ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
Photo
♨️♨️♨️ የምስራች ♨️♨️♨️

ይህ የኡስታዝ ወሒድ መጽሐፍ የሚሽነሪዎችን ጽርፈት በጥሩ ሁኔታ የሚፈትሽ እና መልስ የሚሰጥ ነው። ሙግቱ የስማ በለው ሳይሆን የቁርኣንን ታሪካዊ ዳራ በመረጃና በማስረጃ በመጥቀስ ተገቢ መልስ ሰቶበታል። ሚሽነሪዎች ዐላዋቂዎችን በመዋዕለ ንዋይ እየበዘበዙ ቢሆንም ይህ መጽሐፍ ግን ዝምታ ፍርሓት የመሰለበትን ሁኔታ የሚያንኮታኩት ሆኖ አግኝተነዋል።

በገበያ ላይ ውሏል፤ እንዳያመልጥዎ አሁኑኑ ይግዙት በአዲስ አበባ በየትኛውም የመጽሐፍት መደብር በተለይ በነጃሺ የመጽሐፍት መደብር እና በአት-ተውባህ የመጽሐፍት መደብር ላይ ያገኙታል።
በርዘኽ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

23፥100 *ከስተፊታቸውም እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ ግርዶ አለ*፡፡ ۖ وَمِن وَرَائِهِم بَرْزَخٌ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ

ሞት በመጣ ጊዜ “ሙንከር” مُنْكَر እና “ነኪር” نَّكِير የተባሉት ሁለት መላእክት ለሟቹ በሩሑ፦ “ጌታህ ማን ነው? ዲንህ ምንድን ነው? ነቢይህ ማን ነው?” ብለው በቀብር ውስጥ ይጠይቃሉ፤ አማኝም ከሆነ፦ “ጌታዬ አላህ ነው፣ ዲኔ ኢስላም ነው፣ ነብዬም የአላህ መልእክተኛ ነው” ብሎ ይመልሳል፤ ለእርሱ ጀነት እዲገባ ይከፈትለታል። ከሃዲ ከሆነ፦ “ዐላውቅም፣ ዐላውቅም፣ ዐላውቅም” ብሎ ይመልሳል፤ ለእርሱ እሳት እዲገባ ይከፈትለታል። አቢ ዳውድ እና ተርሚዚ ዘግበውታል፤ ሐዲሱ እረጅም ስለሆነ ገብተው ያንብቡ፦
ሱነን አቢ ዳውድ: መጽሐፍ 42, ሐዲስ 158
ጃምዒ አት-ተርሚዚ: መጽሐፍ 10, ሐዲስ 107

“በርዘኽ” برزخ ማለት የቃሉ ትርጉም “ጋራጅ” ወይም “ግርዶ” ማለት ነው፤ ጥቁር ባሕር፣ አትላንቲ ውቂያኖስ፣ ባልቲክ ባሕር፣ ፓስፊክ ውቂያኖስ፣ ሜድትራኒያን ባሕር፣ ኢንዲያን ውቂያኖስ፣ ቀይ ባሕር በውስጣቸው መራራ ውኃ እና ጣፋጭ ውኃ ይዘዋል፤ እነዚህ ሁለቱ ባሕሮች እንዳይገናኙ በመካከላቸው “በርዘኽ” አለ፦
55፥19 *ሁለቱን ባሕሮች የሚገናኙ ሲኾኑ ለቀቃቸው*፡፡ مَرَجَ الْبَحْرَيْنِ يَلْتَقِيَانِ
55፥20 *እንዳይገናኙ በመካከላቸው “ጋራጅ” አለ፡፡ አንዱ ባንዱ ላይ ወሰን አያልፉም*፡፡ بَيْنَهُمَا بَرْزَخٌ لَّا يَبْغِيَانِ
25፥53 *እርሱም ያ ሁለቱን ባሕሮች፣ አጐራብቶ የለቀቀ ነው፤ ይህ ጥምን የሚቆርጥ ጣፋጭ ነው፤ ይህም የሚመረግግ ጨው ነው፤ በመካከላቸውም ከመቀላቀል መለያንና የተከለለን “ግርዶ” ያደረገ ነው*። وَهُوَ ٱلَّذِى مَرَجَ ٱلْبَحْرَيْنِ هَٰذَا عَذْبٌۭ فُرَاتٌۭ وَهَٰذَا مِلْحٌ أُجَاجٌۭ وَجَعَلَ بَيْنَهُمَا بَرْزَخًۭا وَحِجْرًۭا مَّحْجُورًۭا
27፥61 *በሁለቱ ባሕሮችም በጣፋጩና በጨው ባሕር መካከል “ግርዶን” ያደረገ ይበልጣልን? ወይስ የሚያጋሩት?* ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም። أَمَّن جَعَلَ ٱلْأَرْضَ قَرَارًۭا وَجَعَلَ خِلَٰلَهَآ أَنْهَٰرًۭا وَجَعَلَ لَهَا رَوَٰسِىَ وَجَعَلَ بَيْنَ ٱلْبَحْرَيْنِ حَاجِزًا ۗ أَءِلَٰهٌۭ مَّعَ ٱللَّهِ ۚ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ

በተመሳሳይ ከሞት በኃላ የገነትም ሰዎች እና የእሳትን ሰዎች እንዳይገናኙ በመካከላቸውም ግርዶሽ አለ፦
7፥46 *በመካከላቸውም “ግርዶሽ” አለ፤ በአዕራፍም ላይ ሁሉንም በምልክታቸው የሚያውቁ ሰዎች አሉ፡፡ የገነትንም ሰዎች ሰላም ለእናንተ ይኹን በማለት ይጣራሉ፡፡ እነርሱም የአዕራፍ ሰዎች የሚከጅሉ ሲኾኑ ገና አልገቧትም*፡፡ وَبَيْنَهُمَا حِجَابٌ ۚ وَعَلَى الْأَعْرَافِ رِجَالٌ يَعْرِفُونَ كُلًّا بِسِيمَاهُمْ ۚ وَنَادَوْا أَصْحَابَ الْجَنَّةِ أَن سَلَامٌ عَلَيْكُمْ ۚ لَمْ يَدْخُلُوهَا وَهُمْ يَطْمَعُون

“አዕራፍ” أَعْرَاف በጀነት ሰዎች እና በእሳት ሰዎች መካከል ያለ ስፍራ ሲሆን ሚዛናቸው እኩል የሆኑ ሰዎች ደግሞ የአዕራፍ ሰዎች ይባላሉ፤ የገነት ሰዎች የእሳት ሰዎችን እንዲሁ የእሳት ሰዎች የገነት ሰዎችን ያነጋግሯቸዋል፦
7፥44 *የገነትም ሰዎች የእሳትን ሰዎች፦ «ጌታችን ቃል የገባልንን እውነት ኾኖ አገኘን፡፡ ጌታችሁ የዛተባችሁንስ እውነት ኾኖ አገኛችሁትን» ሲሉ ይጣራሉ፡፡ «አዎን አገኘን» ይላሉ፡፡ በመካከላቸውም «የአላህ ርግማን በበደለኞች ላይ ይኹን» ሲል ለፋፊ ይለፍፋል*፡፡ وَنَادَىٰ أَصْحَابُ الْجَنَّةِ أَصْحَابَ النَّارِ أَن قَدْ وَجَدْنَا مَا وَعَدَنَا رَبُّنَا حَقًّا فَهَلْ وَجَدتُّم مَّا وَعَدَ رَبُّكُمْ حَقًّا ۖ قَالُوا نَعَمْ ۚ فَأَذَّنَ مُؤَذِّنٌ بَيْنَهُمْ أَن لَّعْنَةُ اللَّهِ عَلَى الظَّالِمِينَ
7፥50 *የእሳትም ሰዎች የገነትን ሰዎች፦ «በእኛ ላይ ከውሃ አፍስሱብን ወይም አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ ጣሉልን» ብለው ጠሩዋቸዋል፡፡ እነርሱም «አላህ በከሓዲዎች ላይ እርም አድርጓቸዋል» ይሏቸዋል*፡፡ وَنَادَىٰ أَصْحَابُ النَّارِ أَصْحَابَ الْجَنَّةِ أَنْ أَفِيضُوا عَلَيْنَا مِنَ الْمَاءِ أَوْ مِمَّا رَزَقَكُمُ اللَّهُ ۚ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ حَرَّمَهُمَا عَلَى الْكَافِرِينَ

ምን ዋጋ አለው አይደለም ሰውን ይቅርና ጌታን ወደ ምድረ ዓለም መልሱኝ ብሎ ማናገር ለከሃድያን ከንቱ ቃል ናት፤ ነገር ግን ለአማንያን መላእክት «ሰላም በእናንተ ላይ» እያሉ የሚወስዷቸው ናቸው፡፡ «ትሠሩት በነበራችሁት ሥራ ገነትን ግቡ» ይሏቸዋል፦
39፥58 *ቅጣቱን በምታይ ጊዜ «ለእኔ ወደ ምድረ ዓለም አንድ ጊዜ መመለስ በኖረኝ እና ከበጎ አድራጊዎቹ በኾንኩ» ማለቷን ለመፍራት መልካሙን ተከተሉ*፡፡ أَوْ تَقُولَ حِينَ تَرَى الْعَذَابَ لَوْ أَنَّ لِي كَرَّةً فَأَكُونَ مِنَ الْمُحْسِنِينَ
23፥99 አንዳቸውንም ሞት በመጣበት ጊዜ እንዲህ ይላል፦ *«ጌታዬ ሆይ! ወደ ምድረ ዓለም መልሱኝ*፡፡ حَتَّىٰ إِذَا جَاءَ أَحَدَهُمُ الْمَوْتُ قَالَ رَبِّ ارْجِعُونِ
23፥100 *«በተውኩት ነገር በጎን ሥራ ልሠራ እከጅላለሁና፡፡» ይህን ከማለት ይከልከል፡፡ እርስዋ እርሱ ተናጋሪዋ የኾነች ከንቱ ቃል ናት*፡፡ لَعَلِّي أَعْمَلُ صَالِحًا فِيمَا تَرَكْتُ ۚ كَلَّا ۚ إِنَّهَا كَلِمَةٌ هُوَ قَائِلُهَا
16፥32 እነዚያ በመልካም ኹኔታ ላይ ኾነው መላእክት «ሰላም በእናንተ ላይ» እያሉ የሚወስዷቸው ናቸው፡፡ «ትሠሩት በነበራችሁት ሥራ ገነትን ግቡ» ይባላሉ፡፡ الَّذِينَ تَتَوَفَّاهُمُ الْمَلَائِكَةُ طَيِّبِينَ ۙ يَقُولُونَ سَلَامٌ عَلَيْكُمُ ادْخُلُوا الْجَنَّةَ بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُون

እንግዲህ በርዘኽ የሚባለው የገነት ሰዎች እና የእሳት ሰዎች እንዳይገናኙ በመካከላቸውም እስከ ትንሳኤ ቀን ድረስ መካከል ያለ ሁኔታ”Intermediate zone ነው፦
23፥100 *ከስተፊታቸውም እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ ግርዶ አለ*፡፡ ۖ وَمِن وَرَائِهِم بَرْزَخٌ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ

ይህ በርዘኽ ውስጥ የገነት ሰዎች ሩሕ በዒሊዪን ሲሆን “ዒሊዪን” عِلِّيِّين “ማለት “ከፍተኛ” ወይም “አርያም” ማለት ነው፤ “ዐሊየት” عَالِيَة ማለት ደግሞ “ከፍተኛይቱ” ማለት ነው፦
88፥10 *በከፍተኛ ገነት* ውስጥ ናቸው፡፡ فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٍ
83፥18 በእውነቱ *የእውነተኞቹ ምእምናን መጽሐፍ በዒሊዮን ውስጥ ነው*፡፡ كَلَّا إِنَّ كِتَابَ الْأَبْرَارِ لَفِي عِلِّيِّينَ
የእሳት ሰዎች ሩሕ ደግሞ በሢጂን ነው፤ “ሢጂን” سِجِّين የሚለው ቃል “ዩሥጀነ” يُسْجَنَ ማለትም “ታሰረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “እስር” ወይም “እንጦሮጦስ” ማለት ነው፤ “ሠጅን” سِّجْن ማለት “መታሰር” ማለት ሲሆን “መሥጁኒን” مَسْجُونِين ደግሞ “እስረኞች” ማለት ነው፦
83፥7 በእውነት *የከሓዲዎቹ መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው*፡፡ كَلَّا إِنَّ كِتَابَ الْفُجَّارِ لَفِي سِجِّينٍ

ሩሕ በትንሳኤ ቀን ከአካል ጋር ተዋሕዶ ፍርድ እስከሚሰጠው ድረስ በበርዘኽ ያለው ጊዚያዊ ቆይታ በግርድፉና በሌጣው ይህንን ይመስላል። “ሩሕ” رُّوح ማለት “መንፈስ” ማለት ሲሆን ይህ የሰው መንፈስ ሥረ-መሰረቱ ከዐፈር ሳይሆን ከጌታችን ነገር ነው፤ ስለ “ሩሕ” የተሰጠን ዕውቀት ጥቂት ብቻ ነው፦
17፥85 *ስለ ሩሕም ይጠይቁሃል፤ «ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው፤ ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም» በላቸው*፡፡ وَيَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلرُّوحِ ۖ قُلِ ٱلرُّوحُ مِنْ أَمْرِ رَبِّى وَمَآ أُوتِيتُم مِّنَ ٱلْعِلْمِ إِلَّا قَلِيلًۭا

አላህ በዒሊዮን ውስጥ ከሚደሰቱ ባሮቹ ያድርገን፤ ከሢጂን ውስጥ ቅጣት ይጠብቀን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የተሳከረ ምልከታ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

10፥68 በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን? ۚ أَتَقُولُونَ عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ

” አሏህ” በዕብራይስ “ላሜድን” ל ተሽዲድ ስናደርገው “አሏህ” אללה‌‎ ሲሆን ይህንን ቃል በዕብራይስጥ የቁርአን ትርጉም ላይ እናገኘዋለን፤ ነገር ግን ጥራዝ ነጠቅ ዕውቀት ያላቸው ሚሽነሪዎች ግልብ እና ድልብ ሃሳብ ይዘው ቃላትን በምላሶቻቸው ሲያጣምሙ ይታያሉ፤ “ኣላህ” אלה አንድ “ላሜድ” ל ብቻ ሲሆን ይላላል፤ ይህ ቃል 36 ጊዜ በብሉይ ኪዳን የተጠቀሰ ሲሆን፦
1ኛ. “መሃላ” ማለት ነው፦
ዘፍጥረት 24:41የዚያን ጊዜ “ከመሐላዬ” אָלָה ንጹሕ ነህ፤ ወደ ዘመዶቼ ሄደህ እነርሱ ባይሰጡህ ካማልሁህ መሐላ ንጹሕ ትሆናለህ።”
2. “እርግማን” ማለት ነው፦
ዘኍልቍ 5:23 ካህኑም እነዚህን “መርገሞች” אָלָה በሰሌዳ ይጽፈዋል፥ በመራራውም ውኃ ይደመስሰዋል፤”

“አሏህ” የሚለው ቃል ግን ይለያል። አሏህ በዕብራይስ አሁንም “ላሜድን” ל ተሽዲድ ስናደርገው “አሏህ” אללה‌‎ ሲሆን በውስጡ ሁለት “ላሜድ” ל አለው። ነገር ግን አሏህ የሚለው አንድ “ላሜድ” ל በመቀነስና በማላላት አሏህ ማለት “እርግማን” አስተግፊሩላህ! ማለት ነው እያሉ ይሳለቃሉ፤ ሌላው “አክበር” أكبر ማለት “ታላቅ” ማለት ሲሆን “elative degree” ነው፤ ይህንን ቃል ወደ ዕብራይስጥ “ከ” የነበረውን ወደ “ኸ” ይቀይሩትና ያጣምማሉ፤ “አኽባር” עַכְבָּר ማለት “አይጥ” ማለት ነው፤ “አሏሁ አኽባር” ማለት “አሏህ አይጥ ነው” አስተግፊሩላህ! ብለው ንግግርን ከስፍራው ይቀይራሉ፤ ይህ ዛሬ ያሉት ከሃድያን ንግግሮችን ቢያጣምሙ አይደንቅም፤ ነብያችን”ﷺ” ነብይ ሆነው በተላኩበትም ጊዜ አይሁዳውን ቃላትን ያጣምሙ ነበር፤ “ራዒና” َرَٰعِنَا ማለት “ጠብቀን” ማለት ሲሆን በዕብራይስጥ ግን “ጅል” ማለት ነው፤ ለዛ ነው አላህ “አንዙርና” ٱنظُرْنَا ማለትም “ተመለከትን” በሉ ያለው፦
4፥46 ከነዚያ አይሁዳውያን ከኾኑት ሰዎች ንግግሮችን ከስፍራዎቹ የሚያጣምሙ አልሉ፡፡ «ሰማንም አመጽንም የማትሰማም ስትኾን ስማ» ይላሉ፡፡ በምላሶቻቸውም ለማጣመምና ሃይማኖትንም ለመዝለፍ *”ራዒና”* ይላሉ፡፡ እነሱም «ሰማን ታዘዝንም ስማም ተመልከተንም» ባሉ ኖሮ ለነሱ መልካምና ትክክለኛ በኾነ ነበር፡፡ ግን በክህደታቸው አላህ ረገማቸው፡፡ ጥቂትንም እንጅ አያምኑም፡፡ مِّنَ ٱلَّذِينَ هَادُوا۟ يُحَرِّفُونَ ٱلْكَلِمَ عَن مَّوَاضِعِهِۦ وَيَقُولُونَ سَمِعْنَا وَعَصَيْنَا وَٱسْمَعْ غَيْرَ مُسْمَعٍۢ وَرَٰعِنَا لَيًّۢا بِأَلْسِنَتِهِمْ وَطَعْنًۭا فِى ٱلدِّينِ ۚ وَلَوْ أَنَّهُمْ قَالُوا۟ سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا وَٱسْمَعْ وَٱنظُرْنَا لَكَانَ خَيْرًۭا لَّهُمْ وَأَقْوَمَ وَلَٰكِن لَّعَنَهُمُ ٱللَّهُ بِكُفْرِهِمْ فَلَا يُؤْمِنُونَ إِلَّا قَلِيلًۭا
2፥104 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *”ራዒና”* አትበሉ፡፡ *”ተመለከትን”* በሉም፡፡ ስሙም፤ ለከሓዲዎችም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تَقُولُوا۟ رَٰعِنَا وَقُولُوا۟ ٱنظُرْنَا وَٱسْمَعُوا۟ ۗ وَلِلْكَٰفِرِينَ عَذَابٌ أَلِيمٌۭ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አርካኑል ኢሥላም

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

3፥19 አላህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት *“ኢሥላም”* ብቻ ነው፡፡ إِنَّ ٱلدِّينَ عِندَ ٱللَّهِ ٱلْإِسْلَٰمُ

“ኢሥላም” إِسْلَٰم የሚለው ቃል “አሥለመ” أَسْلَمَ ማለትም “ታዘዘ” “ተገዛ” ” አመለከ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "መታዘዝ" "መገዛት" "ማምለክ" ማለት ነው፤ አላህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት ኢሥላም ብቻ ነው፦
3፥19 *አላህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት “ኢሥላም” ብቻ ነው*፡፡ إِنَّ ٱلدِّينَ عِندَ ٱللَّهِ ٱلْإِسْلَٰمُ

"አርካን" أَرْكان‎ ማለት "ምሰሶ" ማለት ነው፤ የኢሥላም ምሰሶ አምስት ናቸው፤ እነርሱም፦ ሸሃደተይን፣ ሶላት፣ ዘካህ፣ ሰውም እና ሐጅ ናቸው፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 4
ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ኢሥላም በአምስቱ መሠረቶች ላይ ተገንብቷል፤ እነርሱም፦ "ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፥ ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ ነው" በሚል ምስክርነት፣ ሶላትን በመቆም፣ ዘካህን በመስጠት፣ ረመዷንን በመፆም እና የአላህ በይት በመጎብኘት"*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ بُنِيَ الإِسْلاَمُ عَلَى خَمْسٍ شَهَادَةُ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللَّهِ وَإِقَامُ الصَّلاَةِ وَإِيتَاءُ الزَّكَاةِ وَصَوْمُ رَمَضَانَ وَحَجُّ الْبَيْتِ

ነጥብ አንድ
"ሸሃደተይን"
“አሽ-ሸሃዳ” الشهادة የሚለው ቃል “ሸሂደ” شَهِدَ ማለትም “መሰከረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ምስክርነት” ማለት ነው፤ ሻሂድ شَاهِد አሊያም “ሸሂድ” شَهِيد ደግሞ “ምስክር” ማለት ሲሆን የሻሂድ ብዙ ቁጥር “ሹሀዳ” شُهَدَاء ነው። አንድ ሰው ወደ ዲኑል ኢሥላም የሚገባበት “ከሊመተ-ሸሃዳ” كلمة الشهادة ማለትም “ቃለ-ምስክርነት” ይባላል፤ ይህም ቃለ-ምስክርነት “ላ ኢላሀ ኢለሏህ ሙሐመዱን ረሱሉሏህ” لا إله إلا الله محمد رسول الله ትርጉሙ “ከአላህ በስተቀር አምላክ የለም፤ ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ ነው” የሚል ነው፥ በእያንዳንዱ ዘመን የተለያዩ መልእክተኛ ስላሉ በዛ ዘመን ባለው መልእክተኛ ለምሳሌ በዒሣ ከሆነ "ዒሣ ረሱሉሏህ" ብለው ይቀበሉ ነበር። ለምሳሌ አላህ በዒሣ ዘመን "በእኔ እና በመልክተኛዬ እመኑ" በማለት ወሕይ አውርዷል፦
5፥111 ወደ ሐዋርያትም *«በእኔ እና በመልክተኛዬ እመኑ»* በማለት ባዘዝኩ ጊዜ አስታውስ፡፡ «አመንን፤ እኛ ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክር» አሉ፡፡ وَإِذْ أَوْحَيْتُ إِلَى الْحَوَارِيِّينَ أَنْ آمِنُوا بِي وَبِرَسُولِي قَالُوا آمَنَّا وَاشْهَدْ بِأَنَّنَا مُسْلِمُونَ

ስለዚህ የኢሥላም ማዕዘን የሆነው ሸሃደተይን ከጥንት ጀምሮ አለ፤ አላህም ሲልካቸው “ማ ለኩም ሚን ኢላሂ ገይሩሁ” مَا لَكُمْ مِنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ማለትም “ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የላችሁም” ብለው እንዲናገሩ ነው፦
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ *”ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ”* በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ
16፥2 ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ መላእክትን ከራእይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል ከሓዲዎችን በቅጣት አስጠንቅቁ፤ እነሆ *”ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ፍሩኝም”* ማለትን አስታውቁ በማለት ያወርዳል፡፡ يُنَزِّلُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةَ بِٱلرُّوحِ مِنْ أَمْرِهِۦ عَلَىٰ مَن يَشَآءُ مِنْ عِبَادِهِۦٓ أَنْ أَنذِرُوٓا۟ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱتَّقُونِ

ነጥብ ሁለት
"ሶላት"
“ሶላት” صَلَوٰة ማለት “ፀሎት” ሲሆን በውስጡ ሦስት አበይት ክፍሎች ያቅፋል፤ እነርሱም፦
1. “ቂያም” قيام “መቆም”
2. “ሩኩዕ” رُكوع “ማጎንበስ”
3. “ሡጁድ” سُّجُود “ስግደት” ናቸው፤
ሶላት የሚፈፅሙ ሰዎች ደግሞ “ሙሰሊን” مُصَلِّين ይባላሉ፤ ሙሰሊን በቂያም “ሙቂሚ” مُّقِيم ” ሲባሉ፣ በሩኩዕ “ራኪዕ” رَاكِع ሲባሉ፣ በሱጁድ ደግሞ "ሣጂድ" سَاجِد ይባላሉ። ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናት፤ በኢማን እና በኩፍር መካከል ያለው ግድግዳ ሶላት ነው፦
4፥103 *"ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና"*፡፡ إِنَّ الصَّلَاةَ كَانَتْ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ كِتَابًا مَّوْقُوتًا
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 40, ሐዲስ 13
ጃቢር እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በኢማን እና በኩፍር መካከል ያለው ሶላት ነው"*። عَنْ جَابِرٍ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ بَيْنَ الْكُفْرِ وَالإِيمَانِ تَرْكُ الصَّلاَةِ

ከነቢያችን"ﷺ" በፊት በነበሩት ነቢያት በቀን አምስት ጊዜ ሶላት ላይቆሙ ይችላሉ፤ ወይ ያንሳል አሊያም ይበዛ ይሆናል፤ ነገር ግን ሶላትን መስገድ ወደ እነርሱ ተወርዷል፦
21፥73 *”ወደ እነርሱም መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን አወረድን”*፡፡ وَأَوْحَيْنَآ إِلَيْهِمْ فِعْلَ ٱلْخَيْرَٰتِ وَإِقَامَ ٱلصَّلَوٰةِ وَإِيتَآءَ ٱلزَّكَوٰة

ስለዚህ የኢሥላም ማዕዘን የሆነው ሶላት ኢሥላም እስካለ ድረስ ከጥንት ጀምሮ አለ ማለት ነው። ኢንሻላህ የተቀሩትን አርካኑል ኢሥላም በክፍል ሁለት እንዳስሳለን........

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አርካኑል ኢሥላም

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

3፥85 *”ከእሥልምና ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከእርሱ ተቀባይ የለውም”፡፡ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው*፡፡ وَمَن يَبْتَغِ غَيْرَ ٱلْإِسْلَٰمِ دِينًۭا فَلَن يُقْبَلَ مِنْهُ وَهُوَ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ

ነጥብ ሦስት
"ዘካህ"
“ዘካህ" زَكَوٰة ማለት "ምጽዋት" ማለት ነው፤ አምላካችን አላህ ከሰጠን ሲሳይ ላይ የምንለግሰው ልግስና ዘካህ ይባላል፦
8፥3 እነዚያ ሶላትን ደንቡን አሟልተው የሚሰግዱ *"ከሰጠናቸውም ሲሳይ የሚለግሱ ናቸው"*፡፡ الَّذِينَ يُقِيمُونَ الصَّلَاةَ وَمِمَّا رَزَقْنَاهُمْ يُنفِقُون

“ኢንፋቅ” إِنفَاق ማለት “ልግስና” ማለት ሲሆን “ሙንፊቂን” مُنفِقِين ደግሞ “ለጋሾች” ማለት ነው፤ ልግስና የበረከት ምንጭና ለአላህ ውዴታ ያለን መገለጫ ነው፤ ዘካህ ከትርፍ ላይ ከመቶ 2.5 % የሚሰጥ ነው። ዘካህ ከነቢያችን"ﷺ" በፊት በነበሩት ነቢያት ጊዜ ከመቶ 2.5 % ላይሰጥ ይችላል፤ ወይ ያንሳል አሊያም ይበዛ ይሆናል፤ ምናልባት ከመቶ 10 % አሥራት ሊሆን ይችል ይሆናል፥ አላህ ነው ሁሉን ዐዋቂ። ነገር ግን አላህ ዘካንም ስለ መስጠት ትእዛዝ ወደ ነቢያት አውርዷል፦
21፥73 *”ወደ እነርሱም መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን አወረድን”*፡፡ وَأَوْحَيْنَآ إِلَيْهِمْ فِعْلَ ٱلْخَيْرَٰتِ وَإِقَامَ ٱلصَّلَوٰةِ وَإِيتَآءَ ٱلزَّكَوٰة

ስለዚህ የኢሥላም ማዕዘን የሆነው ዘካህ ኢሥላም እስካለ ድረስ ከጥንት ጀምሮ አለ ማለት ነው።

ነጥብ አራት
"ሰውም"
“ሰውም” صَوْم ማለት "ጾም" ማለት ነው፤ አንድ ሰው ምንም ነገር ሳይቀምስ ሲቀር "ጾሙን ዋለ" ይባላል፤ ያ ማለት ከምግብና ከመጠጥ “ተከለከለ” አሊያም “ተቆጠበ” ማለት ነው፤ አምላካችን አላህ ጾምን ከነቢያችን"ﷺ" በፊት በነበሩት ላይ እንደ እንደደነገገ በእኛም ላይ ደነገገ፦
2፥183 *“እናንተ ያመናችሁ ሆይ “ጾም” በእነዚያ ከእናንተ በፊት በነበሩት ላይ እንደ ተጻፈ በእናንተም ላይ ተጻፈ፤ ልትጠነቀቁ ይከጀላልና”*፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كُتِبَ عَلَيْكُمُ ٱلصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

በዚህ አንቀጽ ላይ “ኩቲበ” كُتِبَ ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ከተበ” كَتَبَ ከሚለው የመጣ ሲሆን “ተገለጸ" "ተደነገገ" "ተደነባ"prescribed” ማለት ነው፤ ጾም የምጾምበት ምክንያት ደግሞ “ተቅዋ” تَقْوَى ማለትም “አላህ መፍራት” ለማግኘት ነው፤ "ተተቁን" تَتَّقُون ማለት "አላህን ልትፈሩ" ማለት ነው፤ “ይከጀላልና” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ለዐለኩም” لَعَلَّكُمْ ነው፤ "ለዐለኩም" በሚለው ቃል ላይ መነሻ ቅጥያ ሆኖ የመጣው “ለዐል” لَعَلَّ ነው፤ "ለዐል" ማለት "ምክንያት" “ዘንድ”so that” ማለት ሲሆን ምክንያታዊ መስተዋድድ ነው፤ "ጾም አላህን ልትፈሩ ዘንድ በእነዚያ ከእናንተ በፊት በነበሩት ላይ እንደ ተነደገገ በእናንተም ላይ ተደነገገ" ማለት ነው። “ረመዷን” رمضان‎ ማለት “ድርቀት” “ሞቃታማ” ማለት ሲሆን የጾም ስም ሳይሆን የወር ስም ነው፤ የዘጠነኛው ወር ስም ነው፤ ይህ ወር ቁርኣን የወረደበትና መውረድ የጀመረበት ወር ነው። ጾም ከነቢያችን"ﷺ" በፊት በነበሩት ነቢያት ጊዜ በዚህ ወር ላይጾሙት ይችላል። ነገር ግን አላህ ጾምን ከነቢያችን"ﷺ" በፊት በነበሩት ላይ እንደደነገገ ከላይ ያለው አንቀጽ ያስረዳል። ስለዚህ የኢሥላም ማዕዘን የሆነው ሰውም ኢሥላም እስካለ ድረስ ከጥንት ጀምሮ አለ ማለት ነው።
ነጥብ አምስት
"ሐጅ"
“ሐጅ” حَجّ የሚለው ቃል “ሐጀ” حَجَّ ማለትም “ጎበኘ” ከሚል ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን “ጉብኝት”pilgrimage” ማለት ነው፤ “ሐጅ” መደበኛ ዐብይ ጉብኝት ሲሆን “ዑምራ” عُمْرَة ደግሞ መደበኛ ያልሆነ ንዑስ ጉብኝት ነው፦
2፥158 *ሶፋና መርዋ ከአላህ ምልክቶች ናቸው፤ “ቤቱን በሐጅ ወይም በዑምራህ ሥራ የጎበኘ” ሰው በሁለቱ መካከል በመመላለሱ በእርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም*፡፡ إِنَّ الصَّفَا وَالْمَرْوَةَ مِن شَعَائِرِ اللَّهِ ۖ فَمَنْ حَجَّ الْبَيْتَ أَوِ اعْتَمَرَ فَلَا جُنَاحَ عَلَيْهِ أَن يَطَّوَّفَ بِهِمَا

“የጎበኘ” ለሚለው ቃል የገባው “ሐጀ” حَجَّ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ የታወቁ ቀኖች 12ኛ ወር- ዙል-ሒጃህ ላይ የመጀመሪያዎቹ ዐሥሩ ሌሊቶች ናቸው። አላህ በዚህ ወቅት ቤቱን እንዲጎበኙ ያዘዘው ለኢብራሂም ነው፦
22፥27 *አልነውም፡- በሰዎችም ውስጥ በሐጅ ትዕዛዝ ጥራ*፡፡ እግረኞች ከየሩቅ መንገድ በሚመጡ ከሲታ ግመሎችም ሁሉ ላይ ሆነው ይመጡሃልና፡፡ وَأَذِّن فِي النَّاسِ بِالْحَجِّ يَأْتُوكَ رِجَالًا وَعَلَىٰ كُلِّ ضَامِرٍ يَأْتِينَ مِن كُلِّ فَجٍّ عَمِيقٍ
22፥26 *ለኢብራሂምም የቤቱን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ «በእኔ ምንንም አታጋራ፣ ቤቴንም ለሚዞሩት፣ ለሚቆሙበት፣ ለሚያጎነብሱት እና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው» ባልነው ጊዜ አስታውስ*፡፡ وَإِذْ بَوَّأْنَا لِإِبْرَاهِيمَ مَكَانَ الْبَيْتِ أَن لَّا تُشْرِكْ بِي شَيْئًا وَطَهِّرْ بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْقَائِمِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ

“ለሚዞሩት” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሊጧዒፊነ” لِلطَّائِفِينَ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ “ጠዋፍ” طَواف የሚለው ቃል “ጧፈ” طَافَ ማለትም “ዞረ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ዙረት” ማለት ነው፤ ቤቱን በመጎብኘት ሰባት ጊዜ መዞር አምላካችን አላህ ለኢብራሂም የሰጠው ትእዛዝ ነው፦
22፥29 ከዚያም እንደ ጠጉርና ጥፍር ያሉትን ትርፍ አካላቸውንና ዕድፋቸውን ያስወግዱ፡፡ ስለቶቻቸውንም ይሙሉ፤ *በጥንታዊውም ቤት ይዙሩ*፡፡ ثُمَّ لْيَقْضُوا تَفَثَهُمْ وَلْيُوفُوا نُذُورَهُمْ وَلْيَطَّوَّفُوا بِالْبَيْتِ الْعَتِيقِ

“ይዙሩ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የጠወፉ” يَطَّوَّفُوا መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል፤ ቤቱን የሚዞሩት ዘዋሪዎች ደግሞ “ጧዒፍ” طَآئِف ይባላሉ፦
2፥125 ቤቱንም ለሰዎች መመለሻ እና ጸጥተኛ ባደረግን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከኢብራሂምም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ፡፡ *ወደ ኢብራሂም እና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን “ለዘዋሪዎቹ”፣ ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃል ኪዳን ያዝን*፡፡ وَإِذْ جَعَلْنَا الْبَيْتَ مَثَابَةً لِّلنَّاسِ وَأَمْنًا وَاتَّخِذُوا مِن مَّقَامِ إِبْرَاهِيمَ مُصَلًّى ۖ وَعَهِدْنَا إِلَىٰ إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ أَن طَهِّرَا بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْعَاكِفِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ

አምላካችን አላህ ለሁሉም ሕዝቦች የሚዞሩባት ቂብላህ እና ወደ እርሱ መስዋዕት ማቅረብን ደንግጓል፦
2፥148 *“ለሁሉም እርሱ የሚያዞርባት አግጣጫ አለችው”*። وَلِكُلٍّ وِجْهَةٌ هُوَ مُوَلِّيهَا
22፥34 *ለሕዝብም ሁሉ ወደ አላህ መስዋዕት ማቅረብን ደነገግን*፡፡ وَلِكُلِّ أُمَّةٍ جَعَلْنَا مَنسَكًا لِّيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ عَلَىٰ مَا رَزَقَهُم مِّن بَهِيمَةِ الْأَنْعَامِ

ከነቢያችን"ﷺ" በፊት ያሉት ቂብላህ የሚቀጣጩበት የአላህ ቤት መስጂዱል አቅሳ ስለነበር ምናልባት የሚጎበኙት ያንን ቤት ይሆናል፥ ሆነም ቀረ ጉብኝት የተጀመረው በነቢያችን"ﷺ" ሳይሆን በጥንቱ ነቢይ በኢብራሂም ዘመን ነው። ስለዚህ የኢሥላም ማዕዘን የሆነው ሐጅ ኢሥላም እስካለ ድረስ ከጥንት ጀምሮ አለ ማለት ነው።
እንግዲህ አምስቱ የኢሥላም ምሰሶች ከጥንት ጀምሮ ያሉ ወደፊትም የሚኖሩ ዐቂደቱል ረባኒያህ ናቸው። ከእሥልምና ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከእርሱ ተቀባይ የለውም፤ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው። ያ አዩሀል ሙሽሪኩን የተውበት በሩ ሳይዘጋ ወደ ዲኑል ኢሥላም ኑ፦
3፥85 *”ከእሥልምና ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከእርሱ ተቀባይ የለውም”፤ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው*፡፡ وَمَن يَبْتَغِ غَيْرَ ٱلْإِسْلَٰمِ دِينًۭا فَلَن يُقْبَلَ مِنْهُ وَهُوَ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
መመሳሰል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

4፥144 *"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከምእምናን ሌላ ከሓዲዎችን ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ*፤ ለአላህ በእናንተ ላይ ግልጽ ማስረጃዎችን ልታደርጉ ትፈልጋላችሁን? يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا الْكَافِرِينَ أَوْلِيَاءَ مِن دُونِ الْمُؤْمِنِينَ ۚ أَتُرِيدُونَ أَن تَجْعَلُوا لِلَّهِ عَلَيْكُمْ سُلْطَانًا مُّبِينًا

አምላካችን አላህ ከሰው ጋር በሚኖረን ማሕበራዊ ዘይቤ እንዴት መኗኗር እንዳለብን እንዲህ ይነግረናል፦
4፥36 *አላህንም አምልኩ፤ በእርሱም ምንንም አታጋሩ፡፡ በወላጆች፣ በቅርብ ዝምድና ባለቤትም፣ በየቲሞችም፣ በምስኪኖችም፣ በቅርብ ጎረቤትም፣ በሩቅ ጎረቤትም፣ በጎን ባልደረባም፣ በመንገደኛም፣ እጆቻችሁም ንብረት ባደረጓቸው መልካምን ሥሩ*፤ አላህ ኩራተኛ ጉረኛ የኾነን ሰው አይወድም፡፡ وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا ۖ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا وَبِذِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَالْجَارِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَالْجَارِ الْجُنُبِ وَالصَّاحِبِ بِالْجَنبِ وَابْنِ السَّبِيلِ وَمَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخْتَالًا فَخُورًا
4፥135 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *በትክክል ፍትሕ ቀዋሚዎች በራሳችሁ ወይም በወላጆች እና በቅርብ ዘመዶች ላይ ቢኾንም እንኳ ለአላህ መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሀብታም ወይም ድኻ ቢኾን አላህ በእነርሱ ከእናንተ ይበልጥ ተገቢ ነው፡፡ እንዳታደሉም ዝንባሌን አትከተሉ፡፡ ብታጠምሙም ወይም መመስከርን ብትተው አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ بِالْقِسْطِ شُهَدَاءَ لِلَّهِ وَلَوْ عَلَىٰ أَنفُسِكُمْ أَوِ الْوَالِدَيْنِ وَالْأَقْرَبِينَ ۚ إِن يَكُنْ غَنِيًّا أَوْ فَقِيرًا فَاللَّهُ أَوْلَىٰ بِهِمَا ۖ فَلَا تَتَّبِعُوا الْهَوَىٰ أَن تَعْدِلُوا ۚ وَإِن تَلْوُوا أَوْ تُعْرِضُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا

እዚህ አንቀጽ ላይ “ተዕዲሉ” تَعْدِلُوا የሚለው ቃል ይሰመርበት፤ ይህ ቃል የስም መደቡ “ዐድል” عَدْل ሲሆን “ፍትሕ” ማለት ነው፤ ፍትሕ ለአላህ ፍራቻ ተብሎ እና አላህ በምንሠራው ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው ተብሎ የሚደረግ ነው። ይህ ለአላህ ተብሎ የሚደረግ ፍትሕ ለአማንያን ብቻ ሳይሆን ለከሃድያንም ጭምር ነው፦
60፥8 *ከእነዚያ በሃይማኖት ካልተጋደሏችሁ፣ ከአገሮቻችሁም ካላወጡዋችሁ ከሓዲዎች መልካም ብትውሉላቸው እና ወደ እነርሱ ብታስተካክሉ አላህ አይከለክላችሁም፡፡ አላህ ትክክለኞችን ይወዳልና*፡፡ لَّا يَنْهَاكُمُ اللَّهُ عَنِ الَّذِينَ لَمْ يُقَاتِلُوكُمْ فِي الدِّينِ وَلَمْ يُخْرِجُوكُم مِّن دِيَارِكُمْ أَن تَبَرُّوهُمْ وَتُقْسِطُوا إِلَيْهِمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ

ዲናችንን አክብረው ካልተጋደሉንና ካላሳደዱን ከሃድያን ጋር በዝምድና፣ በባልደረባ፣ በጉርብትና መልካም መዋዋል እና ማስተካከል ይቻላል፤ “ብታስተካክሉ” ለሚለው ቃል አሁንም የገባው “ቱቅሢጡ” َتُقْسِطُوا ሲሆን የስም መደቡ “ቂሥጥ” قِسْط ማለትም “ፍትሕ” ነው፤ ለአላህ ብለን ስናስተካክል “ሙቅሢጢን” مُقْسِطِين ማለትም “ፍትኸኞችን” “ትክክለኞች” “አስተካካዮች” እንሰኛለን፤ አላህ ሙቅሢጢንን ይወዳልና፦
49፥9 *በነገሩ ሁሉ አስተካክሉም፡፡ አላህ አስተካካዮችን ይወዳልና*፡፡ وَأَقْسِطُوا ۖ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ
ነገር ግን ከዚያ አልፎ ወደ ኩፍርና ሺርክ ሊያስገባ የሚችለውን ሥራ ከሌላ እምነት ጋር መሥራት ከኢሥላም ያስወጣል፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 15, ሐዲስ 311
ሰሙራህ ኢብኑ ጁንዱብ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እዲህ አሉ፦ *"ከሙሽሪክ ጋር ያበረ እና የተኗኗረ እርሱን(ሙሽሪኩን) ይመስላል"*። أَمَّا بَعْدُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ مَنْ جَامَعَ الْمُشْرِكَ وَسَكَنَ مَعَهُ فَإِنَّهُ مِثْلُهُ ‏
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 12, ሐዲስ 34
ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም አሉ፦ *"ከማንኛውም ሕዝብ ጋር የሚመሳሰል ከእነርሱ ነው"*። عَنِ ابْنِ عُمَرَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ مَنْ تَشَبَّهَ بِقَوْمٍ فَهُوَ مِنْهُمْ

ስለዚህ የማይመለከተን ነገር ውስጥ ለመመሳሰል ለምሳሌ ቤተ ክርስቲያንና የጥምቀት ቦታ ማጽዳት፥ ታቦት መሸኘት፣ በዓላቸውን ማክበር፣ መዝሙራቸውን መዘመር ከኢሥላም አጥር ያስወጣል። አንዳንድ ቂሎች፦ "ለመረዳዳት ነው" ይሉናል፤ በጋራ እሴት ማለትም በልማት፣ በጉርብትና፣ በአስኳላ ትምህርት፣ በሰብአዊነት ወዘተ... ልንረዳዳ እንችላለን፥ ነገር ግን በእምነት ጉዳይ እረዳቶች አድርገን ከያዝናቸው ከእነርሱ እንደ አንዱ ነን፦
4፥144 *"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከምእምናን ሌላ ከሓዲዎችን ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ*፤ ለአላህ በእናንተ ላይ ግልጽ ማስረጃዎችን ልታደርጉ ትፈልጋላችሁን? يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا الْكَافِرِينَ أَوْلِيَاءَ مِن دُونِ الْمُؤْمِنِينَ ۚ أَتُرِيدُونَ أَن تَجْعَلُوا لِلَّهِ عَلَيْكُمْ سُلْطَانًا مُّبِينًا
5፥51 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ፡፡ ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ ረዳቶች የሚያደርጋቸው ሰው እርሱ ከእነርሱ ነው*፡፡ አላህ አመጸኞችን ሕዝቦች አያቀናም፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَتَّخِذُوا الْيَهُودَ وَالنَّصَارَىٰ أَوْلِيَاءَ ۘ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ ۚ وَمَن يَتَوَلَّهُم مِّنكُمْ فَإِنَّهُ مِنْهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 24, ሐዲስ 2939
ዓኢሻህ"ረ.ዐ." እንደተረከችው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"የሙሽሪክ እርዳታ አያስፈልገንም"* عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّا لاَ نَسْتَعِينُ بِمُشْرِكٍ ‏

ስለዚህ፦ "ገና እኛ ይመለከተናል፣ የጋራ በዓል አለን፣ የጋራ መዝሙር እናውጣ" እያሉ የሚያስተምሩ ኡስታዞች በግል ሊመከሩ ይገባል። አሻፈረኝ ካሉ በዑማው ላይ የሚረጩትን ፈሳድ ከነስማቸው መጋለጥ አለበት። ዝም ከተባሉ ትንሽ ቆይተው እምነታቸውንና አስተምህሮታቸውንም እንቀበል እንዳይሉን እሰጋለው። አንድነት እናመጣለን በሚል ሽፋን ዑማውን የዝቅተኝነት ስሜት በማከናነብ ከድጡ ወደ ማጡ አትክተቱት። ኢትዮጵያዊነት በመሆን እንጂ በመምሰል አይለካም። ምንም ሳይገባውና ሳያውቀው የሚሳተፈውን ሙሥሊም በትህትና የማስጠንቀቅ የሁላችንም ሃላፍትና ነው። ይህንን መልእክት ለሁሉም በማስተላለፍ ዲናዊ ግዴታዎን ይወጡ! አላህ ለሁላችንም ሂዳያ ይስጠን! አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የኢየሱስ ፈጣሪ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥117 «በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል፦ *ጌታዬን እና ጌታችሁን አላህን አምልኩ* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ

በቁርኣን አስተምህሮት የተፈጠረ ማንነትና ምንነት ተመልሶ አይፈጥርም። የሚፈጠርን ምንም መፍጠር የማይችልን ማንነትና ምንነት ማምለክ በአላህ ላይ ማጋራት ነው፦
7፥191 *"ምንንም የማይፈጥሩትንና እነርሱም የሚፈጠሩትን በአላህ ያጋራሉን?* أَيُشْرِكُونَ مَا لَا يَخْلُقُ شَيْئًا وَهُمْ يُخْلَقُونَ

ኢየሱስ ሊያርግ ሲል የፈጠረውን አንዱን አምላክ "ፈጣሪዬ" ብሏል፦
ዮሐንስ 20፥17 *"ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ፦ "ወዳባቴ ወዳባታችምሁ "ወደ ፈጣሪዬ" ወደ ወደ ፈጣሪያችሁ ዓርጋለው" ብለሽ ንገሪያቸው"*። (አንድምታ ትርጓሜ)

ካረገም በኃላ የፈጠረውን አንዱን አምላክ "ፈጣሪዬ" ብሏል፦
ራእይ 3፥2 *"በፈጣሪዬ ዘንድ ሥራህን ፍጹም ሆኖ አላገኘሁትም"*። (አንድምታ ትርጓሜ)

"ፈጣሪ" በሚለው ቃል ላይ "ዬ" የሚል አገናዛቢ ተውላጠ-ስም መድረሻ ቅጥያ ሆኖ ገብቷል፤ "ዬ" የመጀመሪያ መደብ ነጠላ አገናዛቢ ተውላጠ-ስም "የእኔ" የሚለው የሚወክል ህቡዕ ምጻረ-ቃል ነው። ኢየሱስ፦ "የእኔ ፈጣሪ" ብሎ ካለ የኢየሱስ ሙሉ "እኔነት" ፈጣሪ አለው ማለት ነው። የኢየሱስን ሙሉ ሁለንተናዊ እኔነት የፈጠረው አብ ነው። "ፈጣሪያችን" በማለት ፋንታ "ፈጣሪዬ እና ፈጣሪያችሁ" ማለቱ አንዳች የትርጉም ልዩነት የለውም። ይህንን በአንድ ጥቅስ ማየት ይቻላል፦
ዘፍጥረት 43፥23 እርሱም አላቸው፦ ሰላም ለእናንተ ይሁን፥ አትፍሩ፤ *አምላካችሁ እና የአባታችሁ አምላክ* በዓይበታችሁ የተሰወረ ገንዘብ ሰጣችሁ፤ ብራችሁስ ደርሶኛል።

“አምላካችሁ እና የአባታችሁ አምላክ” ስለተባለ አንዱ አምላክ ለአባታቸው ለያዕቆብ እና ለልጆቹ አምላክነቱ ይለያልን? "እና" በሚልስ አያያዥ መስተጻምር ስለተለየ ያዕቆብ እና ልጆቹ ምንነታቸው ይለያያልን? በፍጹም! አንዱ አምላክ ለያዕቆብ እና ለልጆቹ ሁለንተናዊ እኔነት አምላክ እንደሆነ ሁሉ ለኢየሱስ እና ለሐዋርያት ሁለንተናዊ እኔነት ፈጣሪ ነው።
ስለዚህ ኢየሱስ የተፈጠረ ማንነትና ምንነት ከሆነ ኢየሱስን የፈጠረውን የኢየሱስ ፈጣሪ በብቸኝነት አምልኩት። አላህ ዒሣን እንዲናገር ያዘዘው ቃል፦ "ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን አምልኩ" ማለትን ነው፤ ከዚያ አልፎ ግን ፍጡርን በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በእርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፤ መኖሪያውም እሳት ናት፤ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፦
5፥117 «በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል፦ *ጌታዬን እና ጌታችሁን አላህን አምልኩ* ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَآ أَمَرْتَنِى بِهِۦٓ أَنِ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ
5፥72 እነዚያ «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ *አልመሲህም አለ፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታዬን እና ጌታችሁን አላህን አምልኩ*፡፡» እነሆ! *በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በእርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት*፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡ لَقَدْ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْمَسِيحُ ٱبْنُ مَرْيَمَ ۖ وَقَالَ ٱلْمَسِيحُ يَٰبَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ ۖ إِنَّهُۥ مَن يُشْرِكْ بِٱللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ ٱللَّهُ عَلَيْهِ ٱلْجَنَّةَ وَمَأْوَىٰهُ ٱلنَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّٰلِمِينَ مِنْ أَنصَارٍۢ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
በስጋ ተገለጠ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥72 እነዚያ *«አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው»* ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

በክርስትና ስልታዊ ሥነ-መለኮት”systematic theology” የአምላክ ሰው መሆን አስተምህሮት “ተሰግዎት”Incarnation” ሲባል በአገራችን “ሚስጥረ-ስጋዌ” ይሉታል፣ “ስጋዌ” የሚለው ቃል "ስግው” ማለትም “ስጋ” ከሚለው የመጣ ነው፣ መለኮት በትስብእት ተገለጠ ብለው ድምዳሜ ላይ ያደረሳቸው ይህ ጥቅስ ነው፦
1 ጢሞቴዎስ 3፥16 እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ *"እርሱ በሥጋ የተገለጠ"*፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ *"በክብር ያረገ"*። (NIV)

እዚህ አንቀጽ ላይ በ 330 ዓመተ-ልደት የተዘጋጀው ኮዴክስ ሳይናቲከስ እና በ 350 ዓመተ-ልደት የተዘጋጀው ኮዴክስ ቫቲካነስ ላይ እንዲህ ተቀምጧል፦
"እርሱ በሥጋ የተገለጠ" Ὃς ἐφανερώθη ἐνσαρκί,

"ሆስ" Oς ማለት አንጻራዊ ተውላጠ-ስም ሲሆን "እርሱ" ማለት ነው፤ "እርሱ" የተባለው "ክርስቶስ" ነው። ነገር ግን በ 400 ዓመተ-ልደት የተዘጋጀው ኮዴክስ አሌክሳንድሪየስ ላይ ሌላ ተቃራኒ ቃል ተቀምጧል፦
"አምላክ በሥጋ የተገለጠ" Θς ἐφανερώθη ἐνσαρκί,

በግሪክ ኮይኔ አስራ አምስተኛው ፊደል "ሆሞክሮን" O መሃል ላይ "አግድም ሰረዝ" - ሲጨመርበት ስምተኛው ፊደል "ቴታ" Θ ይሆናል፤ በአስራ ስምንተኛው ፊደል "ሲግማ" ς መነሻ ላይ ሆሞክሮን ወይንም ቴታ ሲመጡ የትርጉም ልዩነት አላቸው፤ ይህም "ሆስ" Oς ማለትም "ሆሞክሮን ሲግማ" የነበረው "ቴስ" Θς ማለትም "ቴታ ሲግማ" ይሆናል ማለት ነው፤ "ቴስ" Θς የሚለው "ቴኦስ" θεός ለሚለው ምጻረ ቃል ሲሆን "አምላክ" ማለት ነው። እንግዲህ ኮዴክስ አሌክሳንድሪየስ ላይ "ሆስ" Oς (እርሱ) የነበረው "ቴስ" Θς (አምላክ) በማለት በርዘው የትርጉም ልዩነት አምጥተዋል። ሲበርዙ የአምላክ ንግግር ያልሆነውን የጳውሎስንም ንግግር አላስተረፉትም።
እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 1690 ዓመተ-ልደት አይዛክ ኒውተን ሁለት የባይብል ብርዘት ካላቸው መካከል የመጀመሪያው 1 ጢሞቴዎስ 3፥16 ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ 1 ዮሐንስ 5፥7 ናቸው። የሮሙ ቢሾፕ ጄሮም በ 382 ዓመተ-ልደት ባዘጋጀው በላቲን ቩልጌት ላይ ሆነ፥ በ 1611 ዓመተ-ልደት በተዘጋጀው በኪንግ ጀምስ ቨርዥን ላይ፦ "አምላክ በሥጋ የተገለጠ" የሚለውን አስቀምጠውታል። ይህ ስህተት ነው፤ ምክንያቱም 5800 የሚደርሱ የአዲስ ኪዳን የግሪክ እደ-ክታባት አሉ፤ ከኮዴክስ አሌክሳንድሪየስ ውጪ ሁሉም "ቴስ" የሚለውን አይጨምሩም።

ሲቀጥል ብዙ የአዲስ ኪዳን ንባባት፦ አምላክ ተገለጠ ሳይሆን የአምላክ ልጅ ተገለጠ ወይም ሰው ተገለጠ ነው የሚሉት፦
1 ዮሐንስ 3፥9 ስለዚህ የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ *"የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ"*። the Son of God was manifested.
የሐዋርያት ሥራ 2፥22 የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም *ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ"*፤

እግዚአብሔር አንድ ነው፤ ከአንዱ እግዚአብሔር የተገለጠው ሰው ነው፤ እግዚአብሔር ከተገለጠ "ከእግዚአብሔር ዘንድ እግዚአብሔር ተገለጠ" ትርጉም ይሰጣል? ግን የተገለጠ ሰው ነበረ። ስለዚህ በስጋ የተገለጠው የእግዚአብሔር ልጅ የተባለው ሰው ነው።
ሢሰልስ አንቀጹ፦ "በክብር ያረገ" ይላል። "እግዚአብሔር በስጋ ተገለጠ፥ እግዚአብሔር በክብር ያረገ" ትርጉም ይሰጣልን? ምክንያቱም ዐራጊው ማንነት የሚያርገው ወደ እግዚአብሔር ነው፤ ዐርጎም የሚቀመጠው በእግዚአብሔርም ቀኝ ነው፦
ማርቆስ 16፥19 ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ *ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ*።
ዮሐንስ 17፥11 *"እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ"*።
ዮሐንስ 20፥17 *እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ"* ብለሽ ንገሪአቸው፥ አላት።

ልብ አድርጉ ኢየሱስ እራሱን በመጀመሪያ መደብ "እኔ" እያለ እግዚአብሔር ደግሞ በሁለተኛ መደብ "አንተ" እያለ በጸሎት ሲናነጋግረው ተመልከቱ፤ ዓራጊው ኢየሱስ ሲሆን ከሚያርግበት ከእግዚአብሔር ማንነት ለመለየት "ወደ" የሚል መስተዋድድ ተጠቅሟል፤ "ወደ አምላኬ ዓርጋለሁ" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ "አምላኬ" ማለቱ የሚያርገው ማንነት አምላክ አለው። እግዚአብሔር ከሆነ ወደ እግዚአብሔር የሚያርገው እግዚአብሔር አምላክ አለውን? አዎ! ብሎ ማመን ምን አይነት ድራማና ቁማር ነው? ፈጣሪ ፍጡር ሆኖ በተፈጠረ ማንነቱ ተገለጠ ማለት ክህደት ነው። እነዚያ፦ "አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው" ያሉ በእርግጥ ካዱ፦
5፥72 እነዚያ *«አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው»* ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ
5፥17 እነዚያ *"አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው"* ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ቁርኣን ይጋጫልን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

“ኢኽቲላፍ” ٱخْتِلَٰف ማለት “መለያየት” “ግጭት”contradiction” ማለት ነው፤ የአእምሮ ባለቤቶችም ቁርኣን የአላህ ንግግር ብቻ መሆኑን አንዳች መለያየት እንደሌለበት እንዲያስተነትኑ ይጋብዛል፤ የቁርኣን ተናጋሪ የዐለማቱ ጌታ አላህ ነው፤ ቁርኣን ከአላህ ሌላ ከሆነ ማንነትና ምንነት ቢገኝ ኖሮ በውስጡ ብዙ መለያየት በተገኘ ነበር፦
4፥82 *ቁርኣንን አያስተነትኑምን ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በእርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር*፡፡ أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ الْقُرْآنَ ۚ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا

ከዚህ በተቃራኒው ክርስቲያን ሚሽነሪዎች፦ "ቁርኣን እርስ በእርሱ ይጋጫል" ብለው በጥራዝ ነጠቅ ዕውቀት ይዶሶክራሉ፤ ይህ ትችት ባይብል እርስ በእርሱ ስለሚጋጭ ልከክልህ እከክልኝ ነገር ነው። እስቲ ይጋጫል ያሉትን አናቅጽ በጥራዝ ጠለቅ ዕውቀት እናስተንትን፦
ጥያቄውም፦ አላህ ቀድሞ የፈጠረው ምድርን ወይስ ሰማይን?
A. ምድርን
ምድርን ፈጥሮ በምድር ያለውን ከፈጠረ በኃላ ሰማይን ፈጠረ፦
2፥29 *"እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው፡፡ ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ፤ ሰባት ሰማያትም አደረጋቸው"*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ هُوَ الَّذِي خَلَقَ لَكُم مَّا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا ثُمَّ اسْتَوَىٰ إِلَى السَّمَاءِ فَسَوَّاهُنَّ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ ۚ وَهُوَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

B. ሰማይን
ሰማይን ገንብቶ ከፈጠረ በኃላ ምድርን ፈጠረ፦
79፥27 *"ባፈጣጠር እናንተ ይበልጥ የበረታችሁ ናችሁን? ወይንስ ሰማይ? አላህ ገነባት"*፡፡ أَأَنتُمْ أَشَدُّ خَلْقًا أَمِ السَّمَاءُ ۚ بَنَاهَا
79፥30 *"ምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት"*፡፡ وَالْأَرْضَ بَعْدَ ذَٰلِكَ دَحَاهَا

ነጥብ አንድ
"ምድር"
አምላካችን አላህ ምድርን ፈጥሮ በምድር ያለውን ፈጠረ ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ፤ ሰባት ሰማያትም አደረጋቸው፦
2፥29 *"እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው፡፡ ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ፤ ሰባት ሰማያትም አደረጋቸው"*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ هُوَ الَّذِي خَلَقَ لَكُم مَّا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا ثُمَّ اسْتَوَىٰ إِلَى السَّمَاءِ فَسَوَّاهُنَّ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ ۚ وَهُوَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ፦ "በምድር ያለውን ከፈጠረ በኃላ ሰማይ ፈጠረ" የሚል ሽታው የለውም። ከዚህ ይልቅ "ወደ ሰማይ አሰበ" የሚል ሃይለ-ቃል አለ፤ "ኢላ"إِلَى ማለትም "ወደ" የሚለው መስተዋድድ መግባቱ በራሱ ሰማይ እንደነበረች ያሳያል። "ወደ" ፒያሳ አስቤአለው ማለት ፒያሳን ፈጠርኳት ማለት አይደለም፤ ፒያሳ ሳትኖር ወደ ፒያሳ ማቅናት አይቻልም። ሰማይ በህልውና ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፦
41፥11 *"ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፡፡ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው"*፡፡ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ፡፡ ثُمَّ اسْتَوَىٰ إِلَى السَّمَاءِ وَهِيَ دُخَانٌ فَقَالَ لَهَا وَلِلْأَرْضِ ائْتِيَا طَوْعًا أَوْ كَرْهًا قَالَتَا أَتَيْنَا طَائِعِينَ

"ሳለች" የሚለው ሃይለ-ቃል ይሰመርበት፤ ለሰማይም ለምድርም፦ ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ" ማለቱ በራሱ ሰማይ እንደነበረች መረዳት ይቻላል። ከዚያም በጭስ ደረጃ የነበረችውን ሰማይ ሰባት ሰማያት አደረጋቸው፦
41፥12 በሁለት ቀኖችም ውስጥ *"ሰባት ሰማያት አደረጋቸው"*፡፡ فَقَضَاهُنَّ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ فِي يَوْمَيْنِ
2፥29 እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው፡፡ ከዚያም ወደ ሰማይ አሰበ፤ *"ሰባት ሰማያትም አደረጋቸው"*፡፡ እርሱም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ هُوَ الَّذِي خَلَقَ لَكُم مَّا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا ثُمَّ اسْتَوَىٰ إِلَى السَّمَاءِ فَسَوَّاهُنَّ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ ۚ وَهُوَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ
ነጥብ ሁለት
"ከዚያም"
"ሱመ" ثُمَّ ማለትም ከዚያም" የሚለው አያያዥ መስተጻምር ተርቲብ ነው፤ "ተርቲብ" ترتيب ማለት "ቅድመ-ተከተል" ማለት ነው፤ ይህ ቅድመ-ተከተል በሁለት ይከፈላል፤ አንዱ የጊዜ ቅድመ-ተከተል ሲሆን ሁለተኛው የንግግር ቅድመ-ተከተል ነው፤ የንግግር ቅድመ-ተከተል ናሙናዎችን ማየት ይቻላል፦
7፥11 *በእርግጥም ፈጠርናችሁ፥ ከዚያም ቀረጽናችሁ፡፡ ከዚያም ለመላእክት «ለአዳም ስገዱ» አልን*፡፡ ወዲያውም ሰገዱ፡፡ ኢብሊስ ዲያብሎስ ሲቀር ከሰጋጆቹ አልኾነም፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَاكُمْ ثُمَّ صَوَّرْنَاكُمْ ثُمَّ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ لَمْ يَكُن مِّنَ السَّاجِدِينَ

ይህ አንቀጽ ለአደም እና ለሐዋ ቢሆን ኖሮ በሙተና “ኸለቅናኩማ” خَلَقْنَاكُما “ሰወርናኩማ” صَوَّرْنَاكُما ይሆን ነበር፤ ነገር ግን ከሁለት በላይ እኛን ለማሳየት በጀመዕ “ኸለቅናኩም” خَلَقْنَاكُمْ “ሰወርናኩም” صَوَّرْنَاكُمْ ነው የሚለው፤ ከዚያም ለመላእክት ለአደም ስገዱ አለ፤ በጊዜ ቅድመ-ተከተል ካየነው እኛ ከመፈጠራችን በፊት ነው አላህ ለመላእክት፦ "ለአዳም ስገዱ" ያለው፤ ነገር ግን መስተጻምሩ የገባው የንግግር ቅድመ-ተከተል ለማሳየት ስለሆነ "ፈጠርናችሁ" "ቀረጽናችሁ" በንግግር ይቀድማል፦
6፥153 *«ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም፡፡ የጥመት መንገዶችንም አትከተሉ"*፡፡ ከቀጥተኛው መንገዱ እናንተን ይለያዩዋችኋልና፡፡እነሆ ትጠነቀቁ ዘንድ በርሱ አዘዛችሁ፡፡» وَأَنَّ هَـٰذَا صِرَاطِي مُسْتَقِيمًا فَاتَّبِعُوهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعُوا السُّبُلَ فَتَفَرَّقَ بِكُمْ عَن سَبِيلِهِ ۚ ذَٰلِكُمْ وَصَّاكُم بِهِ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُون
6፥154 *"ከዚያም ለሙሳ በዚያ መልካም በሠራው ላይ ለማሟላት ነገርንም ሁሉ ለመዘርዘር መጽሐፉን ለእስራኤል ልጆች መሪና እዝነት ይኾን ዘንድ ሰጠነው*"፡፡ ثُمَّ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ تَمَامًا عَلَى الَّذِي أَحْسَنَ وَتَفْصِيلًا لِّكُلِّ شَيْءٍ وَهُدًى وَرَحْمَةً لَّعَلَّهُم بِلِقَاءِ رَبِّهِمْ يُؤْمِنُون

"ይህም ቀጥተኛ ሲኾን መንገዴ ነው፤ ተከተሉትም" የተባለው ቁርኣን ሲሆን በንግግር ከቁርኣን በኃላ ስለ ተውራት ሲናገር፦ "ከዚያም" የሚል የንግግር ቅድመ-ተከተል ይጠቀማል፤ ያ ማለት ተውራት ከቁርኣን በኃላ መውረዱ ሳይሆን አላህ ስለ ቁርኣን ከተናገረ በኃላ ስለ ተውራት መናገሩ የሚያሳይ ነው፤ በተመሳሳይም አላህ ስለ ምድር ከተናገረ በኃላ ስለ ሰማይ መናገሩ የሚያሳይ ነው። እንደውም "ሱመ" የሚለውን ተርቲብ "እንዲሁ"simultaneously" በሚል ቃል ይመጣል። "እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው፡፡ "እንዲሁ" ወደ ሰማይ አሰበ፤ ሰባት ሰማያትም አደረጋቸው" ብለን መረዳት እንችላለን።

ነጥብ ሦስት
"ሰማይ"
አምላካችም አላህ ሰማይን በኀይል ፈጥሯታል፦
79፥27 *"ባፈጣጠር እናንተ ይበልጥ የበረታችሁ ናችሁን? ወይንስ ሰማይ? አላህ ገነባት"*፡፡ أَأَنتُمْ أَشَدُّ خَلْقًا أَمِ السَّمَاءُ ۚ بَنَاهَا
51፥47 *"ሰማይንም በኀይል ገነባናት"*፡፡ እኛም በእርግጥ ቻዮች ነን፡፡ وَالسَّمَاءَ بَنَيْنَاهَا بِأَيْدٍ وَإِنَّا لَمُوسِعُونَ
91፥5 *"በሰማይቱም በገነባትም ጌታ*፤ وَالسَّمَاءِ وَمَا بَنَاهَا

"በና" بَنَا የሚለው ቃል "ኸለቀ" خَلَقَ ለሚለው ቃል ተለዋዋጭ ቃል ሆኖ እንደመጣ እሙንና ቅቡል ነው። አላህ ሰማይን ጭስ እንድትሆን አድርጎ ከፈጠረ በኃላ ምድርንም ዘረጋት፦
79፥30 *"ምድርንም ከዚህ በኋላ ዘረጋት"*፡፡ وَالْأَرْضَ بَعْدَ ذَٰلِكَ دَحَاهَا

"ፈጠራት" ሳይሆን "ዘረጋት" ነው የሚለው፤ “ዘረጋት” ተብሎ የገባው ቃል “ደሓሃ” دَحَاهَا ሲሆን “ደሓ” دَحَىٰ ደግሞ በቁርኣን ላይ የመጣው በግስ መደብ እዚህ አንቀፅ ላይ ብቻ ነው፤ “ደሓ” በስም መደብ ሲመጣ “አድ-ደሕያ” الدِّحْية ነው፤ ትርጉሙም “የሰጎን እንቁላል” ማለት ነው፤ አላህ ምድርን “የእንቁላል ቅርጽ አደረጋት”He made the earth egg-shaped” የሚል ትርጉም አለው፤ ይህንን አንዳንድ የእንግሊዝኛ ትርጉም ላይ ይገኛል፦
1.Dr. Kamal Omar Translation
“And the earth, after this stage, He gave it *an oval form”*
2. Ali Unal Translation
“And after that He has spread out the earth in *the egg-shape”*
3. Shabbir Ahmed Translation
“And after that He made the earth *egg-shaped"*.
አላህ ምድርን ለእኛ የዘረጋት በርሷም ውስጥ እንመራ ዘንድ መንገዶችን አደረገልን፦
43፥10 *"እርሱ ያ ምድርን "ለእናንተ" ምንጣፍ ያደረገላችሁ በርሷም ውስጥ ትመሩ ዘንድ ለእናንተ መንገዶችን ያደረገላችሁ ነው"*፡፡ الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ الْأَرْضَ مَهْدًا وَجَعَلَ لَكُمْ فِيهَا سُبُلًا لَّعَلَّكُمْ تَهْتَدُونَ
71፥19 *"አላህም ምድርን "ለእናንተ" ምንጣፍ አደረጋት"*፡፡ وَاللَّهُ جَعَلَ لَكُمُ الْأَرْضَ بِسَاطًا

"ለእናንተ" የሚለው ይሰመርበት፤ ለእኛ መንገድ መኪና ስንነዳ ዝርግ ሆኖ የሚታየን ልክ እንደ ምንጣፍ ነው፤ አላህ ሰማይን ከፈጠረ በኃላ ለእኛ የነበረችውን ምድር እንደ ምንጣፍ ዘረጋት። "በዕደ" بَعْدَ ማለትም "ከዚያም" የሚለው ተሳቢ የጊዜ ተውሳከ-ግስ ልክ እንደ "ሱመ" ቅድመ-ተከተል ሲሆን የንግግር ቅድመ-ተከተል ሆኖ ሊመጣ ይችላል፦
68.13 *"ልበ ደረቅን ከዚህ በኋላ ዲቃላን ሁሉ አትታዘዝ*"። عُتُلٍّ بَعْدَ ذَٰلِكَ زَنِيم

እዚህ አንቀጽ ላይ "ልበ ደረቅን እንዲሁ ዲቃላን ሁሉ አትታዘዝ" ተብሎ እንደተቀመጠ ሁሉ "ሰማይንም በኀይል ገነባናት እንዲሁ ምድርንም ዘረጋት" ተብሎ ሊቀመጥ ይችላል።
ስለዚህ ቁርኣን ላይ ግጭት የለም። ይጋጫል የሚል ተሟጋች ካለ ግን ያቀረብነውን ሙግት የሚያስተባብልበት የዐውድ፣ የተዛማች፣ የቋንቋና የሰዋስው ሙግት ማቅረብ ይጠበቅበታል።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
በእኔም በእናንተም ምን እንደሚሠራም ዐላውቅም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

43፥43 ያንንም ወደ አንተ የተወረደልህን አጥብቀህ ያዝ፡፡ *አንተ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነህና*፡፡ فَٱسْتَمْسِكْ بِٱلَّذِىٓ أُوحِىَ إِلَيْكَ ۖ إِنَّكَ عَلَىٰ صِرَٰطٍۢ مُّسْتَقِيمٍۢ

መቼም ሚሽነሪዎች ቆዳዬ ጠበበኝ ብለው የሚያላዝኑት ነገር ቢገርምም የአገራችን ሰዎች ደግሞ እነርሱን በቁርኣን ላይ የሚያነሷቸውን ኂሶች እንደ ገደል ማሚቱ ሲያስተጋቡ ማየት ያስደምማል፤ ሚሽነሪዎች እራሳቸው መጽሐፍት ላይ ያሉትን አበሳና አሳር እንደማይወጡት ስለሚያውቁት በጊዜ ቁርኣን ላይ መደበቁን መርጠዋል፤ የእኛ ጥያቄ ግን ተከድኖ ይብሰል ከተባለ ይኸው ጊዜ አስቆጠረ፤ እኛም ጠቃሚውን ነገር ከማይጠቅም ነገር ጋር ሳይሆን ጠቃሚውን ነገር ከሚጐዳ ነገር ጋር እያነጻጸርነው እንገኛለን። መቼም ስላቅና ፈሊጥ በአሉታዊ ሳይሆን በአውንታዊ ተመልክተን እዳው ገብስ ስለሆነ ሰው እንዲማርበት መልስ እንሰጣለን፤ ወደ ጉዳዩ ስንገባ ነቢያችን”ﷺ” ወሕይ ከመጣላቸው በኃላ በቀጥተኛው መንገድ ላይ እንደሆኑ አምላካችን አላህ ተናግሯል፦
43፥43 ያንንም ወደ አንተ የተወረደልህን አጥብቀህ ያዝ፡፡ *አንተ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነህና*፡፡ فَٱسْتَمْسِكْ بِٱلَّذِىٓ أُوحِىَ إِلَيْكَ ۖ إِنَّكَ عَلَىٰ صِرَٰطٍۢ مُّسْتَقِيمٍۢ

አላህ ነቢያችን”ﷺ” በቀጥተኛ መንገድ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ጀነት ገብተውም በጀነት ያለው ፀጋ እንደሚሰጣቸው ቃል ገብቶላቸዋል፦
108፥1 *እኛ በጣም ብዙ በጎ ነገሮችን ሰጠንህ*፡፡ إِنَّآ أَعْطَيْنَٰكَ ٱلْكَوْثَرَ

በዚህ አንቀጽ ላይ “በጎ ነገር” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ከውሰር” كَوْثَر ሲሆን በጀነት ውስጥ ያለ ከወተት የነጻና ከማር የጣፈጠ ወንዝ ነው፤ ይህ ከውሰር ለነቢያችን”ﷺ” የተሰጠ ዋስትና ነው፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3684
አነስ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፦ “እኛ ከውሰርን ሰጠንህ” ነቢዩም”ﷺ” አሉ፦ *"በጀነት ወንዝ ነው፤ በጀነት ወንዝ ድንኳኖቹ ከድንጋይ የተሠሩ አየው፤ ጂብሪል ሆይ! ምንድን ነው? አልኩት፤ እርሱም ከውሰር ነው፤ አላህ ለአንተ የሰጠህ” አለኝ"*።
عَنْ أَنَسٍ ‏:‏ ‏(‏ إناَّ، أَعْطَيْنَاكَ الْكَوْثَرَ ‏)‏ أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ هُوَ نَهْرٌ فِي الْجَنَّةِ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ فَقَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ رَأَيْتُ نَهْرًا فِي الْجَنَّةِ حَافَتَاهُ قِبَابُ اللُّؤْلُؤِ قُلْتُ مَا هَذَا يَا جِبْرِيلُ قَالَ هَذَا الْكَوْثَرُ الَّذِي قَدْ أَعْطَاكَهُ اللَّهُ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ أَبُو عِيسَى هَذَا حَدِيثٌ حَسَنٌ صَحِيحٌ


ነቢያችን”ﷺ” ጀነት አይደለም መግባት በተጨማሪ የጀነት ጀረጃቸውንም አላህ እንደነገረን ከላይ ያለው አንቀጽ በወፍ በረር ለቅምሻ ያክል በቂ ነው፤ ታዲያ ይህ ዋስትና እያለ አላህ ነቢያችንን”ﷺ” “በእኔም በእናንተም ምን እንደሚሠራም ዐላውቅም” በል ሲላቸው እውን ሚሽነሪዎች እንደሚሉት "ወደ ፊት የት እንደምንገባ ዐናውቅም" በል ማለታቸውን ያሳያልን? ይህንን የተንሸዋረረና የተወላገደ መረዳት ጥንልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ እንየው፦
46፥9 *ከመልክተኞች ብጤ የሌለኝ አይደለሁም፤ በእኔም በእናንተም ምን እንደሚሠራም ዐላውቅም፤ ወደ እኔ የሚወረደውን እጅግ ሌላን አልከተልም፤ እኔም ግልጽ አስጠንቃቂ እንጅ ሌላ አይደለሁም* በላቸው። قُلْ مَا كُنتُ بِدْعًۭا مِّنَ ٱلرُّسُلِ وَمَآ أَدْرِى مَا يُفْعَلُ بِى وَلَا بِكُمْ ۖ إِنْ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ وَمَآ أَنَا۠ إِلَّا نَذِيرٌۭ مُّبِينٌۭ

ነጥብ አንድ
“ብጤ የሌለኝ አይደለሁም”
ከነቢያችን”ﷺ” በፊት የመጡት በእርግጥ ምግብን የሚበሉ፣ በገበያዎችም የሚሄዱ ሰዎች ነበሩ፣ በተመሳሳይም ነቢያችን”ﷺ” ሰው ናቸው፣ በደረጃ እንጂ በሃልዎት ከሰው የተለዩ አልነበሩም፣ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የሆኑ መልክተኛ ነበሩ፦
36፥3 አንተ በእርግጥ *ከመልክተኞቹ ነህ*። إِنَّكَ لَمِنَ ٱلْمُرْسَلِينَ
2፥252 አንተም *በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነህ*፡፡ وَإِنَّكَ لَمِنَ ٱلْمُرْسَلِينَ
3፥144 ሙሐመድም *ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የሆነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም*፤ وَمَا مُحَمَّدٌ إِلَّا رَسُولٌۭ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ ٱلرُّسُلُ
ነጥብ ሁለት
“ዐላውቅም”
ነቢያችን”ﷺ” በራሳቸውና በሰዎች ምን እንደሚከናወን የወደፊቱን ዐያውቁም፣ ያ ማለት ሰዎች የሚያስጠነቅቁበት ቅርብ ይሁን እሩቅ ዐያውቁም፣ ከሚወርድላቸው ግህደተ-መለኮት ውጪ ምንም ዐያውቁም፦
6፥50 «ለእናንተ የአላህ ግምጃ ቤቶች እኔ ዘንድ ናቸው አልልም፡፡ *ሩቅንም አላውቅም*፡፡ ለእናንተም እኔ መልአክ ነኝ አልልም፡፡ *ወደ እኔ የሚወርድልኝን እንጅ ሌላን አልከተልም*» በላቸው፡፡ قُل لَّآ أَقُولُ لَكُمْ عِندِى خَزَآئِنُ ٱللَّهِ وَلَآ أَعْلَمُ ٱلْغَيْبَ وَلَآ أَقُولُ لَكُمْ إِنِّى مَلَكٌ ۖ إِنْ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ ۚ قُلْ هَلْ يَسْتَوِى ٱلْأَعْمَىٰ وَٱلْبَصِيرُ ۚ أَفَلَا تَتَفَكَّرُونَ
7፥188 አላህ የሻውን በስተቀር ለራሴ ጥቅምንም፣ ጉዳትንም፣ ማምጣት አልችልም፣ *ሩቅንም የማውቅ በነበርኩ ኖሮ* ከመልካም ነገር ባበዛሁና ክፉም ነገር ባልነካኝ ነበር፤ እኔ ለሚያምኑ ሕዝቦች አስጠንቃቂና አብሳሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም”* በላቸው። قُل لَّآ أَمْلِكُ لِنَفْسِى نَفْعًۭا وَلَا ضَرًّا إِلَّا مَا شَآءَ ٱللَّهُ ۚ وَلَوْ كُنتُ أَعْلَمُ ٱلْغَيْبَ لَٱسْتَكْثَرْتُ مِنَ ٱلْخَيْرِ وَمَا مَسَّنِىَ ٱلسُّوٓءُ ۚ إِنْ أَنَا۠ إِلَّا نَذِيرٌۭ وَبَشِيرٌۭ لِّقَوْمٍۢ يُؤْمِنُونَ
21፥109 እምቢም ቢሉ በማወቅ በእኩልነት ላይ ሆነን የታዘዝኩትን አስታወቅኋችሁ፤ *የምትስፈራሩበትም ነገር ቅርብ፣ ወይም ሩቅ፣ መሆኑን ዐላውቅም*፤ በላቸው። فَإِن تَوَلَّوْا۟ فَقُلْ ءَاذَنتُكُمْ عَلَىٰ سَوَآءٍۢ ۖ وَإِنْ أَدْرِىٓ أَقَرِيبٌ أَم بَعِيدٌۭ مَّا تُوعَدُونَ
21፥111 እርሱም *ቅጣትን ማቆየት ምናልባት ለእናንተ ፈተናና እስከ ጊዜው መጣቀሚያ እንደኾነም “አላውቅም”*፤ በላቸው። وَإِنْ أَدْرِى لَعَلَّهُۥ فِتْنَةٌۭ لَّكُمْ وَمَتَٰعٌ إِلَىٰ حِينٍۢ

ነጥብ ሶስት
“ሚወረደው”
ወደ ነቢያችን”ﷺ” የሚወርደው ለቀደሙት መልክተኞች የሚወርደው የነበረው የአንድ አምላክ አስተምህሮት ነው፣ ከነቢያችን"ﷺ" በፊት ለነበሩት መልክተኞች የተባለው ይህ የተውሒድ ተስተምህሮት ነው ነቢያችን”ﷺ” የሚከተሉት፦
21፥108 «ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ *”አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው”* ማለት ነው፤ ታዲያ እናንተ ፍጹም “ታዛዦች” ናችሁን» *በላቸው*፡፡ قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ
18፥110 እኔም ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚወረድልኝ፦ *”አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው” ማለት ነው”*፤ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም አምልኮ አንድንም አያጋራ» *”በላቸው”*፡፡ قُلْ إِنَّمَآ أَنَا۠ بَشَرٌۭ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَمَن كَانَ يَرْجُوا۟ لِقَآءَ رَبِّهِۦ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًۭا صَٰلِحًۭا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِۦٓ أَحَدًۢا
21፥25 ከአንተ በፊትም፣ እነሆ *ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ፣ በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢሆን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም*። وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ
41፥43 ከአንተ በፊት ለነበሩት መልክተኞች *የተባለው ቢጤ* እንጅ ለአንተ ሌላ አይባልም፤ مَّا يُقَالُ لَكَ إِلَّا مَا قَدْ قِيلَ لِلرُّسُلِ مِن قَبْلِكَ ۚ إِنَّ رَبَّكَ لَذُو مَغْفِرَةٍۢ وَذُو عِقَابٍ أَلِيمٍۢ
ነጥብ አራት
“አስጠንቃቂ”
አላህ የነቢያችን”ﷺ” ቢጤዎች መልክተኞችን አብሳሪና አስጠንቃቂ አድርጎ ከነቢያችን”ﷺ” በፊት ልኳል፦
18፥56 መልክተኞችንም *አብሳሪዎችና አስጠንቃቂዎች* ሆነው እንጂ አንልክም፤ وَمَا نُرْسِلُ ٱلْمُرْسَلِينَ إِلَّا مُبَشِّرِينَ وَمُنذِرِين
4፥165 ከመልክተኞቹ በኋላ ለሰዎች በአላህ ላይ አስረጅ እንዳይኖር *አብሳሪዎችና አስጠንቃቂዎች* የሆኑን መልክተኞች ላክን፤ رُّسُلًۭا مُّبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَ لِئَلَّا يَكُونَ لِلنَّاسِ عَلَى ٱللَّهِ حُجَّةٌۢ بَعْدَ ٱلرُّسُلِ ۚ وَكَانَ ٱللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمًۭا
2፥213 አላህም ነቢያትን *አብሳሪዎችና አስጠንቃቂዎች* አድርጎ ላከ፡፡ وَٰحِدَةًۭ فَبَعَثَ ٱللَّهُ ٱلنَّبِيِّـۧنَ مُبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَ

በተመሳሳይ መልኩ በጀነት አብሳሪ በጀሃነም አስጠንቃቂ ይሆኑ ዘንድ ነቢያችንን”ﷺ” አብሳሪና አስጠንቃቂ አድርጎ ልኳል፦
2፥119 እኛ *አብሳሪና አስጠንቃቂ* ኾነህ በእውነት ላክንህ፡፡ ከእሳትም ጓዶች አትጠየቅም፡፡ إِنَّآ أَرْسَلْنَٰكَ بِٱلْحَقِّ بَشِيرًۭا وَنَذِيرًۭا ۖ وَلَا تُسْـَٔلُ عَنْ أَصْحَٰبِ ٱلْجَحِيمِ
34፥28 አንተንም ለሰዎች ሁሉ በሙሉ *አብሳሪና አስጠንቃቂ* አድርገን ቢሆን እንጂ አላክንህም፤ وَمَآ أَرْسَلْنَٰكَ إِلَّا كَآفَّةًۭ لِّلنَّاسِ بَشِيرًۭا وَنَذِيرًۭا وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ
33፥45 አንተ ነቢዩ ሆይ! እኛ መስካሪ *አብሳሪና አስጠንቃቂ* አድርገን ላክንህ። يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ إِنَّآ أَرْسَلْنَٰكَ شَٰهِدًۭا وَمُبَشِّرًۭا وَنَذِيرًۭا

አላህም፦ ”አላህን እንጂ ሌላን አታምልኩ፤ አንድ ከኾነው አላህ በቀር ምንም አምላክ የለም፤ እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላክሁ አስጠንቃቂ ነኝ” በል በማለት አስጠንቃቂ መሆናቸውን አውርዷል፦
11፥2 እንዲህ በላቸው ፦ አላህን እንጂ ሌላን አታምልኩ፤ *እኔ ለእናንተ ከእርሱ የተላክሁ አስጠንቃቂ ነኝ*። أَلَّا تَعْبُدُوٓا۟ إِلَّا ٱللَّهَ ۚ إِنَّنِى لَكُم مِّنْهُ نَذِيرٌۭ وَبَشِيرٌۭ
22፥49 ፦ እላንተ ስዎች ሆይ እኔ ለእናንተ *ግልጽ አስጠንቃቂ ብቻ ነኝ*፣ በላቸው። قُلْ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّمَآ أَنَا۠ لَكُمْ نَذِيرٌۭ مُّبِينٌۭ

ስለዚህ ከላይ ያለውን አንቀጽ የወረደበትም ዐውድ ስንመለከተው ነቢያችን”ﷺ” ጀነት ስለ አለመግባታቸው ምንም የሚያወራው ነገር የለም። ዐውዱ ለማስተላለፍ የፈለገውን በግድ ጠምዝዞ ይህን ለማለት ነው የፈለገው ብሎ ማጣመም ከሥነ-አፈታት ጥናት “hermeneutics” ጋር መላተም እና የደፈረሰ የተሳከረ መረዳት ነው፣ ይህ ሙግት የዐውድ ሙግት”contextual approach” ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሶላት

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

4፥103 *“ሶላት” በምእመናን ላይ “በጊዜያት” የተወሰነች ግዴታ ናትና"*። إِنَّ الصَّلَاةَ كَانَتْ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ كِتَابًا مَّوْقُوتًا

ከአምስቱ የኢሥላም ምሰሶዎች አንዱ ሶላት ነው፤ "ሶላት" صَّلَاة ማለት "የግዴታ ጸሎት" ማለት ነው። በእርግጥም ሶላት በአምስት ወቅት የሚፈጸም ነው፤ ሶላት በምእመናን ላይ “በጊዜያት” የተወሰነ ፈርድ ነው፦
4፥103 *“ሶላት” በምእመናን ላይ “በጊዜያት” የተወሰነች ግዴታ ናትና"*። إِنَّ الصَّلَاةَ كَانَتْ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ كِتَابًا مَّوْقُوتًا

ነቢያችንም"ﷺ" በሐዲስ በጊዜያት የተወሰኑትን የሶላት ወቅት ዘርዝረውልናል፦
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 2 , ሐዲስ 3
አቢ ሁራይራ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በእርግጥም ሶላት ጅማሬ አለው ፍጻሜ አለው፤ የሶላቱ አዝ-ዙሁር ወቅት የሚጀምረው ጸሐይ በአናት ትይዩ ማለፍ ከጀመረችበት ነው፥ የሚጨርሰውም እስከ ዐስር መግቢያ ድረስ ነው። የሶላቱል ዐስር ወቅት የሚጀምረው ከጸሐይ መዘንበል ከጀመረችበት ነው፥ የሚጨርሰውም እስከ ጸሐይ መግቢያ ድረስ ነው። የሶላቱል መግሪብ ወቅት የሚጀምረው ከጸሐይ መጥለቅ ከጀመረችበት ነው፥ የሚጨርሰውም እስከ ፊተኛው ሌሊት ድረስ ነው። የሶላቱል ዒሻዕ ወቅት የሚጀምረው ከፊተኛው ሌሊት ማታ ከጀመረችበት ነው፥ የሚጨርሰውም እስከ ሁለተኛይቱ ሌሊት ድረስ ነው። የሶላቱል ፈጅር ወቅት የሚጀምረው ጎህ ከጀመረችበት ነው፥ የሚጨርሰውም እስከ ጸሐይ መውጣት ድረስ ነው"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ إِنَّ لِلصَّلاَةِ أَوَّلاً وَآخِرًا وَإِنَّ أَوَّلَ وَقْتِ صَلاَةِ الظُّهْرِ حِينَ تَزُولُ الشَّمْسُ وَآخِرَ وَقْتِهَا حِينَ يَدْخُلُ وَقْتُ الْعَصْرِ وَإِنَّ أَوَّلَ وَقْتِ صَلاَةِ الْعَصْرِ حِينَ يَدْخُلُ وَقْتُهَا وَإِنَّ آخِرَ وَقْتِهَا حِينَ تَصْفَرُّ الشَّمْسُ وَإِنَّ أَوَّلَ وَقْتِ الْمَغْرِبِ حِينَ تَغْرُبُ الشَّمْسُ وَإِنَّ آخِرَ وَقْتِهَا حِينَ يَغِيبُ الأُفُقُ وَإِنَّ أَوَّلَ وَقْتِ الْعِشَاءِ الآخِرَةِ حِينَ يَغِيبُ الأُفُقُ وَإِنَّ آخِرَ وَقْتِهَا حِينَ يَنْتَصِفُ اللَّيْلُ وَإِنَّ أَوَّلَ وَقْتِ الْفَجْرِ حِينَ يَطْلُعُ الْفَجْرُ وَإِنَّ آخِرَ وَقْتِهَا حِينَ تَطْلُعُ الشَّمْسُ

እዚህ ሐዲስ ላይ የተጠቀሱትን አምስት ወቅት ሶላት፦ ሶላቱል ፈጅር፣ ሶላቱ አዝ-ዙሁር፣ ሶላቱል ዐስር፣ ሶላቱል መግሪብ እና ሶላቱል ዒሻዕ ከቁርኣን ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
"ፈጅር"
“ፈጅር” فَجْر ማለት “ጎህ” ማለት ሲሆን አምላካችን አላህ ይህን የጎህ ወቅት በሶላት እንድንቆም ያዘናል፦
17፥78 ሶላትን ከፀሐይ መዘንበል እስከ ሌሊት ጨለማ ድረስ ስገድ፤ *“የጎህ ሰላት ስገድ፣ የጎህ ሶላት መላእክት የሚጣዱት ነውና"*። أَقِمِ الصَّلَاةَ لِدُلُوكِ الشَّمْسِ إِلَىٰ غَسَقِ اللَّيْلِ وَقُرْآنَ الْفَجْرِ ۖ إِنَّ قُرْآنَ الْفَجْرِ كَانَ مَشْهُودًا
24፥58 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያ እጆቻችሁ የጨበጧቸው እነዚያም ከእናንተ ለአካላ መጠን ያልደረሱት *ከጎህ ስግደት" በፊት፣ በቀትርም ልብሶቻችሁን በምታወልቁ ጊዜ ከምሽት ስግደትም* በኋላ ሦስት ጊዜያት ለመግባት ሲፈልጉ ያስፈቅዷችሁ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لِيَسْتَأْذِنكُمُ الَّذِينَ مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ وَالَّذِينَ لَمْ يَبْلُغُوا الْحُلُمَ مِنكُمْ ثَلَاثَ مَرَّاتٍ ۚ مِّن قَبْلِ صَلَاةِ الْفَجْرِ وَحِينَ تَضَعُونَ ثِيَابَكُم مِّنَ الظَّهِيرَةِ وَمِن بَعْدِ صَلَاةِ الْعِشَاءِ ۚ ثَلَاثُ عَوْرَاتٍ لَّكُم

ጌታችን አላህ ሶላቱል ፈጅርን ለማመልከት፦ “በምታነጉ ጊዜ” “በማለዳም” “በምትንነሳ ጊዜ” “ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት” በማለት በአፅንኦትና በአንክሮት ይናገራል፦
30፥17 *"አላህንም በምታመሹ ጊዜ "በምታነጉም ጊዜ" አጥሩት*"፡፡ فَسُبْحَانَ اللَّهِ حِينَ تُمْسُونَ وَحِينَ تُصْبِحُونَ
40፥55 ታገስም የአላህ ተስፋ እውነት ነውና፡፡ ለስህተትህም ምሕረትን ለምን፡፡ ከቀትር በኋላ በማታም *"በማለዳም" ጌታህን ከማመስገን ጋር አጥራው"*፡፡ فَاصْبِرْ إِنَّ وَعْدَ اللَّهِ حَقٌّ وَاسْتَغْفِرْ لِذَنبِكَ وَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ بِالْعَشِيِّ وَالْإِبْكَارِ
52:48 ለጌታህ ፍርድም ታገሥ፡፡ አንተ በጥበቃችን ውስጥ ነህና፡፡ *"ጌታህንም "በምትነሳ ጊዜ" ከማመስገን ጋር አወድሰው"*፡፡ وَاصْبِرْ لِحُكْمِ رَبِّكَ فَإِنَّكَ بِأَعْيُنِنَا ۖ وَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ حِينَ تَقُومُ
50፥39 በሚሉትም ላይ ታገሥ፤ ጌታህንም ከማመስገን ጋር *"ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት"* ከመግባቷም በፊት አወድሰው፡፡ فَاصْبِرْ عَلَىٰ مَا يَقُولُونَ وَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ قَبْلَ طُلُوعِ الشَّمْسِ وَقَبْلَ الْغُرُوبِ
20፥130 በሚሉትም ላይ ታገስ፡፡ ጌታህንም *"ፀሐይ ከመውጣትዋ በፊት"* ከመግባትዋም በፊት የምታመሰግን ኾነህ አጥራው፤ ከሌሊት ሰዓቶችም በቀን ጫፎችም አጥራው፡፡ በሚሰጥህ ምንዳ ልትወድ ይከጀላልና፡፡ فَاصْبِرْ عَلَىٰ مَا يَقُولُونَ وَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ قَبْلَ طُلُوعِ الشَّمْسِ وَقَبْلَ غُرُوبِهَا ۖ وَمِنْ آنَاءِ اللَّيْلِ فَسَبِّحْ وَأَطْرَافَ النَّهَارِ لَعَلَّكَ تَرْضَىٰ