ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.3K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.73K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ነጥብ ሁለት
“አካላት”
“አካል” ሲባል “ማንነት” ተብሎ መቀመጥ ሲኖርበት ነገር ግን መልክአ-ሥላሴ የተባለው መጽሐፍ “አካል” ማለት “ተክለ-ሰውነት”body” አድርጎ ሥላሴ “ደም” “ወርች” “ጎን” “ከርስ” “ኩላሊት” “ወገብ” “አብራክ” “ተረከዝ” “ጫማ” “ጥፍር” “ጣት” እንዳላቸው ይናገራል፤ ይህንን ጉድ እስቲ እንይ፦
“ደም”
“ሥሉስ ቅዱስ ሆይ! *ስርየተ ደማችሁ* ስርየተ ኃጢኣት ነውና የነፍሴን ቤት መቃን በስርየት *”ደማችሁ”* እርጩት።”
“ወርች”
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! የአዳምን ወርች ላጸና መለኮታዊ *ወርቾቻችሁ* ሰላምታ ይገባል።”
“ጎን”
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! የወርቅ አስፈላጊያቸው ላይደለ መለኮታዊ *ጎኖቻችሁ* ሰላምታ ይገባል።”
“ከርስ”
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! የፍጡራንን ሆድ ለፈጠረ ለማይመረመር *ከርሳችሁ* ሰላምታ ይገባል።”
“ኩላሊት”
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! በህላዌ አካል ትክክል ለሚሆኑ *ኩላሊታችሁ* ሰላምታ ይገባል።”
“ወገብ”
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! መታጠቂያው የቸርነት ሰቅ ለሆነው *ወገባችሁ* ሰላምታ ይገባል።”
“አብራክ”
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! የፍጥረት ሁሉ አብራክ ለሚያሰግድ *አብራካችሁ* ሰላምታ ይገባል።”
“ተረከዝ”
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! ብርሃናት ለተጎናፀፈው *ተረከዛችሁ* ሰላምታ ይገባል።”
“ጫማ”
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! ለሚራመድ *ጫማችሁ* ሰላምታ ይገባል።”
“ጥፍር”
“አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! *ከጥፍሮቻችሁ* ጋር ያለመነጣጠል ተባብረው ተመሳስለው ላሉ *ጣቶቻችሁ* ሰላምታ ይገባል።”

ሌላው ይሁን እሺ “ከርስ” እና “አብራክ” ምን ያረግላቸዋል? ከርስ እኮ የምግብ ማከማቻ ሆድ ነው፤ ይበላሉን? አብራክ እኮ የዘር ከረጢት ነው፤ ይወልዳሉን? እስቲ በባይብል አምላክ ሦስት አካል ነው ወይም ሦስት አካል አለው የሚል ጥቅስ ይፈለግ፤ እስቲ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ናቸው የሚል ጥቅስ ይፈለግ፤ የለም፤ አምላክ አንድ “ነው” እንጂ “ናቸው” የሚል የለም፦
ማርቆስ 12፥29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ፦ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ *”ነው”*፥

“እርሱ” “አንተ” “አለ” እና “ነው” ተብሎ የሚመለክ አምላክ እንጂ “እነርሱ” “እናንተ” “አሉ” እና “ናቸው” ተብሎ የሚመለክ አምላክ ባይብል ላይ ሽታው እንኳን የለም፤ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል የሆነ ቃል በመጽሐፋችሁ “አምላክ አንድ ብቻ ነው” የሚል ነው፦
ዘዳግም 6፥4 እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ *”አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው”*፤
ዘዳግም 6፥6 እኔም ዛሬ አንተን *”የማዝዘውን ይህን ቃል”* በልብህ ያዝ።
ዘዳግም 4:2 *”እኔ ያዘዝኋችሁን”* የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን *”ትእዛዝ ትጠብቃላችሁ እንጂ ባዘዝኋችሁ ቃል ላይ አትጨምሩም፥ ከእርሱም አታጎድሉም”*።

“እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው” ብሎ ያዘዘውን ቃል በልብህ ያዝ፤ ይህ ታላቁና ፊተኛይቱ ትእዛዝ አንድ በሚለው ላይ ሁለት ወይም ሶስት አሊያ ከዚያ በላይ አትጨምር፤ አንድ ከሚለው ላይ ካጎደልክ የለም ማለት ነውና አትቀንስ ግን አንድ የሚለውን ብቻ ያዝ፤ ትክክል ወደ ኾነች “አንድ ብቻ ነው” ወደሚለው ቃል ኑ፦
3፥64 የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! *”በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ እርሷም አላህን እንጅ ሌላን ላናመልክ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው”*፤ በላቸው፡፡ እምቢ ቢሉም፡- እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፡፡ قُلْ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ تَعَالَوْا۟ إِلَىٰ كَلِمَةٍۢ سَوَآءٍۭ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ أَلَّا نَعْبُدَ إِلَّا ٱللَّهَ وَلَا نُشْرِكَ بِهِۦ شَيْـًۭٔا وَلَا يَتَّخِذَ بَعْضُنَا بَعْضًا أَرْبَابًۭا مِّن دُونِ ٱللَّهِ ۚ فَإِن تَوَلَّوْا۟ فَقُولُوا۟ ٱشْهَدُوا۟ بِأَنَّا مُسْلِمُونَ

አል-ሓምዱሊሏሂ ረቢል ዓለሚን ዐላ ኒዕመተል ኢሥላም!

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ሁለት አምላክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

16፥51 አላህም አለ፦ *"ሁለት አማልክትን አትያዙ"*፡፡ እርሱ *"አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ እኔንም ብቻ ፍሩ"*፡፡ وَقَالَ ٱللَّهُ لَا تَتَّخِذُوٓا۟ إِلَٰهَيْنِ ٱثْنَيْنِ ۖ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَإِيَّٰىَ فَٱرْهَبُونِ

"ሸይእ" شَىْء ማለት "ነገር"thing" ማለት ሲሆን ማንኛውንም ነገር ሁሉ የፈጠረ አንድ አምላክ አላህ ብቻ ነው፦
39:62 አላህ *"የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው"*። እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው። ٱللَّهُ خَٰلِقُ كُلِّ شَىْءٍۢ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍۢ وَكِيلٌۭ
40:62 ይሃችሁ፣ ጌታችሁ አላህ ነው፤ *"የነገር ሁሉ ፈጣሪ ነው"*፤ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ ታዲያ ከእምነት ወዴት ትመለሳላችሁ?። ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمْ خَٰلِقُ كُلِّ شَىْءٍۢ لَّآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ فَأَنَّىٰ تُؤْفَكُونَ
6:102 ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ *"ነገርን ሁሉ ፈጣሪ ነው"*፡፡ ስለዚህ አምልኩት፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡ بَدِيعُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۖ أَنَّىٰ يَكُونُ لَهُۥ وَلَدٌۭ وَلَمْ تَكُن لَّهُۥ صَٰحِبَةٌۭ ۖ وَخَلَقَ كُلَّ شَىْءٍۢ ۖ وَهُوَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌۭ
13፥16 *«አላህ ሁሉን ነገር ፈጣሪ ነው"*፡፡ እርሱም አንዱ አሸናፊው ነው» በል፡፡ قُلِ ٱللَّهُ خَٰلِقُ كُلِّ شَىْءٍۢ وَهُوَ ٱلْوَٰحِدُ ٱلْقَهَّٰرُ

ያ ማለት ከነገር ሁሉ ተቃራኒ ነገርን የፈጠረው አላህ ብቻ ነው፤ ለምሳሌ ሰማይንና ምድርን፣ ብርሃንንና ጨለማን፣ ሞትና ህይወትን፣ ወንድና ሴትን ሁሉ ማለት ነው፦
51፥49 ትገነዘቡም ዘንድ *"ከነገሩ ሁሉ ሁለት ተቃራኒ ዓይነትን ፈጠርን"*፡፡ وَمِن كُلِّ شَىْءٍ خَلَقْنَا زَوْجَيْنِ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ
6፥1 ምስጋና ለዚያ *"ሰማያትንና ምድርን ለፈጠረው፤ ጨለማዎችንና ብርሃንንም"* ላደረገው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ وَجَعَلَ ٱلظُّلُمَٰتِ وَٱلنُّورَ
67፥1 ያ የትኛችሁ ሥራው ይበልጥ ያማረ መኾኑን ሊሞክራችሁ *"ሞትንና ሕይወትን የፈጠረ ነው"*፡፡ እርሱም አሸናፊው መሓሪው ነው፡፡ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلْمَوْتَ وَٱلْحَيَوٰةَ لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًۭا ۚ وَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْغَفُورُ
75፥39 ከእርሱም *"ሁለት ዓይነቶችን ወንድና ሴትን አደረገ"*፡፡ فَجَعَلَ مِنْهُ ٱلزَّوْجَيْنِ ٱلذَّكَرَ وَٱلْأُنثَىٰٓ

ይህ ሆኖ ሳለ ግን ዞራስተርያን ወይም ኖስቲዝም፦ "ሰማይን፣ ብርሃንን፣ ህይወትን፣ ወንድን የፈጠረው "አሁራ" የተባለው አምላክ ነው ሲሉ፤ በተቃራኒው ምድርን፣ ጨለማን፣ ሞት፣ ሴትን የፈጠረው "አንግራ" የተባለው አምላክ ነው ብለው ሁለት አምላክ ያመልካሉ፤ ይህ የሁለት አምላክ ጥምረት ትምህርት "ዱአ-ቴእይዝም"duotheism" ይባላል፤ "ዱአ-ቴእይዝም" δυοθεισμός ማለት የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ "ዱአ" δυο "ሁለት" እና "ቴኦስ" θεισμός "አምላክ" የሚል ትርጉም ነው፤ ትርጉሙም "ሁለት አምላክ"dual deity" ማለት ነው፤ ይህንን ትምህርት ቁርአን ክፉኛ ይቃወማል፦
16፥51 አላህም አለ፦ *"ሁለት አማልክትን አትያዙ"*፡፡ እርሱ *"አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ እኔንም ብቻ ፍሩ"*፡፡ وَقَالَ ٱللَّهُ لَا تَتَّخِذُوٓا۟ إِلَٰهَيْنِ ٱثْنَيْنِ ۖ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَإِيَّٰىَ فَٱرْهَبُونِ
ይህ ትምህርት ከሥላሴ የሚለየው አምላክ በምንነት ሆነ በማንነት ሁለት ነው ሲሉ፤ ሥላሴያውያን ደግሞ በማንነት ሦስት በምንነት አንድ ናቸው ብለው ያምናሉ፤ ነገር ግን አንዱ አምላክ በማንነት ሆነ በምንነት አንድ ነው፤ በምንነቱ ሆነ በማንነቱ ተጋሪ የለውም፦
18፥110 ወደ እኔ የሚወረድልኝ "አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ እኔም ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ" ማለት ነው፤ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም አምልኮ *"አንድንም"* አያጋራ» በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَآ أَنَا۠ بَشَرٌۭ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَمَن كَانَ يَرْجُوا۟ لِقَآءَ رَبِّهِۦ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًۭا صَٰلِحًۭا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِۦٓ أَحَدًۢا

"አንድ አምላክ" በሚለው ቃል ላይ "አንድ" የሚለውን የተጠቀመበት "ዋሒድ" وَٰحِد ሲሆን አላህ በምንነቱ ላይ ምንም ምንነት ተጋሪ እንደሌለው ያሳያል፤ "አንድንም አያጋራ" በሚለው ቃል የተጠቀመበት ቃል "አሐድ" أَحَد ሲሆን በአላህ ምንነት ላይ ማንም ማንነት ተጋሪ እንደሌለ ያሳያል፦
72፥20 «እኔ የምግገዛው ጌታየን ብቻ ነው፡፡ በእርሱም *"አንድንም"* አላጋራም» በል፡፡ قُلْ إِنَّمَآ أَدْعُوا۟ رَبِّى وَلَآ أُشْرِكُ بِهِۦٓ أَحَدًۭا
112፥1 በል «እርሱ አላህ *"አንድ"* ነው፡፡ قُلْ هُوَ ٱللَّهُ أَحَدٌ

"አላህ አንድ ነው" በሚለው ቃል ላይ "አንድ" የሚለው "አሐድ" أَحَد መሆኑ በራሱ አላህ አንድ ማንነት ብቻ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፤ ከእርሱ ማንነት ጋር መለኮትን የሚጋራ አንድም ማንነት የለም፦
112፥4 ለእርሱም *"አንድም"* ብጤ የለውም፡፡ وَلَمْ يَكُن لَّهُۥ كُفُوًا أَحَدٌۢ

"ለም" لَمْ ማለት "አፍራሽ ቃል"negative particle" ሲሆን ለማንነት የሚመጣ አፍራሽ ቃል ነው፤ ለእርሱ ማንም ብጤ የሌለው መሆኑን ያሳያል፤ "ለይሠ" لَيْسَ ማለት "አፍራሽ ቃል"negative particle" ሲሆን ለምንነት የሚመጣ አፍራሽ ቃል ነው፤ አላህ የሚመስለው ምንም ምንነት የለም፦
42፥11 *የሚመስለው ምንም ነገር የለም*፡፡ እርሱም *ሰሚው ተመልካቹ* ነው፡፡ لَيْسَ كَمِثْلِهِۦ شَىْءٌۭ ۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ

ይህንን ጥልልና ጥንፍፍ ያለ የተውሒድ ትምህርት ከተረዳን በክርስትናው አንጃ ውስጥ የይሆዋ ምስክሮች ደግሞ፦ "ዓለማት ከመፈጠራቸው በፊት ያህዌህ ኢየሱስ ፈጠረውና በኢየሱስ ሁሉን ነገር ፈጠረ" ብለው ያምናሉ፤ ይህ እንጥል ከመቧጠጥ ምንም አይተናነስም፤ ኢየሱስን አናመልክም ሲሉ ተውሒደል ኡሉሂያን ሲያሟሉ፤ ግን ዓለማትን ሲፈጥር ግን አጋዥ ነበረው ብሎ ማለት ተውሒደ አር-ሩቡቢያን ላይ ማሻረክ ነው፤ ከአላህ ጋር በምንነት ተለይቶ ግን ፍጥረትን ሲፈጥር ሆነ ዓለማትን ሲያስተናብር የሚያግዘው አጋዥ የለውም፤ ወደ አላህ በንስሃ ተመለሱ እንላለን፦
34፥22 እነዚያን ከአላህ ሌላ የምታስቧቸውን ጥሩ፡፡ በሰማያትም በምድርም ውስጥ *"የብናኝ ክብደት ያክል ምንንም አይችሉም"*፡፡ ለእነርሱም በሁለቱም ውስጥ *"ምንም ሽርክና የላቸውም"*፡፡ ከእነርሱም ለእርሱ *"ምንም አጋዥ የለውም"*» በላቸው፡፡ قُلِ ٱدْعُوا۟ ٱلَّذِينَ زَعَمْتُم مِّن دُونِ ٱللَّهِ ۖ لَا يَمْلِكُونَ مِثْقَالَ ذَرَّةٍۢ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَلَا فِى ٱلْأَرْضِ وَمَا لَهُمْ فِيهِمَا مِن شِرْكٍۢ وَمَا لَهُۥ مِنْهُم مِّن ظَهِيرٍۢ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አንድ አምላክ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

18፥110 እኔም ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚወረድልኝ፦ *”አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው” ማለት ነው”*፤ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም አምልኮ አንድንም አያጋራ» *”በላቸው”*፡፡ قُلْ إِنَّمَآ أَنَا۠ بَشَرٌۭ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَمَن كَانَ يَرْجُوا۟ لِقَآءَ رَبِّهِۦ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًۭا صَٰلِحًۭا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِۦٓ أَحَدًۢا

“ኢስላም” ማለት “አንዱን አምላክ በብቸኝነት ማምለክ፣ መገዛት፣ መታዘዝ ማለት ነው”፤ የኢስላም አስኳሉ ደግሞ ተውሒድ ነው፤ ወደ ነብያችን”ﷺ” የሚወርደው ግህደተ-መለኮት፦ “አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው” ማለት ነው፦
18፥110 እኔም ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚወረድልኝ፦ *”አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው” ማለት ነው”*፤ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም አምልኮ አንድንም አያጋራ» *”በላቸው”*፡፡ قُلْ إِنَّمَآ أَنَا۠ بَشَرٌۭ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَمَن كَانَ يَرْجُوا۟ لِقَآءَ رَبِّهِۦ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًۭا صَٰلِحًۭا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِۦٓ أَحَدًۢا
6፥19 *«እርሱ አንድ አምላክ ብቻ ነው”*፡፡ እኔም ከምታጋሩት ነገር ንጹሕ ነኝ» በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَا هُوَ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ وَإِنَّنِى بَرِىٓءٌۭ مِّمَّا تُشْرِكُونَ
21፤108 «ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ *”አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው”* ማለት ነው፤ ታዲያ እናንተ ፍጹም “ታዛዦች” ናችሁን» *በላቸው*፡፡ قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ

“ታዛዦች” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሙስሊሚን” مُّسْلِمُونَ ሲሆን ይህንን አንድ አምላክ በፍፁም መታዘዝን፣ መገዛትን፣ ማምለክን ያሳያል፤ “ኢንነማ” إِنَّمَآ ማለት “ብቻ” ማለት ሲሆን ይህም አንድ አምላክ ብቻ መመለክ የሚገባው ለማሳየት ብዙ ቦታ “አንድ አምላክ ብቻ ነው” በማለት ያስቀምጣል፦
20፥98 *”ጌታችሁ ያ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ የኾነው አላህ ብቻ ነው”*፡፡ እውቀቱ ነገርን ሁሉ አዳረሰ፡፡ إِنَّمَآ إِلَٰهُكُمُ ٱللَّهُ ٱلَّذِى لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ وَسِعَ كُلَّ شَىْءٍ عِلْمًۭا
2፥163 *”አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም”*፡፡ እርሱ እጅግ በጣም ርኅሩህ አዛኝ ነው፡፡ وَإِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ لَّآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلرَّحْمَٰنُ ٱلرَّحِيمُ

ኢስላም ጥልልና ጥንፍፍ ያለ “ሞኖ-ቴእይዝም” መሆኑ ከላይ ያሉት አናቅጽ ቁልጭና ፍንትው አድርገው ያሳያሉ፤ “ሞኖ-ቴእይዝም” μονοθεϊσμός ማለት የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ “ሞኖ” μονο “ብቸኛ” እና “ቴኦስ” θεισμός “አምላክ” የሚል ውቅር ነው፤ ትርጉሙም “ብቸኛ አንድ አምላክ”only one deity” ማለት ነው፤ እንደ ባይብሉ ይህ ብቸኛ አምላክ ኢየሱስን የላከው ብቻ ነው፦
ዮሐንስ 17:3 *”እውነተኛ አምላክ ብቻህን የሆንህ አንተን”* እና የላክኸውን ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት። “ 1980 አዲስ ትርጉም”
τὸν μόνον ἀληθινὸν Θεὸν καὶ ὃν ἀπέστειλας Ἰησοῦν Χριστόν

ኢየሱስ የላከውን “አንተ” በሚል ሁለተኛ መደብ ነጠላ ባለቤት ተውላጠ-ስም በመጥራት ወደ እርሱ ይፀልይ ነበር፤ ይህንን የላከውን ማንነት “እውነተኛ አምላክ ብቻህን የሆንህ” በማለት የላከው ብቻውን እውነተኛ አምላክ መሆኑን ለማመልከት “ብቻህን” የሚል ገላጭ”adjective” ይጠቀማል፤ ከዚያም ባሻገር እራሱን ከዚያ ከእውነተኛ አምላክ ለመለየት “እና” የሚል መስተጻምር”conjuction” ይጠቀማል፣ ይህ አነጋገሩ የሚያሳየው ኢየሱስ የእውነተኛ አምላክ መልእክተኛ መሆኑን ነው፣ “የላከውን” የሚል ሃይለ-ቃል መጠቀሙ ይሰመርበት፣ መመለክ የሚገባው እርሱ ብቻ መሆኑን ለማሳየትም “እርሱን ብቻ አምልክ” በማለት እና የትንሳኤን ቀን መቼ መከሰት “ከአባት ብቻ በቀር ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም” በማለት “ብቻ” የሚል ወሳኝ ቃላት ይጠቀማል፦
ማቴዎስ 4፥10 ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ *እርሱንም ብቻ አምልክ* ተብሎ ተጽፎአልና አለው።
ማቴዎስ 24፥36 ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን *”ከአባት ብቻ በቀር”* የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ *”ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም”*።

ይህ ብቸኛ አምላክ ብቻውን አምላክ የሆነ፣ የማይሞት፣ የማይታይ፣ ብቻውን የሆነ ገዥ፣ አንድ ሰው እንኳ ያላየውም ሊያይም የማይቻለው ነው፦
1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥17 *”ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይሞተው፣ ለማይታየውም”*፣ ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን። NIV
6፥15-16 ያንም መገለጡን በራሱ ጊዜ ብፁዕና *”ብቻውን የሆነ ገዥ”*፥ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ ያሳያል። *”እርሱ ብቻ የማይሞት ነው”*፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ *”አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም”*፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን።

ይህ ብቸኛ አምላክ “እና” በሚል መስተጻምር እና “በ” በሚል መስተዋድድ ከኢየሱስ ተለይቷል፦
ሮሜ 16፥27 ብቻውን ጥበብ ላለው ለአምላክ *”በ”*ኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን። NIV
ይሁዳ 1፥4 *”ብቻውን ያለውን ጌታ አምላክ”* እና ጌታችንንም ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።
denying the only Lord God, and our Lord Jesus Christ.” KJV
ይሁዳ 1፥25 *”ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን”* ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ *”በ”*ጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን።
ይህ ብቸኛ የኢየሱስ አምላክ ጥንት የነበሩት የነብያት እምላክ ነው፤ እርሱ በልዕልናው ብቻውን ያለ እና ብቻውን ሁሉንም ነገር የፈጠረ ነው፦
ዘዳግም 32፥39 አሁንም *እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ*፥ ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ”* እዩ፤
ኢዮብ 23፥13 *”እርሱ ግን ብቻውን ነው”*፤ እርሱንስ የሚመስለው ማን ነው?
ኢዮብ 9፥8 *”ሰማያትን ብቻውን ይዘረጋል”*።
መዝሙር 136፥7 *”ብቻውን ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ”*፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤
ኢሳይያስ 44፥24 ከማኅፀን የሠራህ፥ የሚቤዥህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሁሉን የፈጠርሁ፥ *”ሰማያትን ለብቻዬ የዘረጋሁ ምድርንም ያጸናሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ ከእኔ ጋር ማን ነበረ?”*

“ብቻ” የሚል ገላጭ ቃል ተጠቅሞ ከአንድ በላይ ብዙ ማንነቶች በአንድ መለኮት ውስጥ አሉ ማለት እጅግ ሲበዛ ሞኝነት ነው፤ ሙስሊም በአላህ አንድ እኔነት ላይ ሌላ እኔነት ያላቸው ማንነት ሆነ ምንነት ሳያጋሩ የሚያመልኩ ናቸው፦
24፥55 *”በእኔ ምንም የማያጋሩ ኾነው ያመልኩኛል”*፡፡ ከዚያም በኋላ የካደ ሰው እነዚያ እነርሱ አመጸኞች ናቸው፡፡ يَعْبُدُونَنِى لَا يُشْرِكُونَ بِى شَيْـًۭٔا ۚ وَمَن كَفَرَ بَعْدَ ذَٰلِكَ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْفَٰسِقُونَ
31፥15 *”ለአንተ በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህም አትታዘዛቸው”*፡፡ وَإِن جَٰهَدَاكَ عَلَىٰٓ أَن تُشْرِكَ بِى مَا لَيْسَ لَكَ بِهِۦ عِلْمٌۭ فَلَا تُطِعْهُمَا
22፥26 ለኢብራሂምም የቤቱን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ *«በእኔ ምንንም አታጋራ”*፣ ቤቴንም ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው» *”ባልነው ጊዜ አስታውስ*”፡፡ وَإِذْ بَوَّأْنَا لِإِبْرَٰهِيمَ مَكَانَ ٱلْبَيْتِ أَن لَّا تُشْرِكْ بِى شَيْـًۭٔا وَطَهِّرْ بَيْتِىَ لِلطَّآئِفِينَ وَٱلْقَآئِمِينَ وَٱلرُّكَّعِ ٱلسُّجُودِ
29፥8 ሰውንም በወላጆቹ መልካም አድራጎትን አዘዝነው፡፡ *”ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህ አትታዘዛቸው”*፡፡ መመለሻችሁ ወደ እኔ ነው፡፡ ትሠሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፡፡ وَوَصَّيْنَا ٱلْإِنسَٰنَ بِوَٰلِدَيْهِ حُسْنًۭا ۖ وَإِن جَٰهَدَاكَ لِتُشْرِكَ بِى مَا لَيْسَ لَكَ بِهِۦ عِلْمٌۭ فَلَا تُطِعْهُمَآ ۚ إِلَىَّ مَرْجِعُكُمْ فَأُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

እኛስ አላህ ሆይ! አንተን ብቻ እናመልካለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፤ በአንተ አምልኮ ላይ ማንንም ምንንም አካል ሆነ ህላዌ አናጋራም፦
1፥5 *”አንተን ብቻ እናመልካለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን”*፡፡ إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የጀሀነም ሸለቆ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

19፥59 *ከእነርሱም በኋላ “ሶላትን ያጓደሉ” ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ምትኮች ተተኩ! የገሀነምንም ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ*፡፡ فَخَلَفَ مِن بَعْدِهِمْ خَلْفٌ أَضَاعُوا الصَّلَاةَ وَاتَّبَعُوا الشَّهَوَاتِ ۖ فَسَوْفَ يَلْقَوْنَ غَيًّا

ሶላት በኢማን፣ በኢኽላስ እና በኢቲባዕ ከተፈጸመ ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ በመከልከል ይረዳል፤ ሶላት አላህን በሚፈሩ ላይ እንጅ በሌላው ላይ በእርግጥ ከባድ ናት፦
2፥45 በመታገስ እና *”በሶላትም ተረዱ፡፡ እርሷም ሶላት በፈሪዎች ላይ እንጅ በሌላው ላይ በእርግጥ ከባድ ናት”*፡፡ وَاسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ وَإِنَّهَا لَكَبِيرَةٌ إِلَّا عَلَى الْخَاشِعِينَ
2፥153 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በመታገስ እና *”በሶላት ተረዱ”*፡፡ አላህ ከታጋሾች ጋር ነውና፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اسْتَعِينُوا بِالصَّبْرِ وَالصَّلَاةِ ۚ إِنَّ اللَّهَ مَعَ الصَّابِرِينَ

ሶላት ላይ የሚቆሙ ሙሥሊሞች “ሙሰሊን” ይባላሉ፤ ሶላት የማይቆሙ “ሰቀር” በሚባለው የጀሃነም ሸለቆ ውስጥ ይቀጣሉ፤ እነርሱም ቅጣቱን ሲቀምሱ፦ “ከሙሰሊኖቹ አልነበርንም” ይላሉ፦
74፥43 እነርሱም ይላሉ፦ *”ከሰጋጆቹ አልነበርንም”*፡፡ قَالُوا لَمْ نَكُ مِنَ الْمُصَلِّين

ሶላት በወቅቱ የማይቆሙ እና ያለ ኢኽላስ ሶላት ላይ የሚቆሙ “ወይል” በሚባል የጀሃነም ሸለቆ ውስጥ ይቀጣሉ፦
107፥4 *”ወዮላቸው ለሰጋጆች”*፡፡ فَوَيْلٌ لِّلْمُصَلِّينَ
107፥5 *”ለእነዚያ እነርሱ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለኾኑት ሰጋጆች”*፡፡ الَّذِينَ هُمْ عَن صَلَاتِهِمْ سَاهُونَ
107፥6 *”ለእነዚያ እነርሱ ይዩልኝ ባዮች ለኾኑት”*፡፡ الَّذِينَ هُمْ يُرَاءُونَ

ወዮላቸው የተባሉት ሙሰሊን እነማን እንደሆኑ ለማመልከት “እነዚያ” የሚል አመልካች ተውላጠ-ስም ተጠቅሰዋል። እነዚያ እነርሱ በሶላታቸው ላይ ዘውታሪዎች ሆነው የሚቆሙ ሙሰሊን ሲቀሩ በተቃራኒው ሶላትን ያጓደሉ አሊያም የተዉ “ገይ” በሚባል የጀሃነም ሸለቆ ውስጥ ይቀጣሉ፦
70፥22 *”ሰጋጆቹ ብቻ ሲቀሩ”*፡፡ إِلَّا الْمُصَلِّينَ
70፥23 *እነዚያ እነርሱ በሶላታቸው ላይ ዘውታሪዎች የኾኑት”*፡፡ الَّذِينَ هُمْ عَلَىٰ صَلَاتِهِمْ دَائِمُونَ
19፥59 *ከእነርሱም በኋላ “ሶላትን ያጓደሉ” ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ምትኮች ተተኩ! የገሀነምንም ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ*፡፡ فَخَلَفَ مِن بَعْدِهِمْ خَلْفٌ أَضَاعُوا الصَّلَاةَ وَاتَّبَعُوا الشَّهَوَاتِ ۖ فَسَوْفَ يَلْقَوْنَ غَيًّا

አላህ በሶላታቸው ላይ ዘውታሪዎች ሆነው ከሚቆሙትና ኢኽላስ ካላቸው ሙሰሊን ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ጫት መቃም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥219 *”አእምሮን ከሚቃወም መጠጥ እና ከቁማር ይጠይቁሃል፡፡ «በሁለቱም ውስጥ ታላቅ ኃጢኣትና ለሰዎች ጥቅሞች አሉባቸው፡፡ ግን ኃጢኣታቸው ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ነው» በላቸው”*፡፡ يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْخَمْرِ وَالْمَيْسِرِ ۖ قُلْ فِيهِمَا إِثْمٌ كَبِيرٌ وَمَنَافِعُ لِلنَّاسِ وَإِثْمُهُمَا أَكْبَرُ مِن نَّفْعِهِمَا ۗ

“ጫት”Catha edulis” አእምሮን የሚያመረቅን እና በጤና፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ ሕይወት ላይ እክል ከሚያጋጥሙ እና አሉታዊ የጎንዮሽ ተፅእኖ”negative side effect” ከሚያሳድሩ ነገሮች መካከል እንደሆነ የመስኩ ምሁራን ያትታሉ፥ በኢሥላም ጫት ከኸምር ይመደባል። “ኸምር” خَمْرየሚለው ቃል “ኸመረ” خَمَرَ ማለትም “ሸፈነ” “ደበቀ” “ሰወረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን አእምሮን “የሚሸፍን” “የሚደብቅ” “የሚሰውር” ማለት ነው፥ የሒጃብ አይነት ከሆኑት መካከል “ጉፍታ” እራሱ በቁርኣን “ኺማር” خِمَار ይባላል፦
24፥31 *ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ፡፡ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፡፡ ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ፡፡ ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ*፡፡ وَقُل لِّلْمُؤْمِنَاتِ يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَارِهِنَّ وَيَحْفَظْنَ فُرُوجَهُنَّ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا مَا ظَهَرَ مِنْهَا ۖ وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَىٰ جُيُوبِهِنَّ

“ጉፍታዎች” ለሚለው በብዜት የገባው ቃል “ኹሙር” خُمُر ሲሆን በነጠላ ደግሞ “ኺማር” خِمَار ነው፥ “ኺማር” خِمَار የሚለው ቃል ልክ እንደ “ኸምር” خَمْر ሥርወ-ቃሉ “ኸመረ” خَمَرَ ነው። ጉፍታ ራስን ስለሚሸፍን “ኺማር” خِمَار እንሚባል ሁሉ አእምሮን የሚቃወም ማንኛውም ነገር “ኸምር” خَمْر ይባላል፥ አስካሪ መጠጥ”alcohol” ሆነ “አደንዛዥ ዕፅ”drug” አእምሮን የሚሸፍን ሰለሆነ ኸምር ነው፦
2፥219 *”አእምሮን ከሚቃወም መጠጥ እና ከቁማር ይጠይቁሃል፡፡ «በሁለቱም ውስጥ ታላቅ ኃጢኣትና ለሰዎች ጥቅሞች አሉባቸው፡፡ ግን ኃጢኣታቸው ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ነው» በላቸው”*፡፡ يَسْأَلُونَكَ عَنِ الْخَمْرِ وَالْمَيْسِرِ ۖ قُلْ فِيهِمَا إِثْمٌ كَبِيرٌ وَمَنَافِعُ لِلنَّاسِ وَإِثْمُهُمَا أَكْبَرُ مِن نَّفْعِهِمَا ۗ

ቁማር መሠረቱ ገንዘብ ነው፥ ገንዘብ ለሰዎች ጥቅም አለው። አልክሆል ሆነ ድራግ በህክምና አገልግሎት ለሰዎች ጥቅም አለው። ነገር ግን ኸምር ሆነ ቁማር ኃጢኣታቸው ከጥቅማቸው በጣም ትልቅ ስለሆነ ታላቅ ኃጢኣት አለባቸው። አልክሆል ውስጥ የሚካተቱት ጠላ፣ ጠጅ፣ አረቄ፣ ውስኪ፣ ቮድካ ወዘተ.. ሲሆኑ ድራግ ውስጥ የሚካተቱት ደግሞ ሲጋራ፣ ቶባኮ፣ ሲሻ፣ ጫት፣ ኮኬይን፣ ማሪዋና፣ ናርኮት፣ ሄሮይን ወዘተ ናቸው፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 74, ሐዲስ 14
ኢብኑ ዑመር”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ “ዑመር በአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” አትሮንስ ላይ ኹጥባህ ሲያደርግ እንዲህ አለ፦ *”ኸምር ሐራም መሆኑ የሚናገረው የወረደው ከአምስት ነገር ማለትም ከወይን፣ ከተምር፣ ከስንዴ፣ ከገብስ እና ከማር ስለሚዘጋጁት ኸምር ናቸው። ዐቅልን የሚሰውር ሁሉ ኸምር ነው”*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ ـ رضى الله عنهما ـ قَالَ خَطَبَ عُمَرُ عَلَى مِنْبَرِ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ إِنَّهُ قَدْ نَزَلَ تَحْرِيمُ الْخَمْرِ، وَهْىَ مِنْ خَمْسَةِ أَشْيَاءَ الْعِنَبِ وَالتَّمْرِ وَالْحِنْطَةِ وَالشَّعِيرِ وَالْعَسَلِ، وَالْخَمْرُ مَا خَامَرَ الْعَقْلَ

እዚህ ሐዲስ ላይ “የሚሰውር” ለሚለው የገባው ቃል “ኻመረ” خَامَرَ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ ጠላ፣ ጠጅ፣ አረቄ፣ ውስኪ፣ ቮድካ የሚል ስለሌለ መጠጣቱ ይፈቀዳል እንደማንል እና ቂያሥ በማድረግ ሐራም ነው እንደምንል ሁሉ ሲጋራ፣ ቶባኮ፣ ሲሻ፣ ጫት፣ ኮኬይን፣ ማሪዋና፣ ናርኮት፣ ሄሮይን የሚል ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ ስለሌለ ሐላል ነው አንልም፥ እንዲሁ ቂያሥ በማድረግ ሐራም ነው እንላለን። “ቂያሥ” قِيَاس የሚለው ቃል “ቃሠ” قَاسَ ማለትም “አመጣጠነ” “አመዛዘነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ማመጣጠን” “ማመዛዘን” ማለት ነው። በሸሪዓህ ቂያሥ ከሚደረጉት እሳቦት አንዱ ኸምር ነው፥ አስካሪ መጠጥ ሆነ አደንዛዥ ዕፅ አእምሮን የሚያነቃቃ እና የሚያደነዝዝ እስከሆነ ድረስ ሙሥኪር ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 36, ሐዲስ 95
ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ “ነቢዩ”ﷺ”፦ *”ሙሥኪር ሁሉ ኸምር ነው፥ ኸምር ሁሉ ሐራም ነው”* ሲሉ እንጂ ሌላ ዐላውቅም”። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، قَالَ وَلاَ أَعْلَمُهُ إِلاَّ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ كُلُّ مُسْكِرٍ خَمْرٌ وَكُلُّ خَمْرٍ حَرَامٌ ‏”‏
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 30, ሐዲስ 3514
ሙዓዊያህ የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቼ ነበር፦ *”ሙሥኪር ሁሉ ለሁሉም ምእመናን ሐራም ነው”*። سَمِعْتُ مُعَاوِيَةَ، يَقُولُ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ يَقُولُ ‏ “‏ كُلُّ مُسْكِرٍ حَرَامٌ عَلَى كُلِّ مُؤْمِنٍ ‏”‏
“ሙሥኪር” مُسْكِر የሚለው ቃል “ሠኪረ” سَكِرَ
ማለትም “ደነዘዘ” “ሰከረ” “ነፈዘ” “መረቀነ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “የሚያደነዝዝ” “የሚያሰክር” “የሚያነፍዝ” “የሚያመረቅን” ማለት ነው። “ሠከር” سَكَر እራሱ “አደንዛዥ” “አነፋዥ” “አመርቃኝ” “አስካሪ”intoxicant” ማለት ሲሆን “ሡክር” سُكْر ደግሞ “አደንዛዥነት” “አነፋዥነት” “አመርቃኝነት” “አስካሪነት”intoxication” ማለት ነው፦
22፥2 በምታዩዋት ቀን አጥቢ ሁሉ ከአጠባችው ልጅ ትፈዝዛለች፡፡ የእርግዝና ባለቤት የኾነችም ሁሉ እርጉዟን ትጨነግፋለች፡፡ *”ሰዎች የሰከሩ ኾነው ታያለህ፡፡ እነርሱም ከመጠጥ የሰከሩ አይደሉም፡፡ ግን የአላህ ቅጣት ብርቱ ነው”*፡፡ يَوْمَ تَرَوْنَهَا تَذْهَلُ كُلُّ مُرْضِعَةٍ عَمَّا أَرْضَعَتْ وَتَضَعُ كُلُّ ذَاتِ حَمْلٍ حَمْلَهَا وَتَرَى النَّاسَ سُكَارَىٰ وَمَا هُم بِسُكَارَىٰ وَلَـٰكِنَّ عَذَابَ اللَّهِ شَدِيدٌ

ይህ አንቀጽ መስከር ማለት የመጠጥ ስካር ብቻ እንዳልሆነ ፍንትውና ቁልጭ አርጎ ያሳያል። የዘመናችን ስመ-ጥርና አንጋፋ ምሁራን ጫት”Catha edulis” ሐራም እንደሆነ ፈትዋ ሰተዋል። ለምሳሌ ታላቁ ዐሊም ሸይኽ ኢብኑ ባዛ ስለ ጫት እና ሲጋራ ተጠይቀው፦ *”ጫት እና ሲጋራ ሐራም መሆናቸው ምንም ጥርጥር የለውም፥ የጫትን ሐራምነት አስመልክቶ ዑለሞች በርካታ ኪታቦችን ከትበዋል፡፡ ከእነሱም መካከል የቀድሞው የአሥ-ሠዑዲ ዐረቢያህ ሙፍቲ ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ኢብራሂም አል-ሸይኽ”ረሒመሁሏህ” አንዱ ናቸው። በጥቅሉ ሙሥሊሞች ጫትና ሲጋራን ሊተዋቸው እና ሊጠነቀቋቸው ይገባል፥ ጫትና ሲጋራን ማንኛውም ሙሥሊም የመተው ግዴታ አለበት። ጫትና ሲጋራን መግዛትም ሆነ መሸጥ እናም በእነርሱ መነገድ አይቻልም፥ ሐራም ነው፡፡ የጫትና ሲጋራ ገንዘብ ሐራም ናቸው፥ ሙሥሊሞችን ከእነዚህ ነገሮች አላህ ያርቃቸው ዘንድ እንማፀነዋለን” ብለዋል።
ሸይኽ ሷሊሕ አል-ፈውዛን”ሃፊዘሁሏህ” ስለ ጫት ተጠይቀው፦ *”ጫት ሐራም ነው፥ ጫት ከሲጋራ የበለጠ ጉዳት አለው፡፡ እርሱ(ጫት) ሐራም ነው” ብለዋል።
ምንጭ አል-ፈትዋ 257/2 ይመልከቱ!

ስለዚህ ጫት መቃም ትክክል ወይም ስህተት መሆን የሚችለው አንድ ግለሰብ ጫትን ስለሚቅም እና ስለማይቅም ሳይሆን ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ በተቀመጠው መስፈት ነው። ጫት ለሚቅሙ፣ ለሚያስቅሙ እና ለሚያቃቅሙ ይህ ስንኝ ተሰኝቶላቸዋል፦
በቅጠል በሆነ የሚወጣው ሀጃ
ፍየል ትሆን ነበር ከቢላዋ ነጃ!
ጫት መቃም የእርድና ምልክት፥ አለመቃም የፋርነት መለኪያ አይደለም፥ ይህ አስተሳሰብ መሰልጠን ሳይሆን መሰይጠን ነው። እንግዲያውስ ጫት የምትቅሙ፣ የምታስቅሙ፣ የምታቃቅሙ ቆም ብላችሁ ይህንን ፈሣድ ተመልከቱት! አሏህ ከጫት እና በጫት ከሚመጡ ፈሣዶች ይጠብቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ውግራት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

“ረጅም” رجم የሚለው ቃል “ውግራት”stoning” ማለት ሲሆን የሙሴ አምላክ ለሙሴ የሰጠው ሕግ ነው። “ውግራት” የሚለው ቃል ብሉይ ላይ 22 ጊዜ የተጠቀሰው ለተለያየ ቅጣት ነው፦

ነጥብ አንድ
“ለክህደት ቅጣት”
አንድ ሰው ከአንዱ አምላክ ሌሎች አማልክት እናምልክ ብሎ ቢሰብክ በድንጋይ ተወግሮ ይገደላል፦
ዘዳግም 13፥7-10 የእናትህ ልጅ ወንድምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም በብብትህ ያለች ሚስትህ ወይም እንደ ነፍስህ ያለ ወዳጅህ በስውር፦ ና፥ ሄደን ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ወደ አንተ የቀረቡት ከአንተም የራቁት አንተን ከብበውህ ያሉ አሕዛብ ከሚያመልኩአቸው አማልክት፥ አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን “””ሌሎች አማልክት እናምልክ”” ብሎ ቢያስትህ እሺ አትበለው፥ አትስማውም፤ ዓይንህም አይራራለት፥ እትማረውም፥ አትሸሽገውም፤ ነገር ግን ፈጽመህ ግደለው፤ እርሱን ለመግደል በፊት የአንተ እጅ፥ ከዚያም በኋላ የሕዝቡ ሁሉ እጅ በላዩ ትሁን። ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ካወጣህ ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ሊያርቅህ ወድዶአልና “”እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው”””።

ሌላው ከአንዱ አምላክ ሌሎች አማልክት እናምልክ ብሎ ያስተማረ ብቻ ሳይሆን ከአንዱ አምላክ ሌሎች ሌሎች አማልክትን ያመለከ በድንጋይ ተወግሮ ይገደላል፦
ዘዳግም 17፥3-5 “”ሄዶም ሌሎች አማልክትን ያመለከ””፥ እኔ ላላዘዝኋቸው ለፀሐይና ለጨረቃ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ የሰገደ ቢገኝ፥ ቢያወሩልህም ብትሰማም፥ ያንን ፈጽመህ መርምር፤ እነሆም፥ እውነት ቢሆን፥ በእስራኤልም መካከል እንዲህ ያለ ርኵሰት እንደ ተሠራ እርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥ ይህን ክፉ ነገር የሠሩትን ያን ወንድ ወይም ያችን ሴት ወደ በርህ ታመጣቸዋለህ፥ “””እስኪሞቱም ድረስ በድንጋይ ትወግራቸዋለህ”””።
ዘሌዋውያን 20፥1-2 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ደግሞ የእስራኤልን ልጆች እንዲህ በላቸው፦ ከእስራኤል ልጆች ወይም በእስራኤል ዘንድ ከሚቀመጡ እንግዶች ማናቸውም ሰው “”ዘሩን ለሞሎክ ቢሰጥ”” ፈጽሞ ይገደል፤ “”የአገሩ ሕዝብ በድንጋይ ይውገረው””።

በተጨማሪም አንድ ሰው ቢጠነቁልና ቢያስጠነቁል እና አንዱን አምላክ ቢሳደብ በድንጋይ ተወግሮ ይገደላል፦
ዘሌዋውያን 20፥27 ሰው ወይም ሴት መናፍስትን ቢጠሩ ወይም ጠንቋዮች ቢሆኑ ፈጽመው ይገደሉ፤ በ””ድንጋይ ይውገሩአቸው””፤ ደማቸው በላያቸው ነው።
ዘሌዋውያን 24፥13-26 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ ተሳዳቢውን ከስፈሩ ወደ ውጭ አውጣው፤ የሰሙትም ሁሉ እጃቸውን በራሱ ላይ ይጫኑበት፤ ማኅበሩም ሁሉ ይውገረው። ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብለህ ትነግራለህ፦ ማናቸውም ሰው አምላኩን ቢሰድብ ኃጢአቱን ይሸከማል። የእግዚአብሔርንም ስም የሚሰድብ ፈጽሞ ይገደል፤ ማኅበሩም ሁሉ ይውገሩት፤ መጻተኛ ወይም የአገር ልጅ ቢሆን፥ የእግዚአብሔርን ስም በሰደበ ጊዜ ይገደል።

ነጥብ ሁሉት
“ለአመፅ ቅጣት”
አንድ ሰው ለአባቱና ለእናቱ ቃል የማይታዘዝ ዓመፀኛ በድንጋይ ተወግሮ ይገደላል፦
ዘዳግም 21፥18-21 ማንም ሰው ለአባቱ ቃልና ለእናቱ ቃል የማይታዘዝ ቢቀጡትም የማይሰማቸው እልከኛና ዓመፀኛ ልጅ ቢኖረው፥ አባቱና እናቱ ይዘው ወደ ከተማው ሽማግሌዎች ወደሚኖሩበትም ስፍራ በር ያምጡት፤ የከተማውንም ሽማግሌዎች፦ ይህ ልጃችን እልከኛና ዓመፀኛ ነው፥ ለቃላችንም አይታዘዝም ስስታምና ሰካራም ነው ይበሉአቸው። የከተማውም ሰዎች ሁሉ “”እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩት””፤ እንዲህም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታርቃለህ፥ እስራኤልም ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ።

ነጥብ ሶስት
“ለዝሙት ቅጣት”
ሴት ልጅ በጋብቻ ጊዜ ድንግልናዋ ካልተገኘ በድንጋይ ተወግራ ትገደላለች፦
ዘዳግም 22፥21 ብላቴናይቱን ወደ አባትዋ ቤት ደጅ ያውጡአት፥ በእስራኤልም ዘንድ የማይገባውን ነገር አድርጋለችና፥ በአባትዋም ቤት አመንዝራለችና የከተማዋ ሰዎች “”እስክትሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩአት””፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።

ከጋብቻ በፊት ለጋብቻ የታጨች ከሆነችና ግን ከሌላው ወንድ ጋር አንሶላ ብትጋፈፍ እርሷም ያቀበጣት ወንድ በድንጋይ ይወገራሉ፦
ዘዳግም 22፥23-24 ማናቸውም ሰው ድንግልና ያላትን ልጃገረድ ቢያጭ፥ ሌላ ሰውም በከተማ ውስጥ አግኝቶ ከእርስዋ ጋር ቢተኛ፥ ሁለቱን ወደዚያች ከተማ በር አውጡአቸው፤ ብላቴናይቱ በከተማ ውስጥ ሳለች አልጮኸችምና፥ ሰውዮውም የባልንጀራውን ሚስት አስነውሮአልና “”እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ውገሩአቸው””፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።

ነጥብ አራት
“ለወሰን ማለፍ ቅጣት”
በሬ ወንድን ወይም ሴትን እስኪሞቱ ድረስ ቢወጋ የበሬው ባለቤት ተዋጊ መሆኑን ካላወቀ በሬው ብቻ ይወገራል፤ ግን እያወቀ ከሆነ በሬውም የበሬውም ባለቤት ተወግረው ይገደላሉ፦
ዘፀአት 21፥28-29 በሬም ወንድን ወይም ሴትን እስኪሞቱ ድረስ ቢወጋ፥ “በሬው ይወገር”፤ ሥጋውም፥ አይበላ፤ የበሬው ባለቤት ግን ንጹሕ ነው። በሬው ግን አስቀድሞ ተዋጊ ቢሆን፥ ሰዎችም ለባለቤቱ ቢመሰክሩለት ባይጠብቀውም፥ ወንድንም ወይም ሴትን ቢገድል፥ “”በሬው ይወገር፥ ባለቤቱ ደግሞ ይገደል””።

የሚገርመው ግን በሬ ወንድ ባሪያ ወይም ሴት ባሪያ ከወጋ
የበሬው ባለቤት ለጌቶቻቸው ሠላሳ የብር ሰቅል ይከፍላል በሬው ብቻ ተወግሮ ይገደላል፦
ዘፀአት 21፥32 በሬው ወንድ ባሪያ ወይም ሴት ባሪያ ቢወጋ፥ የበሬው ባለቤት ሠላሳ የብር ሰቅል ለጌታቸው ይስጥ፥ በሬውም ይወገር።
መደምደሚያ
ከላይ የዘረዘርናቸውን ስለ ውግራት የሚያወሩ አራቱ ነጥቦች ሲቀርቡ ከእነዚህ ሕግጋት ማምለጫ ክርስቲያኖች፦ “ይህ ሕግ ክርስቶስ ሲመጣ ቀርቷል” ብለው የዮሐንስ 8፥1-11 ያለውን ጥቅስ ይጠቅሳሉ፦
ዮሐንስ 8፥2-8 ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዘችን ሴት ወደ እርሱ አመጡ በመካከልም እርሱዋን አቁመው። መምህር ሆይ፥ ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች። ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ? አሉት። የሚከሱበትንም እንዲያገኙ ሊፈትኑት ይህን አሉ። ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ፤ መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ። ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው። ደግሞም ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ።

የሚገርመው ነገር ከመነሻው የዮሐንስ 8፥1-11 ላይ ኢየሱስ ሊናገረው ይቅርና የዮሐንስ 8፥1-11 ያለው ክፍል የዮሐንስ ወንጌል ክፍል አይደለም። የትኛውም ቀዳማይ የግሪክ እደ-ክታባት”MSS” ላይ ይህ ንግግር አይገኝም። ይህ ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የተከተተው በ 382 በላቲን ቩልጌት ላይ ሲሆን ጨማሪውም የሮሙ ቢሾፕ ጄሮም ነው። በተጨማሪ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከማጥኛ ፅሁፍ ጋር የሚለውን እትም የግርጌ ማስታወሻ እና ሎሎች ስመጥና ገናና ማብራሪያዎች ይመልከቱ፦
1.The Anchor Bible Dictionary, Vol. 1, 1992, page 585:
2. The International Standard Bible Encyclopedia, Vol. 4, page 2637,
3. The Tyndale New Testament Commentaries, I, page 275:
4። Word Biblical Commentary, Vol 33B, , 1975, page887-888:

ሌላዉ ደግሞ የሙሴ አምላክ ዝሙት የሠራ፣ ከአንድ አምላክ ዉጪ ያመለከ ወዘተ.. በድንጋይ ይወገር ሲል እንዴት ነበር ይህ ሕግ ይፈፀም የነበረዉ? ወይንስ ዝም ብሎ የማይፈፀም ሕግ ነበርን? ብሉይ ኪዳይ ላይ ያለው አምላክ ስለ ውግራት ሲናገር በወቅቱ ተሳስቶ ነበርን? ወይስ ያን ጊዜ ጨካኝ የነበረዉ አምላክ ነዉ በኋላ አዲስ ኪዳን ላይ ሩህሩህ ሆነ? እረ ለመሆኑ የአዲስ ኪዳኑ አምላክ ኢየሱስን ሲልክ አሳቡን ቀየረ? ወይስ ብሉይ ላይ የነበሩት ሕጎች ተደመሰሱ? መረጃ ይቅረብልን! ነገር ግን ኢየሱስ "ሕጉ ተሽሯል" ከሚሉት ሰዎች በተቃራኒው ሰማይና ምድር በቂያማ ቀን እስኪያልፍ ድረስ ከሙሴ ሕግ አንዲቷ ትንሿ ሕግ እንኳን እንደማትሻር በአፅንኦትና በአንክሮት ተናግሯል፦
ማቴ 5:17-18 “”እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ””፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም። እውነት እላችኋለሁ፥ “”ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም””፥ ሁሉ እስኪፈጸም ድረስ።

በኢሥላም ሸሪዓው ባለበት አገር ከጋብቻ በፊት ዚና ላደረጉ ሰዎች ብይኑ መቶ ግርፋት ሲሆን በጋብቻ ላይ ደግሞ ዚና ያደረገው አካል የሚደርስበት ብይን ሞት ነው። ይህንን ሕግ ለመተቸት ቅድሚያ ባይብል ላይ ያለውን ሕግ ማየት ያሻል። እግር እራስን አያክምና።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ግድያ በመጽሐፍ ቅዱስ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

17፥33 *”ያቺንም አላህ ያወገዛትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ”*፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ

መጽሐፍ ቅዱስ የፍቅር እና የሰላም መጽሐፍ ነው ለምትሉ ሁሉ ከፍትሕ ጋር በተያያዘ አራት ጥያቄዎችን እንጠይቃለን፦

ቁጥር አንድ
መጽሐፍ ቅዱስ የሰላምና የፍቅር መጽሐፍ ከሆነ እንዴት ሰውን ግደሉ ይላል?
ሕዝ 9፥6፤ “”ሽማግሌውንና ጐበዙን ቈንጆይቱንም ሕፃናቶቹንና ሴቶቹን”” ፈጽማችሁ “”ግደሉ””፤ ነገር ግን ምልክቱ ወዳለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ፤ በመቅደሴም ጀምሩ አላቸው። በቤቱም አንጻር ባሉ ሽማግሌዎች ጀመሩ።
መሳ 21:10 ማኅበሩም ወደዚያ አሥራ ሁለት ሺህ ኃያላን ሰዎች ሰድደው። ሂዱ በኢያቢስ ገለዓድም ያሉትን ሰዎች “”ከሴቶችና ከሕፃናት”” ጋር በሰይፍ ስለት “ግደሉ””።
1ሳሙ 15:3፤ አሁንም ሄደህ አማሌቅን ምታ፥ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፥ አትማራቸውም፤ “”ወንዱንና ሴቱን ብላቴናውንና ሕፃኑን በሬውንና በጉን ግመሉንና አህያውን ግደል””።
ዘዳ 20:14 ነገር ግን “”ሴቶቹንና ሕፃናትን እንስሶቹንም”” በከተማይቱም ያለውን ምርኮ ሁሉ በዝብዘህ ለአንተ ትወስዳለህ፤ አምላክህም እግዚአብሔር የሚሰጥህን የጠላቶችህን ምርኮ ትበላለህ።
ዘዳ.3:6፤ በሐሴቦንም ንጉሥ በሴዎን እንዳደረግን ፈጽሞ አጠፋናቸው፤ ከተሞቹን ሁሉ “”ከወንዶችና ከሴቶች ከሕፃናቶችም ጋር አጠፋናቸው””።
ኢያ 6:21፤ በከተማይቱም የነበሩትን ሁሉ፥ “”ወንዱንና ሴቱን፥ ሕፃኑንና ሽማግሌውን፥ በሬውንም በጉንም አህያውንም፥ በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ””።

እንደ ምዕራባውያን ሚዛን ሰው የፈለገውን ማምለክ መብቱና ነፃነቱ አይደለምን? ከዚያ አልፎ አረጋውያንን፣ ሴቶችን፣ ሕፃናትንና እንስሳቱን መግደል ለምን አስፈለገ? እስቲ ይነበብ ይህን የፍቅርና የሰላም መጽሐፍ።

ቁጥር ሁለት
መጽሐፍ ቅዱስ የሰላምና የፍቅር መጽሐፍ ከሆነ እንዴት ሰውን እረዱ ይላል?
ዘጸ 32:27 የእናንተም ሰው ሁሉ ወንድሙን ወዳጁንም ጎረቤቱንም “ይረድ” וְהִרְג֧וּ አላቸው።
1ነገ 18:40 ኤልያስም ከበኣል ነቢያት አንድ ሰው እንዳያመልጥ ያዙ አላቸው። ያዙአቸውም፤ ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ በዚያ “”አሳረዳቸው”” וַיִּשְׁחָטֵ֖ם።
2ነገ 10:11 ኢዩም ከአክዓብ ቤት የቀረውን ሁሉ፥ ታላላቆቹንም ሁሉ፥ ወዳጆቹንና ካህናቱን ማንም ሳይቀር በኢይዝራኤል “አረዳቸው” וַיִּשְׁחָטֵ֖ם ።
2ነገ 10:14፤ እርሱም። በሕይወታቸው ያዙአቸው አለ። ያዙአቸውም፥ በበግ ጠባቂዎችም ቤት አጠገብ ባለው ጕድጓድ አርባ ሁለቱን ሰዎች “አረዷቸው” וַיִּשְׁחָטֵ֖ם ፤ ማንንም አላስቀረም።
1ሳሙ 17:51፤ ዳዊትም ሮጦ በፍልስጥኤማዊው ላይ ቆመ፤ ሰይፉንም ይዞ ከሰገባው መዘዘው፥ ገደለውም፥ ራሱንም “አረደው” וַיְמֹ֣תְתֵ֔הוּ ።

ይህ ምንድን ነው? ቄራ ወይስ የፍቅርና የሰላም መጽሐፍ?

ቁጥር ሶስት
መጽሐፍ ቅዱስ የሰላምና የፍቅር መጽሐፍ ከሆነ እንዴት ሰውን በእሳት አቃጥሉ ይላል?
ዘሌ 20:14 ማናቸውም ሰው እናቲቱንና ልጂቱን ቢያገባ ርኵሰት ነው፤ በመካከላችሁ ኃጢአት እንዳይሆን እርሱና እነርሱ “”በእሳት ይቃጠሉ””።
ዘሌ 21:9 የካህንም ልጅ ራስዋን በግልሙትና ብታረክስ አባትዋን ታረክሰዋለች፤ “”በእሳት ትቃጠል””።
ኢያ 7:15 እርም የሆነውም ነገር የተገኘበት ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን አፍርሶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ በደል አድርጎአልና እርሱና ያለው ሁሉ “”በእሳት ይቃጠላሉ””።
ዘዳ 7:5 ነገር ግን እንዲህ አድርጉባቸው፤ መሠዊያቸውን አፍርሱ፥ ሐውልቶቻቸውንም ሰባብሩ፥ የማምለኪያ ዐፀዶቻቸውንም ቍረጡ፥ የተቀረጸውን ምስላቸውንም “”በእሳት አቃጥሉ””።
ዘዳ 7:25 የተቀረጸውንም የአምላኮቻቸውን ምስል “”በእሳት ታቃጥላለህ””፤ የተሠራባቸውን ብርና ወርቅ አትመኝ፤ በአምላክህም በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነውና እንዳትጠመድበት ከእርሱ ምንም አትውሰድ።
ዘዳ 12:3 መሠዊያቸውንም አፍርሱ፥ ሐውልቶቻቸውንም ሰባብሩ፥ የማምለኪያ ዐፀዶቻቸውንም “”በእሳት አቃጥሉ””፥ የአማልክቶቻቸውንም የተቀረጹ ምስሎች አንከታክቱ፤ ከዚያም ስፍራ ስማቸውን አጥፉ።
ኢያ 8:8 በያዛችኋትም ጊዜ ከተማይቱን “”በእሳት አቃጥሉአት””፤ እንደ እግዚአብሔር ቃል አድርጉ፤ እነሆ፥ አዝዣችኋለሁ።

ሰው የሚያመልክበትን የማምለኪያ አፀድ እና የሚኖርበትን ከተማ ማቃጠል ፍቅር ነውን?

ቁጥር አራት
መጽሐፍ ቅዱስ የሰላምና የፍቅር መጽሐፍ ከሆነ እንዴት ሰው ባልሠራው በደል አባቶቻቸው በሠሩት በደል ይገደሉ ይላል?
ይህም ትልቅ በደል ነው፦
በደል አንድ
አካን ሰርቆ ባጠፋው ወንዶችና ሴቶች ልጆቹንም፥ በሬዎቹንም፥ አህያዎቹንም፥ በጎቹንም ለምን መቃጠልና መወገር አስፈለገ?
ኢያሱ 7፥24-25 ኢያሱና እስራኤል ሁሉ የዛራን ልጅ አካንን፥ ብሩንም፥ ካባውንም፥ ወርቁንም፥ #ወንዶችና ሴቶች ልጆቹንም፥ በሬዎቹንም፥ አህያዎቹንም፥ በጎቹንም#፥ ድንኳኑንም፥ ያለውንም ሁሉ ወስደው ወደ አኮር ሸለቆ አመጡአቸው። ኢያሱም። ለምን አስጨነቅኸን? እግዚአብሔር ዛሬ ያስጨንቅሃል አለው እስራኤልም ሁሉ በድንጋይ ወገሩት# በእሳትም አቃጠሉአቸው#፥ #በድንጋይም ወገሩአቸው#።

በደል ሁለት
በሙሴ ዘመን አማሌቃውያን ከእስራኤል በመዋጋት ተዋጉ፦
ዘጸአት 17፥8 አማሌቅም መጥቶ ከእስራኤል ጋር በራፊድም ተዋጋ።

በሙሴ ዘመን አማሌቃውያን ከእስራኤል በመዋጋት በበደሉት ከ 400 ዓመት በኃላ የልጅ ልጆቻቸውን በሬውንና በጉን ግመሉንና አህያውን በማስገደል ተበቀለ፤ ይህ ምን የሚሉት በደል ነው?
1ኛ ሳሙኤል 15፥2-3 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “”እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ”” አማሌቅ በመንገድ እየተቃወመ ያደረገበትን #እበቀላለሁ#። አሁንም ሄደህ አማሌቅን ምታ፥ ያላቸውንም ሁሉ ፈጽመህ አጥፋ፥ አትማራቸውም #ወንዱንና ሴቱን ብላቴናውንና ሕፃኑን በሬውንና በጉን ግመሉንና አህያውን ግደል#።

አባቶች ስለ ልጆች አይገደሉ፥ ልጆችም ስለ አባቶች አይገደሉ ነገር ግን ሁሉ እያንዳንዱ በኃጢአቱ ይገደል የሚለው ትዕዛዛት የት ገባና ነው ምንም የማያቁትን ህፃናት ከ 400 ዓመት በኃላ የተፈጁት?
ዘዳግም 24፥16 አባቶች ስለ ልጆች አይገደሉ፥ ልጆችም ስለ አባቶች አይገደሉ ነገር ግን ሁሉ እያንዳንዱ በኃጢአቱ ይገደል።
2ኛ ነገሥት 14፥6 በሙሴ ሕግ መጽሐፍም እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔርም፦ ሁሉ በኃጢአቱ ይሙት እንጂ አባቶች በልጆች አይሙቱ፥ ልጆችም በአባቶች አይሙቱ ብሎ እንዳዘዘ የነፍሰ ገዳዮቹን ልጆች “አልገደለም””።

ይህንን የሰው ደም ያለበት መጽሐፍ ነው እንግዲህ የፍቅር እና የሰላም መጽሐፍ እየተባለ የሚሰበክለት? ፍርዱ ለኅሊና።
መደምደሚያ
ምእመናን አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ የማይገድሉት ናቸው፦
25፥68 *እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይገዙት፣ “ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ የማይገድሉት፣ የማያመነዝሩትም ናቸው፡፡ ይህንንም የሚሠራ ሰው ቅጣትን ያገኛል*፡፡ وَالَّذِينَ لَا يَدْعُونَ مَعَ اللَّهِ إِلَـٰهًا آخَرَ وَلَا يَقْتُلُونَ النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ وَلَا يَزْنُونَ ۚ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ يَلْقَ أَثَامًا

“እነዚያ” የሚለው አንጻራዊ ተውላጠ ስም ቁጥር 62 ላይ “ምእመናን” የሚለው ተክቶ የመጣ ነው። “ይህን” የሚለው ተውላጠ ስም ከአሏህ ሌላ መገዛት፣ አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ፣ ማመንዘን ሲያመለክት፥ ይህንን የሚሠራ ሰው ቅጣትን ያገኛል። አሏህ ነፍስን ያለ ሐቅ መግደል ሐራም አድርጓል፦
17፥33 *”ያቺንም አላህ ያወገዛትን ነፍስ ያለ ሕግ አትግደሉ”*፡፡ وَلَا تَقْتُلُوا النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ሐርረመ” حَرَّمَ የሚለው ቃል “ከለከለ” ማለት ነው። “ሐራም” حَرَام የሚለው ቃል እራሱ “ክልክል” ማለት ነው። አምላካችን አሏህ አንዲት ነፍስ መግደል ሐራም ስላደረገ “አትግደሉ” የሚል ሕግ አውጥቷል። ግን አንዲት ነፍስ ጥፋት ካጠፋች “በሕግ” ልትገደል ስለምትችል “ያለ ሕግ አትግደሉ” የሚል መርሕ አለ። ሰላማዊ ሰዎችን የገደለ የጀነትን ሽታ እንኳን አያሸትም፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 58 ሐዲስ 08
ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምር “ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"የሰላም ቃል ኪዳን የተገባለትን የገደለ የጀነትን ሽታ እንኳን አያሸትም፥ የእርሷ ሽታ የአርባ ዓመታት የጉዞ ርቀት ላይ ይገኛል"*። «عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ مَنْ قَتَلَ نَفْسًا مُعَاهَدًا لَمْ يَرَحْ رَائِحَةَ الْجَنَّةِ، وَإِنَّ رِيحَهَا يُوجَدُ مِنْ مَسِيرَةِ أَرْبَعِينَ عَامًا ‏

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ማስነጠስ

ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" ባስነጥሳቸው ጊዜ በእጃቸው ወይም በልብሳቸው ፊታቸውን ይሸፍኑታል፥ እንዲሁ ድምፅንም ይቀንሱበታል፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 2969 አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ *"ነቢዩ”ﷺ” ባስነጥሳቸው ጊዜ በእጃቸው ወይም በልብሳቸው ፊታቸውን ይሸፍኑታል፥ እንዲሁ ድምፅንም ይቀንሱበታል"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم كَانَ إِذَا عَطَسَ غَطَّى وَجْهَهُ بِيَدِهِ أَوْ بِثَوْبِهِ وَغَضَّ بِهَا صَوْتَهُ

ከኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ሆነ ለማንኛውም ቫይረስ ለመከላከል አንዱ የነቢያችንን"ﷺ" ፈለግ መከተል ተመራጭ ነው!

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ጨረቃ እና ኮከብ ምልክት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

41፥37 *”ሌሊት እና ቀንም፣ ጸሐይ እና ጨረቃም ከታምራቶቹ ናቸው፥ ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፤ ለዚያም ለፈጠራቸው ለአላህ ሰገዱ፤ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደሆናችሁ ለሌላ አትስገዱ”*። وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ

ጨረቃ እና ኮከብ ምልክት መሆን የተጀመረው መስቀለኞች ክርስቲያን መስቀልን አርማ አድርገው ዓለምን ከወረሩ በኃላ ነው፥ መስቀለኞች ዓለምን ለመውረር የመስቀል ጦርነት ያደረጉት ዘጠኝ ጊዜ ነው። መስቀል ኢየሱስ ከመወለዱ በፊት ጣዖታውን ለጣዖታቸው ምልክት ይጠቀሙበት ነበር፥ የግሪክ ባከስ፣ የጢሮስ ተሙዝ፣ የባቢሎናውያን ቤል፣ የኖርስ ኦዲን፣ የግብጻውያን አንክ ምልክታቸው መስቀል ነው። ለምሳሌ የግብፅ ሥላሴ ኦስሪስ፣ አይሲስ እና ሆረስ አርማቸው “አንክ” የተባለው መስቀል ነው። በኃላ ላይ የአዲስ ኪዳን እደ-ክታባት”manuscripts” ደንገል 66፣ ደንገል 45 እና 75 ልባስ ላይ ይህ አንክ የተባለው መስቀል ምልክት ተደርጓል። ዋቢ ምንጭ ይመልከቱ፦
የብሪታኒካ መድብለ-ዕውቀት(ኢንሳይክሎፔድያ) (1946)፣ ጥራዝ 6፣ ገጽ 753

ጨረቃ እና ኮከብ በ 1299 ድኅረ-ልደት ዑስማን ጋዚ የቱርክ ኢምፓየር ከተመሠረተ በኃላ ከመስቀለኞች ለመለየት አርማ ተደርጎ መጠቀም ተጀመረ። በመቀጠል በሦስተኛው ሙስጠፋ በ1757 ድኅረ-ልደት የአገር ባንዲራ እና በመሥጂድ ማማ ላይ ጨረቃ እና ኮከብ ተደርጎ መጠቀም ተጀመረ። በቁርኣን ሆነ በሐዲስ “ጨረቃ እና ኮከብ የኢሥላም አርማ ነው” የሚል ሽታው እንኳን የለም። ቀደምት ሠለፎች የሆኑት ሦስቱ ትውልዶችም ጨረቃ እና ኮከብ ለምልክትነት ተጠቅመው አያውቁም። መካህ ያለው የአሏህ ቤት ከዕባህ ላይ አለመኖሩ የዚህ ማስረጃ ነው።
ጨረቃ እና የንጋት ኮከብ ፀሐይ አምላካችን አላህ ለሰው ልጆች የዓመታትን ቁጥርና ሒሳብን መቁጠሪያ ያደረጋቸው ፍጡራን ብቻ ናቸው፦
6፥96 እርሱም ጎህን ከሌሊት ጨለማ ፈልቃቂ ሌሊትንም ማረፊያ *”ፀሐይንና ጨረቃንም ለጊዜ መቁጠሪያ አድራጊ ነው”*፡፡ فَالِقُ الْإِصْبَاحِ وَجَعَلَ اللَّيْلَ سَكَنًا وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ حُسْبَانًا ۚ ذَٰلِكَ تَقْدِيرُ الْعَزِيزِ الْعَلِيمِ
10፥5 *እርሱ ያ ፀሐይን አንጻባራቂ ጨረቃንም አብሪ ያደረገ ነው፡፡ የዓመታትን ቁጥርና ሒሳብን ታውቁ ዘንድም ለእርሱ መስፈሪያዎችን የለካ ነው፡፡ አላህ ይህንን በእውነት እንጂ በከንቱ አልፈጠረውም”*፡፡ ለሚያውቁ ሕዝቦች አንቀጾችን ያብራራል፡፡ هُوَ الَّذِي جَعَلَ الشَّمْسَ ضِيَاءً وَالْقَمَرَ نُورًا وَقَدَّرَهُ مَنَازِلَ لِتَعْلَمُوا عَدَدَ السِّنِينَ وَالْحِسَابَ ۚ مَا خَلَقَ اللَّهُ ذَٰلِكَ إِلَّا بِالْحَقِّ ۚ يُفَصِّلُ الْآيَاتِ لِقَوْمٍ يَعْلَمُونَ

የዓመታትን ቀመር መለኪያ ሁለቱ ዐበይት የዘመን መቁጠሪያ “አል-ቀመሪያህ” القَمَرِيَّة ማለትም “የጨረቃ አቆጣጠር”lunar calendar” እና “አሽ-ሸምሢያህ” الشَمْسِيَّة ማለትም “የፀሐይ አቆጣጠር”solar calendar” ናቸው። ሌሊት እና ቀን፥ ጸሐይ እና ጨረቃ አላህ የፈጠራቸው እና ለሰው ልጆች የተፈጠሩ ታምራቶቹ ናቸው እንጂ በኢሥላም አይመለኩም። በኢሥላም የሚመለከው እነርሱን የፈጠራቸው አላህ ብቻ ነው፦
41፥37 *”ሌሊት እና ቀንም፣ ጸሐይ እና ጨረቃም ከታምራቶቹ ናቸው፥ ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፤ ለዚያም ለፈጠራቸው ለአላህ ሰገዱ፤ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደሆናችሁ ለሌላ አትስገዱ”*። وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ይህ ፔጅ የእኔ ነው። እዚህ ታይም ላይኔ ላይ ሙሉ የሆነባችሁ እዛው ገብታችሁ መኮመት ትችላላችሁ፥ ጥያቄ ካላችሁ ኮሜንት ላይ አስቀምጡ! አድሚኖች ስላሉ ይነግሩኛል። ዐቃቢያነ እምነት እና ዐቀብተ-እምነት ምን ማለት ነው? "ዐቅብተ እምነት" ማለት "የእምነት ጥበቃ" ወይም "የእምነት ዘብ" ማለት ነው፥ በዚህ መስክ የተሰማሩ ደግሞ ተባታይ ከሆነ "ዐቃቤ እምነት" አንስታይ ከሆነች "ዐቃቢት እምነት" ትባላለች። "ዐቃቢያን" ደግሞ የዐቃቤ ብዙ ቁጥር ነው። "አፓሎጄቲክስ"Apologetics" የሚለው የኢንግሊሹ ቃል "አፓሎጂአ" ἀπολογία ማለትም "መከላከል" ከሚለው ከግሪክ ኮይኔ ቃል የመጣ ነው።
ለኢሥላም ዘብ እና አበጋዝ የሆኑ ሙሥሊሞች ዐቃቢያነ ኢሥላም ይባላሉ።
እኔ የንጽጽር ተማሪ ስሆን በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የማስቀምጥ ወንድማችሁ ነኝ። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች፣ የታሪክ እና የሥነ-አመክንዮ ሙግት በማቅረብ ተሟጋች እና ጦማሪ ነኝ። ለሙግቴ ነጥቤ በዋነኝነት የምጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

ፔጁን ላይክ እና ሼር በማድረግ የትምህርቱን ተደራሽነት ያስፉ! ፔጁ ይህ ነውና ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፦ https://www.facebook.com/ዐቃቢያነ-እሥልምና-376584689605736/
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 43, ሐዲስ 171
ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ማንም ለታናናሾቻችን የማያዝን እና ታላቆቻችንን የማያከብር ከእኛ አይደለም"*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرٍو، يَرْوِيهِ - قَالَ ابْنُ السَّرْحِ - عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ مَنْ لَمْ يَرْحَمْ صَغِيرَنَا وَيَعْرِفْ حَقَّ كَبِيرِنَا فَلَيْسَ مِنَّا ‏"‏ ‏

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ቀደር በባይብል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

54፥49 *እኛ ሁሉን ነገር በልክ ፈጠርነው*፡፡ إِنَّا كُلَّ شَيْءٍ خَلَقْنَاهُ بِقَدَرٍ

የኢማን መሰረቶች ስድስት ሲሆኑ፤ እነርሱም፦ በአላህ ማመን፣ በመላእክቱ ማመን፣ በመጽሐፍቱ ማመን፣ በነቢያቱ ማመን፣ በመጨረሻው ቀን ማመን እና በቀደር ማመን ናቸው፤ ከስድስቱ የኢማን መሰረቶች ስድስተኛው በቀደር ማመን መሆነ እሙንና ቅቡል ነው፤ ይህ በሐዲሱል ጂብሪል ተገልጿል፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 5
ዑመር ኢብኑ ኽጣብ እንዳስተላለፈው፦ “አንድ በጣም ነጭ ልብስ የለበሰና በጣም ጥቁር ጸጉር ያለው ሰው በመጣ ጊዜ ከአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ጋር ነበርን፤ ወደ እርሳቸው ሲጓዝ የመንገደኛነት ምልክትአይታይበትም ነበር፦ ወደ ነቢዩ”ﷺ” እስከሚደርስ ድረስ ከእኛ መካከል ማንም ዐላወቀውም፤ ጉልበቱን በእራሳቸው ጉልበት አስጠግቶ ከዚያም እንዲህ አለ፦ *”ሙሐመድ ሆይ! ኢማን ምንድን ነው? እርሳቸውም፦ “በአላህ ማመን፣ በመላእክቱ ማመን፣ በመጽሐፍቱ ማመን፣ በነቢያቱ ማመን፣ በመጨረሻው ቀን ማመን እና በሰናይ እና እኩይ ቀደር ማመን ነው” አሉ*። قَالَ عُمَرُ بْنُ الْخَطَّابِ كُنَّا عِنْدَ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَجَاءَ رَجُلٌ شَدِيدُ بَيَاضِ الثِّيَابِ شَدِيدُ سَوَادِ الشَّعَرِ لاَ يُرَى عَلَيْهِ أَثَرُ السَّفَرِ وَلاَ يَعْرِفُهُ مِنَّا أَحَدٌ حَتَّى أَتَى النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم فَأَلْزَقَ رُكْبَتَهُ بِرُكْبَتِهِ ثُمَّ قَالَ يَا مُحَمَّدُ مَا الإِيمَانُ قَالَ ‏”‏ أَنْ تُؤْمِنَ بِاللَّهِ وَمَلاَئِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ وَالْقَدَرِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ ‏”‏

“ቀደር” قَدَر የሚለው ቃል “ቀደረ” قَدَرَ ማለትም “ቻለ” ወይም “ወሰነ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ውሳኔ” ማለት ነው፤ “ቀድር” قَدْر ማለት ደግሞ “ችሎታ” ማለት ነው፤ “አል-ቀዲር” القَدِير ማለት “ሁሉን ቻይ” “ከሃሊ ኩሉ” ማለት ሲሆን ከአላህ ስሞች ውስጥ አንዱ ነው፤ “ተቅዲር” تَقْدِير ማለትም “ሁሉን ቻይነት” የአላህ ባህርይ ነው፤ አላህ “ሁሉን ቻይ” ነው ማለት “ሁሉንም ነገር ማድረግ ይችላል” ማለት ነው። አምላካችን አላህ ሁሉን ቻይ ስለሆነ ነገርን ሁሉ በቀደር ፈጥሮታል፦
5፥17 *የሚሻውን ይፈጥራል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው*፡፡ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِير
54፥49 *እኛ ሁሉን ነገር በልክ ፈጠርነው*፡፡ إِنَّا كُلَّ شَيْءٍ خَلَقْنَاهُ بِقَدَرٍ

“ልክ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ቀደር” قَدَر ሲሆን አላህ ነገርን ሁሉ አስቀድሞ በዕውቀቱ፣ በኪታቡ፣ በፈቃዱ እና በሥራው ቀድሮታል። ይህንን ቅድሚያ ከቁርኣን እንመልከት እና ከዚያ ከባይብል ኢንሿላህ እንመለከታለን፦

ነጥብ አንድ
“የአላህ ዕውቀት”
በቁርአን ከተገለፁት የአላህ መልካም ስሞች መካከል “አል-ዐሊም” الْعَلِيم ወይም “አል-ዓሊም” الْعَٰلِم ሲሆን “ሁሉን ዐዋቂ” ማለት ነው፤ አላህ ሁሉን ነገር ዐዋቂ ነው፦
33፥54 ማንኛውንም ነገር ብትገልጹ ወይም ብትደብቁ በእርሱ ይመነዳችኋል፤ *አላህ ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነውና*። إِن تُبْدُوا شَيْئًا أَوْ تُخْفُوهُ فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا

“ዒልም” عِلْم ማለት “ዕውቀት” ማለት ሲሆን የአላህ ዕውቀት የአላህ የራሱ ባሕርይ ነው፥ "ነገር" ደግሞ ፍጡር ነው። አላህ ፍጥረት ከመፈጠሩ በፊት ያንን ፍጥረት ያውቀዋል፥ ከፍጥረት በፊት የሚከሰቱ ነገሮችን ሁሉ ቀድሞ ያውቃቸዋል።

ነጥብ ሁለት
“ጥብቁ ሰሌዳ”
አምላካችን አላህ ስለ አንድ ነገር ዕውቀት በመጽሐፍ ውስጥ ከሁሉ ነገር መከሰት፣ መደረግ እና መከናወን በፊት መዝግቦቷል፦
22፥70 አላህ *በሰማይና በምድር ውስጥ ያለን ሁሉ በእርግጥ የሚያውቅ መኾኑን አታውቅምን? ይህ በመጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ ነው*፡፡ ይህ በአላህ ላይ ገር ነው፡፡ أَلَمْ تَعْلَمْ أَنَّ اللَّهَ يَعْلَمُ مَا فِي السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ ۗ إِنَّ ذَٰلِكَ فِي كِتَابٍ ۚ إِنَّ ذَٰلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرٌ

አምላካችን አላህ የሚከትብበትና የሚቀድርበት ኪታብ “ለውሐል መሕፉዝ” ይባላል። “ለውሐል መሕፉዝ” لَوحَ المَّحْفُوظ ማለት “የተጠበቀው ሰሌዳ”preserved tablet” ማለት ሲሆን አንድ ክስተት ከመከሰቱ በፊት፣ አንድ ድርጊት ከመደረጉ በፊት፣ አንድ ክንውን ከመከናወኑ በፊት ስለሚያውቀው ያንን ዕውቀት በተጠበቀው ሰሌዳ ከትቦታል፦
57፥22 በምድርም በራሳችሁም መከራ ማንንም አትነካም *ሳንፈጥራት በፊት በመጽሐፍ የተመዘገበች ብትኾን እንጅ*፡፡ ይህ በአላህ ላይ ገር ነው፡፡ مَا أَصَابَ مِن مُّصِيبَةٍ فِي الْأَرْضِ وَلَا فِي أَنفُسِكُمْ إِلَّا فِي كِتَابٍ مِّن قَبْلِ أَن نَّبْرَأَهَا ۚ إِنَّ ذَٰلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرٌ

ነጥብ ሦስት
“የአላህ ፈቃድ”
“ሻአ” شَآءَ ማለት “ፈቃድ” ማለት ሲሆን አምላካችን አላህ በፍጥረተ-ዓለማት ውስጥ የሚሻውን ይፈጥራል፦
24፥45 *አላህ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና*፡፡ يَخْلُقُ اللَّهُ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِير

ሰዎች የሚፈጽሙ እውነትና ውሸት፣ ትክክልና ስህተት፣ መልካሙና ክፉ፣ አላህ የሚወደውና የሚጠላው ሐራምና ሐላል በሙሉ አላህ ስለፈቀደ ነው የሚከናወኑት። ያለ አላህ ፈቃድ ምንም የሚሆን ነገር የለም፣ አላህ ፈቀደ ማለት ግን ጉዳዩን ወዶታል አሊያም ተስማምቶበታል ማለት አይደለም፣ አላህ ስለፈቀደ ነው ሰው ነጻ ፈቃድ ያለው፣ አላህ ሳይፈቅድ ሰው ነጻ ፈቃድ አይኖረውም ነበር፦
81፥29 *የዓለማት ጌታ አላህ ካልሻም አትሹም*፡፡ وَمَا تَشَاءُونَ إِلَّا أَن يَشَاءَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ
76፥30 *አላህም ካልሻ በስተቀር አትሹም፡፡ አላህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና*፡፡ وَمَا تَشَاءُونَ إِلَّا أَن يَشَاءَ اللَّهُ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلِيمًا حَكِيمًا

ነጥብ አራት
“የአላህ ፍጥረት”
“ፊዕል” فِعْل ማለት “ድርጊት”action” ማለት ሲሆን አራት ነገር ናቸው፥ እነርሱም፦ ጊዜ፣ ቦታ፣ ቁስ እና ነጻ ምርጫ ናቸው፤። እነዚህን ነገሮች የፈጠረው አላህ ነው፥ አላህ የነገር ሁሉ ፈጣሪ ነው፦
39፥62 *አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው*፡፡ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ

“ነገር” በሚለው ቃል ውስጥ መልካም ነገር እና መጥፎ ነገር ይካተታሉ። አላህ እኛንም እኛ የምንሰራውን ሁሉ የፈጠረ ነው፦
37፥96 *አላህ እናንተንም የምትሠሩትንም የፈጠረ ሲኾን*፡፡ وَاللَّهُ خَلَقَكُمْ
ስለ ቀደር በግርድፉ እና በሌጣው ይህንን ያክል ከቁርኣን ካየን ዘንዳ ከባይብል ደግሞ እናያለን! ባይብል ላይ ጳውሎስ እንደተናገረው እግዚአብሔር ዓለም ሳይፈጠር እና ዘመን ሳይቆጠር ከፍጥረት በፊት አማንያንን መርጧል፥ ጸጋውንም ሰጥቷል ይለናል፦
ኤፌሶን 1፥5 *"በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን"*።
ኤፌሶን 1፥4 *"ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን"*።
2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥9 *"ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን"*።

"አስቀድሞ ወሰነን"Having predestinated us" የሚለው ይሰመርበት። በክርስቶስ ሥራ ልጆች ለመሆን የመረጠው እና ይህንን ጸጋ የሰጠው ከፍጥረት አስቀድሞ ያወቃቸው አስቀድሞ በመወሰኑ ነው፦
ኤፌሶን 1፥11 *"እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ፥ አስቀድመን የተወሰንን በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን"*።
ሮሜ 8፥29-30 ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ *"አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤ አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው"*፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው።

"አስቀድመን የተወሰንን"being predestinated" እና "አስቀድሞም የወሰናቸው"whom he did predestinate" የሚለው ይሰመርበት። አሁን የሚጠራቸው፣ የሚያጸድቃቸው እና የሚያከብራቸው ከፍጥረት በፊት አስቀድሞም የወሰናቸው ነው። እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እርሱ ከሃድያንም እንዲጠፉ ከፍጥረት አስቀድሞ ወስኗል፦
ቆላስይስ 2፥22 እንደ ሰው ሥርዓትና ትምህርት አትያዝ፥ አትቅመስ፥ አትንካ ለሚሉት ትእዛዛት በዓለም እንደምትኖሩ ስለ ምን ትገዛላችሁ? *"እነዚህ ሁሉ በመደረግ ሊጠፉ ተወስነዋልና"*።

"እነዚህ ሁሉ በመደረግ ሊጠፉ ተወስነዋልና"are all destined to perish with use" የሚለው ይሰመርበት። እግዚአብሔር ኃጢአተኛን የፈጠረው ለክፉ ቀን ነው፥ ኅጥኣን ከማኅፀን ጀምረው ተለይተዋል፦
ምሳሌ 16፥4 እግዚአብሔር ሁሉን ለእርሱ ለራሱ ፈጠረ፥ ኀጥእን ደግሞ ለክፉ ቀን።
መዝሙር 58፥3 *ኅጥኣን ከማኅፀን ጀምረው ተለዩ*።

የያዕቆብ ልጆች ገና ሳይወለዱ አሊያም በጎ ወይም ክፉ ምንም ሳያደርጉ የእርሱ ውሳኔ ይጸና ዘንድ ታላቁ ለታናሹ ይገዛል ብሎ ተናግሯል፦
ሮሜ 9፥11-13 *"ልጆቹ ገና ሳይወለዱ፥ በጎ ወይም ክፉ ምንም ሳያደርጉ፥ ከጠሪው እንጂ ከሥራ ሳይሆን በምርጫ የሚሆን የእግዚአብሔር አሳብ ይጸና ዘንድ፥ ለእርስዋ፦ ታላቁ ለታናሹ ይገዛል፥ ተባለላት። ያዕቆብን ወደድሁ ኤሳውን ግን ጠላሁ ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው"*።

እግዚአብሔር ኃይሉን ለማሳየት አስቀድሞ የፈርዖንን ልብ አደንድኗል፥ እንግዲህ የሚወደውን ይምረዋል፥ የሚወደውንም እልከኛ ያደርገዋል፦
ሮሜ 9፥17 *"መጽሐፍ ፈርዖንን፦ ኃይሌን በአንተ አሳይ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ይነገር ዘንድ ለዚህ አስነሣሁህ፥ ይላልና። እንግዲህ የሚወደውን ይምረዋል፥ የሚወደውንም እልከኛ ያደርገዋል"*።
ምሳሌ 21፥1 *"የንጉሥ ልብ እንደ ውኃ ፈሳሾች በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ ወደ ወደደውም ያዘነብለዋል"*።

እግዚአብሔር የወደደውን ሁሉ ያደርጋል፥ እንደ ፈቃዱ ያደርጋል። ምን ታደርጋለህ? የሚለው የለም፦
መዝሙር 135፥6 *"በሰማይና በምድር በባሕርና በጥልቆች ሁሉ፥ እግዚአብሔር የወደደውን ሁሉ አደረገ"*።
ዳንኤል 4፥35 *"በምድርም የሚኖሩ ሁሉ እንደ ምናምን ይቈጠራሉ፤ በሰማይም ሠራዊት በምድርም ላይ በሚኖሩ መካከል እንደ ፈቃዱ ያደርጋል፤ እጁንም የሚከለክላት ወይም ምን ታደርጋለህ? የሚለው የለም"*።

ጨለማን እና ክፋትንም ሁሉ የፈጠረው እርሱን ነው፦
ኢሳይያስ 45፥7 *"ብርሃንን ሠራሁ፥ “ጨለማውንም ፈጠርሁ” ደኅንነትን እሠራለሁ፥ “ክፋትንም እፈጥራለሁ”፤ “እነዚህን ሁሉ ያደረግሁ” እግዚአብሔር እኔ ነኝ"*።

የተወሰነ ነገር ሁሉ ደግሞ ተጽፏል፥ ለምሳሌ ኢየሱስ ወደላከው እንደሚሄድ አስቀድሞ የተወሰነው ተጽፏል፦
ሉቃስ 22፥22 *"የሰው ልጅስ እንደ ተወሰነው ይሄዳል፥ ነገር ግን አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት"*።
ማቴዎስ 26፥24 የሰው ልጅስ *"ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይሄዳል"፥ ነገር ግን የሰው ልጅ አልፎ ለሚሰጥበት ለዚያ ሰው ወዮለት"*።
ዮሐንስ 7፥33 ኢየሱስም፦ ገና ጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር እቆያለሁ ወደ ላከኝም እሄዳለሁ።
ዮሐንስ 16፥5 *አሁን ግን ወደ ላከኝ እሄዳለሁ ከእናንተም፦ ወዴት ትሄዳለህ? ብሎ የሚጠይቀኝ የለም*።

ሰው የተፈጠረበት ቀን ሆነ ምንም ነገር ሳይቀር አስቀድሞ በመጽሐፍ ተጽፏል፦
መዝሙር 139፥16 ያልተሠራ አካሌን ዓይኖችህ አዩኝ፤ *የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይቀር በመጽሐፍህ ተጻፉ*። Thine eyes did see my substance, yet being unperfect; and in thy book all my members were written, which in continuance were fashioned, when as yet there was none of them.

ከሞላ ጎደል፣ አነሰም በዛ፣ ከብዙ በጥቂቱ ስለ ቀደር በባይብል ይህንን ይመስላል። የይሆዋ ምስክሮች፦ "አምላክ አንድ ነገር ከመከሰቱ በፊት ዐያውቅም፥ ቅድመ-ውሳኔ የሚባል ትምህርት የለም" ሲሉ ከላይ የተዘረዘሩትን አናቅጽ አስተባብለዋል። ፕሮቴስታንቱ ደግሞ በቅድመ ውሳኔ ለሁለት ጎራ ተከፍለዋል፥ አንደኛው ቅድመ-ውሳኔ አለ ብለው የሚያምኑ ካልቪኒስት"Calvinist" ሲባሉ ሁሉተኛው ቅድመ-ውሳኔ የለም ብለው የሚያምኑ ደግሞ አርሚኒያን"Arminian" ይባላሉ። ስለዚህ "ሁሉ ክርስቲያን በቅድመ-ውሳኔ አያምኑም" ብሎ አንድ አግዳሚ ላይ መመዘን አግባብ አይደለም።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም