያዘዘው ቃል “ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ” ማለትን ነው፦
5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል “ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ” ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አላህ መለኮት ነው!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

43፥84 *”እርሱም ያ በሰማይ ውስጥ ሊገዙት የሚገባ፥ በምድርም ውስጥ ሊገዙት የሚገባ አምላክ ነው”*፡፡ እርሱም ብልሃተኛው ዐዋቂው ነው፡፡ وَهُوَ الَّذِي فِي السَّمَاءِ إِلَـٰهٌ وَفِي الْأَرْضِ إِلَـٰهٌ ۚ وَهُوَ الْحَكِيمُ الْعَلِيمُ

“ሥነ መለኮት”theology” በግሪክ “ቴዎ ሎጊያ” θεολογία ሲሆን የሁለት ቃላት ውቅር ነው፥ “ቴዎስ” Θεός ማለትም “አምላክ” እና “ሎጊያ” λογία ማለትም “ጥናት” ነው። “ቴኢዎስ” θεῖος የሚለው ቃል “ቴዎስ” θεός ማለትም “አምላክ”God” ለሚለው ቃል ገላጭ ቅጽል”adjective” ሲሆን “አምላክነት”God-head” ወይም “መለኮት”Divine” ማለት ነው፥ ይህም ቃል በአዲስ ኪዳን ግሪክ ኮይኔ 5 ጊዜ ተጠቅሷል።
ስለዚህ “መለኮት” ማለት በቋንቋ ደረጃ በቀላሉ “አምላክ” ማለት ነው። አምላካችን አላህ”ﷻ” “መለኮት” ነው፦
43፥84 *”እርሱም ያ በሰማይ ውስጥ ሊገዙት የሚገባ፥ በምድርም ውስጥ ሊገዙት የሚገባ አምላክ ነው”*፡፡ እርሱም ብልሃተኛው ዐዋቂው ነው፡፡ وَهُوَ الَّذِي فِي السَّمَاءِ إِلَـٰهٌ وَفِي الْأَرْضِ إِلَـٰهٌ ۚ وَهُوَ الْحَكِيمُ الْعَلِيمُ
6፥3 *”እርሱም ያ በሰማያትና በምድር ሊገዙት የሚገባ አምላክ ነው”*፡፡ ምስጢራችሁን ግልጻችሁንም ያውቃል፡፡ የምትሠሩትንም ሁሉ ያውቃል፡፡ وَهُوَ اللَّهُ فِي السَّمَاوَاتِ وَفِي الْأَرْضِ ۖ يَعْلَمُ سِرَّكُمْ وَجَهْرَكُمْ وَيَعْلَمُ مَا تَكْسِبُونَ

“ኢላህ” إِلَـٰه የሚለው ቃል “መለኮት” ወይም “አምላክ” ማለት ነው። “ኢላሂይ” إِلٰهِيّ‎ ማለት “መለኮታዊ” ወይም “አምላካዊ” ማለት ሲሆን “ኡሉሂያህ” أُلُوهِيَّة‎ ማለት ደግሞ “አምላክነት” ማለት ነው። “ኢላሂያት” إِلٰهِيَّات‎ ማለት በራሱ “ሥነ-መለኮት” ማለት ነው። አላህ ብቻውን አንድ መለኮት ነው፥ ከእርሱ በቀር ሌላ መለኮት የለም፦
4፥171 *አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው”*፡፡ ለእርሱ ልጅ ያለው ከመኾን የጠራ ነው፡፡ በሰማያትና በምድር ያለ ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ መመኪያም በአላህ በቃ፡፡ إِنَّمَا اللَّهُ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ سُبْحَانَهُ أَن يَكُونَ لَهُ وَلَدٌ ۘ لَّهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ ۗ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ وَكِيلًا
6፥19 *«እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው*፡፡ እኔም ከምታጋሩት ነገር ንጹሕ ነኝ» በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَا هُوَ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ وَإِنَّنِي بَرِيءٌ مِّمَّا تُشْرِكُونَ
2፥163 *”አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፥ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም”*፡፡ እርሱ እጅግ በጣም ርኅሩህ አዛኝ ነው፡፡ وَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الرَّحْمَـٰنُ الرَّحِيمُ

“መለኮት” ማለት “ሁሉን ነገር ማድረግ የሚችል” “ሁሉን ነገር የሚያውቅ” “ሁሉን ነገር የሚያይ” “ሁሉን ነገር የሚሰማ” “በባዶነት መነሻ በሞት መዳረሻ የሌለው ሕያው” ማለት ነው። አንተ ምንድን ነህ? ብባል “ሰው ነኝ” ብዬ የሰው ባሕርያት ተራቢ ነኝ፣ ተጠሚ ነኝ፣ በዪ ነኝ፣ ጠጪ ነኝ ወዘተ እያልኩኝ እናገራለን፥ አላህ ምንድን ነው? ብንባል “አምላክ ነው” ወይም “መለኮት” ነው ብለን የመለኮት ባሕርያትን በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፣ ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፣ ሁሉን ሰሚ ነው፣ ሁሉን ተመልካች ነው፥ በባዶነት መነሻ በሞት መዳረሻ የሌለው ሕያው ነው እያልን ታላቁ ባሕርይውን እንናገራለን፦
29፥20 አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው”*። إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
65፥11 *”አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው”*፡፡ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ
58፥1 *”አላህ ሰሚ ተመልካች ነው”*፡፡ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِير
2፥110 *”አላህ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው”*፡፡ إِنَّ اللَّهَ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ
25፥58 *”በዚያም በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ”*፡፡ ከማመስገንም ጋር አጥራው፡፡ በባሮቹ ኀጢኣቶችም ውስጠ ዐዋቂ በእርሱ በቃ፡፡ وَتَوَكَّلْ عَلَى الْحَيِّ الَّذِي لَا يَمُوتُ وَسَبِّحْ بِحَمْدِهِ ۚ وَكَفَىٰ بِهِ بِذُنُوبِ عِبَادِهِ خَبِيرًا

አላህ በሰማያትና በምድር ሊገዙት የሚገባ መለኮት ነው፥ ለእርሱም በሰማያትም በምድርም ታላቅ ባሕርይ አለው፦
16፥60 *”ለአላህም ታላቅ ባሕርይ አለው”*፡፡ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡ وَلِلَّهِ الْمَثَلُ الْأَعْلَىٰ ۚ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ
30፥27 *”ለእርሱም በሰማያትም በምድርም ታላቅ ባሕርይ አለው”*፡፡ እርሱም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡ وَلَهُ الْمَثَلُ الْأَعْلَىٰ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۚ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ

“ባሕርይ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “አል-መሰል”الْمَثَل ሲሆን የአል-መሰል ብዙ ቁጥር ደግሞ “አል-አምሳል” الْأَمْثَال ነው። አላህ የእኔ ባሕርይ ይህ ነው ብሎ በቁርኣን የተናገረውን እንጂ እኛ ለእርሱ ምንም አይነት ባሕርይ ማድረግ ተከልክለናል፦
16፥74 *”ለአላህም ባሕርዮችን አታድርጉ፡፡ አላህ መሳይ እንደሌለው ያውቃል፡፡ እናንተ ግን አታውቁም*፡፡ فَلَا تَضْرِبُوا لِلَّهِ الْأَمْثَالَ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَعْلَمُ وَأَنتُمْ لَا تَعْلَمُون
42፥11 *”የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው”*፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ
በሰማያትም በምድርም የእርሱን ታላቅ ባሕርይ የሚመስል ምንም ነገር የለም። “ነገር” ማለት “አጠቃላይ ፍጥረት” ነው። እርሱ ሰሚው ተመልካቹ ነው፥ የእርሱ መስማት እና ማየት ጊዜና ቦታ አያካብበውም።
የሥነ-ኑባሬ ጥናት”ontology” ምሁራን እንደሚያትቱት “ዛት” ذَات ማለት “ህላዌ”essence” ማለት ሲሆን “ምንድን” ተብሎ የሚጠየቅ “ምንነት” ነው፥ ምንነት የማንነት መሠረት ነው። “ሸኽስ” شَخْص ማለት “እኔነት”person” ማለት ሲሆን “ማን” ተብሎ የሚጠየቅ “ማንነት” ነው፥ ማንነት የምንነት መገለጫ ነው። አላህ የራሱ አንድ ማንነት አለው፦
20፥14 *«እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና አምልከኝ*፡፡ ሶላትንም በእርሷ እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡ إِنَّنِىٓ أَنَا ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدْنِى وَأَقِمِ ٱلصَّلَوٰةَ لِذِكْرِىٓ
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ *”ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ”* በማለት ወደ እርሱ *”የምናወርድለት”* ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ

“አና” أَنَا ማለት “እኔ” ማለት ሲሆን አንድ ነጠላ ማንነትን የሚያሳይ ነጠላ ተውላጠ-ስም ነው፥ ይህም አንድ ማንነት ምንነቱ አምላክ ስለሆነ “ከእኔ ሌላ አምላክ የለም” በማለት ይናገራል። አላህ የራሱ ማንነት ስላለው “ነፍሲ” نَفْسِي ማለትም “እራሴ” ይላል፦
20፥41 *ለነፍሴም መረጥኩህ*፡፡ وَاصْطَنَعْتُكَ لِنَفْسِي

በዚህ አንቀጽ ላይ “ለነፍሴ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሊነፍሢ” لِنَفْسِي ሲሆን “ለራሴ” ማለት ነው፤ የአላህ እራስነት”own self-hood” እንዳለው ያመለክታል።
አላህ ምንነቱን የሚያሳውቀን በሲፋው ነው። “ሲፋህ” صِفَة ማለትም “ባሕርይ”attribute” ማለት ነው፥ የእርሱ ባሕርያት የተሰየሙበት ስም አለው። “ኢሥም” اِسْم ማለት “ስም” ማለት ሲሆን አላህ ከፍጡራኑ ጋር የማይመሳሰል “አሥማኡል ሑሥና” الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ ማለትም “መልካም ስሞች” አሉት፦
20፥8 አላህ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ *”ለእርሱ መልካሞች የኾኑ ስሞች አሉት”*፡፡ اللَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ

አላህ ምንድን ነው? ሲባል የምንነት ጥያቄ ስለሆነ የምንነቱ መታወቂያ የሆኑትን ባሕርያት የተሰየሙበትን ስም በመጥቀስ፦
1. “አል-ኻሊቅ” الْخَالِق ማለትም “ፈጣሪ” ነው፦
29፥24 *እርሱ አላህ “ፈጣሪው”፥ ከኢምንት አስገኚው፣ ቅርጽን አሳማሪው ነው*፡፡ هُوَ اللَّهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ

2. “አስ-ሰመድ” الصَّمَد ማለትም “የሁሉ መጠጊያ” ነው፦
112፥2 *አላህ “የሁሉ መጠጊያ” ነው*፡፡ اللَّهُ الصَّمَدُ

3. “አል-ገኒይ” الْغَنِيّ ማለትም “ተብቃቂ” ነው፦
35፥15 እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ ሁል ጊዜ ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ፡፡ *አላህም እርሱ “ተብቃቂው” ምስጉኑ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ أَنتُمُ الْفُقَرَاءُ إِلَى اللَّهِ ۖ وَاللَّهُ هُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ

4. “አል-ለጢፍ” اللَّطِيف ማለትም “ረቂቅ” ነው፦
6፥103 ዓይኖች አያገኙትም፥ እርሱም ዓይኖችን ያያል፡፡ *እርሱም “ረቂቁ”፥ ውስጠ ዐዋቂው ነው*፡፡ لَّا تُدْرِكُهُ الْأَبْصَارُ وَهُوَ يُدْرِكُ الْأَبْصَارَ ۖ وَهُوَ اللَّطِيفُ الْخَبِيرُ

እያልን እንዘረዝራለን። እርሱ ፍጥረትን ካለመኖር ወደ መኖር ያስገኘ ፈጣሪ፣ ፍጥረታት በእርሱ ላይ ጥገኛ የሆኑ የሁሉ መጠጊያ፣ ከፍጥረቱ ምንም የማይከጅል ተብቃቂ፣ የፍጡራም አእምሮ መርምሮ የማይደርስበት ረቂቅ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አንድያ ልጅ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

19፥35 *ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል*፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

"አንድያ ልጅ" የሚለው የግሪኩ ቃል "ሞኖ-ጌነስ" μονογενὴς ሲሆን የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ "ሞኖስ" μόνος ማለት "ብቸኛ" ማለት ሲሆን "ጌኑስ" γένος ማለት ደግሞ "የተወለደ" ማለት ነው፤ በጥቅሉ "ብቸኛ የተወለደ"the only begotten" ማለት ነው፦
1ኛ ዮሐንስ 4፥9 እግዚአብሔር *"አንድ ልጁን"* μονογενῆ ወደ ዓለም ልኮታልና።

በግዕዝ "ወልድ ዋሕድ" ይሉታል። ይህንን ውልደት እግዚአብሔር በመዝሙር ኢየሱስን እኔ ዛሬ ወለድሁህ ብሎታል፦
መዝሙር 2፥7 ትእዛዙን እናገራለሁ፤ እግዚአብሔር አለኝ፦ አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ *"ዛሬ "ወለድሁህ"* γεγέννηκά ።

"ዛሬ" የሚለው የጊዜ ተውሳከ-ሥስ ጊዜን የሚያሳይ ነው፣ ኢየሱስ መወለዱ ጅማሬ ያለው መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያሳያል፣ ይህ ጊዜ ከሞት ሲነሳ እንደሆነ ጳውሎስ ይናገራል፦
የሐዋርያት ሥራ 13፥33 ይህን ተስፋ እግዚአብሔር በሁለተኛው መዝሙር ደግሞ፦ አንተ ልጄ ነህ *"እኔ ዛሬ ወለድሁህ"* γεγέννηκά ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ *ኢየሱስን አስነሥቶ ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞአልና*።

"እኔ ዛሬ ወለድሁህ" ተብሎ በሁለተኛው መዝሙር የተጻፈው ቃል ኢየሱስ ሲነሳ ተፈጽሞአል እያለን ነው፤ ስለዚህ "ዛሬ ወለድሁህ" የተባለን ቅድመ-ዓለም ከአብ ያለ እናት የሚለው ዶግማ ውኃ የሚያስበላና ድባቅ የሚያስገባ ነው። ኢየሱስ ከሙታን በኵር ተብሏል፤ "በኵር” ተብሎ የተቀመጠው የግሪኩ ቃል “ፕሮቶ-ቶኮስ” πρωτότοκος ሲሆን የሁለት ቃላት ጥምረት ነው፤ አንዱ “ፕሮቶስ” πρῶτος ማለት “ፊተኛ” ሲሆን ሁለተኛው “ቶኮስ” τοκος ማለትም “መወለድ” ነው፤ በጥቅሉ "መጀመሪያ የተወለደ" ማለት ነው። ኢየሱስ በብዙ ወንድሞች መካከል ፊተኛ በመሆን ከሙታን በአብ እንደተወለደ ይናገራል፦
ሮሜ 8፥29 *“ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል “በኵር” πρωτότοκον ይሆን ዘንድ*፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤

"የበኵር ልጅ" ሁለተኛ ልጅ እስኪመጣ ድረስ ለወላጅ "አንድያ ልጅ" ነው፦
ዘካርያስ 12፥10 ሰውም *ለአንድያ ልጁ* እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም *ለበኵር ልጁ* እንደሚያዝን በመራራ ኀዘን ያዝኑለታል።

"አንድያ ልጁ" እና "የበኵር ልጁ" ተለዋዋጭ ሆነው እንደገቡ ልብ በል፤ ታዲያ ቀጣይ ልክ እንደ ኢየሱስ ከአብ የሚወለዱ እነማን ናቸው? ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል፦
1ኛ ዮሐንስ 5:1 ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር *ተወልዶአል* γεγέννηται ፥ ወላጁንም የሚወድ ሁሉ ከእርሱ *የተወለደውን* γεγεννημένον ደግሞ ይወዳል። የሐዋርያት ሥራ 17:28-29 ከእናንተ ከባለ ቅኔዎች አንዳንዶች ደግሞ። እኛ ደግሞ *ውልደቶቹ* γένος ነንና ብለው እንደ ተናገሩ፥ በእርሱ ሕያዋን ነንና እንቀሳቀሳለን እንኖርማለን። እንግዲህ የእግዚአብሔር *ውልደቶች* γένος ከሆንን፥
ዮሐንስ 1፥13 እነርሱም ከእግዚአብሔር *"ተወለዱ"* ἐγεννήθησαν እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ *"አልተወለዱም"*።

"ጌኑስ" γένος የሚለው ቃል ልክ ለኢየሱስ እንደተጠቀመበት እዚህ ላይም ተጠቅሟል፤ እንደ ጳውሎስ ትምህርት ኢየሱስ ከሞት ሲነሳ እንደተወለደ ሁሉ አማኞች በትንሳኤ ቀን ሲነሱ ሲጠባበቁት የነበረውን ልጅነት ዳግም ያገኛሉ፦
ሮሜ 8፥23 *"የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነት እየተጠባበቅን"* ራሳችን በውስጣችን እንቃትታለን።
ማቴዎስ 19፥28 *"በዳግመኛ ልደት"* የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥

ዳግም ልደት ማለት አዲስ ልደት ማለት ነው፤ ኢየሱስ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድያ ልጅ የሚለው እሳቤ ፉርሽ ሆነ ማለት ነው፤ ምክንያቱም ከኢየሱስ በኃላ አማኞች ከእግዚአብሔር እንደሚወለዱ ሁሉ ከኢየሱስ ትንሳኤ በፊት መላእክእት፣ አዳም እና እስራኤል የእግዚአብሔር ልጆች ተብለዋል፦
ኢዮብ 38፥7 አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥ *የእግዚአብሔርም ልጆች* ሁሉ እልል ሲሉ፥
ሉቃስ 3፥38 የሴት ልጅ፥ የአዳም ልጅ፥ *የእግዚአብሔር ልጅ*።
ዘጸአት 4፥22 ፈርዖንንም፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ *"እስራኤል የበኵር ልጄ ነው"*፤

እስራኤል የመጀመሪያ ልጄ ከሆነ ከእስኤል በፊት አዳም እና መላእክት እንዴት ልጆች ተባሉ? "በኵር” ተብሎ የተቀመጠው የግሪኩ ቃል “ፕሮቶ-ቶኮስ” πρωτότοκος ሲሆን ከላይ ለእስራኤል ከዚያ ለኤፍሬም፣ ቀጥሎ ለዳዊት፣ ለጥቆ ለኢየሱስ አገልግሎት ላይ ውሏል፦
ኤርምያስ 31፥9 እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፥ *"ኤፍሬምም በኵሬ ነውና"*።
መዝሙር 89፥27 *እኔም ደግሞ በኵሬ አደርሀዋለው* ከምድር ነገሥታትም ከፍ ይላል።
ዕብራውያን 1፥6 *"እግዚአብሔር የበኵር ልጁን ልኮ ወደ ዓለም"* ሲያገባ፦ የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉ ይስገዱለት፥ ይላል። (1980 አዲስ ትርጉም)

"መውለድ" በእማሬአዊ የአብራክ ክፋይ ማለት ሲሆን ፈጣሪ ጾታ ስለሌለው በፍካሬአዊ ግን "መፍጠርን" ያመለክታል። “ልደት” ማለት “ፍጥረት” ማለት ስለሆነ “አዲስ ፍጥረት” የሚለውን ተክቶ “አዲስ ልደት” ተብሏል፦
2ኛ ቆሮንቶስ 5፥17 ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን *”አዲስ ፍጥረት”* ነው።
ቲቶ 3፥5 እንደ ምሕረቱ መጠን *”ለአዲስ ልደት”* γένεσις በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥
መወለድ መፈጠር ባይሆን ኖሮ ሰማይንና ምድር ፍጥረት ሆኖ ሳለ “ልደት” ባልተባለ ነበር፤ ስለ ሰማይንና ምድር አፈጣጠር የሚናገረው መጽሐፍ “ዘፍጥረት” ይባላል፤ “ፍጥረት” በሚል ቃል ላይ ያለው መነሻ ቅጥያ “ዘ’ አያያዥ መስተዋድድ “የ” ማለት ነው፤ “የፍጥረት” ማለት ነው፤ በግዕዙ አርስት ላይ “ዘልደት” ይባላል፦
ዘፍጥረት 2፥4 እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን ባደረገ ቀን፥ በተፈጠሩ ጊዜ *”የሰማይና የምድር ልደት”* ይህ ነው።
ግዕዙ፦
ዝንቱ *”ፍጥረተ ሰማይ ወምድር”* ዘምአመ ኮነት ዕለት አንተ ባቲ ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ወምድረ።
ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦
Αὕτη ἡ βίβλος γενέσεως οὐρανοῦ καὶ γῆς, ὅτε ἐγένετο· ᾗ ἡμέρᾳ ἐποίησε Κύριος ὁ Θεὸς τὸν οὐρανὸν καὶ τὴν γῆν

“ጀነሲዋስ” γενέσεως ማለት “ልደት” ማለት ነው፤ “Genesis” የሚለው የኢንግሊዝኛው ስያሜ “ጀነሲስ” γένεσις ከሚለው ከግሪኩ ቃል የመጣ ነው፤ መቼም ሰማይና ምድር ልደት አለው ሲባል ፈጣሪ በእማሬአዊ ወለደው ማለት ሳይሆን በፍካሬአዊ መፍጠሩን የሚያሳይ ስለሆነ ግዕዙ፦ “ፍጥረተ ሰማይ ወምድር” ማለትም “የሰማይና የምድር ፍጥረት” ይለዋል። “ወለደ” ማለት “ፈጠረ” ማለት መሆኑን “የወለደህን አምላክ” የሚለው ቃል “የፈጠረውን አምላክ” በሚል ተለዋዋጭ ቃል መምጣቱ ነው፦
ዘዳግም 32፥18 *የወለደህን አምላክ ተውህ*፥ NIV
ዘዳግም 32፥15 ይሹሩን ወፈረ፥ ረገጠ፤ ወፈረ፥ ደነደነ፥ ሰባ፤ *የፈጠረውንም አምላክ ተወ*፤ NIV

“ይሽሩ” የእስራኤላውያን የቁልምጫ ስም ነው፤ አምላክ እስራኤላውን “ወለደ” ወይስ “ፈጠረ”? ተራራ እንደተወለደ ይናገራል፤ ያ ማለት ተራራ ተሰራ ማለት ነው፦
አሞፅ 4፥13 እነሆ፥ *”ተራሮችን የሠራ”*፥
መዝሙር 90፥2 *”ተራሮች ሳይወለዱ”*፥
ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦
psalms 90፥2 πρὸ τοῦ ὄρη γενηθῆναι καὶ πλασθῆναι τὴν γῆν καὶ τὴν οἰκουμένην,

ግሪክ ሰፕቱአጀንት ላይ “ጌኒቲና” γενηθηναι ማለትም “ሳይወለዱ” የሚለው በተመሳሳይ “ጌኑስ” γένος ማለትም “ወለደ” ከሚል ግሥ የመጣ ነው። ፈጣሪ ኢየሱስን፣ አማኞችን፣ እስራኤላውያንን፣ ተራራን፣ ሰማይና ምድር ሳይቀር ወለደ ማለት ፈጠረ ማለት ካልሆነ ምን ማለት ነው? ሃይማኖተ-አበው ላይ የቂሳሪያው ባስልዮስ “ወለደኝ” ማለት “ፈጠረኝ” ማለት ነው ብሎ እንቅጩን ፍርጥ አድርጎ ነግሮናል፦
ሃይማኖተ-አበው ዘባስልዮስ ምዕራፍ 32 ቁጥር 18
ግዕዙ፦
*”ወለደኒ ይተረጎም በወልደ እግዚአብሔር ወብሂለ ፈጠረኒ በእንተ ትስብእቱ”*
ትርጉም፦
*”ወለደኝ” ማለት የእግዚአብሔር ልጅ ስለመሆኑ “ፈጠረኝ” ማለትም ሰው ስለ መሆኑ ይተረጎማል”*

ልጅ ማለት፦ “አብን አህሎና መስሎ ከአብ ባህርይ ዘእም-ባህርይ አካል ዘእም-አካል" ማለትም "ከባህርይው ባህርይ ወስዶ ከአካሉ አካሉን ወስዶ ተወለደ" ወይም "አምላክ ዘእም-አምላክ" ማለትም "ከአምላክ የተገኘ አምላክ” ካላችሁ ይህንን እሳቤ አይደለም ቁርኣን ባይብላችሁም አይደግፋችሁ። በዚህ ስሌት ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፦
19፥35 *ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል*፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የእግዚአብሔር ልጅ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

18፥4 *እነዚያንም፦ “አላህ ልጅን ይዟል” ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት አወረደው*፡፡ وَيُنذِرَ الَّذِينَ قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا

ክርስቲያኖች ኢየሱስ “የእግዚአብሔር ልጅ” ነው ይላሉ፤ “ልጅ” ማለት ምን ማለት ነው? ስንላቸው፦ “አብን አህሎና መስሎ ከአብ “ባህርይ ዘእም-ባህርይ አካል ዘእም-አካል” ማለትም ከባህርይው ባህርይ ወስዶ ከአካሉ አካሉን ወስዶ ተወለደ” ይሉናል። እረ ከሰማናቸው፦ “አምላክ ዘእም-አምላክ ማለትም ከአምላክ የተገኘ አምላክ” ይሉናል። ይህ ኑባሬአዊ እሳቤ”ontological sense” ነው፤ ከእዚህ እሳቤ ቁርኣን በተቃራኒው፦ “አላህ ወለደ” ያሉ በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፤ አላህ አልወለደም፤ አልተወለደምም፤ እንደውም አላህ ቁርኣን ካወረደበት ምክንያት አንዱ እነዚያንም፦ “አላህ ልጅን ይዟል” ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት ነው፦
37፥152 ፦ *“አላህ ወለደ” አሉ፤ እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው*፡፡ وَلَدَ اللَّهُ وَإِنَّهُمْ لَكَاذِبُونَ
112፥3 *አልወለደም፤ አልተወለደምም*፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ
18፥4 *እነዚያንም፦ “አላህ ልጅን ይዟል” ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት አወረደው*፡፡ وَيُنذِرَ الَّذِينَ قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا

ይህንን የቁርኣን እሳቤ ካየን ዘንዳ ባይብል ላይ እግዚአብሔር አባት መባሉ “አስገኚ” ወይም “ፈጣሪ” በሚል ፍካሬአዊ እሳቤ “ideological sense” መጥቷል፦
ሚልክያስ 2፥10 ለሁላችን *”አንድ አባት”* ያለን አይደለምን? *አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን*?
ዮሐንስ 8፥41 *አንድ አባት* አለን *እርሱም እግዚአብሔር ነው*፡ አሉት።
ኤፌሶን 4፥6 ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር *አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ*።

ለምሳሌ መላእክት መናፍስት ተብለዋል፤ እግዚአብሔር የመናፍስት አባት ነው። መናፍስቱ መላእክት የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው፦
ዕብራውያን 12፥9 እንዴትስ ይልቅ *ለመናፍስት አባት* አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን?
ዕብራውያን 1፥14 *ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?*
ኢዮብ 38፥7 አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥ *የእግዚአብሔርም ልጆች* ሁሉ እልል ሲሉ፥

መላእክት የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት ያለ እናት እና ያለ አባት ስለፈጠራቸው እንደሆነ ቅቡል ነው፤ አዳምም የእግዚአብሔር ልጅ ተብሏል፦
ሉቃስ 3፥38 የሴት ልጅ፥ የአዳም ልጅ፥ *የእግዚአብሔር ልጅ*።

አዳም የእግዚአብሔር ልጅ የተባለው ያለ እናት እና ያለ አባት ስለፈጠረው እንደሆነ እሙን ነው፤ ታዲያ ያለ አባት በእናት ብቻ የተፈጠረው ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ቢባል ምን ይደንቃል? ከማርያም ተጸንሶ የተወለደው ሰው መሆኑን አንርሳ፦
ሉቃስ 1፥35 ስለዚህ ደግሞ *ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል*።
ገላትያ 4 ፥4 ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ *እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ*፤
ማርያም የወለደችው መለኮትን ሳይሆን ሰው ብቻ ነው፤ ያም ሰው የእግዚአብሔር ልጅ መባሉ ፈጣሪ ያለ አባት ከእርሷ መፍጠሩን ያሳያል። አይ እግዚአብሔር ኢየሱስን ወለደው ይሉናል፦
መዝሙር 2፥7 ትእዛዙን እናገራለሁ፤ *እግዚአብሔር አለኝ። አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ “ወለድሁህ”*።
ዕብራውያን 1:5 ከመላእክትስ። *እግዚአብሔር አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ “ወልጄሃለሁ”*፥ (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ጭራሽ ይህ ጥቅስ “ዛሬ” የምትለዋ ቃል መነሻ ጊዜን ታመለክታለች፣ ይህም የኢየሱስ መፈጠር በጊዜ ውስጥ መሆኑን ያሳያል፤ ሲቀጥል እዚህ ጥቅስ ላይ እግዚአብሔር ኢየሱስን፦ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ” ብሏል ተብሏል፤ ይህ የሚያሳየው ኢየሱስ “አንተ” ብሎ ካናገረው እግዚአብሔር የተለየ መሆኑን ያሳያል፣ እግዚአብሔር ለኢየሱስ “አባት እሆነዋለው” ኢየሱስ ለእግዚአብሔር “ልጅ ይሆነኛል” ብሏል ተብሏል” ሲሰልስ “ወልጄሃለሁ” የሚለው ቃል “ጌኔካ” γεγέννηκά ሲሆን “ጌኑስ” γένος ማለትም “ወለደ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን በፍካሬአዊ ትርጉም “ፈጠረ” ሲሆን አይሁዳውያን አምላክ ፆታ ስለሌለውን “መወለድ” ማለት “መፈጠር” ነው ብለው ያምናሉ፤ ምክንያቱን ተራራ እንደተወለደ ስለሚናገር፤ ያ ማለት ተራራ ተሰራ ማለት ነው፦
አሞፅ 4:13 እነሆ፥ *”ተራሮችን የሠራ”*፥
መዝሙር 90:2 *”ተራሮች ሳይወለዱ”*፥ בְּטֶרֶם, הָרִים יֻלָּדו
ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦
πρὸ τοῦ ὄρη γενηθῆναι καὶ πλασθῆναι τὴν γῆν καὶ τὴν οἰκουμένην,
በዕብራይስጡ “ዩላዱ” יֻלָּדו ማለት “ሳይወለዱ” ማለት ነው። “ሳይወለዱ” የሚለው ፍካሬአዊ ቃል በእማሬያዊ ቃል “ሳይፈጠሩ” ማለት ነው። ግሪክ ሰፕቱአጀንት ላይ ደግሞ በተመሳሳይ “ጌኒቲና” γενηθηναι ማለትም “ሳይወለዱ” የሚለው በተመሳሳይ “ጌኑስ” γένος ማለትም “ወለደ” ከሚል ግስ የመጣ ነው፤ “ወለደ” ማለት “ፈጠረ” ማለት መሆኑን “የወለደህን አምላክ” የሚለው ቃል “የፈጠረውን አምላክ” በሚል ተለዋዋጭ ቃል መምጣቱ ነው፦
ዘዳግም 32፥18 *የወለደህን አምላክ ተውህ*፥ NIV
ዘዳግም 32፥15 ይሹሩን ወፈረ፥ ረገጠ፤ ወፈረ፥ ደነደነ፥ ሰባ፤ *የፈጠረውንም አምላክ ተወ*፤ NIV

“ይሽሩ” የእስራኤላውያን የቁልምጫ ስም ነው፤ አምላክ እስራኤላውን “ወለደ” ወይስ “ፈጠረ” ? አይ ፈጣሪ ጾታ ስለሌለው በእማሬአዊ ቃል ወለደ ማለት ሳይሆን በፍካሬአዊ ቃል ፈጠረ ለማለት ነው ከተባለ እንግዲያውስ ከላይ ያለውንም በዚህ ስሌትና ቀመር ተረዱት። መወለድ መፈጠር ባይሆን ኖሮ ሰማይንና ምድር ፍጥረት ሆኖ ሳለ “ልደት” ባልተባለ ነበር፤ ስለ ሰማይንና ምድር አፈጣጠር የሚናገረው መጽሐፍ “ዘፍጥረት” ይባላል፤ “ፍጥረት” በሚል ቃል ላይ ያለው መነሻ ቅጥያ “ዘ’ አያያዥ መስተዋድድ “የ” ማለት ነው፤ “የፍጥረት” ማለት ነው፤ በግዕዙ አርስት ላይ “ዘልደት” ይባላል፦
ዘፍጥረት 2፥4 እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን ባደረገ ቀን፥ በተፈጠሩ ጊዜ *”የሰማይና የምድር ልደት”* ይህ ነው።
ግዕዙ፦
ዝንቱ *”ፍጥረተ ሰማይ ወምድር”* ዘምአመ ኮነት ዕለት አንተ ባቲ ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ወምድረ።
ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦
Αὕτη ἡ βίβλος γενέσεως οὐρανοῦ καὶ γῆς, ὅτε ἐγένετο· ᾗ ἡμέρᾳ ἐποίησε Κύριος ὁ Θεὸς τὸν οὐρανὸν καὶ τὴν γῆν

“ጀነሲዋስ” γενέσεως ማለት “ልደት” ማለት ነው፤ “Genesis” የሚለው የኢንግሊዝኛው ስያሜ “ጀነሲስ” γένεσις ከሚለው ከግሪኩ ቃል የመጣ ነው፤ መቼም ሰማይና ምድር ልደት አለው ሲባል ፈጣሪ ወለደው ማለት ሳይሆን መፍጠሩን የሚያሳይ ስለሆነ ግዕዙ፦ “ፍጥረተ ሰማይ ወምድር” ማለት “የሰማይና የምድር ፍጥረት” ማለት ነው፤ “ልደት” ማለት “ፍጥረት” ማለት ስለሆነ “አዲስ ፍጥረት” የሚለውን ተክቶ “አዲስ ልደት” ተብሏል፦
2ኛ ቆሮንቶስ 5፥17 ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን *”አዲስ ፍጥረት”* ነው።
ቲቶ 3፥5 እንደ ምሕረቱ መጠን *”ለአዲስ ልደት”* γένεσις በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥

ታዲያ ኢየሱስ ልደት አልነበረውምን? ልደቱ ግን ከመንፈስ ቅዱስ በመጸነስ ነው፤ ፈጣሪ ያለ ወንድ ዘር ስለፈጠረው ልደት አለው፤ ዓለም ሳይፈጠር በነበረው የቀድሞ ዕቅዱ ከድንግል ማርያም ማህጸን ፈጠረው፦
ማቴዎስ 1፥18 የኢየሱስ ክርስቶስም *”ልደት”* γένεσις እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች።
መዝሙር 110፥3 ከአንተ ጋር ቀድሞ በኃይልህ ቀን፥ በቅዱሳን ብርሃን፥ ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ *”ከማህጸን ወለድሁህ”*። μετὰ σοῦ ἡ ἀρχὴ ἐν ἡμέρᾳ τῆς δυνάμεώς σου ἐν ταῖς λαμπρότησι τῶν ἁγίων σου· ἐκ γαστρὸς πρὸ ἑωσφόρου ἐγέννησά σε.

የተወለደው በኃይሉ ቀን ነው፤ የቅዱሳን ብርሃን በሆነው በመንፈስ ቅዱስ ነው፤ ይህ የግሪክ ሰፕቱጀንት እንጂ የማሶሬቲኩ ላይ ቃላቱ የለም። ከማርያም ማህጸን “ወለድሁህ” ማለት “ፈጠርኩ” ማለት ካልሆነ ችግር ይፈጠራል። ሃይማኖተ-አበው ላይ የቂሳሪያው ባስልዮስ “ወለደኝ” ማለት “ፈጠረኝ” ማለት ነው ብሎ ፍርጥ አድርጎ ነግሮናል፦
ሃይማኖተ-አበው ዘባስልዮስ ምዕራፍ 32 ቁጥር 18
ግዕዙ፦
*”ወለደኒ ይተረጎም በወልደ እግዚአብሔር ወብሂለ ፈጠረኒ በእንተ ትስብእቱ”*
ትርጉም፦
*”ወለደኝ” ማለት የእግዚአብሔር ልጅ ስለመሆኑ “ፈጠረኝ” ማለትም ሰው ስለ መሆኑ ይተረጎማል”*

አንዳንድ ቂሎች “መወለድ” ከአብ “መውጣት” ነው ይላሉ፤ ምነው መንፈስ ቅዱስ ከአብ የሚወጣ ነው ትሉ የለ እንዴ? ለምን መንፈስ ቅዱስን የአብ ልጅ አትሉትም? አይ “መውጣት” ማለት “መስረጽ” ነው ካላችሁ ለምንስ ወልድን ከአብ የሰረጸ ነው አትሉትም? ምክንያቱም ወልድም ከአብ የወጣ ነው ስለሚል፤ አይ መውጣት መላክ ማለት ነው ካላችሁ ጥሩ። ካልሆነ ልጅ ማለት፦ “አብን አህሎና መስሎ ከአብ ባህርይ ዘእም-ባህርይ አካል ዘእም-አካል ማለትም ከባህርይው ባህርይ ወስዶ ከአካሉ አካሉን ወስዶ ተወለደ፤ አምላክ ዘእም-አምላክ ማለትም ከአምላክ የተገኘ አምላክ” ካላችሁ ይህንን እሳቤ አይደለም ቁርኣን ባይብላችሁም አይደግፋችሁ። በዚህ ስሌት ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፦
19፥35 *ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል*፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
2፥116 *አላህም ልጅ አለው አሉ፡፡ ከሚሉት ጥራት ተገባው፡፡ አይደለም በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ሁሉም ለእርሱ ታዛዦች ናቸው*፡፡ وَقَالُوا۟ ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ وَلَدًۭا ۗ سُبْحَٰنَهُۥ ۖ بَل لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۖ كُلٌّۭ لَّهُۥ قَٰنِتُونَ
2፥117 ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ *ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን» ነው፤ ወዲያውም ይኾናል*፡፡ بَدِيعُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ይህ የኡስታዝ አቡ ዩሥራ የሃይማኖት ንጽጽር ፔጅ ነው፥ ላይክ እና ሼር በማድረግ የትምህርቱን ተደራሽነት ያስፉ!
https://www.facebook.com/Abucomparative/
ፈጣሪ ፍጡር አይደለም!

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

13፥16 *አላህ ሁለመናውን ፈጣሪ ነው*፤ እርሱም አንዱ አሸናፊው ነው፤ በል፡፡ قُلِ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ

አምላካችን አላህ የሁሉን ነገር ፈጣሪ ነው፥ አላህ በፈጣሪነቱ ላይ ፍጡርነት የሚባል የነውር እና የጎደሎ ባሕርይ የለውም። አላህ ሁለመናው ፈጣሪ ነው፥ ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን ነው» ወዲያውም ይኾናል፦
13፥16 *አላህ ሁለመናውን ፈጣሪ ነው፥ እርሱም አንዱ አሸናፊው ነው”* በል፡፡ قُلِ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ
2፥117 ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ *ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን ነው» ወዲያውም ይኾናል*፡፡ بَدِيعُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ፈጣሪ እና ፍጡር ሁለት ተቃራኒ ባሕርይ ናቸው፥ “ኢየሱስ ማህጸን ውስጥ የተፈጠረ ፍጡር ነው” ስንላቸው፥ እነርሱም ቅብል አርገው፦ “አዎ! ኢየሱስ ፍጡርም ፈጣሪም ነው” ይሉናል፦
ሃይማኖተ-አበው ስምዓት 124:19
ቄርሎስም አለ፦
“ለሊሁ ፍጡር ወለሊሁ ፈጣሪ”

ትርጉም፦
“እርሱ ፍጡር ነው እርሱ ፈጣሪ ነው”

ይህንን ስብጥር እሳቤ አዕምሮአችሁ ይቀበለዋልን? “እርሱ ፍጡር ነው እርሱ ፈጣሪ ነው” ምን ማለት ነው? ሁሉን ቻይ እና ሁሉን የማይችል፥ ሁሉን ዐዋቂ እና ሁሉን የማያውቅ” ሁለት ባሕርይ እንዴት አንድ ላይ ይዋሕዳል? “አይ ፈጣሪ ፍጡር ሆነ” ብለውን አረፉት፦
ሃይማኖተ-አበው ዘአክርስቶዶሎስ 112:31
አክርስቶዶሎስም አለ፦
“ወፈጣሪ ኮነ ፍጡረ እንተ ይእቲ እምህላዌነ ድንግል ዘበአማን ማርያም”

ትርጉም፦
“ፈጣሪ ከእኛ ባሕረይ ከተገኘች በእውነት ድንግል ከምትሆን ከማርያም ፍጡር ሆነ”

እሰይ! ይቀጥሉና፦ “ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር አብን መስሎና አህሎ ከአብ ማንነትና ምንነት የተገኘ ነው” ይሉናል። አብ ማለት “አስገኚ” ሲሆን ወልድ ደግሞ “ግኝት” ነው። በ 325 ድኅረ-ልደት”AD” የተሰበሰበው የኒቅያ ጉባኤም፦
ግሪኩ፦ Φῶς ἐκ Φωτός, Θεὸν ἀληθινὸν ἐκ Θεοῦ ἀληθινοῦ,

ግዕዙ “ብርሃን ዘምብርሃን፤ አምላክ ዘምአምላክ”

ትርጉም፦
“ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፤ ከአምላክ የተገኘ አምላክ” ብሎታል።

አምላክ አምላክን ካስገኘ ሁለት አምላክ አይሆንም ወይ? አምላክ ተገኘ የሚለው ሲያስገርም አምላክ ተፈጠረ ደግሞ ያስደምማል፦
አማርኛ፦
ምሳሌ 8፥22 *እግዚአብሔር ከሁሉ በፊት ፈጠረኝ*፥ (1980 አዲስ ትርጉም)

ግዕዝ፦
ምሳሌ 8፥22 “ፈጠረኒ እግዚእ መቅድመ ተግባሩ”

ኢንግሊሽ፦
Proverbs 8፥22 “The LORD made me as he began his planning, (International Standard Version)

ዕብራይስጥ፦
ምሳሌ 8፥22 יְהוָה–קָנָנִי, רֵאשִׁית דַּרְכּוֹ: קֶדֶם מִפְעָלָיו מֵאָז.

ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦
Proverbs 8፥22 κύριος ἔκτισέν με ἀρχὴν ὁδῶν αὐτοῦ εἰς ἔργα αὐτοῦ

በተለይ በግሪኩ ሰፕቱአጀንት”LXX” ላይ “ኪትዞ” ἔκτισέν ማለት “ፈጠረኝ” ማለት ነው፤ በተመሳሳይ ዕብራይስጡ “ቃናኒ” קָ֭נָנִי ማለት “አስገኘኝ” ማለት ነው፤ ይህ ቃል ሔዋን “አገኘሁ” ብላ ለተጠቀመችበት የዋለው ቃል “ቃኒቲ” קָנִ֥יתִי ሲሆን ዳዊት ደግሞ ኲላሊቴን “ፈጥረሃል” ለሚለው የተጠቀመው “ቃኒታ” קָנִ֣יתָ ብሎ ነው፦
ዘፍጥረት 4፥1 ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር *አገኘሁ* קָנִ֥יתִי አለች።
መዝሙር 139፥13 አቤቱ፥ አንተ ኵላሊቴን *ፈጥረሃልና* קָנִ֣יתָ ፥
ዘዳግም 32፥6፤ ለእግዚአብሔር ይህንን ትመልሳለህ? የገዛህ አባትህ አይደለምን? *የፈጠረህ* קָּנֶ֔ךָ እና ያጸናህ እርሱ ነው።

የመጨረሻው ጥቅስ ላይ “የፈጠረክ” ለሚለው የገባው “ቃነካ” קָּנֶ֔ךָ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። እግዚአብሔር “የገዛህ አባትህ” መባሉ “አባት” ማለት ለእግዚአብሔር ፈጣሪ ማለት እንደሆነ ይህ ጥቅስ ያስረዳል።
እንግዲህ “መገኘት” እና “መፈጠር” ተለዋዋጭ ቃል ከሆነ ኢየሱስ ፍጡር እና ግኝት እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል። ይህንን ጥቅስ ተሃድሶና እና ፕሮቴስታት ስለ ኢየሱስ አይደለም ብለው ሽምጥጥ አርገው ቢክዱም፤ ቀደምት ኦርቶዶክስ፣ካቶሊክ፣ አንግሊካን እና የኒቂያ ጉባኤ ስለ ኢየሱስ ፍጥረት ሳይፈጠር መወለዱን ያሳያል ይላሉ፤ በ 325 AD በኒቂያ ጉባኤ አርዮስንና አትናቲዎስ ኢየሱስ ፍጡር ነው ወይስ አይደለም ለሚለው ክርክራቸው ይህ ጥቅስ ነበር፤ አንዳንድ ኦርቶዶክሳውያንም ይህ ስለ ኢየሱስ አይደለም ብለው ሊያቅማሙ ሲሞክሩ አንድምታው ሆነ ሃይማኖተ-አበው አጋልጧቸዋል፤ ቄርሎስ በሃይማኖተ-አበው ላይ ለኢየሱስ ነው ይለናል፦
ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 76:12
ቄርሎስም አለ፦
“ተፈጥረ ጥበብ ዘውእቱ ቃል”

ትርጉም፦
*“ጥበብ ተፈጠረ ይኸውም ቃል ነው”*

ቄርሎስም አለ፦
“ወይእዜኒ ጥበብ ትቤ ፈጠረኒ እግዚእ መቅድመ ተግባሩ”

ትርጉም፦
*“ከፍጥረት አስቀድሞ የነበርኩኝ በቀድሞ ተግባሩ ጌታ ፈጠረኝ አለች”*

የመቃብያን ጸሐፊም ሰሎሞን በምሳሌ መጽሐፍ ላይ ስለ ኢየሱስ፦ “ዛሬም የሚታየው ሁሉ ሳይታይ ዛሬም የሚጠራው ስም ሁሉ ሳይጠራ ፈጠረኝ” ማለቱን ተናግሯል፦
3ኛ መቃብያን 4፥18 ሰሎሞን ፦ *“ዛሬም የሚታየው ሁሉ ሳይታይ ዛሬም የሚጠራው ስም ሁሉ ሳይጠራ ፈጠረኝ”* ብሎ ተናገረ፤

እንግዲህ አባት ማለት “አስገኚ” ወይም “ፈጣሪ” መሆኑን እንዲሁ ልጅ ማለት “ተገኚ” ወይም “ፍጡር” መሆኑን ካየን ዘንዳ ኢየሱስ በየትኛው መልኩ ፍጡር ነው።
የዓለማቱ ጌታ አላህ ጌታችሁ ነው፥ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው፤ እርሱን በብቸኝነት አምልኩት፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነውና፦
6፥102 ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ *ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው፤ ስለዚህ አምልኩት*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ ۖ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ فَاعْبُدُوهُ ۚ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዒሣ ወፍ ፈጥሯልን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

46፥4 በል *ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን አያችሁን? ከምድር ምንን እንደ ፈጠሩ አሳዩኝ"*። قُلْ أَرَءَيْتُم مَّا تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَرُونِى مَاذَا خَلَقُوا۟ مِنَ ٱلْأَرْضِ أَمْ لَهُمْ شِرْكٌۭ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ

አሏህ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው፥ ከአሏህ ሌላ ፈጣሪ የለም። ከአሏህ ሌላ ያለ ማንነት ሆነ ምንነት ትንሿን ዝንብ እንኳን መፍጠር አይችሉም፦
46፥4 በል *ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውን አያችሁን? ከምድር ምንን እንደ ፈጠሩ አሳዩኝ"*። قُلْ أَرَءَيْتُم مَّا تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَرُونِى مَاذَا خَلَقُوا۟ مِنَ ٱلْأَرْضِ أَمْ لَهُمْ شِرْكٌۭ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ
22:73 እላንተ ሰዎች ሆይ! አስደናቂ ምስሌ ተገለጸላችሁ ለእርሱም አድምጡት። *እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ዝምብን ፈጽሞ አይፈጥሩም። ለእርሱ ለመፍጠር ቢሰበስቡም እንኳ አይችሉም አንዳችንም ነገር ዝንቡ ቢነጥቃቸው ከእርሱ አያስጥሉትም ፈላጊውም ተፈላጊውም ደከሙ"*። يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ ضُرِبَ مَثَلٌۭ فَٱسْتَمِعُوا۟ لَهُۥٓ ۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ لَن يَخْلُقُوا۟ ذُبَابًۭا وَلَوِ ٱجْتَمَعُوا۟ لَهُۥ ۖ وَإِن يَسْلُبْهُمُ ٱلذُّبَابُ شَيْـًۭٔا لَّا يَسْتَنقِذُوهُ مِنْهُ ۚ ضَعُفَ ٱلطَّالِبُ وَٱلْمَطْلُوبُ

አሏህ ከአለመኖር ወደ መኖር የሚፈጥር እርሱ ብቻ እንደሆነ እና ከአላህ ውጪ ዝንብን እንኳን መፍጠር የሚችል ፈጣሪ ከሌለ ካየን ዘንዳ፥ ታዲያ ዒሣ እንዴት ወፍ ሊፈጥር ቻለ? በቁርኣን ውስጥ ዒሣ ወፍ ፈጠረ የሚል አንቀጽ የለም፦
3፥49 ወደ እስራኤልም ልጆች መልክተኛ ያደርገዋል፡፡ ይላልም፡- *"እኔ ከጌታዬ በተአምር ወደ እናንተ መጣሁላችሁ፡፡ እኔ ለናንተ ከጭቃ እንደ ወፍ ቅርፅ እፈጥራለሁ፡፡ በእርሱም እተነፍስበታለሁ፡፡ በአላህም ፈቃድ ወፍ ይኾናል"*፡፡ وَرَسُولًا إِلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنِّي قَدْ جِئْتُكُم بِآيَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ ۖ أَنِّي أَخْلُقُ لَكُم مِّنَ الطِّينِ كَهَيْئَةِ الطَّيْرِ فَأَنفُخُ فِيهِ فَيَكُونُ طَيْرًا بِإِذْنِ اللَّهِ


ነጥብ አንድ
“ተአምር”
አንቀፁ ላይ ዒሣ፦ ”እኔ ከጌታዬ "በተአምር” መጣሁላችሁ” ይላል፥ ይህ የሚያሳየው ከዛ በኃላ የሚያደርጋቸው ሥራዎች ለነብይነቱ ማስረጃ ተአምር ነው። ምክንያቱም ሙሣም፦ "ከጌታችሁ በተዓምር በእርግጥ መጣሁላችሁ" ብሎ ይናገረዋል፦
7፥105 «በአላህ ላይ ከእውነት በቀር አለመናገር ተገቢዬ ነው፡፡ *"ከጌታችሁ በተአምር በእርግጥ መጣሁላችሁ"*፡፡ የእስራኤልንም ልጆች ከእኔ ጋር ልቀቅ፡፡ حَقِيقٌ عَلَىٰ أَن لَّا أَقُولَ عَلَى اللَّهِ إِلَّا الْحَقَّ ۚ قَدْ جِئْتُكُم بِبَيِّنَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ فَأَرْسِلْ مَعِيَ بَنِي إِسْرَائِيلَ

እዚሁ ዐውደ-ንባብ ላይ ሙሣ የመጣበት ተአምር ግዑዝ የነበረውን በትር ሕይወት ወዳለው እባብ ማድረግ ነው፦
7፥106 ፈርዖንም፦ *"በተአምር የመጣህ እንደኾንክ ከእውነተኞቹ ከኾንክ እርሷን አምጣት"* አለው፡፡ قَالَ إِن كُنتَ جِئْتَ بِآيَةٍ فَأْتِ بِهَا إِن كُنتَ مِنَ الصَّادِقِينَ
7፥107 *"በትሩንም ጣለ፡፡ እርስዋም ወዲያውኑ ግልጽ እባብ ኾነች"*፡፡ فَأَلْقَىٰ عَصَاهُ فَإِذَا هِيَ ثُعْبَانٌ مُّبِينٌ

ታዲያ የቱ ተአምር ይበልጣል? የወፍ ቅርፅ መሥራት ወይስ በትር እባብ ማድረግ? እባብም ሆነ ወፍ እንስሳ ናቸው፥ ልዩነቱ በትሩን እባብ ያደረገው ሆነ የጭቃውን ቅርፅ ወፍ ያደረገው አላህ መሆኑ ነው። ሙሣም እባብ ዒሣም ወፍ አልፈጠሩም። ለሙሣ ነብይነት ሆነ ለዒሣ ነብይነት የተሰጣቸው ታምር ከራሳቸው ያገኙት ሳይሆን ከአላህ የተሰጣቸው ተአምራት ነው፦
2፥87 *"የመርየምን ልጅ ዒሳንም ግልጽ ተአምራትን ሰጠነው"*፡፡ وَآتَيْنَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ الْبَيِّنَاتِ
4፥101 *"ለሙሳም ግልጽ የኾኑን ዘጠኝ ተአምራትን በእርግጥ ሰጠነው"*፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَىٰ تِسْعَ آيَاتٍ بَيِّنَاتٍ

ዒሣም የሠራውን እና እፍ ያለበትን ቅርፅ አሏህ ወፍ ሲያረግለት የደመደመው "እኔ ወፍ ፈጠርኩኝ" ብሎ ሳይሆን "በዚህ ውስጥ በእርግጥ ተዓምር አለበት" በማለት ደምድሟል፦
4፥49 *"ምእመናን እንደኾናችሁ ለእናንተ በዚህ ውስጥ በእርግጥ ተዓምር አለበት"*፡፡ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ
ነጥብ ሁለት
"እፈጥራለሁ"
“አኽሉቁ” أَخْلُقُ ማለት "እፈጥራለሁ" ማለት ሲሆን "እቀርጻለው" በሚል ይመጣል፥ ነቢያችን”ﷺ” በቁርኣን ከተሰጣቸው አንዱ አንድ ቃላት ሰፊ ትርጉም ነው። ይህም “ጀዋሚዓል ከሊም” ነው፥ “ጀዋሚዓል ከሊም” جَوَامِعَ الْكَلِم ማለት “አንድ ቃል ሆኖ ብዛት ትርጉም ያለው” ማለት ነው። ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ አሳብና ትርጉም አለው ማለት አይደለም፥ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጉም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው። መታየት ያለበት ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው አሳብ ነው፥ ለምሳሌ፦
23፥14 *ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ*፡፡ فَتَبَارَكَ اللَّهُ أَحْسَنُ الْخَالِقِينَ

“ሰዓሊዎች” ለሚለው ቃል የገባው “ኻሊቂን” خَالِقِين ሲሆን “ሙሶዊሪን” مُصَوِّرِين ማለት ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 37, ሐዲስ 150
ዐብደላህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”በትንሳኤ ቀን ከሰዎች በጣም ተቀጪ ሰዓሊዎች ናቸው”*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِنَّ أَشَدَّ النَّاسِ عَذَابًا يَوْمَ الْقِيَامَةِ الْمُصَوِّرُونَ ‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 182
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”የስዕላት ባለቤት በትንሳኤ ቀን ይቀጣሉ፥ ለእነርሱም፦ “የፈጠራችሁትን ሕያው አድርጉ” ይባላሉ”*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ إِنَّ أَصْحَابَ هَذِهِ الصُّوَرِ يُعَذَّبُونَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ، وَيُقَالُ لَهُمْ أَحْيُوا مَا خَلَقْتُمْ

“ሙሶዊር” مُصَوِّر ማለት “ቀራፅ” “ሰዓሊ” “ሠሪ” “ፈጣሪ” ማለት ሲሆን የሙሶዊር ብዙ ቁጥር ደግሞ “ሙሶዊሩን” مُصَوِّرُون ወይም “ሙሶዊሪን” مُصَوِّرِين ሲሆን “ቀራፆች” “ሰዓሊዎች” ማለት ነው፥ “የፈጠራችሁትን” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ኸለቅቱም” خَلَقْتُمْ ሲሆን አሏህ ሰዓሊዎችን፦ "የፈጠራችሁትን" ማለቱ "የሳላችሁትን" ወይም "የቀረፃችሁን" ለማለት እንጂ ከሕይወት አልባነት ወደ ሕይወት የፈጠራችሁን ማለት በፍጹም እንዳልሆነ ሁሉ ዒሣም ሕይወት ያለው ወፍ በፍጹም አልፈጠረም፦
57፥27 *"አዲስ የፈጠሩዋትንም* ምንኩስና በእነርሱ ላይ አልጻፍናትም፡፡ ግን የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ ፈጠሩዋት፡፡ ተገቢ አጠባበቋንም አልጠበቋትም"*፡፡ وَرَهْبَانِيَّةً ابْتَدَعُوهَا مَا كَتَبْنَاهَا عَلَيْهِمْ إِلَّا ابْتِغَاءَ رِضْوَانِ اللَّهِ فَمَا رَعَوْهَا حَقَّ رِعَايَتِهَا

እዚህ አንቀጽ ላይ ክርስቲያኖች ምንኩስና እንደፈጠሩ ለማሳየት አምላካችን አሏህ፦ "የፈጠሩዋትን" "ፈጠሩዋት" በማለት ይናገራል፥ ያ ማለት ክርስቲያኖች አዲስ አሳብ እና ምናብ ማምጣታቸውን ያሳያል እንጂ ሕያው ኑባሬ መፍጠራቸውን እንደማያሳይ ሁሉ ዒሣ ቅርፅ ስለፈጠረ ሕይወት ፈጠረ አያሰኝም። “ሀይኣህ” هَيْـَٔة ማለት “ቅርፅ” ማለት ከሆነ “አኽሉቁ” أَخْلُقُ ማለት "እቀርጻለው" ማለት ነው። አንድ ቃል ሁሌ በተመሳሳይ ትርጉም መረዳት ስሑት ተፋልሶ"Fallacy of equivocation" ነው።

ነጥብ ሦስት
"በአሏህ ፈቃድ"
"ወፍ" ማለት እና "የወፍ ቅርፅ" ማለት ሁለት ለየቅል ነገሮች ናቸው፥ በመርካቶ አዳራሽ ውስጥ በሰው ፈጠራ የሰው ቅርፅ ተሠርቷል። ግን ያ የሰው ቅርፅ ሕይወት የለውም፥ በውስጡ እፍ ማለትም እንችላለን። ቅሉ ግን የሰው ቅርፅ መሥራታችን እፍ ማለታችን ቅርፁን ሰው አያረገውም፥ አምላካችን አሏህ ግን ለነቢዩ ዒሣ ነቢይነት ተአምር እንዲሆን ዒሣ የሠራውን እና እፍ ያለበትን ቅርፅ በራሱ ፈቃድ ወፍ አድርጎታል። “ቢኢዝኒሏህ” بِإِذْنِ اللَّهِ ማለት "በአሏህ ኃይል"in the empowerment of Allah" ማለት ነው፥ ይህም ቅርፁን ወፍ ያደረገው አሏህ ብቻ መሆኑን ቁልጭ እና ፍንትው አድርጎ ያሳያል። "አል-ፋጢር" الفَاطِر ከአሏህ ስሞች አንዱ ሲሆን "ፈጣሪው" ማለት ነው፦
6፥14 *«ሰማያትንና ምድርን "ፈጣሪ" ከኾነው አላህ እርሱ የሚመግብ የማይመገብም ሲኾን ሌላን አምላክ እይዛለሁን?»* በላቸው፡፡ قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَتَّخِذُ وَلِيًّۭا فَاطِرِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَهُوَ يُطْعِمُ وَلَا يُطْعَم

ይህ በግስ መደብ “ፈጠረ” فَطَرَ ሲሆን ይህ ቃል ለፍጡራን አግልግሎት ላይ የዋለበት ጥቅስ የለም። ከላይ ያቀረብነውን የቋንቋ፣ የሰዋስው እና የዐውድ ሙግት አልገባህ ካላችሁ ይህን ለማስረዳት ከባይብል የቋንቋ ሙግት ላቅርብ፦
ኤርምያስ 10፥16 *"የያዕቆብ እድል ፈንታ እንደ እነዚህ አይደለም፥ እርሱ የሁሉ ”ፈጣሪ" יוֹצֵ֤ר ነውና"*

እዚህ አንቀጽ ላይ “ፈጣሪ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል በዕብራይስጡ “ዮውጸር” יוֹצֵ֤ר ሲሆን ትርጉሙ “ፈጣሪ” ወይም “ሠሪ” ሲሆን ለሰዎች ቃሉ ውሏል፦
መዝሙር 2፥9 በብረት በትር ትጠብቃቸዋለህ፥ እንደ ሸክላ *”ሠሪ”* יוֹצֵ֣ר ዕቃዎች ትቀጠቅጣቸዋለህ።

ሸክላን የሚሠሩ ሰዎች “ዮውጸር” יוֹצֵ֤ר ማለትም "ሠሪ" ወይም "ፈጣሪ" ስለተባሉ አንዱ አምላክ በተባለበት ስሌት እና ቀመር ነውን? እነርሱም ፦ምን ነካህ ወሒድ? ማየት ያለብህ ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው አሳብን እና ዓረፍተ-ነገር ነው" ይሉኛል። እንግዲያውስ ከላይ ያለውንም የቁርኣን ቃል በዚህ ልክና መልክ ተረዱት! አሏህ ቅኑን መንገድ ይምራችሁ! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መተት

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

17፥47 እኛ ወደ አንተ በሚያዳምጡ ጊዜ እነርሱም በሚንሾካሾኩ ጊዜ በዳዮች እርስ በርሳቸው *”የተደገመበትን ሰው እንጂ አትከተሉም በሚሉጊዜ”* በእርሱ የሚያዳምጡበትን ምክንያት ዐዋቂ ነን፡፡ نَّحْنُ أَعْلَمُ بِمَا يَسْتَمِعُونَ بِهِۦٓ إِذْ يَسْتَمِعُونَ إِلَيْكَ وَإِذْ هُمْ نَجْوَىٰٓ إِذْ يَقُولُ ٱلظَّٰلِمُونَ إِن تَتَّبِعُونَ إِلَّا رَجُلًۭا مَّسْحُورًا

“ዒስማ” عِصْمَة‌‎ ማለት ከኃጢያት “ጥበቃ”protection” ማለት ሲሆን “ማዕሱም” معصوم‌‎ ደግሞ ከኃጢያት የሚጠበቀው ነብይ ነው፤ ኃጢያት በሁለት ይከፈላል፦
“ከባኢር” كبائر ማለት “አበይት ኃጢያት”ሲሆን እነርሱም፦ ሺርክ፣ ዝሙት፣ አራጣ፣ ቁማር፣ ቅጥፈት፣ ሌብነት ወዘተ..ናቸው።
“ሰጋኢር” صغائر ማለት “ንዑሳን ኃጢያት” ሲሆኑ በአለማወቅ አሊያም በአለፍፅምና የሚመጡ ስህተት ናቸው፤ ለምሳሌ መናደድ፣ መቆጣት፣ ማዘን፣ መበሳጨት ወዘተ፦
53፥32 እነዚያ የኃጢያትን “ታላላቆችና” አስጠያፊዎቹን የሚርቁ ናቸው፤ ግን “ትናንሾቹ” የሚማሩ ናቸው። ጌታህ ምሕረተ ሰፊ ነውና፤ ٱلَّذِينَ يَجْتَنِبُونَ كَبَٰٓئِرَ ٱلْإِثْمِ وَٱلْفَوَٰحِشَ إِلَّا ٱللَّمَمَ ۚ إِنَّ رَبَّكَ وَٰسِعُ ٱلْمَغْفِرَةِ
4፥31 ከእርሱ ከተከለከላችሁት “ታላላቆቹን” ብትርቁ “ትናንሾቹን ኃጢአቶቻችሁን” ከእናንተ እናብሳለን፤ የተከበረንም ስፍራ እናገባችኋለን፡፡ إِن تَجْتَنِبُوا۟ كَبَآئِرَ مَا تُنْهَوْنَ عَنْهُ نُكَفِّرْ عَنكُمْ سَيِّـَٔاتِكُمْ وَنُدْخِلْكُم مُّدْخَلًۭا كَرِيمًۭا
42፥37 ለእነዚያም “የኀጢያትን ታላላቆችና” ጠያፎችን የሚርቁ በተቆጡም ጊዜ እነርሱ የሚምሩ ለሆኑት። وَٱلَّذِينَ يَجْتَنِبُونَ كَبَٰٓئِرَ ٱلْإِثْمِ وَٱلْفَوَٰحِشَ وَإِذَا مَا غَضِبُوا۟ هُمْ يَغْفِرُونَ

እንግዲያውስ በኢስላም ነብያት የሚጠበቁት ከአበይት ኃጢያት ነው፤ ከንዑሳን ኃጢያት እንደማንኛውም ሰው አለፍፅምና ስላለባቸው በራሳቸው ሆነ በሰይጣን ሊሳሳቱ ይችላሉ፤ ለምሳሌ አደም ነብይ ነው፤ ግን ሰይጣን ወደ እርሱ ጎትጉቶት የጌታውን ትእዛዝ ጣሰ፤ ተሳሳተም፦
20፥120 ሰይጣንም ወደ እርሱ ጎተጎተ «አደም ሆይ! በመዘውተሪያ ዛፍ በማይጠፋ ንግሥናም ላይ ላመላክትህን አለው፡፡ فَوَسْوَسَ إِلَيْهِ ٱلشَّيْطَٰنُ قَالَ يَٰٓـَٔادَمُ هَلْ أَدُلُّكَ عَلَىٰ شَجَرَةِ ٱلْخُلْدِ وَمُلْكٍۢ لَّا يَبْلَىٰ
20፥121 ከእርሷም በሉ፡፡ ለእነርሱም ኀፍረተ ገላቸው ተገለጸች፡፡ ከገነትም ቅጠል በላያቸው ላይ ይለጥፉ ጀመር፡፡ *”አደምም የጌታውን ትእዛዝ ጣሰ፤ ተሳሳተም”*፡፡ فَأَكَلَا مِنْهَا فَبَدَتْ لَهُمَا سَوْءَٰتُهُمَا وَطَفِقَا يَخْصِفَانِ عَلَيْهِمَا مِن وَرَقِ ٱلْجَنَّةِ ۚ وَعَصَىٰٓ ءَادَمُ رَبَّهُۥ فَغَوَىٰ

በተመሳሳይ ሰይጣን ኢዮብን በጉዳትና በስቃይ ጎድቶታል፤ እንደ ባይብሉም ከእግሩ ጫማ ጀምሮ እስከ አናቱ ድረስ በክፉ ቍስል መቶታል፤ ይህ ሲደረግ ሰይጣንን እግዚአብሔርም ሕይወቱን ተወው እንጂ እርሱ በእጅህ ነው አለው፦
38፥41 ባሪያችንን አዩብንም አውሳላቸው፡፡ *«እኔ ሰይጣን በጉዳትና በስቃይ ነካኝ»* ሲል ጌታውን በተጣራ ጊዜ፡፡ وَٱذْكُرْ عَبْدَنَآ أَيُّوبَ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُۥٓ أَنِّى مَسَّنِىَ ٱلشَّيْطَٰنُ بِنُصْبٍۢ وَعَذَابٍ
ኢዮብ 2፥6-7 እግዚአብሔርም ሰይጣንን ሕይወቱን ተወው እንጂ እነሆ፥ እርሱ በእጅህ ነው አለው። ሰይጣንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጣ፥ ኢዮብንም ከእግሩ ጫማ ጀምሮ እስከ አናቱ ድረስ በክፉ ቍስል መታው።

እንዲሁ ሰይጣን ዳዊትን፦ “ሂድ፥ እስራኤልንና ይሁዳን ቍጠር” ብሎ አዞት ቆጥሯል፦
2ኛ ሳሙኤል 24.1 ደግሞም የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ ዳዊትንም፦ *ሂድ፥ እስራኤልንና ይሁዳን ቍጠር* ብሎ በላያቸው አስነሣው።
1ኛ ዜና መዋዕል 21፥1 ሰይጣንም በእስራኤል ላይ ተነሣ፥ እስራኤልንም ይቈጥር ዘንድ ዳዊትን “አንቀሳቀሰው”።

በተመሳሳይ ሰይጣን ኢየሱስን ወደ ከተማና ወደ ተራራ እየወሰደ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም ያሳየው ነበር፦
ማቴዎስ 4፥5 ከዚህ በኋላ *”ዲያቢሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደው”* እና እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ።
ማቴዎስ 4፥8 ደግሞ *”ዲያቢሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው”*፥ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ።
ሉቃስ 4:13 ዲያቢሎስም ፈተናውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ *”እስከ ጊዜው ከእርሱ ተለየ”*።

“እስከ ጊዜው ከእርሱ ተለየ” የሚለው ይሰመርበት፤ ሰይጣን ከኢየሱስ ከመለየቱ በፊት ከኢየሱስ ጋር ነበር ማለት ነው፤ የተለየውም ለጊዜው እንደሆነ ተጽፏል፤ ሰይጣን ይህ ሁሉ ነገር በነብያቱ ላይ ሲፈፀም አምላክ እንዴት ዝም አለ? አይ ፈጣሪ ዝም የሚልበት የራሱ ጥበብ አለው ከሆነ መልሱ እንግዲያውስ ነብያችን”ﷺ” በድግምት ተፅእኖ ቢደርስባቸው ምኑ ያስደንቃል? እስቲ ስለ መተት ተፅዕኖ በሁለቱም መጽሐፍት እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
“መተት በቁርአን”
ስለ መተት በቁርአን ያለው እሳቤ እንመልከት፤ “ሲሕር” سِحْر የሚለው ቃል “ሰሐረ” سحر ማለትም “ደገመ” ከሚል ስርወ-ግንድ የረባ ሲሆን “ድግምት” “መተት” “አስማት” ማለት ነው፤ ድግምቱን የሚሰራው ሰው ደግሞ “ሳሒር” سَٰحِر ይባላል፤ “ሱሑር” سحور ማለትም በረመዳን ፆም ለመያዝ ከሌሊቱ መጨረሻ የሚመገቡት ምግብ እና “ሰሐር” سَحَر ማለትም “የሌሊት መጨረሻ”before down” የሚሉት ሁለቱ ቃላት ልክ እንደ ሲሕር “ሰሐረ” سحر ከሚለው ስርወ-ግንድ የመጡ ናቸው።
በባቢሎት በሚገኙት በሀሩትና በማሩት ላይ የተወረደው የሲሕር ትምህርት ሰዎችን እንዴት እንደሚጎዳ ማስጠንቀቂያ ሆኖ ነው፤ ነገር ግን ሰይጣናትም በሱለይማን ዘመነ መንግስት ሰዎችን የሚያስተምሩት ለአሉታዊ ነገር ነበር፦
2፥102 ሰይጣናትም በሱለይማን ዘመነ መንግስት የሚያነቡትን ተከተሉ፡፡ ሱለይማንም አልካደም፤ ግን ሰይጣናት ሰዎችን ድግምትን የሚያስተምሩ ሲኾኑ ካዱ፡፡ ያንንም በባቢል በሁለቱ መላእክት በሃሩትና ማሩት ላይ የተወረደውን ነገር ያስተምሩዋቸዋል፡፡ «እኛ መፈተኛ ነንና አትካድ» እስከሚሉም ድረስ አንድንም አያስተምሩም፡፡ ከእነሱም በሰውየውና በሚስቱ መካከል በርሱ የሚለዩበትን ነገር ይማራሉ፡፡ وَٱتَّبَعُوا۟ مَا تَتْلُوا۟ ٱلشَّيَٰطِينُ عَلَىٰ مُلْكِ سُلَيْمَٰنَ ۖ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَٰنُ وَلَٰكِنَّ ٱلشَّيَٰطِينَ كَفَرُوا۟ يُعَلِّمُونَ ٱلنَّاسَ ٱلسِّحْرَ وَمَآ أُنزِلَ عَلَى ٱلْمَلَكَيْنِ بِبَابِلَ هَٰرُوتَ وَمَٰرُوتَ ۚ وَمَا يُعَلِّمَانِ مِنْ أَحَدٍ حَتَّىٰ يَقُولَآ إِنَّمَا نَحْنُ فِتْنَةٌۭ فَلَا تَكْفُرْ ۖ فَيَتَعَلَّمُونَ مِنْهُمَا مَا يُفَرِّقُونَ بِهِۦ بَيْنَ ٱلْمَرْ
ءِ وَزَوْجِهِۦ

ሲሕር በግብጻውያን ዘንድ በጣም የታወቀ ስራ ነው፤ የግብጻውያን ሳሒሪን ዘንጎቻቸውን ወደ እባብ በመቀየት የሰዎች ዓይኖች ላይ ደግመውባቸው ነበር፦
20፥66 «አይደለም ጣሉ» አላቸው፡፡ ወዲያውም ገመዶቻቸውና ዘንጎቻቸው *”ከድግምታቸው የተነሳ እነርሱ የሚሮጡ እባቦች ኾነው ወደ እርሱ ተመለሱ”*፡፡ قَالَ بَلْ أَلْقُوا۟ ۖ فَإِذَا حِبَالُهُمْ وَعِصِيُّهُمْ يُخَيَّلُ إِلَيْهِ مِن سِحْرِهِمْ أَنَّهَا تَسْعَىٰ
7፥116 «ጣሉ» አላቸው፡፡ በጣሉም ጊዜ *”የሰዎቹን ዓይኖች ደገሙባቸው”*፡፡ አስፈራሩዋቸውም፡፡ *ትልቅ ድግምትንም”* አመጡ፡፡ قَالَ أَلْقُوا۟ ۖ فَلَمَّآ أَلْقَوْا۟ سَحَرُوٓا۟ أَعْيُنَ ٱلنَّاسِ وَٱسْتَرْهَبُوهُمْ وَجَآءُو بِسِحْرٍ عَظِيمٍۢ

ትእይንቱን ከሚከታተሉት እና አይኖቻቸው የሚቀጣጥፉትን የድግምተኛ ተንኮል ካዩት መካከል ሙሳ በነፍሱ ውስጥ ፍርሃትን አሳደረ፦
20፥67 ሙሳም *”በነፍሱ ውስጥ ፍርሃትን አሳደረ”*፡፡ فَأَوْجَسَ فِى نَفْسِهِۦ خِيفَةًۭ مُّوسَىٰ

ነገር ግን አላህ ሲሕር ሲሰራ ዝም ማለቱ ለሲሕሩ ማክሸፈያ ሊያመጣ መሆኑን ያሳያል፤ የሙሳ በትር የሚቀጣጥፉትን ዘንግ ውጣዋለች፦
20፤69 «በቀኝ እጅህ ያለቸውንም በትር ጣል፡፡ ያንን የሠሩትን ትውጣለችና፡፡ *”ያ የሠሩት ሁሉ የድግምተኛ ተንኮል ነውና”*፡፡ ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም» አልን፡፡ وَأَلْقِ مَا فِى يَمِينِكَ تَلْقَفْ مَا صَنَعُوٓا۟ ۖ إِنَّمَا صَنَعُوا۟ كَيْدُ سَٰحِرٍۢ ۖ وَلَا يُفْلِحُ ٱلسَّاحِرُ حَيْثُ أَتَىٰ
7፥117 ወደ ሙሳም፡- «በትርህን ጣል» ስንል ላክን፡፡ ጣላትም ወዲያውኑም *”የሚቀጣጥፉትን ትውጣለች”*፡፡ وَأَوْحَيْنَآ إِلَىٰ مُوسَىٰٓ أَنْ أَلْقِ عَصَاكَ ۖ فَإِذَا هِىَ تَلْقَفُ مَا يَأْفِكُونَ

በተመሳሳይ ነብያችን”ﷺ” ላይ ሲሕር ተደርጎባቸው ነበር፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 80 , ሐዲስ 86:
ዓኢሻ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” በድግምት ተፅእኖ ደርሶባቸው ነበር፤ ያላደረጉትን እንዳደረጉ ያስቡ ነበር፤ عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم طُبَّ حَتَّى إِنَّهُ لَيُخَيَّلُ إِلَيْهِ قَدْ صَنَعَ الشَّىْءَ وَمَا صَنَعَهُ،

አላህም ለሲሕሩ ማክሸፈያ “አል-ሙዐወዘተይን” الْمُعَوِّذَتَيْن የሚባሉት ሁለቱ ሱራዎች ሱረቱል ፈለቅ እና ሱረቱ አን-ናስ አውርዷል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 6 , ሐዲስ 319:
የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ ዛሬ ምን አስደናቂ አንቀጾች ዛሬ ወርደዋል፤ ይህም ብጤአቸው ታይቶ አያውቅም! እነርሱም፦ “በል «በተፈልቃቂው ጎህ ጌታ እጠበቃለሁ” እና በል «በሰዎች ፈጣሪ እጠበቃለሁ» ናቸው። قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ أَلَمْ تَرَ آيَاتٍ أُنْزِلَتِ اللَّيْلَةَ لَمْ يُرَ مِثْلُهُنَّ قَطُّ ‏{‏ قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ الْفَلَقِ‏}‏ وَ ‏{‏ قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ النَّاسِ‏}‏ ‏”‏

ታላቁ ሙፈሲር ኢብኑ ከሲር ስለ “አል-ሙዐወዘተይን” ሲናገር፦ “በሌላ ሐዲስ እንደተዘገበው፦ “ጂብሪል ወደ ነብዩ”ﷺ” መጥቶ እንዲህ አላቸው፦ “ሙሐመድ”ﷺ” ሆይ በማንኛውም ህመም እየተሰቃየህ ነውን? ነብዩም”ﷺ” ነዐም ብለው መለሱ፤ ጂብሪልም በአላህ ስም ሩቂያ እቀራብሃለው፤ ከማንኛውም በሽታ አንተን የጎዳህን፤ ከእያንዳንዱ ሸረኛ እና ክፉ ዓይን፤ አላህ ይፈውስሃል”።
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 10 , ሐዲስ 8:
“ጂብሪል ወደ ነብዩ”ﷺ” መጥቶ እንዲህ አላቸው፦ “ሙሐመድ”ﷺ” ሆይ በማንኛውም ህመም እየተሰቃየህ ነውን? ነብዩም”ﷺ” ነዐም ብለው መለሱ፤ ጂብሪልም በአላህ ስም ሩቂያ እቀራብሃለው፤ ከማንኛውም በሽታ አንተን የጎዳህን፤ ከእያንዳንዱ ሸረኛ እና ክፉ ዓይን፤ አላህ ይፈውስሃል”። أَنَّ جِبْرِيلَ، أَتَى النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ يَا مُحَمَّدُ اشْتَكَيْتَ قَالَ ‏ “‏ نَعَمْ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ بِاسْمِ اللَّهِ أَرْقِيكَ مِنْ كُلِّ شَيْءٍ يُؤْذِيكَ مِنْ شَرِّ كُلِّ نَفْسٍ وَعَيْنِ حَاسِدٍ بِاسْمِ اللَّهِ أَرْقِيكَ وَاللَّهُ يَشْفِيكَ ‏.‏
.
“አል-ሙዐወዘተይን” እራሱ ለሲሕር “ሩቂያ” رقيّة ነው፤ ሩቂያ ማለት “ፈውስ” ማለት ሲሆን የቁርአን አናቅፅ መድሃኒት ነው፦
17:82 “ከቁርአንም” ለምእመናን ”መድኀኒት” እና እዝነት የሆነን ”እናወርዳለን”፤በዳዮችንም ከሳራን እንጂ ሌላን አይጨምርላቸውም። وَنُنَزِّلُ مِنَ ٱلْقُرْءَانِ مَا هُوَ شِفَآءٌۭ وَرَحْمَةٌۭ لِّلْمُؤْمِنِينَ ۙ وَلَا يَزِيدُ ٱلظَّٰلِمِينَ إِلَّا خَسَارًۭا
10:57 እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ግሳጼ ”በደረቶች” ውስጥም ላለው በሽታ “”መድኃኒት”” ለምእምናንም ብርሃንና እዝነት በእርግጥ “መጣችላችሁ”፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ قَدْ جَآءَتْكُم مَّوْعِظَةٌۭ مِّن رَّبِّكُمْ وَشِفَآءٌۭ لِّمَا فِى ٱلصُّدُورِ وَهُدًۭى وَرَحْمَةٌۭ لِّلْمُؤْمِنِينَ
የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” የሲሕር በሽታ ፈውስ ካገኙ በኃላ ይህ በቅጠላ-ቅጠል እና የዕፅ ስር በመበጠስ ሰው ላይ ለሚተበተብ በሽታ ጠዋት ጠዋት ሰባት የዘንባባ ተምር መብላት መድሃኒት እንደሆነ ነግረውናል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 70 , ሐዲስ 74:
የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ ማንኛውም ሰው ጠዋት ጠዋት ሰባት የዘንባባ ተምር የሚበላ በበላበት ቀን በመርዝ እና በመተት አይጠቃም። حَدَّثَنَا جُمْعَةُ بْنُ عَبْدِ اللَّهِ، حَدَّثَنَا مَرْوَانُ، أَخْبَرَنَا هَاشِمُ بْنُ هَاشِمٍ، أَخْبَرَنَا عَامِرُ بْنُ سَعْدٍ، عَنْ أَبِيهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ تَصَبَّحَ كُلَّ يَوْمٍ سَبْعَ تَمَرَاتٍ عَجْوَةً لَمْ يَضُرُّهُ فِي ذَلِكَ الْيَوْمِ سُمٌّ وَلاَ سِحْرٌ ‏”‌‏.‏

በኢስላም ወንጀለኛ ሲሕር የተደረገበት ሰው ሳይሆን ድግምተኛ ሰው ነው፤ በነብያችን”ﷺ” ወቅት የነበሩ በዳዮች ነብያችንን”ﷺ” የተደገመበትን ሰው ይሉ ነበር፤ ይህ የከንቱዎች መሳለቂያ ነበር፦
17፥47 እኛ ወደ አንተ በሚያዳምጡ ጊዜ እነርሱም በሚንሾካሾኩ ጊዜ በዳዮች እርስ በርሳቸው *”የተደገመበትን ሰው እንጂ አትከተሉም በሚሉ ጊዜ”* በእርሱ የሚያዳምጡበትን ምክንያት ዐዋቂ ነን፡፡ نَّحْنُ أَعْلَمُ بِمَا يَسْتَمِعُونَ بِهِۦٓ إِذْ يَسْتَمِعُونَ إِلَيْكَ وَإِذْ هُمْ نَجْوَىٰٓ إِذْ يَقُولُ ٱلظَّٰلِمُونَ إِن تَتَّبِعُونَ إِلَّا رَجُلًۭا مَّسْحُورًا
25፥8 «ወይም ወደ እርሱ ድልብ አይጣልለትምን ወይም ከእርሷ የሚበላላት አትክልት ለእርሱ አትኖረውምን» አሉ፡፡ *በዳዮቹም ለአመኑት «የተደገመበትን ሰው እንጂ ሌላ አትከተሉም» አሉ*፡፡ أَوْ يُلْقَىٰٓ إِلَيْهِ كَنزٌ أَوْ تَكُونُ لَهُۥ جَنَّةٌۭ يَأْكُلُ مِنْهَا ۚ وَقَالَ ٱلظَّٰلِمُونَ إِن تَتَّبِعُونَ إِلَّا رَجُلًۭا مَّسْحُورًا

ለተሳላቂዎች ደግሞ አላህ በቂ ምላሽ ሰጥቷል፦
25፥41 ባዩህም ጊዜ ያ አላህ መልእክተኛ አድርጎ የላከው ይህ ነውን እያሉ *” መሳለቂያ እንጂ ሌላ አያደርጉህም”*፡፡ وَإِذَا رَأَوْكَ إِن يَتَّخِذُونَكَ إِلَّا هُزُوًا أَهَٰذَا ٱلَّذِى بَعَثَ ٱللَّهُ رَسُولًا
15፥95 *”ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሃል”*፡፡ إِنَّا كَفَيْنَٰكَ ٱلْمُسْتَهْزِءِينَ

ኢንሻላህ ስለ መተት በባይብል በክፍል ሁለት ይቀጥላል….

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም