ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.7K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ጥንቧ ዘረኝነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

49፥13 *እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፡፡ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَاكُم مِّن ذَكَرٍ وَأُنثَىٰ وَجَعَلْنَاكُمْ شُعُوبًا وَقَبَائِلَ لِتَعَارَفُوا ۚ إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ اللَّهِ أَتْقَاكُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌ

“ዘረኝነት”racism” ማለት የራስን ቋንቋና ዘውግ አተልቆ የሌላውን ማሳነስ፣ ማግለል፣ መቃረን እና ማራከስ ነው። ዘረኝነት ትዳርን፣ ቤተሰብን፣ ጉርብትናን፣ ማህበረሰብን፣ ሃይማኖት፣ መንግሥትን፣ አገርን የሚበትን ክፉ በሽታ ነው። ዘረኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ጠርዘኝነት፣ ቡድንተኝነት ምንጫቸው “አህዋ” أَهْوَآء ማለትም “ዝንባሌ”inclination” ነው፤ አንድ ሙስሊም ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፦
79፥40-41 በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ *ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት*፡፡ وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَىٰ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ

ዝንባሌ ደግሞ ከተከተሉት ሊመለክ የሚችል አደገኛ ጣዖት ነው፦
25:43 *ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን? አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትሆናለህን?* أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا

ዘረኝነት ምንጯ ዝንባሌ ከሆነ ታዲያ ከዘረኝነት በሽታ ለመገላገል መፍትሔው ምንድን ነው? አዎ አምላካችን አላህ በቅዱስ ቃሉ የሚናገረውን እና ነብያችን”ﷺ” በሐዲሳቸው የተናገሩትን በጥሞና ሰምቶ መተግበር ነው፤ እስቲ ከቁርኣን እንጀምር፦
4፥1 *እናንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ የፈጠራችሁን ከእርስዋም መቀናጆዋን የፈጠረውን ከእነርሱም ብዙ ወንዶችንና ሴቶች የበተነውን ጌታችሁን ፍሩ*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ اتَّقُوا رَبَّكُمُ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَاحِدَةٍ وَخَلَقَ مِنْهَا زَوْجَهَا وَبَثَّ مِنْهُمَا رِجَالًا كَثِيرًا وَنِسَاءً

“ነፍሥ” نَفْس የሚለው ቃል አደምን ያሳያል፤ “መቀናጃዋ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል ”ዘውጀሃ” زَوْجَهَا ሲሆን የአደም ጥንድን ያሳያል፤ ይህቺም ጥንድ ሐዋ ናት፤ “ነፍሥ” በሚለው መነሻ ቅጥያ ላይ “ከ” የሚል መስተዋድድ አለ፤ ይህም ከአደም መፈጠራችንን ያሳያል፤ “ከእነርሱም” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሚንሁማ” مِنْهُمَا ሲሆን ሙተና ማለትም ሁለትዮሽ”dual” የሚያሳይ ነው፤ እነዚህ ሁለቱ አደምና ሐዋ ናቸው፤ “እነርሱም” በሚለው መነሻ ቅጥያ ላይ “ከ” የሚል መስተዋድድ አለ፤ ይህም ከአደምና ከሐዋ መፈጠራችንን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ታዲያ የአንድ እናት እና አባት ልጆች ከሆንን አንዱን ዘር ማብለጥ ሌላውን ማሳነስ ጠባብነት አይደለምን? አንድ ሙስሊምስ እንዲህ አይነት ውዝግብ ውስጥ መግባት የእምነትን ገመድ የሚበጥስ አይደለምን? አላህ ሁላችንንም የፈጠረን ከአንድ አባትና እናት ነው፦
49፥13 *እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፡፡ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَاكُم مِّن ذَكَرٍ وَأُنثَىٰ وَجَعَلْنَاكُمْ شُعُوبًا وَقَبَائِلَ لِتَعَارَفُوا ۚ إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ اللَّهِ أَتْقَاكُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌ

“ወንድ” እና “ሴት” በሚለው መነሻ ቅጥያ ላይ “ከ” የሚል መስተዋድድ አለ፤ ይህም ሰዎች ከወንድና ከሴት መፈጠራቸውን ያሳያል፤ አላህ ነገድ እና ጎሳ ያደረገን ብዙ ስለሆንን ለትውውቅ የትውልድ መዝገብ እንጂ አላህ ዘንድ ማነስ እና መተለቅ አላህ በመፍራት ብቻ ነው።
አማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ፣ ትግሬ ወዘተ ቋንቋ ነው፤ የቋንቋዎቻችን መለያየት ከአስደናቂ ታምራቶቹ ነው፤ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አሉበት፦
30፥22 ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፣ *የቋንቋዎቻችሁ እና የመልኮቻችሁም መለያየት ከአስደናቂ ታምራቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አሉበት*፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ خَلْقُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَاخْتِلَافُ أَلْسِنَتِكُمْ وَأَلْوَانِكُمْ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّلْعَالِمِينَ

ቋንቋዎች ይዘውት የመጡት ታሪክ፣ ባህል፣ ልማድ፣ ትውፊት፣ ወግ፣ ክህሎት እና ሙዳየ-ቃላት “ዘውግ” ethnic” ሆኗል፤ ይህ እራሱ የቻለ ውበት ነው። ነገድ እና ጎሳ ለዐዋቂዎች ተዓምራቶችና መተዋወቂያ ነው። ዘረኝነት ግን ከቋንቋ አሊያም ከቀለም የሚመጣ ሳይሆን የልብና የአስተሳሰብ በሽታ ነው። በኢስላም ደሃ ሃብታም ሳንል፤ ዘመድ ባዕድ ሳንል፣ ዝንባሌ ተከትለን ሳናዳላ ለአላህ ብለን ለሰው ሁሉ በትክክል ፍትሕ ቀዋሚዎች መሆን አለብን፦
4፥135 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *በትክክል ፍትሕ ቀዋሚዎች በራሳችሁ ወይም በወላጆችና በቅርብ ዘመዶች ላይ ቢኾንም እንኳ ለአላህ መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሀብታም ወይም ድኻ ቢኾን አላህ በእነርሱ ከእናንተ ይበልጥ ተገቢ ነው፡፡ እንዳታደሉም ዝንባሌን አትከተሉ፡፡ ብታጠምሙም ወይም መመስከርን ብትተው አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ بِالْقِسْطِ شُهَدَاءَ لِلَّهِ وَلَوْ عَلَىٰ أَنفُسِكُمْ أَوِ الْوَالِدَيْنِ وَالْأَقْرَبِينَ ۚ إِن يَكُنْ غَنِيًّا أَوْ فَقِيرًا فَاللَّهُ أَوْلَىٰ بِهِمَا ۖ فَلَا تَتَّبِعُوا الْهَوَىٰ أَن تَعْدِلُوا ۚ وَإِن تَلْوُوا أَوْ تُعْرِضُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا
6፥152 *”በተናገራችሁም ጊዜ በዘመዶቻችሁ ላይ ቢኾንም እንኳ እውነትን በመናገር አስተካክሉ”*፡፡ በአላህም ቃል ኪዳን ሙሉ፡፡ እነሆ ትገሰጹ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ፡፡ وَإِذَا قُلْتُمْ فَاعْدِلُوا وَلَوْ كَانَ ذَا قُرْبَىٰ ۖ وَبِعَهْدِ اللَّهِ أَوْفُوا ۚ ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُم بِهِ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ

ስለዚህ የቋንቋዎቻችሁ እና የመልኮቻችሁም መለያየት ከአስደናቂ ታምራቶቹ እንጂ መኩሪያ ወይም ማብጠልጠሊያ አይደለም፤ ዘረኝነት በዲንያ በአላህ ዘንድ ዋጋ የሚያሳጣ ሲሆን በአኺራም ደግሞ ለጀሃነም ይዳርጋል፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 344
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ *”አላህ ዐዘ ወጀል ከእናንተ የዘመነ-ጃሂሊያን ኩራት አስወግዷል፤ ይህም በዘር መኩራት ነው። ይ
ህ ለጥንቁቁ አማኝም ወይም ለአደገኛው ካሃዲ አንድ ብቻ ነው። እናንተ የአደም ልጆች ናችሁ፤ አደም ከአፈር ነው የመጣው፤ ሰዎች በዘራቸው የሚኮሩ ከሆነ ጀሃነምን ይሞሏታል፤ ወይም አላህ ዘንድ ዋጋቸው ጥንዚዛ በአፍንጫው ከሚሽከረከር ጉድፍ ያነሰ ከሆኑት ይሆናል*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ إِنَّ اللَّهَ عَزَّ وَجَلَّ قَدْ أَذْهَبَ عَنْكُمْ عُبِّيَّةَ الْجَاهِلِيَّةِ وَفَخْرَهَا بِالآبَاءِ مُؤْمِنٌ تَقِيٌّ وَفَاجِرٌ شَقِيٌّ أَنْتُمْ بَنُو آدَمَ وَآدَمُ مِنْ تُرَابٍ لَيَدَعَنَّ رِجَالٌ فَخْرَهُمْ بِأَقْوَامٍ إِنَّمَا هُمْ فَحْمٌ مِنْ فَحْمِ جَهَنَّمَ أَوْ لَيَكُونُنَّ أَهْوَنَ عَلَى اللَّهِ مِنَ الْجِعْلاَنِ الَّتِي تَدْفَعُ بِأَنْفِهَا النَّتْنَ ‏”‏

የአደም ልጆች የአንድ አባት እና እናት ልጆች ነን ብሎ ማስተንተን መጠበብ ሲሆን በዘረኝነት አራንቋ መለከፍ መጥበብ ነው፦
ሱነን ነሳኢ መጽሐፍ 37 , ሐዲስ 150
ጁንደብ ኢብኑ ዐብደላህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ *”ማንም ሰው ግልጽ ባልሆነ ነገር፣ በዘረኝነት ጥብቅና፣ በዘረኝነት መንገድ የተጋደለ ግድያው የጃህሊያ ነው*። عَنْ جُنْدُبِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ قَاتَلَ تَحْتَ رَايَةٍ عُمِّيَّةٍ يُقَاتِلُ عَصَبِيَّةً وَيَغْضَبُ لِعَصَبِيَّةٍ فَقِتْلَتُهُ جَاهِلِيَّةٌ ‏”‏

“ጃህሊያህ” جَاهِلِيَّةٌ ማለት “መሃይምነት” ማለት ነው፤ ቅድመ-ቁርኣን ያለው ጊዜ ዘመነ-ጃህሊያህ ይባላል፤ በእርግጥም በዘመነ-ጃህሊያህ ጊዜ የነበረችው ዘረኝነት ጥንብ ናት፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 45, ሐዲስ 81
ጃቢር ኢብኑ ዐብደላህ እንዳስተላለፈው፦ “በጉዞ ከነቢዩ”ﷺ” ጋር ነበርን፤ አንድ ሰው ከሙሃጅር ከአንሷር የሆነውን አንድ ሰው ጀርባውን መታው፤ አንሷሩም፦ “አንሷሪ ሆይ! አለ፤ ሙሃጅሩም፦ “ሙሃጅር ሆይ! አለ። ከዚያም የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” *”ይህ የጃህሊያህ አጠራር አይደለምን? አሉ፤ እነርሱም፦ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አንድ ሰው ከሙሃጅር ከአንሷር የሆነውን አንድ ሰው ጀርባውን መታው” አሉ፤ እርሳቸው፦ “እርሷን(ዘረኝነትን) ተዋት ጥንብ ናት” አሉ*። جَابِرَ بْنَ عَبْدِ اللَّهِ يَقُولُ كُنَّا مَعَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم فِي غَزَاةٍ فَكَسَعَ رَجُلٌ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ رَجُلاً مِنَ الأَنْصَارِ فَقَالَ الأَنْصَارِيُّ يَا لَلأَنْصَارِ وَقَالَ الْمُهَاجِرِيُّ يَا لَلْمُهَاجِرِينَ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ مَا بَالُ دَعْوَى الْجَاهِلِيَّةِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا يَا رَسُولَ اللَّهِ كَسَعَ رَجُلٌ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ رَجُلاً مِنَ الأَنْصَارِ ‏.‏ فَقَالَ ‏”‏ دَعُوهَا فَإِنَّهَا مُنْتِنَةٌ ‏
‏ ‏
“ሙሃጅር” مُهَاجِر ማለት “ስደተኛ” ማለት ሲሆን ከመካ የተሰደዱትን ሶሓብይን ያመለክታል፤ “አንሷር” أَنْصَارٍ ማለት “ረዳት” ማለት ሲሆን ከመካ የተሰደዱት የተቀበሉ የመዲና ሶሓብይን ያመለክታል።
አንዱ ዘር ተነስቶ ሌላውን ዘር ሲበድል የተበደለው ያልበደለውን በዘሩ ብቻ በቁርሾ ለመበቀል መነሳት ጠባብነት ነው፤ በኢስላም የቀደሙት ትውልድ በሰሩት ወንጀል የአሁኑን ትውልድ መጠየቅ ወይም መቅጣት እራሱ ሕግ መተላለፍ ነው፦
ሱነን ነሳኢ መጽሐፍ 37 , ሐዲስ 162
ዐብደላህ እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” አሉ፦.. *ሰው በአባቱ ወይም በወንድሙ ወንጀል አይቀጣም*። وَلاَ يُؤْخَذُ الرَّجُلُ بِجَرِيرَةِ أَبِيهِ وَلاَ بِجَرِيرَةِ أَخِيهِ ‏”
በተጨማሪም አንድ ሰው ባጠፋው ብዙኃኑን ዘር ማንቋሸሽ ወይም ማዋረድ ሐራም ነው፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 33, ሐዲስ 106
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ከሰዎች መካከል ትልቁ ውሸታም ሌላው ሰው ማንቋሸሽ እና መላውን ዘር ማዋረድ ነው*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ “‏ إِنَّ أَعْظَمَ النَّاسِ فِرْيَةً لَرَجُلٌ هَاجَى رَجُلاً فَهَجَا الْقَبِيلَةَ بِأَسْرِهَا

እረ እሩቅ ሳንሄድ ወደ ዘረኝነት የሚጣራ፣ በዘረኝነት መንገድ የሚታገል፣ በዘረኝነት መንገድ ሲከተል የሞተ ሰው ከነብያችን”ﷺ” ሱናህ ውጪ ነው፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 349
ጁበይር እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ወደ ዘረኝነት የሚጣራ ከእኛ አይደለም። በዘረኝነት መንገድ የሚታገኝ ከእኛ አይደለም። በዘረኝነት መንገድ ሲከተል የሞተ ከእኛ አይደለም*። عَنْ جُبَيْرِ بْنِ مُطْعِمٍ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ لَيْسَ مِنَّا مَنْ دَعَا إِلَى عَصَبِيَّةٍ وَلَيْسَ مِنَّا مَنْ قَاتَلَ عَلَى عَصَبِيَّةٍ وَلَيْسَ مِنَّا مَنْ مَاتَ عَلَى عَصَبِيَّةٍ ‏”‏

በድንበር፣ በክልል፣ በወሰን የከፋፈሉን ሰዎች ናቸው። ምድር እኮ የአላህ ናት፤ ተቸግረን ብንሰደድ ሰፊ ናት፤ ዋናው ይህቺ አንድ የተውሒድ መንገድ ሃይማኖታችን ናትና አላህን በብቸኝነት ማምለክ ነው፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! *ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ እኔንም ብቻ አምልኩኝ*፡፡ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّ أَرْضِي وَاسِعَةٌ فَإِيَّايَ فَاعْبُدُونِ
21፥91 *ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፡፡ እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ*፡፡ إِنَّ هَـٰذِهِ أُمَّتُكُمْ أُمَّةً وَاحِدَةً وَأَنَا رَبُّكُمْ فَاعْبُدُونِ

እንግዲህ ዲነል ኢስላምን የመሰለ ሰውን የሚያስተሳስር የአላህ ገመድ እያለ በዘረኝነት፣ በጎጠኝነት፣ በጠርዘኝነት፣ በቡድንተኝነት መለያየት “አትለያዩ” ያለን አላህ አለመታዘዝ ነው። በዘመነ-ጃህሊያህ ጊዜ ጠበኞችም በነበርን ጊዜ በእኛ ላይ የዋለውን የአላህን ጸጋ እናስታውስ፤ በልቦቻችሁም መካከል አስማማን፤ በጸጋውም ወንድማማቾች ሆንን፥ በእሳት ጉድጓድ አፋፍም ላይ በነበር ጊዜ አዳነን፦
3፥103 *የአላህንም የማመን ገመድ ሁላችሁም ያዙ፡፡ አትለያዩም፡፡ ጠበኞችም በነበራችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ የዋለውን የአላህን ጸጋ አስታውሱ፡፡ በልቦቻችሁም መካከል አስማማ፡፡ በጸጋውም ወንድማማቾች ኾናችሁ፡፡ በእሳት ጉድጓድ አፋፍም ላይ ነበራችሁ፡፡ ከእርስዋም አዳናችሁ*፡፡ እንደዚሁ ትመሩ ዘንድ አላህ ለእናንተ አንቀጾቹን ያብራራል፡፡ وَاعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللَّهِ جَمِيعًا وَلَا تَفَرَّقُوا ۚ وَاذْكُرُوا نِعْمَتَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ كُنتُمْ أَعْدَاءً فَأَلَّفَ بَيْنَ قُلُوبِكُمْ فَأَصْبَحْتُم بِنِعْمَتِهِ إِخْوَانًا وَكُنتُمْ عَلَىٰ شَفَا حُفْرَةٍ مِّنَ النَّارِ فَأَنقَذَكُم مِّنْهَا ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ لَكُمْ آيَاتِهِ لَعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ

በተሰጠን ጸጋ ልክ ወንድማማች መሆን ሲገባን ዛሬ በመሃይምነት አራንቋ ተጠቅተን በማህበራዊ ሚድያ ዘረኝነትን ስናራግብ እንውላለን፤ ኢስላም ዓለም-ዐቀፍ ሆኖ ሳለ ምነው ጠበብንሳ? ምነው ይህ ያህል ኢማናችን ወረደሳ? የኢሥላም ልዕልና ከዘር፣ ከብሔር፣ ከቋንቋ፣ ከቀለም፣ ከፓለቲካ በላይ ነው። አላህ ሁላችንም ያስተካክለን፥ ሂዳያ ይስጠን፣ ከጥንቧ ዘረኝነት ይጠብቀን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ኢሥላም ሰም እና ወርቅ የያዘ ቅኔ ነው፥ ሰሙ ሐቅ ሲሆን ወርቁ ፍትሕ ነው።
ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በራሱ በቂ ነው። እነዚህ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ እስር ቤት እየማቀቁ፣ እየተሰቃዩ፣ እየሞቱ ይገኛሉ፥ ለሚመለከተው አካል አቤት ማለት ይገባል። ዓለማችንን እያመሱት ያሉት ጥቂት ሰዎች ናቸው። አሏህ ፍርዱን ለንጹሃን ፍጡሮቹ የሚፈርድላቸው እና በበዳዮች ላይ የሚፈርድባቸው ጊዜ ቅርብ ነው። አሏህ ለፕላኔታችን ነስሩን ያቅርብልን! አሚን።

14፥42 *አላህንም በደለኞች ከሚሠሩት ግፍ ዘንጊ አድርገህ አታስብ፡፡ የሚያቆያቸው ዓይኖች በእርሱ እስከሚፈጡበት ቀን ድረስ ብቻ ነው*፡፡ وَلَا تَحْسَبَنَّ اللَّهَ غَافِلًا عَمَّا يَعْمَلُ الظَّالِمُونَ ۚ إِنَّمَا يُؤَخِّرُهُمْ لِيَوْمٍ تَشْخَصُ فِيهِ الْأَبْصَار

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ዐቅመ-ጋብቻ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

65፥4 *"እነዚያም ከሴቶቻቸው ከዐደፍ ያቋረጡት በዒዳቸው ሕግ ብትጠራጠሩ ዒዳቸው ሦስት ወር ነው፡፡ እነዚያም ገና ዐደፍ ያላዩት ዒዳቸው እንደዚሁ ነው፡፡ የእርግዝና ባለቤቶችም ጊዜያቸው እርጉዛቸውን መውለድ ነው"*፡፡ وَاللَّائِي يَئِسْنَ مِنَ الْمَحِيضِ مِن نِّسَائِكُمْ إِنِ ارْتَبْتُمْ فَعِدَّتُهُنَّ ثَلَاثَةُ أَشْهُرٍ وَاللَّائِي لَمْ يَحِضْنَ ۚ وَأُولَاتُ الْأَحْمَالِ أَجَلُهُنَّ أَن يَضَعْنَ حَمْلَهُنَّ

"ዐቅመ-ጋብቻ" ማለት አንድ ተባእት ለዐቅመ-አደም ሲደርስ እና አንዲት እንስት ለዐቅመ-ሐዋህ ስትደርስ ማለት ነው። ለምሳሌ “የቲም” يَتِيم ስንል አጠቃላይ “ወላጅ-አልባ” ማለትም “እናትና አባቱ” ወይም “አባቱን በልጅነቱ በሞት የተነጠቀ ሕፃን” ማለት ነው። የቲሞች እራሳቸው ይችሉ ወይም አይችሉ እንደሆነ ይፈተናሉ፥ ይህም ፈተና ለጋብቻ እስከሚደርሱበት ድረስ ነው፦
4፥6 *"የቲሞችንም ጋብቻን እስከደረሱ ጊዜ ድረስ ፈትኑዋቸው"*፡፡ وَابْتَلُوا الْيَتَامَىٰ حَتَّىٰ إِذَا بَلَغُوا النِّكَاحَ

"ኢዛ" إِذَا ማለት "ጊዜ" ማለት ሲሆን የጊዜ ተውሳከ-ግስ ነው። ጋብቻ የራሱ የሆነ ጊዜ እንዳለው አመላካች ነው፥ ይህም ጊዜ ለማመልከት "ጋብቻን እስከደረሱ" ድረስ በማለት ይናገራል። "በለጉ" بَلَغُوا ማለት "ለጋብቻ በሰሉ" ማለት ነው፥ "በለገ" بَلَغَ ማለት "ለጋብቻ በሰለ" ማለት ሲሆን "በለገት" بَلَغَت ማለት ደግሞ "ለጋብቻ በሰለች" ማለት ነው። "ባሊግ" بَٰلِغ ማለት እራሱ "ዐቅመ-ጋብቻ"Puberty" ማለት ነው፦
ተፍሢሩል ኢብኑ ከሲር 4፥6
*"ጋብቻን እስከደረሱ ጊዜ" የሚለውን ሙጃሂድ፦ "ለዐቅመ-ጋብቻ ነው" ብሏል፥ ዐበይት ምሁራን፦ "ለዐቅመ-ጋብቻ" ለጋዎች ኢሕቲላም ሲኖራቸው ነው" ብለዋል። አቢ ዳውድ በሡናው እንደዘገበው፥ ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአላህ መልዕክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ከዐቅመ-ጋብቻ በኃላ የቲምነት የለም"*።
( حتى إذا بلغوا النكاح ) قال مجاهد : يعني : الحلم . قال الجمهور من العلماء : البلوغ في الغلام تارة يكون بالحلم ، وهو أن يرى في منامه ما ينزل به الماء الدافق الذي يكون منه الولد . وقد روى أبو داود في سننه عن أمير المؤمنين علي بن أبي طالب ، رضي الله عنه ، قال : حفظت من رسول الله صلى الله عليه وسلم : " لا يتم بعد احتلام
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 18, ሐዲስ 12
ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ እንደተረከው፦ "የአላህ መልዕክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ከዐቅመ-ጋብቻ በኃላ የቲምነት የለም"*። قَالَ عَلِيُّ بْنُ أَبِي طَالِبٍ حَفِظْتُ عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لاَ يُتْمَ بَعْدَ احْتِلاَمٍ

"ዐቅመ-ጋብቻ" አካል ተራክቦ ለማድረግ ሲበስል ነው፥ ከዐቅመ-ጋብቻ በኃላ የቲምነት ስለሌለ የቲሞች እራሳቸው እንዲችሉ ይፈተናሉ። "ኢሕቲላም" احْتِلاَم ማለት አንድ ልጅ ወይም አንዲት ልጂት ተራክቦ ለማድረግ የሚኖራቸው ፈሳሽ ነው። ይህ ፈሳሽ እስኪመጣ ድረስ ለዐቅመ-ጋብቻ ስላልደረሱ የሚሠሩት ሥራ አይመዘገብም፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 48
ዓኢሻህ "ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአላህ መልዕክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ብዕር ከሦስት ሰዎች ተነስቷል። እነርሱም፦ የተኛ ሰው እስኪነሳ ድረስ፣ ዕብደ ወደ ዐቅሉ እስኪመለስ ድረስ፣ ልጅ እስኪጎሎብት ድረስ"*። عَنْ عَائِشَةَ، رضى الله عنها أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ رُفِعَ الْقَلَمُ عَنْ ثَلاَثَةٍ عَنِ النَّائِمِ حَتَّى يَسْتَيْقِظَ وَعَنِ الْمُبْتَلَى حَتَّى يَبْرَأَ وَعَنِ الصَّبِيِّ حَتَّى يَكْبَرَ ‏
በእንቅልፍ ልብ፣ በዕብደት እና በእንጭጭነት የሚደረግ ሥራ መላእክት አይመዘግቡትም። አንድ ሕጻን ለዐቅመ-አደም ከደረሰ የሰው ቤት ዘው ብሎ አይገባም፥ ከዚያ ይልቅ አንኳክቶ ያስፈቅዳል፦
24፥59 *"ከእናንተም ሕፃናቶቹ አቅመ አዳምን በደረሱ ጊዜ እነዚያ ከእነርሱ በፊት የነበሩት እንዳስፈቀዱ ያስፈቅዱ"*፡፡ وَإِذَا بَلَغَ الْأَطْفَالُ مِنكُمُ الْحُلُمَ فَلْيَسْتَأْذِنُوا كَمَا اسْتَأْذَنَ الَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ

አሁን እዚህ አንቀጽ ላይ "ኢዛ" إِذَا የሚለው የጊዜ ተውሳከ-ግስ የዐቅመ-ጋብቻ ጊዜ አመላካች ነው፥ ይህንን ዐቅመ-ጋብቻ ለማመልከት "በለገ" بَلَغَ የሚል የግስ መደብ ይጠቀማል። አንዲት እንስት ለዐቅመ-ሐዋህ የመድረሷ የመጀመሪያው እና ዐቢይ ምልክት አድሬን-አርክ"adrenarche" አካሏ ለተራክቦ ዝግጁ ሲሆን እንዲሁ ጡቷ ሲያጎጠጉጥ ቴል-አርክ"thelarche" እና ብብቷና ብልቷ አካባቢ ጸጉር መብቀል ፑብ-አርክ"Pubarche" ሲጀምር የምታመነጨው ፈሳሽ"Vaginal lubrication" እንጂ የወር አበባ አይደለም፥ የወር አበባ ማየት አንዲት ሴት ለዐቅመ-ሐዋህ መድረሷን ከሚያሳዩ ሁለተኛ እና ንዑስ ምልክት ዕንቁላል ማምረት ጎናድ-አርክ"gonadarche" እንዲሁ የወር አበባ ደም ሜን-አርክ"menarche" ነው። አንዲት ሴት ስታርጥ የወር አበባ ይቋረጣል፥ ያኔ የምታመነጨው ፈሳሽ ያለ የወር አበባ ተራክቦ ማድረግ ትችላለች። ምክንያቱም ተራክቦ ለማድረግ የወር አበባ ብቻውን መስፈት አይደለም፥ የወር አበባ ለፅንስ እንጂ ለተራክቦ መስፈት አይደለም፦
65፥4 *"እነዚያም ከሴቶቻቸው ከዐደፍ ያቋረጡት በዒዳቸው ሕግ ብትጠራጠሩ ዒዳቸው ሦስት ወር ነው፡፡ እነዚያም ገና ዐደፍ ያላዩት ዒዳቸው እንደዚሁ ነው፡፡ የእርግዝና ባለቤቶችም ጊዜያቸው እርጉዛቸውን መውለድ ነው"*፡፡ وَاللَّائِي يَئِسْنَ مِنَ الْمَحِيضِ مِن نِّسَائِكُمْ إِنِ ارْتَبْتُمْ فَعِدَّتُهُنَّ ثَلَاثَةُ أَشْهُرٍ وَاللَّائِي لَمْ يَحِضْنَ ۚ وَأُولَاتُ الْأَحْمَالِ أَجَلُهُنَّ أَن يَضَعْنَ حَمْلَهُنَّ

“ዒዳህ” عِدَّة ማለት ሁለት ጥንዶች ከተጋቡ በኃላ ተራክቦ አድርገው ከዚያም አለመግባባት ቢፈጠር ፍቺ ለማድረግ ቢያስቡ ቅድሚያ ነፍሰ-ጡር መሆኗን ለማረጋገጥ የሚቆይበት የሦስት ወር ጊዜ ቆይታ ነው። "ዐደፍ" ለሚለው የገባው ቃል "መሒድ" مَحِيض ሲሆን "የወር አበባ" ማለት ነው። አንድ ወንድ ከዐደፍ ያቋረጠች ማለትም ያረጠች ሴት ለመፍታት ምናልባት አርጣለች ተብሎ እግዝና ስለሚከሰት የሦስት ወር ጊዜ ይኖራታል። አንዲት ሴት ልጅ ለዐቅመ-ሐዋህ ስደርስ ግንኙነትን ሲታሰብ ወይም ሲፈለግ የሚወጣ ያዝ የሚያደርግና የሚያጣብቅ ቀለም አልባ እና ሽታ አልባ ቀጭን ፈሳሽ"nocturnal emission" አላት፥ ነገር ግን ይህ ፈሳሽ ኖሮ የወር አበባዋ ሳይመጣ ብዙ ጊዜ ሊቆይ ይችላል። ይህንን የወር አበባ ያላዩ ሴቶች መሃል ላይ እንቁላል ማምረት ችለው እርግዝና ሊከሰት ስለሚችል ሦስት ወር ባል የማይፈታበት ጊዜ አለ፦
2፥235 *የተጻፈውም ዒዳህ ጊዜውን እስከሚደርስ ድረስ ጋብቻን ለመዋዋል ቁርጥ አሳብ አታድርጉ፡፡ አላህም በነፍሶቻችሁ ያለውን ነገር የሚያውቅ መኾኑን ዕወቁ፤ ተጠንቀቁትም፡፡ አላህም መሓሪ ታጋሽ መኾኑን ዕወቁ"*፡፡ وَلَا تَعْزِمُوا۟ عُقْدَةَ ٱلنِّكَاحِ حَتَّىٰ يَبْلُغَ ٱلْكِتَٰبُ أَجَلَهُۥ ۚ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ يَعْلَمُ مَا فِىٓ أَنفُسِكُمْ فَٱحْذَرُوهُ ۚ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ حَلِيمٌۭ

እንግዲህ ዐቅመ-ሐዋህ ጅማሬው አካላዊ ሽግግር"physical transition" የሆኑት ጡቷ ማጎጥጎጥ፣ ብብትና ብልት አካባቢ ጸጉር ማብቀል፣ የተራክቦ ፈሳሽ ማመንጨት ሲሆን ቀጣዩ የእንቁላል እድገት"ovarian development" ልጅ ለመፅነስ መደላድል ነው፥ እንቁላሉ የወንድ የዘር ሕዋስ ካላገኘ የወር አበባ ሆኖ ይወጣል። ይህንን በቅጡ ያልተረዱ ሚሽነሪዎች ዐይናቸውን በማንሸዋረር "የወር አበባ ያላየች ሴት" የሚለውን "ለዐቅመ-ሐዋህ ያልደረሰች" ብለው በማውረግረግ ኢሥላምን ሊዘልፉ ይፈልጋሉ፥ ይህ የደፈረሰ መረዳት ከላይ ያለውን ተስተምህሮት ጥልልና ጥንፍፍ አድርጎ ካለማየት የመጣ የተሳከረ መረዳት ነው። በኢሥላም ምንም ነገር መጉዳት አይፈቀድም፥ ጉዳትም ካለ በቂሷስ ይፈረዳል እንጂ ጉዳት አይመለስም፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 13, ሐዲስ 34
ኢብኑ ዐባሥ እንደተረከው፦ የአላህ መልዕክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ *"መጉዳት የለም፥ ጉዳትንም መመለስ የለም"*። عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ لاَ ضَرَرَ وَلاَ ضِرَارَ ‏”‏ ‏.‏

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ብዙዎችን ለመቀየር ብዙዎች መሆን የለብህም፥ በዋጋ ከሁሉም የምታንሰው ትንሿ ጨው በዋጋ በሚበልጧት መኃል ገብታ ለሁሉም ለውጥ እና ጣዕምን እንደምትሰጥ ሁሉ በገባንበት ሁሉ የለውጥ እና የጣዕም ምክንያት ኢንሻሏህ እንሆናለህ፡፡ ከአንድ እስራ ሐሞት ይልቅ ጠብታ ማር ብዙ ንቦችን ትስባለች፥ ከጉልበት ብልሃት ከድፍረት ዕውቀት ይበልጣል።

ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
የቁርኣን ልኬት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

41፥42 *ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም፤ ጥበበኛ ምስጉን ከኾነው ጌታ የተወረደ ነው*፡፡ لَّا يَأْتِيهِ ٱلْبَٰطِلُ مِنۢ بَيْنِ يَدَيْهِ وَلَا مِنْ خَلْفِهِۦ ۖ تَنزِيلٌۭ مِّنْ حَكِيمٍ حَمِيدٍۢ

“አት-ተቅዪሥ” التقييس ማለት “ልኬት”Standardization” ማለት ነው፥ ቁርኣን በወረደበት ጊዜ ዐረቦች የተለያየ “ለህጃህ” لهجة ማለትም “ዘዬ”dialect” ነበራቸው፤ እነርሱም፦ “ቁሬይሽ” “ሁድኸይል” “ጠቂፍ” “ሃዋዚን” “ኪናነህ” “ተሚን” “የመኒ” የመሳሰሉት ነበሩ፣ እነዚህ ዘዬዎች የአነባነብ ሥርአታቸው ላይ “ተሽኪል” تَشْكِيل ማለትም “አናባቢ ድምጽ”Vowelling mark” ይለያያሉ፤ ይህም ልዩነት በማጥበቅና በማላላት፣ በመጎተትና በመጠቅለል የቃሉን መልእክት የተለያየ ትርጉም እንዲኖረው ሊያደርግ ይችላል። ለምሳሌ በአገራችን፦
“ገና” ብለን “ገ” ሆሄን ስናጥብቀው “ልደት” ማለት ሲሆን ስናላላው “መዘግየት” የሚል ትርጉም ይኖረዋል።
“የማይገባው” ብለን “ገ” ሆሄን ስናጥብቀው “ብቃት” ማለት ሲሆን ስናላላው ደግሞ “መረዳት” የሚል ትርጉም ይኖረዋል።
“የማይረዳኝ” ብለን “ዳ” ሆሄን ስናጥብቀው “ሃሳቤን የማይገባው” ማለት ሲሆን ስናላላው “የችግሬ መፍትሄ የማይሆን” የሚል ትርጉም ይኖረዋል።
“ዋና” ብለን “ዋ” ሆሄን ስናጥብቀው “ዐብይ” ማለት ሲሆን ስናላላው “መዋኘት” የሚል ትርጉም ይኖረዋል። እንዲሁ በዐረቢኛ ለምሳሌ፦
“አሊም” أَلِيم የሚለው በመነሻ ላይ በሃራካ “ሀምዛህ” ا ፈትሓህ “አ” أ አድርገን ስንቀራ “ህመም” ማለት ሲሆን “ዐሊም” عَلِيم የሚለውን በመነሻ ላይ በሃረካ “ዐይን” ع ፈትሓህ “ዐ” عَ አድርገን ስንቀራ ደግሞ “ዐዋቂ” ማለት ነው፡፡
“ከፈረ” كَفَرَ የሚለውን በግንድ ላይ በሃረካ “ፋ” ف ፈትሓህ “ፈ” فَ አድርገን ስንቀራ “ካደ” ማለት ሲሆን “ከፈረ” كَفَّرَ የሚለውን በግንድ ላይ በሸዳ “ፋ” ف ተሽዲድ ፈትሓህ “ፍፈ” فَّ አድርገን ስንቀራ “ሸፈነ” ማለት ነው።
“ነዘለ” نَزَلَ የሚለውን በግንድ ላይ በሃረካ “ዛል” ز ፈትሓህ “ዘ” زَ አድርገን ስንቀራ “ወረደ” ማለት ሲሆን “ነዘለ” نَزَّلَ የሚለውን በግንድ ላይ በሸዳ “ዛል” ز ፈትሓህ ተሽዲድ ፈትሓ “ዝዘ” زَّ አድርገን ስንቀራ “አወረደ” ማለት ነው። ብዙ ናሙና ማቅረብ ይቻል ነበር፤ ግን ይህ በቂ ነው፤ ይህ ሙግት የሥነ-አናባቢ ጥናት”orthography” ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ነው።

ሌላው “አብጀድ” أَبْجَد ማለትም “ተነባቢ ፊደላት”consonant” ላይም ልዩነት አላቸው፤ ድምጽ ያላቸው ሐርፎች 28 ሲሆን “አሊፍ” ا ደግሞ “አጫዋች ፊደል”stretch letter” ነው፤ በጥቅሉ 29 ሐርፎች ሲሆኑ በመካከላቸው ስናነባቸው የሚቀጥኑ ሐርፎች 19 ሲሆኑ “ተርቂይቅ” تَرْقِيْقٌ ይባላሉ፣ የሚወፍሩ ሐርፎች ደግሞ 7 ሲሆኑ “ተፍኺይም” تَفْخِيْمُ ይባላሉ፣ የሚወፍርና የሚቀጥኑ ሐርፎች ደግሞ ሁለት ሲሆኑ አንደኛው “ሯ” ر በፈትሓህ እና በደማ ሲቀራ ይወፍራል፤ በከስራ ሲቀራ ይቀጥናል። ሁለተኛ “ላም” ل በለፍዙል ጀላላ ማለትም በአላህ ስም ላይ ሲቀራ ይወፍራል፤ በሌሎች ላይ ሲቀራ ይቀጥናል።
በእነዚህ ተነባቢ ፊደላት ላይ “ኑቅጧህ” نُقْطَة‎ ማለትም “ነጥብ” ያላቸው 16 ሐርፎች “ሙአጀማ” ሲባሉ ነጥብ የሌላቸው 14 ሐርፎች ደግሞ “ሙሃመላ” ይባላል፣ አንዷ ሐርፍ “ያ” ي ደግሞ ሁለቱንም ናት።
ሐርፎች በመነሻ ቅጥያ”Prefix” ላይ፣ በግንድ”stem” ላይ እና በመዳረሻ ቅጥያ”Suffix” ላይ ቅርጻቸው ሲቀያየር “ረሥም” رَسْم ይባላል። ለናሙና ያክል አንዳንድ ሃርፎችን እንመልከት፦
1. ባ ب
መነሻ بـ መካከልـبـ መዳረሻ ـب
2. ታ ت
መነሻ تـ መካከልـتـ መዳረሻ ـت
3. ሳ ث
መነሻ ثـ መካከል ـثـ መዳረሻ ـث
4. ጂም ج
መነሻ جـ መካከል ـجـ መዳረሻ ـج
5. ሐ ح
መነሻح ـ መካከል ـحـ መዳረሻ ـح
6. ኸ خ
መነሻ خـ መካከል ـخـ መዳረሻ ـخ
ይህ ሙግት የሥነ-ተናባቢ ጥናት”Typography” ታሳቢ እና ዋቢ ያደረገ ነው። ይህ እንዲህ በእንዲህ እያለ ቁርኣን በቁሬይሽ ዘዬ ወረደ፤ ሌሎች ሁድኸይል፣ ጠቂፍ፣ ሃዋዚን፣ ኪናነህ፣ ተሚን፣ የመኒ ወዘተ ከዚህ ዘዬ ወስደው ሲጠቀሙ በማጥበቅና በማላላት፤ በማቅጠንና በማወፈር በትርጉም ላይ ልዩነት አመጣ፤ ይህ ልዩነት ከዐረብ ውጪ ላሉት መከፋፈል አመጣ፤ ይህንን ልዩነት የታዘበው የነቢያችን”ﷺ” ሰሃቢይ ሑደይፋህ ኢብኑል-የማን በወቅቱ ኸሊፋህ ለነበረው ለዑስማን በመናገር በቁሬይሽ ዘዬ አንድ የጋራ ልኬት እንዲደረግ ተደርጓል፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 9
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ *”የሻም ሕዝብ እና የኢራቅ ሕዝብ አርመንያን እና አዛርባጃንን ለማሸነፍ ጦርነት ባደረጉ ጊዜ ሑደይፋህ ኢብኑል-የማን ወደ ዑስማን ሲመጣ የሻም እና የኢራቅ ሕዝቦች በቂርኣት ዘዬ ላይ ሲለያዩ ፈራ፤ ከዚያም ሑደይፋህም ለዑስማን፦ “የምእመናን አሚር ሆይ! ይህንን ዑማህ ታደግ፤ ስለ መጽሐፉ ከዑማህ በፊት ልክ የሁዲ እና ነሳራህ እንደተለያዩት እንዳይለያዩ። ከዚያም ዑስማንም ለሐፍሷህ፦ “የቁርኣን መሷሒፍ ላኪልኝ፤ በጥሩ ሙስሐፍ ካዘጋጀን በኃላ መሷሒፉን እመልስልሻለው” ብሎ ላከባት፤ ሐፍሷህም ለዑስማን ላከችለት፤ ከዚያም ዑስማን ለዘይድ ኢብኑ ሳቢት፣ ለዐብደሏህ ኢብኑ አዝ-ዙበይር፣ ለሠዒድ ኢብኑል ዓስ እና ለዐብዱ አር-ረሕማን ኢብኑል ሓሪስ ኢብኑ ሂሻም ከመሷሒፍ እንዲገለብጡ አዘዛቸው፤ ዑስማንም ለሦስቱ የቁሬይሽ ሰዎች፦ “ምናልባት በአገለባበጡ ከዘይድ ኢብኑ ሳቢት ጋር ያልተስማማችሁበት ነጥብ ካለ በቁሬሽ ዘዬ ጻፉት፤ ቁርኣን በእነርሱ ዘዬ ነው የወረደው፤ ከዚያም በእነርሱ ዘዬ አደረጉ። ብዙ ሱሑፎችን ገለበጡ፤ ዑስማንም የቁርኣንን መሷሒፍ ለሐፍሷህ መለሰላት። ከዚያም ዑስማንም ለሁሉም ሙስሊም አውራጃ እነርሱ ከገለበጡት ከላከ በኃላ ማንኛውም ሌሎች የቁርኣን እደ-ክታባት ሆኑ ግልባጮች ተቃጠሉ*። أَنَّ أَنَسَ بْنَ مَالِكٍ، حَدَّثَهُ أَنَّ حُذَيْفَةَ بْنَ الْيَمَانِ قَدِمَ عَلَى عُثْمَانَ وَكَانَ يُغَازِي أَهْلَ الشَّأْمِ فِي فَتْحِ إِرْمِينِيَةَ وَأَذْرَبِيجَانَ مَعَ أَهْلِ الْعِرَاقِ فَأَفْزَعَ حُذَيْفَةَ اخْتِلاَفُهُمْ فِي الْقِرَاءَةِ فَقَالَ حُذَيْفَةُ لِعُثْمَانَ يَا أَمِيرَ الْمُؤْمِنِينَ أَدْرِكْ هَذِهِ الأُمَّةَ قَبْلَ أَنْ يَخْتَلِفُوا فِي الْكِتَابِ اخْتِلاَفَ الْيَهُودِ وَالنَّصَارَى فَأَرْسَلَ عُثْمَانُ إِلَى حَفْصَةَ أَنْ أَرْسِلِي إِلَيْنَا بِالصُّحُفِ نَنْسَخُهَا فِي الْمَصَاحِفِ ثُمَّ نَرُدُّهَا إِلَيْكِ فَأَرْسَلَتْ بِهَا حَفْصَةُ إِلَى عُثْمَانَ فَأَمَرَ زَيْدَ بْنَ ثَابِتٍ وَعَبْدَ اللَّهِ بْنَ الزُّبَيْرِ وَسَعِيدَ بْنَ الْعَاصِ وَعَبْدَ الرَّحْمَنِ بْنَ الْحَارِثِ بْنِ هِشَامٍ فَنَسَخُوهَا فِي الْمَصَاحِفِ وَقَالَ عُثْمَانُ لِلرَّهْطِ الْقُرَشِيِّينَ الثَّلاَثَةِ إِذَا اخْتَلَفْتُمْ أَنْتُمْ وَزَيْدُ بْنُ ثَابِتٍ فِي شَىْءٍ مِنَ الْقُرْآنِ فَاكْتُبُوهُ بِلِسَانِ قُرَيْشٍ فَإِنَّمَا نَزَلَ بِلِسَانِهِمْ فَفَعَلُوا حَتَّى إِذَا نَسَخُوا الصُّحُفَ فِي الْمَصَاحِفِ رَدَّ عُثْمَانُ الصُّحُفَ إِلَى حَفْصَةَ وَأَرْسَلَ إِلَى كُلِّ أُفُقٍ بِمُصْحَفٍ مِمَّا نَسَخُوا وَأَمَرَ بِمَا سِوَاهُ مِنَ الْقُرْآنِ فِي كُلِّ صَحِيفَةٍ أَوْ مُصْحَفٍ أَنْ يُحْرَقَ‏.‏

ይህ ትልቅ መርሐ-ግብር ነው፤ የነቢያችን”ﷺ” ባልደረቦች ከቁርኣን ውጪ የነቢያችን”ﷺ” የሚሰሟቸው የቁርኣን ማብራሪያዎችን እና ዱዓዎችም በራሳቸው በሚጽፏቸው ቁርኣን ላይ ከግርጌ ፣ከራስጌ፣ ከፊት እና ከኃላ ይጽፉ ነበር፤ ይህ ጽሑፍ ለመጪው ትውልድ የቁርኣን ሱራ ተደርጎ እንዳይወሰድ ከላይ ከተጠቀሱ ችግሮች ጋር አብሮ ተቃጥሏል። ይህ የዑሥማን ልኬት ቱርክ ስታንቡል ቶካፒ በሚባል ሙዝየም ይገኛል። ይህንን ካርበን 14 በምርምር ከ 100-200 ዓመተ-ሒጅራህ ያሳያል። ይህንን የብራና ሙስሐፍ ከታች በፎቶ አስቀምጫለው። ይህ ከላይ ያለው መጣጥፍ የቁርኣን ዳራ ከሚል መጽሐፌ የተቀነጨበ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሲፍር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

39፥62 *አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፡፡ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ

አላህ “አል-ኻሊቅ” الخَٰلِق ማለትም “ፈጣሪ” ነው፥ ነገር ሁሉ ደግሞ “መኽሉቅ” مَخْلُق ማለትም “ፍጡር” ሲሆን አላህ የነገር ሁሉ ፈጣሪ ነው፦
39፥62 *አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፡፡ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ

“ሸይእ” شَىْء ማለት “ነገር’thing” ማለት ሲሆን “ነገር” በሚለው ቃል ውስጥ ዘመካን ይካተታል፥ “ዘመካን” زَمَكَان ማለት የዘማንና የመካን ቃላት ውቅር ነው። “ዘማን” زَمَان ማለት “ጊዜ”time” ማለት ነው፥ “መካን” مَكَان ደግሞ “ቦታ”space” ማለት ነው። ምንም ነገር ሳይኖር አላህ ብቻውን ነበረ፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 59, ሐዲስ 2
ዒምራም ኢብኑ ሑሰይን እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”ምንም ነገር ሳይኖር አላህ ነበረ። ከዚያ ዙፋኑን በውኃ ላይ ነበረ፥ ከዚያ ሁሉን ነገር ጻፈ። ከዚያ ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ"*። عَنْ عِمْرَانَ بْنِ حُصَيْنٍ، قَالَ إِنِّي عِنْدَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم كَانَ اللَّهُ وَلَمْ يَكُنْ شَىْءٌ غَيْرُهُ، وَكَانَ عَرْشُهُ عَلَى الْمَاءِ، وَكَتَبَ فِي الذِّكْرِ كُلَّ شَىْءٍ، وَخَلَقَ السَّمَوَاتِ وَالأَرْضَ ‏

"ነገር" ከመፈጠሩ በፊት "ምንም" ነው። "ሲፍር" صِفْر የሚለው ቃል "ሶፊረ" صَفِرَ ማለትም "ምንም አደረገ" "ባዶ አደረገ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ምንም"empty" "no-thing" ማለት ነው፥ በግዕዝ "አልቦ" ሲባል በኢንግሊዝ "ዜሮ" 0 ይባላል። ሁሉም ነገር ዜሮ ምድገት"zero volume" ሆኖ ሳለ አምላካችን አላህ እምኀበ አልቦ ኀበቦ ማለትም ካለመኖር ወደ መኖር በይኹን ቃል ያስገኘው ነው፦
2፥117 *ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን» ነው፤ ወዲያውም ይኾናል*፡፡ بَدِيعُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
16፥40 *ለማንኛውም ነገር መኾኑን በሻነው ጊዜ ቃላችን ለእርሱ “ኹን” ማለት ብቻ ነው፥ ወዲውም ይኾናል*፡፡ إِنَّمَا قَوْلُنَا لِشَيْءٍ إِذَا أَرَدْنَاهُ أَن نَّقُولَ لَهُ كُن فَيَكُونُ

“ቃላችን” የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። የሚፈጥበት የይኹን ቃል ግን ከነገር ውጪ የፈጣሪ ባሕርይ ነው። "ነገርን" ማስገኘት ሲፈልግ በቃሉ “ኩን” كُن ማለትም “ኹን” ይለዋል፥ ይኾናል። አምላካችን አሏህ ሁሉን ነገር በይሁን ንግግሩ ከማስገኘቱ በፊት ቀድሮታል፦
65፥3 *"አላህ ለነገሩ ሁሉ የተወሰነ ጊዜን በእርግጥ አድርጓል"*፡፡ إِنَّ اللَّهَ بَالِغُ أَمْرِهِ ۚ قَدْ جَعَلَ اللَّهُ لِكُلِّ شَيْءٍ قَدْرًا

አላህ መጀመሪያ የፈጠረው ቀለምን ነው፥ አሏህ ለቀለም፦ "ለዘላለም የሚሆነውን ጻፍ" አለው። አሏህ ከአምስት መቶ ሺህ ዓመት በፊት የፍጥረትን ግብዓት በጥብቁ ሰሌዳ ጻፈ፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3637
አቡ ሙሐመድ አለ፦ አባቴ ከአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሰማው ብሎ እንደተከልኝ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ *"መጀመሪያ አላህ የፈጠረው ቀለምን ነው፥ አሏህ ለእርሱ ለዘላለም የሚሆነውን ጻፍ አለው"*። فَقَالَ عَطَاءٌ لَقِيتُ الْوَلِيدَ بْنَ عُبَادَةَ بْنِ الصَّامِتِ قَالَ حَدَّثَنِي أَبِي قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ “‏ إِنَّ أَوَّلَ مَا خَلَقَ اللَّهُ الْقَلَمَ فَقَالَ لَهُ اكْتُبْ فَجَرَى بِمَا هُوَ كَائِنٌ إِلَى الأَبَدِ ‏
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 46, ሐዲስ 27
ዐብደላህ ኢብኑ ዐምር ኢብሙል ዓስ ሰምቶ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"አላህ ሰማያትን እና ምድርን ከመፍጠሩ ከአምስት መቶ ሺህ ዓመት በፊት የፍጥረትን ግብዓት ጻፈ"*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرِو، بْنِ الْعَاصِ قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ كَتَبَ اللَّهُ مَقَادِيرَ الْخَلاَئِقِ قَبْلَ أَنْ يَخْلُقَ السَّمَوَاتِ وَالأَرْضَ بِخَمْسِينَ أَلْفَ سَنَةٍ

አላህ ፍጥረትን ከምንም እንደ ፈጠረ እንዲሁ ፍጥረትን በፍርድ ቀን "ምንም" ያረገዋል፦
21፥104 *የመጀመሪያን ፍጥረት እንደ ጀመርን እንመልሰዋለን*፡፡ መፈጸሙ በእኛ ላይ የኾነን ቀጠሮ ቀጠርን፡፡ እኛ ሠሪዎች ነን፡፡ كَمَا بَدَأْنَا أَوَّلَ خَلْقٍ نُّعِيدُهُ ۚ وَعْدًا عَلَيْنَا ۚ إِنَّا كُنَّا فَاعِلِينَ

ከፍጥረት በፊት መጀመሪያ የሌለው ቀዳማይ እንደሆነ ሁሉ ከፍጥረት በኃላ መጨረሻ የሌለው ደኃራይ ይሆናል። የመጀመሪያን ፍጥረት ምንም በማድረግ ያጠፋውና ከፍጥረት በፊት ብቻውን እንደነበረ ይሆናል፦
28፥88 ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ አትግገዛ፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ *ነገሩ ሁሉ ከአላህ በቀር ጠፊ ነው*፡፡ ፍርዱ የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ወደ እርሱም ትመለሳላችሁ፡፡ وَلَا تَدْعُ مَعَ اللَّهِ إِلَـٰهًا آخَرَ ۘ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ كُلُّ شَيْءٍ هَالِكٌ إِلَّا وَجْهَهُ ۚ لَهُ الْحُكْمُ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ

"ነገሩ ሁሉ ከአላህ በቀር ጠፊ ነው" የሚለው ይሰመርበት። "ነገር" በሙሉ ጠፊ ነው፥ አላህ ብቻውን ይቀራል። ከዚያም በፍርዱ ቀን "ኹን" ሲል ፍጥረት ካለመኖር ወደ መኖር ተመልሶ ይመጣል፦
6፥73 እርሱም ያ ሰማያትንና ምድርን በእውነት የፈጠረ ነው፡፡ *«ኹን» የሚልበትንና ወዲያውም የሚኾንበትን ቀን አስታውስ፡፡ ቃሉ እውነት ነው*፡፡ በቀንዱም በሚነፋ ቀን ንግሥናው የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ጥበበኛው ውስጥ ዐዋቂው ነው፡፡ وَهُوَ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ بِالْحَقِّ ۖ وَيَوْمَ يَقُولُ كُن فَيَكُونُ ۚ قَوْلُهُ الْحَقُّ ۚ وَلَهُ الْمُلْكُ يَوْمَ يُنفَخُ فِي الصُّورِ ۚ عَالِمُ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ ۚ وَهُوَ الْحَكِيمُ الْخَبِيرُ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ወሕይ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

42፥51 *ለሰው አላህ በራእይ፣ ወይም ከግርዶ ወዲያ፣ ወይም መልክተኛን መልአክን የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን “የሚያወርድለት” ቢሆን እንጅ በገሃድ “ሊያናግረው” ተገቢው አይደለም”*፥ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና። وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ ٱللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِن وَرَآئِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًۭا فَيُوحِىَ بِإِذْنِهِۦ مَا يَشَآءُ ۚ إِنَّهُۥ عَلِىٌّ حَكِيمٌۭ

“ወሕይ” وَحْى የሚለው ቃል “አውሓ” أَوْحَىٰ ማለትም “ገለጠ” ወይም “አወረደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ግልጠተ-መለኮት” ወይም “ግህደተ-መለኮት”Revelation” ማለት ነው። “ወሕይ” የሚለው የስም መደብ በቁርኣን 6 ጊዜ ተጠቅሷል፥ “አውሓ” የሚለው የግስ መደብ እንደየ ዐውዱ የተለያየ ትርጉም ለመስጠት 72 ጊዜ ተጠቅሷል። ቁርኣን ላይ ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ አሳብና ትርጉም አለው ማለት አይደለም፥ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጉም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው። ለምሳሌ ዘከርያ ወደ ሕዝቦቹ ጌታችሁን አወድሱ! በማለት ተናግሯል፦
19፥11 ከምኩራቡም በሕዝቦቹ ላይ ወጣ፥ *"ወደ እነርሱ፦ "በጧት እና በማታ ጌታችሁን አወድሱ! በማለት "ጠቀሰ"*፡፡ فَخَرَجَ عَلَىٰ قَوْمِهِ مِنَ الْمِحْرَابِ فَأَوْحَىٰ إِلَيْهِمْ أَن سَبِّحُوا بُكْرَةً وَعَشِيًّا

"ጠቀሰ" ለማለት የገባው ቃል "አውሓ" أَوْحَىٰ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። እዚህ አንቀጽ ላይ መታየት ያለበት ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው አሳብ ነው። ስለዚህ “አውሓ” أَوْحَىٰ ማለት "ገለጠ" ማለት ብቻ ሳይሆን "አሳወቀ" ወይም "ተናገረ" በሚል ይመጣል፦
16፥68 *"ጌታህም ወደ ንብ እንዲህ ሲል አስታወቀ፦ «ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ ሰዎች ከሚሠሩትም ቀፎ ቤቶችን ያዢ"*፡፡ وَأَوْحَىٰ رَبُّكَ إِلَى النَّحْلِ أَنِ اتَّخِذِي مِنَ الْجِبَالِ بُيُوتًا وَمِنَ الشَّجَرِ وَمِمَّا يَعْرِشُونَ
99፥5 *"ጌታህ ለእርሷ በማሳወቁ ምክንያት"*፡፡ بِأَنَّ رَبَّكَ أَوْحَىٰ لَهَا

ሁለቱም አናቅጽ ላይ "አሳወቀ" ለሚለው የገባው ቃል "አውሓ" أَوْحَىٰ ነው። አምላካችን አሏህ በሁሉም ሰማያት ውስጥ ትእዛዙ አውርዷል፦
41፥12 *"በሁለት ቀኖችም ውስጥ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው፡፡ በሰማይቱም ሁሉ ነገሯን አዘጋጀ"*፡፡ فَقَضَاهُنَّ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ فِي يَوْمَيْنِ وَأَوْحَىٰ فِي كُلِّ سَمَاءٍ أَمْرَهَا ۚ
65፥12 አላህ ያ ሰባትን ሰማያት የፈጠረ ነው፡፡ ከምድርም መሰላቸውን ፈጥሮአል፥ *"በመካከላቸው ትእዛዙ ይወርዳል"*፡፡ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ وَمِنَ الْأَرْضِ مِثْلَهُنَّ يَتَنَزَّلُ الْأَمْرُ بَيْنَهُنَّ لِتَعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ وَأَنَّ اللَّهَ قَدْ أَحَاطَ بِكُلِّ شَيْءٍ عِلْمًا

"ነገሯን" ለሚለው የገባው ቃል "አምረ-ሃ" أَمْرَهَا ሲሆን "ትእዛዝ" በሚል ለማመልከት "አምር" أَمْر ተብሏል። "አዘጋጀ" ለሚለው የገባው ቃል "አውሓ" أَوْحَىٰ ሲሆን "የተነዘሉ" يَتَنَزَّلُ ማለትም "ይወርዳል" በሚል መጥቷል። አምላካችን አሏህ በሰማያት ውስጥ ወዳሉት መላእክት ትእዛዙን መናገሩን ፍትውና ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፦
53፥26 *"በሰማያት ውስጥ ካሉ መላእክትም ብዙዎች ሊማለዱለት ለሚሻውና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢኾን እንጅ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም"*፡፡ وَكَم مِّن مَّلَكٍ فِي السَّمَاوَاتِ لَا تُغْنِي شَفَاعَتُهُمْ شَيْئًا إِلَّا مِن بَعْدِ أَن يَأْذَنَ اللَّهُ لِمَن يَشَاءُ وَيَرْضَىٰ
8፥12 *ጌታህ ወደ መላእክቱ፦ «እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና እነዚያን ያመኑትን አጽናኑ! በእነዚያ በካዱት ልቦች ውስጥ ፍርሃትን በእርግጥ እጥላለሁ፡፡ ከአንገቶችም በላይ ራሶችን ምቱ! ከእነርሱም የቅርንጫፎችን መለያልይ ሁሉ ምቱ» ሲል ያወረደውን አስታውስ*፡፡ إِذْ يُوحِي رَبُّكَ إِلَى الْمَلَائِكَةِ أَنِّي مَعَكُمْ فَثَبِّتُوا الَّذِينَ آمَنُوا ۚ سَأُلْقِي فِي قُلُوبِ الَّذِينَ كَفَرُوا الرُّعْبَ فَاضْرِبُوا فَوْقَ الْأَعْنَاقِ وَاضْرِبُوا مِنْهُمْ كُلَّ بَنَانٍ

"ያወረደው" ለሚለው የገባው ቃል "ዩሒ" يُوحِي ሲሆን "ያሳወቀው" "የተናገረው" ለማለት ተፈልጎ ነው። አሏህ ለሙሳ እናት ያሳወቃትን ነገር ለማመልከት "አውሐይና" أَوْحَيْنَا ማለትም "አሳወቅን" ብሎ ተናግሯል፦
20፥38 *"ወደ እናትህ በልብ የሚፈስን ነገር ባሳወቅን ጊዜ"*፡፡ إِذْ أَوْحَيْنَا إِلَىٰ أُمِّكَ مَا يُوحَىٰ
ነገር ግን አምላካችን አሏህ ወደ አንድ ረሡል የሚያወርደው ወሕይ “ከላሙ አት-ተሽሪዒይ” كَلَٰم التَشْرِعِي ነው፥ “ተሽሪዒይ” تَشْرِعِي የሚለው ቃል “ሸረዐ” شَرَّعَ‎ ማለትም “ደነገገ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ድንጋጌ” ወይም “ሕግጋት” ማለት ነው። ይህ ሸሪዓህ ከአላህ ወደ ነቢያቱ የሚወርድ አድርግ እና አታድርግ መመሪያ፣ መርሕ፣ ሥርዓት ነው፥ “ሸሪዓህ” شَرِيعَة ማለት “ትክክለኛ ሕግ” ማለት ነው። ይህ ወሕይ ለአንድ ነቢይ ከሦስት መንገድ በአንዱ መንገድ ይወርድለታል፦
42፥51 *ለሰው አላህ በራእይ፣ ወይም ከግርዶ ወዲያ፣ ወይም መልክተኛን መልአክን የሚልክ እና በፈቃዱ የሚሻውን “የሚያወርድለት” ቢሆን እንጅ በገሃድ “ሊያናግረው” ተገቢው አይደለም”*፥ እርሱ የበላይ ጥበበኛ ነውና። وَمَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُكَلِّمَهُ ٱللَّهُ إِلَّا وَحْيًا أَوْ مِن وَرَآئِ حِجَابٍ أَوْ يُرْسِلَ رَسُولًۭا فَيُوحِىَ بِإِذْنِهِۦ مَا يَشَآءُ ۚ إِنَّهُۥ عَلِىٌّ حَكِيمٌۭ

"የሚያወርድለት" ለሚለው የገባው ቃል "ዩሒየ" فَيُوحِىَ መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። ለአንድ ነቢይ ወሕይ የሚመጣለት መንገድ በራእይ ወይም ያለ ራእይ እና ያለ መልአክ ከግርዶ ወዲያ አሊያል በመልአክ ነው። “መለክ” مَلَك ወይም “መልአክ” مَلْأَك የሚለው ቃል “ለአከ” لَأَكَ ማለትም “ላከ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ተላላኪ” ማለት ነው።
ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ የጂን ሸያጢን ወደ የሰው ሸያጢን ወደ መተተኛ፣ ወደ ድግምተኛ፣ ወደ ጠንቋይ ወዘተ ንግግራቸውን ያወርዳሉ፦
6፥112 *"እንደዚሁም ለነቢያት ሁሉ ከሰውና ከጋኔን የኾኑን ሰይጣናት ጠላት አደረግን፡፡ ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ለማታለል ልብስብስን ቃል ይጥላሉ"*፡፡ وَكَذَٰلِكَ جَعَلْنَا لِكُلِّ نَبِيٍّ عَدُوًّا شَيَاطِينَ الْإِنسِ وَالْجِنِّ يُوحِي بَعْضُهُمْ إِلَىٰ بَعْضٍ زُخْرُفَ الْقَوْلِ غُرُورًا
6፥121 በእርሱም ላይ የአላህ ስም ካልተጠራበት ነገር አትብሉ፡፡ እርሱም በእርግጥ አመጽ ነው፡፡ *"ሰይጣናትም ወደ ወዳጆቻቸው በክትን በመብላት ይከራከሯችሁ ዘንድ ያሾከሹካሉ"*፡፡ وَلَا تَأْكُلُوا مِمَّا لَمْ يُذْكَرِ اسْمُ اللَّهِ عَلَيْهِ وَإِنَّهُ لَفِسْقٌ ۗ وَإِنَّ الشَّيَاطِينَ لَيُوحُونَ إِلَىٰ أَوْلِيَائِهِمْ لِيُجَادِلُوكُمْ

"ይጥላሉ" ለሚለው የገባው የግስ መደብ "ዩሒ" يُوحِي ሲሆን "ያሾካሽካሉ" ለሚለው የገባው የግስ መደብ ደግሞ "ለዩሑነ" لَيُوحُونَ ሲሆን "ያወርዳሉ" ማለት ነው። ይህ የሚወሠውሱት ነገር ወሥዋሥ ነው፥ “ወሥዋሥ” وَسْوَاس ማለት “ጉትጎታ” ማለት ነው። ስለ ወሕይ እሳቤ በግርድፉ እና በሌጣው ይህንን ይመስላል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሐዲሱ አን-ነበዊይ እና ሐዲሱል ቁድሢይ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት! ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

“ሐዲስ” حَدِيث የሚለው ቃል “ሐደሰ” حَدَّثَ‎ ማለትም “ተናገረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ንግግር” ማለት ነው፥ ነቢያችን”ﷺ” በዐቂዳህ እና በፊቅህ ነጥብ ላይ የሚናገሩት ሐዲስ ሁሉ ወሕይ ነው፦
53፥3 *ከልብ ወለድም አይናገርም*፡፡ وَمَا يَنطِقُ عَنِ الْهَوَىٰ
53፥4 *እርሱ ንግግሩ የሚወረድ ወሕይ እንጅ ሌላ አይደለም*፡፡ إِنْ هُوَ إِلَّا وَحْيٌ يُوحَىٰ

“ወሕይ” وَحْي የሚለው ቃል “አውሓ” أَوْحَىٰٓ ማለትም “ገለጠ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ግልጠተ-መለኮት” ማለት ነው። “መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት! ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ” የሚለው ይህንኑ ሡናህ ዋቢና ታሳቢ ያደረገ ነው፦
59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት! ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

ታዲያ ቁርኣን እና ሐዲስ ልዩነቱ ምንድን ነው? አዎ! ቁርኣን ለፍዙ ሆነ መዕናው የአላህ ነው፥ ሐዲስ ግን ለፍዙ የነቢያችን”ﷺ” ሲሆን ማዕናው የአላህ ነው። “ለፍዝ” لَفْظ ማለት “ቃል”Verbatim” ማለት ሲሆን “መዕና” مَعْنًى ማለት “መልእክት” “እሳቤ” “አሳብ”notion” ማለት ነው። የቁርኣን ተናጋሪ አላህ ብቻ ነው፥ ቃሉም የወከለው መልእክቱ፣ “እሳቤው፣ አሳቡ የራሱ ነው። ሐዲስ ደግሞ መልእክቱ፣ “እሳቤው፣ አሳቡ የአላህ ሲሆን ቃሉ ግን የራሳቸው የነቢያችን”ﷺ” ነው። አላህ የሐዲስን መልእክት ሲያወርድላቸው እሳቸው በራሳቸው ባህል፣ ወግ፣ ልምድ፣ ክህሎት፣ ትውፊት ያብራሩታል። ይህ ሐዲስ ደግሞ በሁለት ይከፈላል፥ እርሱም ሐዲሱ አን-ነበዊይ እና ሐዲሱል ቁድሢይ ነው።

ነጥብ አንድ
"ሐዲሱ አን-ነበዊይ"
“ነቢይ” نَبِيّ የሚለው ቃል “ነበአ” نَبَّأَ ማለትም “የሩቅ ወሬን አወራ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “የሩቅ ወሬ አውሪ” ማለት ነው፥ የነቢይ ገላጭ መደብ ደግሞ "ነበዊይ" نَبَوِيّ‎ ሲሆን "ነቢያዊ" ማለት ነው። በጥቅሉ "ሐዲሱ አን-ነበዊይ" حَدِيث الْنَبَوِيّ‎ ማለት "ነቢያዊ ሐዲስ" ማለት ነው፥ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ" ወይም "ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ" ተብሎ የሚናገሩት ንግግር ሁሉ ሐዲሱ አን-ነበዊይ ይባላል። ለምሳሌ፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 27, ሐዲስ 62
አቢ ዘር እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”የአንተ ፈገግታ በወንድምህ ፊት ለአንተ ሶደቃህ ነው”*። عَنْ أَبِي ذَرٍّ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ تَبَسُّمُكَ فِي وَجْهِ أَخِيكَ لَكَ صَدَقَةٌ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 80, ሐዲስ 102
አቢ ሙሣ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ጌታውን የሚዘክር እና የማይዘክር ምሳሌ፥ ልክ እንደ ሕያው እና እንደ ሙታን ነው”*። عَنْ أَبِي مُوسَى ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَثَلُ الَّذِي يَذْكُرُ رَبَّهُ وَالَّذِي لاَ يَذْكُرُ مَثَلُ الْحَىِّ وَالْمَيِّتِ
ነጥብ ሁለይ
"ሐዲሱል ቁድሢይ"
"ቁድሥ" قُدْس የሚለው ቃል "ቀዱሠ" قَدُسَ ማለትም "ቀደሰ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ቅዱስ" ማለት ነው፥ የቁድሥ ገላጭ መደብ ደግሞ "ቁድሢይ" قُدْسِيّ ሲሆን "ቅዱሳዊ" ማለት ነው። በጥቅሉ "ሐዲሱል ቁድሢይ" حَدِيث الْقُدْسِيّ ማለት "ቅዱሳዊ ንግግር" ማለት ነው፥ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "አላህም እንዲህ አለ" ተብሎ የሚናገሩት ንግግር ሁሉ ሐዲሱል ቁድሢይ ይባላል። ለምሳሌ፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 13, ሐዲስ 212
አቢ ሁረይራ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "አላህም እንዲህ አለ፦ *“ከፆም በስተቀር የአደም ልጅ መልካም ሥራ ሁሉ ለራሱ ነው፥ ፆም ለእኔ ነው። እኔም ምንዳውን በእርሱ እከፍላለው"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ يَقُولُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ قَالَ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ كُلُّ عَمَلِ ابْنِ آدَمَ لَهُ إِلاَّ الصِّيَامَ فَإِنَّهُ لِي وَأَنَا أَجْزِي بِهِ

ነቢያችን"ﷺ" ይህንን ወደ አሏህ አስጠግተው የሚነግሩን ቅዱሳዊ ንግግራቸው ከቁርኣን የሚለየው፦
1ኛ. ቁርኣን የአሏህ ንግግር ብቻ ሲሆን ሐዲሱል ቁድሢይ ግን በነቢያችን"ﷺ" ንግግር "አሏህ አለ" ተብሎ በኒስባህ መነገሩ ነው።
2ኛ. ቁርኣን አሏህ በጂብሪል በኩል የተናገረው የራሱ ንግግር ሲሆን ሐዲሱል ቁድሢይ ግን በነቢያችን"ﷺ" ሕልም "አሏህ አለ" ተብሎ በኒስባህ መነገሩ ነው።
3ኛ. ቁርኣን ሲቀራ ዒባዳህ የሚፈጸምበት ሲሆን ሐዲሱል ቁድሢይ ግን አይቀራም፥ በመነበቡ ዒባዳም አይፈጸምበትም።
4ኛ. ቁርኣን እያንዳንዱ ሐርፍ መቅራት አስር ሐሠናት ሲኖረው ሐዲሱል ቁድሢይ ግን በውስጡ ያሉትን በመታዘዝ እንጂ በመነበቡ ሐሠናት የለውም።
5ኛ. ቁርኣን በሡራህ፣ በአያት እና በጁዝ የተከፋፈለ ሲሆን ሐዲሱል ቁድሢይ ግን በምንም አልተከፋፈለም።
6ኛ. ቁርኣን በውዱእ መንካት ሙስተሐብ እና ያለ ውዱእ መንካት መክሩህ ሲሆን ሐዲሱል ቁድሢይ ግን ያለ ውዱእ መንካት ሙባሕ ነው።
7ኛ. ከተራክቦ በኃላ ቁርኣን ለመንካት የጀናባህ ትጥበት ፈርድ ሲሆን ሐዲሱል ቁድሢይ ግን ያለ ጀናባህ ትጥበት መንካት ሙባሕ ነው።
8ኛ. በሐይድ ይ ያለች እንስት ቁርኣንን መንካት ክልክል ሲሆን ሐዲሱል ቁድሢይን ግን መንካት ሙባሕ ነው።
9ኛ. ቁርኣን ለነቢያችን"ﷺ" ነቢይነት ታምር ሲሆን ሐዲሱል ቁድሢይ ግን ለነቢያችን"ﷺ" ነቢይነት ታምር አይደለም።
10ኛ. ቁርኣን ከፊቱ እና ከኃላው ውሸት እንይመጣበት አሏህ ሙሉ ለሙሉ እንደሚጠብቀው ቃል የገባለት የራሱ ንግግር እና በሙተዋቲር የመጣ ሲሆን ሐዲሱል ቁድሢይ ግን ሐዲስ ውስጥ ስለሚካተት መቅቡል እና መርዱድ አሉት። "መቅቡል" مَقْبُول ማለት "ቅቡል" ማለት ሲሆን ተቀባይነት ያላቸው የሚባሉት ሶሒሕ እና ሐሰን የሆኑ ናቸው። "መርዱድ" مَردُود "ውድቅ" ማለት ሲሆን ውድቅ ሐዲስ የሚባሉት ዶዒይፍ እና መውዱዕ የሆኑ ናቸው።

ዋቢ መጽሐፍ የሼይኽ ዶክተር ያሲር ቋዲ መጽሐፍ ይመልከቱ፦
Abu Ammaar Yasir Qadhi 1999. Introduction to the Sciences of the Qura̓an. Page 72-74

“አሏሁ አዕለም” اَللّٰهُ أَعْلَم‎

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
👇🙏💜

በሽታ ከሰው ወደ ሰው እንደሚጋባ ሁሉ ጤንነትም ከሰው ወደ ሰው ይጋባል። ጤናማ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ጋር መዋል ጤናማ አስተሳሰብ እንድንይዝ ያረገናል። ሰው የአስተሳሰብ እና የድርጊት ውጤት ነው።

የአስተሳሰብ ውጤት
ሰው ለራሱ እራሱ የሚሰጠው እና የሚነገረው ነገር ያ ማንነቱ ነው። ወሒድ ማለት ወሒድ ለወሒድ የነገረው ነገር ነው። ለራሴ እችላለው፣ እሞክራለው፣ እጎብዛለው ብዬ ካልኩት እችላለው፣ እሞክራለው፣ እጎብዛለው፥ በተቃራኒው ለራሴ አትችልም፣ አረባም፣ ደካማ ነኝ ካልኩት እራሴ የማይችል፣ የማይረባ እና ደካማ እሆናለው።

የድርጊት ውጤት
ሰው አስተዳደጉ እና አዋዋሉ በሕይወቱ ላይ አውንታዊ ሆነ አሉታዊ ተጽእኖ ማድረግ ይችላል። ልጆቻችንን በጥሩ አስተዳደግ ማሳደግ እና አዋዋላቸውን ማሳመር አለብን! ይህ ትውልድን የመቅረጽ መርሐ-ግብር ለትውልድ የሚሆን መደላድል ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
የቂራኣት ልዩነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

25፥32 እነዚያ የካዱትም «ቁርኣን በእርሱ ላይ ለምን በጠቅላላ አንድ ጊዜ አልተወረደም» አሉ፡፡ *እንደዚሁ በእርሱ ልብህን ልናረጋ ከፋፍለን አወረድነው፤ ቀስ በቀስ መለያየትንም ለየነው*፡፡ وَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لَوْلَا نُزِّلَ عَلَيْهِ الْقُرْآنُ جُمْلَةً وَاحِدَةً ۚ كَذَٰلِكَ لِنُثَبِّتَ بِهِ فُؤَادَكَ ۖ وَرَتَّلْنَاهُ تَرْتِيلًا

“ቁርኣን” قُرْءَان የሚለው ቃል “ቀረአ” قَرَأَ ማለትም “አነበበ” ወይም “አነበነበ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “መነባነብ”recitation” ማለት ነው፤ የቁርኣን “አነባነብ” ደግሞ “ቂራኣት” قـِراءات ይባላል፤ አምላካችን አላህ በጂብሪል ለነቢያችን”ﷺ” ቁርኣንን አስቀርቷቸዋል፦
87፥6 *ቁርኣንን በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም*፡፡ سَنُقْرِئُكَ فَلَا تَنسَىٰ
75፥18 *ባነበብነውም ጊዜ ንባቡን ተከተል*፡፡ فَإِذَا قَرَأْنَاهُ فَاتَّبِعْ قُرْآنَهُ

“እናስነብብሃለን” ለሚለው የገባው “ሠኑቅኡሪኡከ” سَنُقْرِئُكَ ሲሆን “ባነበብነው” ለሚለው ደግሞ “ቀረእናሁ” قَرَأْنَاهُ ነው፤ ይህ የሚያሳየው የአላህ ንግግር መነባነብ መሆኑን ነው፤ አምላካችን አላህ ይህንን ቁርኣን ወደ ነቢያችን”ﷺ” ያስቀራው በተርቲል ነው፦
25፥32 እነዚያ የካዱትም «ቁርኣን በእርሱ ላይ ለምን በጠቅላላ አንድ ጊዜ አልተወረደም?» አሉ፤ *እንደዚሁ በእርሱ ልብህን ልናረጋ በተርቲል አነበብነው*፡፡ وَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لَوْلَا نُزِّلَ عَلَيْهِ الْقُرْآنُ جُمْلَةً وَاحِدَةً ۚ كَذَٰلِكَ لِنُثَبِّتَ بِهِ فُؤَادَكَ ۖ وَرَتَّلْنَاهُ تَرْتِيلًا

“ረተልናሁ” رَتَّلْنَاهُ ማለት “አነበብነው” ማለት ሲሆን “ተርቲል” تَرْتِيل ማለት “የአነባነብ ስልት”manner of recitation” ማለት ነው፦
73፥4 ወይም በእርሱ ላይ ጨምር፤ *ቁርኣንንም በተርቲል ማንበብን አንብብ*፡፡ أَوْ زِدْ عَلَيْهِ وَرَتِّلِ الْقُرْآنَ تَرْتِيلًا

እዚህ አንቀጽ ላይ “አንብብ” ለሚለው የገባው “ረተል” رَتَّلْ ሲሆን በተርቲል መቅራትን ያመልክታል፤ “ተርቲላ” تَرْتِيلًا የሚለው የተርቲል አንስታይ መደብ ነው። ይህ አንዱ ቁርኣን ወደ ነቢያችን”ﷺ” የወረደው በሰባት አይነት የአቀራር ስልት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 13
ኢብኑ ዐባሥ”ረ.ዐ.” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ጂብሪል ለእኔ በአንድ ሐርፍ አቀራር ይቀራልኝ ነበር፤ ከዚያም እኔ በሌላ ሐርፍ እንዲያስቀራኝ ጠየኩት፤ በተደጋጋሚ ስጠይቀው በሰባት አሕሩፍ በመቅራት ጨመረልኝ*። أَنَّ ابْنَ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما ـ حَدَّثَهُ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ أَقْرَأَنِي جِبْرِيلُ عَلَى حَرْفٍ فَرَاجَعْتُهُ، فَلَمْ أَزَلْ أَسْتَزِيدُهُ وَيَزِيدُنِي حَتَّى انْتَهَى إِلَى سَبْعَةِ أَحْرُفٍ ‏”‌‏.‏
“ሐርፍ” حَرف ማለት ቋንቋዊ ትርጉሙ “ፊደል” ማለት ሲሆን እዚህ ዐውድ ላይ ግን “የአነባነብ ስልት”mode of recitation” ማለት ነው፤ ምክንያቱም “አቅረአኒ” أَقْرَأَنِي ማለትም “ይቀራልኝ” የሚል ሃይለ-ቃል ስላለ፤ የሐርፍ ብዙ ቁጥር “አሕሩፍ” أَحْرُف ነው፤ ይህ የቁርኣን አነባነብ ልዩነት ከአላህ በጂብሪል ለነቢያችን”ﷺ” የተወረደ ሲሆን ይህንን ልዩነት በነብያችን”ﷺ” ዘመን በአንድ የቁሬሽ ዘዬ በነበሩት በዑመር ኢብኑል ኸጧብ”ረ.ዐ.” እና በሂሻም ኢብኑ ሐኪም”ረ.ዐ.” መካከል በነበረው የቂራኣት ልዩነት ማየት ይቻላል፦
ኢማም ቡኻርይ: መጽሐፍ 66, ሐዲስ 14
ዑመር ኢብኑል ኸጧብ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ *”የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” በሕይወት እያሉ ሂሻም ኢብኑ ሐኪም”ረ.ዐ.” ሱረቱል ፉርቃንን ሲቀራ ሰማሁት፤ የእርሱ አቀራር የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ለእኔ ባልቀሩልኝ በተለየ በሌላ ሐርፍ ሲቀራ ሰማሁት፤ በሶላቱ ላይ እያለ ወደ እርሱ ዘልዬ ነበር፤ ነገር ግን ንዴቴን መቆጣጠር ነበረብኝ፤ ሶላቱን በጨረሰ ጊዜ በአንገቱ ዙሪያ ከላይ ያለውን ልብስ አውልቄ በእርሱ ያዝኩትና፦ “እኔ የሰማሁትን ይህንን ማን ነው ያስተማረህ? ብዬ ስለው፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ብሎ መለሰልኝ፤ እኔም፦ “ከአንተ በተለየ ለእኔ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ያስተማሩኝ? ትዋሻለህ አልኩት፤ ከዚያም ወደ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አመጣሁት፤ ከዚያም፦ “ለአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ይህንን ሰው ሱረቱል ፉርቃንን እርሶ ባላስተማሩኝ ሐርፍ ሲቀራ ሰማሁት፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ “ልቀቀው፤ ሂሻም ሆይ! ቅራ አሉት፤ ከዚያም እኔ በሰማሁበት ሐርፍ ሲቀራ ሰማሁት፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ “በዚህ ሐርፍ ለእኔ ተወርዶልኛል፤ ዑመር ሆይ! ቅራ አሉኝ፤ እኔ እሳቸው ባስተማሩኝ ቀራሁኝ፤ እርሳቸውም፦ “ለእኔ በዚህ ሐርፍ ተወርዶልኛል፤ ቁርኣንን በሰባት ሐርፎች እንድቀራ ተወርዶልኛል፤ ስለዚህ የትኛውንም የሚቀላችሁን ቅሩት*። سَمِعَا عُمَرَ بْنَ الْخَطَّابِ، يَقُولُ سَمِعْتُ هِشَامَ بْنَ حَكِيمٍ، يَقْرَأُ سُورَةَ الْفُرْقَانِ فِي حَيَاةِ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَاسْتَمَعْتُ لِقِرَاءَتِهِ فَإِذَا هُوَ يَقْرَأُ عَلَى حُرُوفٍ كَثِيرَةٍ لَمْ يُقْرِئْنِيهَا رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَكِدْتُ أُسَاوِرُهُ فِي الصَّلاَةِ فَتَصَبَّرْتُ حَتَّى سَلَّمَ فَلَبَّبْتُهُ بِرِدَائِهِ فَقُلْتُ مَنْ أَقْرَأَكَ هَذِهِ السُّورَةَ الَّتِي سَمِعْتُكَ تَقْرَأُ‏.‏ قَالَ أَقْرَأَنِيهَا رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم‏.‏ فَقُلْتُ كَذَبْتَ فَإِنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَدْ أَقْرَأَنِيهَا عَلَى غَيْرِ مَا قَرَأْتَ، فَانْطَلَقْتُ بِهِ أَقُودُهُ إِلَى رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَقُلْتُ إِنِّي سَمِعْتُ هَذَا يَقْرَأُ بِسُورَةِ الْفُرْقَانِ عَلَى حُرُوفٍ لَمْ تُقْرِئْنِيهَا‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ أَرْسِلْهُ اقْرَأْ يَا هِشَامُ ‏”‌‏.‏ فَقَرَأَ عَلَيْهِ الْقِرَاءَةَ الَّتِي سَمِعْتُهُ يَقْرَأُ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ كَذَلِكَ أُنْزِلَتْ ‏”‌‏.‏ ثُمَّ قَالَ ‏”‏ اقْرَأْ يَا عُمَرُ ‏”‌‏.‏ فَقَرَأْتُ الْقِرَاءَةَ الَّتِي أَقْرَأَنِي، فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ كَذَلِكَ أُنْزِلَتْ، إِنَّ هَذَا الْقُرْآنَ أُنْزِلَ عَلَى سَبْعَةِ أَحْرُفٍ فَاقْرَءُوا مَا تَيَسَّرَ مِنْهُ ‏”‌‏.‏

እንግዲህ ይህንን ሰባት የአነባነብ ስልት ከነብያችን”ﷺ” በዋነኝነት ያስተላለፉ ሰሃባዎች ዑበይ ኢብኑ ከዐብ፣ ዘይድ ኢብኑ ሣቢት፣ ዐብደሏህ ኢብኑ መሥዑድ፣ አቡ አዝ-ዘርዳ፣ ዐሊ ኢብኑ አቡ ጧሊብ፣ አቡ ሙሳ አልሻሪ፣ ዑስማን ኢብኑ አፋን ናቸው።
በሰባቱ አነባነብ ስልት የተላለፈ ሪዋያህ ደግሞ፦
1ኛ. ቃሪ ከመዲና ናፊ ኢብኑ አብ ሲሆን ቂራአቱ የተላለፈው ደግሞ ከዑበይ ኢብኑ ከዐብ ነው።
2ኛ. ቃሪ ከመካ ኢብኑ ከሲር ሲሆን ቂራአቱ የተላለፈው ደግሞ ከዘይድ ኢብኑ ሣቢት ነው።
3ኛ. ቃሪ ከደማስቆ አቡ አምር ሲሆን ቂራአቱ የተላለፈው ደግሞ ከዐብደሏህ ኢብኑ መሥዑድ ነው።
4ኛ. ቃሪ ከባስራ ኢብኑ አምር ሲሆን ቂራአቱ የተላለፈው ደግሞ ከአቡ አዝ-ዘርዳ ነው።
5ኛ. ቃሪ ከኩፋ አሲም ኢብኑ አብ ሲሆን ቂራአቱ የተላለፈው ደግሞ ከዐሊ ኢብኑ አቡጣሊብ ነው።
6. ቃሪ ከኩፋ ሃምዛ ኢብኑ ሲሆን ቂራአቱ የተላለፈው ደግሞ ከአቡ ሙሳ አልሻሪ ነው።
7. ቃሪ ከኩፋ አል-ኪሳኢ ሲሆን ቂራአቱ የተላለፈው ሃቢብደግሞ ከዑስማን ኢብኑ አፋን ነው።

“ሪዋያህ” رِواية ማለት “መስተጋብ” “ስንክሳር” “transmission” ማለት ነው፤ ይህ በሙተዋቲር የተላለፈው ሰንሰለት የሃፍሥ ሪዋያ፣ የወርሽ ሪዋያ፣ የቃሉን ሪዋያ፣ የዱሪ ሪዋያ፣ የሂሻም ሪዋያ፣ የሩህ ሪዋያ እና የባዚ ሪዋያ ሲባል ሲሆን ከአላህ በጂብሪል የተወረደ ግህደተ-መለኮት እንጂ ሰዎች የፈጠሩት ልዩነት አይደለም።