ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.3K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ፈጣሪ አይተኛም አያንቀላፋም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

ሰው በፍጡርነቱ ያንቀላፋል ይተኛልም፤ ፈጣሪ ግን ፍጡር ስላልሆነ አይተኛም አያንቀላፋም፦
መዝ.121:4 እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ #አይተኛም #አያንቀላፋምም

ኢየሱስ ደግሞ በተቃራኒው ፍጡር ስለሆነ ይተኛን ያንቀላፋል፦
ማርቆስ 4:38 እርሱም በስተኋላዋ ትራስ ተንተርሶ #ተኝቶ ነበር፤ #አንቅተውም። መምህር ሆይ፥ ስንጠፋ አይገድህምን? አሉት።

መቼም ኢየሱስ ለእኛ ሲል ነው የተኛውና ያንቀላፋው ከተባለ ለምን ማንቀላፋትና መተኛት አላቆማችሁም? "እኔ የምተኛው የማይተኛ አምላክ ስላለኝ ነው" ተብሎ የተፓሰተው እጅግ በጣም ስህተት ነው፤ የፈጣሪን ባህርይ ለፍጡር መስጠት አይገባም፤ ይህ ቃል መባል ያለበት ፍጡር ለሆነው ለሚተኛው ለኢየሱስ ሳይሆን ኢየሱስ ሲተኛ ሲጠብቀው ለነበረው ለአላህ ብቻ ነው፤ አላህ በጥበቃው ላይ እንቅልፍ የሚባል ባህርይ የለውም፦
2፥255 አላህ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ሕያው ራሱን ቻይ ነው፡፡ "#ማንገላጀትም #እንቅልፍም አትይዘውም"፡፡ በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው፡፡ ያ እርሱ ዘንድ በፈቃዱ ቢኾን እንጅ የሚያማልድ ማነው? ከፍጡሮች በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ በሻውም ነገር እንጂ ከዕውቀቱ በምንም ነገር አያካብቡም፡፡ መንበሩ ሰማያትንና ምድርን ሰፋ፡፡ ጥበቃቸውም አያቅተውም፡፡ እርሱም የሁሉ በላይ ታላቅ ነው፡፡

አንዱ አምላክ የማይተኛና የማያንቀላፋ ከሆነ፣ ኢየሱስ ደግሞ የሚተኛና የሚያንቀላፋ ከሆነ ፣ የሚተኛና የሚያንቀላፋ ኢየሱስ ፣ የማይተኛና የማያንቀላፋውን አንዱን አምላክ በምን አይነት መልኩ እንዴት አድርጎ ሊሆን ይችላል?

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም