ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
69 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
የእግዚአብሔር ልጅ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

18፥4 *እነዚያንም፦ “አላህ ልጅን ይዟል” ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት አወረደው*፡፡ وَيُنذِرَ الَّذِينَ قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا

ክርስቲያኖች ኢየሱስ “የእግዚአብሔር ልጅ” ነው ይላሉ፤ “ልጅ” ማለት ምን ማለት ነው? ስንላቸው፦ “አብን አህሎና መስሎ ከአብ “ባህርይ ዘእም-ባህርይ አካል ዘእም-አካል” ማለትም ከባህርይው ባህርይ ወስዶ ከአካሉ አካሉን ወስዶ ተወለደ” ይሉናል። እረ ከሰማናቸው፦ “አምላክ ዘእም-አምላክ ማለትም ከአምላክ የተገኘ አምላክ” ይሉናል። ከእዚህ እሳቤ ቁርኣን በተቃራኒው፦ “አላህ ወለደ” ያሉ በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፤ አላህ አልወለደም፤ አልተወለደምም፤ እንደውም አላህ ቁርኣን ካወረደበት ምክንያት አንዱ እነዚያንም፦ “አላህ ልጅን ይዟል” ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት ነው፦
37፥152 ፦ *“አላህ ወለደ” አሉ፤ እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው*፡፡ وَلَدَ اللَّهُ وَإِنَّهُمْ لَكَاذِبُونَ
112፥3 *አልወለደም፤ አልተወለደምም*፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ
18፥4 *እነዚያንም፦ “አላህ ልጅን ይዟል” ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት አወረደው*፡፡ وَيُنذِرَ الَّذِينَ قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا

ይህንን የቁርኣን እሳቤ ካየን ዘንዳ ባይብል ላይ እግዚአብሔር አባት መባሉ “አስገኚ” ወይም “ፈጣሪ” በሚል ፍካሬአዊ ቃል መጥቷል፦
ሚልክያስ 2፥10 ለሁላችን *”አንድ አባት”* ያለን አይደለምን? *አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን*?
ዮሐንስ 8፥41 *አንድ አባት* አለን *እርሱም እግዚአብሔር ነው*፡ አሉት።
ኤፌሶን 4፥6 ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር *አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ*።

ለምሳሌ መላእክት መናፍስት ተብለዋል፤ እግዚአብሔር የመናፍስት አባት ነው። መናፍስቱ መላእክት የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው፦
ዕብራውያን 12፥9 እንዴትስ ይልቅ *ለመናፍስት አባት* አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን?
ዕብራውያን 1፥14 *ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?*
ኢዮብ 38፥7 አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥ *የእግዚአብሔርም ልጆች* ሁሉ እልል ሲሉ፥

መላእክት የእግዚአብሔር ልጆች የተባሉት ያለ እናት እና ያለ አባት ስለፈጠራቸው እንደሆነ ቅቡል ነው፤ አዳምም የእግዚአብሔር ልጅ ተብሏል፦
ሉቃስ 3፥38 የሴት ልጅ፥ የአዳም ልጅ፥ *የእግዚአብሔር ልጅ*።

አዳም የእግዚአብሔር ልጅ የተባለው ያለ እናት እና ያለ አባት ስለፈጠረው እንደሆነ እሙን ነው፤ ታዲያ ያለ አባት በእናት ብቻ የተፈጠረው ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ቢባል ምን ይደንቃል? ከማርያም ተጸንሶ የተወለደው ሰው መሆኑን አንርሳ፦
ሉቃስ 1፥35 ስለዚህ ደግሞ *ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል*።
ገላትያ 4 ፥4 ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ *እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ*፤

ማርያም የወለደችው መለኮትን ሳይሆን ሰው ብቻ ነው፤ ያም ሰው የእግዚአብሔር ልጅ መባሉ ፈጣሪ ያለ አባት ከእርሷ መፍጠሩን ያሳያል። አይ እግዚአብሔር ኢየሱስን ወለደው ይሉናል፦
መዝሙር 2፥7 ትእዛዙን እናገራለሁ፤ *እግዚአብሔር አለኝ። አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ “ወለድሁህ”*።
ዕብራውያን 1:5 ከመላእክትስ። *እግዚአብሔር አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ “ወልጄሃለሁ”*፥ (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ጭራሽ ይህ ጥቅስ “ዛሬ” የምትለዋ ቃል መነሻ ጊዜን ታመለክታለች፣ ይህም የኢየሱስ መፈጠር በጊዜ ውስጥ መሆኑን ያሳያል፤ ሲቀጥል እዚህ ጥቅስ ላይ እግዚአብሔር ኢየሱስን፦ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ” ብሏል ተብሏል፤ ይህ የሚያሳየው ኢየሱስ “አንተ” ብሎ ካናገረው እግዚአብሔር የተለየ መሆኑን ያሳያል፣ እግዚአብሔር ለኢየሱስ “አባት እሆነዋለው” ኢየሱስ ለእግዚአብሔር “ልጅ ይሆነኛል” ብሏል ተብሏል” ሲሰልስ “ወልጄሃለሁ” የሚለው ቃል “ጌኔካ” γεγέννηκά ሲሆን “ጌኑስ” γένος ማለትም “ወለደ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን በፍካሬአዊ ትርጉም “ፈጠረ” ሲሆን አይሁዳውያን አምላክ ፆታ ስለሌለውን “መወለድ” ማለት “መፈጠር” ነው ብለው ያምናሉ፤ ምክንያቱን ተራራ እንደተወለደ ስለሚናገር፤ ያ ማለት ተራራ ተሰራ ማለት ነው፦
አሞፅ 4:13 እነሆ፥ *”ተራሮችን የሠራ”*፥
መዝሙር 90:2 *”ተራሮች ሳይወለዱ”*፥ בְּטֶרֶם, הָרִים יֻלָּדו
ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦
πρὸ τοῦ ὄρη γενηθῆναι καὶ πλασθῆναι τὴν γῆν καὶ τὴν οἰκουμένην,
በዕብራይስጡ “ዩላዱ” יֻלָּדו ማለት “ሳይወለዱ” ማለት ነው። “ሳይወለዱ” የሚለው ፍካሬአዊ ቃል በእማሬያዊ ቃል “ሳይፈጠሩ” ማለት ነው። ግሪክ ሰፕቱአጀንት ላይ ደግሞ በተመሳሳይ “ጌኒቲና” γενηθηναι ማለትም “ሳይወለዱ” የሚለው በተመሳሳይ “ጌኑስ” γένος ማለትም “ወለደ” ከሚል ግስ የመጣ ነው፤ “ወለደ” ማለት “ፈጠረ” ማለት መሆኑን “የወለደህን አምላክ” የሚለው ቃል “የፈጠረውን አምላክ” በሚል ተለዋዋጭ ቃል መምጣቱ ነው፦
ዘዳግም 32፥18 *የወለደህን አምላክ ተውህ*፥ NIV
ዘዳግም 32፥15 ይሹሩን ወፈረ፥ ረገጠ፤ ወፈረ፥ ደነደነ፥ ሰባ፤ *የፈጠረውንም አምላክ ተወ*፤ NIV

“ይሽሩ” የእስራኤላውያን የቁልምጫ ስም ነው፤ አምላክ እስራኤላውን “ወለደ” ወይስ “ፈጠረ” ? አይ ፈጣሪ ጾታ ስለሌለው በእማሬአዊ ቃል ወለደ ማለት ሳይሆን በፍካሬአዊ ቃል ፈጠረ ለማለት ነው ከተባለ እንግዲያውስ ከላይ ያለውንም በዚህ ስሌትና ቀመር ተረዱት። አንዳንድ ቂሎች “መወለድ” ከአብ “መውጣት” ነው ይላሉ፤ ምነው መንፈስ ቅዱስ ከአብ የሚወጣ ነው ትሉ የለ እንዴ? ለምን መንፈስ ቅዱስን የአብ ልጅ አትሉትም? አይ “መውጣት” ማለት “መስረጽ” ነው ካላችሁ ለምንስ ወልድን ከአብ የሰረጸ ነው አትሉትም? ምክንያቱም ወልድም ከአብ የወጣ ነው ስለሚል፤ አይ መውጣት መላክ ማለት ነው ካላችሁ ጥሩ። ካልሆነ ልጅ ማለት፦ “አብን አህሎና መስሎ ከአብ ባህርይ ዘእም-ባህርይ አካል ዘእም-አካል ማለትም ከባህርይው ባህርይ ወስዶ ከአካሉ አካሉን ወስዶ ተወለደ፤ አምላክ ዘእም-አምላክ ማለትም ከአምላክ የተገኘ አምላክ” ካላችሁ ይህንን እሳቤ አይደለም ቁርኣን ባይብላችሁም አይደግፋችሁ። በዚህ ስሌት ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፦
19፥35 *ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ ከጉድለት ሁሉ ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል*፡፡ مَا كَانَ لِلَّهِ أَن يَتَّخِذَ مِن وَلَدٍ ۖ سُبْحَانَهُ ۚ إِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ
2፥116 *አላህም ልጅ አለው አሉ፡፡ ከሚሉት ጥራት ተገባው፡፡ አይደለም በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ሁሉም ለእርሱ ታዛዦች ናቸው*፡፡ وَقَالُوا۟ ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ وَلَدًۭا ۗ سُبْحَٰنَهُۥ ۖ بَل لَّهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۖ كُلٌّۭ لَّهُۥ قَٰنِتُونَ
2፥117 ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ *ነገርንም ማስገኘት በሻ ጊዜ ለእርሱ የሚለው፡- «ኹን» ነው፤ ወዲያውም ይኾናል*፡፡ بَدِيعُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አባት እና ልጅ

ገቢር አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

112፥3 *አልወለደም አልተወለደም*። لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ

“ዋሊዳእ” وَٰلِدَي ማለት “ወላጅ” ማለት ነው፤ አባት የሆነ ወላጅ “ዋሊድ” وَالِد ወይም “መውሉድ” مَوْلُود ሲባል እናት የሆነች ወላጅ ደግሞ “ዋሊዳ” وَٰلِدَٰت ወይም “ዋሊደ” وَٰلِدَة ትባላለች፤ ከወላጅ የሚገኝ ልጅ ደግሞ “ወለድ” وَلَد ወይም “ወሊድ” وَلِيد ይባላል፤ ሁሉም የስም መደብ የመጡት “ወለደ” وَلَدَ ማለትም “ወለደ” ከሚል ግስ የመጡ ናቸው። አላህ ፃታ የለውም፤ ወንድም ሴትም አይደለም፤ አባት ሆኖ አልወለደም ልጅ ሆኖ አልተወለደም፦
112፥3 *አልወለደም አልተወለደም*። لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ

የሥላሴ አማንያን ኢየሱስ ልጅ ሲሆን አባቱ እግዚአብሔር ነው ይላሉ፤ ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር አብን መስሎና አህሎ ከአብ ማንነትና ምንነት የተገኘ ነው የሚል እሳቤ አላቸው፤ “ተወለደ” ሲባል “ተገኘ” ማለት ነው ይሉናል፤ አብ ማለት “አስገኚ” ሲሆን ወልድ ደግሞ “ግኝት” ማለት ነው፤ በ 325 AD የተሰበሰበው የኒቅያ ጉባኤም፦
በግሪክ፦
Φῶς ἐκ Φωτός, Θεὸν ἀληθινὸν ἐκ Θεοῦ ἀληθινοῦ,
በግዕዝ፦
“ብርሃን ዘእም-ብርሃን፤ አምላክ ዘእም-አምላክ”
በአማርኛ፦
*“ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፤ ከአምላክ የተገኘ አምላክ”* ብሎታል።

አምላክ አምላክን ካስገኘ ሁለት አምላክ አይሆንም ወይ? አምላክ ተገኘ የሚለው ሲያስገርም አምላክ ተፈጠረ ደግሞ ያስደምማል፦
አማርኛ፦
ምሳሌ 8፥22 *እግዚአብሔር ከሁሉ በፊት ፈጠረኝ*፥ (1980 አዲስ ትርጉም)
ግዕዝ፦
ምሳሌ 8፥22 “ፈጠረኒ እግዚእ መቅድመ ተግባሩ”
ኢንግሊሽ፦
Proverbs 8፥22 “The LORD made me as he began his planning, (International Standard Version)
ዕብራይስጥ፦
ምሳሌ 8፥22 יְהוָה–קָנָנִי, רֵאשִׁית דַּרְכּוֹ: קֶדֶם מִפְעָלָיו מֵאָז.
ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦
Proverbs 8፥22 κύριος ἔκτισέν με ἀρχὴν ὁδῶν αὐτοῦ εἰς ἔργα αὐτοῦ

በተለይ በግሪኩ ሰፕቱአጀንት”LXX” ላይ “ኪትዞ” ἔκτισέν ማለት “ፈጠረኝ” ማለት ነው፤ በተመሳሳይ ዕብራይስጡ “ቃናኒ” קָ֭נָנִי ማለት “አስገኘኝ” ማለት ነው፤ ይህ ቃል ሔዋን “አገኘሁ” ብላ ለተጠቀመችበት የዋለው ቃል “ቃኒቲ” קָנִ֥יתִי ሲሆን ዳዊት ደግሞ ኲላሊቴን “ፈጥረሃል” ለሚለው የተጠቀመው “ቃኒታ” קָנִ֣יתָ ብሎ ነው፦
ዘፍጥረት 4፥1 ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር *አገኘሁ* קָנִ֥יתִי አለች።
መዝሙር 139፥13 አቤቱ፥ አንተ ኵላሊቴን *ፈጥረሃልና* קָנִ֣יתָ ፥
ዘዳግም 32፥6፤ ለእግዚአብሔር ይህንን ትመልሳለህ? የገዛህ አባትህ አይደለምን? *የፈጠረህ* קָּנֶ֔ךָ እና ያጸናህ እርሱ ነው።
የመጨረሻው ጥቅስ ላይ “የፈጠረክ” ለሚለው የገባው “ቃነካ” קָּנֶ֔ךָ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። እግዚአብሔር “የገዛህ አባትህ” መባሉ “አባት” ማለት ለእግዚአብሔር ፈጣሪ ማለት እንደሆነ ይህ ጥቅስ ያስረዳል።
እንግዲህ “መገኘት” እና “መፈጠር” ተለዋዋጭ ቃል ከሆነ ኢየሱስ ፍጡር እና ግኝት እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል። ይህንን ጥቅስ ተሃድሶና እና ፕሮቴስታት ስለ ኢየሱስ አይደለም ብለው ሽምጥጥ አርገው ቢክዱም፤ ቀደምት ኦርቶዶክስ፣ካቶሊክ፣ አንግሊካን እና የኒቂያ ጉባኤ ስለ ኢየሱስ ፍጥረት ሳይፈጠር መወለዱን ያሳያል ይላሉ፤ በ 325 AD በኒቂያ ጉባኤ አርዮስንና አትናቲዎስ ኢየሱስ ፍጡር ነው ወይስ አይደለም ለሚለው ክርክራቸው ይህ ጥቅስ ነበር፤ አንዳንድ ኦርቶዶክሳውያንም ይህ ስለ ኢየሱስ አይደለም ብለው ሊያቅማሙ ሲሞክሩ አንድምታው ሆነ ሃይማኖተ-አበው አጋልጧቸዋል፤ ቄርሎስ በሃይማኖተ-አበው ላይ ለኢየሱስ ነው ይለናል፦
ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 76:12
ቄርሎስም አለ፦
“ተፈጥረ ጥበብ ዘውእቱ ቃል”
ትርጉም፦
*“ጥበብ ተፈጠረ ይኸውም ቃል ነው”*
ቄርሎስም አለ፦
“ወይእዜኒ ጥበብ ትቤ ፈጠረኒ እግዚእ መቅድመ ተግባሩ”
ትርጉም፦
*“ከፍጥረት አስቀድሞ የነበርኩኝ በቀድሞ ተግባሩ ጌታ ፈጠረኝ አለች”*

የመቃብያን ጸሐፊም ሰሎሞን በምሳሌ መጽሐፍ ላይ ስለ ኢየሱስ፦ “ዛሬም የሚታየው ሁሉ ሳይታይ ዛሬም የሚጠራው ስም ሁሉ ሳይጠራ ፈጠረኝ” ማለቱን ተናግሯል፦
3ኛ መቃብያን 4፥18 ሰሎሞን ፦ *“ዛሬም የሚታየው ሁሉ ሳይታይ ዛሬም የሚጠራው ስም ሁሉ ሳይጠራ ፈጠረኝ”* ብሎ ተናገረ፤

እንግዲህ አባት ማለት “አስገኚ” ወይም “ፈጣሪ” መሆኑን እንዲሁ ልጅ ማለት “ተገኚ” ወይም “ፍጡር” መሆኑን ካየን ዘንዳ ኢንሻላህ በገቢር ሁለት አብ ማን ነው? ወልድ ማን ነው? የሚለውን እናብራራለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የፕሮቴስታንት ቅጥፈት ማጋለጥ ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ወደዚህ ቻናል ይቀላቀሉ፦
http://tttttt.me/protestant_lie
የኦርቶዶክስን ኮተት እና ተረት ማጋለጥ ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ወደዚህ ቻናል ይቀላቀሉ፦
@orthox
አባት እና ልጅ

ገቢር ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

112፥3 *አልወለደም አልተወለደም*። لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ

“ኣብ” אַבָּא ማለት በዕብራይስጥ “አስገኚ”orginator” ማለት ሲሆን በግዕዝ “አብ” ማለት “አባት” ማለት ነው፤ የአብ ተመሳሳይ ትርጉም “አባ” ሲሆን “አባት” ማለት ነው፤ “አበው” የአብ ብዙ ቁጥር ሲሆን “አባቶች” ማለት ነው።
በመጀመሪያ መደብ፦
“አቡየ” ማለት ነጠላ ሲሆን “አባቴ” ማለት ነው፤ “አቡነ” ማለት “አባታችን” ማለት ነው።
ሁለተኛ መደብ፦
“አቡከ” ለወንድ ሲሆን “አባትህ” ማለት ነው፤ “አቡኪ” ለሴት “አባትሽ” ማለት ነው። በብዜት ለወንድ “አቡክሙ” ማለት “አባታችሁ” ሲሆን ለሴት “አቡክን” ማለት “አባታችሁ” ነው።
ሦስተኛ መደብ፦
“አቡሁ” ለወንድ ሲሆን “አባቱ” ማለት ነው፤ “አቡሃ” ለሴት “አባቷ” ማለት ነው። በብዜት ለወንድ “አቡሆሙ” ማለት “አባታቸው” ሲሆን ለሴት “አቡሆን” ማለት “አባታቸው” ነው። ይህንን ካየን ዘንዳ የሚገርመው አበይት ክርስቲያኖች ማለትም ኦርቶዶስ፣ ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት እና አንግሊካን፦ “ኢየሱስ አብ ሳይሆን ወልድ ብቻ ነው” ይላሉ፤ ትክክል! ምክንያቱም ኢየሱስ የእራሱን ማንነት ከአብ ነጥሎ አስቀምጧል፦
ዮሐንስ 5፥31-32 *እኔ ስለ እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር ምስክሬ እውነት አይደለም*፤ ስለ እኔ የሚመሰክር *ሌላ ነው፥ እርሱም ስለ እኔ የሚመሰክረው ምስክር እውነት እንደ ሆነ አውቃለሁ።
ዮሐንስ 8፥18 *ስለ ራሴ የምመሰክር እኔ ነኝ፥ የላከኝም አብ ስለ እኔ ይመሰክራል*።
ዮሐንስ 12፥49 *እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ*።

ወልድ ማን ነው? ስንል ኢየሱስ ይሉናል፤ አብ ማን ነው? አብ ደግሞ እግዚአብሔር ነው፦
ቆላስይስ 1፥3 *የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አባት እግዚአብሔርን* ሁልጊዜ እናመሰግናለን፤
ሮሜ 15፥5 *እግዚአብሔርን፥ እርሱም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት*፥ ታከብሩ ዘንድ፥
1ቆሮንቶስ 15፥24 በኋላም፥ መንግሥቱን *ለእግዚአብሔር ለአባቱ* አሳልፎ በሰጠ ጊዜ፤
ዮሐንስ 5፥18 *እግዚአብሔር አባቴ ነው* ስላለ፥ ስለዚህ አይሁድ ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር።

የኢየሱስ አባት እግዚአብሔር ከሆነ ኢየሱስ እግዚአብሔር አይደለም ማለት ነው፤ ምክንያቱም አብ እግዚአብሔር ነውና፤ እግዚአብሔር ደግሞ አንድ ነው፤ እስራኤላውያን አምላካችን የሚሉት አንዱን እግዚአብሔር ነው፣ ኢየሱስም፦ “እናንተ አምላካችን የምትሉት አባቴ ነው” ብሏል፦
ዘዳ.6:4፤ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ *አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው*፤
ዮሐ.8:54 *እናንተ አምላካችን የምትሉት አባቴ ነው*፤

ይህ አንድ አምላክ የሁሉም አንድ አባት ነው፦
ሚልክያስ 2፥10 ለሁላችን *”አንድ አባት”* ያለን አይደለምን? *አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን*?
ማቴዎስ 23፥9 *አባታችሁ አንዱ* እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ *ማንንም፦ አባት ብላችሁ አትጥሩ*።
ዮሐንስ 8፥41 *አንድ አባት* አለን *እርሱም እግዚአብሔር ነው*፡ አሉት።
ኤፌሶን 4፥6 ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር *አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ*።
ዮሐንስ 20፥17 *እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ* ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት።
አባትና ልጅ ለኢየሱስ እና ለእግዚአብሔር ብቻ ሳይሆን ለመላእክት ልጅነት እና ለእግዚአብሔር አባትነት አገልግሎት ላይ ውሏል። መላእክት መናፍስት ተብለዋል፤ እግዚአብሔር የመናፍስት አባት ነው። መናፍስትም የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው፦
ዕብራውያን 12፥9 እንዴትስ ይልቅ *ለመናፍስት አባት* አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን?
ዕብራውያን 1፥14 *የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?*
ኢዮብ 38፥7 አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥ *የእግዚአብሔርም ልጆች* ሁሉ እልል ሲሉ፥

የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር በሚል ስሌት ኢየሱስን እግዚአብሔር ካረግን መላእክት የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና እግዚአብሔሮች መሆን ነበረባቸው። ኢየሱስ እግዚአብሔር ቢሆን ኖሮ “የእግዚአብሔር አባት”የሚል ቃል ታገኙ ነበር፤ ግን ኢየሱስ እግዚአብሔር ስላልሆነ 42 ቦታ ላይ “የእግዚአብሔር ልጅ” ብቻ ተብሏል፦
ሉቃስ 1፥35 ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ *የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል*።

ኢየሱስ እግዚአብሔር ቢሆን ኖሮ “እግዚአብሔር ወልድ”የሚል ቃል ታገኙ ነበር፤ ግን ኢየሱስ እግዚአብሔር ስላልሆነ እግዚአብሔር የሚባለው አብ ብቻ ስለሆነ “እግዚአብሔር አብ” የሚል ቃላት 13 ቦታ እናገኛለን፦
ያዕቆብ 1፥27 ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ *በእግዚአብሔር አብ* ዘንድ ይህ ነው፤

ባይብሉ እግዚአብሔር እና ኢየሱስን አባት እና ልጅ አርጎ ነው የሚያስቀምጠው፤ አባት ልጅ አይደለም ልጅም አባት አይደለም ካላችሁ እግዚአብሔር ኢየሱስ አይደለም፤ ኢየሱስም እግዚአብሔር አይደለም። እግዚአብሔር ለኢየሱስ ግህደተ-መለኮት”revelation” ማለትም “ወሕይ” ሰቶቷል፦
ራእይ 1፥1 *እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው ግልጠት በእርሱም የተገለጠው ይህ ነው*፥ The Revelation of Jesus Christ, which God gave unto him,
ዮሐንስ 7፥16-17 ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው፦ *ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም*፤ ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ *ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር ቢሆን ወይም እኔ ከራሴ* የምናገር ብሆን ያውቃል።

“ከእግዚአብሔር ወይም እኔ ከራሴ” የሚለው ይሰመርበት፤ የሚገርመው እራሱን ከእግዚአብሔር በመለየት “እራሴ” በሚል ድርብ ተውላጠ-ስም”reflexive pronoun ” ተጠቅሟል፤ ትምህርቱ ከላከው ከእግዚአብሔር እንጂ ከራሱ አይደለም። እግዚአብሔር ለኢየሱስ የሰጠው ግልጠት በግሪክ “አፓልካሊፕስ” Ἀποκάλυψις ይባላል፤ ኢየሱስ በአንድ እግዚአብሔር እና በሰዎች መካከል እየሰማ የሚናገር ሰው ነው፦
1 ጢሞቴዎስ 2፥5፤ *አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው*፤
ዮሐንስ 8፥40 ነገር ግን አሁን *ከእግዚእብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው* ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ?
ሐዋ ሥራ 2፥22 *የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ*፤

እግዚአብሔር አንድ ከሆነ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ቃል እንዲናገር ከአንድ እግዚአብሔር የተላከ መልእክተኛና አገልጋይ ነው፦
ዮሐንስ 3፥34 *እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራልና*፤
ሐዋ ሥራ 3፥26፤ ለእናንተ አስቀድሞ *እግዚአብሔር አገልጋዩን አስነሥቶ፥ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ፥ ላከው*። NIV

እግዚአብሔር አንድ ከሆነ ኢየሱስ ሌሊቱንም ሁሉ ሲጸልይ ያደረው ወደዚህ ወደ አንድ እግዚአብሔር ነው፤ ይህ አንድ እግዚአብሔር ኢየሱስን ቀብቶታል፤ ለዲያብሎስም የተገዙትን እንዲፈውስ እግዚአብሔር ከኢየሱስ ጋር ነበረ፦
ሉቃስ 6፥12 በነዚህም ወራት ይጸልይ ዘንድ ወደ ተራራ ወጣ፥ *ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ አደረ*።
ሐዋ ሥራ 10፥38 *እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው*፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ *እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና*፤

ክርስቶስ የእግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር የክርስቶስ ራስ ማለትም የበላይ ነው፦
1 ቆሮንቶስ 3፥23 *ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው*።
1 ቆሮንቶስ 11፥3 *የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ*።

ኢየሱስ እግዚአብሔር ነው ለምትሉ አልቆላችኃል። ምክንያቱም እግዚአብሔር የኢየሱስ አባት ነው ተብላችኃል፤ ኢየሱስ ደግሞ አብ አይደለም ብላችኃል።
ስለዚህ ኢየሱስ አብ ማለትም እግዚአብሔር ሳይሆን የእግዚአብሔር ልጅ ነው፤ እግዚአብሔርም ወልድ ማለትም ኢየሱስ ሳይሆን አብ”አባት” ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሙት ማስነሳት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

46፥33 ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ፥ እነርሱንም በመፍጠሩ ያልደከመው አላህ ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ መኾኑን አላስተዋሉምን? በማስነሳት ቻይ ነው፡፡ እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፡፡ أَوَلَمْ يَرَوْا أَنَّ اللَّهَ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَلَمْ يَعْيَ بِخَلْقِهِنَّ بِقَادِرٍ عَلَىٰ أَن يُحْيِيَ الْمَوْتَىٰ ۚ بَلَىٰ إِنَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

ሚሽነሪዎች ሁልጊዜ ቋ ያለ ጉፋያ ሃሳብ እንደ በቀቀን መደጋገም ይወዳሉ፤ የማይመክን ሃሳብ ይዞ ከመሞገት ይልቅ መንፈቅፈቁንና መነፋረቁን፥ መንሰክሰኩንና መንከንከኑን ተያይዘውታል፤ ጭራሽ ኢየሱስ ሙት ማስነሳቱ ለአምላክነቱ ማስረጃ አድርገው አርፈውታል።
አምላካችን እና ጌታችን አላህ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ፤ እነርሱንም በመፍጠሩ ያልደከመው፤ ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ ነው፤ እርሱም በመጀመሪያ መደብ፦ "እኛ ሙታንን በእርግጥ ሕያው እናደርጋለን" ይለናል፦
46፥33 ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ፤ እነርሱንም በመፍጠሩ ያልደከመው አላህ ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ መኾኑን አላስተዋሉምን? በማስነሳት ቻይ ነው፡፡ እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፡፡ أَوَلَمْ يَرَوْا أَنَّ اللَّهَ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَلَمْ يَعْيَ بِخَلْقِهِنَّ بِقَادِرٍ عَلَىٰ أَن يُحْيِيَ الْمَوْتَىٰ ۚ بَلَىٰ إِنَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
36፥12 *"እኛ ሙታንን በእርግጥ ሕያው እናደርጋለን"*፡፡ ያስቀደሙትንም ሥራ ፈለጎቻቸውንም እንጽፋለን፡፡ ነገሩንም ሁሉ ገላጭ መሪ በኾነ መጽሐፍ ውስጥ አጠቃለልነው፡፡ إِنَّا نَحْنُ نُحْيِي الْمَوْتَىٰ وَنَكْتُبُ مَا قَدَّمُوا وَآثَارَهُمْ ۚ وَكُلَّ شَيْءٍ أَحْصَيْنَاهُ فِي إِمَامٍ مُّبِينٍ

"ትንሳኤ" ለሚለው የግስ መደብ የገባው ቃል "አቃመ" أَقَامَ "አሕያ" أَحْيَا "በዐሰ" بَعَثَ ነው። ይህንን ቃል ይዘን ወደ ባይብል ከገባን በባይብል ሙት አስነሺ የተባለው ኢየሱስ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያት እና ነቢያትም ጭምር ናቸው፦
ማቴዎስ 10፥8 ድውዮችን ፈውሱ፤ *"ሙታንን አስነሡ"*፤ ለምጻሞችን አንጹ፤ አጋንንትን አውጡ፤ በከንቱ ተቀበላችሁ፥ በከንቱ ስጡ። اشفُوا المَرضَى، أقِيمُوا المَوتَى، اشفُوا البُرصَ، أخرِجُوا الأرواحَ الشِّرِّيرَةَ. أخَذْتُمُ السُّلطانَ لِعَمَلِ ذَلِكَ مَجّاناً، فَأعطُوا الآخَرِينَ مَجّاناً أيضاً.

"አስነሱ" ለሚለው ቃል "አቂሙ" أقِيمُوا በሚል መጥቷል፤ ታዲያ ሐዋርያቱ አምላክ ነበሩን? ኢየሱስ የሠራውን ሥራ በእርሱ መልእክተኝነት ያመኑ ሰዎችም እርሱ ከሠራው ሥራ ይበልጥ ሊሠሩ እንደሚችሉ እራሱ ተናግሯል፦
ዮሐንስ 14፥13 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን *”እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል”*፥

በዚህ መሰረት በኢየሱስ ነብይነት ያመኑት ሃዋርያትም ኢየሱስ የሠራውን ሥራ ማለትም ሰው ከሞት ማስነሳት ሠርተውቷል፦
የሐዋርያት ሥራ 9:40 ጴጥሮስም ሁሉን ወደ ውጭ አስወጥቶ ተንበርክኮም ጸለየ፥ *"ወደ ”ሬሳውም ዘወር ብሎ። ጣቢታ ሆይ፥ ”ተነሺ” አላት። እርስዋም ዓይኖችዋን ከፈተች ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ተቀመጠች"*።

ብሉይ ኪዳን ላይ የነበሩት ሁለት ነቢያት ኤልያስ እና ኤልሳዕ የሁለት ሴቶችን ልጆች አስነስተዋል፦
1. ኤልያስ፦
1ኛ ነገሥት 17፥21-23 *በብላቴናውም ላይ ሦስት ጊዜ ተዘረጋበት፥ ወደ እግዚአብሔርም። አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ የዚህ ብላቴና ነፍስ ወደ እርሱ ትመለስ ዘንድ እለምንሃለሁ ብሎ ጮኸ፤ እግዚአብሔርም “የኤልያስን ቃል ሰማ፤ የብላቴናው ነፍስ ወደ እርሱ ተመለሰች”፥ እርሱም ዳነ፤ ኤልያስም ብላቴናውን ይዞ ከሰገነቱ ወደ ቤት አወረደው፥ ኤልያስም። እነሆ፥ “ልጅሽ በሕይወት ይኖራል” ብሎ ለእናቱ ሰጣት*።

2. ኤልሳዕ፦
1ኛ ነገሥት 4፥32-34 *ኤልሳዕም ወደ ቤት በገባ ጊዜ እነሆ፥ “ሕፃኑ ሞቶ” በአልጋው ላይ ተጋድሞ ነበር። ገብቶም በሩን ከሁለቱ በኋላ ዘጋ፥ ወደ እግዚአብሔርም ጸለየ፤ መጥቶም በሕፃኑ ላይ ተኛ፤ “አፉንም በአፉ፥ ዓይኑንም በዓይኑ፥ እጁንም በእጁ ላይ አድርጎ ተጋደመበት፤ የሕፃኑም ገላ ሞቀ”፤ ተመልሶም በቤቱ ውስጥ አንድ ጊዜ ወዲህና ወዲያ ተመላለሰ፤ ደግሞም ወጥቶ ሰባት ጊዜ በሕፃኑ ላይ ተጋደመ፤ ሕፃኑም ዓይኖቹን ከፈተ*።

የዕብራውያን ጸሐፊ ይህንን ጉዳይ በማስታወስ በኤልያስ እና በኤልሳዕ ዘመን የነበሩት ሁለት ሴቶሽ ሙታን ልጆቻቸውን በትንሳኤ ተቀበሉ ይለናል፦
11፥35 *ሴቶች ሙታናቸውን “በትንሣኤ” ተቀበሉ*፤

ልብ በል “ትንሳኤ” የተባለው በብሉይ ኪዳን ሁለት ነብያት የሞቱ ሰዎችን ያስነሱትን የሴቶችን ህፃናት እንደሆነ እሙንና ቅቡል ነው፤ ታዲያ ሁለት ነቢያት ኤልያስ እና ኤልሳዕ የሁለት ሴቶችን ልጆች ስላስነሱ አምላክ ናቸውን? አይ፦ "ሐዋርያቱ እና ነቢያቱ ሙት ያስነሱት በጸሎት ነው" ይሉናል፤ ኢየሱስስ ጸልዮ እኮ ነው ሙት ያስነሳው፤ ኢየሱስ እግዚአብሔርን ለምኖ ሰዎች እግዚአብሔር እንዳላከው እንዲያምኑበት የተሰጠው ስራ እንደሆነ ተናግሯል፦
ዮሐንስ 11፥41-44 ድንጋዩንም አነሡት። *ኢየሱስም ዓይኖቹን ወደ ላይ አንሥቶ። “አባት ሆይ፥ ስለ ሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ፤ ሁልጊዜም እንድትሰማኝ” አወቅሁ፤ ነገር ግን “አንተ እንደ ላክኸኝ ያምኑ ዘንድ” በዚህ ዙሪያ ስለ ቆሙት ሕዝብ ተናገርሁ አለ። ይህንም ብሎ በታላቅ ድምፅ። አልዓዛር ሆይ፥ ወደ ውጭ ና ብሎ ጮኸ። የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ፤ ፈቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበር። ኢየሱስም። ፍቱትና ይሂድ ተዉት አላቸው*።

ኢየሱስ የሚያደርጋቸው ታምራት ሁሉ በፈጣሪ ስም እንጂ ከራሱ ምንም ማድረግ አይችልም፦
ዮሐንስ 10፥25 ኢየሱስም መለሰላቸው፥ እንዲህ ሲል። ነገርኋችሁ አታምኑምም *”እኔ በአባቴ ስም የማደርገው ሥራ ስለ እኔ ይመሰክራል"*።
ዮሐንስ 5:30 *”እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም”*፤

እንዴት አምላክ የሆነ ህላዌ "ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም" ይላል? እንዴትስ አምላክ የሆነ ህላዌ በሌላ ማንነትና ምንነት ስም ታምር ያደርጋል? ጭራሽኑ የሚያደርጋቸው ሥራዎች ከፈጣሪ በጸጋ ያገኛቸው እንደሆኑ እና ለእርሱ መእክተኛነት ማስረጃ እንደሆኑ አበክሮ እና አዘክሮ ይናገራል፦
ዮሐንስ 17፥4 እኔ ላደርገው *የሰጠኸኝን* ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ፤
ዮሐንስ 5፥36 አብ ልፈጽመው *የሰጠኝ* ሥራ” ይህ የማደርገው ሥራ፥ አብ እንደ ”ላከኝ” ስለ እኔ ይመሰክራልና።
ዮሐንስ 11፥42 ሁልጊዜም እንድትሰማኝ አወቅሁ፤ ነገር ግን *”አንተ እንደ ላክኸኝ ያምኑ ዘንድ"* በዚህ ዙሪያ ስለ ቆሙት ሕዝብ ተናገርሁ አለ።
የየናዝሬቱ ኢየሱስ ያደረጋቸው ተአምራት፣ ድንቆች እና ምልክቶችም እግዚአብሔር በኢየሱስ በኩል ያደረገው ነው፤ በተጨማሪም ከእግዚአብሔር ለእስራኤል ሰዎች የተላከ ሰው መሆኑን በአጽንዖትና በአንክሮት የሚያሳይ ነው፦
የሐዋርያት ሥራ 2፥22 የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ *የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ “በእርሱ”” በኩል ባደረገው “”ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም” ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእስራኤል ሰዎች የተላከ ሰው ነበረ፤ ይህ ሰው በራሱ ፈቃድ ሳይሆን በላከውን ፈቃድ ሙት ሲያስነሳ የነበረ ሰው ነው፦
ዮሐንስ 5፥30 *እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም"*፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ *"የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና"*።

አምላካችን እና ጌታችን አላህም ዒሣ ምን አስተምሮ እንደነበር በተናገረበት አንቀጽ ላይ ዒሣ ሙት ማስነሳቱ ለመልእክተኛነቱ ማስረጃ እንደሆነ ነግሮናል፦
3፥49 ወደ እስራኤልም ልጆች መልክተኛ ያደርገዋል፡፡ ይላልም፡- «እኔ ከጌታዬ ዘንድ በተዓምር ወደ እናንተ መጣሁ፡፡ እኔ ለናንተ ከጭቃ እንደ ወፍ ቅርፅ እፈጥራለሁ፡፡ በርሱም እተነፍስበታለሁ፡፡ በአላህም ፈቃድ ወፍ ይኾናል፡፡ በአላህም ፈቃድ ዕውር ኾኖ የተወለደን፣ ለምጸኛንም አድናለሁ፡፡ ሙታንንም *"አስነሳለሁ"*፡፡ የምትበሉትንና በቤታችሁ የምታደልቡትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፡፡ የምታምኑ እንደኾናችሁ ለእናንተ በዚህ ውስጥ በእርግጥ ተዓምር አለበት፡፡» وَرَسُولًا إِلَىٰ بَنِي إِسْرَائِيلَ أَنِّي قَدْ جِئْتُكُم بِآيَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ ۖ أَنِّي أَخْلُقُ لَكُم مِّنَ الطِّينِ كَهَيْئَةِ الطَّيْرِ فَأَنفُخُ فِيهِ فَيَكُونُ طَيْرًا بِإِذْنِ اللَّهِ ۖ وَأُبْرِئُ الْأَكْمَهَ وَالْأَبْرَصَ وَأُحْيِي الْمَوْتَىٰ بِإِذْنِ اللَّهِ ۖ وَأُنَبِّئُكُم بِمَا تَأْكُلُونَ وَمَا تَدَّخِرُونَ فِي بُيُوتِكُمْ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

ስለዚህ ኢየሱስ በአላህ ፈቃድ ሙት ማስነሳቱ ለእርሱ መልእክተኛነት ማስረጃ መሆኑን እንረዳለን እንጂ ጭራሽ ለአምላክነት ሸርጥ ነው ብሎ እንደ ደሊል መረጃ ማቅረብ እጅግ በጣም ሲበዛ ቂልነት ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ገለባ ክስ

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

15፡95 ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሃል إِنَّا كَفَيْنَٰكَ ٱلْمُسْتَهْزِءِينَ ፡፡

መግቢያ
ለእስልምና መልስ በሚል ድህረ-ገፅ ላይ የነቢያችንን”ﷺ” ነብይነትን ከንቱ ለማድረግ ሳም ሻሙስ የተባለ ተሳላቂ ነብያችን”ﷺ” ትንቢት ተናግረው ያ ትንቢት እንዳልተፈፀመና አንድ ነብይ ትንቢት ተናግሮ ያ ትንቢት ካልተፈፀመ ሐሳዌ ነብይ እንደሚያስብለው ሁሉ ነብያችንን”ﷺ” ሐሳዌ ነብይ ለማድረግ ወሊአዑዙቢላህ ሲቃጣው ይታያል፤ አንድ ሐሳዌ ነብይ ነብይነቱ ውድቅ የሚሆንበት በሁለት ምክንያት ነው፤ አንደኛ የሚናገረው ከገዛ ልቡ ከሆነ እና ሁለተኛ ከሸይጣን ከሆነ ነው፤ ነገር ግን ነብያችን”ﷺ” ከገዛ ልባችው ወይም ከሌላ አካል አላህ ካላቸው ውጪ ምንም እንደማይናገሩ ለተሳላቂዎች ትችት በቅቶላቸዋል፦
53፥3-4 ከልብ ወለድም አይናገርም وَمَا يَنطِقُ عَنِ ٱلْهَوَىٰٓ ፡፡
እርሱ ንግግሩ የሚወርረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም إِنْ هُوَ إِلَّا وَحْىٌۭ يُوحَىٰ ፡፡
69፥44-46 በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት ያላልነውን በቀጠፈ ኖሮ وَلَوْ تَقَوَّلَ عَلَيْنَا بَعْضَ ٱلْأَقَاوِيلِ ፤ በኀይል በያዝነው ነበር لَأَخَذْنَا مِنْهُ بِٱلْيَمِينِ ፡፡ ከዚያም ከእርሱ የልቡን ሥር በቆረጥን ነበር ثُمَّ لَقَطَعْنَا مِنْهُ ٱلْوَتِينَ ፡፡

ይህንን እሳቤ ይዘን በነቢያችንን”ﷺ” ላይ የተሰጡት ገለባ ክሶች አንድ በአንድ በአላህ ፈቃድ ጥርስ እና ምላሱን እየነቀስን ጥልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ እናየዋለን፦

ገለባ አንድ
ሱነን አቢ ዳውድ :መጽሐፍ 39, ሐዲስ 6
የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ በታላቁ ጦርነት እና በከተማይቱ ውድቀት መካከል ያለው ጊዜ ስድስት ዓመት ነው፤ በሰባተኛው ዓመት ደጃል ይወጣል፤ ዘገባው ደኢፍ ነው أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ بَيْنَ الْمَلْحَمَةِ وَفَتْحِ الْمَدِينَةِ سِتُّ سِنِينَ وَيَخْرُجُ الْمَسِيحُ الدَّجَّالُ فِي السَّابِعَةِ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ أَبُو دَاوُدَ هَذَا أَصَحُّ مِنْ حَدِيثِ عِيسَى ‏.‏ ضعيف ።

ትችቱ ሲጀምር፦ “ቆንስጣንጥኒያ የወደቀችው እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር ግንቦት 29 በ 1453 AD ነው፤ ከ 1453-1461 ደጃል መምጣት ነበረበት፤ ይህ ትንቢት ሳይፈፀም ይኸው 556 ዓመት አስቆጠረ፤ ስለዚህ ትንቢቱ ከሽፏል” ወሊአዑዙቢላህ፤ ሲጀመር ሐዲሱ ላይ “አል-መዲናህ” الْمَدِينَةِ ማለትም “ከተማይቱ” አለ እንጂ በስም መቼ ተጠቀሰ? ሲቀጥል ከተማይቱ የሚለው ቆንስጣንጥኒያ ብንል እንኳን በሰለፎች አረዳድ ቆንስጣንጥኒያ መላውን አውሮፓ እንጂ ኦቶማን ግንቦት 29 1453 AD የተቆጣጠራትን ከተማ ነው ማን ነው ያለው?፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 36, ሐዲስ 167
ጃቢር አለ፦ ደጃል አይመጣም እናንተ ከሮማዎች ሳትታገሉ قَالَ جَابِرٌ فَمَا يَخْرُجُ الدَّجَّالُ حَتَّى تُفْتَحَ الرُّومُ ‏ ።
በተመሳሳይ ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 54, ሐዲስ 50 ላይም ተዘግቧል፦
ጃቢር አለ፦ ደጃል አይመጣም እናንተ ከሮማዎች ሳትታገሉ قَالَ فَقَالَ نَافِعٌ يَا جَابِرُ لاَ نَرَى الدَّجَّالَ يَخْرُجُ حَتَّى تُفْتَحَ الرُّومُ ‏ ።

እንግዲህ ከተማይቱ የሚለው በዚህ ሪዋያ ሮማዎች ማለትም አውሮፓውያን እንደሆኑ ስለተገለፀ ኦቶማን የያዛት ከተማ ናት የሚለው ገለባ ክስ ድባቅ ይገባል። ምክንያቱን ታላቁ ቆስጠንጥኒዎስ በ 330 AD ባዛንታይንን መሰረት ያደረገ የቆስጠንጥንያ ግዛት መላውን አውሮፓ ያካልል ነበር። ሲሰልስ ሐዲሱ ደረጃው በሸኽ አልባኒ ከመነሻው “ደኢፍ” ضعيف ነው ተብሎ መዝጊያው ላይ ተቀምጧል፤ የሚሽነሪዎች ትልቁ ችግራቸው አንደኛ ታማኝ የሆኑ ምንጮች አለመጠቀማቸው ሲሆን ሁለተኛ የኢስላም መጽሐፍት ሥረ-መሰረቱ”orgin” አረቢኛው እያለ ከጎግል በሚገኘው ትርጉም ላይ መንጠልጠላቸው ነው፤ ሚሽነሪዎች ሥነ-ሐዲስ ጥናት መሰረታዊ ጭብጦች ለማወቅ ፍላጎቱም የላቸውም፤ ምክንያቱም ኃሳውያን ሚሽነሪዎች ኃሳዊ ትምህርታቸው ጽርፈት ማለትም ክህደት ነውና፤ ለዛ ነው ዓሊሞቻችን ያስቀመጡትን የደርስ መዋቅርና መርሃ ግብር ዕቡይ ተግዳሮት የሚሆንባቸው፤ እኔ ለአንባቢያን ስለ ሐዲስ በግርድፉና በሌጣው ከሙስጠለሑል ሐዲስ ልጀምር፤ “ሙስጠለሑል ሐዲስ” مُصْطَلَحُ الحَدِيْث‌‎ ማለት የሐዲስ ስያሜ”Hadith terminology” ናቸው፤ እነርሱም፦ ሰሒሕ፣ ሐሠን፣ ደኢፍ እና መውዱዕ ናቸው፤ ከላይ የተተቸበት ሐዲስ ደኢፍ ይባላል። “ደኢፍ” ضَعِيْف ማለት “ደካማ”weak” ማለት ሲሆን አንድን ዘገባ ደካማ የሚያሰኘው ወደ ሙሐዲስ የሚመጣበት አካሔድ ደካማ መሆኑ ነው። “ሙሐዲስ”محديث‎ ማለት “ዘጋቢ”collector” ማለት ሲሆን እነዚህም ሙሐዲሲን ኢማም ቡኻሪይ፣ ኢማም ሙስሊም፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጃህ፣ አቢ ዳውድ፣ ነሳኢ ወዘተ ናቸው፤ አንድ ዘገባ ደካማ ነው የሚያሰኘው አምስት ሸርጦች አሉት፤ እነርሱም፦
1ኛ. “ሙአለቅ”
“ሙአለቅ” مُعَلَّق ማለት በሙሐዲስ እና በነብያችን”ﷺ” መካከል ምንም አይነት ተራኪና ትረካ ሳይኖር ሲቀር “ሙአለቅ” ይባላል።
2ኛ. “ሙርሰል”
“ሙርሠል”مُرْسَل ማለት በነብያችን”ﷺ” እና በዘጋቢው መካከል ተራኪ ከሌለው ግን ትረካ ካለው “ሙርሰል” ይባላል።
3ኛ. “ሙንቀጢዕ”
“ሙንቀጢዕ” مُنْقَطِع ማለት በነብያችን”ﷺ” እና በተራኪው መካከል ትረካ ከሌለው “ሙንቀጢዕ” ይባላል።
4ኛ. “ሙንከር”
“ሙንከር” مُنْكَر በደካማ ተራኪ ተተርኮ ትረካው ከሰሒሕ ዘገባ ጋር ከተጋጨ “ሙንከር” ይባላል።
5ኛ. “ሙጠሪብ”
“ሙጠሪብ” مُضْطَرِب ማለት አንድ ሐዲስ የተቃረኑ የዘገባ ሰነዶች ሲኖሩት ወይንም ዘገባው የተቃረኑ መትኖች ሲኖሩት “ሙጠሪብ” ይባላል።

ይህ ትውልድ የኢስላም ታሪክ ምፀት ለሚቀጥለው ትውልድ የሚሆን ሰፊ ምዕላድ ትተን መሄድ ግድ ይላል፤ ሚሽነሪዎች እየቀጠፉ አይኖሯትም፤ ኢንሻላህ ገለባው ክስ ድባቅ የሚገባበት ሙግት ይቀጥላል…

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ገለባ ክስ

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

15፡95 ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሃል إِنَّا كَفَيْنَٰكَ ٱلْمُسْتَهْزِءِينَ ፡፡

ገለባ ሁለት
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 3 , ሐዲስ 58:
ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፤ ነብዩም"ﷺ" በመጨረሻቸው ህይወት በኢሻህ ሶላት ላይ መሩንና እንዲህ አሉ፦ "ይህን ሌሊት አጢናችሁታል? ከዚህ ሌሊት እስከ መቶ ሙሉ ዓመት በኃላ በምድር ወለል ማንም አይኖርም" حَدَّثَنَا سَعِيدُ بْنُ عُفَيْرٍ، قَالَ حَدَّثَنِي اللَّيْثُ، قَالَ حَدَّثَنِي عَبْدُ الرَّحْمَنِ بْنُ خَالِدٍ، عَنِ ابْنِ شِهَابٍ، عَنْ سَالِمٍ، وَأَبِي، بَكْرِ بْنِ سُلَيْمَانَ بْنِ أَبِي حَثْمَةَ أَنَّ عَبْدَ اللَّهِ بْنَ عُمَرَ، قَالَ صَلَّى بِنَا النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم الْعِشَاءَ فِي آخِرِ حَيَاتِهِ، فَلَمَّا سَلَّمَ قَامَ فَقَالَ ‏ "‏ أَرَأَيْتَكُمْ لَيْلَتَكُمْ هَذِهِ، فَإِنَّ رَأْسَ مِائَةِ سَنَةٍ مِنْهَا لاَ يَبْقَى مِمَّنْ هُوَ عَلَى ظَهْرِ الأَرْضِ أَحَدٌ ‏"‌‏.‏ ።

በዚህ ሐዲስ መሰረት ሳም ሻሙስ፦ "ይህንን ነብያችን"ﷺ" ሲናገሩ በ 632 AD ነው፤ ከዚህ ቀን ጀምሮ መቶ ዓመት ሲቆጠር 732 AD ትንሳኤ ቆሞ ሁሉም ሰው አይኖርም፤ ግን ይኸው 1285 ዓመት አለፈው፤ ስለዚህ የተነገረው ትንቢት ከሽፋል" የሚል ስሁት ሙግት ያቀርባል፤ አለማወቅ በራሱ ኀጢአት አይደለም፤ ከመተቸት በፊት ይህ ምንድን ነው? ብሎ መጠየቅ ብልህነት ነው፤ አምላካችን አላህ፦ 16፥43 "የማታውቁ ብትሆኑ የዕውቀት ባለቤቶችን ጠይቁ" ይላል፤ እኛም ደረሳ እንደመሆናችን መጠን ኡስታዞቻችን ጠይቀን ያገኘነው መልስ፦ "በነብያችን"ﷺ" ጊዜ ከቆሙት ሰዎች ከመቶ ዓመት በኃላ ማንም አይኖርም ይሞታል" የሚል ነው፤ ይህንን ደሊል የሆነ ሐዲስ እራሱ ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር በተረከው ሐዲስ ላይ እንዲህ ተቀምጧል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 9 , ሐዲስ 77:
ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር እንደተረከው፤ ነብዩም"ﷺ" በመጨረሻቸው ህይወት በኢሻህ ሶላት ላይ አሰላምተው ሲጨርሱ ቆሙና እንዲህ አሉ፦ "ይህን ሌሊት አጢናችሁታል? ከዚህ ሌሊት እስከ መቶ ሙሉ ዓመት በኃላ በምድር ወለል ማንም አይኖርም"፤ ይህንን የአላህን መልክተኛ"ﷺ" አነጋገር ሰዎች በተሳሳተ ነው የተረዱት፤ አንዳንድ ተራኪዎች( የመጨረሻው ቀን ከመቶ አመት በኃላ ይሆናል) ብለው ተረዱት፤ ነገር ግን ነብዩ"ﷺ" ለማለት የፈለጉት፦ " ያ ክፍለ ዘመን ትውልድ ያልፋል" ነው أَنَّ عَبْدَ اللَّهِ بْنَ عُمَرَ، قَالَ صَلَّى النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم صَلاَةَ الْعِشَاءِ فِي آخِرِ حَيَاتِهِ، فَلَمَّا سَلَّمَ قَامَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ ‏"‏ أَرَأَيْتَكُمْ لَيْلَتَكُمْ هَذِهِ فَإِنَّ رَأْسَ مِائَةٍ لاَ يَبْقَى مِمَّنْ هُوَ الْيَوْمَ عَلَى ظَهْرِ الأَرْضِ أَحَدٌ ‏"‌‏.‏ فَوَهِلَ النَّاسُ فِي مَقَالَةِ رَسُولِ اللَّهِ ـ عَلَيْهِ السَّلاَمُ ـ إِلَى مَا يَتَحَدَّثُونَ مِنْ هَذِهِ الأَحَادِيثِ عَنْ مِائَةِ سَنَةٍ، وَإِنَّمَا قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ لاَ يَبْقَى مِمَّنْ هُوَ الْيَوْمَ عَلَى ظَهْرِ الأَرْضِ ‏"‏ يُرِيدُ بِذَلِكَ أَنَّهَا تَخْرِمُ ذَلِكَ الْقَرْنَ‏.‏ ።

ገለባ ሶስት
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 54 , ሐዲስ 172:
ዓኢሻ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ የዐረብ ቆለኞች የሆኑትም ወደ አላህ መልእክተኛ"ﷺ" በመምጣት ስለ ሰዓቲቱ ጠየቋቸው፤ እርሳቸውም በዕድሜ ትንሽ የሆነውን ተመልክተው፦ "ይህ ልጅ እርጅና ሳያገኘው ማደግ ከቻለ የእናንተ ሰዓታችሁ በእናንተ ላይ ትመጣለች" ብለው አሉ عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كَانَ الأَعْرَابُ إِذَا قَدِمُوا عَلَى رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم سَأَلُوهُ عَنِ السَّاعَةِ مَتَى السَّاعَةُ فَنَظَرَ إِلَى أَحْدَثِ إِنْسَانٍ مِنْهُمْ فَقَالَ ‏ "‏ إِنْ يَعِشْ هَذَا لَمْ يُدْرِكْهُ الْهَرَمُ قَامَتْ عَلَيْكُمْ سَاعَتُكُمْ ‏"‏ ።

"ሣዐቱኩም" سَاعَتُكُمْ ማለት "የእናንተ ሰአት" ማለት እንጂ የቂያማ ቀን ሰአት በፍፁም አያመለክትም፤ ምክንያቱም "ኩም" ُكُمْ የሚለው ተሳቢ ተውላጠ ስም በሁለተኛ መደብ ያሉትን የዐረብ ቆለኞች ስለሚያመለክት ነው። ህፃኑ አድርጎ ከማርጀቱ በፊት የዐረብ ቆለኞች የመሞቻ ቀናቸው ወደ እነርሱ ይመጣል፤ ለዛ ነው "ዐለይኩም" عَلَيْكُمْ የሚል ሁለተኛ መደብ ያለበት ተውላጠ ስም ላይ መስተዋድድ መነሻ ቅጥያ ሆኖ የገባው፤ መጨረሻ የሚለው ቃል ለትንሳኤ ቀን ብቻ ሳይሆን ለሞት ቀንም ያገለግላል፤ "ሞት" የሰዎችን ህይወት ሰአት መጨረሻ የሚያደርግ የቂን ነው፦
15:99 "እውነቱም (ሞት) እስኪመጣህ ድረስ" ጌታህን አምልከው وَٱعْبُدْ رَبَّكَ حَتَّىٰ يَأْتِيَكَ ٱلْيَقِينُ ፡፡
62፥8 "ያ ከእርሱ የምትሸሹት ሞት እርሱ በእርግጥ የሚመጣባችሁ ነው፡፡ ከዚያም ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ ወደ ኾነው ጌታ ትመለሳላችሁ፡፡ ትሠሩትም የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል" በላቸው قُلْ إِنَّ ٱلْمَوْتَ ٱلَّذِى تَفِرُّونَ مِنْهُ فَإِنَّهُۥ مُلَٰقِيكُمْ ۖ ثُمَّ تُرَدُّونَ إِلَىٰ عَٰلِمِ ٱلْغَيْبِ وَٱلشَّهَٰدَةِ فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ ፡፡
63፥10 "አንዳችሁንም ሞት ሳይመጣው" እና ጌታዬ ሆይ! እንድመጸውትና ከደጋጐቹም ሰዎች እንድኾን ወደ ጥቂት ጊዜ ብታቆየኝ ኖሮ እመኛለሁ ከማለቱ በፊት ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ وَأَنفِقُوا۟ مِن مَّا رَزَقْنَٰكُم مِّن قَبْلِ أَن يَأْتِىَ أَحَدَكُمُ ٱلْمَوْتُ فَيَقُولَ رَبِّ لَوْلَآ أَخَّرْتَنِىٓ إِلَىٰٓ أَجَلٍۢ قَرِيبٍۢ فَأَصَّدَّقَ وَأَكُن مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ ፡፡

ኢንሻላህ ይቀጥላል.....ድምዳሜውን በባይብል ትንቢት እንደመድማለን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ገለባ ክስ

ክፍል ሶስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

15፡95 ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሃል إِنَّا كَفَيْنَٰكَ ٱلْمُسْتَهْزِءِينَ ፡፡

መደምደሚያ
አንድ ነብይ ትንቢት ተናግሮ ያ ትንቢት አለመፈፀሙ ያንን ትንቢት የተናገረው ነብይ ሐሳዌ ነብይ ያሰኘዋል የሚል የሳም ሻሙስን ሙግት እና በቂ ምላሽ በክፍል አንድ እና ሁለት አይተን ነበር፤ አቶ ሻም ሻሙሽ ይህንን ሸርጥ ያገኘው ከዚህ ጥቅስ ነው፦
ዘዳግም 18:22 ነቢዩ በእግዚአብሔር ስም በተናገረ ጊዜ ""የተናገረው ነገር ባይሆን ባይመጣም""፥ ያ ነገር እግዚአብሔር ያልተናገረው ነው፤ ነቢዩ በድፍረቱ ተናግሮታል እርሱን አትፍራው።

ይህንን መስፈት ይዘን ተነግረው ያልሆኑ የባይብል ትንቢት እናያለን፦

ትንቢት አንድ ኢያሱ 1:1-6 እንዲህም ሆነ፤ የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ከሞተ በኋላ እግዚአብሔር የሙሴን አገልጋይ የነዌን ልጅ ኢያሱን እንዲህ ብሎ ተናገረው። ባሪያዬ ሙሴ ሞቶአል፤ አሁንም አንተና ይህ ሕዝብ ሁሉ ተነሥታችሁ ለእስራኤል ልጆች ወደምሰጣቸው ምድር ይህን ዮርዳኖስ ተሻገሩ። ለሙሴ እንደ ነገርሁት ""የእግራችሁ ጫማ የሚረግጠውን ቦታ ሁሉ ለእናንተ ሰጥቼአለሁ""። ከምድረ በዳው ከዚህም ከሊባኖስ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ የኬጥያውያን ምድር ሁሉ እስከ ፀሐይ መግቢያ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ዳርቻችሁ ይሆናል። በሕይወትህ ዕድሜ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ አልጥልህም፥ አልተውህም። ለአባቶቻቸው። እሰጣችኋለሁ ብዬ የማልሁላቸውን ምድር ለዚህ ሕዝብ ታወርሳለህና ጽና፥ አይዞህ።
ኢያሱ 3:10 ኢያሱም አለ። ሕያው አምላክ በመካከላችሁ እንደ ሆነ፥ እርሱም ከፊታችሁ ከነዓናዊውን ኬጢያዊውንም ኤዊያዊውንም ፌርዛዊውንም ጌርጌሳዊውንም አሞራዊውንም ኢያቡሳዊውንም ፈጽሞ እንዲያወጣ በዚህ ታውቃላችሁ።

"የእግራችሁ ጫማ የሚረግጠውን ቦታ ሁሉ ለእናንተ ሰጥቼአለሁ" ብሎ ቃል ገብቶለታል ይለናል፤ ይህ ቦታ ከምድረ በዳው ከዚህም ከሊባኖስ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ድረስ የኬጥያውያን ምድር ሁሉ እስከ ፀሐይ መግቢያ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ዳርቻችሁ ይሆናል ተብሎ ተነግሯል፤ ልብ አድርግ ይህ ሁሉ የሚሆነው በኢያሱ የህይወት እድሜ ነው፤ ነገር ግን እስራኤላውያን አይደለም በኢያሱ ዘመን ይቅርና በዳዊት ዘመን እንኳን ኢያቡሳውያንን፣ ከነዓናውያንን፣ ኬጢያውያንን፣ አሞራውያንን፣ ፌርዛውያንን፣ ኤዊያውያንን ሊያጠፏቸው፣ ሊያሳድዱአቸውና ሊያስወጣቸው አልተቻላቸውም፤ እነርሱም በዚያ አገር በመቀመጥ ጸኑ፦
ኢያሱ 15:63 በኢየሩሳሌም የተቀመጡትን ኢያቡሳውያንን ግን የይሁዳ ልጆች ሊያሳድዱአቸው አልተቻላቸውም፤ ኢያቡሳውያንም እስከ ዛሬ በይሁዳ ልጆች መካከል በኢየሩሳሌም ውስጥ ተቀምጠዋል።
ኢያሱ 17:12 የምናሴ ልጆች ግን የእነዚህን ከተሞች ሰዎች ሊያሳድዱአቸው አልቻሉም፤ ነገር ግን ከነዓናውያን በዚያ አገር በመቀመጥ ጸኑ። ኢያሱ 17:13 የእስራኤልም ልጆች በጸኑ ጊዜ ከነዓናውያንን የጕልበት ግብር አስገበሩአቸው፥ ፈጽመውም አላሳደዱአቸውም።
መሳፍንት 1:21፤ ነገር ግን በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያንን የብንያም ልጆች አላወጡአቸውም፤ ኢያቡሳውያንም ከብንያም ልጆች ጋር እስከ ዛሬ ድረስ በኢየሩሳሌም ተቀምጠዋል። መሳፍንት 3:5 የእስራኤልም ልጆች በከነዓናውያን በኬጢያውያንም በአሞራውያንም በፌርዛውያንም በኤዊያውያንም በኢያቡሳውያንም መካከል ተቀመጡ። መሳፍንት 19:11 ወደ ኢያቡስም በደረሱ ጊዜ መሸባቸው፥ አሽከሩም ጌታውን። ና፥ ወደዚህ ወደ ኢያቡሳውያን ከተማ፥ እባክህ፥ እናቅና፥ በእርስዋም እንደር አለው። 2ሳሙኤል 5:6፤ ንጉሡና ሰዎቹም በአገሩ ውስጥ ከተቀመጡት ከኢያቡሳውያን ጋር ለመዋጋት ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ፤ እነርሱም። ዳዊት ወደዚህ ሊገባ አይችልም ብለው አስበው ነበርና ዳዊትን። ዕውሮችንና አንካሶችን ካላወጣህ በቀር ወደዚህ አትገባም አሉት።

ትንቢት ሁለት
ምነው በሙሴ በኩል ተነገረ የተባለው ትንቢት መቼ ተፈፀመ? ሰባቱን አሕዛብ ማለትም ኬጢያዊውን፣ ጌርጌሳዊውን፣ አሞራዊውን፣ ከነዓናዊውን፣ ፌርዛዊውን፣ ኤዊያዊውን፣ ኢያቡሳዊውን ሁሉ ፈፅመው ይጠፋሉ የሚል ንግርት መቼ ተፈፀመ?፦ ዘዳግም 11:23-25 እግዚአብሔር እነዚህን አሕዛብ ሁሉ ከፊታችሁ ያወጣል፥ ከእናንተም የሚበልጡትን የሚበረቱትንም አሕዛብ ትወርሳላችሁ። የእግራችሁ ጫማ የምትረግጣት ""ስፍራ ሁሉ ለእናንተ ትሆናለች""፤ ከምድረ በዳም ከሊባኖስም ከታላቁም ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ባሕር ድረስ ዳርቻችሁ ይሆናል። """በእናንተም ፊት ማንም መቆም አይችልም""፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር፥ እርሱ እንደ ተናገራችሁ፥ ማስፈራታችሁን ማስደንገጣችሁንም በምትረግጡአት ""ምድር ሁሉ ላይ ያኖራል""። ዘጸአት 23:23 መልአኬ በፊትህ ይሄዳልና፥ ወደ አሞራውያንም ወደ ኬጢያውያንም ወደ ፌርዛውያንም ወደ ከነዓናውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ኢያቡሳውያንም ያገባሃል፤ እኔም ""አጠፋቸዋለሁ""።
ዘዳግም 20:16-18 ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ ከሚሰጥህ ከእነዚህ አሕዛብ ከተሞች ""ምንም ነፍስ አታድንም""። አምላክህ እግዚአብሔር እንዳዘዘህ ኬጢያዊውን አሞራዊውንም ከነዓናዊውንም ፌርዛዊውንም ኤዊያዊውንም ኢያቡሳዊውንም ""ፈጽመህ ታጠፋቸዋለህ""።
ዘዳግም 9:3፤ አምላክህም እግዚአብሔር እንደሚበላ እሳት ሆኖ በፊትህ እንዲያልፍ ዛሬ እወቅ፤ እርሱ ያጠፋቸዋል፥ በፊትህም ያዋርዳቸዋል፤ እግዚአብሔርም ""እንደ ነገረህ"" አንተ ታሳድዳቸዋለህ፥ ""ፈጥነህም ታጠፋቸዋለህ""

ኬጢያዊውንን፣ ጌርጌሳዊውንን፣ አሞራዊውንን፣ ከነዓናዊውንን፣ ፌርዛዊውንን፣ ኤዊያዊውንን፣ ኢያቡሳዊውንን የእስራኤልም ልጆች ያጠፉአቸው ዘንድ አልቻሉም። ትንቢቱ የት ገባ?፦
1ነገስት 9:20-21 ከእስራኤልም ልጆች ዘንድ ያልነበሩትን ከአሞራውያንና ከኬጢያውያን፥ ከፌርዛውያን፥ ከኤዊያውያንና ከኢያቡሳውያን የቀሩትን፥ ""የእስራኤልም ልጆች ያጠፉአቸው ዘንድ ያልቻሉትን""፥ በኋላቸው የቀሩትን ልጆቻቸውን፥ ሰሎሞን እስከ ዛሬ ድረስ ገባሮች አድርጎ መለመላቸው።

የነህምያ መጽሐፍ ደግሞ ትንቢቱ ተፈፅሟል ይለናል፦
ነህምያ 9:8 ልቡም በፊትህ የታመነ ሆኖ አገኘኸው፤ የከነዓናዊውንና የኬጢያዊውን የአሞራዊውንም የፌርዛዊውንም የኢያቡሳዊውንም የጌርጌሳዊውንም ምድር ለእርሱና ለዘሩ ትሰጥ ዘንድ ""ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረግህ"" አንተም ጻድቅ ነህና ""ቃልህን ፈጸምህ""።


ትንቢት ሶስት
ሕዝ.26:7-9 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና። እነሆ፥ ከሰሜን የነገሥታት ንጉሥ የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን ከፈረሶችና ከሰረገሎች ከፈረሰኞችም ከጉባኤና ከብዙ ሕዝብ ጋር "በጢሮስ" ላይ አመጣለሁ። በሜዳ ያሉትን ሴቶች ልጆችሽን በሰይፍ ይገድላቸዋል፥ አምባም ይሠራብሻል አፈርንም ይደለድልብሻል ጋሻም ያነሣብሻል። ማፍረሻውን በቅጥርሽ ላይ ያደርጋል፥ ግንቦችሽንም በምሳር ያፈርሳል።

በታሪክ ላይ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ጢሮስን ሊያጠፋት ይቅርና ዝንቧን እሽ ብሎ አያውቅም። ነገር ግን ጢሮስን ያጠፋት ከናቡከደነፆር በኃላ በ 332 BC የግሪኩ ንጉሥ ታላቁ እስክንድር ነው። ዋቢ የታሪክ ሙግት ይመልከቱ፦
Joukowsky, M., The Heritage of Tyre, 1992, chapter 2, p. 13

ትንቢት አራት
ኢሳይያስ 7:5-7 ሶርያና ኤፍሬም "የሮሜልዩም ልጅ" ወደ ይሁዳ እንውጣ እናስጨንቀውም፥ እንስበረውም፥ የጣብኤልንም ልጅ እናንግሥበት ብለው ክፋት ስለ መከሩብህ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ""ይህ ምክር አይጸናምና አይሆንም""።

የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ፦ ወደ ይሁዳ እንውጣ እናስጨንቀውም፥ እንስበረውም ብለው ያሉት ምክር እንደማይፀና እና እንደማይሆን ትንቢት ነበረ፤ ግን የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ በአንድ ቀን ከይሁዳ መቶ ሀያ ሺህ ገደለ፤ ትንቢቱ ሳይፈፀም ቀረ፦
2ዜና.28:6፤ የአባቶቻቸውንም አምላክ እግዚአብሔርን ትተው ነበርና የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ በአንድ ቀን ከይሁዳ መቶ ሀያ ሺህ ገደለ፤ ሁሉም ጽኑዓን ነበሩ።

ትንቢት አምስት
ኢሳይያስ 7:14 ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።

ጥያቄአችን ማርያም ልጇን አማኑኤል ብላ ጠርታዋለች ወይ? አሊያም ሌሎች ሰዎች ጠርተው ነበር ወይ? የኢሳይያስ 7፥14 ጥቅሱ የሚለው ብላ ትጠራዋለች ነው፣ ነገር ግን የማቴዎስ ጸሃፊ የሚለው ይሉታል ነው፣ *ትለዋለች* የሚለውን ለውጦ *ይሉታል* የሚለውን ከየት አምጥቶ ነው? ምን አለ ኮፒ ሲደረግ በትክክል ኮፒ ቢደረግ? ማን ነው የተሳሳተው መንፈስ ቅዱስ ወይስ ጸሃፊው? በፍጹም አላህ ባሮቹን የሚደግፍበት ሩህ ቅዱስ አይሳሳትም፦
ማቴዎስ 1፥22-23 በነቢይ ከጌታ ዘንድ፦ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።

ነገር ግን እናት ትለዋለች የተባለው ስም ስሙ ነው፤ ይህንን በእስማኤል ማየት ይቻላል፤ ግን ማርያም ስሙን ኢየሱስ አለችው፦
ዘፍጥረት 16:11 የእግዚአብሔር መልአክም አላት። እነሆ አንቺ ፀንሰሻል፥ ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም እስማኤል ብለሽ ትጠሪዋለሽ፥ እግዚአብሔር መቸገርሽን ሰምቶአልና። ሉቃስ 1:31 እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።
ሉቃስ 2:21 ሊገርዙት ስምንት ቀን በሞላ ጊዜ፥ በማኅፀን ሳይረገዝ በመልአኩ እንደ ተባለ፥ ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ።

ኢንሻላህ ይቀጥላል......

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ገለባ ክስ

የመጨረሻው ክፍል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ትንቢት ስድስት
አይሁዳውያን ማለትም ሁለቱ ነገዶች የቢንያምና የይሁዳ ነገድ በምርኮ ለሰባ ዓመት እንደሚማረኩ እና ሰባው ዓመት ሲፈፀም የባቢሎንን ንጉሥና ያንን ሕዝብ ስለ ኃጢአታቸው እንደሚቃጣ ትንቢት አለ፦
ኤርምያስ 29:10 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና። “”ሰባው ዓመት”” በባቢሎን በተፈጸመ ጊዜ እጐበኛችኋለሁ፥ ወደዚህም ስፍራ እመልሳችሁ ዘንድ መልካሚቱን ቃሌን እፈጽምላችኋለሁ።
ኤርምያስ 25፥12 “ሰባው ዓመትም” በተፈጸመ ጊዜ፥ የባቢሎንን ንጉሥና ያንን ሕዝብ ስለ ኃጢአታቸው እቀጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥
2ኛ ዜና 36፥21 በኤርምያስም አፍ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል እንዲፈጸም፥ ምድሪቱ ሰንበትን በማድረግዋ እስክታርፍ ድረስ በተፈታችበትም ዘመን ሁሉ፥ “ሰባ ዓመት” እስኪፈጸም ድረስ፥ ሰንበትን አገኘች።

ነገር ግን አይሁዳውን በባቢሎን የተማረኩት 605 BC ሲሆን ከምርኮ የተመለሱት እና ባቢሎናውያን የተቀጡት 538 BC ነው። ይህም የምርኮ ዓመት 70 ሳይሆን 67 ነው፤ 605-538=67 ። ታዲያ 3 ዓመት ይቀረው አልነበረምን? ትንቢቱ ትክክል ነውን?

ትንቢት ሰባት
2ኛ ነገሥት 22:18-20 እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ለላካችሁ ለይሁዳ ንጉሥ ግን እንዲህ በሉት፦ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለ ሰማኸው ቃል፥ ልብህ ገር ሆኖአልና፥ እነርሱም ለድንቅና ለመርገም እንዲሆኑ በዚህ ስፍራና በሚኖሩበት ላይ የተናገርሁትን ሰምተህ በእግዚአብሔር ፊት ተዋርደሃልና፥ ልብስህን ቀድደሃልና፥ በፊቴም አልቅሰሃልና እኔ ደግሞ ሰምቼሃለሁ ይላል እግዚአብሔር፦ ስለዚህም ደግሞ ወደ አባቶችህ እሰበስብሃለሁ፥ በሰላምም ወደ መቃብርህ ትሰበሰባለህ፤ በዚህም ስፍራ ላይ የማመጣውን ክፉ ነገር ዓይኖችህ አያዩም። ይህንም ለንጉሡ አወሩለት።

እዚህ ጥቅስ ላይ ኢዮስያስ በሰላም እንደሚሞት ከእግዚአብሔር በነብይ ትንቢት መጥቶለት ነበር፤ ነገር ግን በሰው እጅ ተገድሎ ሞተ፤ ስለዚህ “በሰላምም ወደ መቃብርህ ትሰበሰባለህ፤ በዚህም ስፍራ ላይ የማመጣውን ክፉ ነገር ዓይኖችህ አያዩም” የተባለው ትንቢት አልሰራም ፦
2ኛ ዜና 35:23-24 ቀስተኞችም ንጉሡን ኢዮስያስን “”ወጉት””፤ ንጉሡም ብላቴናዎቹን፦ አጥብቄ “”ቈስያለሁና”” ከሰልፉ ውስጥ አውጡኝ አላቸው። ብላቴኖቹም ከሰረገላው አውርደው ለእርሱ በነበረው በሁለተኛው ሰረገላ ውስጥ አስቀመጡት፥ ወደ ኢየሩሳሌምም አመጡት፤ እርሱም ሞተ፥ በአባቶቹም መቃብር ተቀበረ ይሁዳና ኢየሩሳሌምም ሁሉ ለኢዮስያስ አለቀሱ።

ትንቢት ስምንት
የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም ሲሞት ወዮ! እያሉ አያለቅሱለትም። አህያም እንደሚቀበር ይቀበራል፥ ከኢየሩሳሌምም በር ወደ ውጭ ተጐትቶ ይጣላል እና በዳዊት ዙፋን ላይ ተቀማጭ አይኖርለትም፥ ሬሳውም በቀን ለትኩሳት በሌሊትም ለውርጭ ይጣላል” በማለት አሟሟቱ እንደማያምርና በእርሱ ምትክ በዳዊት ዙፋን ላይ ማንም ተቀማጭ እንደማይኖር ትንቢት ተነገረ፦
ኤርሚያስ 22:18-19 ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ ይላል። ወንድሜ ሆይ፥ ወዮ! እያሉ አያለቅሱለትም፥ ወይም። ጌታ ሆይ፥ ወዮ! እያሉ አያለቅሱለትም። አህያም እንደሚቀበር ይቀበራል፥ ከኢየሩሳሌምም በር ወደ ውጭ ተጐትቶ ይጣላል። ኤርሚያስ 36:30 ስለዚህም ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮአቄም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። በዳዊት ዙፋን ላይ “”ተቀማጭ አይኖርለትም””፥ ሬሳውም በቀን ለትኩሳት በሌሊትም ለውርጭ ይጣላል።

ነገር ግን ኢዮአቄም የተቀበረው ከኢየሩሳሌምም በር ወደ ውጭ ተጐትቶ ሳይሆን ከአባቶቹ ጋር በሰላም አንቀላፍቷል። ልጁም በእርሱ ፋንታ በዙፋኑ ላይ ነገሰ፦
2ኛ ነገሥት 24:6፤ ኢዮአቄምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ልጁም ዮአኪን፤ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
ትንቢት ዘጠኝ
ማቴዎስ 24:2 እርሱ ግን መልሶ፡- ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም አላቸው።

“”ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀር”” ማለት የኢየሩሳሌም ግንብ ይፈርሳል እያለን ነው፤ ግን ይህ ግን በ 66 AD ሆነ የሮሙ ጀነራል ቲቶ በ 70 AD ኢየሩሳሌምን ሲያጋያት ድንጋዩ አልፈረሰም። ይህ ግንብ እስካሁን አለ። ታዲያ ሳይፈርስ አይቀርም የተባለው ሳይፈርስ መቅረቱ ትንቢቱ የት ገባ?

ትንቢት አስር
ማቴዎስ 10:23 በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፥ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም።

ሐዋርያት በትምህርታቸው የእስራኤልን ከተሞች ከመዝለቃቸው በፊት ተመልሶ እንደሚመጣ ነግሯቸዋል፤ ግን እስራኤላውያን የእስራኤልን ከተሞች ዘልቀው ከዚያም ወደ ጠፉት የእስራኤል ቤት ድረስ ሄደው ከዘለቁ እና ከሞቱ ይኸው 2000 ዓመት ሞላቸው። እንዴት ሳይመጣ ቀረ? ጭራሽ ለአይሁዳውያን ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ ብሏቸዋል፦
ማቴዎስ 26:64 ኢየሱስም፡- አንተ አልህ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህ “”የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ”” አለው።

ሲናገራቸው ከነበሩት አይሁዳውያን የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ ያየስ አለን? በሰማይም ደመና ሲመጣ ያየስ አለን?
ትንቢት አስራ አንድ
ዘፍጥረት 4:15 እግዚአብሔርም እርሱን አለው። እንግዲህ ቃየንን የገደለ ሁሉ ሰባት እጥፍ ይበቀልበታል። “”እግዚአብሔርም ቃየንን ያገኘው ሁሉ እንዳይገድለው ምልክት አደረገለት””።

እግዚአብሔርም ቃየንን ያገኘው ሁሉ እንዳይገድለው ምልክት አደረገለት ይለናል። ግን የቃየን የልጅ ልጅ ላሜሕ ገድሎታል፤ ስለዚህ ላሜሕን ግን ሰባ ሰባት እጥፍ ይበቀሉታል፦
ዘፍጥረት 4:23 ላሜሕም ለሚስቶቹ ለዓዳና ለሴላ አላቸው። እናንት የላሜሕ ሚስቶች ቃሌን ስሙ፥ ነገሬንም አድምጡ፤ እኔ “”ጕልማሳውን”” ለቍስሌ፥ ብላቴናውንም ለመወጋቴ “”ገድዬዋለሁና””፤ ቃየንን ሰባት እጥፍ ይበቀሉታል፤ “”ላሜሕን ግን ሰባ ሰባት እጥፍ ይበቀሉታል””።

ታዲያ ያገኘው ሁሉ እንዳይገድለው ምልክት አደረገለት የተባለው ቃል የት ገባ?
ይህንን እና የመሳሰሉት ትንቢት በቁና ማቅረብ ይቻላል፤ ግን በወፍ በረር እነዚህ አስራ አንዱን ጥያቄዎች መልስ ያሻቸዋል፤ ነገሩ አንድ ነብይ ቢታለል የሚያታልለው እርሱ እግዚአብሔር እንደሆነ፣ በነቢያቶቹ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ አድርጎ ክፉ የሚያናግረው እግዚአብሔር እንደሆነ እና በትንቢቱ የሚስተውም ሆነ የሚያስተው ለእግዚአብሔር እንደሆነ ባይብል ይናገራል፦
ሕዝቅኤል 14:9 ነቢዩም “”ቢታለል”” ቃልንም ቢናገር፥ ያንን ነቢይ “”ያታለልሁ”” እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥
ኤርሚያስ 20:7 አቤቱ፥ “”አታለልኸኝ”” እኔም “”ተታለልሁ””፥
ኤርሚያስ 4:10 እኔም። ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ፥ አንተ ሰይፍ እስከ ነፍስ ድረስ በደረሰ ጊዜ። ሰላም ይሆንላችኋል ብለህ ይህን ሕዝብና ኢየሩሳሌምን እጅግ “””አታለልህ”” አልሁ።
1ነገሥት 22:23 መንፈስም ወጣ በእግዚአብሔርም ፊት ቆሞ። እኔ “”አሳስተዋለሁ”” አለ። እግዚአብሔርም። በምን? አለው፤ እርሱም። ወጥቼ “”በነቢያቶቹ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ እሆናለሁ”” አለ። እግዚአብሔርም። ማሳሳትስ ታሳስተዋለህ፥ ይሆንልሃልም፤ ውጣ፥ እንዲሁም አድርግ አለ። አሁንም። እነሆ፥ እግዚአብሔር በእነዚህ በነቢያትህ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ “”አድርጎአል””፤ እግዚአብሔርም “”በላይህ ክፉ ተናግሮብሃል””። ኢዮ.12:16፤ ኃይልና ጥበብ በእርሱ ዘንድ ናቸው፤ የሚስተውና የሚያስተው ለእርሱ ናቸው።

ስለዚህ ትችትና ሻወር የሚጀምረው ከራስ ነው ይላሉ የሎቢ ጀግኖች። ቅድሚያ የባይብል ትንቢት ይፈተሽ።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
አወዛጋቢው ዶክትሪን

ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ የማን ባሪያ ነው?
ክርስቲያኑ፦ "የእግዚአብሔር ባሪያ ነው።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እራሱ የራሱ ባሪያ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "ኖ! የአብ ባሪያ እንጂ የራሱ ባሪያ አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ አብ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "አብ ማን ነው?
ክርስቲያኑ፦ "እግዚአብሔር ነው።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እግዚአብሔር ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አዎ! በትክክል።

ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ የማን ነቢይ ነው?
ክርስቲያኑ፦ "የእግዚአብሔር ነቢይ ነው።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እራሱ የራሱ ነቢይ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "ኖ! የአብ ነቢይ እንጂ የራሱ ነቢይ አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ አብ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "አብ ማን ነው?
ክርስቲያኑ፦ "እግዚአብሔር ነው።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እግዚአብሔር ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አዎ! በትክክል።

ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስን የላከው ማን ነው?
ክርስቲያኑ፦ "እግዚአብሔር።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እራሱ በራሱ ላከው?
ክርስቲያኑ፦ "ኖ! አብ ነው የላከው እንጂ ራሱን በራሱ አላከውም።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ አብ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "አብ ማን ነው?
ክርስቲያኑ፦ "እግዚአብሔር ነው።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እግዚአብሔር ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አዎ! በትክክል።

ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ ሰውነቱ ፍጡር ነው?
ክርስቲያኑ፦ "አዎ!
ሙሥሊሙ፦ "ማን ፈጠረው?
ክርስቲያኑ፦ "እግዚአብሔር።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እራሱ በራሱ ፈጠረው?
ክርስቲያኑ፦ "ኖ! አብ ነው የፈጠረው እንጂ ራሱ እራሱን አልፈጠረውም።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ አብ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "አብ ማን ነው?
ክርስቲያኑ፦ "እግዚአብሔር ነው።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እግዚአብሔር ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አዎ! በትክክል።

ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ ሲጸልይና ሲሰግድ የነበረው ወደ ማን ነው?
ክርስቲያኑ፦ "ወደ እግዚአብሔር።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ ሲጸልይና ሲሰግድ የነበረው ወደ ራሱ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "ኖ! ወደ አብ ነው ሲጸልይና ሲሰግድ የነበረው እንጂ ወደ ራሱ አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ አብ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "አብ ማን ነው?
ክርስቲያኑ፦ "እግዚአብሔር ነው።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እግዚአብሔር ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አዎ! በትክክል።

ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ አምላክ አለው?
ክርስቲያኑ፦ "አዎ!
ሙሥሊሙ፦ "አምላኩ ማን ነው?
ክርስቲያኑ፦ "እግዚአብሔር!
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ ራሱ የራሱ አምላክ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "ኖ! አምላኩ አብ ነው እንጂ ራሱ የራሱ አምላክ አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ አብ ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አይደለም።
ሙሥሊሙ፦ "አብ ማን ነው?
ክርስቲያኑ፦ "እግዚአብሔር ነው።
ሙሥሊሙ፦ "ኢየሱስ እግዚአብሔር ነውን?
ክርስቲያኑ፦ "አዎ! በትክክል።

የዚህ ዶክትሪን መልስ ኅሊና ይቀበለዋልን? መልስ ለኅሊና።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የቁርአን ደራሲ ማን ነው?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡

መግቢያ
ይህ አርስት ሃሳቡ የተወሰደው አላህ ይጠብቀው ከዶክተር ዛኪር ነው፣ አንድ ድርሰት ደራሲው ማን እንደሆነ የሚታወቀው በመግቢያ ላይ አሊያም በሽፋኑ ላይ ስሙ መጠቀሱ ነው፣ ነገር ግን የቁርአን ደራሲ ግን ማን እንደሆነ የሚታወቀው ደራሲው በመጽሐፉ ውስጥ እራሱ ብቻ መናገሩና ያ ደራሲው የማንንም ቃል አለማስገባቱ ነው፣ የቁርአን ባለቤት አላህ ነው፣ ቁርአንን ሆነ የቁርአንን ሱራና አንቀጽ ያወረደው እራሱ አላህ ነው፦
15:9 እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡
76:23 እኛ ቁርአንን ባንተ ላይ ማውረድን እኛው አወረድነው።
39:41 እኛ መጽሐፉን ባንተ ላይ ለሰዎች ጥቅም በእውነት አወረድነው፤
2:23 በባሪያችንም ላይ ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትኾኑ ከብጤው አንዲትን ምዕራፍ አምጡ፡፡
24:1 ይህች ያወረድናትና የደነገግናት ምዕራፍ ናት፣ በርሷም ውስጥ ትገሠጹ ዘንድ ግልጾችን አንቀጾች አውርደናል።
24:46 አብራሪን አንቀጾች በእርግጥ አወረድን፤

ነቢያችን ላይ የሚደርሰው የቃላት መሳለቅ ማለትም ቀጣፊ ነው ሲሉ ቀጣፊ አይደለም፣ ድግምተኛ ነው ሲሉ ድግምተኛ አይደለም፣ ጠንቋይ ነው ሲሉ ጠንቋይ አይደለም ፣ እብድ ነው እብድ አይደለም ብሎ መልስ የሚሰጠው ኃላፊነቱን ወስዶ አላህ እራሱ ነው፦
15:94-95 የታዘዝክበትንም ነገር በይፋ ግለጽ፣ አጋሪዎችንም ተዋቸው፣ ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንሃል፡፡
32:3 ይልቁንም ቀጠፈው ይላሉን? አይደለም፤ እርሱ ከጌታህ ዘንድ የኾነ እውነት ነው፤
52:29 ሰዎችን አስታውስም፤ አንተም በጌታህ ጸጋ ምክንያት ጠንቋይም ዕብድም አይደለህም።
81:22 ነቢያችሁ በፍጹም ዕብድ بِمَجْنُونٍ አይደለም።

ነጥብ አንድ
ቁርአን ዓለም-ዓቀፋዊ መልዕክት ነው፦
38:87 «እርሱ ቁርኣን ለዓለማት መገሠጫ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡
25:1 ያ ፉርቃንን በባሪያው ላይ፣ ለዓለማት አስጠንቃቂ ይሆን ዘንድ፣ ያወረደው አምላክ፣ ክብርና ጥራት ተገባው።
6:19 ይህም ቁርኣን እናንተንና የደረሰውን ሰው ሁሉ በርሱ ላስጠነቅቅበት ወደኔ ተወረደ፡፡ ከአላህ ጋር ሌሎች አማልክት መኖራቸውን እናንተ ትመሰክራላችሁን» በላቸው፡፡

ቁርአን ለአንድ ብሔር ቢወርድ ኖሮ ያንን የወረደበት ብሔር ብልጫ ይሰጥ ነበር ነገር ግን የቁርአኑ ደራሲ አላህ በመሆኑ አላህ በዓለማት ላይ ያበለጠው የአረቡን ብሔር ሳይሆን የእስራኤልን ልጆች ነው፦
2:47 የእስራኤል ልጆች ሆይ! ያችን በናንተ ላይ የለገስኳትን ጸጋዬንና እኔም በዓለማት ላይ ያበለጥኳችሁ መኾኔን አስታውሱ፡፡
2:122 የእስራኤል ልጆች ሆይ! ያችን በናንተ ላይ የለገስኳትን ጸጋዬንና እኔም በዓለማት ላይ ያበለጥኳችሁ መኾኔን አስታውሱ፡፡
ነጥብ ሁለት
ነቢያችን ዓለም-ዓቀፋዊ መልዕክተኛ ናቸው ፦
21:107 ለዓለማትም እዝነት አድርገን እንጅ አልላክንህም።
7:158 በላቸው፦እላንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ወደ እናንተ ወደሁላችሁም የአላህ መልክተኛ ነኝ፤
34:28 አንተንም ለሰዎች ሁሉ በመላ፣ አብሳሪና አስጠንቃቂ አድርገን ቢሆን እንጂ አልላክንህም፤
4:79 ለሰዎችም ሁሉ መልክተኛ ኾነህ ላክንህ መስካሪም በአላህ በቃ።

የቁርአኑ ደራሲ ነቢያችን ቢሆኑ ኖሮ የእናታቸውን ስም አሚናን አሊያም የራሳቸውን ስም በስፋት ያስገቡ ነበር፣ ነገር ግን የቁርአኑ ደራሲ አላህ ስለሆነ መርየምንና ልጅዋን ለዓለማት ታምር አድርጓል፦
3:42 መላእክትም ያሉትን አስታዉስ – መርየም ሆይ! አላህ በእርግጥ መረጠሽ፣ አነጻሽም፣ በዓለማት ሴቶችም ላይ መረጠሽ።
21:91 ያችንም ብልቷን የጠበቀቺውን፣ በርሷም ውስጥ ከመንፈሳችን የነፋንባትን እርስዋንም ልጅዋንም እንደዚሁ፣ ለዓለማት ታምር ያደረግናትን፣ መርየምን፣ አታውስ።

ነጥብ ሶስት
ዓለም-ዓቀፋዊ አንድነት፦
49:13 እላንተ ሰዎች ሆይ እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፤ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፤ አላህ ዘንድ በላጫችሁ፣ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፤ አላህ ግልጽን ዐዋቂ፣ ውስጥንም ዐዋቂ ነው።
3:103 የአላህንም የማመን ገመድ ሁሉችሁም ያዙ፤ አትለያዩም፤ ጠበኞችም በነበራችሁ ጊዜ በናንተ ላይ የዋለዉን የአላህን ጸጋ አስታውሱ፤ በልቦቻችሁም መካከል አስማማ፤ በጸጋዉም ወንድማማቾች ሆናችሁ፤

የአላህንም የማመን ገመድ ሰዎችን ሁሉ በጾታ፣ በብሔር፣ በቀለም፣ በዘር፣ በቋንቋ ሳይለያይ የሚያስተሳስር የአላህ ዲን ነው፣ አላህ ዘንድ በላጩ ሰው ሙጠቂን ባሪያ እንጂ ጾታ፣ ብሔር፣ ቀለም፣ ዘር፣ ቋንቋ አይደለም፣ የቁርአኑ ደራሲ የሰው ልጆችን ከአዳምና ከሔዋን የፈጠረው አላህ ነው፦
4:1 እላንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ (ከአዳም) የፈጠራችሁን፣ ከእርስዋም መቀናጆዋን (ሔዋንን) የፈጠረውን፣ ከነርሱም ብዙ ወንዶችንና ሴቶችን የበተነውን፣ ጌታችሁን ፍሩ።
7:189 እርሱ ያ ከአንዲት ነፍስ (ከአደም) የፈጠራችሁ ከርሷም መቀናጆዋን ወደርሷ ይረካ ዘንድ ያደረገ ነው።
39:6 ከአንዲት ነፍስ ፈጠራችሁ፤ ከዚያም ከርሷ መቀናጆዋን አደረገ።
6:98 እርሱም ያ ከአንዲት ነፍስ ያስገኛችሁ፤ ነው፡፡