ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
69 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ጌታ እና ባሪያ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፤

5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል *”ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ”* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

ዒሣ የትምህርቱ ጭብጥ፦ “አላህ ጌታዬና ጌታችሁ ነው፤ ስለዚህ አምልኩት” የሚል ነው፤ አምላካችን አላህም ኢየሱስን ተናገር! ብሎ ያዘዘው ቃል “ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ” ማለትን ነው፦
3፥51 *”አላህ ጌታዬና ጌታችሁ ነው፤ ስለዚህ አምልኩት”* ፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው» አላቸው፡፡ إِنَّ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبُّكُمْ فَٱعْبُدُوهُ ۗ هَٰذَا صِرَٰطٌۭ مُّسْتَقِيمٌۭ
5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል *”ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ”* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

ጌታችን አላህ ላኪ ባሪያው ኢየሱስ መልእክተኛ ነው። ባሪያ ከጌታው አይበልጥም፥ መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም፦
ዮሐንስ 13፥16 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ *ባሪያ ከጌታው አይበልጥም። መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም*።

ፈጣሪ ኢየሱስን “አብዲ” עַבְדִּי֙ ማለትም “ባሪያዬ” በማለት ፈጣሪ ተመላኪ ኢየሱስ አምላኪ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፦
ኢሳይያስ 42፥1 እነሆ *ደግፌ የያዝሁት “ባሪያዬ” עַבְדִּי֙፤ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ*፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፥ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል።

ይህንን በኢሳያያስ በኩል “ባሪያዬ” የሚለውን ትንቢት ወደ አዲስ ኪዳን ስንመጣ ተርጓሚዎች “ብላቴና” ማለትም “ልጄ” ብለው ለመለወጥ ቢዳዱም ግሪኩ ግን “ፔይስ ሞዩ” παῖς ማለትም “ባሪያዬ” ብሎ አስቀምጦታል፤ “ፔይስ” παῖς ማለት “ባሪያ” ማለት ነውና፦
ማቴዎስ 12፥17-18 በነቢዩ ለአሕዛብ በኢሳይያስ የተባለው ይፈጸም ዘንድ እንዲህ ሲል፦እነሆ *"የመረጥሁት “ባሪያዬ” παῖς μου ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ወዳጄ*፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፥ ፍርድንም ያወራል።

በትርጉም ኢየሱስን “ልጅ” ብለው ቢቀይሩትም ግሪኩ ግን “ባሪያ” ብሎ ያስቀመጠበት ጥቅስ በቁና ነው፣ በተጨማሪም የአማርኛው ትርጉም እና KJV ትርጉም “ልጅ” እያሉ ቢለውጡም NIV ትርጉም በትክክል የግሪኩን ትርጉም ይዞ “ባሪያ” ብሎ አስቀምጦታል፦
የሐዋርያት ሥራ 3፥13 የአብርሀምና የይስሐቅ የያዕቆብም አምላክ፥ የአባቶቻችን አምላክ፥ እናንተ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትንና ሊፈታው ቈርጦ ሳለ በጲላጦስ ፊት የካዳችሁትን *“ባሪያዬውን” παῖς ኢየሱስን አከበረው*።
የሐዋርያት ሥራ 3፥26 ለእናንተ አስቀድሞ *እግዚአብሔር “ባሪያዬውን” παῖς አስነሥቶ*፥ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ፥ ሰደደው።
የሐዋርያት ሥራ 4፥27-28 *"በቀባኸው በቅዱሱ “ባሪያህ” παῖς በኢየሱስ"* ላይ ሄሮድስና ጴንጤናዊው ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር፥ እጅህና አሳብህ እንዲሆን አስቀድመው የወሰኑትን ሁሉ ሊፈጽሙ፥ በዚች ከተማ በእውነት ተሰበሰቡ።
የሐዋርያት ሥራ 4፥29-30 አሁንም፥ ጌታ ሆይ፥ ወደ ዛቻቸው ተመልከት፤ ለመፈወስም እጅህን ስትዘረጋ *በቅዱስ “ባሪያህም” παῖς በኢየሱስ"* ስም ምልክትና ድንቅ ሲደረግ፥ ባሪያዎችህ በፍጹም ግልጥነት ቃልህን እንዲናገሩ ስጣቸው ።

በተለይ ጴጥሮስ አብን፦ "ጌታ ሆይ" ካለ በኃላ ስለ ኢየሱስ ለአብ፦ "ባሪያህ" ማለቱ አብ ጌታ ወልድ ባሪያ መሆኑን አስምሮበታል። በእርግጥም አብ የሰማይና የምድር ጌታ ነው፦
ማቴዎስ 11፥25 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ፦ *"አባት ሆይ፥ የሰማይና የምድር ጌታ"*፥
የሐዋርያት ሥራ 17፥24 ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ *"እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና"* እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም።

"እርሱ" ተብሎ በነጠላ ተውላጠ-ስም የተቀመጠ አንድ ማንነት የሰማይና የምድር ጌታ ነው፥ ይህም አብ ነው። አብ በጌትነቱ ላይ ባርነት የለበትም። ማርያምና ዮሴፍ ይህንን የአብን ባሪያ ኢየሱስን በጌታ ፊት አቁመው ለጌታው መስዋዕት አቅርበዋል፤ ኢየሱስ በጌታ የተቀባና ለመፈወስ የጌታ ኃይል የሆነለት ባሪያ ነው፦
ሉቃስ 2፥24 እንደ ሙሴም ሕግ የመንጻታቸው ወራት በተፈጸመ ጊዜ፥ በጌታ ሕግ፡— የእናቱን ማኅፀን የሚከፍት ወንድ ሁሉ ለጌታ የተቀደሰ ይባላል፡ ተብሎ እንደ ተጻፈ፡ *"በጌታ ፊት ሊያቆሙት"*፥ በጌታም ሕግ፡— ሁለት ዋሊያ ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች፡ እንደ ተባለ፥ መሥዋዕት ሊያቀርቡ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት።
ሉቃስ 2፥26 *"በጌታም የተቀባውን"* ሳያይ ሞትን እንዳያይ በመንፈስ ቅዱስ ተረድቶ ነበር።
ሉቃስ 5፥17 እርሱም *"እንዲፈውስ የጌታ ኃይል ሆነለት"*።

አንድ ህላዌ ባሪያ ከሆነ ተመልሶ ጌታ አይሆንም። ጌታ ከተባለ ደግሞ ግን ስልጣንና ሹመትን አሊያም እልቅናና ክብርን ያመለክታል። ስለዚህ የኢየሱስ ጌትነት የፍጡር ማእረግ ብቻ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር ኢየሱስን ጌታ አደረገው ስለሚል፦
የሐዋርያት ሥራ 2፥36 አለ። እንግዲህ ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን *ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው* የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ።

መቼም አንድ ጤነኛ የሆነ ሰው ፈጣሪን ፈጣሪ ጌታ አደረገው ብሎ እንደማይቀበል እሙን ነው፤ ይስሐቅ ያዕቆብን ጌታ አደረግሁት ይላል፦
ዘፍጥረት 27፥37 ይስሐቅም መለሰ ዔሳውንም አለው። እነሆ፥ *ጌታህ አደረግሁት*፥ ወንድሞቹንም ሁሉ ለእርሱ ተገዦች ይሆኑ ዘንድ ሰጠሁት፥

ይህም ስልጣንና ሹመትን አሊያም እልቅናና ክብርን ያመለክታል፤ ዮሴፍ፦ "እግዚአብሔር ጌታ አደረገኝ” ይላል፦
ዘፍጥረት 45፥9 *እግዚአብሔር በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ጌታ አደረገኝ*፤ ወደ እኔ ና፥ አትዘግይ፤

ኢየሱስ ጌታ ተደረገ ሲባል ያዕቆብ ጌታ ተደረገ ዮሴፍ ጌታ ተደረገ በተባለበት ሒሳብ እንጂ የዓለማቱ ጌታ የሚለውን አያመለክትም፤ ይህም በራሡ የተብቃቃ አሊያም የባህርይ ገንዘቡ ሣይሆን በስጦታ ያገኘው ነው። ታዲያ ኢየሱስ ለምን "አንድ ጌታ" ተባለ? አዎ "አንድ ጌታ" ማለት "አንድ መምህር" ማለት ነው፦
1ኛ ቆሮንቶስ 8፥6 ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን *"አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን"*።
ማቴዎስ 23፥8 እናንተ ግን፡- *መምህር* Ῥαββί ተብላችሁ አትጠሩ፤ *መምህራችሁ አንድ* ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ።
ቅድሚያ "ረቢ" Ῥαββί ማለት በአገናዛቢ ሙያ "መምህር" ማለት እንደሆነ ይሰመርበት፦
ዮሐንስ 1፥38 እርሱም፦ *"ረቢ" Ῥαββί ፥ ወዴት ትኖራለህ? አሉት፤ ትርጓሜው "መምህር ሆይ"* ማለት ነው።
ዮሐንስ 20፥16 ኢየሱስም፦ ማርያም አላት። እርስዋ ዘወር ብላ *በዐረማይክ፦ "ረቡኒ" Ραββουνι አለችው፤ ትርጓሜውም፦ "መምህር ሆይ" ማለት ነው*። NIV

"ረቢ" Ῥαββί በነጠላ "መምህሬ" ማለት ሲሆን "ረቡኒ" Ραββουνι በብዜት "መምህራችን" ማለት ነው። ማርቆስ ጴጥሮስ ኢየሱስን "ረቢ" ῥαββί አለው ሲል የማቴዎስ ጸሐፊ ደግሞ ጴጥሮስ ኢየሱስን "ኩሪዮስ" κύριος አለው ይለናል፦
ማርቆስ 9፥5 ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን። *"መምህር ሆይ"* ῥαββί ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ አለው።
ማቴዎስ 17፥4 ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን፡- *"ጌታ ሆይ"* κύριος ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ።

በግሪክ "ኩሪዮስ" κύριος የሚለው ቃል "ወንድ መምህር" ሲባል "ሴት መምህር" ደግሞ "ኩርያ" κυρία ትባላለች። ጥያቄአችን "ኩሪዮስ" ማለት "ረብ" ለሚለው ትርጉም ነው? አዎ! ከተባለ እንግዲያውስ ኢየሱስ፦ "ረብ አንድ ነው" ማለቱ እና ጳውሎስ፦ "አንድ ኩሪዮስ ነው" ማለቱ አንድ ትርጉም ካለው ኢየሱስ በአንድ አምላክ እና በሕዝቦቹ መካከል ያለ አንድ መምህር ነው፦
1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥5 *አንድ አምላክ Θεὸς አለና፥ በአምላክ Θεὸς እና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ *አንድ* አለ፥ እርሱም ሰው ἄνθρωπος የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው"*።
ዮሐንስ 3፥2 *"መምህር ሆይ" Ῥαββί ፥ "አምላክ" Θεὸς ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና "መምህር" ሆነህ "ከአምላክ" Θεὸς ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን አለው*።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ፓስተር ኃይሉ እና የእግዚአብሔሮች እሳቤ

በክርስትና አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ ትምህርት እንዳለ ሁሉ እንዲሁ ሰዎች አማልክት ይሆናሉ የሚል ትምህርትም አለ፥ ይህ ትምህርት “ቴኦሲስ” ይባላል። “ቴኦሲስ” θέωσις ማለት ሰው አምላክ የሚሆንበት ሶስተኛው ደረጃ”divinization” ሲሆን ይህንን ደረጃ ለማሳለፍ ሁለት ደረጃዎችን ያሳልፋል፥ አንደኛው “ካታርሲስ” θέωσις ማለትም “ንፅህና” ሲሆን ሁለተኛው “ቴኦሪዎስ” θεωρός ማለትም “መላቀቅ” ነው። ይህንን ትምህርት ከግሪክ እሳቤ ወደ ክርስትና ውስጥ የቀላቀሉት የቤተክርስቲያን አበው ኢራንየስ፣ ጀስቲን ማርቲን፣ የአሌክሳንድሪያው አትናቴዎስ፣ የአሌክሳድሪያው ክሌመንት፣ የሂፓፑ አውግስቲን፣ የአንጾኪያው ቴኦፍሎስ፣ የሮሙ ሂፓቲየስ፣ የእንዚዛዙ ጎርጎርዮስ፣ የአሌክሳንድርያው ሳውርዮስ፣ የቂሳርያው ባስሊዎስ ናቸው። “አምላክ ሰው የሆነው ሰዎች አምላክ መሆን እንደሚችሉ ለማሳየት ነው”God became a man so that a man how to become God” ይሉናል።

ሥላሴን እና ተሰግዎትን ያረቀቁት እንዚህ አበው ይህንን ትምህርት አርቅቀውታል። ሰዎች አማልክት ይሆናሉ ተብሎ በሞርሞን ክርስቲያኖች የሚታመንበት እሳቤ ተጠያቂዎቹ እነዚህ አበው ናቸው። ይህንን ትምህርት የምስራቋ ቤተክርስቲያን ኦርቶዶክስ፣ የምዕራቧ ቤተክርስቲያን ካቶሊክ እና አግሊካን ቤተክርስቲያን ዶግማቸው ላይ አለ፥ "መላእክትና ነብያት የፀጋ አማልክት ናቸው" የሚል ትምህርት አለ።

ፓስተር ኃይሉ ዮሐንስ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ሊጠየቁ ይገባል፥ አብዛኛው ፕሮቴስታንት ይህንን እሳቤ ሳያጣራ ፓስተር ኃይሉ ዮሐንስን ይዘልፋል። የቀድሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ፓትሪያርክ አቡነ ጳውሎስ በአንድ ወቅት፦ "ወደ ቤተርክስቲያን የምንመጣው በምድር ላይ ትናንሽ እግዚአብሔሮች ልንሆን ነው" ብለዋል። ቪድዮውን ያድምጡ!

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ዘውታሪነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

6፥128 *"እሳት አላህ የሻው ሲቀር በውስጧ ዘውታሪዎች ስትኾኑ መኖሪያችሁ ናት ይላቸዋል"*፡፡ ጌታህ ጥበበኛ ዐዋቂ ነውና፡፡ قَالَ النَّارُ مَثْوَاكُمْ خَالِدِينَ فِيهَا إِلَّا مَا شَاءَ اللَّهُ ۗ إِنَّ رَبَّكَ حَكِيمٌ عَلِيمٌ

“ሪባ” رِّبَوٰا ማለት "አራጣ" ወይም" "ወለድ" ማለት ሲሆን ሪባን ወደ መብላት የተመለሰም ሰው የእሳት ጓድ ነው፡፡ እርሱ በውስጧ ዘውታሪ ነው፦
2፥275 *"አራጣን ወደ መብላት የተመለሰም ሰው እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው"*፡፡ وَمَنْ عَادَ فَأُولَـٰئِكَ أَصْحَابُ النَّارِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ

ሰውን ለጀሀነም የሚያዘወትር ወንጀል ሺርክ ብቻ ከሆነ ሪባ እንዴት ሊያዘወትር ይችላል? ቁልፉ ያለው“ኻሊድ” የሚለው ቃል ላይ ነው። “ኻሊድ” خَالِد ማለት “ዘውታሪ” ማለት ሲሆን በቁርኣን ሰዋስው ውስጥ ሁለት ዓይነት ዘውታሪነት አለ፥ አንደኛው “ኻሊዱል ሙጥለቅ” خَالِد ٱلْمُطْلَق ማለትም “ፍጹማዊ ዘውታሪ“Absolute for ever” ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ “ኻሊዱል ቀሪብ” أَوَّل ٱلْقَرِيب‎ ማለትም “አንጻራዊ ዘውታሪ“Relative for ever” ነው። ይህንን ነጥብ በነጥብ እንይ፦

ነጥብ አንድ
“ኻሊዱል ሙጥለቅ”
“ሙጥለቅ” مُطْلَق ማለት “ፍጹም” ማለት ነው፥ “ኹሉድ” خُلُود‎ የሚለው ቃል “ኸለደ” خَلَدَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ዘውታሪነት” ማለት ነው፥ “የውሙል ኹሉድ” يَوْمُ الْخُلُود ማለት “የመዘውተሪያ ቀን” ማለት ነው፦
50፥34 *”«በሰላም ግቧት ይህ “የመዘውተሪያ ቀን” ነው»* ይባላሉ፡፡ ادْخُلُوهَا بِسَلَامٍ ۖ ذَٰلِكَ يَوْمُ الْخُلُودِ

የትንሳኤ ቀን የጀነት ባለቤቶች በጀነት ውስጥ ለዘላለም ይኖራሉ፥ የእሳት ባለቤቶች በእሳት ውስጥ ለዘላለም ይኖራሉ። ሞት ይጠፋል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 81, ሐዲስ 134
አቡ ሁራይራህ እንደተረከው፦ “ነቢዩ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ለጀነት ባለቤቶች፦ “ለእናንተ ዘላለማዊነት እንጂ ሞት የለም” ይባላሉ፥ ለእሳት ባለቤቶች፦ “ለእናንተ ዘላለማዊነት እንጂ ሞት የለም” ይባላሉ”*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ يُقَالُ لأَهْلِ الْجَنَّةِ خُلُودٌ لاَ مَوْتَ‏.‏ وَلأَهْلِ النَّارِ يَا أَهْلَ النَّارِ خُلُودٌ لاَ مَوْتَ ‏”‌‏

“ኻሊድ” خَالِد ማለት “ዘውታሪ” ማለት ነው፥ የኻሊድ ብዙ ቁጥር ደግሞ “ኻሊዲን” خَالِدِين ወይም “ኻሊዱን” خَالِدُون ሲሆን “ዘውታሪያን” ማለት ነው። በጀነት የሚኖሩ አማንያን “አስሓቡል ጀናህ” أَصْحَابُ الْجَنَّة ማለትም “የገነት ጓዶች” ሆነው ለዘላለም ይኖራሉ፦
2፥82 *እነዚያም ያመኑት በጎ ሥራዎችንም የሠሩት እነዚያ የገነት ጓዶች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናቸው*፡፡ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ أُولَـٰئِكَ أَصْحَابُ الْجَنَّةِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ

በተቃራኒው ጀሀነም የሚኖሩ ከሃድያን “አስሓቡ አን-ናር” أَصْحَابُ النَّار ማለትም “የእሳት ጓዶች” ሆነው ለዘላለም ይኖራሉ፦
2፥39 *እነዚያም በመልክተኞቻችን የካዱ በአንቀጾቻችንም ያስተባበሉ እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው*፡፡ وَالَّذِينَ كَفَرُوا وَكَذَّبُوا بِآيَاتِنَا أُولَـٰئِكَ أَصْحَابُ النَّارِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ

ይህ ዘውታሪነት "አበደን" أَبَدًا ማለትም "ዘላለም" በሚል ስለመጣ ፍጹማዊ ዘውታሪነት ነው፦
9፥22 *"በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ሲኾኑ ያበስራቸዋል"*፡፡ አላህ እርሱ ዘንድ ታላቅ ምንዳ አለና፡፡ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ إِنَّ اللَّهَ عِندَهُ أَجْرٌ عَظِيمٌ
72፥23 *"አላህን እና መልክተኛውንም የሚያምጽ ሰው ለእርሱ የገሀነም እሳት አለው፡፡ በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ሲኾኑ"*፡፡ وَمَن يَعْصِ اللَّهَ وَرَسُولَهُ فَإِنَّ لَهُ نَارَ جَهَنَّمَ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا
ነጥብ ሁለት
“ኻሊዱል ቀሪብ”
“ቀሪብ” قَرِيب‎ ማለት “አንጻራዊ” ማለት ነው፥ ሪባ የበላ ሰው እሳት ውስጥ የሚዘወተርበት ጊዜ መጨረሻ ያለው ሲሆን ግን መጨረሻውን አሏህ ብቻ ስለሚያው ይህ ዘውታሪነት አንጻራዊ ነው፦
11፥107 *"ጌታህ ከሻው ሰማያትና ምድር እስከ ዘወተሩ ድረስ በውስጧ ዘውታሪዎች ሲኾኑ በእሳት ይኖራሉ፡፡ ጌታህ የሚሻውን ሠሪ ነውና"*፡፡ خَالِدِينَ فِيهَا مَا دَامَتِ السَّمَاوَاتُ وَالْأَرْضُ إِلَّا مَا شَاءَ رَبُّكَ ۚ إِنَّ رَبَّكَ فَعَّالٌ لِّمَا يُرِيدُ

እዚህ አንቀጽ ላይ ሰማያትና ምድር "ኻሊዲን" خَالِدِين ማለትም "ዘውታሪዎች" ተብለዋል። ጀሀነም ውስጥ ጌታ ያሻው የሚዘወተሩት ሰማያትና ምድር እንደሚዘወተሩት ነው፥ ሰማያትና ምድር ዘውታሪነታቸው እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ ነው፦
14፥48 *ምድር በሌላ ምድር የምትለወጥበትን ሰማያትም እንደዚሁ፥ ፍጡራን ሁሉ አንድ አሸናፊ ለኾነው አላህም የሚገለጹበት ቀን አስታውሱ*፡፡ يَوْمَ تُبَدَّلُ الْأَرْضُ غَيْرَ الْأَرْضِ وَالسَّمَاوَاتُ ۖ وَبَرَزُوا لِلَّهِ الْوَاحِدِ الْقَهَّارِ

ሰማያትና ምድር በሌላ ሰማያትና ምድር የሚለወጡ እንጂ ዘላለም ዘውታሪ አይደሉም። ያላሻረኩ ግን እኩይ ሥራ የሠሩ ሙዋሒድ እንደ ሰማያትና ምድር መዘውተር በጀሀነም ይዘወተራሉ፦
6፥128 *"እሳት አላህ የሻው ሲቀር በውስጧ ዘውታሪዎች ስትኾኑ መኖሪያችሁ ናት ይላቸዋል"*፡፡ ጌታህ ጥበበኛ ዐዋቂ ነውና፡፡ قَالَ النَّارُ مَثْوَاكُمْ خَالِدِينَ فِيهَا إِلَّا مَا شَاءَ اللَّهُ ۗ إِنَّ رَبَّكَ حَكِيمٌ عَلِيمٌ

አህሉ አት-ተፍሢር ኢብኑ ከሲር እና ኢብኑ ዐባሥ ሡረቱል ሁድ ምዕራፍ 11 አንቀጽ 107 ላይ ያለውን በዚህ መልኩ ፈሥረውታል። አሏህ የሻው ማለት ቅጣቱን ተቀብሎ በአሏህ ምህረት እና በነቢያችን”ﷺ” ሸፋዓህ ከእሳት ይወጣል። ማንም ሙሥሊም በአላህ እስካላሻረከ ድረስ ለሠራው እኩይ ሥራ ተቀጥቶ ቅጣቱን ሲጨርስ በአላህ ይቅርታና ምሕረት ወደ ጀነት ይገባል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97, ሐዲስ 113
አቡ ዘር እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” *”እንዲህ አሉ፦ ጂብሪል ወደ እኔ መጥቶ እንዲህ ሲል አበሰረኝ፦ “ማንም ምንም ነገር በአላህ ላይ ያላሻረከ ወደ ጀነት ይገባል። እኔም፦ “ቢሰርቅም፥ ቢያመነዝርም? ብዬ ጠየኩት። እርሱም፦ “ቢሰርቅም፥ ቢያመነዝርም” አለኝ”*። عَنِ الْمَعْرُورِ، قَالَ سَمِعْتُ أَبَا ذَرٍّ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ أَتَانِي جِبْرِيلُ فَبَشَّرَنِي أَنَّهُ مَنْ مَاتَ لاَ يُشْرِكُ بِاللَّهِ شَيْئًا دَخَلَ الْجَنَّةَ ‏”‌‏.‏ قُلْتُ وَإِنْ سَرَقَ وَإِنْ زَنَى قَالَ ‏”‏ وَإِنْ سَرَقَ وَإِنْ زَنَى
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 10, ሐዲስ 201
አቢ ሁረይራ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦…. *”ከሰዎች መካከል በሥራቸው ለዘላለም በጀሀነም ሲዘወትሩ፥ ሌሎች ደግሞ ቅጣት ተቀብለው ከጀሃነም ይወጣሉ። አላህ የሻው ከጀሃነም ሰዎች መካከል ምሕረት ያደርግለታል፥ ለመላእክትም፦ “እርሱን ብቻ ያመለከውን አውጡ” ብሎ ያዛቸዋል”*። تَخْطَفُ النَّاسَ بِأَعْمَالِهِمْ، فَمِنْهُمْ مَنْ يُوبَقُ بِعَمَلِهِ، وَمِنْهُمْ مَنْ يُخَرْدَلُ ثُمَّ يَنْجُو، حَتَّى إِذَا أَرَادَ اللَّهُ رَحْمَةَ مَنْ أَرَادَ مِنْ أَهْلِ النَّارِ، أَمَرَ اللَّهُ الْمَلاَئِكَةَ أَنْ يُخْرِجُوا مَنْ كَانَ يَعْبُدُ اللَّهَ
ከሰዎች መካከል በሥራቸው ለዘላለም በጀሀነም የሚዘወተሩ በአላህ ላይ ያጋሩ ናቸው፥ አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም። የሚያጋራን ሰው አላህ ጀነትን በእርሱ ላይ በእርግጥ እርም አደረገ፥ የአጋሪው መኖሪያውም እሳት ናት፦
4፥48 *”አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለውንም ኀጢአት ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው ታላቅን ኀጢአት በእርግጥ ቀጠፈ”*፡፡ إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَاءُ ۚ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدِ افْتَرَىٰ إِثْمًا عَظِيمًا
5:72 *”እነሆ በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በእርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፥ መኖሪያውም እሳት ናት”*። ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም። إِنَّهُ مَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ اللَّهُ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ وَمَأْوَاهُ النَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ

“ከዚህ ሌላ ያለውንም ኀጢአት ለሚሻው ሰው ይምራል” የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። አላህ የሻው ከጀሀነም ሰዎች መካከል ምሕረት ያደርግለታል፥ ለመላእክትም፦ “እርሱን ብቻ ያመለከውን አውጡ” ብሎ ያዛቸዋል። አላህ ከሺርክ ሌላ ያለውንም ኀጢአት ለሚሻው ሰው ቀጥቶት አሊያም በነቢያችን”ﷺ” ሸፋዓህ ይምራል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 81, ሐዲስ 155
ዒምራን ኢብኑ ሑሴይን”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ጥቂት ሕዝብ ከእሳት ወጥተው ወደ ጀነት በሙሐመድ”ﷺ” ሸፋዓህ ይገባሉ፥ ጀሀነሚዪን ተብለው ይጠራሉ*። حَدَّثَنَا عِمْرَانُ بْنُ حُصَيْن ٍ ـ رضى الله عنهما ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ يَخْرُجُ قَوْمٌ مِنَ النَّارِ بِشَفَاعَةِ مُحَمَّدٍ صلى الله عليه وسلم فَيَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ، يُسَمَّوْنَ الْجَهَنَّمِيِّينَ ‏
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 3, ሐዲስ 41
አቢ ሁረይራ እንደተረከው፦ *”እኔም፦ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሆይ! በትንሳኤ ቀን ማነው እድለኛ ሰው የእርስዎን ሸፋዓህ የሚያገኘው? አልኩኝ። የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ “አቢ ሁረይራ ሆይ! ንግግር ለመማር የአንተን ቆይታ ዐውቃለው፥ እንደማስበው ስለዚህ ጉዳይ ከአንተ በፊት ማንም አልጠየቀኝም። በትንሳኤ ቀን የእኔን ሸፋዓህ የሚያገኝ እድለኛ ሰው ከልቡ ወይም ከነፍሱ፦ “ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም” ያለ ነው*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّهُ قَالَ قِيلَ يَا رَسُولَ اللَّهِ، مَنْ أَسْعَدُ النَّاسِ بِشَفَاعَتِكَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ لَقَدْ ظَنَنْتُ يَا أَبَا هُرَيْرَةَ أَنْ لاَ يَسْأَلَنِي عَنْ هَذَا الْحَدِيثِ أَحَدٌ أَوَّلُ مِنْكَ، لِمَا رَأَيْتُ مِنْ حِرْصِكَ عَلَى الْحَدِيثِ، أَسْعَدُ النَّاسِ بِشَفَاعَتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ مَنْ قَالَ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ، خَالِصًا مِنْ قَلْبِهِ أَوْ نَفْسِهِ ‏”‌‏.‏

“አሏሁ አዕለም” اَللّٰهُ أَعْلَم‎

አሏህ በጀሀነም ከመዘውተር ይጠብቀን! የጀነት ዘውታሪዎች ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የፓለቲካ ትርፍ

ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከሲቪክ ማኅበራት ጋር ባደረገው ቆይታ፦ "ከአንድ ዓመት በፊት የሃይማኖት ግጭት እንደሚመጣ ተናግሬ ነበር፥ ልክ እንደ ቦኮሐራም ማለት ነው" ሲል ነበር። ይህንን አጀንዳ ለማስፈጸም እና የዓለም ትኩረት ለመሳብ ዛሬ ሆን ተብሎ የመንግሥት አካላት በየቦታው የመሣጂድ ኢማሞችን እያደኑ መግደል እና ለልማት መሣጂዶችን ማፍረስ ተያይዘውታል። ሕዝበ-ሙሥሊም ይህንን አይቶ መብቱን ለማስከበር ሲታገል ቁማርተኛው መንግሥት፦ "ይኸው ያልኩት የሃይማኖት ግጭት ሆነ" ብሎ የፓለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚደረግ ቁማር ነው። የአንድ ሃይማኖት እና የአንድ ብሔር የበላይነት እሳቤ ያለው የነፍጠኛው የዓጼውን ሥርዓት እቃወማለው። መንግሥት እጁን ከሙሥሊሞች ላይ ያንሳ!

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ኢሥላም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

37፥84 *ወደ ጌታው “በቅን ልብ” በመጣ ጊዜ የኾነውን አስታውስ*፡፡፡ إِذْ جَاءَ رَبَّهُ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ

ኢሥላም የግስ መደቡ "ሠሊመ" سَلِمَ‎ ሲሆን "ሠላም" ማለት ነው፥ "ሠላም" سَلَام የሚለው ቃል እራሱ "ሠሊመ" سَلِمَ‎ ማለትም "ሰላም ሆነ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ሰላም" ማለት ነው። በልቡ ሰላም ያለው ሙሢሊም ደግሞ "ሣሊም" سَالِم‎ ማለትም "ሰላመኛ" ይባላል፦
37፥84 *ወደ ጌታው “በቅን ልብ” በመጣ ጊዜ የኾነውን አስታውስ*፡፡፡ إِذْ جَاءَ رَبَّهُ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ
26፥89 *ወደ አላህ “በንጹህ ልብ” የመጣ ሰው ቢኾን እንጅ*፡፡» إِلَّا مَنْ أَتَى اللَّهَ بِقَلْبٍ سَلِيم

እነዚህ አናቅጽ ላይ “ቅን” ወይም “ንጹህ” ለሚለው ቃል የገባው “ሠሊም” سَلِيم ሲሆን የሣሊም ገላጭ ቅጽል"adjective" ነው። "ቀልብ" قَلْب ማለት "ልብ" ማለት ነው፥ በልብ የሚኖረው የአሏህ ሰላምን ያመለክታል።

ኢሥላም የግስ መደቡ "ሠለመ" سَلَّمَ‎ ሲሆን "ተሥሊም" ማለት ነው፥ "ተሥሊም" تَسْلِيم‎ የሚለው ቃል እራሱ "ሠለመ" سَلَّمَ‎ ማለትም "ሰላምታ ሰጠ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ሰላምታ" ማለት ነው። ይህም ሰላምታ “አሥ-ሠላሙ ዐለይኩም” السَّلَامُ عَلَيْكُم ነው፥ "ሙሠሊም" مُسَلِّم‎ ማለት "ሰላምተኛ" ማለት ነው፦
4፥86 *በሰላምታ በተከበራችሁም ጊዜ ከእርሷ ይበልጥ ባማረ “ሰላምታ” አክብሩ፤ ወይም እርሷኑ መልሷት*። وَإِذَا حُيِّيتُم بِتَحِيَّةٍ فَحَيُّوا بِأَحْسَنَ مِنْهَا أَوْ رُدُّوهَا
24፥61 *ቤቶችንም በገባችሁ ጊዜ ከአላህ ዘንድ የኾነችን የተባረከች መልካም ሰላምታ በነፍሶቻችሁ ላይ ሰላም በሉ*፡፡ فَإِذَا دَخَلْتُم بُيُوتًا فَسَلِّمُوا عَلَىٰ أَنفُسِكُمْ تَحِيَّةً مِّنْ عِندِ اللَّهِ مُبَارَكَةً طَيِّبَة

"ሠሊሙ” سَلِّمُوا ማለት “ሰላም በሉ” ማለት ሲሆን ትእዛዛዊ ግስ ነው፥ “አሥ-ሠላሙ ዐለይኩም” السَّلَامُ عَلَيْكُم ማለት “የአሏህ ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን” ማለት ነው። ተሥሊም ካለን ይበልጥ ባማረ መልኩ “ወዐለይኩም አሥ-ሠላም፣ ወራሕመቱሏሂ ወበረካቱሁ” السَّلاَمُ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَةُ اللهِ وَبَرَكَاتُهُ ማለትም “የአሏህ ሰላም፣ ምህረት እና በረከት በእናንተ ላይ ይሁን” ብለን እንመልሳለን። ወይንም እራሷኑ “ወዐለይኩም አሥ-ሠላም” وَعَلَيْكُم السَّلَام ብለን እንመልሳለን። ይህ የጀነት ሰላምታ በመካከላችን መለዋወጥ ውዴታ ያመጣል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 101
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ጀነት አትገቡም እስካላመናችሁ ድረስ፥ አላመናችሁም እርስ በእርሳችሁ እስካልተዋደዳችሁ ድረስ። እርስ በእርሳችሁ የምትዋደዱበትን አላመላክታችሁን? እንግድያውስ በመካከላችሁ ሰላምታ አብዙ"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لاَ تَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ حَتَّى تُؤْمِنُوا وَلاَ تُؤْمِنُوا حَتَّى تَحَابُّوا ‏.‏ أَوَلاَ أَدُلُّكُمْ عَلَى شَىْءٍ إِذَا فَعَلْتُمُوهُ تَحَابَبْتُمْ أَفْشُوا السَّلاَمَ بَيْنَكُمْ

ኢሥላም የግስ መደቡ "ኢሥተሥለመ" اِسْتَسْلَمَ ሲሆን "ኢሥቲሥላም" ማለት ነው፥ "ኢሥቲሥላም" اِسْتِلَام የሚለው ቃል እራሱ "ኢሥተሥለመ" اِسْتَسْلَمَ ማለትም "ታዘዘ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መታዘዝ" ማለት ነው። አሏህን ለማምለክ የታዘዘ ደግሞ "ሙሥተሥሊም" مُسْتَلِم‎ ይባላል፦
37፥26 *"በእርግጥ እነርሱ ዛሬ እጃቸውን የሰጡ ናቸው"*፡፡ بَلْ هُمُ الْيَوْمَ مُسْتَسْلِمُونَ

በጥቅሉ "ኢሥላም" إِسْلَام‎ የሚለው ቃል "አሥለመ" أَسْلَمَ‎ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አንዱን አምላክ በመገዛት የሚገኝ ሰላም፣ ጸጥታ፣ ሰላምታ" ማለት ነው። "ሙሥሊም" مُسْلِم‎ ማለት ደግሞ "አሏህን በብቸኝነት ተገዢ" ማለት ነው፥ አሏህን በብቸኝነት ተገዢ ሰላመኛ እና ሰላምተኛ ነው። የአሏህን ሐቅ መንካት በደል ነው፥ እምነትን በደል አለመቀላቀል ጸጥታና መረጋጋት አለው፦
6፥82 *እነዚያ ያመኑ እና እምነታቸውን “በበደል” ያልቀላቀሉ እነዚያ ለእነርሱ “ጸጥታ” አላቸው*፤ እነርሱም የተመሩ ናቸው። ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَلَمْ يَلْبِسُوٓا۟ إِيمَٰنَهُم بِظُلْمٍ أُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمُ ٱلْأَمْنُ وَهُم مُّهْتَدُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “በደል” የተባለው በአላህ ላይ ማጋራት ለማመልከት የገባ ነው፥ ሱረቱል አንዓም 6፥82 አንቀጽ በወረደ እና በተነበበ ጊዜ “በደል” የተባለው ሺርክን መሆኑን ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ነግረውናል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 65 , ሐዲስ 4776:
ዐብደሏህ"-ረ.ዐ." እንደተረከው፦ *“እነዚያ ያመኑ እና እምነታቸውን “በበደል” ያልቀላቀሉ እነዚያ ለእነርሱ “ጸጥታ” አላቸው፥ እነርሱም የተመሩ ናቸው” የሚለው አንቀፅ በወረደ ጊዜ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ባልደረቦች የሆኑት ቃሉ ከባድ ስለነበር እነርሱም፦ “ከእኛ ውስጥ በደለኛ ያልሆነ ማን አለ?” ብለው ሲጠይቁ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሉቅማን ለልጁ፡- በአላህ አታጋራ! ማጋራት “ታላቅ በደል ነው” ያለውን አልሰማችሁምን? ብለው ተናገሩ*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ لَمَّا نَزَلَتْ هَذِهِ الآيَةُ ‏{‏الَّذِينَ آمَنُوا وَلَمْ يَلْبِسُوا إِيمَانَهُمْ بِظُلْمٍ‏}‏ شَقَّ ذَلِكَ عَلَى أَصْحَابِ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَقَالُوا أَيُّنَا لَمْ يَلْبِسْ إِيمَانَهُ بِظُلْمٍ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّهُ لَيْسَ بِذَاكَ، أَلاَ تَسْمَعُ إِلَى قَوْلِ لُقْمَانَ لاِبْنِهِ ‏{‏إِنَّ الشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ‏}‌‏”‏
31፥13 ሉቅማንም ለልጁ እርሱ የሚገስጸው ሲሆን፦ ልጄ ሆይ! *በአላህ አታጋራ! ማጋራት ታላቅ በደል ነውና* ያለውን አስታውስ። وَإِذْ قَالَ لُقْمَانُ لِابْنِهِ وَهُوَ يَعِظُهُ يَا بُنَيَّ لَا تُشْرِكْ بِاللَّهِ ۖ إِنَّ الشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ

ሙሥሊም ያልሆናችሁ ሰዎች ለአሏህ በመታዘዝ የውስጥ ሰላም ከፈለጋችሁ ወደ ዲኑል ኢሥላም እንድትመጡ ጥሪያችን ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ስጦታ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

38፥29 *ይህ ወደ አንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፥ የአእምሮ ባለቤቶችም አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑ እና እንዲገሰጹ አወረድነው*፡፡ كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ إِلَيْكَ مُبَارَكٌ لِّيَدَّبَّرُوا آيَاتِهِ وَلِيَتَذَكَّرَ أُولُو الْأَلْبَاب

በዐረቢኛ ሰዋስው ውስጥ “ነህኑ” نَحْنُ ማለት “እኛ” ማለት ሲሆን ይህ የመጀመሪያ መደብ ተውላጠ-ስም ለብዙ ቅዋሜ-ማንነቶች ብዜት ሆኖ ይመጣል፥ አሊያም ለነጠላ ቅዋሜ-ማንነት ግነት ሆኖ ይመጣል። ለብዙ ቅዋሜ-ማንነቶች ብዜት ሆኖ የሚመጣው እኛነት “ጀምዑ ነህኑ” جَمْع نَحْنُ ማለትም “የብዜት እኛነት”Plular of multitude” ነው፥ “ጀምዕ” جَمْع ማለት “ብዜት” ማለት ነው። ለአንድ ለነጠላ ቅዋሜ-ማንነት ግነት ሆኖ የሚመጣው እኛነት ደግሞ “ተዐዚሙ ነህኑ” تَعَظِيم نَحْنُ ማለትም “የግነት እኛነት”Plural of amplitude” ይባላል፥ “ተዓዚም” تَعَظِيم ማለት “ግነት፣ ክብር፣ ግርማ፣ ሞገስ፣ ሉአላዊነት፣ ልዕልና ማለት ነው።
“ነህኑ” نَحْنُ ሙንፈሲል ሆኖ የሚመጣ ተውላጠ-ስም ነው፥ "ሙንፈሲል" مُنْفَصِل ማለት "የተነጠለ"detached" እራሱ ችሎ ያለ ተውላጠ-ስም ነው። “ነህኑ” نَحْنُ ሙተሲል ሆኖ ሲመጣ “ና” نَا‎ ይሆናል፥ "ሙተሲል" مُتَّصِل ማለት "የተያያዘ"attached" ማለት ሲሆን በግስ እና በመስተዋድድ ተያይዞ የሚመጣ ተውላጠ-ስም ነው። እዚህ ድረስ ከተግባባን አምላካችን አሏህ ለእኛ ለሰዎች የሚሰጠው ሕግ፣ ጸጋ፣ ልጅ እና ሲሳይ ስጦታ ነው፦
የሚሰጠውን ሕግን ለማመልከት "አተይ-ና-"
የሚሰጠውን ጸጋን ለማመልከት "አዕጠይ-ና-"
የሚሰጠውን ልጅን ለማመልከት "ወሀብ-ና-"
የሚሰጠውን ሲሳይን ለማመልከት "ረዘቅ-ና-" እያለ ይናገራል። "ና” نَا‎ በግስ መደብ መዳረሻ ተንጠልጥላ የመጣች ተዐዚም ናት። እነዚህን ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"አተይና"
"ኢየታእ" إِيتَاء ማለት "መስጠት" ማለት ሲሆን አምላካችን አሏህ ሑክም ለነቢያት "ሰጠን" በሚልበት አንቀጽ ላይ "አተይና" آتَيْنَا በሚል ቃል ይናገራል፦
2፥87 *ሙሳንም መጽሐፍን በእርግጥ "ሰጠነው"*፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ
4፥163 *ለዳውድም ዘቡርን "ሰጠነው"*፡፡ وَآتَيْنَا دَاوُودَ زَبُورًا
57፥27 ከዚያም በዱካዎቻቸው ላይ መልክተኞቻችንን አስከታተልን፡፡ የመርየምን ልጅ ዒሳንም አስከተልን፡፡ *ኢንጂልንም ሰጠነው"*፡፡ ثُمَّ قَفَّيْنَا عَلَىٰ آثَارِهِم بِرُسُلِنَا وَقَفَّيْنَا بِعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ وَآتَيْنَاهُ الْإِنجِيلَ
20፥99 *ከእኛም ዘንድ ቁርኣንን በእርግጥ "ሰጠንህ"*፡፡ وَقَدْ آتَيْنَاكَ مِن لَّدُنَّا ذِكْرًا

እንዲሁ ጥበብን፣ ዕውቀትን፣ ሥልጣን መስጠቱን ለማመልከት "አተይና" آتَيْنَا በሚል ቃል ይናገራል፦
31፥12 *ለሉቅማንም ጥበብን በእርግጥ "ሰጠነው"፡፡ وَلَقَدْ آتَيْنَا لُقْمَانَ الْحِكْمَةَ
21፥74 ሉጥንም ፍርድንና ዕውቀትን ሰጠነው፡፡ وَلُوطًا آتَيْنَاهُ حُكْمًا وَعِلْمًا
4፥153 *ሙሳንም ግልጽ ስልጣንን "ሰጠነው"*፡፡ وَآتَيْنَا مُوسَىٰ سُلْطَانًا مُّبِينًا

ነጥብ ሁለት
"አዕጠይና"
አምላካችን አሏህ ለፍጥረቱ የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ የሰጠ ነው፥ ለአማንያን ሆነ ለከሃድያን የአሏህ ጸጋ በዚች ዓለም ክልክል አይደለም፦
20፥50 «ጌታችን ያ *ለፍጥረቱ የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ "የሰጠ"* ከዚያም የመራው ነው» አለው፡፡ قَالَ رَبُّنَا الَّذِي أَعْطَىٰ كُلَّ شَيْءٍ خَلْقَهُ ثُمَّ هَدَىٰ
17፥20 *"ሁሉንም እነዚህን እና እነዚያን ከጌታህ ስጦታ በዚህ ዓለም እንጨምርላቸዋለን፡፡ የጌታህም ስጦታ በዚች ዓለም ክልክል አይደለም"*፡፡ كُلًّا نُّمِدُّ هَـٰؤُلَاءِ وَهَـٰؤُلَاءِ مِنْ عَطَاءِ رَبِّكَ ۚ وَمَا كَانَ عَطَاءُ رَبِّكَ مَحْظُورًا

"ስጦታ" ለሚለው የገባው ቃል "ዐጧእ" عَطَاء መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። ለምሳሌ አምላካችን አሏህ ለነቢያችን"ﷺ" በጀነት ስለሚሰጠው ስጦታ ለማመልከት "አዕጠይና" أَعْطَيْنَا በማለት ይናገራል፦
108፥1 *እኛ በጣም ብዙ በጎ ነገሮችን "ሰጠንህ"*፡፡ إِنَّا أَعْطَيْنَاكَ الْكَوْثَرَ

በዚህ አንቀጽ ላይ “በጎ ነገር” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ከውሰር” كَوْثَر ሲሆን በጀነት ውስጥ ያለ ከወተት የነጻና ከማር የጣፈጠ ወንዝ ነው፥ ይህ ከውሰር ለነቢያችን”ﷺ” የተሰጠ ስጦታ ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3684
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ “እኛ ከውሰርን ሰጠንህ” ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”በጀነት ወንዝ ነው፥ በጀነት ወንዝ ድንኳኖቹ ከድንጋይ የተሠሩ አየው። ጂብሪል ሆይ! ምንድን ነው? አልኩት፥ እርሱም" ከውሰር ነው፥ አላህ ለአንተ የሰጠህ” አለኝ”*። عَنْ أَنَسٍ ‏:‏ ‏(‏ إناَّ، أَعْطَيْنَاكَ الْكَوْثَرَ ‏)‏ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ هُوَ نَهْرٌ فِي الْجَنَّةِ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ فَقَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ رَأَيْتُ نَهْرًا فِي الْجَنَّةِ حَافَتَاهُ قِبَابُ اللُّؤْلُؤِ قُلْتُ مَا هَذَا يَا جِبْرِيلُ قَالَ هَذَا الْكَوْثَرُ الَّذِي قَدْ أَعْطَاكَهُ اللَّهُ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ أَبُو عِيسَى هَذَا حَدِيثٌ حَسَنٌ صَحِيحٌ
ነጥብ ሦስት
"ወሀብና"
በቁርኣን ከተገለጹ የአሏህ ስሞች መካከል "አል-ወሃብ" الْوَهَّاب ሲሆን "እጅግ በጣም ለጋስ" ማለት ነው፥ አምላካችን አሏህ ልጅን በመስጠት ይለግሳል፦
42፥49 *ለሚሻው ሰው ሴቶችን "ይሰጣል"፡፡ ለሚሻውም ሰው ወንዶችን "ይሰጣል"*፡፡ يَهَبُ لِمَن يَشَاءُ إِنَاثًا وَيَهَبُ لِمَن يَشَاءُ الذُّكُورَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ይሰጣል" ለሚለው የገባው ቃል "የሀቡ" መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ልጅን በመስጠት በሚናገርበት አንቀጽ ላይ "ወሀብና" وَهَبْنَا ይላል፦
27፥27 *ለእርሱም(ለኢብራሂም) ኢስሐቅንና ያዕቆብን "ሰጠነው"*፡፡ وَوَهَبْنَا لَهُ إِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ
38፥30 *ለዳውድም ሱለይማንን "ሰጠነው"*፡፡ وَوَهَبْنَا لِدَاوُودَ سُلَيْمَانَ
21፥90 ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው። *ለእርሱም(ለዘከሪያም) የሕያን "ሰጠነው"*፡፡ فَاسْتَجَبْنَا لَهُ وَوَهَبْنَا لَهُ يَحْيَىٰ

ነጥብ አራት
"ረዘቅና"
"ሪዝቅ" رِزْق ማለት "ሲሳይ" ማለት ሲሆን አምላካችን አሏህ ሲሳይን ሰጪ ስለሆነ "አር-ረዛቅ" الرَّزَّاق ተብሏል፦
51፥58 *"አላህ እርሱ "ሲሳይን ሰጪ" የብርቱ ኀይል ባለቤት ነው*፡፡ إِنَّ اللَّهَ هُوَ الرَّزَّاقُ ذُو الْقُوَّةِ الْمَتِينُ

ሲሳይን በመስጠት በሚናገርበት አንቀጽ ላይ "ረዘቅና" رَزَقْنَا ይላል፦
2፥172 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከነዚያ "ከሰጠናችሁ" ጣፋጮች ብሉ*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُلُوا مِن طَيِّبَاتِ مَا رَزَقْنَاكُمْ
8፥3 *እነዚያ ሶላትን ደንቡን አሟልተው የሚሰግዱ "ከሰጠናቸውም" ሲሳይ የሚለግሱ ናቸው*፡፡ الَّذِينَ يُقِيمُونَ الصَّلَاةَ وَمِمَّا رَزَقْنَاهُمْ يُنفِقُونَ

“ተደቡር” تَدَبُر ማለት “ማስተንተን” ማለት ሲሆን “ዱቡር” دُبُر ማለት እራሱ “ጀርባ” ማለት ነው፥ ከቁርኣን ሑሩፍ በስተ-ጀርባ ያለውን የአሏህን ንግግር የአእምሮ ባለቤቶችም እንዲያስተነትኑ ቁርኣን ወርዷል፦
38፥29 *ይህ ወደ አንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፥ የአእምሮ ባለቤቶችም አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑ እና እንዲገሰጹ አወረድነው*፡፡ كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ إِلَيْكَ مُبَارَكٌ لِّيَدَّبَّرُوا آيَاتِهِ وَلِيَتَذَكَّرَ أُولُو الْأَلْبَاب

“እንዲያስተነትኑ” ለሚለው ቃል የገባው “ሊየደበሩ” لِيَدَّبَّرُوا መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። አምላካችን አሏህ ንግግሩን ከሚያስተነትኑ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
መሰልጠን ወይስ መሰይጠን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥32 *"አላህም ከፊላችሁን በከፊሉ ላይ በእርሱ ያበለጠበትን ጸጋ አትመኙ! ለወንዶች ከሠሩት ሥራ እድል አላቸው፥ ለሴቶችም ከሠሩት ሥራ ዕድል አላቸው፡፡ አላህንም ከችሮታው ለምኑት፥ አላህ በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው"*፡፡ وَلَا تَتَمَنَّوْا مَا فَضَّلَ اللَّهُ بِهِ بَعْضَكُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ ۚ لِّلرِّجَالِ نَصِيبٌ مِّمَّا اكْتَسَبُوا ۖ وَلِلنِّسَاءِ نَصِيبٌ مِّمَّا اكْتَسَبْنَ ۚ وَاسْأَلُوا اللَّهَ مِن فَضْلِهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا

"ሥልጣኔ"Civilization" ማለት ባህልን፣ ወግን፣ ሙያን፣ ዕደ-ጥበብን፣ አእምሮን ማሳደግ እና ማበልጸግ ነው። ሸይጧን” شَّيْطَان የሚለው ቃል “ሸጠነ” شطن ማለትም “ራቀ” ወይም “ተገለለ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “የተገለለ” ወይም “የራቀ” ማለት ነው። የእንስታዊነት"Feminism" እኩልነት መሰልጠን ነው ወይስ መሰይጠን? ይህንን የሙግት ነጥብ እስቲ እንመልከት! "ፈድል" فَضْل የሚለው ቃል "ፈዶለ" فَضَّلَ ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ስጦታ" "ችሮታ" "ጸጋ"Bounty" ማለት ነው፥ ሴትነት እና ወንድነት በተፈጥሮ ከአሏህ የተሰጠን ጸጋ ነው፦
4፥32 *"አላህም ከፊላችሁን በከፊሉ ላይ በእርሱ ያበለጠበትን ጸጋ አትመኙ! ለወንዶች ከሠሩት ሥራ እድል አላቸው፥ ለሴቶችም ከሠሩት ሥራ ዕድል አላቸው፡፡ አላህንም ከችሮታው ለምኑት፥ አላህ በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው"*፡፡ وَلَا تَتَمَنَّوْا مَا فَضَّلَ اللَّهُ بِهِ بَعْضَكُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ ۚ لِّلرِّجَالِ نَصِيبٌ مِّمَّا اكْتَسَبُوا ۖ وَلِلنِّسَاءِ نَصِيبٌ مِّمَّا اكْتَسَبْنَ ۚ وَاسْأَلُوا اللَّهَ مِن فَضْلِهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا

እዚህ አንቀጽ ላይ "ያበለጠበ" ለሚለው ቃል የገባው "ፈዶለ" فَضَّلَ መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። ወንድነት ለወንድ የተሰጠ ጸጋ ነው፥ ለወንዶች ከሠሩት ሥራ እድል አላቸው። ሴትነት ለሴት የተሰጠ ጸጋ ነው፥ ለሴቶችም ከሠሩት ሥራ ዕድል አላቸው። ለወንድ የተሰጠውን ጸጋ ሴት መመኘት የለባትም! ለሴት የተሰጠ ጸጋ ወንድ መመኘት የለበትም። አንዱ የሌላው ማሟያ"complement" እንጂ እኩል አይደሉም፥ ወንድ በሴት ላይ ሴት በወንድ ላይ የሚበላለጡት ጸጋ አለ። ይህ ሆኖ ሳለ ዛሬ እኩልነት በሚል መርሕ ሴት ቆማ ትሽና፣ ወንድ ማርገዝ ይችላል፣ ጾታን በኦፕሬሽን ማስቀየር፣ ወንድ ወንድን ማግባት፣ ሴት ሴትን ማግባት የእንስታዊነት እኩልነት እሳቤ ነው፥ ይህ እሳቤ ከአሏህ መራቅና መገለል ነው። ከዚህ የአሏህን ፍጥረት ከማስለወጥ አጀንዳ በስተ ጀርባ ያለው ሸይጧን ነው፥ ሸይጧን፦ "አዛቸውና የአላህን ፍጥረት ይለውጣሉ" ብሏል፦
4፥119 *"በእርግጥ አጠማቸዋለሁም፡፡ ከንቱን አስመኛቸዋለሁም፡፡ አዛቸውምና የእንስሶችን ጆሮዎች ይተለትላሉ፡፡ አዛቸውና የአላህን ፍጥረት ይለውጣሉ" ያለውን ይከተላሉ፡፡ ከአላህም ሌላ ሰይጣንን ረዳት አድርጎ የሚይዝ ሰው ግልጽ ክስረትን በአርግጥ ከሰረ፡፡ وَلَأُضِلَّنَّهُمْ وَلَأُمَنِّيَنَّهُمْ وَلَآمُرَنَّهُمْ فَلَيُبَتِّكُنَّ آذَانَ الْأَنْعَامِ وَلَآمُرَنَّهُمْ فَلَيُغَيِّرُنَّ خَلْقَ اللَّهِ ۚ وَمَن يَتَّخِذِ الشَّيْطَانَ وَلِيًّا مِّن دُونِ اللَّهِ فَقَدْ خَسِرَ خُسْرَانًا مُّبِينًا

ስለዚህ የእንስታዊነት እኩልነት እሳቦትና አብዮት መሰልጠን ሳይሆን መሰይጠን ነው፥ ሥልጣኔ በምጣኔ ካልሆነ መሰልጠን ሳይሆን መሰይጠን ነው። ኢሥላም፦ "ወንድና ሴት አንዱ በሌላው ላይ ይበላለጣሉ፤ አንዱ ያነሰበትን ሌላው ማሟያ ነው እንጂ እኩል አይደሉም" ስለሚል ሚሽነሪዎች የምዕራባውያንን እሳቦትና ርዕዮት ለማራገብ ጠብ እርግፍ፣ ደፋ ቀና፣ ሰበር ሰካ፣ ወጋ ነቀል ሲሉ ይታያሉ። ባይብልም ቢሆን፦ "ወንድና ሴት እኩል ናቸው" አይልም፥ ባይሆን ወንድ የሴት ጌታ፣ ራስ፣ ገዢ እንደሆነ ይናገራል፦
ዘፍጥረት3፥16 ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም *ገዥሽ* ይሆናል።
ኤፌሶን 5፥23 ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ *"ባል የሚስት ራስ ነውና"*።
1ኛ ጴጥሮስ 3፥5-6 *እንዲህ በቀድሞ ዘመን በእግዚአብሔር ተስፋ ያደረጉት ቅዱሳት ሴቶች ደግሞ "ለባሎቻቸው ሲገዙ" ተሸልመው ነበርና፤ እንዲሁም ሣራ ለአብርሃም፦ "ጌታ" ብላ እየጠራችው ታዘዘችለት*።

ሕግ ደግሞ እንደሚል ሴቶች እንዲገዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውምና፥ ይህም ሕግ፦ "ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል" የሚል ነው። ሚስት ለጌታ እግዚአብሔር እንደምትገዛ ለባሏ መገዛት እንዳለባት ጳውሎስ ይናገራል፦
1ኛ ቆሮንቶስ 14፥34 *"ሴቶች በማኅበር ዝም ይበሉ! ሕግ ደግሞ እንደሚል እንዲገዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውምና"*።
ኤፌሶን 5፥22 *"ሚስቶች ሆይ! ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ"*።

ጳውሎስ ሴት በማኅበር ብቻ ሳይሆን በነገር ሁሉ ለባሏ እየተገዛች በዝግታ እንድትማር እና እንድትኖር እንጂ ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን አይፈቅድም፦
1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥11 *"ሴት በነገር ሁሉ *እየተገዛች* በዝግታ ትማር! ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም"*።

በማኅበር ማለትም ሰዎች በተሰበሰቡበት ስብስብ ሁሉ በውይይት፣ በምክክር፣ በንግግር መናገር የለባትም ዝም ትበል የሚል ወፍራም ትእዛዝ አለ፥ በማሕበራዊ ሚድያ ላይ የሚንጦሎጦሉ ክርስቲያያን ሴቶች ምን ይውጣቸው ይሆን? በዚህ ቢበቃ ጥሩ ነበር! ቅሉና ጥቅሉ ባይብል እና አዋልድ፦ “ሴት “ደካማ ፍጥረት ናት። በተፈጥሮዋ ደካማ ናት፤ የሰማችውን ሁሉ ሳታመዛዝን አሜን ብላ ትቀበላለችና” ይለናል፦
1 ጴጥሮስ 3፥7 እንዲሁም፥ እናንተ ባሎች ሆይ፥ *”ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑ”* ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ።
ቀለሜንጦስ 2÷14 *”ሴት በተፈጥሮዋ ደካማ ናት፤ የሰማችውን ሁሉ ሳታመዛዝን አሜን ብላ ትቀበላለችና”*።

የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ ይሉሃል እንደዚህ ነው። ለማንኛውም ሲራክ ለመሆን ይህቺን መጣጥፍ ስንክሳር አድርጋችሁ ያዟት! ስርጉት እና ትሩፋት ከአላህ ዘንድ ነው፥ አላህ ይወፍቃችሁ! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አሥ-ሠላሙ ዐለይኩም ያ ጀመዓህ!

ጽሑፎችን ወደ ድምጽ በመቀየት ለአዳማጮች ማቅረብ ጀምረናል። በመንገድ ላይ፣ በሥራ ላይ፣ በመኝታዎት ላይ ሆነው ያድምጡ! ሰብስክራይብ እና ሼር ማድረግዎን አይርሱ!
https://m.youtube.com/watch?feature=youtu.be&v=fEqBN-j5g24
ኢየሱስ አብ ነውን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

59፥24 እርሱ አላህ ፈጣሪው *አስገኚው*፣ ቅርጽን አሳማሪው ነው፡፡ ለእርሱ መልካሞች ስሞች አሉት፡፡ በሰማያትና በምድርም ያለው ሁሉ ለእርሱ ያሞግሳል፡፡ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው። هُوَ ٱللَّهُ ٱلْخَٰلِقُ ٱلْبَارِئُ ٱلْمُصَوِّرُ ۖ لَهُ ٱلْأَسْمَآءُ ٱلْحُسْنَىٰ ۚ يُسَبِّحُ لَهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۖ وَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ

“ኣብ” אַבָּא ማለት በዕብራይስጥ “አስገኚ”orginator” ማለት ነው፤ ሁላችንንም ያስገኘ “አንድ አስገኚ” አለ፦
ሚልክያስ 2፥10 ለሁላችን *”አንድ አባት”* ያለን አይደለምን? *አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን*?
ማቴዎስ 23፥9 *አባታችሁ አንዱ* እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ *ማንንም፦ አባት ብላችሁ አትጥሩ*።
ዮሐንስ 8፥41 *አንድ አባት* አለን *እርሱም እግዚአብሔር ነው*፡ አሉት።

በምድር ላይ ማንም አባት ብላችሁ አትጥሩ ሲባል የሰማዩ አባት አንድ ኣብ ነው ሲባል “አንድ ፈጣሪ” ነው በሚል ሒሳብ ነው አይሁዳውያን የሚረዱት እንጂ “ያለድ” יָלַד ማለትም “ወላጅ” የሚለውን አይደለም፤ ይህ አንድ ኣብ አንድ አምላክ ነው፤ የሁሉም ማለትም የኢየሱስ እና የሐዋርያትም አስገኚ ነው፦
ኤፌሶን 4፥6 ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር *አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ*።
ዮሐንስ 20፥17 እኔ ወደ *አባቴ* እና ወደ *አባታችሁ* ወደ *አምላኬ* እና ወደ *አምላካችሁ* ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው፡ አላት።

በዚህ ቀመርና ስሌት ከሆነ አላህ “አል-ባሪ” البَارِئ ማለትም “አስገኚው” ነው፤ “አል-ባሪ” የሚለው ስም ሶስት ጊዜ በቁርአን መጥቷል፤ ዒሳ ሆነ መላው ኑባሬ “ባሪያህ” بَرِيَّة ማለትም “ግኝት” ነው፦
59፥24 እርሱ አላህ ፈጣሪው *አስገኚው*፣ ቅርጽን አሳማሪው ነው፡፡ ለእርሱ መልካሞች ስሞች አልሉት፡፡ በሰማያትና በምድርም ያለው ሁሉ ለእርሱ ያሞግሳል፡፡ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው። هُوَ ٱللَّهُ ٱلْخَٰلِقُ ٱلْبَارِئُ ٱلْمُصَوِّرُ ۖ لَهُ ٱلْأَسْمَآءُ ٱلْحُسْنَىٰ ۚ يُسَبِّحُ لَهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۖ وَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ
2፥54 ሙሳም ለሕዝቦቹ፡- «ሕዝቦቼ ሆይ! እናንተ ወይፈንን አምላክ አድርጋችሁ፤ በመያዛችሁ ነፍሶቻችሁን በደላችሁ፡፡ ወደ *ፈጣሪያችሁም* ተመለሱ፤ ነፍሶቻችሁንም ግደሉ፤ ይሃችሁ *በፈጣሪያችሁ* ዘንድ ለእናንተ በላጭ ነው» ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ በእናንተም ላይ ጸጸትን በመቀበል ተመለሰላችሁ፡፡ እነሆ እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡ وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِۦ يَٰقَوْمِ إِنَّكُمْ ظَلَمْتُمْ أَنفُسَكُم بِٱتِّخَاذِكُمُ ٱلْعِجْلَ فَتُوبُوٓا۟ إِلَىٰ بَارِئِكُمْ فَٱقْتُلُوٓا۟ أَنفُسَكُمْ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌۭ لَّكُمْ عِندَ بَارِئِكُمْ فَتَابَ عَلَيْكُمْ ۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلتَّوَّابُ ٱلرَّحِيمُ

እዚህ ድረስ ከተግባባ ኢየሱስ አብ ነው ብለው የሚያምኑት የሐዋርያት ቤተክርስቲያን በተለምዶ “ኦንልይ ጂሰስ” የሚባሉት ሲሆኑ በጥንት ሳባልዮሳውያን ይባላሉ፤ የሊብያው ኤጲስ ቆጶስ የሰባልዮስን እሳቤ ስለሚያራምዱ ነው። የሰባልዮሳውያን ትምህርት ከሥላሴአውያን”Trinitarian” ትምህርት የማይተናነስ መወዛገብ የያዘ ትምህርት ነው፤ ይህንን መወዛገብ እስቲ እንመልከት፦
ዮሐንስ 14፥10 *እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ* አታምንምን? እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም፤ ነገር ግን *በእኔ የሚኖረው አብ* እርሱ ሥራውን ይሠራል።

ነጥብ አንድ
“አብም በእኔ እኔ በአብ”
እዚህ ጥቅስ ላይ “እኔ አብ ነኝ” የሚል ሽታው እንኳን የለም፤ ጭራሽ ኢየሱስ ከአብ የተለየ ማንነት መሆኑን የሚያሳይ ነው፤ “እኔ በአብ እንዳለሁ” i am in the Father” ἐγὼ ἐν τῷ πατρὶ ማለት ኢየሱስ በአብ ውስጥ እንዳለ እንጂ ኢየሱስ አብ መሆኑን በፍፁም አያሳይም፤ “ኤን” ἐν የሚለው መስተዋድ በተሳቢ “አብ” እና በባለቤት “እኔ” መካከል የገባ ነው፤ “እኔ አብ ነኝ” i am the Father” ለማለት “ውስጥ” የሚለው መስተዋድ ወጥቶ መነበብ ነበረበት፤ በመቀጠል “አብም በእኔ እንዳለ”The Father in me” ὁ πατὴρ ἐν ἐμοί ἐστιν ማለት አሁንም አብ በኢየሱስ ውስጥ እንዳለ እንጂ ኢየሱስ አብ መሆኑን በፍፁም አያሳይም፤ “ኤን” ἐν የሚለው መስተዋድ በተሳቢ “እኔ” እና በባለቤት “አብ” መካከል የገባ ነው፤ የሐዋርያት ቤተክርስቲያን ወልድ የአብ ስጋ ስለሆነ አብ በእኔ ውስጥ ማለቱ አብ በስጋ ውስጥ መሆኑን ያሳያል ይላሉ፤ ይህ አያስኬድም፤ ምክንያቱም አንደኛ ስጋ “እኔ” አይልም፤ ሁለተኛ አብ በእኔ አለው ማለት በስጋ ውስጥ አብ አለ ማለት ከሆነ እኔ በአብ አለው ማለት ስጋው በአብ ውስጥ አለ ማለት ነውን? ሲሰልስ “እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ” ማለት “ኢየሱስ ከአብ ጋር አብ ከኢየሱስ ጋር ያለውን ግንኙነት”inter-Relationship” ያሳያል፤ ይህንን እዛው አውድ ላይ መረዳት ይቻላል፦
ዮሐንስ 14፥20 እኔ በአባቴ እንዳለሁ *”እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ”* በዚያን ቀን ታውቃላችሁ።

“እናንተም በእኔ እንዳላችሁ” you are in me” ὑμεῖς ἐν ἐμοὶ ማለት ሐዋርያት በኢየሱስ ውስጥ እንዳሉ እንጂ ሐዋርያት ኢየሱስ መሆቸውን በፍፁም እንደማያሳይ ሁሉ “እኔ በአባቴ እንዳለሁ” ማለት ኢየሱስ አብ መሆኑን አያሳይም፤ “ኤን” ἐν የሚለው መስተዋድ በተሳቢ “ኢየሱስ” እና በባለቤት “ሐዋርያት” መካከል የገባ ነው፤ በመቀጠል “እኔም በእናንተ እንዳለሁ” i am in you” κἀγὼ ἐν ὑμῖν ማለት ኢየሱስ በሐዋርያት ውስጥ እንዳሉ እንጂ ሐዋርያት ኢየሱስ መሆቸውን በፍፁም እንደማያሳይ ሁሉ “አብም በእኔ እንዳለ” ማለት ኢየሱስ አብ መሆኑን አያሳይም፤ “ኤን” ἐν የሚለው መስተዋድ በተሳቢ “ሐዋርያት” እና በባለቤት “ኢየሱስ” መካከል የገባ ነው፤ “እናንተም በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ” ማለት ኢየሱስ ከሐዋርያት ጋር ሐዋርያት ከኢየሱስ ጋር ያላቸውን ግንኙነት”intet-Relationship” ያሳያል እንጂ ኢየሱስ ሐዋርያት መሆኑን አሊያም ሐዋርያት ኢየሱስ መሆናቸውን ካላሳየ “እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ” ማለት ኢየሱስ ከአብ ጋር አብም ከኢየሱስ ጋር ያላቸውን ግንኙነት”intet-Relationship” ያሳያል እንጂ ኢየሱስ አብ መሆኑን አሊያም አብ ኢየሱስ መሆኑን አያሳይም። ይህ የሰዋስው ሙግት ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው።
ነጥብ ሁለት
“በእኔ የሚኖረው አብ”
“የሚኖረው” dwelleth” የሚለው ቃል አሁንም አብ በአብሮነት ከኢየሱስ ጋር እንዳለ ያሳያል እንጂ ኢየሱስ የአብ ስጋ ወይም አብ መሆኑን አያሳይም፤ ይህንን ሙግት እስቲ እንመልከት፦
1 ዮሐንስ 4፥16 እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል፥ አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር *በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል*።

“ይኖራል” dwelleth” የሚለው ይሰመርበት፤ “አማኝ በእግዚአብሔር ይኖራል” ማለት እግዚአብሔር የአማኙ ስጋ ነው ማለት ነውን? አማኙ እግዚአብሔር ነው ማለት ነውን? “እግዚአብሔርም በአማኙ ይኖራል” ማለት አማኙ የእግዚአብሔር ስጋ ነው ማለት ነውን? እግዚአብሔር አማኙ ነው ማለት ነውን? አይ አማኙ ከእግዚአብሔር ጋር እግዚአብሔር ከአማኙ ጋር ያላቸውን ግንኙነት”intet-Relationship” ያሳያል ከሆነ መልሱ እንግዲያውስ “በእኔ የሚኖረው አብ” የሚለውንም በዚህ ስሌት ተረዱት። ይህ የሥነ-አመክንዮ ሙግት ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው።

መደምደሚያ
አብ የሁሉም አስገኚ ከሆነ “ኣብ” የኢየሱስ አባት ነው፤ ይህ የኢየሱስ አባት ማን ነው? እራሱ ኢየሱስ? አይደለም፤ ታዲያ ማን ነው? ይህ የኢየሱስ አባት አንዱ እግዚአብሔር ነው፦
ሮሜ 15፥5 በአንድ ልብ ሆናችሁ በአንድ አፍ *እግዚአብሔርን፥ እርሱም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት*፥ ታከብሩ ዘንድ፥
ቆላስይስ 1፥5 የጌታችንን *የኢየሱስ ክርስቶስን አባት እግዚአብሔርን* ሁልጊዜ እናመሰግናለን፤

በአበይት ክርስትና ማለትም በካቶሊክ፣ በኦርቶዶክስ፣ በፕሮቴስታት እና በእንግሊካን ኢየሱስ አብ አይደለም፤ ታዲያ አብ ማን ነው? መልሱ አብ እግዚአብሔር ነው፤ ስለዚህ ኢየሱስ አብ ስላልሆነ አብ እግዚአብሔር ከሆነ ኢየሱስ እግዚአብሔር ሳይሆን የእግዚአብሔር ልጅ ነው፤ አንዱ አምላክ የሁሉም አስገኚ ስለሆነ አዳምም ሆነ መላእክት የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው፦
ሉቃስ 3፥38 የመላልኤል ልጅ፥ የቃይናን ልጅ፥ የሄኖስ ልጅ፥ የሴት ልጅ፥ *የአዳም ልጅ፥ የእግዚአብሔር ልጅ*።
ኢዮብ 38፥6 አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥ *የእግዚአብሔርም ልጆች* ሁሉ እልል ሲሉ፥ መሠረቶችዋ በምን ላይ ተተክለው ነበር? የማዕዘንዋንስ ድንጋይ ያቆመ ማን ነው?

መላእክት ሆነ አዳም እናት እና አባት የላቸው ያስገኛቸው አንዱ አምላክ ነው፤ በተመሳሳይ ኢየሱስ አባት የለውም፤ ያለ አባት ያስገኘው አንዱ አምላክ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የተቀረጸ ምስል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ነቢያት አንድም ቀን ለተቀረጸ ምስል ሰግደው አያውቁም፥ ለተቀረጸ ምስል ስገዱለት የሚል መመሪያም አልተቀበሉም አላስተላለፉም። ከዚያ በተቃራኒው የሙሴ አምላክ ለሙሴ፦ “የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ፣ የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፣ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም” ብሎ አዞልታ፤ እንደውም መዝሙረኛው፦ “ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ ይፈሩ” ይላል፦
ዘሌዋውያን 26፥1 እኔ ያህዌህ አምላካችሁ ነኝና ለእናንተ *”ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ”፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ*።
ዘጸአት 20፥4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር *”የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፤ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም”*፤
መዝሙር 97፥7 *”ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ፥ በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ*”፤ መላእክቱ ሁሉ ስገዱለት።

የሰው እጅ ሥራን የተቀረጸ ምስልን የሚያደርግ፥ በስውርም የሚያቆመው ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላና የተረገመ ነው። ነቢያትም የተቀረጸውን ምስል ሠራተኛ እንደሚሰራው፣ የተቀረጸውን ምስል የሚሠሩ ከንቱ እንደኾኑ እና ለእጃቸውም ሥራ ስለ ሰገዱ ፍርድ በእነርሱ ላይ እንደለ ተናግረዋል፦
ዘዳግም 27፥15 *በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ የሠራተኛ እጅ ሥራን የተቀረጸ ወይም ቀልጦ የተሠራ ምስልን የሚያደርግ፥ በስውርም የሚያቆመው ሰው ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ መልሰው አሜን ይላሉ*።
ኢሳይያስ 40፥19 *የተቀረጸውንስ ምስል ሠራተኛ ሠርቶታል*፥ አንጥረኛም በወርቅ ለብጦታል፥ የብሩንም ሰንሰለት አፍስሶለታል።
ኢሳይያስ 44፥9 *የተቀረጸውን ምስል የሚሠሩ ሁሉ ከንቱዎች ናቸው*፥
ኤርምያስ 1፥16 ስለ ክፋታቸውም ሁሉ፥ እኔን ስለ ተው ለሌሎችም አማልክት ስላጠኑ *ለእጃቸውም ሥራ ስለ ሰገዱ፥ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ*።

ሰው ለሠራው የእጅ ሥራ እንዴት ይሰገዳል? በኦርቶዶክስ፣ በካቶሊክ እና በአንግሊካን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለተቀረጸ ምስል የጸጋ ስግደት ይሰገዳል፤ ልብ አድርግ የጸጋ ስግደት ስገዱ የሚል ትእዛዝ የለም። በተቃራኒው ለተቀረጸ ምስል “አትስገድላቸው” የሚል ትእዛዝ ቢኖር እንጂ። ነገር ግን ይህ ግዑዝ ነገር በዐበይት ክርስቲያኖች ይሰገድለታል፥ ምስጋና ይቀርበለታል። ነቢያት፦ “ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ ይፈሩ” ሲሉ፥ ፈጣሪ “ለእጃቸውም ሥራ ስለ ሰገዱ፥ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ” ሲል እዚህ ቪድዮ ላይ ግን ለማይሰማ ለማይለማ፥ ለማይናገር ለማይጋገር ለተቀረጸ የኢየሱስ ምስል ተሸክመው ምስጋና ያቀርቡለታል። አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም