ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ነጥብ ሁለት
“ነሥኽ”
“ነሥኽ” نسخ ማለት “ሽረት”abrogation” ማለት ሲሆን ይህም ሽረት በሁለት እሳቤዎች አቅፏል፤ እነርሱም፦
1ኛ. “ናሢኽ” الناسخ ማለትም “ሻሪ”Abrogator” ሲሆን ይህ አንቀፅ ሻሪ አንቀፅ ይባላል።
2ኛ. “መንሡኽ” المنسوخ “ተሻሪ”Abrogated” ነው፤ ይህ አንቀጽ ተሻሪ አንቀፅ ይባላል።
“ሽረት” ህጉን ታሳቢና ዋቢ ያረደገ ሲሆን የማህበረሰቡትን ዕድገትና የአስተሳሰብ ደረጃ፣ የጊዜውን ቅድመ-ተከተል እና ዘመነ-መግቦት”dispensation” ያማከለ ነው፣ ይህም “ተከታታይ ግህደተ-መለኮት”progressive revelation” እሴትና ግብአት ነው፦
2:106 #ከአንቀጽ #ብንለውጥ نَنْسَخْ ወይም እርሷን ብናስረሳህ ከርሷ የሚበልጥን ወይም ብጤዋን #እናመጣለን#አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ #ቻይ #መኾኑን አታውቅምን?፡፡
16:101 #በአንቀጽም #ስፍራ #አንቀጽን #በለውጥን ጊዜ፣ አላህም #የሚያወርደውን ነገር አዋቂ ነው፤ አንተ ቀጣፊ እንጂ ሌላ አይደለህም ይላሉ፤ በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም።

አላህ የሕጉን አንቀጽ በሌላ የህግ አንቀጽ የመሻሩ ሂደት በሁለት ይከፈላል፤ እርሱም፦
1ኛ. “ሁክሙ” ማለትም “ህጉ” ተነሥኾ ነገር ግን “መትኑ” ማለትም “የህጉ ጥሬ ቃል” የማይነሠኸው ሲሆን የተነሠኸው እና የነሠኸው አያህ ቁርአን ውስጥ ሰፍሮ ይገኛል።
2ኛ. ሁክሙ ተነሥኾ በተጨማሪም መትኑ ተነሥኾ፤ የነሠኸው አያህ ቁርአን ውስጥ ሰፍሮ፤ ነገር ግን የተነሠኸው አያህ ሁክሙና መትኑ የማይገኝ ሲሆን የተነሠኸው አያህ በማስረሳት በሌላ አያህ መተካት ነው፦
87:6-7 ቁርአንን በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ #አትረሳምምአላህ #ከሻዉ #በስተቀር
2:106 ከአንቀጽ ብንለውጥ ወይም እርሷን #ብናስረሳህ ከእርሷ የሚበልጥን ወይም ብጤዋን እናመጣለን፤

ስለዚህ ሁለት የተለያዩ ነጥቦችን አምጥቶ ይጋጫሉ ማለት የሥነ-አመክንዮ ተፋልሶ ነው። መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም