ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
"በአላህ ማመን" ማለት እራሱ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም ብሎ በጣዖት መካድና በእርሱ ማመን ነው። ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም ብሎ በጣዖትም የሚክድ እና በአላህ የሚያምን ሰው ለእርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ፦
2፥256 *በጣዖትም የሚክድ እና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ*፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡ فَمَن يَكْفُرْ بِالطَّاغُوتِ وَيُؤْمِن بِاللَّهِ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ لَا انفِصَامَ لَهَا ۗ وَاللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ
31፥22 *እርሱ መልካም ሠሪ ሆኖ ፊቱን ወደ አላህ የሚሰጥም ሰው ጠንካራን ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ*፡፡ የነገሩም ሁሉ ፍጻሜ ወደ አላህ ነው፡፡ وَمَن يُسْلِمْ وَجْهَهُ إِلَى اللَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ ۗ وَإِلَى اللَّهِ عَاقِبَةُ الْأُمُور

“የሰጠ” ለሚለው ቃል የገባው “ዩሥሊም” يُسْلِمْ ሲሆን “ሙሥሊም” مُسْلِم እና “ኢሥላም” إِسْلَٰم የሚሉት ቃላት ከረባበት “አሥለመ” أَسْلَمَ ማለትም “ታዘዘ” “ተገዛ” ”አመለከ” “ሁሉ ነገሩን ሰጠ” ከሚል የመጣ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። ሰው ሢሠልም ጠንካራን ዘለበት ይጨብጣል፤ ይህም ጠንካራን ዘለበት በጣዖትም የሚክድ እና በአላህ የሚያምን ሰው የሚይዘው እሥልምና ነው። አላህ ዘንድ ያለው ሃይማኖት ኢሥላም ብቻ ነው፤ ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ተቀባይ የለውም፤ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው፦
3፥19 አላህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት *“ኢሥላም”* ብቻ ነው፡፡ إِنَّ ٱلدِّينَ عِندَ ٱللَّهِ ٱلْإِسْلَٰمُ
3፥85 *”ከኢሥላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከእርሱ ተቀባይ የለውም”*፡፡ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው፡፡ وَمَن يَبْتَغِ غَيْرَ ٱلْإِسْلَٰمِ دِينًۭا فَلَن يُقْبَلَ مِنْهُ وَهُوَ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ

2፥62 ላይ የክርስትና እምነት፣ የአይሁድ እምነት እና የሳቢያን እምነት ትክክል ነው እያለ ሳይሆን ይሁዳውያን፣ ክርስቲያን እና ሳቢያን ግለሰብ በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ያመኑ መልካምንም ሥራ የሠሩ ከሆኑ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው። ምክንያቱም አንድ ሰው በአርካኑል ኢማን ካመነ ሙሥሊም ነውና። ግን አህሉል ኪታብ በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ስለማያምኑ ነው በሙሥሊም አገር ውስጥ ጂዚያህ የሚከፍሉት፦
9፥29 *"ከእነዚያ መጽሐፍን ከተሰጡት ሰዎች እነዚያን በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የማያምኑትን"*፣ አላህና መልክተኛው እርም ያደረጉትንም እርም የማያደርጉትንና እውነተኛውንም ሃይማኖት የማይቀበሉትን እነርሱ የተዋረዱ ኾነው ግብርን በእጆቻቸው እስከሚሰጡ ድረስ ተዋጉዋቸው፡፡ قَاتِلُوا الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَلَا بِالْيَوْمِ الْآخِرِ وَلَا يُحَرِّمُونَ مَا حَرَّمَ اللَّهُ وَرَسُولُهُ وَلَا يَدِينُونَ دِينَ الْحَقِّ مِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ حَتَّىٰ يُعْطُوا الْجِزْيَةَ عَن يَدٍ وَهُمْ صَاغِرُونَ

ልብ አድርግ "አለዚነ" الَّذِينَ ማለትም "እነዚያ" ከሚለው አመልካች-ተውላጠ ስም መነሻ ላይ "ሚን" مِن ማለትም "ከ" የሚል መስተዋድ አለ። ይህ የሚያሳየው ከአህሉል ኪታብ በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የማያምኑ እንዳሉ ሁሉ በተቃራኒው ከአህሉል ኪታብ በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑ በእነርሱ ላይ ቁርኣን በሚነበብላቸውም ጊዜ "በእርሱ(በቁርኣን) አምነናል፥ እርሱ ከጌታችን የኾነ እውነት ነው፡፡ እኛ ከእርሱ(ከቁርኣኑ) በፊት ሙሥሊሞች ነበርን" ይላሉ። ከመጽሐፉ ሰዎች ቀጥ ያሉ በሌሊት ሰዓቶች እነርሱ የሚሰግዱ ኾነው የአላህን አንቀጾች የሆነውን ቁርኣን የሚያነቡ ሕዝቦች አሉ፦
28፥52 *"እነዚያ ከእርሱ(ከቁርአን) በፊት መጽሐፍን የሰጠናቸው እነርሱ በእርሱ(በቁርኣን) ያምናሉ"*፡፡ الَّذِينَ آتَيْنَاهُمُ الْكِتَابَ مِن قَبْلِهِ هُم بِهِ يُؤْمِنُون
28፥53 *"በእነርሱ ላይ በሚነበብላቸውም ጊዜ «በእርሱ አምነናል፡፡ እርሱ ከጌታችን የኾነ እውነት ነው፡፡ እኛ ከእርሱ በፊት ሙሥሊሞች ነበርን» ይላሉ"*፡፡ وَإِذَا يُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ قَالُوا آمَنَّا بِهِ إِنَّهُ الْحَقُّ مِن رَّبِّنَا إِنَّا كُنَّا مِن قَبْلِهِ مُسْلِمِين
3፥113 *"የመጽሐፉ ሰዎች ሁሉ እኩል አይደሉም፡፡ ከመጽሐፉ ሰዎች ቀጥ ያሉ በሌሊት ሰዓቶች እነርሱ የሚሰግዱ ኾነው የአላህን አንቀጾች የሚያነቡ ሕዝቦች አሉ"*፡፡ لَيْسُوا سَوَاءً ۗ مِّنْ أَهْلِ الْكِتَابِ أُمَّةٌ قَائِمَةٌ يَتْلُونَ آيَاتِ اللَّهِ آنَاءَ اللَّيْلِ وَهُمْ يَسْجُدُونَ

እነዚህ ታዲያ ሙሥሊሞች አይደሉምን? እንዴታ! ናቸው እንጂ። የመጽሐፉም ባለቤቶች በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ቢያምኑ እና በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ከመካድ ቢጠነቀቁ አላህ ኃጢኣቶቻቸውን በእርግጥ ያስተሰርይ እና የመጠቀሚያ ገነቶችንም በእርግጥ ያገባቸው ነበር። ከእነርሱ ውስጥ በአላህ እና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑ ትክክለኞች ሕዝቦች አሉ፡፡ ከእነሱም ብዙዎቹ በአላህ እና በመጨረሻው ቀን በመካድ የሚሠሩት ነገር ከፋ፦
5፥65 *"የመጽሐፉም ባለቤቶች ባመኑ እና ከክህደትም በተጠነቀቁ ኖሮ ከእነርሱ ኃጢኣቶቻቸውን በእርግጥ ባበስንና የመጠቀሚያ ገነቶችንም በእርግጥ ባገባናቸው ነበር"*፡፡ وَلَوْ أَنَّ أَهْلَ الْكِتَابِ آمَنُوا وَاتَّقَوْا لَكَفَّرْنَا عَنْهُمْ سَيِّئَاتِهِمْ وَلَأَدْخَلْنَاهُمْ جَنَّاتِ النَّعِيمِ
5፥66 *"ከእነርሱ ውስጥ ትክክለኞች ሕዝቦች አሉ፡፡ ከእነርሱም ብዙዎቹ የሚሠሩት ነገር ከፋ!"* مِّنْهُمْ أُمَّةٌ مُّقْتَصِدَةٌ ۖ وَكَثِيرٌ مِّنْهُمْ سَاءَ مَا يَعْمَلُونَ

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር ሃያ ሰባት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 27
ያላመኑ ቤተሰቦችን መወዳጀት ተፈቅዷል ወይስ አልተፈቀደም?

ተፈቅዷል፡- 
ሱራ 31:15 “ለአንተ በርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር በኔ እንድታጋራ ቢታገሉህም፣ አትታዘዛቸው፤ በቅርቢቱም ዓለም፣ በመልካም ስራ ተወዳጃቸው፤ ወደ እኔም የተመለሰን ሰው መንገድ ተከተል፤ ከዚያም መመለሻችሁ ወደኔ ነው፤ ትሰሩት የነበራችሁንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፤ (አልነው)።”

አልተፈቀደም፡- 
ሱራ 9:23 “እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አባቶቻችሁና ወንድሞቻችሁ ክሕደትን ከእምነት አብልጠው ቢወዱ፣ ወዳጆች አድርጋቸሁ አትያዙዋቸው፤ ከናንተም ዉስጥ ወዳጅ የሚያደርጋቸው፣ እነዚያ እርሱ በዳዮች ናቸው፡፡”

መልስ
የወላጅ ሃቅ በኢሥላም ትልቅ ቦታ አለው፥ ወላጅን ማመስገን፣ ለወላጅ መልካም መሥራት፣ በጎ መዋል፣ መልካም ንግግር መናገር የወላጅ ሃቅ ነው፦
31፥14 *ለእኔም ለወላጆችህም አመስግን በማለት አዘዝነው*፡፡ መመለሻው ወደ እኔ ነው፡፡ أَنِ اشْكُرْ لِي وَلِوَالِدَيْكَ إِلَيَّ الْمَصِيرُ
45፥15 *ሰውንም በወላጆቹ በጎ መዋልን በጥብቅ አዘዝነው*፡፡ وَوَصَّيْنَا الْإِنسَانَ بِوَالِدَيْهِ إِحْسَانًا
17፥23 ጌታህም እንዲህ ሲል አዘዘ፡- እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ *በወላጆቻችሁም መልካምን ሥሩ፡፡ በአንተ ዘንድ ኾነው አንዳቸው ወይም ሁለታቸው እርጅናን ቢደርሱ ፎህ አትበላቸው፡፡ አትገላምጣቸውም፡፡ ለእነርሱም መልካምን ቃል ተናገራቸው*፡፡ وَقَضَىٰ رَبُّكَ أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا إِيَّاهُ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا ۚ إِمَّا يَبْلُغَنَّ عِندَكَ الْكِبَرَ أَحَدُهُمَا أَوْ كِلَاهُمَا فَلَا تَقُل لَّهُمَا أُفٍّ وَلَا تَنْهَرْهُمَا وَقُل لَّهُمَا قَوْلًا كَرِيمًا
6፥151 «ኑ፤ ጌታችሁ በእናንተ ላይ እርም ያደርገውን ነገር በእርሱም ያዘዛችሁን ላንብብላችሁ» በላቸው፡፡ «በእርሱ በአላህ ላይ ምንንም ነገር አታጋሩ፡፡ *ለወላጆችም በጎን ሥራ ሥሩ*፡፡ قُلْ تَعَالَوْا أَتْلُ مَا حَرَّمَ رَبُّكُمْ عَلَيْكُمْ ۖ أَلَّا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا ۖ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا
4፥36 *አላህንም አምልኩ፤ በእርሱም ምንንም አታጋሩ፡፡ በወላጆች፣ በቅርብ ዝምድና ባለቤትም፣ በየቲሞችም፣ በምስኪኖችም፣ በቅርብ ጎረቤትም፣ በሩቅ ጎረቤትም፣ በጎን ባልደረባም፣ በመንገደኛም፣ እጆቻችሁም ንብረት ባደረጓቸው መልካምን ሥሩ*፤ አላህ ኩራተኛ ጉረኛ የኾነን ሰው አይወድም፡፡ وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا ۖ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا وَبِذِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَالْجَارِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَالْجَارِ الْجُنُبِ وَالصَّاحِبِ بِالْجَنبِ وَابْنِ السَّبِيلِ وَمَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخْتَالًا فَخُورًا
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 79, ሐዲስ 47
አቢ በክራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ *"ትላልቅ ወልጀሎችን ልንገራችሁን? እነርሱም፦ "አዎ የአላህ መልእክተኛ ሆይ!" እርሳቸው፦ "በአላህ ላይ ማሻረክ እና ለወላጆች ግዴለሽ መሆን ነው" አሉ"*። عَنْ عَبْدِ الرَّحْمَنِ بْنِ أَبِي بَكْرَةَ، عَنْ أَبِيهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ أَلاَ أُخْبِرُكُمْ بِأَكْبَرِ الْكَبَائِرِ ‏"‌‏.‏ قَالُوا بَلَى يَا رَسُولَ اللَّهِ‏.‏ قَالَ ‏"‏ الإِشْرَاكُ بِاللَّهِ، وَعُقُوقُ الْوَالِدَيْن
ነገር ግን ለወላጅም ቢሆን በትክክል ፍትሕ ቀዋሚዎች እና ለአላህ መስካሪዎች መሆን አለብን፦
4፥135 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *በትክክል ፍትሕ ቀዋሚዎች በራሳችሁ ወይም በወላጆች እና በቅርብ ዘመዶች ላይ ቢኾንም እንኳ ለአላህ መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሀብታም ወይም ድኻ ቢኾን አላህ በእነርሱ ከእናንተ ይበልጥ ተገቢ ነው፡፡ እንዳታደሉም ዝንባሌን አትከተሉ፡፡ ብታጠምሙም ወይም መመስከርን ብትተው አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ بِالْقِسْطِ شُهَدَاءَ لِلَّهِ وَلَوْ عَلَىٰ أَنفُسِكُمْ أَوِ الْوَالِدَيْنِ وَالْأَقْرَبِينَ ۚ إِن يَكُنْ غَنِيًّا أَوْ فَقِيرًا فَاللَّهُ أَوْلَىٰ بِهِمَا ۖ فَلَا تَتَّبِعُوا الْهَوَىٰ أَن تَعْدِلُوا ۚ وَإِن تَلْوُوا أَوْ تُعْرِضُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا

እዚህ አንቀጽ ላይ “ተዕዲሉ” تَعْدِلُوا የሚለው ቃል ይሰመርበት፤ ይህ ቃል የስም መደቡ “ዐድል” عَدْل ሲሆን “ፍትሕ” ማለት ነው፤ ፍትሕ ለአላህ ፍራቻ ተብሎ እና አላህ በምንሠራው ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው ተብሎ የሚደረግ ነው። ይህ ለአላህ ተብሎ የሚደረግ ፍትሕ ዝንባሌን ከመከተል ነጻ ያወጣል። አላህ ሰውንም በወላጆቹ በመልካም አድራጎትን እንድንወዳጅ ቢያዘንም ነገር ግን ወላጅ ጣዖት አምልክ ቢለን በዚህ ነጥብ በፍጹም እንዳንታዘዛቸው ከልክሎናል፦
31፥15 ለአንተ በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር *"በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህም አትታዘዛቸው፡፡ "በቅርቢቱም ዓለም በመልካም ሥራ ተወዳጃቸው"*፡፡ ወደ እኔም የተመለሰን ሰው መንገድ ተከተል፡፡ ከዚያም መመለሻችሁ ወደእኔ ነው፡፡ ትሠሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፡፡وَإِن جَاهَدَاكَ عَلَىٰ أَن تُشْرِكَ بِي مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ فَلَا تُطِعْهُمَا ۖ وَصَاحِبْهُمَا فِي الدُّنْيَا مَعْرُوفًا ۖ وَاتَّبِعْ سَبِيلَ مَنْ أَنَابَ إِلَيَّ ۚ ثُمَّ إِلَيَّ مَرْجِعُكُمْ فَأُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
29፥8 *ሰውንም በወላጆቹ መልካም አድራጎትን አዘዝነው፡፡ ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ጣዖት በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህ አትታዘዛቸው*፡፡ መመለሻችሁ ወደ እኔ ነው፡፡ ትሠሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፡፡ وَوَصَّيْنَا الْإِنسَانَ بِوَالِدَيْهِ حُسْنًا ۖ وَإِن جَاهَدَاكَ لِتُشْرِكَ بِي مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ فَلَا تُطِعْهُمَا ۚ إِلَيَّ مَرْجِعُكُمْ فَأُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

"በቅርቢቱም ዓለም በመልካም ሥራ ተወዳጃቸው" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት። "ተወዳጃቸው" የሚለው ቃል "ሷሒብሁማ" صَاحِبْهُمَا ሲሆን "ሷሒብ" صَىٰحِب ማለትም "ባልደረባ" ከሚለው የስም መደብ የረባ ሲሆን "ባልደረባ ሁናቸው" ማለት ነው። በመልካም ሥራ ባልደረባነት ማለት ወላጅን ማመስገን፣ ለወላጅ መልካም መሥራት፣ በጎ መዋል፣ መልካም ንግግር መናገር እና ጡረታ መጦር ወዘተ ነው። እርሱም ቢሆን በቅርቢቱም ዓለም ጉዳይ ላይ ነው። ግን በተቃራኒው፦ "ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ጣዖት በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህ አትታዘዛቸው" የሚለውን ሃይለ-ቃል ይሰመርበት። ይህንን ክህደት ከእምነት አብልጠው ቢወዱ እረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙዋቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ እረዳት የሚያደርጋቸው እነዚያ እነርሱ በዳዮች ናቸው፦
9፥23 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *"አባቶቻችሁና ወንድሞቻችሁ ክህደትን ከእምነት አብልጠው ቢወዱ ወዳጆች አድርጋችሁ አትያዙዋቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ ወዳጅ የሚያደርጋቸው እነዚያ እነርሱ በዳዮች ናቸው*። يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا آبَاءَكُمْ وَإِخْوَانَكُمْ أَوْلِيَاءَ إِنِ اسْتَحَبُّوا الْكُفْرَ عَلَى الْإِيمَانِ ۚ وَمَن يَتَوَلَّهُم مِّنكُمْ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الظَّالِمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "አውሊያ" أَوْلِيَاءَ በብዜት የመጣው "ወሊይ" وَلِىّ ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ "ወሊይ" ማለት "እረዳት" ማለት ነው። በመልካም በማዘዝ በመጥፎ በመከልከል ለአማኞች ወሊይ እራሳቸው አማኞች እንጂ ከሃድያን ወላጆች ወሊይ አይደሉም፦
9፥71 *"ምእምንና ምእምናትም ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ በደግ ነገር ያዛሉ፤ ከክፉም ይከለክላሉ"*፡፡ ሶላትንም ይሰግዳሉ፡፡ ዘካንም ይሰጣሉ፡፡ አላህንና መልክተኛውንም ይታዘዛሉ፡፡ እነዚያን አላህ በእርግጥ ያዝንላቸዋል፡፡ አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና፡፡ وَالْمُؤْمِنُونَ وَالْمُؤْمِنَاتُ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ ۚ يَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ وَيُقِيمُونَ الصَّلَاةَ وَيُؤْتُونَ الزَّكَاةَ وَيُطِيعُونَ اللَّهَ وَرَسُولَهُ ۚ أُولَـٰئِكَ سَيَرْحَمُهُمُ اللَّهُ ۗ إِنَّ اللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ

ይህ ወደ ሺክር የሚያመራ ወዳጅነት በትንሳኤ ቀን፦ "ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ" የሚያስብል ጸጸት ነውና እንጠንቀቅ፦
25፥28 «ዋ ጥፋቴ! *"እገሌን ወዳጅ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ"*፡፡ يَا وَيْلَتَىٰ لَيْتَنِي لَمْ أَتَّخِذْ فُلَانًا خَلِيلًا

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር ሃያ ስምንት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 28
ሙስሊሞች ከክርስቲያኖች ጋር እንዲወዳጁ ተፈቅዷል ወይስ አልተፈቀደም?

ተፈቅዷል፡- 
ሱራ 5:82 “ይሁዶችንና እነዚያን ያጋሩትን፣ ለነዚያ ለአመኑት በጠላትነት ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ የበረቱ ሆነው በእርግጥ ታገኛለህ፤ እነዚያንም እኛ ክርስቲያኖች ነን ያሉትን ለነዚያ ለአመኑት በወዳጅነት በእርግጥ ይበልጥ የቀረቧቸው ሆነው ታገኛለህ፤ ይህ ከነሱ ውስጥ ቀሳውስትና መነኮሳት በመኖራቸውና እነሱም የማይኮሩ በመሆናቸው ነው።”

አልተፈቀደም፡- 
ሱራ 5:51 “እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ይሁዶችንና ክርስቲያኖችን ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ፤ ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፤ ከናንተም ውስጥ ረዳቶች የሚያደርጋቸው ሰው እርስ ከነርሱ ነው፤ አላህ አመጠኞችን ሕዝቦች አያቀናም።”

መልስ
5፥82 *"አይሁዶችንና እነዚያን ያጋሩትን ለእነዚያ ለአመኑት በጠላትነት ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ የበረቱ ኾነው በእርግጥ ታገኛለህ፡፡ እነዚያንም «እኛ ክርስቲያኖች ነን» ያሉትን ለእነዚያ ለአመኑት በወዳጅነት በእርግጥ ይበልጥ የቀረቧቸው ኾነው ታገኛለህ፡፡ ይህ ከእነርሱ ውስጥ ቀሳውስትና መነኮሳት በመኖራቸውና እነርሱም የማይኮሩ በመኾናቸው ነው"*፡፡ لَتَجِدَنَّ أَشَدَّ النَّاسِ عَدَاوَةً لِّلَّذِينَ آمَنُوا الْيَهُودَ وَالَّذِينَ أَشْرَكُوا ۖ وَلَتَجِدَنَّ أَقْرَبَهُم مَّوَدَّةً لِّلَّذِينَ آمَنُوا الَّذِينَ قَالُوا إِنَّا نَصَارَىٰ ۚ ذَٰلِكَ بِأَنَّ مِنْهُمْ قِسِّيسِينَ وَرُهْبَانًا وَأَنَّهُمْ لَا يَسْتَكْبِرُونَ

"ጠላትነት" እና "ወዳጅነት" ሁለት ጠርዝ ነው። እዚህ አንቀጽ ላይ አይሁዶችና እነዚያን ያጋሩት ለአማንያን ጠላትነት አላቸው አለ እንጂ አይሁዶችና እነዚያን ያጋሩት ጥሉ አይልም። እንዲሁ ክርስቲያኖች ለአማንያን ወዳጅነት አላቸው አለ እንጂ ክርስቲያኖች ውደዱ አይልም። "ሙስሊሞች ከክርስቲያኖች ጋር እንዲወዳጁ ተፈቅዷል" የሚል እሳቤ ጭራሹኑ የለም። "መወዳህ" مَّوَدَّة ማለት "ፍቅር" ማለት ነው። ይህ አንቀጽ የወረደበት ምክንያት ንጉሥ ዐርማህን እና ባልደረቦቹን በተመለከተ ነው። እርሱ ጋር ቀሳውስትና መነኮሳት በመኖራቸውና እነርሱም የማይኮሩ በመኾናቸው ነው። ወደ መልክተኛውም የተወረደውን ቁርኣን በሰሙ ጊዜ እውነቱን ከማወቃቸው የተነሳ ዓይኖቻቸው እንባን የሚያፈሱ ነበሩ፦
5፥83 *"ወደ መልክተኛውም የተወረደውን ቁርኣን በሰሙ ጊዜ እውነቱን ከማወቃቸው የተነሳ ዓይኖቻቸው እንባን ሲያፈሱ ታያለህ"*፡፡ «ጌታችን ሆይ! አመንን ከመስካሪዎቹም ጋር ጻፈን » ይላሉ፡፡ وَإِذَا سَمِعُوا مَا أُنزِلَ إِلَى الرَّسُولِ تَرَىٰ أَعْيُنَهُمْ تَفِيضُ مِنَ الدَّمْعِ مِمَّا عَرَفُوا مِنَ الْحَقِّ ۖ يَقُولُونَ رَبَّنَا آمَنَّا فَاكْتُبْنَا مَعَ الشَّاهِدِينَ

እነዚህ ቁርኣንን አምነው ከመስካሪዎቹ የሆኑት ናቸው። በተረፈ አይደለም ክርስቲያን እና አይሁድ ማንንም ከምእምናን ሌላ ረዳቶች አድርገን አንይዝም፦
3፥28 *"ምእምናን ከሓዲዎችን ከምእምናን ሌላ ረዳቶች አድርገው አይያዙ፡፡ ይኼንንም የሚሠራ ሰው ከአላህ ሃይማኖት በምንም ውስጥ አይደለም"*፡፡ ከእነርሱ መጥጠበቅን ብትጠበቁ እንጂ፡፡ አላህ እራሱ ያስጠነቅቃችኋል፡፡ መመለሻም ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡ لَّا يَتَّخِذِ الْمُؤْمِنُونَ الْكَافِرِينَ أَوْلِيَاءَ مِن دُونِ الْمُؤْمِنِينَ ۖ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ فَلَيْسَ مِنَ اللَّهِ فِي شَيْءٍ إِلَّا أَن تَتَّقُوا مِنْهُمْ تُقَاةً ۗ وَيُحَذِّرُكُمُ اللَّهُ نَفْسَهُ ۗ وَإِلَى اللَّهِ الْمَصِيرُ
5፥51 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *"አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ፡፡ ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ ረዳቶች የሚያደርጋቸው ሰው እርሱ ከእነርሱ ነው"*፡፡ አላህ አመጸኞችን ሕዝቦች አያቀናም፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا الْيَهُودَ وَالنَّصَارَىٰ أَوْلِيَاءَ ۘ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ ۚ وَمَن يَتَوَلَّهُم مِّنكُمْ فَإِنَّهُ مِنْهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِين

እዚህ አንቀጽ ላይ "አውሊያ" أَوْلِيَاءَ በብዜት የመጣው "ወሊይ" وَلِىّ ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ "ወሊይ" ማለት "እረዳት" ማለት ነው። በመልካም በማዘዝ በመጥፎ በመከልከል ለአማኞች ወሊይ እራሳቸው አማኞች እንጂ ከሃድያን ወሊይ አይደሉም፦
9፥71 *"ምእምንና ምእምናትም ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ በደግ ነገር ያዛሉ፤ ከክፉም ይከለክላሉ"*፡፡ ሶላትንም ይሰግዳሉ፡፡ ዘካንም ይሰጣሉ፡፡ አላህንና መልክተኛውንም ይታዘዛሉ፡፡ እነዚያን አላህ በእርግጥ ያዝንላቸዋል፡፡ አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና፡፡ وَالْمُؤْمِنُونَ وَالْمُؤْمِنَاتُ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ ۚ يَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ وَيُقِيمُونَ الصَّلَاةَ وَيُؤْتُونَ الزَّكَاةَ وَيُطِيعُونَ اللَّهَ وَرَسُولَهُ ۚ أُولَـٰئِكَ سَيَرْحَمُهُمُ اللَّهُ ۗ إِنَّ اللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ

ይህ ወደ ሺክር የሚያመራ ወዳጅነት በትንሳኤ ቀን፦ "ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ" የሚያስብል ጸጸት ነውና እንጠንቀቅ፦
25፥28 «ዋ ጥፋቴ! *"እገሌን ወዳጅ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ"*፡፡ يَا وَيْلَتَىٰ لَيْتَنِي لَمْ أَتَّخِذْ فُلَانًا خَلِيلًا

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር ሃያ ዘጠኝ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 29
መልእክተኞች ሆነው የተላኩት ሰዎች ብቻ ወይስ ሌሎች ፍጥረታትም ጭምር?

ሰዎች ብቻ፡- 
ሱራ 12:109 “ካንተ በፊትም ከከተሞች ሰዎች ወደነርሱ ራዕይ የምናወርድላቸው የሆኑን ወንዶችን እንጂ አልላክንም፤ በምድር ላይ አይኼዱምና የነዚያን ከነሱ በፊት የነበሩትን ሰዎች መጨረሻ አይመለከቱምን? የመጨረሻይቱም አገር፣ ለነዚያ ለተጠነቀቁት በእርግጥ የተሻለች ናት፤ አታውቁምን?”

ሌሎች ፍጥረታትም ተልከዋል፡- 
ሱራ 22:75 “አላህ ከመላእክት ውስጥ መልክተኞችን ይመርጣል፤ ከስዎችም፣ (እንደዚሁ) አላህ ስሚ ተመልካች ነው።”

መልስ
“ወሕይ” وَحْى የሚለው ቃል “አውሓ” أَوْحَىٰٓ “ገለጠ” ወይም “አወረደ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ግልጠተ-መለኮት” ወይም “ግህደተ-መለኮት”Revelation” ማለት ነው። አምላካችን አላህ ወሕይ የሚያወርድላቸው ነቢያት ሰዎች ብቻ ነበሩ። ይህንን ያስተባበሉት ዐረብ ሙሽሪኪን፦ “ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጅ ሌላ ነውን? በማለት ተናገሩ፦
21፥3 ልቦቻቸው ዝንጉዎች ኾነው እነዚያም የበደሉት ሰዎች መንሾካሾክን ደበቁ፡፡ *”ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጅ ሌላ ነውን?”* እናንተም የምታዩ ስትኾኑ *”ድግምትን ለመቀበል ትመጣላችሁን?”*» አሉ لَاهِيَةًۭ قُلُوبُهُمْ ۗ وَأَسَرُّوا۟ ٱلنَّجْوَى ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ هَلْ هَٰذَآ إِلَّا بَشَرٌۭ مِّثْلُكُمْ ۖ أَفَتَأْتُونَ ٱلسِّحْرَ وَأَنتُمْ تُبْصِرُونَ

ዐረብ ሙሽሪኪን፦ “ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጅ ሌላ አይደለምና ይህ መልክተኛ ምግብን የሚበላ፣ በገበያዎችም የሚኼድ ሲኾን”* ምን አለው አስጠንቃቂ ይኾን ዘንድ እርሱ መልአክ አይወረድም ኖሯልን? አሉ፦
25፥7 ለእዚህም *”መልክተኛ ምግብን የሚበላ፣ በገበያዎችም የሚኼድ ሲኾን”* ምን አለው ከእርሱ ጋር *”አስጠንቃቂ ይኾን ዘንድ ወደ እርሱ መልአክ አይወረድም”* ኖሯልን? *”አሉ”* وَقَالُوا۟ مَالِ هَٰذَا ٱلرَّسُولِ يَأْكُلُ ٱلطَّعَامَ وَيَمْشِى فِى ٱلْأَسْوَاقِ ۙ لَوْلَآ أُنزِلَ إِلَيْهِ مَلَكٌۭ فَيَكُونَ مَعَهُۥ نَذِيرًا
25፥21 እነዚያም መገናኘታችንን የማይፈሩት፦ *”በእኛ ላይ ለምን መላእክት አልወረደም”*፡፡ ወይም ጌታችንን ለምን አናይም *”አሉ”*፡ በነፍሶቻቸው ውስጥ በእርግጥ ኮሩ፡፡ ታላቅንም አመጽ አመፁ وَقَالَ ٱلَّذِينَ لَا يَرْجُونَ لِقَآءَنَا لَوْلَآ أُنزِلَ عَلَيْنَا ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ أَوْ نَرَىٰ رَبَّنَا ۗ لَقَدِ ٱسْتَكْبَرُوا۟ فِىٓ أَنفُسِهِمْ وَعَتَوْ عُتُوًّۭا كَبِيرًۭا

አላህም ከዚህ በፊት አስጠንቃቂ ይኾኑ ዘንድ ወሕይ የምናወርድላቸው የኾነን ሰዎችን እንጂ ሌላን አላክንም፤ ምግብን የማይበሉ አካልም አላደረግናቸውም፤ የማታውቁም ብትኾኑ የመጽሐፉን ባለቤቶች ጠይቁ ብሎ ምላሽ ሰጠ፦
21፥7 ከአንተም በፊት ወደ እነርሱ ወሕይ የምናወርድላቸው የኾነን *”ሰዎችን እንጂ ሌላን አላክንም”*፡፡ የማታውቁም ብትኾኑ የመጽሐፉን ባለቤቶች *”ጠይቁ”* وَمَآ أَرْسَلْنَا قَبْلَكَ إِلَّا رِجَالًۭا نُّوحِىٓ إِلَيْهِمْ ۖ فَسْـَٔلُوٓا۟ أَهْلَ ٱلذِّكْرِ إِن كُنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ
21፥8 *”ምግብን የማይበሉ አካልም አላደረግናቸውም*”፡፡ ዘውታሪዎችም አልነበሩም وَمَا جَعَلْنَٰهُمْ جَسَدًۭا لَّا يَأْكُلُونَ ٱلطَّعَامَ وَمَا كَانُوا۟ خَٰلِدِينَ
25፥20 ከአንተ በፊትም *”ከመልክተኞች እነርሱ በእርግጥ ምግብን የሚበሉ በገበያዎችም የሚኼዱ ኾነው በስተቀር አልላክንም”* وَمَآ أَرْسَلْنَا قَبْلَكَ مِنَ ٱلْمُرْسَلِينَ إِلَّآ إِنَّهُمْ لَيَأْكُلُونَ ٱلطَّعَامَ وَيَمْشُونَ فِى ٱلْأَسْوَاقِ ۗ وَجَعَلْنَا بَعْضَكُمْ لِبَعْضٍۢ فِتْنَةً أَتَصْبِرُونَ ۗ وَكَانَ رَبُّكَ بَصِيرًۭا

አላህ ጠይቁ ያለው ጠያቂዎች ዐረብ ሙሽሪኮችን መሆኑን ካየን ጠይቁ የተባሉት ጥያቄ፦ “ከነቢያችን"ﷺ" በፊት ወሕይ ሲወርድላቸው የነበሩት ሰዎች ወይስ መልአክ? የሚለውን ነው። ዐረብ ሙሽሪኮች ከእነርሱ ውስጥ ወደ ኾነ አንድ ሰው አላህ ወሕይ ማውረዱ ድንቅ ስለሆነባቸው ያንን ወሕይ ድግምት ነው፤ መልእክተኛውን ድግምተኛ ነው ብለው አስተባበሉ፦
10፥2 *”ሰዎችን አስጠንቅቅ”*፤ እነዚያንም ያመኑትን ለእነርሱ ከጌታቸው ዘንድ መልካም ምንዳ ያላቸው መኾኑን *”አብስር”*» በማለት *”ከእነርሱው”* ወደ ኾነ አንድ ሰው *”ራእይን ማውረዳችን ለሰዎች ድንቅ ኾነባቸውን”* ከሓዲዎቹ፡- «ይህ በእርግጥ ግልጽ ድግምተኛ ነው» *”አሉ”* أَكَانَ لِلنَّاسِ عَجَبًا أَنْ أَوْحَيْنَآ إِلَىٰ رَجُلٍۢ مِّنْهُمْ أَنْ أَنذِرِ ٱلنَّاسَ وَبَشِّرِ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَنَّ لَهُمْ قَدَمَ صِدْقٍ عِندَ رَبِّهِمْ ۗ قَالَ ٱلْكَٰفِرُونَ إِنَّ هَٰذَا لَسَٰحِرٌۭ مُّبِينٌ
38፥4 *”ከእነርሱ የሆነ አስጠንቃቂም”* ስለ መጣላቸው ተደነቁ፡፡ ከሓዲዎቹም፦ *”ይህ ድግምተኛ ውሸታም ነው”*» *”አሉ”* وَعَجِبُوٓا۟ أَن جَآءَهُم مُّنذِرٌۭ مِّنْهُمْ ۖ وَقَالَ ٱلْكَٰفِرُونَ هَٰذَا سَٰحِرٌۭ كَذَّابٌ
50፥2 ይልቁንም *”ከእነርሱ”* ጎሳ የኾነ *”አስጠንቃቂ”* ስለ *”መጣላቸው”* ተደነቁ፡፡ *”ከሓዲዎቹም”* «ይህ አስደናቂ ነገር ነው» *”አሉ*” بَلْ عَجِبُوٓا۟ أَن جَآءَهُم مُّنذِرٌۭ مِّنْهُمْ فَقَالَ ٱلْكَٰفِرُونَ هَٰذَا شَىْءٌ عَجِيبٌ
አላህም ነቢያችንን"ﷺ"፦ “ለእናንተም እኔ መልአክ ነኝ አልልም፤ ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ” በላቸው በማለት ተናግሯል፦
6:50 «ለእናንተ የአላህ ግምጃ ቤቶች እኔ ዘንድ ናቸው አልልም፡፡ ሩቅንም አላውቅም፡፡ *”ለእናንተም እኔ መልአክ ነኝ አልልም”*፡፡ ወደ እኔ *”የሚወርድልኝን”* እንጅ ሌላን አልከተልም» በላቸው قُل لَّآ أَقُولُ لَكُمْ عِندِى خَزَآئِنُ ٱللَّهِ وَلَآ أَعْلَمُ ٱلْغَيْبَ وَلَآ أَقُولُ لَكُمْ إِنِّى مَلَكٌ ۖ إِنْ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ
18፥110 «እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ወደ እኔ የሚወረድልኝ *”ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ”*፡፡ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ» *”በላቸው”* قُلْ إِنَّمَآ أَنَا۠ بَشَرٌۭ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَمَن كَانَ يَرْجُوا۟ لِقَآءَ رَبِّهِۦ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًۭا صَٰلِحًۭا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِۦٓ أَحَدًۢا

አላህ መላእክትን ወደ ነቢያት እና ወደ ሙዕሚኒን ይልክ ስለበር መላእክት መልእክተኞች ተብለዋል፦
22፥75 *"አላህ ከመላእክት ውስጥ መልክተኞችን ይመርጣል፥ ከሰዎችም እንደዚሁ ይመርጣል"*፡፡ አላህ ሰሚ ተመልካች ነው፡፡ اللَّهُ يَصْطَفِي مِنَ الْمَلَائِكَةِ رُسُلًا وَمِنَ النَّاسِ ۚ إِنَّ اللَّهَ بَصِيرٌ

"መላእክት" በሚለው ቃል መነሻ ቅጥያ ላይ "ከ" የሚል መስተዋድድ መምጣቱ በራሱ አላህ መላእክትን እንደሚልክ እና እነዚያ መላእክት እንደ ሰው የማይመገቡ መሆናቸው ተገልጿል፦
11፥69 *መልእክተኞቻችንም ኢብራሂምን በልጅ ብስራት በእርግጥ መጡት፡፡ ሰላም አሉት፡፡ ሰላም አላቸው፡፡ ጥቂትም ሳይቆይ ወዲያውኑ የተጠበሰን የወይፈን ስጋ አመጣ*፡፡ وَلَقَدْ جَاءَتْ رُسُلُنَا إِبْرَاهِيمَ بِالْبُشْرَىٰ قَالُوا سَلَامًا ۖ قَالَ سَلَامٌ ۖ فَمَا لَبِثَ أَن جَاءَ بِعِجْلٍ حَنِيذٍ
11፥70 *እጆቻቸውም ወደ እርሱ የማይደርሱ መኾነቸውን ባየ ጊዜ ሸሻቸው፡፡ ከእነርሱም ፍርሃት ተሰማው፡፡ «አትፍራ እኛ ወደ ሉጥ ሕዝቦች ተልከናልና» አሉት*፡፡ فَلَمَّا رَأَىٰ أَيْدِيَهُمْ لَا تَصِلُ إِلَيْهِ نَكِرَهُمْ وَأَوْجَسَ مِنْهُمْ خِيفَةً ۚ قَالُوا لَا تَخَفْ إِنَّا أُرْسِلْنَا إِلَىٰ قَوْمِ لُوطٍ

"ሰዎች" በሚለው ቃል መነሻ ቅጥያ ላይ "ከ" የሚል መስተዋድድ መምጣቱ በራሱ አላህ ነቢያትን እንደሚልክ እና እነዚያ ነቢያት የሚመገቡ መሆናቸው ተገልጿል፦
25፥20 ከአንተ በፊትም *”ከመልክተኞች እነርሱ በእርግጥ ምግብን የሚበሉ በገበያዎችም የሚኼዱ ኾነው በስተቀር አልላክንም”* وَمَآ أَرْسَلْنَا قَبْلَكَ مِنَ ٱلْمُرْسَلِينَ إِلَّآ إِنَّهُمْ لَيَأْكُلُونَ ٱلطَّعَامَ وَيَمْشُونَ فِى ٱلْأَسْوَاقِ ۗ وَجَعَلْنَا بَعْضَكُمْ لِبَعْضٍۢ فِتْنَةً أَتَصْبِرُونَ ۗ وَكَانَ رَبُّكَ بَصِيرًۭا

እዚህ አንቀጽ ላይ "ኢላ" إِلَّا የሚለው አፍራሽ ቃል “ኢስቲስናዕ” اِسْتِثْنَاء‏ ማለትም “ግድባዊት”Exceptional” ሆኖ የመጣው አንጻራዊ ሆኖ ነው፥ "ምግብ የሚበሉ በገበያዎችም የሚኼዱ ኾነው በስተቀር አልላክንም" ማለት "ምግብ እዲበሉ በገበያዎችም እንዱኼዱ ኾነው ብቻ ነው የተላኩት" የሚለውን አያሲዝም። ምክንያቱም በአንጻራዊነት ስለመጣ። ለምሳሌ፦
51፥56 *ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም*፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ
6፥164 በላቸው «እርሱ የሁሉ ጌታ ሲኾን ከአላህ በቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን *ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም*፡፡ قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَبْغِى رَبًّۭا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَىْءٍۢ ۚ وَلَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ إِلَّا عَلَيْهَا
2፥174 *እነዚያ አላህ ከመጽሐፍ ያወረደውን የሚደብቁ በርሱም በመደበቃቸው ጥቂትን ዋጋ የሚገዙ እነዚያ በሆዶቻቸው ውስጥ እሳትን እንጂ አይበሉም”*፡፡ አላህም በትንሣኤ ቀን አያናግራቸውም፤ ከኃጢኣት አያጠራቸውምም፡፡ ለነርሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡ إِنَّ الَّذِينَ يَكْتُمُونَ مَا أَنزَلَ اللَّهُ مِنَ الْكِتَابِ وَيَشْتَرُونَ بِهِ ثَمَنًا قَلِيلًا ۙ أُولَـٰئِكَ مَا يَأْكُلُونَ فِي بُطُونِهِمْ إِلَّا النَّارَ وَلَا يُكَلِّمُهُمُ اللَّهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَلَا يُزَكِّيهِمْ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

"ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም" ማለት ሰዎች እንዳይበሉ እንዳይጠጡ እንዳይጋቡ አልተፈጠሩም ማለትን አያሲዝም፥ "ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ ክፉን አትሠራም" ማለት እራሷን ትጎዳለች ለማለት ተፈልጎ እንጂ ሌላውን ሰው አትጎዳም ማለትን አያሲዝም፥ "ሆዶቻቸው ውስጥ እሳትን እንጂ አይበሉም” ማለት ምግብ አይበሉም ማለትን አያሲዝም። ልክ እንደዚሁ ከላይ ያለውን ጥቅስ በዚህ ልክና መልክ መረዳት ይቻላል።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር ሠላሳ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 30
የሙሐመድ"ﷺ" ገነት መግባት እርግጥ ነው ወይስ አይታወቅም?

እርግጥ ነው፡- 
ሱራ 48፡1-2 “እኛ ላንተ ግልጽ የሆነን መክፈት ከፈትንልህ። አላህ ከኃጥያትህ ያለፈውንና የሚመጣውን ላንተ ሊምር ጸጋውንም ባንተ ላይ ሊሞላ ቀጥተኛውንም መንገድ ሊመራህ፣ (ከፈተልህ)።”

አይታወቅም፡- 
ሱራ 46:9 “ከመልክተኞች ብጤ የሌለኝ አይደለሁም በኔም በናንተም ምን እንደሚሠራም አላውቅም ወደኔ የሚወረደውን እጅግ ሌላን አልከተልም እኔም ግልጽ አስፈራሪ እንጅ ሌላ አይደለሁም በላቸው፡፡”

መልስ
ነቢያችን”ﷺ” ወሕይ ከመጣላቸው በኃላ በቀጥተኛው መንገድ ላይ እንደሆኑ አምላካችን አላህ ተናግሯል፦
43፥43 ያንንም ወደ አንተ የተወረደልህን አጥብቀህ ያዝ፡፡ *አንተ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነህና*፡፡ فَٱسْتَمْسِكْ بِٱلَّذِىٓ أُوحِىَ إِلَيْكَ ۖ إِنَّكَ عَلَىٰ صِرَٰطٍۢ مُّسْتَقِيمٍۢ

አላህ ነቢያችን”ﷺ” በቀጥተኛ መንገድ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ጀነት ገብተውም በጀነት ያለው ፀጋ እንደሚሰጣቸው ቃል ገብቶላቸዋል፦
108፥1 *እኛ በጣም ብዙ በጎ ነገሮችን ሰጠንህ*፡፡ إِنَّآ أَعْطَيْنَٰكَ ٱلْكَوْثَرَ

በዚህ አንቀጽ ላይ “በጎ ነገር” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ከውሰር” كَوْثَر ሲሆን በጀነት ውስጥ ያለ ከወተት የነጻና ከማር የጣፈጠ ወንዝ ነው፤ ይህ ከውሰር ለነቢያችን”ﷺ” የተሰጠ ዋስትና ነው፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3684
አነስ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ “እኛ ከውሰርን ሰጠንህ” ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *”በጀነት ወንዝ ነው፤ በጀነት ወንዝ ድንኳኖቹ ከድንጋይ የተሠሩ አየው፤ ጂብሪል ሆይ! ምንድን ነው? አልኩት፤ እርሱም ከውሰር ነው፤ አላህ ለአንተ የሰጠህ” አለኝ”*።
عَنْ أَنَسٍ ‏:‏ ‏(‏ إناَّ، أَعْطَيْنَاكَ الْكَوْثَرَ ‏)‏ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ هُوَ نَهْرٌ فِي الْجَنَّةِ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ فَقَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ رَأَيْتُ نَهْرًا فِي الْجَنَّةِ حَافَتَاهُ قِبَابُ اللُّؤْلُؤِ قُلْتُ مَا هَذَا يَا جِبْرِيلُ قَالَ هَذَا الْكَوْثَرُ الَّذِي قَدْ أَعْطَاكَهُ اللَّهُ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ أَبُو عِيسَى هَذَا حَدِيثٌ حَسَنٌ صَحِيحٌ

ነቢያችን”ﷺ” ጀነት አይደለም መግባት በተጨማሪ የጀነት ጀረጃቸውንም አላህ እንደነገረን ከላይ ያለው አንቀጽ በወፍ በረር ለቅምሻ ያክል በቂ ነው፤ ታዲያ ይህ ዋስትና እያለ አላህ ነቢያችንን”ﷺ” “በእኔም በእናንተም ምን እንደሚሠራም ዐላውቅም” በል ሲላቸው እውን ሚሽነሪዎች እንደሚሉት “ወደ ፊት የት እንደምንገባ ዐናውቅም” በል ማለታቸውን ያሳያልን? ይህንን የተንሸዋረረና የተወላገደ መረዳት ጥንልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ እንየው፦
46፥9 *ከመልክተኞች ብጤ የሌለኝ አይደለሁም፤ በእኔም በእናንተም ምን እንደሚሠራም ዐላውቅም፤ ወደ እኔ የሚወረደውን እጅግ ሌላን አልከተልም፤ እኔም ግልጽ አስጠንቃቂ እንጅ ሌላ አይደለሁም* በላቸው። قُلْ مَا كُنتُ بِدْعًۭا مِّنَ ٱلرُّسُلِ وَمَآ أَدْرِى مَا يُفْعَلُ بِى وَلَا بِكُمْ ۖ إِنْ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ وَمَآ أَنَا۠ إِلَّا نَذِيرٌۭ مُّبِينٌۭ
ከነቢያችን”ﷺ” በፊት የመጡት በእርግጥ ምግብን የሚበሉ፣ በገበያዎችም የሚሄዱ ሰዎች ነበሩ፣ በተመሳሳይም ነቢያችን”ﷺ” ሰው ናቸው፣ በደረጃ እንጂ በሃልዎት ከሰው የተለዩ አልነበሩም፣ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የሆኑ መልክተኛ ነበሩ፦
36፥3 አንተ በእርግጥ *ከመልክተኞቹ ነህ*። إِنَّكَ لَمِنَ ٱلْمُرْسَلِينَ
2፥252 አንተም *በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነህ*፡፡ وَإِنَّكَ لَمِنَ ٱلْمُرْسَلِينَ
3፥144 ሙሐመድም *ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የሆነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም*፤ وَمَا مُحَمَّدٌ إِلَّا رَسُولٌۭ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ ٱلرُّسُلُ

ነቢያችን”ﷺ” በራሳቸውና በሰዎች ምን እንደሚከናወን የወደፊቱን ዐያውቁም፣ ያ ማለት ሰዎች የሚያስጠነቅቁበት ቅርብ ይሁን እሩቅ ዐያውቁም፣ ከሚወርድላቸው ግህደተ-መለኮት ውጪ ምንም ዐያውቁም፦
6፥50 «ለእናንተ የአላህ ግምጃ ቤቶች እኔ ዘንድ ናቸው አልልም፡፡ *ሩቅንም አላውቅም*፡፡ ለእናንተም እኔ መልአክ ነኝ አልልም፡፡ *ወደ እኔ የሚወርድልኝን እንጅ ሌላን አልከተልም*» በላቸው፡፡ قُل لَّآ أَقُولُ لَكُمْ عِندِى خَزَآئِنُ ٱللَّهِ وَلَآ أَعْلَمُ ٱلْغَيْبَ وَلَآ أَقُولُ لَكُمْ إِنِّى مَلَكٌ ۖ إِنْ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ ۚ قُلْ هَلْ يَسْتَوِى ٱلْأَعْمَىٰ وَٱلْبَصِيرُ ۚ أَفَلَا تَتَفَكَّرُونَ
7፥188 አላህ የሻውን በስተቀር ለራሴ ጥቅምንም፣ ጉዳትንም፣ ማምጣት አልችልም፣ *ሩቅንም የማውቅ በነበርኩ ኖሮ* ከመልካም ነገር ባበዛሁና ክፉም ነገር ባልነካኝ ነበር፤ እኔ ለሚያምኑ ሕዝቦች አስጠንቃቂና አብሳሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም”* በላቸው። قُل لَّآ أَمْلِكُ لِنَفْسِى نَفْعًۭا وَلَا ضَرًّا إِلَّا مَا شَآءَ ٱللَّهُ ۚ وَلَوْ كُنتُ أَعْلَمُ ٱلْغَيْبَ لَٱسْتَكْثَرْتُ مِنَ ٱلْخَيْرِ وَمَا مَسَّنِىَ ٱلسُّوٓءُ ۚ إِنْ أَنَا۠ إِلَّا نَذِيرٌۭ وَبَشِيرٌۭ لِّقَوْمٍۢ يُؤْمِنُونَ
21፥109 እምቢም ቢሉ በማወቅ በእኩልነት ላይ ሆነን የታዘዝኩትን አስታወቅኋችሁ፤ *የምትስፈራሩበትም ነገር ቅርብ፣ ወይም ሩቅ፣ መሆኑን ዐላውቅም*፤ በላቸው። فَإِن تَوَلَّوْا۟ فَقُلْ ءَاذَنتُكُمْ عَلَىٰ سَوَآءٍۢ ۖ وَإِنْ أَدْرِىٓ أَقَرِيبٌ أَم بَعِيدٌۭ مَّا تُوعَدُونَ
21፥111 እርሱም *ቅጣትን ማቆየት ምናልባት ለእናንተ ፈተናና እስከ ጊዜው መጣቀሚያ እንደኾነም “አላውቅም”*፤ በላቸው። وَإِنْ أَدْرِى لَعَلَّهُۥ فِتْنَةٌۭ لَّكُمْ وَمَتَٰعٌ إِلَىٰ حِينٍۢ

ወደ ነቢያችን”ﷺ” የሚወርደው ለቀደሙት መልክተኞች የሚወርደው የነበረው የአንድ አምላክ አስተምህሮት ነው፣ ከነቢያችን”ﷺ” በፊት ለነበሩት መልክተኞች የተባለው ይህ የተውሒድ ተስተምህሮት ነው ነቢያችን”ﷺ” የሚከተሉት፦
21፥108 «ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ *”አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው”* ማለት ነው፤ ታዲያ እናንተ ፍጹም “ታዛዦች” ናችሁን» *በላቸው*፡፡ قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ
18፥110 እኔም ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚወረድልኝ፦ *”አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው” ማለት ነው”*፤ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም አምልኮ አንድንም አያጋራ» *”በላቸው”*፡፡ قُلْ إِنَّمَآ أَنَا۠ بَشَرٌۭ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَمَن كَانَ يَرْجُوا۟ لِقَآءَ رَبِّهِۦ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًۭا صَٰلِحًۭا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِۦٓ أَحَدًۢا
21፥25 ከአንተ በፊትም፣ እነሆ *ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ፣ በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢሆን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም*። وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ
41፥43 ከአንተ በፊት ለነበሩት መልክተኞች *የተባለው ቢጤ* እንጅ ለአንተ ሌላ አይባልም፤ مَّا يُقَالُ لَكَ إِلَّا مَا قَدْ قِيلَ لِلرُّسُلِ مِن قَبْلِكَ ۚ إِنَّ رَبَّكَ لَذُو مَغْفِرَةٍۢ وَذُو عِقَابٍ أَلِيمٍۢ

ስለዚህ ከላይ ያለውን አንቀጽ የወረደበትም ዐውድ ስንመለከተው ነቢያችን”ﷺ” ጀነት ስለ አለመግባታቸው ምንም የሚያወራው ነገር የለም። ዐውዱ ለማስተላለፍ የፈለገውን በግድ ጠምዝዞ ይህን ለማለት ነው የፈለገው ብሎ ማጣመም ከሥነ-አፈታት ጥናት “hermeneutics” ጋር መላተም እና የደፈረሰ የተሳከረ መረዳት ነው፣ ይህ ሙግት የዐውድ ሙግት”contextual approach” ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ስኬት

ስኬት አንድ መሠረት፣ አራት ማዕዘን እና አንድ ጣሪያ አለው።

የስኬት መሠረቱ አሳብ"idea" ነው።

የስኬት ማዕዘናት አራት ሲሆኑ እነርሱም፦
1. ያንን አሳብ መፈለግ"inspiration"
2. ያንን አሳብ መውደድ"affection"
3. ለዛ አሳብ መጣር"dedication"
4. ያንን አሳብ ላይ ማተኮር"concentration"

የስኬት ጣሪያው "ግብ"goal" ነው።

አንድ ግብ ካለን ለዛ ግብ ቅድሚያ አሳብ ማመንጨት አለብንም። ያንን አሳብ በአራት ኮርነር መገንባት አለብን። ያኔ ጣሪያውን ግብ ስናገኝ ያኔ ስኬት ይባላል።

ወሒድ ዑመር
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር ሠላሳ አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 31
ዮናስ በምድረ በዳ ተጥሏል ወይስ አልተጣለም?

አልተጣለም፡- 
ሱራ 68:49 “ከጌታው የሆነ ጸጋ ባላገኘው ኖሮ፣ በምድረ በዳ ተወቃሽ ሆኖ በተጣለ ነበር።”

ተጥሏል፡- 
ሱራ 37፡145 “እርሱ በሽተኛ ሆኖ በቃይ በሌለው በባሕር ዳርቻ ላይ ጣልነውም፡፡”

መልስ
የዓሳውንም ባለቤት ዩኑስ ዓሳም ዋጠው፥ በዓሳው ሆድ ጨለማዎች ውስጥ ኾኖ አላህን፦ "ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ጥራት ይገባህ፡፡ እኔ በእርግጥ ከበዳዮቹ ነበርኩ" በማለት ተጣራ። አላህም ጥሪውን ተቀበለው፥ ከጭንቅም አዳነው፦
21፥87 *የዓሳውንም ባለቤት ተቆጥቶ በኼደ ጊዜ አስታውስ፡፡ በእርሱም ላይ ፈጽሞ የማንፈርድበት መኾናችንን ጠረጠረ፡፡ ዓሳም ዋጠው፥ በጨለማዎችም ውስጥ ኾኖ ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ጥራት ይገባህ፡፡ እኔ በእርግጥ ከበዳዮቹ ነበርኩ በማለት ተጣራ*፡፡ وَذَا النُّونِ إِذ ذَّهَبَ مُغَاضِبًا فَظَنَّ أَن لَّن نَّقْدِرَ عَلَيْهِ فَنَادَىٰ فِي الظُّلُمَاتِ أَن لَّا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنتَ سُبْحَانَكَ إِنِّي كُنتُ مِنَ الظَّالِمِينَ
21፥88 *"ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፡፡ ከጭንቅም አዳነው"*፡፡ እንደዚሁም ምእመናንን እናድናለን፡፡ فَاسْتَجَبْنَا لَهُ وَنَجَّيْنَاهُ مِنَ الْغَمِّ ۚ وَكَذَٰلِكَ نُنجِي الْمُؤْمِنِينَ

ዩኑስ ከዓሳው ሲወጣ በሽተኛ ሆኖ በቃይ በሌለው በባሕር ዳርቻ ላይ ጣለው፦
37፥145 *"እርሱ በሽተኛ ሆኖ በቃይ በሌለው በዳርቻ ላይ ጣልነውም"*፡፡ فَنَبَذْنَاهُ بِالْعَرَاءِ وَهُوَ سَقِيمٌ

ልብ አድርግ ምን ሆኖ "በሽተኛ" ሆኖ። የት ላይ ነው የተጣለው? "በባሕር ዳርቻ" አስተውል! ከጌታው የኾነ ጸጋ ባላገኘው ኖሮ በምድረ በዳ ተወቃሽ ኾኖ በተጣለ ነበር፦
68፥49 *"ከጌታው የኾነ ጸጋ ባላገኘው ኖሮ በዳርቻ ተወቃሽ ኾኖ በተጣለ ነበር"*፡፡ لَّوْلَا أَن تَدَارَكَهُ نِعْمَةٌ مِّن رَّبِّهِ لَنُبِذَ بِالْعَرَاءِ وَهُوَ مَذْمُومٌ

"ዐራ" عَرَآء ማለት "ዳርቻ" ማለት ነው። የባሕር ዳርቻ ከጌታው የኾነ ጸጋ ባላገኘው ኖሮ በሽተኛ ሳይሆን ተወቃሽ ኾኖ በተጣለ ነበር። ነገር ግን በሽተኛ ኾኖ ተጣለ። ስለዚህ ቁርኣንን ከመተቸት በፊት "በሽተኛ" እና "ተወቃሽ" የሚሉትን ሃይለ-ቃል አጥኑ። "መዝሙም" مَذْمُوم ማለት "ተወቃሽ" ማለት ሲሆን በራስ ስህተት የሚመጣ ወቀሳን ያሳያል፥ ተወቃሽነት ተውበት ካልታከለበት ያስቀጣል፦
17፥18 ቸኳይቱን ዓለም በሥራው የሚፈልግ ሰው ለእርሱ በርሷ ውስጥ የሻነውን ጸጋ ለምንሻው ሰው እናስቸኩልለታለን፡፡ *"ከዚያም ለእርሱ ገሀነምን መኖሪያ አድርገንለታል፡፡ "ተወቃሽ" ብራሪ ኾኖ ይገባታል"*፡፡ مَّن كَانَ يُرِيدُ الْعَاجِلَةَ عَجَّلْنَا لَهُ فِيهَا مَا نَشَاءُ لِمَن نُّرِيدُ ثُمَّ جَعَلْنَا لَهُ جَهَنَّمَ يَصْلَاهَا مَذْمُومًا مَّدْحُورًا

"ሠቂም" سَقِيم ማለት ግን "በሽተኛ" ማለት ሲሆን በሽታ የጤና መታወክ እንጂ የሚያስቀጣ የሚያስጠይቅ ነገር አይደለም።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር ሠላሳ ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 32
ሕፃናት ጡት እንዲጥሉ አላህ ያዘዘው ከምን ያህል ጊዜ በኋላ ነው?

ከ30 ወራት በኋላ፡- 
ሱራ 46:15 “ሰውንም በወላጆቹ በጎ መዋልን በጥብቅ አዘዝነው እናቱ በችግር ላይ ሆና አረገዘችው በችግርም ወለደችው፥ እርግዝናውና ከጡት መለያውም ሠላሳ ወር ነው።

ከሁለት ዓመት (ከ24 ወራት) በኋላ፡- 
ሱራ 31:14 “ሰውንም በወላጆቹ (በጎ እንዲያደርግ ) በጥብቅ አዘዝነው፤ እናቱ ከድካም በላይ በሆነ ድካም አረገዘችው፤ ጡት መጣያውም በሁለት ዓመት ውስጥ ነው፤ ለኔም ለወላጆችህም አመስግን በማለት (አዘዝነው)፤ መመለሻው ወደኔ ነው።”

መልስ
46፥15 ሰውንም በወላጆቹ በጎ መዋልን በጥብቅ አዘዝነው፡፡ እናቱ በችግር ላይ ኾና አረገዘችው፡፡ በችግርም ወለደችው፡፡ *"እርግዝናው እና ጡት መለያውም ሠላሳ ወር ነው"*፡፡ وَوَصَّيْنَا الْإِنسَانَ بِوَالِدَيْهِ إِحْسَانًا ۖ حَمَلَتْهُ أُمُّهُ كُرْهًا وَوَضَعَتْهُ كُرْهًا ۖ وَحَمْلُهُ وَفِصَالُهُ ثَلَاثُونَ شَهْرًا ۚ

"ሠላሳ ወር" ማለት "ሁለት ዓመት ከስድስት ወር" ነው፥ "እርግዝና" እና "ጡት መለያው" ሁለት ዑደት ነው። እርግዝና በአማካኝ ዘጠኝ ወር ሲሆን ሠላሳ ወሩ የሚቆጠረው ከእርግዝናው ሲሆን ጡት መጣያውን ለማግኘት ከሠላሳ ወር ላይ ዘጠኝ ወር መቀነስ ነው። ውጤቱ "ሃያ አንድ ወር" አሊያም አንድ ዓመት ከዘጠኝ ወር ይሆናል ማለት ነው። አንድ ዓመት ከዘጠኝ ወር ደግሞ በሁለት ዓመት ውስጥ ያለ ቁጥር ነው፦
31፥14 ሰውንም በወላጆቹ በጎ እንዲያደርግ በጥብቅ አዘዝነው፡፡ እናቱ ከድካም በላይ በሆነ ድካም አረገዘችው፡፡ *"ጡት መጣያውም በሁለት ዓመት ውስጥ ነው"*፡፡ ለእኔም ለወላጆችህም አመስግን በማለት አዘዝነው፡፡ መመለሻው ወደ እኔ ነው፡፡ وَوَصَّيْنَا الْإِنسَانَ بِوَالِدَيْهِ حَمَلَتْهُ أُمُّهُ وَهْنًا عَلَىٰ وَهْنٍ وَفِصَالُهُ فِي عَامَيْنِ أَنِ اشْكُرْ لِي وَلِوَالِدَيْكَ إِلَيَّ الْمَصِيرُ

"ፊ" ማለት فِي "ውስጥ" ማለት እንጂ "በኃላ" ማለት አይደለም። "በኃላ" የምትለዋ የሚሽነሪዎች ቅጥፈት ናት። እንደውም እናት ወተት ኖሯት ማጥባት ከቻለች ሁለት ዓመታት ሙሉውን ታጠባለች፦
2፥233 *"እናቶችም ልጆቻቸውን ሙሉ የኾኑን ሁለት ዓመታት ያጥቡ፡፡ ይህም ማጥባትን መሙላት ለሻ ሰው ነው"*፡፡ وَالْوَالِدَاتُ يُرْضِعْنَ أَوْلَادَهُنَّ حَوْلَيْنِ كَامِلَيْنِ ۖ لِمَنْ أَرَادَ أَن يُتِمَّ الرَّضَاعَةَ ۚ

"አንድ ዓመት ከዘጠኝ ወር ጡት መለያውም" የተባለው እና "ጡት መጣያውም በሁለት ዓመት ውስጥ ነው" የተባለው ትእዛዛዊ መርሕ ሳይሆን አብዛኛው ላይ ያለውን ጥቅላዊ ደንብ ነው። "ሙሉ የኾኑን ሁለት ዓመታት ያጥቡ" ግን ቀመራዊ መርሕ ነው። ይህም ማጥባትን መሙላት ለፈለገች እናት ነው።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር ሠላሳ ሦስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 33
ለጦርነት ላለመዝመት መሐመድን"ﷺ" ፈቃዱ የጠየቁት ሁሉ ተወቃሾች ናቸው ወይስ አይደሉም?

ሁሉም ተወቃሾች ናቸው፡-
9፡44-45 “እነዚያ በአላህና በመጨረሻዉ ቀን የሚያምኑት በገንዘቦቻቸዉና በነፍሶቻቸው ከመታገላቸው ለመቅረት ፈቃድን አይጠይቁህም፤ አላህም የሚፈሩትን ዐዋቂ ነው። ፈቃድን የሚጠይቁህ እነዚያ በአላህና በመጨረሻዉ ቀን የማያምኑት ልቦቻቸዉም የተጠራጠሩት ብቻ ናቸው፤ እነሱም በጥረጣሬያቸው ዉስጥ ይዋልላሉ።”

የማይወቀሱ አሉ፡-
9፡93 “የወቀሳ መንገዱ በነዚያ እነሱ ባለጸጋዎች ሆነዉ ሳሉ ለመቅረት ፈቃድ በሚጠይቁህ ሰዎች ላይ ብቻ ነዉ፣ ከቀሪዎቹ ጋር መኾናቸውን ወደዱ፤ አላህም በልቦቻቸው ላይ አተመባቸው፣ ስለዚህ እነሱ አያውቁም።”

መልስ
9፥44 *"እነዚያ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑት በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው ከመታገላቸው ለመቅረት ፈቃድን አይጠይቁህም"*፡፡ አላህም የሚፈሩትን ዐዋቂ ነው፡፡ لَا يَسْتَأْذِنُكَ الَّذِينَ يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ أَن يُجَاهِدُوا بِأَمْوَالِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ بِالْمُتَّقِينَ

በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑት ምዕመናን በገንዘቦቻቸውና በጉልበታቸው ጂሃድን ከመታገላቸው እንቅር ብለው ነቢያችንን"ﷺ" ፈቃድ አይጠይቁም። ምክንያቱም በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑ ሙዕሚን ስለሆኑ በራስ ለመታገል አቅም አላቸው ለመለገስም ገንዘብ አላቸው። ግን በራስ ለመታገል አቅም የሌላቸው ደካሞች፣ በሽተኞች እንዲሁ ገንዘብ የሌላቸው ለአላህና ለመልክተኛው ፍጹም ታዛዦች ከኾኑ ባይወጡም ወቀሳ የለባቸውም፦
8፥91 *በደካሞች ላይ በበሽተኞችም ላይ በነዚያም የሚያወጡት ገንዘብ በማያገኙት ላይ ለአላህና ለመልክተኛው ፍጹም ታዛዦች ከኾኑ ባይወጡም ኃጢኣት የለባቸውም"*፡፡ በበጎ አድራጊዎች ላይ የወቀሳ መንገድ ምንም የለባቸውም፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ لَّيْسَ عَلَى الضُّعَفَاءِ وَلَا عَلَى الْمَرْضَىٰ وَلَا عَلَى الَّذِينَ لَا يَجِدُونَ مَا يُنفِقُونَ حَرَجٌ إِذَا نَصَحُوا لِلَّهِ وَرَسُولِهِ ۚ مَا عَلَى الْمُحْسِنِينَ مِن سَبِيلٍ ۚ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

ይቀጥልና ዐውዱ የሚወቀሱት ዐቅም ኖራቸው ትግሉን ለመቅረት ነቢያችንን"ﷺ" ፈቃድ የሚጠይቁ ተጠራጣሪዎች ብቻ ነው፦
9፥93 *የወቀሳ መንገዱ በእነዚያ እነርሱ ባለጸጋዎች ኾነው ሳሉ ለመቅረት ፈቃድ በሚጠይቁህ ሰዎች ላይ ብቻ ነው፡፡ ከቀሪዎቹ ጋር መኾናቸውን ወደዱ፡፡ አላህም በልቦቻቸው ላይ አተመባቸው፤ ስለዚህ እነርሱ አያውቁም"*፡፡ إِنَّمَا السَّبِيلُ عَلَى الَّذِينَ يَسْتَأْذِنُونَكَ وَهُمْ أَغْنِيَاءُ ۚ رَضُوا بِأَن يَكُونُوا مَعَ الْخَوَالِفِ وَطَبَعَ اللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ فَهُمْ لَا يَعْلَمُونَ

"አላህም በልቦቻቸው ላይ አተመባቸው" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት። እነዚህ አላህ በልቦቻቸው ላይ ያተመባቸው ከሃድያን በዐቅም ጉዳይ ቀሪዎች ከሆኑት ደካሞች ጋር መቅረትን ፈለጉ፥ እነዚህ ነቢያችንን"ﷺ" ለመቅረት ፈቃድ የሚጠይቁት እነዚህ ዐቅም ኖሯቸው በአላህና በመጨረሻው ቀን የማያምኑት እና ልቦቻቸውም የተጠራጠሩት ናቸው፦
9፥45 *"ፈቃድን የሚጠይቁህ እነዚያ በአላህና በመጨረሻው ቀን የማያምኑት እና ልቦቻቸውም የተጠራጠሩት ብቻ ናቸው"*፡፡ እነርሱም በጥርጣሬያቸው ውስጥ ይዋልላሉ፡፡ إِنَّمَا يَسْتَأْذِنُكَ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَارْتَابَتْ قُلُوبُهُمْ فَهُمْ فِي رَيْبِهِمْ يَتَرَدَّدُونَ

"ወ" وَ ማለት "እና" ማለት ሲሆን አያያዥ መስተጻምር ነው። ይህም መስተጻምር በአላህና በመጨረሻው ቀን የማያምኑት እና ልቦቻቸውም የተጠራጠሩት ለመለየት የገባ ነው። "ልቦቻቸውም የተጠራጠሩት" በመጠራጠራቸው አላህም ልቦቻቸው ላይ ያተመባቸው ናቸው። ልቦቻቸውም የተጠራጠሩት ልባቸው ታትሟል፦
63፥3 ይህ *እነርሱ በምላስ ያመኑ ከዚያም በልብ የካዱ በመኾናቸው* ነው፡፡ *በልቦቻቸውም ላይ ታተመባቸው*፤ ስለዚህ እነርሱ አያውቁም፡፡ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ ءَامَنُوا۟ ثُمَّ كَفَرُوا۟ فَطُبِعَ عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ فَهُمْ لَا يَفْقَهُونَ
47፥16 *እነዚህ እነዚያ በልቦቻቸው ላይ አላህ ያተመባቸው ዝንባሌዎቻቸውንም የተከተሉ ናቸው*፡፡ أُو۟لَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ طَبَعَ ٱللَّهُ عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ وَٱتَّبَعُوٓا۟ أَهْوَآءَهُمْ

ስለዚህ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑት በገንዘቦቻቸውና በጉልበታቸው አቅም የሌላቸው ደካሞች፣ በሽተኞች እንዲሁ ገንዘብ የሌላቸው ለመቅረት ቢጠይቁ ወቀሳ የለባቸውም። በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑት በገንዘቦቻቸውና በጉልበታቸው አቅም ያላቸው ጂሃድ ለመቅረት አይጠይቁም። እነዚያ በአላህና በመጨረሻው ቀን የማያምኑት ባለጸጎች ሆነው በገንዘቦቻቸውና በጉልበታቸው አቅም ያላቸው ጂሃድ ለመቅረት የሚጠይቁት ይወቀሳሉ።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር ሠላሳ አራት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 34
ሙሴ ሕዝቡን ነፃ ለማውጣት በተላከ ጊዜ ያመኑለት ጥቂት ወገኖቹ ብቻ ወይንስ የግብፅ ደጋሚዎችም ጭምር?

ጥቂት እስራኤላውያን ብቻ፡-
10፡83 “ለሙሳም ከፈርዖንና ከሹማምንቶቻቸው ማሰቃየትን ከመፍራት ጋር ከወገኖቹ የኾኑ ጥቂቶች ትውልዶች እንጂ አላመኑለትም፡፡ ፈርዖንም በምድር ላይ በእርግጥ የኮራ ነበር፡፡ እርሱም በእርግጥ ወሰን ካለፉት ነበር፡፡”

የግብፅ ደጋሚዎችም ጭምር፡-
7፡120-122 “ድግምተኞችም ሰጋጆች ኾነው ወደቁ። አሉ፦ በዓለማት ጌታ አመንን፤ በሙሳና በሃሩን ጌታ።” (እንዲሁም 20፡56-73፣ 26፡29-51)

መልስ
20፥70 *"ድግምተኞቹም ሰጋጆች ኾነው ወደቁ፡፡ «በሃሩንና በሙሳ ጌታ አመንን» አሉ"*፡፡ فَأُلْقِيَ السَّحَرَةُ سُجَّدًا قَالُوا آمَنَّا بِرَبِّ هَارُونَ وَمُوسَىٰ

እዚህ አንቀጽ ላይ እያወራ ያለው ስለ ድግምተኞቹ መሆኑን ልብ ይለዋል፣ ድግምተኞቹ የሙሳ አምላክ በሰራው ታምር አምነዋል፦
26፥47 እነሱም አሉ «በዓለማት ጌታ አመንን"*፡፡ قَالُوا آمَنَّا بِرَبِّ الْعَالَمِين

እዚህ ድረስ ከተግባባን ይጋጫል የተባለውን ሁለተኛውን አንቀጽ እስቲ እንመልከት፦
10፥83 ለሙሳም ከፈርዖንና ከሹማምንቶቻቸው ማሰቃየትን ከመፍራት ጋር *"ከወገኖቹ የኾኑ ጥቂቶች ትውልዶች እንጂ አላመኑለትም"*፡፡ ፈርዖንም በምድር ላይ በእርግጥ የኮራ ነበር፡፡ እርሱም በእርግጥ ወሰን ካለፉት ነበር፡፡ فَمَا آمَنَ لِمُوسَىٰ إِلَّا ذُرِّيَّةٌ مِّن قَوْمِهِ عَلَىٰ خَوْفٍ مِّن فِرْعَوْنَ وَمَلَئِهِمْ أَن يَفْتِنَهُمْ ۚ وَإِنَّ فِرْعَوْنَ لَعَالٍ فِي الْأَرْضِ وَإِنَّهُ لَمِنَ الْمُسْرِفِينَ

"ወገኖቹ" በሚለው ቃል መነሻ ቅጥያ ላይ "ከ" የሚል መስተዋድድ ይጠቀማል። ስለዚህ ከወገኖቹ ጥቂት እንጂ አላመኑም፥ ግን ከወገኖቹ ውጪ ድግምተኞቹ በሃሩንና በሙሳ ጌታ አምነዋል። ሲቀጥል "ቀውም" قَوْم የሚለው የዐረቢኛ ቃል በአንድ አካባቢ ተመሳሳይ ባህል፣ ቋንቋ፣ አኗኗር፣ ታሪክ፣ መንግሥት እና ቦታ ያለው ማህበረሰብን ያመለክታል። ይህንን ከተረዳን ድግምተኞቹስ ከጥቂት ትውልድ መካከል የማይሆኑበት ምን ምክንያት አለው? አላህ ሙሳን ወደ ህዝቦቹ "በታምራት" እንደላከው እነዚያም ህዝቦች "ፈሮዖንና ሹማምንቶቹ" የሚጠቀልል መሆኑን ለማመልከት፦ "ወደ ፈሮዖንና ወደ ሹማምንቶቹ በእርግጥ ላክን" በማለት ይናገራል፦
14፥5 ሙሳንም *"ወገኖችህን ከጨለማዎች ወደ ብርሃን አውጣ አላህንም ቀኖች አስገንዝባቸው በማለት በተዓምራታችን በእርግጥ ላክነው"*፡፡ وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا مُوسَىٰ بِآيَاتِنَا أَنْ أَخْرِجْ قَوْمَكَ مِنَ الظُّلُمَاتِ إِلَى النُّورِ وَذَكِّرْهُم بِأَيَّامِ اللَّه
43፥46 *"ሙሳንም በተዓምራቶቻችን ወደ ፈርዖንና ወደ ሹማምንቶቹ በእርግጥ ላክን"*፡፡ «እኔ የዓለማት ጌታ መልክተኛ ነኝ» አላቸውም፡፡ وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا مُوسَىٰ بِآيَاتِنَا إِلَىٰ فِرْعَوْنَ وَمَلَئِهِ فَقَالَ إِنِّي رَسُولُ رَبِّ الْعَالَمِينَ

ከሹማምቶቹ መካከል ድግምተኞቹ የሙሳ አምላክ በሰራው ታምር አምነዋል። ሢሰልስ "ኢላ" إِلَّا የሚለው አፍራሽ ቃል “ኢስቲስናዕ” اِسْتِثْنَاء‏ ማለትም “ግድባዊት”Exceptional” ሆኖ የመጣው አንጻራዊ ሆኖ ነው፥ "ከወገኖቹ የኾኑ ጥቂቶች ትውልዶች እንጂ አላመኑለትም" ማለት "ወገኖቹ ብቻ አመኑ" የሚለውን አያሲዝም። ምክንያቱም በአንጻራዊነት ስለመጣ። ለምሳሌ፦
43፥59 እርሱ በርሱ ላይ የለገስንለት ለእስራኤለም ልጆች ተዓምር ያደረግነው የኾነ *"ባሪያ እንጅ ሌላ አይደለም"*፡፡ إِنْ هُوَ إِلَّا عَبْدٌ أَنْعَمْنَا عَلَيْهِ وَجَعَلْنَٰهُ مَثَلًۭا لِّبَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ

"ባሪያ እንጅ ሌላ አይደለም" ማለት ነቢይና መልእክተኛ አይደለም ማለትን እንደማያሲዝ ሁሉ ከላይ ያለውን ጥቅስ በዚህ ልክና መልክ መረዳት ይቻላል።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር ሠላሳ አምስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 35
ዒሳ እንደ ማንኛውም ሰው የሆነ ሰው ወይንስ የአላህ ቃልና መንፈስ ብቻ?

እንደ ማንኛውም ሰው የሆነ ሰው፡- 
5፡75 “የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የሆነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፤ እናቱም በጣም እውነተኛ ናት፤ (ሁለቱም) ምግብን የሚበሉ ነበሩ፤ አንቀጾችን ለነርሱ (ለከሐዲዎች) እንዴት እንደምናብራራ ተመልከት፤ ከዚያም (ከውነት) እንዴት እንደሚመለሱ ተመልከት።”

የአላህ ቃልና መንፈስ ብቻ፡- 
4፡171 “እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፤ በአላህም ላይ እውነትን እንጂ አትናገሩ፤ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ፣ የአላህ መልክተኛ፣ ወደ መርየም የጣላት (የሁን) ቃሉም ከርሱ የሆነ መንፈስም ብቻ ነው፤ …”

መልስ
ከላም” كَلَٰم የሚለው ተባታይ ቃል “ከለመ” كَلَّمَ ማለትም “ተናገረ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ንግግር” ማለት ነው፤ “ከሊማህ” كَلِمَة ደግሞ የከላም አንስታይ ነው፤ የከሊማህ ብዙ ቁጥር “ከሊመት” ِكَلِمَةٍ ሲሆን “ቃላት” ማለት ነው። አላህ “ሲፋቱል ከላም” صفات الكلام ማለትም “የመናገር ባህርይ” አለው፤ አምላካችን አላህ “ሙተከለም” مُتَكَلِّم ማለትም “ተናጋሪ”speaker” ነው፤ የራሱ “ከላም” كَلَٰم ማለትም “ንግግር”speech” የራሱ ባህርይ ነው፤ “ከላም” እራሱ “ሐርፍ” حَرْف ማለትም “ሆሄ” ነው።

አላህ “አል-ኻሊቅ” الخَٰلِق ማለትም “ፈጣሪ” ሲሆን ነገር ሁሉ “መኽሉቅ” مَخْلُق ነው፤ አላህ ነገርን የሚፈጥርበት ንግግሩ ደግሞ ፈጣሪም ፍጡርም ሳይሆን የራሱ ባህርይ ነው፤ አምላካችን አላህ ደግሞ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው፤ ነገር ማስገኘት በሻ ጊዜ “ኹን” ይለዋል፤ ወዲያው ይኾናልም፦
39፥62 *አላህ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው፡፡ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ
36፥82 *ነገሩም አንዳችን በሻ ጊዜ “ኹን” ማለት ነው፡፡ ወዲያው ይኾናልም*፡፡ إِنَّمَا أَمْرُهُ إِذَا أَرَادَ شَيْئًا أَن يَقُولَ لَهُ كُن فَيَكُونُ
40፥68 እርሱ ያ ሕያው የሚያደርግ የሚገድልም ነው፡፡ *አንዳችን ነገር በሻም ጊዜ ለእርሱ የሚለውን «ኹን» ነው፤ ወዲያውም ይኾናል*፡፡ هُوَ الَّذِي يُحْيِي وَيُمِيتُ ۖ فَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
16፥40 *ለማንኛውም ነገር መኾኑን በሻነው ጊዜ ቃላችን ለእርሱ “ኹን” ማለት ብቻ ነው፤ ወዲውም ይኾናል*፡፡ إِنَّمَا قَوْلُنَا لِشَيْءٍ إِذَا أَرَدْنَاهُ أَن نَّقُولَ لَهُ كُن فَيَكُونُ
“ቃላችን” የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ “ሸይዕ” شَىْء ማለት “ነገር’thing” ማለት ሲሆን “ነገር” በሚለው ቃል ውስጥ ፍጥረት ይካተታል፤ የሚፈጥበት የይኹን ቃል ግን ከነገር ውጪ የፈጣሪ ባህርይ ነው፤ ክርስቲያኖች ፈጣሪ ልጅ አለው ሲሉ አምላካችን አላህ፦ “ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው “ኹን” ነው፤ ወዲያውም ይኾናል” የሚል ምላሽ ሰጠ፦
2፥116 *አላህም ልጅ አለው አሉ፡፡ ከሚሉት ጥራት ተገባው፡፡ አይደለም በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ሁሉም ለእርሱ ታዛዦች ናቸው*፡፡ وَقَالُوا۟ ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ وَلَدًۭا ۗ سُبْحَٰنَهُۥ ۖ بَل لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۖ كُلٌّۭ لَّهُۥ قَٰنِتُونَ
2፥117 ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ *ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን» ነው፤ ወዲያውም ይኾናል*፡፡ بَدِيعُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
19፥35 *ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል*፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ለአላህ ልጅ መውለድ አያስፈልገው፤ ነገርን ማስገኘት ሲፈልግ በንግግሩ “ኹን” ይላል ይሆናል፤ መርየምም”ዐ.ሰ.”፦ “ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል?” ስትል፤ መለኮታዊ ምላሽ፦ “አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፤ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል” የሚል ምላሽ ነው፦
3፥47 *፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፤ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት*፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

አንድ ጊዜ ነጅራኖች ማለትም የየመን ክርስቲያኖች፦ “ዒሣ የአላህ ልጅ ካልሆነ እንግዲያውስ አባቱ ማን ነው? ብለው ጠየቁ፤ አምላካችን አላህም ይህንን አንቀጽ አወረደ፦
3፥59 አላህ ዘንድ *የዒሳ ምሳሌ እንደ አዳም ብጤ ነው፡፡ ከዐፈር ፈጠረው፡፡ ከዚያም ለእርሱ «ኹን» አለው፤ ኾነም*፡፡ إِنَّ مَثَلَ عِيسَىٰ عِندَ اللَّهِ كَمَثَلِ آدَمَ ۖ خَلَقَهُ مِن تُرَابٍ ثُمَّ قَالَ لَهُ كُن فَيَكُونُ

አላህ አደምን ከዐፈር ቅርጹን ካበጀ በኃላ በቃሉ “ኹን” አለው ሰው ሆነ፤ በተመሳሳይም ዒሣን ከመርየም “ኹን” አለው ሰው ሆነ፤ “ወከሊመቱሁ አልቃሃ ኢላ መርየም* وَكَلِمَتُهُ أَلْقَاهَا إِلَىٰ مَرْيَمَ ማለትም “ወደ መርየም የጣላት የይኹን ቃል ነው” የሚለው ለዛ ነው፦
4:171 እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፤ በአላህም ላይ እውነትን እንጂ አትናገሩ፤ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ፣ የአላህ መልክተኛ፣ *ወደ መርየም የጣላት የሁን ቃሉም ነው፤ ከእርሱ የሆነ መንፈስም ብቻ ነው"*። يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَا تَغْلُوا۟ فِى دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا۟ عَلَى ٱللَّهِ إِلَّا ٱلْحَقَّ ۚ إِنَّمَا ٱلْمَسِيحُ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ رَسُولُ ٱللَّهِ وَكَلِمَتُهُۥٓ أَلْقَىٰهَآ إِلَىٰ مَرْيَمَ وَرُوحٌۭ مِّنْهُ

ልብ አድርግ “ከሊመት” كَلِمَت ነው፤ ዒሣን ወንድ እንጂ ሴት አይደለም፤ “የይኹን ቃል” መንስኤ ሲሆን ዒሣ ውጤት ነው። ሲቀጥ "ብቻ" የሚለው የዐረቢኛ ቃል "ወሒድ" وَاحِد ነው፥ "ወሒድ" የሚል ቃል አንቀጹ ላይ የለም። ሢሰልስ ከአላህ የሆነው መንፈስ ነው ማለት የዒሣ መንፈስ ከአላህ የሆነ ነው ማለት ነው፥ "ሩሑ ሚንሁ" رُوحٌۭ مِّنْهُ የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት። ከመርየም አካል ሲሆን "ከእርሱ(ከአላህ) የሆነው መንፈስ ነው፥ የማንኛውም ሰው አካል ከወላጆቹ ሲሆን ሩሕ ግን ከአላህ ነው፦
17፥85 *ከሩሕም ይጠይቁሃል፡፡ «ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው* ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም» በላቸው፡፡ وَيَسْأَلُونَكَ عَنِ الرُّوحِ ۖ قُلِ الرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّي وَمَا أُوتِيتُم مِّنَ الْعِلْمِ إِلَّا قَلِيلًا

ስለዚህ ሰው የሩሕ እና የአካል ውሕደት ከሆነ የመርየም ልጅ ዒሣ ልክ እንደ እናቱ ምግብ የሚበላ ሰው ነበር፦
5፥75 *"የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ እናቱም በጣም እውነተኛ ናት፡፡ ሁለቱም ምግብን የሚበሉ ነበሩ"*፤ አንቀጾችን ለነርሱ ለከሓዲዎች እንዴት እንደምናብራራ ተመልከት ከዚያም ከእውነት እንዴት እንደሚመለሱ ተመልከት፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ وَأُمُّهُ صِدِّيقَةٌ ۖ كَانَا يَأْكُلَانِ الطَّعَامَ ۗ انظُرْ كَيْفَ نُبَيِّنُ لَهُمُ الْآيَاتِ ثُمَّ انظُرْ أَنَّىٰ يُؤْفَكُون

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር ሠላሳ ስድስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 36
የዒሳ “አፈጣጠር” እንደ አደም ከአፈር ወይንስ በልደት?

እንደ አደም፡- 
3፡59 “አላህ ዘንድ የዒሳ ምሳሌ፥ እንደ አደም ብጤ ነዉ፤ ከዐፈር ፈጠረዉ፤ ከዚያም ለርሱ (ሰዉ) ሁን አለዉ፥ ሆነም።”


በልደት፡- 
19፡22-23 “ወዲያዉኑም አረገዘችዉ፤ በርሱም በሆድዋ ይዛዉ ወደ ሩቅ ስፍራ ገለል አለች። ምጡም ወደ ዘንባባይቱ ግንድ አስጠጋት…”

መልስ
ሰው የተፈጠረው ከምድር ነው፤ “ምድር” የሚለው ቃል ተክቶ የመጣ “ሃ” ْهَا ማለትም “እርሷ” የሚል ተውላጠ-ስም አለ፤ “ሃ” በሚለው ቃል ላይ “ሚን” مِنْ ማለትም “ከ” የሚል መስተዋድድ መነሻ ቅጥያ አለ፦
20፥ 55 *ከእርሷ ከምድር ፈጠርናችሁ*፡፡ በእርሷም ውስጥ እንመልሳችኋለን፡፡ ከእርሷም በሌላ ጊዜ እናወጣችኋለን፡፡ مِنْهَا خَلَقْنَاكُمْ وَفِيهَا نُعِيدُكُمْ وَمِنْهَا نُخْرِجُكُمْ تَارَةً أُخْرَىٰ

ይህ የሚያሳየው ሰው የተፈጠረው ከምድር ነው፤ ምድር ለአካል መሰራት ግኡዝ ንጥረ-ነገር ነው፤ አላህ ምድርን ወደ እራሱ በማስጠጋት እልቅና ክብር ለመስጠት “አርዲ” أَرْضِي ማለትም “ምድሬ” በማለት በአገናዛቢ ተውላጠ-ስም ይናገራል፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! *ምድሬ* በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ እኔንም ብቻ አምልኩኝ፡፡ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّ وَاسِعَةٌ فَإِيَّايَ فَاعْبُدُونِ

ይህንን ከምድር የተፈጠረውን ሰው አላህ በሩሕ ሕያው ያደርገዋል፤ “ሩሕ” رُوح ማለትም “መንፈስ” አላህ ግኡዛን ነገሮችን ህያው የሚያደርግበት ንጥረ-ነገር ነው። አላህ ከምድር በተፈጠረው አካል ከመንፈሱ ሲነፋበት ያ ግኡዝ አካል ሕያው ሆነ፦
38፥72 *ፍጥረቱንም ባስተካከልኩ እና ከመንፈሴ በነፋሁበት ጊዜ* ለእርሱ ሰጋጆች ኾናችሁ ውደቁ» አልኩ፡፡ فَإِذَا سَوَّيْتُهُۥ وَنَفَخْتُ فِيهِ مِن رُّوحِى فَقَعُوا۟ لَهُۥ سَٰجِدِينَ

“ሩሕ” رُوح በሚለው ቃል ላይ “ሚን” مِنْ ማለትም “ከ” የሚል መነሻ ቅጥያ አለ፤ ይህ የሚያሳየው “ሩሕ” አካል ህያው የሚሆንበት ንጥረ-ነገር መሆኑን ነው፤ "ከ"ምድር "ከ"መንፈስ የሚለው ቃላት ይሰመርበት። አላህ ምድርን ወደ እራሱ በማስጠጋት እልቅና ክብር ለመስጠት “አርዲ” أَرْضِي ማለትም “ምድሬ” በማለት እንደተናገረ ሁሉ በተመሳሳይም ሩሕን ወደ እራሱ በማስጠጋት እልቅና ክብር ለመስጠት “ሩሒ” رُّوحِى ማለትም “መንፈሴ” በማለት በአገናዛቢ ተውላጠ-ስም” ተናግሯል። ምድርም መንፈስም የሰው ምንነት ነው፥ አላህ ልክ አደምን ከዐፈር ሰርቶ ከመንፈሱ አካሉ ላይ ሲነፋበት ሰው እንደሆነ ሁሉ መርየም ውስጥ ያለውን አካል ከመንፈሱ ሲነፋበት ዒሣ ሰው ሆነ፦
21፥91 ያችንም ብልቷን የጠበቀቺውን *"በእርሷም ውስጥ ከመንፈሳችን የነፋንባትን"* እርሷንም ልጅዋንም ለዓለማት ተዓምር ያደረግናትን መርየምን አስታውስ፡፡ وَالَّتِي أَحْصَنَتْ فَرْجَهَا فَنَفَخْنَا فِيهَا مِن رُّوحِنَا وَجَعَلْنَاهَا وَابْنَهَا آيَةً لِّلْعَالَمِينَ

ዐደም እና ዒሣ አፈጣጠራቸው የሚያመሳስላቸው ለዚህ ነው፦
3፥59 *”አላህ ዘንድ የዒሳ ምሳሌ እንደ አዳም ብጤ ነው፡፡ ከዐፈር ፈጠረው፡፡ ከዚያም ለእርሱ «ኹን» አለው፤ ኾነም"*፡፡ إِنَّ مَثَلَ عِيسَىٰ عِندَ ٱللَّهِ كَمَثَلِ ءَادَمَ ۖ خَلَقَهُۥ مِن تُرَابٍۢ ثُمَّ قَالَ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ

"ኸለቀ" خَلَقَ ማለትም "ፈጠረ" በሚለው ግስ መዳረሻ ቅጥያ ላይ "ሁ" هُۥ ማለት "እርሱ" የሚል ተሳቢ ተውላጠ-ስም አለ፥ ይህም የስም ምትክ "ኣደም" ءَادَم የሚለውን የተጻውዖ ስም ተክቶ የመጣ ነው። "ከአፈር" ፈጠረው የሚለው አደምን እንጂ በፍጹም ዒሣን አይደለም። አደም እና ዒሣ የተመሳሰሉበት ነጥብ የተፈጠሩበት ንጥረ-ነገር ሳይሆን የተፈጠሩበት ሁኔታ ነው፣ ሁለቱም በታምር ኹን በሚለው ቃል መፈጠራቸው ነው። አላህ ዐደምን ከዐፈር ፈጥሮ ኹን እንዳለው እንደሆነ ሁሉ ዒሣን ከመርየም ኹን በማለት ፈጥሮታል፦
3፥47 *፡-ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስኾን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል? አለች፡፡ ነገሩ እንዳልሽው ነው፡፡ አላህ የሚሻውን ይፈጥራል፤ አንዳችን በሻ ጊዜ ለእርሱ ኹን ይለዋል፤ ወዲውኑም ይኾናል አላት*፡፡ قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِي وَلَدٌ وَلَمْ يَمْسَسْنِي بَشَرٌ ۖ قَالَ كَذَٰلِكِ اللَّهُ يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
በግ በግን ከወለደ ሁለት በጎች ናቸው እንጂ ሁለቱ አንድ በግ አይባሉም፥ ሰው ሰውን ከወለደ ሁለት ሰዎች ናቸው እንጂ ሁለቱ አንድ ሰው አይባሉም፥ አምላክ አምላክን ወለደ ከተባለ ሁለት አምላክ ናቸው ማለት ነው እንጂ ሁለቱም አንድ አምላክ አይባሉም።
ግን በኢሥላም አላህ አንድ ነው። አልወለደም፤ አልተወለደምም፦
112፥3 *አልወለደም፤ አልተወለደምም*፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር ሠላሳ ሰባት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 37
ዒሳ ፈጣሪ ነው ወይስ አይደለም?

ፈጣሪ ነው፡- 
“ወደ እሥራኤልም ልጆች መልክተኛ የደርገዋል፤ (ይላልም) ፡-እኔ ከጌታዬ ዘንድ በታምር መጣኋችሁ። እኔ ለናንተ ከጭቃ አንደ ወፍ ቅርጽ እፈጥራለሁ፤ በርሱም እተነፍስበታለሁ፤ በአላህም ፈቃድ ወፍ ይሆናል።” (ሱራ 3፡49)

አይደለም፡- 
በሌሎች የቁርአን ክፍሎች ግን የኢየሱስ ፈጣሪነት ተክዷል፡፡ ይህም ግልፅ ግጭት ነው፡፡

መልስ
3፥49 ወደ እስራኤልም ልጆች መልክተኛ ያደርገዋል፡፡ ይላልም፡- *«እኔ ከጌታዬ በተዓምር ወደ እናንተ መጣሁ፡፡ እኔ ለናንተ ከጭቃ እንደ ወፍ ቅርፅ እፈጥራለሁ፡፡ በርሱም እተነፍስበታለሁ፡፡ በአላህም ፈቃድ ወፍ ይኾናል፡፡ በአላህም ፈቃድ ዕውር ኾኖ የተወለደን፣ ለምጸኛንም አድናለሁ፡፡ ሙታንንም አስነሳለሁ፡፡ የምትበሉትንና በቤታችሁ የምታደልቡትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፡፡ የምታምኑ እንደኾናችሁ ለእናንተ በዚህ ውስጥ በእርግጥ ተዓምር አለበት»* وَرَسُولًا إِلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنِّي قَدْ جِئْتُكُم بِآيَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ ۖ أَنِّي أَخْلُقُ لَكُم مِّنَ الطِّينِ كَهَيْئَةِ الطَّيْرِ فَأَنفُخُ فِيهِ فَيَكُونُ طَيْرًا بِإِذْنِ اللَّهِ ۖ وَأُبْرِئُ الْأَكْمَهَ وَالْأَبْرَصَ وَأُحْيِي الْمَوْتَىٰ بِإِذْنِ اللَّهِ ۖ وَأُنَبِّئُكُم بِمَا تَأْكُلُونَ وَمَا تَدَّخِرُونَ فِي بُيُوتِكُمْ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

”እኔ ከጌታዬ ዘንድ በታምር” መጣኋችሁ" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት። ይህ የሚያሳየው ከዛ በኃላ የሚያደርጋቸው ሥራዎች ለነብይነቱ ማስረጃ ነው። ሙሳም በተመሳሳይ ከጌታችሁ በተዓምር በእርግጥ መጣኋችሁ ብሏል፦
7፥105 በአላህ ላይ ከእውነት በቀር አለመናገር ተገቢዬ ነው፡፡ *"ከጌታችሁ በተዓምር በእርግጥ መጣኋችሁ"*፡፡ የእስራኤልንም ልጆች ከእኔ ጋር ልቀቅ፡፡ حَقِيقٌ عَلَىٰ أَن لَّا أَقُولَ عَلَى اللَّهِ إِلَّا الْحَقَّ ۚ قَدْ جِئْتُكُم بِبَيِّنَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ فَأَرْسِلْ مَعِيَ بَنِي إِسْرَائِيلَ

ሙሳ በምን አይነት ታምር ነው የመጣው? ስንል ማንኛው ሰው ሊፈጥረውን የሚችለውን ቅርፅ ሳይሆን ለደረቅ እንጨት ህይወት መስጠት የሚያስችል ታምር ነው፦
7፥106 ፈርዖንም *«በተዓምር የመጣህ እንደኾንክ ከውነተኞቹ ከኾንክ እርሷን አምጣት»* አለው፡፡ قَالَ إِن كُنتَ جِئْتَ بِآيَةٍ فَأْتِ بِهَا إِن كُنتَ مِنَ الصَّادِقِينَ
7፥107 *"በትሩንም ጣለ፡፡ እርስዋም ወዲያውኑ ግልጽ እባብ ኾነች"*፡፡ فَأَلْقَىٰ عَصَاهُ فَإِذَا هِيَ ثُعْبَانٌ مُّبِينٌ

ታዲያ የቱ ታምር ይበልጣል? የወፍ ቅርፅ መስራት ወይስ በትር እባብ ማድረግ? እባብም ሆነ ወፍ እንስሳ ናቸው፤ ልዩነቱ በትሩን እባብ ያደረገው ሆነ የጭቃውን ቅርፅ ወፍ ያደረገው አላህ ነው። ለሙሳ ነብይነት ሆነ ለኢየሱስ ነብይነት የተሰጣቸው ታምር ከራሳቸው ያገኙት ሳይሆን ከአላህ የተሰጣቸው ፀጋ ነው።
ሲቀጥል “ከሀይዓህ” كَهَيْئَﺔ ማለት “ቅርጽ” ማለት ነው፣ ጥቅሱ ላይ ዒሣ ወፍ ፈጠረ አይልም፤ “የወፍ ቅርጽ” ማለትና “ወፍ” ማለት በይዘትም ሆነ በአይነት፣ በመንስኤም ሆነ በውጤት ሁለት የተለያዩ ቃላት ናቸው። ምነው የወፍ ቅርጽ መስራትና መፍጠር ፈጣሪ የሚያሰኝ ከሆነማ ዛሬ የሰው ቅርጽ የሚፈጥሩ ሞልተው የለ እንዴ? በመርካቶ ገበያ መዞሩ በቂ ነው።
ሢሰልስ “አኹሉቁ” أَخْلُقُ ማለት “አበጃለውም” ይሆናል፤ በዐማርኛ እንኳን እከሌ “የመፍጠር ችሎታው ይገርማል” ስንል መቼም አላህ ነው እያልን አይደለም፤ ዐረቢኛ ሰፊ ቋንቋ ነው “ኸልቅ” خَلْق ማለትም “መፍጠር” የሚለው ቃል “ተስዊር” تصویر ማለትም "መቅረጽ" በሚል እንደሚመጣ ዐታውቁምን? “ኸለቀ” خَلَقَ የሚለው ቃል “ሰወረ” صَوَّر ማለትም “ቀረጸ” በሚል የመጣበት ሰዋስው እንመልከት፦
37፥125 በዕልን ትገዛላችሁን? *"ከሰዓሊዎቹ ሁሉ ይበልጥ በጣም አሳማሪ የሆነውንም አምላክ ትተዋላችሁን?"* أَتَدْعُونَ بَعْلًا وَتَذَرُونَ أَحْسَنَ الْخَالِقِينَ
23፥14 *"ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ"*፡፡ فَتَبَارَكَ اللَّهُ أَحْسَنُ الْخَالِقِين

አየህ “ሰዓሊ” የሚለው ቃል “ኻሊቅ” خَٰلِق ሲሆን የብዙ ቁጥሩ ደግሞ “ኻሊቂን” خَالِقِين ማለትም “ሰዓሊዎች” ነው። ታዲያ “ኻሊቂን” ካለመኖር ወደ መኖር ህይወትን መስጠት ማለት ነውን? በፍጹም ቅርጽ መፍጠር ማለት ነው እንጂ ፤ “ኻሊቅ” خَٰلِق የሚለው ቃል “ሙሰዊር” مُصَوِّر ማለትም “ቅርፅን ቀራጺ” በሚል መጥቷል፤ ስለዚህ ስዕል የሚያበጁና የሚቀርፁ ሰዎችን ፈጠሩ ካላቸው ዒሣን የወፍ ቅርጽ ፈጠረ ወይም አበጀ ቢለው ምን ያስደንቃል? አላህ በትንሳኤ ቀን ለሸርና ለሺርክ አገልግሎት ስዕል የሳሉትንና ቅርፅ የቀረጹትን ሰዎች እንዲህ ይጠይቃቸዋል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 67 ሐዲስ 116
ዓኢሻህ እንደተረከችው፦ "የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ *“የምስል ባለቤቶች በትንሳኤ ቀን ይቀጣሉ፤ *የፈጠራችሁን” ህያው አድርጉት ይባላሉ"*። فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ أَصْحَابَ هَذِهِ الصُّوَرِ يُعَذَّبُونَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ، وَيُقَالُ لَهُمْ أَحْيُوا مَا خَلَقْتُمْ ‏”‌‏
“የፈጠራችሁትን” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ኸለቅቱም” خَلَقْتُمْ ሲሆን “ኸለቀ” خَلَقَ ከሚል ግን የመጣ እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። አላህ “የፈጠራችሁትን” ሕይወት ስጡት ብሎ ይጠይቃቸዋል፤ አየህ ሕይወት መስጠቱ ነው ቁም ነገሩ እንጂ መቅረጻቸው አይደለም። መቅረጻቸውንማ “የፈጠራችሁትን” በማለት እንደፈጠሩት ያሳያል። እንዲሁ ጥቅሱ ላይ ዒሣ የወፍ ቅርጽ ፈጠረ ማለት አበጀ እንጂ ወፍ አላደረገም አልፈጠረም። እሩቅ ሳንሄድ በክርስትና የምድረ-በዳ አበው የሚባሉት ምንኩስናን ፈጥረዋል፦
57፥27 ከዚያም በዱካዎቻቸው ላይ መልክተኞቻችንን አስከታተልን፡፡ የመርየምን ልጅ ዒሳንም አስከተልን፡፡ ኢንጂልንም ሰጠነው፡፡ በእነዚያም በተከተሉት ልቦች ውሰጥ መለዘብን እና እዝነትን አደረግን፡፡ በእነርሱ ላይ አዲስ *"የፈጠሩዋትንም" ምንኩስና አልጻፍናትም፡፡ ግን የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ ፈጠሩዋት"*፡፡ ተገቢ አጠባበቋንም፤ አልጠበቋትም፡፡ ከእነርሱም ለእነዚያ ላመኑት ምንዳቸውን ሰጠናቸው፡፡ ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፡፡ ثُمَّ قَفَّيْنَا عَلَىٰ آثَارِهِم بِرُسُلِنَا وَقَفَّيْنَا بِعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ وَآتَيْنَاهُ الْإِنجِيلَ وَجَعَلْنَا فِي قُلُوبِ الَّذِينَ اتَّبَعُوهُ رَأْفَةً وَرَحْمَةً وَرَهْبَانِيَّةً ابْتَدَعُوهَا مَا كَتَبْنَاهَا عَلَيْهِمْ إِلَّا ابْتِغَاءَ رِضْوَانِ اللَّهِ فَمَا رَعَوْهَا حَقَّ رِعَايَتِهَا ۖ فَآتَيْنَا الَّذِينَ آمَنُوا مِنْهُمْ أَجْرَهُمْ ۖ وَكَثِيرٌ مِّنْهُمْ فَاسِقُونَ

"የፈጠሩዋትንም" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት። እውን የምድረ-በዳ አበው ፈጣሪ ናቸውን? “ኸልቅ” ጠቢባን ለሚጠበቡት ፈጠራ “ተስዊር” ሲሆን አላህ ለፈጠረበት ግን “ፊጥራህ” فِطْرَت ነው። አላህ “ፋጢር” فَاطِر ነው፤ ይህ በስም መደብ "ፋጢር" ሲሆን በግስ መደብ ደግሞ “ፈጠረ” فَطَرَ ነው፤ ይህ ቃል ለፍጡራን አግልግሎት ላይ የዋለበት ጥቅስ የለም፦
6፥14 «ሰማያትንና ምድርን *ፈጣሪ* ከኾነው አላህ እርሱ የሚመግብ የማይመገብም ሲኾን ሌላን አምላክ እይዛለሁን» በላቸው፡፡ قُلْ أَغَيْرَ اللَّهِ أَتَّخِذُ وَلِيًّا فَاطِرِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَهُوَ يُطْعِمُ وَلَا يُطْعَمُ

ሲያረብብ “ቢኢዝኒሏህ” بِإِذْنِ اللَّه ማለት "በአላህ ፈቃድ" ማለት ሲሆን ዒሣ ያበጀውንና እፍ ያለበትን የወፍ ቅርጽ አላህ ነው በፈቃዱ ወፍ ያረገው እንጂ ዒሣ ወፍ አደረገ አሊያም ፈጠረ የሚል የለም። የወፍ ቅርጽ መፍጠር ሁሉም ሰው የጭቃ ንጥረ-ነገር ከተሰጠው ይፈጥራል እፍ ብሎም እላዩ ላይ መተንፈስ ይችላል። ቁም ነገሩ ግን ሰዎች የፈጠሩትን ቅርጽ እና እፍ ያሉበትን ጭቃ አላህ ህይወት አይሰጥም። ነገር ግን ለዒሣ ነብይነት ማረጋገጫ አላህ በራሱ ፈቃድ ዒሣ የሰራውን የወፍ ቅርጽ ወፍ አድርጎታል። ሙግቱ የስነ-ቋንቋና የዐውድ ሙግት ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው።

ከላይ የቀረቡትን የቁርኣን የቋንቋ ሙግት ነጥቦች አልገባህ ካላችሁ በቀላሉ ለማስረዳት ከራሳችሁ ባይብል አንድ የቋንቋ ሙግት ለናሙና እንይ፦
ኤርምያስ 10፥16 የያዕቆብ እድል ፈንታ እንደ እነዚህ አይደለም፤ እርሱ የሁሉ *”ፈጣሪ”* יוֹצֵ֤ר ነውና፤ እስራኤልም የርስቱ ነገድ ነውና፤ ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።
ኤርምያስ 51፥19 የያዕቆብ እድል ፈንታ እንደ እነዚህ አይደለም፥ እርሱ የሁሉ *”ፈጣሪ”* יוֹצֵ֤ר ነውና፤ እስራኤልም የርስቱ ነገድ ነው፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።

እነዚህ አናቅጽ ላይ “ፈጣሪ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል በዕብራይስጡ “ዮውሰር” יוֹצֵ֤ר ሲሆን ትርጉሙ “ፈጣሪ” ወይም “ሠሪ” ሲሆን ለሰዎች ቃሉ ውሏል፦
መዝሙር 2፥9 በብረት በትር ትጠብቃቸዋለህ፥ እንደ ሸክላ *”ሠሪ”* יוֹצֵ֣ר ዕቃዎች ትቀጠቅጣቸዋለህ።
ኢሳይያስ 41፥25 አንዱን ከሰሜን አነሣሁ መጥቶአልም፤ አንዱም ከፀሐይ መውጫ ስሜን የሚጠራ ይመጣል፤ በጭቃ ላይ እንደሚመጣ ሰው አፈርም እንደሚረግጥ *”ሸክለኛ”* יוֹצֵ֣ר በአለቆች ላይ ይመጣል።
ኤርምያስ 19፥1 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ ሂድ፥ ከሸክላ *”ሠሪ”* יוֹצֵ֣ר ገምቦ ግዛ፥ ከሕዝቡም ሽማግሌዎችና ከካህናት ሽማግሌዎች ከአንተ ጋር ውሰድ፤
ሰቆቃው ኤርምያስ 4፥2 ቤት። ጥሩ ወርቅ የሚመስሉ የከበሩ የጽዮን ልጆች፥ የሸክላ *”ሠሪ”* יוֹצֵ֣ר እጅ እንደ ሠራው እንደ ሸክላ ዕቃ እንዴት ተቈጠሩ!

እና ሸክላ ሰሪ ሸክለኛ ሁሉ ፈጣሪዎች ናቸውን? አይ ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው ሃሳብንና ዓረፍተ-ነገር ይወስነዋል ከሆነ መልሱ እንግዲያውስ ከላይ ያለውንም የቁርኣን ቃል በዚህ ቀመርና ስሌት ተረዱት፤ በሰፈሩት ቁና መሰፈር ይሉሃል እንደዚህ ነው።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር ሠላሳ ስምንት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 38
ኢብሊስ መልአክ ወይንስ ጂን?

መልአክ-
2:34 “ለመላእክትም «ለአደም ስገዱ» ባልን ጊዜ አስታውስ፡፡ ሁሉም ወዲያውኑ ሰገዱ፤ ኢብሊስ ብቻ ሲቀር እምቢ አለ፤ ኮራም ከከሓዲዎቹም ኾነ፡፡”

ጂን- 18:50 “ለመላእክትም ለአደም ስገዱ፥ ባልናቸው ጊዜ የሆነውን አስታውስ። ወዲያውም ሰገዱ፤ ኢብሊስ ብቻ ሲቀር፤ ከጋኔን ነበር፤…”

መልስ
“ጂን” جِنّ የሚለው ቃል “ጀንነ” جَنَّ ማለትም “ተሰወረ” ወይም “ተደበቀ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ስውር” ወይም “ድብቅ” ማለት ነው፤ “ጅኒ” جني ደግሞ የጂን ብዙ ቁጥር ነው፤ ጂኒዎች የተፈጠሩት ከሰው በፊት ነው፤ ሰው የተፈጠረበት ንጥረ-ነገር ዐፈር እንደሆነ፤ መልአክ የተፈጠረበት ንጥረ-ነገር ብርሃን እንደሆነ ሁሉ ጂን የተፈጠረበት ንጥረ-ነገር ደግሞ እሳት ነው፦
15፥27 *ጃንንም ከሰው በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው*፡፡ وَالْجَانَّ خَلَقْنَاهُ مِن قَبْلُ مِن نَّارِ السَّمُومِ
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 55, ሐዲስ 78
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”መላእክት ከብርሃን ተፈጥረዋል፤ ጂንዎች ከእሳት ነበልባል ተፈጥረዋል፤ አደም ለእናንተ እንደተገለጸላችሁ ከሚጭለቀለቅ ሸክላ ተፈጥሯል”*፡፡ عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم‏ خُلِقَتِ الْمَلاَئِكَةُ مِنْ نُورٍ وَخُلِقَ الْجَانُّ مِنْ مَارِجٍ مِنْ نَارٍ وَخُلِقَ آدَمُ مِمَّا وُصِفَ لَكُمْ ‏.‏

ጂኒዎች የተፈጠሩበት አላማ የፈጠራቸው አላህ እንዲያመልኩ ነው፦
51፥56 *ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም*፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

“ኢብሊሥ” إِبْلِيس በተፈጥሮው ከሰው ወይም ከመልአክ ሳይሆን ከጂን ሲሆን በመጥፎ ባህርይው ደግሞ “ሸይጧን” ነው፤ ለአደም አልሰግድም ብሎ በአላህ ላይ ያመጸው እርሱ ነው፦
18፥50 ለመላእክትም ለአደም ስገዱ፥ ባልናቸው ጊዜ የሆነውን አስታውስ ። ወዲያውም ሰገዱ፤ *ኢብሊስ ብቻ ሲቀር ከጂን ነበር፤ ከጌታውም ትእዛዝ ወጣ"*፡፡ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ كَانَ مِنَ الْجِنِّ فَفَسَقَ عَنْ أَمْرِ رَبِّهِ