ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ልከክልህ እከክልኝ

ቁጥር ስምንት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ጥያቄ 8
የአላህ ቃል ይለወጣል ወይስ አይለወጥም?

ይለወጣል፡–
ሱራ 2፡106 “ከአንቀፅ ብንለውጥ ወይም እርሷን ብናስረሳህ ከርሷ የሚበልጥን ወይም ቢጤዋን እናመጣለን፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ከሃሊ (ቻይ) መሆኑን አታውቅምን?”

አይለወጥም፡-
ሱራ 18፡27 “ለቃላቱ ለዋጭ የላቸውም፡፡”

መልስ
የባይብል ሃያሲ በሃያሲያነ-ፅሑፍ”textual criticism” ላይ ባይብልን ሂስ ሲሰጡ ውጤቱ አይን ያስፈጠጠ ጥርስ ያስገጠጠ ግጭትና ፍጭት መሆኑ ብዙዎች ወደ ኢስላም እንዲመጡ ምክንያት ሆኗል፤ የሚሽነሪ ነውጠኞች ሰዎች ከክርስትና አካውንት ወደ ኢስላም አካውንት ሲጎፉ ሲያዩ በእልህ መሳ ለመሳ ቁርአን ላይ ግጭት ለማግኘት ያልቆፈረሩት ጉድጓድ ያልፈነቀለሉት ድንጋይ የለም፤ ይህ አልበቃ ሲላቸው የግለሰቦችን ስም ማንጓጠጥ ስራዬ ብለው ተያይዘውታል፤ በዚህ መሃል ግን ቁርአን ላይ የሚያነሱት ሂስ ተፋልሶ”Fallacy” ቢሆንም ለጊዜው እንደ እኔ አይነቱ ላይ ብዥታ መፍጠሩ አይቀሬ ነው፤ ይህንን ስሑት ሙግት ገለባ መሆኑን በስሙር ሙግት ማሳየት የሁላችንም ተቀዳሚ አላማ ሊሆን ይገባል፤ ለዚህም የተንሸዋረረ እይታ ምንጨታዊ ሥነ-አመክንዮ”deductive logic” በመጠቀም ሙግቴን እጀምራለው፤ አላህ ቃሉን ይለውጣል ወይስ አይለውጥም የሚለው ሂስ ከመነሻው በቋንቋ ሙግት ድባቅ ይገባል፤ ይህንን ለመረዳት ሁለት የሙግት ነጥቦች”premises” ተጠቅሜአለው፦

ነጥብ አንድ
“ተብዲል”
“ተብዲል” تَبْدِيل ማለት ደግሞ “ማስቀየር” ነው፤ ተብዲል የንግግርን ሃሳብ፣ የውሳኔ ቃል እና የተስፋ ቃል ማስቀየርን ያመለክታል፤ አላህ የተናገረውን የውሳኔ ቃል አሊያም የትንቢትና የተስፋ ቃል ማንም ማስቆም አሊያም ማስቀረት እንደማይችል አላህ በቃሉ ይናገራል፦
6:115 “”የጌታህም ቃላት እውነተኛና ትክክለኛ ስትኾን “ተፈጸመች”፡፡ ለቃላቱ #ለዋጭ የለም” لَا مُبَدِّلَ፡፡ እርሱም ሰሚው ዐዋቂው ነው፡፡
10:64 ለእነሱ በቅርቢቱ ሕይወትም በመጨረሻይቱም “ብስራት” አላቸው፤ “”የአላህ ቃላት “#መለወጥ የላትም*لَا تَبْدِيلَ ፤ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው፡፡
6:34 ከበፊትህም መልክተኞች በእርግጥ ተስተባበሉ፡፡ በተስተባበሉበትም ነገርና በተሰቃዩት ላይ እርዳታችን እስከመጣላቸው ድረስ ታገሱ፡፡ “”የአላህንም ንግግሮች *#ለዋጭ የለም*وَلَا مُبَدَِّ፡፡
18:27 ከጌታህም መጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፤ “ለቃላቶቹ #ለዋጭ የላቸውም” لَا مُبَدِّلَ፤

በተለይ “ተፈጸመች” እና “ብስራት” የሚሉት ቃላት የሚበሰርን እና የሚፈጸም ቃልን እንጂ በቀድሞ መጽሐፍት የተናገረውን መልእክት አያመለክትም፣ ኢማም ጦበራኒ ለሱረቱል አንአም 6፡115 የሰጡት ማብራሪያ እንዲህ ይላል፦
‹‹ለቃላቱ ለዋጭ የለም የሚለው ቃል አላህ በእርሱ መጽሀፍ ውስጥ ጉዳዩ ይከሰታል ብሎ ለመተግበሩ የሰጠው ቃል በጊዜው ከመተግበር ማንም አያግደውም እሱ እነደተናገረው ይፈጸማል ማለት ነው››
ኢማም ቁርጡቢም ተመሳሳይ ሀሳብ ያዘለ ማብራሪያቸውን እንዲህ ሲሉ ይገልጻል፦
‹‹ አልራሚኒ እንዳስተላለፉት አቡ ቀታዳ እንዲህ ይላሉ፡-ለኣላህ ፍርድ ምንም ለዋጭ የለውም የመጽሀፉ ሰዎች እንዳደረጉት ቃላቱን አንድ ሰው እንኳ ቢቀይረው የአላህ እውነተኛ ቃል ግን ከመፈጸም ወደ ኋላ አይልም የተለወጠው ቃል የሚፈጸመውን ቃል መለወጥ አይችልም፡፡››

ግራም ነፈሰ ቀኝ ሲጀመር “መለወጥ” የሚለው ቃል ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ ሀሳብና ትርጉም አለው ማለት አይደለም፤ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጒም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው፤ ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው ሐሳብ መታየት ያለበት።
ሲቀጥል “መለወጥ” የሚለው ንግግርን ማስቀየር “ተብዲል” መሆኑን እንጂ “ነሥኽ” እንዳልሆነ አይተናል።
ሲሰልስ ” መለወጥ” “ነሥኽ” ነው ተብሎ ቢባል እንኳን አላህ ሁሉን ቻይ ስለሆነ ቃሉን በሌላ ቃል መለወጥ ይችላል፤ ፍጡሮቹ ግን ወደ ነብያችን የወረደውን ቃል መለወጥ አይችሉም፤ ምክንያቱም “ሙበዲል” مُبَدِّل “ለዋጭ” የሚለው ቃል ከአላህ ውጪ የሆኑትን ማንነቶች እና ምንነቶች የሚያሳይ ስለሆነ፤ እንደዛ ከሆነ የሚቀጥለውን የሙግት ነጥብ እንመልከት፦