ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
69 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
መስቀል

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

41፥37 ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ ለፀሐይና ለጨረቃ “አትስገዱ”፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው አላህ “ስገዱ” ፡፡ እርሱን ብቻ “የምታመልኩ” እንደ ኾናችሁ *”ለሌላ አትስገዱ”*፡፡

“ሡጁድ” سُّجُود የሚለው ቃል የዐረቢኛው ቃል“ሠጀደ” سَجَدَ ማለት “ሰገደ” ወይም “ታዘዘ” ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን “ስግደት” ወይም “መታዘዝ” ማለት ነው፤ ሡጁድ ደግሞ በሁለት ይከፈላል፦ አንዱ “ሡጁዱል ዒባዳ” سُّجُود العبادة ማለትም “የአምልኮ ስግደት” ሲሆን ሌላው “ሡጁዱ አተሒያ” سُّجُود التحيه ማለትም “የአክብሮት ስግደት” ነው፤ ነገር ግን ይህ አክብሮት አቅጣጫውን ቀይሮ አምልኮ እየሆነ ስላለ ከሰላምታ ውጪ በሱጁድ ለፍጡራን ማጎብደድ፣ መተናነስ፣ ማሸርገድ ቁርአን ሲወርድ ቆሟል፤ የአክብሮት ስግደት ከአምልኮ ስግደት ጋር እንዳይደባለቅ የተከለከለው በነብያችን”ﷺ” ጊዜ ነው፤ አላህም ሁሉን ለፈጠረው ለእርሱ እንጂ ለሌላ አትስገዱ ብሎናል፤ ከአላህ ሌላ የሚገዙት ግኡዛን ነገር የገሀነም ማገዶዎች ናቸው፦
41፥37 ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ ለፀሐይና ለጨረቃ “አትስገዱ”፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው አላህ “ስገዱ” ፡፡ እርሱን ብቻ “የምታመልኩ” እንደ ኾናችሁ *”ለሌላ አትስገዱ”*፡፡
21፥8 እናንተ ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውም የገሀነም ማገዶዎች ናችሁ፡፡ እናንተ ለእርሷ ወራጆች ናችሁ إِنَّكُمْ وَمَا تَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ حَصَبُ جَهَنَّمَ أَنتُمْ لَهَا وَٰرِدُونَ ፡፡

ማገዶዎች በሚለው ቃላት “ማ” َمَا የሚለው አንፃራዊ ተውላጠ-ስም አቅል የሌላቸውን ጣኦታት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፤ አቅል ያላቸውን ማንነቶች “መን” مَّن የሚል አንፃራዊ ተውላጠ-ስም የሚጠቀመው፤ ግን እዚህ አንቀፅ ላይ “ማ” የሚል አንፃራዊ ተውላጠ-ስም መጠቀሙ አቅል የሌላቸውን ጣኦታት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፤ ከአላህ ውጪ የሚደረግ ባዕድ አምልኮ “ጣጉት” لطَّاغُوتِ ይባላል፤ ይህም ጣዖት በሁለት ይከፈላል፤ አንዱ “አውሳን” أَوْثَٰن ሲሆን ሁለተኛው “አስናም” أَصْنَام ነው፤ “አውሳን” ማለት ከድንጋይ ተቀርፀው አምልኮ ለሚቀርብላቸው ሲሆን፤ “አስናም” ደግሞ ከእንጨት፣ ብር፣ ነሐስ ተሰርተው አምልኮ ለሚቀርብላቸው ነው፤ እነዚህ ሁለቱም በቁርአን ተጠቅሰዋል፦
1.”አውሳን”
29:17 ከአላህ ሌላ የምታመልኩት “ጣዖታትን” أَوْثَانًا ብቻ ነው፤ ውሸትንም ትቀጣጥፋላችሁ፤ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምታመልኩአቸው ለእናንተ ሲሳይን ሊሰጧችሁ አይችሉም፤
2. “አስናም”
6:74 ኢብራሒምም ለአባቱ ለአዘር “ጣዖታትን” أَصْنَامًا አማልክት አድርገህ ትይዛለህን እኔ አንተንም ሕዝቦችህንም በግልጽ መሳሳት ውስጥ ኾናችሁ አያችኋለሁ» ባለ ጊዜ አስታውስ።
ወደ ባይብል ስንመጣ “ስግደት” የሚለው ቃል በዕብራይስጥ “ሻኻህ” שָׁחָה ሲሆን በግሪክ ደግሞ “ፕሩስኩኔኦ” προσκυνέω ይባላል፤ ይህም ለተለያየ ምንነት ሆነ ማንነት በኒያ”intention” የሚቀርብ አምልኮን”Adoration” ወይም አክብሮትን”prostration” ነው ለማመልከት በባይብል ተጠቅሞበታል፤ የአምልኮት ስግደት በባህርይ የአንድ አምላክ ሃቅና ገንዘብ ሲሆን የአክብሮት ስግደት ደግሞ በፀጋ ለህያዋን ማንነት ማክበርን ያመለክታል፤ ግን ለግኡዛን ነገሮች አምልኮም ይሁን ስግደት ተከልክሏል፤ በዕብራይስጥ “ኤሊል” אֱלִיל ማለት “ምስል”፣ “ቅርፅ”፣ “ጣዖት” ማለት ሲሆን በግሪክ ደግሞ “ኤዶሎን” εἴδωλον ነው፤ ትርጉሙ ተመሳሳይ ነው። የሙሴ አምላክ ለሙሴ “”ለእናንተ ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ፣ የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፣ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም”” ብሎ ተናግሯል፤ እንደውም ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ ይፈሩ ይላል፦
ዘሌዋውያን 26፥1 እኔ ያህዌህ አምላካችሁ ነኝና ለእናንተ *”ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ”*፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ።
ዘጸአት 20፥4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር *”የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፤ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም”*፤
መዝሙር 97፥7 *”ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ፥ በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ*”፤ መላእክቱ ሁሉ ስገዱለት።

ታዲያ ነጥብህ ምንድን ነው? ከመስቀል ጋር ምን የሚያገናኘው ነገር አለ? ትሉ ይሆናል፤ መስቀል እኮ በሃውልት ድንጋይ፣ እንጨት፣ ወርቅ፣ ብር፣ ብረት፣ ነሐስ ወዘተ ነው፤ ይህ ግኡዝ ነገር በአበይት ክርስቲያኖች ይሰገድለታል ምስጋና ይቀርበለታል፤ ይህ በተግባር ሲሆን በጽሑፍ የዘወትር ፀሎት ላይ ደግሞ እንዲህ ይነበባል፦
ግዕዙ፦
“እሰግድ “ለ”መስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተቀደሰ በደሙ ክቡር”
ትርጉም፦
“ዓለምን ለማዳን ሲል ኢየሱስ ክርስቶስ “ለ”ተሰቀለበት መስቀል እሰግዳለው”
ግዕዙ፦
“ስብሐት “ለ”መስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ በምህረቱ ይዘከረነ”
ትርጉም፦
” “ለ”ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ምስጋና ይገባዋል”

ምን ትፈልጋለህ? “ለ”ተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ ይፈሩ እየተባለ ለምንድን ነው ለግኡዝ ነገር የፀጋ ስግደት የሚሰገድለት? ምስጋናስ የሚቅብለት የሚሰማበት ዐቅል የት አለውና ነው? መስቀል መሳለም ሆነ በመስቀል ማሳለም የትኛው ነብይና ሃዋርያ አደረገስ አድርጉስ አለ? እኔስ ኢሳይያስ የተናገረው ትንቢት ትዝ አለኝ፦
ኢሳይያስ 44፥15-19 ለሰውም ማገዶ ይሆናል፤ ከእርሱም ወስዶ ይሞቃል፥ አንድዶም እንጀራ ይጋግርበታል፤ ከእርሱም አምላክ አበጅቶ ይሰግድለታል፥ የተቀረጸውንም ምስል ሠርቶ በእርሱ ፊት ይንበረከካል። ግማሹን በእሳት ያቃጥላል፥ በዚያ በግማሹ ሥጋ ይበላል፥ ሥጋም ይጠብስበትና ይጠግባል፤ ይሞቃልና፦ እሰይ ሞቅሁ፥ እሳቱን አይቻለሁ ይላል። የቀረውንም እንጨት አምላክ አድርጎ ምስል ይቀርጽበታል፤ በፊቱም ተጐንብሶ ይሰግዳል ወደ እርሱም እየጸለየ፦ አምላኬ ነህና አድነኝ ይላል። አያውቁም፥ አያስቡም፤ እንዳያዩ ዓይኖቻቸውን፥ እንዳያስተውሉ ልቦቻቸውን ጨፍነዋል። በልቡም ማንም አያስብም፦ ግማሽዋን በእሳት አቃጥያለሁ፥ በፍምዋም ላይ እንጀራን ጋግሬአለሁ፥ ሥጋም ጠብሼ በልቻለሁ፤ የቀረውንም አስጸያፊ ነገር አደርጋለሁን? ለዛፍስ ግንድ እሰግዳለሁን? እንዲልም እውቀትና ማስተዋል የለውም።

ከአላህ በቀር የምትጠሯቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፤ እራሳቸውንም አይረዱምና ወደ አላህ በንስሃ ተመለሱ፦
7፥197 እነዚያም ከእርሱ በቀር የምትጠሯቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፤ እራሳቸውንም አይረዱም وَٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِهِۦ لَا يَسْتَطِيعُونَ نَصْرَكُمْ وَلَآ أَنفُسَهُمْ يَنصُرُونَ ፡፡

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለመስቀሉ መቃጠል አደረሳችሁ።

ይህም በዓል መስቀል የማቃጠል በዓል ነውና፣ የምታምኑበት እና የምትሰግዱለት መስቀል ሃይል ነው፣ መድህን ነው፣ ቤዛ ነው የምትሉለትን መስቀል ማቃጠላችሁ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ፣ ምክንያቱም ከእንጨት፣ ከብር፣ ከወርቅ የተሰራ ማንኛውም ምስል መቃጠል አለበት፦
ዘዳግም 12፥3 መሠዊያቸውንም አፍርሱ፥ ሐውልቶቻቸውንም ሰባብሩ፥ የማምለኪያ ዐፀዶቻቸውንም በእሳት አቃጥሉ፥ የአማልክቶቻቸውንም የተቀረጹ ምስሎች አንከታክቱ፤
ዘዳግም 7፣25 የተቀረጸውንም የአምላኮቻቸውን ምስል በእሳት ታቃጥላለህ፤ የተሠራባቸውን ብርና ወርቅ አትመኝ፤ በአምላክህም በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነውና እንዳትጠመድበት ከእርሱ ምንም አትውሰድ።

መቃጠል ያለበት ምክንያት የማንንም ምስል ማድረግ የተከለከለ ስለሆነ ነው፦
ዘጸአት 20፥4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ።
ዘዳግም 5፥8 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፤
ኢሳይያስ 44፥17 የቀረውንም እንጨት አምላክ አድርጎ ምስል ይቀርጽበታል፤ በፊቱም ተጐንብሶ ይሰግዳል ወደ እርሱም እየጸለየ፦ አምላኬ ነህና አድነኝ ይላል።
ኢሳይያስ 45፥20 እናንተ ከአሕዛብ ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ፥ ተሰብስባችሁ ኑ በአንድነትም ቅረቡ፤ የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት የሚሸከሙና ያድን ዘንድ ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ እውቀት የላቸውም።

መስቀልን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ምስል ማቃጠል ይልመድባችሁ፣ የማቃጠሉ በዓል ከአመታዊ ወደ ወራዊ አሊያም ቀናዊ እንዲሆን በትህትና እጠይቃለው።
በመስቀሉ ላይ ያለው እባብ ከፓጋኑ ሰይጣን ጋር ምን ያህል እንደሚመሳሰል ተመልከቱ። የኦርቶዶክስን ገድላት እና ድርሳናት ጉድ ለማየት በቴሌግራም ያግኙን https://tttttt.me/orthox
ሲሯጥ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

19፥71 *ከእናንተም ወደ እርሷ ወራጅ እንጂ አንድም የለም፡፡ መውረዱም ጌታህ የፈረደው ግዴታ ነው*፡፡ ከዚያም *እነዚያን የተጠነቀቁትን እናድናለን፡፡ በደለኞችንም የተንበረከኩ ኾነው በውስጧ እንተዋቸዋለን*፡፡ وَإِن مِّنكُمْ إِلَّا وَارِدُهَا ۚ كَانَ عَلَىٰ رَبِّكَ حَتْمًا مَّقْضِيًّا ثُمَّ نُنَجِّي الَّذِينَ اتَّقَوا وَّنَذَرُ الظَّالِمِينَ فِيهَا جِثِيًّا

“ዒሊዪን” عِلِّيِّين “ማለት “ከፍተኛ” ወይም “አርያም” ማለት ሲሆን “ዐሊየት” عَالِيَة ማለት ደግሞ “ከፍተኛይቱ” ማለት ነው፤ የምእምናን መጽሐፍ በእርግጥ በዒሊዮን ውስጥ ነው፦
88፥10 *በከፍተኛ ገነት* ውስጥ ናቸው፡፡ فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٍ
69፥22 *በከፍተኛይቱ ገነት* ውስጥ፡፡ فِي جَنَّةٍ عَالِيَةٍ
83፥18 በእውነቱ *የእውነተኞቹ ምእምናን መጽሐፍ በዒሊዮን ውስጥ ነው*፡፡ كَلَّا إِنَّ كِتَابَ الْأَبْرَارِ لَفِي عِلِّيِّينَ

“ሢጂን” سِجِّين የሚለው ቃል “ዩሥጀነ” يُسْجَنَ ማለትም “ታሰረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “እስር” ወይም “እንጦሮጦስ” ማለት ነው፤ “ሠጅን” سِّجْن ማለት “መታሰር” ማለት ሲሆን “መሥጁኒን” مَسْجُونِين ደግሞ “እስረኞች” ማለት ነው፤ የከሓዲዎቹ መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው፦
83፥7 በእውነት *የከሓዲዎቹ መጽሐፍ በእርግጥ በሲጂን ውስጥ ነው*፡፡ كَلَّا إِنَّ كِتَابَ الْفُجَّارِ لَفِي سِجِّينٍ

“ሲሯጥ” صِرَٰط በጀነት እና በጀሀነም መካከል ያለ “ድልድይ” ነው፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 81 , ሐዲስ 124
አቢ ሠዒድ አል-ኹድሪይ”ረ.ዐ.” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ “ምእመናን ከእሳት ይድናሉ፤ በጀነትን እና በጀሃነም መካከል ድልድይ ይቆማል። قَالَ حَدَّثَنَا سَعِيدٌ عَنْ قَتَادَةَ عَنْ أَبِي الْمُتَوَكِّلِ النَّاجِيِّ أَنَّ أَبَا سَعِيدٍ الْخُدْرِيَّ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ يَخْلُصُ الْمُؤْمِنُونَ مِنَ النَّارِ، فَيُحْبَسُونَ عَلَى قَنْطَرَةٍ بَيْنَ الْجَنَّةِ وَالنَّارِ،

ሁሉም የሰው ልጆች ወደዚያ ድልድይ ወራጅ እንጂ አንድም የለም፤ መውረዱም ጌታህ የፈረደው ግዴታ ነው፤ ከዚያም እነዚያን የተጠነቀቁትን ይድናሉ፤ በደለኞችንም ግን የተንበረከኩ ኾነው ተንሸራተው በጀሃነም ይተዋሉ፦
19፥71 *ከእናንተም ወደ እርሷ ወራጅ እንጂ አንድም የለም፡፡ መውረዱም ጌታህ የፈረደው ግዴታ ነው*፡፡ ከዚያም *እነዚያን የተጠነቀቁትን እናድናለን፡፡ በደለኞችንም የተንበረከኩ ኾነው በውስጧ እንተዋቸዋለን*፡፡ وَإِن مِّنكُمْ إِلَّا وَارِدُهَا ۚ كَانَ عَلَىٰ رَبِّكَ حَتْمًا مَّقْضِيًّا ثُمَّ نُنَجِّي الَّذِينَ اتَّقَوا وَّنَذَرُ الظَّالِمِينَ فِيهَا جِثِيًّا
ነጥብ አንድ
“ሲሯጥ”
በሱረቱል መርየም 19፥71 ላይ “ሃ” ُهَا ማለትም “እርሷ” የሚለው ሦስተኛ መደብ ተሳቢ ተውላጠ-ስም ”ሲሯጥ” መሆኗን ነብያችን”ﷺ” ነግረውናል፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 44, ሐዲስ 235
በሃፍሳ ፊት ከነብዩ”ﷺ” ሰምታ ኡሙ ሙበሽር እንደተረከችው፦ ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ “በአላህ ፈቃድ የጀነት ባለቤቶች በዚያው መሠረት ታማኝነታቸውን ከሚቀበሉት መካከል ወደ እሳት አይገቡም። ሃፍሳም የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሆይ! ለምን?
ብላ ጠየቀቻቸው፤ እርሳቸውም ገሰጿት፤ እርሷም፦ “ከእናንተም ወደ ድልድይ ወራጅ እንጂ አንድም የለም” አለች፤ ነብዩን”ﷺ”፦ “የላቀውና ክብራማው አላህ፦ “ከዚያም እነዚያን የተጠነቀቁትን እናድናለን፡፡ በደለኞችንም የተንበረከኩ ኾነው በውስጧ እንተዋቸዋለን” ብሏል፤ አሉ። يَقُولُ أَخْبَرَتْنِي أُمُّ مُبَشِّرٍ، أَنَّهَا سَمِعَتِ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ عِنْدَ حَفْصَةَ ‏”‏ لاَ يَدْخُلُ النَّارَ إِنْ شَاءَ اللَّهُ مِنْ أَصْحَابِ الشَّجَرَةِ أَحَدٌ ‏.‏ الَّذِينَ بَايَعُوا تَحْتَهَا ‏”‏ ‏.‏ قَالَتْ بَلَى يَا رَسُولَ اللَّهِ ‏.‏ فَانْتَهَرَهَا فَقَالَتْ حَفْصَةُ ‏{‏ وَإِنْ مِنْكُمْ إِلاَّ وَارِدُهَا‏}‏ فَقَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ قَدْ قَالَ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ ‏{‏ ثُمَّ نُنَجِّي الَّذِينَ اتَّقَوْا وَنَذَرُ الظَّالِمِينَ فِيهَا جِثِيًّا‏}‏
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 17, ቁጥር 1475
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ እንደተረከው፤ የአላህ መልክተኛ”ﷺ” አሉ፦ “ሰዎች ወደ ድልድል ይወርዳሉ፤ ከዚያም ከእርሷ በሥራቸው ይወጣሉ። Narrated Abdullah ibn Mas’ud
Allah’s Messenger (peace be upon him) said, “mankind will go down to bridge and then come up from it because of their deeds.
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 37, ሐዲስ 4420
“ዓኢሻ”ረ.ዐ.” ስትናገር እንደተረከችው፦ እኔ የአላህን መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ስል ጠየኳቸው፦ “ምድር በሌላ ምድር የምትለወጥበትን ሰማያትም እንደዚሁ አንድ አሸናፊ ለኾነው አላህም ፍጡራን ሁሉ የሚገለጹበት ቀን አስታውሱ” የሚል አለ፤ ታዲያ የዚያ ቀን ሰዎች የት ይሆናሉ? እርሳቸውም፦ “በድልድይ ላይ” ሲሉ መለሱ። حَدَّثَنَا أَبُو بَكْرِ بْنُ أَبِي شَيْبَةَ، حَدَّثَنَا عَلِيُّ بْنُ مُسْهِرٍ، عَنْ دَاوُدَ، عَنِ الشَّعْبِيِّ، عَنْ مَسْرُوقٍ، عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ سَأَلْتُ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ عَنْ قَوْلِهِ ‏{يَوْمَ تُبَدَّلُ الأَرْضُ غَيْرَ الأَرْضِ وَالسَّمَوَاتُ ‏}‏ فَأَيْنَ تَكُونُ النَّاسُ يَوْمَئِذٍ قَالَ ‏”‏ عَلَى الصِّرَاطِ ‏”‏

“ዐላ” ﻋَﻠَﻰٰ ማለት “ላይ”over” ማለት ነው፤ እንጂ ውስጥ ማለት አይደለም፤ ሲቀጥል “መውረድስ” ማለት “መግባት” ብቻ ነው ያለው ማን ነው? ውሃ ቀጂዎች ወደ ውሃ ኩሬ “ወረዱ” ማለት ውሃ ውስጥ ገቡ ማለት ነውን? አይደለም፦
12:19 *መንገደኞችም መጡ፡፡ ውሃ ቀጂያቸውንም ላኩ*፡፡ አኮሊውንም ወደ ጉድጓዱ ሰደደ «የምስራች! ይህ ወጣት ልጅ ነው» አለ፡፡ ሸቀጥ አድርገውም ደበቁት፡፡ አላህም የሚሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡ وَجَاءَتْ سَيَّارَةٌ فَأَرْسَلُوا وَارِدَهُمْ فَأَدْلَىٰ دَلْوَهُ ۖ قَالَ يَا بُشْرَىٰ هَـٰذَا غُلَامٌ ۚ وَأَسَرُّوهُ بِضَاعَةً ۚ وَاللَّهُ عَلِيمٌ بِمَا يَعْمَلُونَ
28:23 *ወደ መድየንም ውሃ በወረደ* ጊዜ በእርሱ ላይ ከሰዎች ጭፍሮችን መንጋዎቻቸውን የሚያጠጡ ሆነው አገኘ፡፡ وَلَمَّا وَرَدَ مَاءَ مَدْيَنَ وَجَدَ عَلَيْهِ أُمَّةً مِّنَ النَّاسِ يَسْقُونَ وَوَجَدَ مِن دُونِهِمُ امْرَأَتَيْنِ تَذُودَانِ ۖ قَالَ مَا خَطْبُكُمَا ۖ قَالَتَا لَا نَسْقِي حَتَّىٰ يُصْدِرَ الرِّعَاءُ ۖ وَأَبُونَا شَيْخٌ كَبِيرٌ

በተመሳሳይ ሰዎች ወደ ሲሯጥ ወረዱ ማለት ጀሃነም ገቡ ማለት አይደለም።
ነጥብ ሁለት
“ሙተቂን”
“ሙተቂን” ﻣُﺘَّﻘِﻴﻦ ማለት አላህን የሚፈራ “ፈሪሃ” ነው፤ አላህ ሁሉን ያየናል ብለው ከመጥፎ ድርጊት፣ ሁሉን ይሰማናል ብለው ከመጥፎ ንግግር፣ ሁሉን ያውቃል ብለው ከመጥፎ ሃሳብ የሚጠነቀቁ ሲሆን አላህ ከጀሃነም ያድናቸዋል፦
78:31 *ለጥንቁቆቹ መዳኛ ስፍራ አላቸው*። إِنَّ لِلْمُتَّقِينَ مَفَازًا
19፥72 ከዚያም *እነዚያን የተጠነቀቁትን እናድናለን*፡፡ በደለኞችንም የተንበረከኩ ኾነው በውስጧ እንተዋቸዋለን፡፡ ثُمَّ نُنَجِّي الَّذِينَ اتَّقَوا وَّنَذَرُ الظَّالِمِينَ فِيهَا جِثِيًّا

አላህ ጀነትን ያዘጋጀው ሙተቂን ለሚባሉት ባሮቹ ነው፦
3፥133 *ከጌታችሁ ወደ ኾነችም ምሕረትና ስፋትዋ እንደ ሰማያትና ምድር ወደ ኾነች ገነት ለጥንቁቆቹ የተዘጋጀች ስትኾን ተቻኮሉ*፡፡ وَسَارِعُوا إِلَىٰ مَغْفِرَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ وَجَنَّةٍ عَرْضُهَا السَّمَاوَاتُ وَالْأَرْضُ أُعِدَّتْ لِلْمُتَّقِينَ
68:34 “ለጥንቁቆቹ” በጌታቸው ዘንድ መጠቀሚያ ገነቶች አሏቸው። إِنَّ لِلْمُتَّقِينَ عِندَ رَبِّهِمْ جَنَّاتِ النَّعِيمِ
44፥51 ጥንቁቆቹ በእርግጥ በጸጥተኛ መኖሪያ ውስጥ ናቸው፡፡ إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي مَقَامٍ أَمِينٍ
77:41 ጥንቁቆቹ በጥላዎችና በምንጮች ውስጥ ናቸው፡፡ إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي ظِلَالٍ وَعُيُونٍ
38፥49 ይህ መልካም ዝና ነው፡፡ *ለጥንቁቆቹ በእርግጥ ውብ የኾነ መመለሻ አላቸው*፡፡ هَـٰذَا ذِكْرٌ ۚ وَإِنَّ لِلْمُتَّقِينَ لَحُسْنَ مَآبٍ

ስለዚህ ሙስሊሞች ሁሉ ገሃነም ይገባሉ የሚለው ፕሮፓጋንዳ ከጥራዝ-ነጠቅ ዕውቀት የሚመጣ ጥያቄ ነው፤ የሙስሊሞችማ እጣ ፈንታ ጀነት እንደሆነ በግልፅና በማያሻማ መልኩ ተቀምጧል፦
4:124 *ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ ከበጎ ሥራዎች አንዳችን የሚሠራም ሰው እነዚያ ገነትን ይገባሉ፡፡ በተምር ፍሬ ላይ ያለችን ነጥብ ያክል እንኳ አይበደሉም*፡፡ وَمَن يَعْمَلْ مِنَ الصَّالِحَاتِ مِن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُولَـٰئِكَ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ وَلَا يُظْلَمُونَ نَقِيرًا
40:40 *እርሱ አማኝ ሆኖ ከወንድ ወይም ከሴት በጎን የሠራም ሰው እነዚያ ገነትን ይገባሉ፤ በእርሷ ውስጥ ያለ ቁጥጥር ይመገባሉ*። مَنْ عَمِلَ سَيِّئَةً فَلَا يُجْزَىٰ إِلَّا مِثْلَهَا ۖ وَمَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُولَـٰئِكَ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ يُرْزَقُونَ فِيهَا بِغَيْرِ حِسَابٍ
43፥69-70 *እነዚያ በአንቀጾቻችን ያመኑ እና ፍጹም ታዛዦች የነበሩ «ገነትን ግቡ* እናንተም ጥንዶቻችሁም ትደሰታላችሁ ትከበሩማላችሁ» ይባላሉ፡፡ الَّذِينَ آمَنُوا بِآيَاتِنَا وَكَانُوا مُسْلِمِينَ ادْخُلُوا الْجَنَّةَ أَنتُمْ وَأَزْوَاجُكُمْ تُحْبَرُونَ

እዚህ ላይ “ታዛዦች” ለሚለው ቃል የተቀመጠው “ሙስሊሚን” مُسْلِمِينَ ነው፤ “ገነት ግቡ” የሚባሉት ሙስሊሚን እንደሆኑ ልብ አድርግ።
ነጥብ ሦስት
“ዛሊም”
“ዛሊም” ﻇَﺎﻟِﻢ ማለት “በዳይ” ማለት ሲሆን በአላህ ላይ ሌላ ሃልዎትንና ኑባሬን ማጋራት ትልቁ በደል ነው፤ አላህ በደለኞቹንም የተንበረከኩ ኾነው በእሳት ውስጥ ይተዋቸዋል፦
31፥13 ሉቅማንም ለልጁ እርሱ የሚገስጸው ሲሆን፦ ልጄ ሆይ! *በአላህ አታጋራ፤ ማጋራት ታላቅ በደል ነውና* ያለውን አስታውስ። وَإِذْ قَالَ لُقْمَانُ لِابْنِهِ وَهُوَ يَعِظُهُ يَا بُنَيَّ لَا تُشْرِكْ بِاللَّهِ ۖ إِنَّ الشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ
4፥30 ወሰን በማለፍ እና *በመበደልም ይህንን የሠራ ሰው እሳትን እናገባዋለን*። ይኸም በአላህ ላይ ገር ነው፡፡ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ عُدْوَانًا وَظُلْمًا فَسَوْفَ نُصْلِيهِ نَارًا ۚ وَكَانَ ذَٰلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرًا
19፥72 ከዚያም እነዚያን የተጠነቀቁትን እናድናለን፡፡ *በደለኞችንም የተንበረከኩ ኾነው በውስጧ እንተዋቸዋለን*፡፡ ثُمَّ نُنَجِّي الَّذِينَ اتَّقَوا وَّنَذَرُ الظَّالِمِينَ فِيهَا جِثِيًّا

“ፊሃ” ﻓِﻴﻬَﺎ ማለት “በእርሷ ውስጥ” የሚለው መስተዋድድ አገልግሎት ላይ የዋለው ለበደለኞች እንጂ ለሙተቂን በፍጹም አይደለም። “አምን” أَمْن ማለት “ጸጥታ” ማለት ሲሆን አላህን በማንነት ሆነ በምንነት አንድ ነው ብሎ በማመንና በብቸኝነት በማምለክ በቀልብ ላይ የሚመጣ “ጸጥታ” “መረጋጋት” እና “ሰላም” ነው፦
6፥82 *እነዚያ ያመኑ እና እምነታቸውን “በበደል” ያልቀላቀሉ እነዚያ ለእነርሱ “ጸጥታ” አላቸው*፤ እነርሱም የተመሩ ናቸው ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَلَمْ يَلْبِسُوٓا۟ إِيمَٰنَهُم بِظُلْمٍ أُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمُ ٱلْأَمْنُ وَهُم مُّهْتَدُونَ ።

የአላህ ሃቅ የሆነውን አምልኮ ለሌላ ማንነት ሆነ ምንነት መስጠት በእርሱ ላይ የሚፈፀም ዙልም ነው፤ “ዙልም” ظُلْم ማለት “በደል” ማለት ሲሆን በአላህ ላይ ማጋራት ታላቁ በደል ነው፤ ሱረቱል አንዓም 6፥82 አንቀጽ በወረደ እና በተነበበ ጊዜ “ዙልም” የተባለው ሺርክን መሆኑን በዚህ ሐዲስ ላይ ተገልጿል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 65 , ሐዲስ 4776:
“እነዚያ ያመኑ እና እምነታቸውን “በበደል” ያልቀላቀሉ እነዚያ ለእነርሱ “ጸጥታ” አላቸው፤ እነርሱም የተመሩ ናቸው” የሚለው አንቀፅ በወረደ ጊዜ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ባልደረቦች የሆኑት ቃሉ ከባድ ስለነበር እነርሱም፦ “ከእኛ ውስጥ በደለኛ ያልሆነ ማን አለ?” ብለው ሲጠይቁ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሉቅማን ለልጁ፡- በአላህ አታጋራ፤ ማጋራት “ታላቅ በደል” ያለውን አልሰማችሁምን? ብለው ተናገሩ። حَدَّثَنَا قُتَيْبَةُ بْنُ سَعِيدٍ، حَدَّثَنَا جَرِيرٌ، عَنِ الأَعْمَشِ، عَنْ إِبْرَاهِيمَ، عَنْ عَلْقَمَةَ، عَنْ عَبْدِ اللَّهِ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ لَمَّا نَزَلَتْ هَذِهِ الآيَةُ ‏{‏الَّذِينَ آمَنُوا وَلَمْ يَلْبِسُوا إِيمَانَهُمْ بِظُلْمٍ‏}‏ شَقَّ ذَلِكَ عَلَى أَصْحَابِ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَقَالُوا أَيُّنَا لَمْ يَلْبِسْ إِيمَانَهُ بِظُلْمٍ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّهُ لَيْسَ بِذَاكَ، أَلاَ تَسْمَعُ إِلَى قَوْلِ لُقْمَانَ لاِبْنِهِ ‏{‏إِنَّ الشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ‏}‌‏”‏

አላህ ሙተቂን ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን፤ በአላህ ላይ በማጋራት ከሚደረግ ዙልም ይጠብቀን አሚን።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ክርስቲያ ወገኖች ዘንዶውን ለማምለክ የሚቀርቡ ሰንካላ ምክኒያቶች ሲፈተሹ ይህንን ይመስላል፦

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ጳጳሳት ቀሳውስት ሚይዙትን እባብ ቅዱስ አስመስለው ለማቅረብ ሲሞክሩ ያስደምማል።
ይህን እባብ ለማምለክ ሚያቀርቡት ምክኒያት እግዚአብሔር እስራኤላውያን በምድረ በዳ በሚጓዙበት ጊዜ ከመርዛማ እባብ እንዲድኑ የናስ እባብ እንዲሰራና እንዲያዩት አዞት ስለ ነበር እኛም በዛ ምክኒያት ነው ምንይዘው የሚል ነው ።

1ኛ ሙሴ የሰቀለው አንድ የነሃስ እባብ ሲሆን አሁን ግን መስቀሉ ላይ ያሉት ሁለት እባቦች ናቸው ይህ ደግሞ ሚመሳሰለው በዘመናችን ኢሉሚያቲዎች የሰይጣን አምላኪዎች አርማ ጋር ነው ባፎሜት የሚባለው የሰይጣን አምላኪዎች አርማ የያዘውና እና አሁን የኦርቶዶክስ ቀሳውስት ሚይዙት የእባብ አርማ በተመሳሳይ ሁለት እባቦች ይገኙበታል።

2ኛ እግዚአብሔር ለሙሴ ይህን የነሃስ እባብ እንዲሰቅል ያዘዘው ለዚያን ወቅት ብቻ ነበር ከዘመናት በኋላ ግን የእስራኤል ልጆች ይህን የናስ እባብ አምላክ አድርገው ይሰግዱለትና ያጥኑለት ነበር፦
" በኮረብታም ያሉትን መስገጃዎች አስወገደ፥ ሐውልቶችንም ቀለጣጠመ፥ የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ቈረጠ፤ የእስራኤልም ልጆች እስከዚህ ዘመን ድረስ ያጥኑለት ነበርና #ሙሴ #የሠራውን #የናሱን #እባብ #ሰባበረ፤ ስሙንም ነሑሽታን ብሎ ጠራው። "
(መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 18:4)

ከጊዜ በኃላ ይህን የነሃስ እባብ አምላክ አድርገው ስለያዙት በንጉሱ የአካዝ ልጅ ሕዝቅያስ እንደ ጣኦት ተቆጥሮ ተሰባብሯል ይህ ስራውም በእግዚአብሔር ዘንድ ቅን አደረገ ተብሎ ተነግሮለታል፦
(መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 18:3)

ትናንት እንደ ጣኦት ተቆጥሮ የተሰባበረውን የአውሬ መገለጫ የሰይጣን ምሳሌ የሆነው እባብ መስቀል ላይ አድርጎ ልክ ነው ብሎ መከራከር እንደ ቃሉ አያስኬድም የበሰበሰውን የጣኦቶ አምልኮ ቀስቅሶ ሰዉን ለማሳት አትሞክሩ ይህ ጣኦቶ ተሰባብሮ መውደቅ አለበት እንደ መፅሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ከሆነ።

3ኛ በሙሴ ዘመን ያ የነሃስ እባብ ከማየት ውጭ አይሰገድለትም። ዛሬ ላይ ግን ይሰገድለታል ይሳማልም ይህ ደግሞ የጣዖት አምልኮ ነው፦
ዘጸአት 20፥4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር ”የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፤ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም”፤
መዝሙር 97፥7 ”ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ፥ በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ”፤ መላእክቱ ሁሉ ስገዱለት።

ይህ ግኡዝ ነገር በአበይት ክርስቲያኖች ይሰገድለታል ምስጋና ይቀርበለታል፤ ይህ በተግባር ሲሆን በጽሑፍ የዘወትር ፀሎት ላይ ደግሞ እንዲህ ይነበባል፦
ግዕዙ፦
“እሰግድ “ለ”መስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተቀደሰ በደሙ ክቡር”

አማርኛ ትርጉም፦
“ዓለምን ለማዳን ሲል ኢየሱስ ክርስቶስ “ለ”ተሰቀለበት መስቀል #እሰግዳለው

ግዕዙ፦
#ስብሐት “ለ”መስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ በምህረቱ ይዘከረነ”

አማርኛ ትርጉም፦“ለ”ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል #ምስጋና ይገባዋል”

ምን ትፈልጋለህ? “ለ”ተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ ይፈሩ እየተባለ ለምንድን ነው ለግኡዝ ነገር የፀጋ ስግደት የሚሰገድለት? ምስጋናስ የሚቅብለት የሚሰማበት ዐቅል የት አለውና ነው? መስቀል መሳለም ሆነ በመስቀል ማሳለም እና መስገድ የትኛው ነብይና ሃዋርያ አደረገስ አድርጉስ አለ?

ከአላህ በቀር የምትጠሯቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፤ እራሳቸውንም አይረዱምና ወደ አላህ በንስሃ ተመለሱ፦
7፥197 እነዚያም ከእርሱ በቀር የምትጠሯቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፤ እራሳቸውንም አይረዱም وَٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِهِۦ لَا يَسْتَطِيعُونَ نَصْرَكُمْ وَلَآ أَنفُسَهُمْ يَنصُرُونَ ፡፡

በቴሌግራም ያግኙን @orthox
የሰይጣን አምላኪዎች አርማ ከሙሴ ጋር አይገናኝም!

ዘንዶውን ለማምለክ የሚቀርቡ ሰንካላ ምክኒያቶች ሲፈተሹ 👇👇👇

https://tttttt.me/orthox
ለመስቀል ይሰገዳልን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

41፥37 ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ *"ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው ለአላህ ስገዱ ፡፡ እርሱን ብቻ የምትገዙ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ”*፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ

በቁርኣን "ሡጁድ” سُّجُود የሚለው ቃል “ሠጀደ” سَجَدَ ማለት “ሰገደ” ወይም “ታዘዘ” ከሚል ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን “ስግደት” ወይም “መታዘዝ” ማለት ነው፤ ሡጁድ ደግሞ በሁለት ይከፈላል፦ አንዱ “ሡጁዱል ዒባዳ” سُّجُود العبادة ማለትም “የአምልኮ ስግደት” ሲሆን ሌላው “ሡጁዱ አተሒያ” سُّجُود التحيه ማለትም “የአክብሮት ስግደት” ነው፤ ነገር ግን ይህ አክብሮት አቅጣጫውን ቀይሮ አምልኮ እየሆነ ስላለ ከሰላምታ ውጪ በሱጁድ ለፍጡራን ማጎብደድ፣ መተናነስ፣ ማሸርገድ ቁርአን ሲወርድ ቆሟል፤ የአክብሮት ስግደት ከአምልኮ ስግደት ጋር እንዳይደባለቅ የተከለከለው በነቢያችን”ﷺ” ጊዜ ነው፤ አላህም፦ "ሁሉን ለፈጠረው ለእርሱ እንጂ ለሌላ አትስገዱ" ብሎናል፤ ከአላህ ሌላ የሚገዙት ግዑዛን ነገር የገሀነም ማገዶዎች ናቸው፦
41፥37 ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ *"ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው ለአላህ ስገዱ ፡፡ እርሱን ብቻ የምትገዙ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ”*፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ
21፥8 እናንተ *"ከአላህ ሌላ የምትገዟቸውም የገሀነም ማገዶዎች ናችሁ*፡፡ እናንተ ለእርሷ ወራጆች ናችሁ። إِنَّكُمْ وَمَا تَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ حَصَبُ جَهَنَّمَ أَنتُمْ لَهَا وَٰرِدُونَ

ማገዶዎች በሚለው ቃላት “ማ” َمَا የሚለው አንፃራዊ ተውላጠ-ስም አቅል የሌላቸውን ጣዖታት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፤ አቅል ያላቸውን ማንነቶች “መን” مَّن የሚል አንፃራዊ ተውላጠ-ስም የሚጠቀመው፤ ግን እዚህ አንቀፅ ላይ “ማ” የሚል አንፃራዊ ተውላጠ-ስም መጠቀሙ አቅል የሌላቸውን ጣዖታት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው፤ ከአላህ ውጪ የሚደረግ ባዕድ አምልኮ “ጣጉት” لطَّاغُوتِ ማለትም "ጣዖት" ይባላል።
ወደ ባይብል ስንመጣ “ስግደት” የሚለው ቃል በዕብራይስጥ “ሻኻህ” שָׁחָה ሲሆን በግሪክ ደግሞ “ፕሩስኩኔኦ” προσκυνέω ይባላል፤ ይህም ለተለያየ ምንነት ሆነ ማንነት በኒያ”intention” የሚቀርብ አምልኮን”Adoration” ወይም አክብሮትን”prostration” ነው ለማመልከት በባይብል ተጠቅሞበታል፤ የአምልኮት ስግደት በባህርይ የአንድ አምላክ ሃቅና ገንዘብ ሲሆን የአክብሮት ስግደት ደግሞ በፀጋ ለህያዋን ማንነት ማክበርን ያመለክታል፤ ግን ለግዑዛን ነገሮች አምልኮም ይሁን ስግደት ተከልክሏል፤ በዕብራይስጥ “ኤሊል” אֱלִיל ማለት “ምስል”፣ “ቅርፅ”፣ “ጣዖት” ማለት ሲሆን በግሪክ ደግሞ “ኤዶሎን” εἴδωλον ነው፤ ትርጉሙ ተመሳሳይ ነው። የሙሴ አምላክ ለሙሴ “”ለእናንተ ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ፣ የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፣ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም”” ብሎ ተናግሯል፤ እንደውም ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ ይፈሩ ይላል፦
ዘሌዋውያን 26፥1 እኔ ያህዌህ አምላካችሁ ነኝና ለእናንተ *”ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ”*፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ።
ዘጸአት 20፥4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር *”የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፤ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም”*፤
መዝሙር 97፥7 *”ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ፥ በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ*”፤ መላእክቱ ሁሉ ስገዱለት።

መስቀል በሃውልት ድንጋይ፣ እንጨት፣ ወርቅ፣ ብር፣ ብረት፣ ነሐስ ወዘተ ነው፤ ይህ ግዑዝ ነገር በአበይት ክርስቲያኖች ይሰገድለታል፥ ምስጋና ይቀርበለታል፤ ይህ በተግባር ሲሆን በጽሑፍ ደግሞ የዘወትር ፀሎት ላይ እንዲህ ይነበባል፦
ግዕዙ፦
“እሰግድ “ለ”መስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተቀደሰ በደሙ ክቡር”
ትርጉም፦
“ዓለምን ለማዳን ሲል ኢየሱስ ክርስቶስ “ለ”ተሰቀለበት መስቀል እሰግዳለው”
ግዕዙ፦
“ስብሐት “ለ”መስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ በምህረቱ ይዘከረነ”
ትርጉም፦
” “ለ”ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ምስጋና ይገባዋል”
“ለ”ተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ ይፈሩ እየተባለ ለምንድን ነው ለግዑዝ ነገር የፀጋ ስግደት የሚሰገድለት? የሚሰማበት ዐቅል የት አለውና ነው ምስጋናስ የሚቅብለት? ይህንን ስንላቸው ለመስቀል ስግደት እንደሚገባው ይህ ጥቅስ ያሳያል ይላሉ፦
መዝሙር 132፥7 ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን፤ *እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን*።

እዚህ አንቀጽ ላይ "መስቀል" የሚለው ቃል ይቅርና ስለ መስቀል እሳቤው እንኳን የለም። "እግሮቹ የቆሙበት በመስቀል ላይ ነው" የሚል ተልካሻ ምክንያት በማቅረብ ይዳዳሉ። ቅሉ ግን "እግሮቹ "በ"ሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን" አለ እንጂ "እግሮቹ "ለ"ሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን" አላለም፤ "ለ" እና "በ" የሚሉ በይዘትና በአይነት ሁለት መስተዋድዶች ናቸው። ሲቀጥል "በ"ሚቆሙበት "ስፍራ" አለ እንጂ "በ"ሚቆሙበት "መስቀል" መቼ አለ? አውዱ ላይ "ስፍራ" የሚለው ቦታን እንደሆነ ይናገራል፦
መዝሙር 132፥5 *ለእግዚአብሔር "ስፍራ"፥ ለያዕቆብ አምላክ "ማደሪያ" እስካገኝ ድረስ ብሎ*።

ምን ትፈልጋለህ? "ስፍራ" የተባለው መስቀል ሳይሆን "የቅድስናው ስፍራ" ነው፤ "በ"ዚህ ስፍራ "ለ"እግዚአብሔር ይሰገዳል ይላል፦
መዝሙር 96፥9 *"በ"ቅድስናው ስፍራ "ለ"እግዚአብሔር ስገዱ"*፤

አሁንም "ለ" እና "በ" የሚሉ ሁለት መስተዋድዶች ለዩ፤ "በ" ቦታን "ለ" ምነነትን ያመለክታል፤ በቅድስና ስፍራ ለእግዚአብሔር ይሰገዳል እንጂ ለስፍራ አይሰገድም። የእግሮቹ መቆሚያ ማለትም የእግሮቹ መረገጫ የቅድስናው ስፍራ እንጂ መስቀሉ አይደለም፦
ሕዝቅኤል 43፥7 እንዲህም አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ በእስራኤል ልጆች መካከል ለዘላለም የምቀመጥበት *የዙፋኔ ስፍራና የእግሬ ጫማ መረገጫ ይህ ነው*።

ይህንን ጉድ እያየ ወደ ክርስትና የሚገባ ሰው ቂል ካልሆነ ወይም በጥቅማ ጥቅም አሊያም በተቃራኒ ጾታ ፍቅር መነደፍ ካልሆነ በስተቀር አይሞክረውም። መስቀል በሃውልት ድንጋይ፣ እንጨት፣ ወርቅ፣ ብር፣ ብረት፣ ነሐስ ወዘተ ነው፤ ለዚህ ግዑዝ ነገር የምትሰግዱ ካላችሁ ጊዜው ሳይረፍድ ወደ አላህ በንስሃ ተመለሱ። ከአላህ በቀር የምትጠሯቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፤ እራሳቸውንም አይረዱምና፦
7፥197 *እነዚያም ከእርሱ በቀር የምትጠሯቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፤ እራሳቸውንም አይረዱም*። وَٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِهِۦ لَا يَسْتَطِيعُونَ نَصْرَكُمْ وَلَآ أَنفُسَهُمْ يَنصُرُونَ

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ኦርቶዶክስ እና ኦሮሞ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከአዋልድ መጽሐፍ አንዱ "ራዕየ ማርያም" ነው፤ እዚህ መጽሐፍ ላይ በሲዖል ስላሉት ሰዎች እንዲህ ይላል፦
ራዕየ ማርያም ገጽ 36-37 "ከዚህም በኃላ ከሥር እስከ ጫፍ፥ ከጫፍ እስከ ሥር ድረስ በአምስት ሺህ ዓመት የማይደረስ ገደል አሳየኝ። ያንዱ ነፍስ ባንዱ ነፍስ ላይ ሲወድቅ አየሁ። እኔም ምንድን ናቸው? ብዬ ልጄን ጠየኩት፤ እርሱም፦ "በአባታቸው፣ በወንድማቸው፣ በልጃቸው፣ በባልንጀራቸው ሚስት የሚሴስኑ ናቸው" አለኝ።
1. አራስ መርገም
2. ደንቆሮን
3. እስላም
3. ጋላ
4. ሻንቅላ
5. ፈላሻ
6. የተኙ ፈረስ፥ አህያ የሚያደርጉ
7. ምድርን ሰንጥቀው የሚያደርጉ
8. ወንዱን ግብረ ሰዶም ወገሞራ የሚያደርጉ
9. ካህን ሆኖ ከሌላ ሴት የካህኑ ሚስት ከሌላ ወንድ ቢሄዱ።
እነዚህ ሁሉ ኲነኔያቸው ይህ ነው" አለኝ።

ልብ አድርግ አራስ መርገም ማለት ሴት በወሊድ ጊዜ የሚኖራት ደም ነው፤ ይህ ደም እንዴት ለሲዖል ይዳርጋታል? ፈልጋ የምታመጣው ነገር አይደለም? ሲቀጥ ከዚህ የአራስ መርገም ነጻ የምትሆን ሴት የት አለች?
ሻንቅላ የተባሉት ጥቁር ሰዎች ናቸው። ጥቁርነት በተፈጥሮ የሚታደሉት ከሆነ እንዴት ለሲዖል ይዳርጋቸዋል?
ከዚህ ሁሉ የሚገርመው ጋላ ማለትም ኦሮሞ መሆን እንዴትስ ለሲዖት ይዳርጋል? ኦሮሞ ሆኖ ይህንን እምነት የሚከተል አማኝ ካለ ለምን በኦሮሞነቱ ሲዖል እንደሚገባ መጠየቅ አለበት።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ዋቄፈና

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ *”እኔንም ብቻ አምልኩኝ”*፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ

አምላካችን አላህ መለኮት ነው፤ “መለኮት” ማለት ሁሉን ነገር የሚሰማ፣ ሁሉን ነገር የሚመለከት፣ ሁሉን ነገር የሚያውቅ፣ ሁሉን ነገር የፈጠረ፣ በሁሉን ነገር ላይ ቻይ ማለት ነው፤ እርሱ በእኔነት የሚናገር ነባቢና ሕያው መለኮት ነው፤ ብዙ አንቀጾች ላይ “አምልኩኝ” እያለ በመጀመሪያ መደብ ይናገራል፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ *”እኔንም ብቻ አምልኩኝ”*፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ
21፥92 ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ *”እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ”*፡፡ إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةًۭ وَٰحِدَةًۭ وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُونِ
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ *”ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ”* በማለት ወደ እርሱ *”የምናወርድለት”* ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ
51፥56 *ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም*፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

እኛ ሙስሊም አላህ ስናመልከው እርሱን እንዴት ማምለክ እንዳለብን በቅዱስ ቃሉ በቁርኣን ውስጥ እና በእርሱ ነቢይ ሐዲስ ውስጥ በተቀመጠልን መስፈርት ብቻ ነው። ይህንን ካወቅን ስለ ዋቄፈና ደግሞ በግርድፉና በሌጣው እንይ።

"ዋቄፈና" የሚለው ቃል "ዋቃ" ማለትም "አምላክ" ከሚለው ቃል የመጣ ሲሆን የእምነቱ ስም ነው፤ ይህንን እምነት የሚከተል ሰው ደግሞ "ዋቄፈታ" ይባላል፤ “ኢሬቻ” ማለት "ምስጋና" ወይም "አምልኮ" ማለት ሲሆን "ገልማ" ማለትም "ቤተ-አምልኮ" ውስጥ በጭፈራዎቹና በፌሽታዎች የሚከበር በዓል ነው፤ ኢሬቻን የምትለዋ ቃል የምትወክለው እርጥብ ሣር ወይም አበባ በማቅረብ “መሬሆ” ማለትም "መዝሙር" መዘመሩን ነው። ይህንን አምልኮ የሚፈጽሙ ምዕመናኑ “ሚሤንሣ” ሲባሉ እምነቱን የሚመሩት ካህናቱ "ቃሉ" ይባላሉ፤ ፓለቲካውን "ሲርነ ገዳ" ሲባል ፓለቲካውን የሚመሩት መሪዎች ደግሞ "አባ ገዳ" ይባላሉ።

ይህ እምነት አምልኮውን የሚፈጽመው በተራራ እና በሃይቅ ወዘተ ነው፤ "ቱሉ" ማለት "ተራራ" ማለት ሲሆን "ቱሉ ጩቋላ(የዝቋላ ተራራ) "ቱሉ ፊሪ" "ቱሉ ኤረር" እየተባለ ወደ ስምንት ተራሮች ላይ አምልኮ ይፈጸማል። "ሆረ" ማለት "ሃይቅ" ማለት ሲሆን "ሆረ አርሰዴ" "ሆረ ፊንፊኔ" "ሆረ ኪሎሌ" እየተባሉ ሰባቱ የዋቃ ሃይቆች ላይ አምልኮ ይፈጸማል፤ ይህ በዓል በአመት ሁለት ጊዜ ይከበራል።

ይህ እምነት ታሪካዊ ዳራው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ3000 ቅድመ-ልደት እንደተጀመረ እና ጅምሩ የአንድ አምላክ አስተምህሮት እንደነበር ይገመታል ይነገራል። እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር በ 2007 ድህረ-ልደት በተደረገው የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ከኦሮሞ ሕዝብ ወደ 3.3 በመቶ የሚደርሰው ሕዝብ የዚህ እምነት ተከታይ ነበር፤ በአሁኑ ጊዜ ይሄ ቁጥር ወደ 3 በመቶ ዝቅ እንዳለ ይነገራል፤ አንዳንዶች ደግሞ፦ "አብዛኛው ዋቄፈናን ከእስልምና ጋር ወይንም ከክርስትና ጋር ቀይጦ ነው የሚያመልከው" ይላሉ፤ ይህ ስህተት ነው። ምክንያቱም የሚያመልኩት ዋቃ አንድም ቀን እንዴት መመለክ እንዳለበት አልነገራቸውም፥ ደግሞም "አይናገርምም" ይላሉ፤ እነርሱም ባወጡት ሰው ሰራሽ አምልኮ ያመልኩታል፤ ይህ ደግሞ ቢድዓ ነው፤ እዚህ አምልኮ ውስጥ ለወንዙ፣ ለተራራው፣ ለሃይቁ የሚደረገው የሁሉ አምላክነት"Pantheism" እሳቤ ሺርክ ነው፤ በዚህ አምልኮ ውስጥ ልመና፣ ምስጋና፣ ስለት፣ ስግደት የመሳሰሉት ይካሄዳሉ፤ ዛፍ ቅቤ በመቀባት መለማመን፣ ማመስገን፣ መሳል፣ መስገድ ባዕድ አምልኮ ካልሆነ ምንድን ነው? እንደውም "ቃሊቻ" የሚለው ቃል የተገኘው "ቃሉ" ከሚለው እንደሆነም ይነገራል፤ "ቃሉ" የተባሉት መሪዎች ከአጋንንት ጋር እየተነጋገሩ ሺርክ እንደሚያደርጉ የዚህ ባዕድ አምልኮ ነጻ የወጡ ሰዎች ይናገራሉ።
ነብያችን”ﷺ” የነገሩን ዓመታዊ በዓል ሁለት ብቻና ብቻ ናቸው፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓ ናቸው፦
ሡነን አቢ ዳዉድ : መጽሐፍ 2, ሐዲስ 745
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” መዲና ሲገቡ የመዲና ሠዎች የሚደሰቱባቸው ሁለት በዓላት እንዳሏቸው አወቁ። እርሳቸውም እነዚህ ሁለቱ ቀናት ምንድን ናቸው? በማለት ጠየቁ፤ ሰዎችም በጃሂሊያ ጊዜ እንጫወትባቸው የነበሩ በዓላት ናቸው አሏቸው። የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ *“አላህ ከእነርሱ የተሻሉ ሁለት ዒዶችን ሠጥቷችኋል፤ እነርሱም፦ ዒዱል ፊጥር እና ዒዱል አድሓን። አሏቸው*። عَنْ أَنَسٍ، قَالَ قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْمَدِينَةَ وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ ‏”‏ مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ ‏”‏ ‏.‏ قَالُوا كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ ‏”‏ ‏.‏
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 8, ሐዲስ 121
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“ዒዱል ፈጥር ሰዎች ጾም የሚፈቱበት ነው፤ ዒዱል አደሐ ደግሞ መስዋዕት የሚያቀርቡበት ቀን ነው*። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الْفِطْرُ يَوْمَ يُفْطِرُ النَّاسُ وَالأَضْحَى يَوْمَ يُضَحِّي النَّاسُ ‏”‏
ከእነዚህ ሁለት በዓል ውጪ ሌሎች በዓላት ተቀባይነት የላቸውም፤ ማንም ሰው አላህ እና መልእክተኛው ያልደነገጉትን ቢድዓን ያስተዋወቀ ያንን ፈለግ የተከተሉትን ሰዎች የሚያገኙትን ኀጢአት ከእነርሱ ላይ ሳይቀነስና ሳይጨመር ይሸከማል፤ ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓ ነው፤ ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው፦
ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 53, ሐዲስ 7
ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *"ማንኛውም ሰው ከትእዛዛችን ያልሆነ አንድ ነገር ቢፈጥር ተቀባይነት የለውም"* عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ قَالَتْ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَنْ أَحْدَثَ فِي أَمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ فِيهِ فَهُوَ رَدٌّ ‏”‌‏.‏
ሡነን ኢብኑ ማጃህ : መጽሐፍ 1, ሐዲስ 210
ከሲር ኢብኑብ ዐብደላህ እንደተረከው አባቱ ከአያቱ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰማው ያለው፦ “ማንኛውም ሰው የእኔን ሡናህ ሱናህ ያደረገ ከእኔ በኃላ የእኔን ፈለግ የሚከተሉትን ሰዎች የሚያገኙትን አጅር ከእነርሱ ላይ ሳይቀነስና ሳይጨመር ያገኛል፤
*ማንም ሰው አላህ እና መልእክተኛው ያልደነገጉትን ቢድዓን ያስተዋወቀ ያንን ፈለግ የተከተሉትን ሰዎች የሚያገኙትን ኀጢአት ከእነርሱ ላይ ሳይቀነስና ሳይጨመር ይሸከማል*። حَدَّثَنِي كَثِيرُ بْنُ عَبْدِ اللَّهِ، عَنْ أَبِيهِ، عَنْ جَدِّهِ، قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ يَقُولُ ‏ “‏ مَنْ أَحْيَا سُنَّةً مِنْ سُنَّتِي قَدْ أُمِيتَتْ بَعْدِي فَإِنَّ لَهُ مِنَ الأَجْرِ مِثْلَ أَجْرِ مَنْ عَمِلَ بِهَا مِنَ النَّاسِ لاَ يَنْقُصُ مِنْ أُجُورِ النَّاسِ شَيْئًا وَمَنِ ابْتَدَعَ بِدْعَةً لاَ يَرْضَاهَا اللَّهُ وَرَسُولُهُ فَإِنَّ عَلَيْهِ مِثْلَ إِثْمِ مَنْ عَمِلَ بِهَا مِنَ النَّاسِ لاَ يَنْقُصُ مِنْ آثَامِ النَّاسِ شَيْئًا ‏”‏ ‏.‏
ሡነን ነሣኢ : መጽሐፍ 19, ሐዲስ 23
ጃቢር ኢብኑ ዐብደላህ እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሑጥባቸው ላይ እንደተናገሩት፦ “አላህ የመራውን ማንም አያጠመውም፤ አላህ ያጠመመውን ማንም አያቀናውም። ከንግግር ሁሉ በላጩ የአላህ መጽሐፍ ነው፤ ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነው። *ከሁሉ የተጠላ ነገር ቢድዓ ነው፤ ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው*። عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ قَالَ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ فِي خُطْبَتِهِ يَحْمَدُ اللَّهَ وَيُثْنِي عَلَيْهِ بِمَا هُوَ أَهْلُهُ ثُمَّ يَقُولُ مَنْ يَهْدِهِ اللَّهُ فَلَا مُضِلَّ لَهُ وَمَنْ يُضْلِلْهُ فَلَا هَادِيَ لَهُ إِنَّ أَصْدَقَ الْحَدِيثِ كِتَابُ اللَّهِ وَأَحْسَنَ الْهَدْيِ هَدْيُ مُحَمَّدٍ وَشَرُّ الْأُمُورِ مُحْدَثَاتُهَا وَكُلُّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ وَكُلُّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ وَكُلُّ ضَلَالَةٍ فِي النَّارِ

ስለዚህ እዚህ እምነት ውስጥ ያላችሁ ዋቄፈታዎች የነቢያት አምላክ የሆነውን አንዱን አምላክ አላህን በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው፤ ሙስሊሞች ሆናችሁ ይህንን በዓል ባለማወቅ የምታከብሩምና የምታመልኩ ካላችሁ በንስሃ ወደ አላህ ተመለሱ። አላህ ወደ እርሱ በመጸጸት ለሚመለሱት ይቅር ባይና አዛኝ ነው፦
2፥160 እነዚያ ከመደበቅ የተጸጸቱና ሥራቸውን ያሳመሩም የደበቁትን የገለጹም ብቻ ሲቀሩ፡፡ *እነዚህም በእነርሱ ላይ ጸጸታቸውን እቀበላለሁ፤ እኔም ጸጸትን በጣም ተቀባይ አዛኙ ነኝ*፡፡ إِلَّا الَّذِينَ تَابُوا وَأَصْلَحُوا وَبَيَّنُوا فَأُولَـٰئِكَ أَتُوبُ عَلَيْهِمْ ۚ وَأَنَا التَّوَّابُ الرَّحِيمُ

ስለ ዋቄፈና ዋቢ መጽሐፍት፦
1. Mulugeta Jaleta Gobenooromo; Indiginious Religion: Anthroplogical Understanding of Waaqeffanna-Nature Link, With Highlight on Livelihood in Guji Zone, Adola Redde and Girja Districts, A thesis submitted to the department of Social Anthropology, College of Social Science Addis Ababa University, June 2017,
2. Census (PDF), Ethiopia, 2007,
3. Workinesh Kelbessa, Traditional Oromo Attitudes towards the Environment, Social Science Research Report Series.

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
የወር አበባ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥222 ከወር አበባም ይጠይቁሃል፡፡ እርሱ “የተበከለ” ነው፡፡ ሴቶችንም በወር አበባ ጊዜ “ራቋቸው”፡፡ ንጹሕ እስከሚኾኑም ድረስ “አትቅረቡዋቸው”፡፡ ንጹሕ በኾኑም ጊዜ አላህ ካዘዛችሁ ስፍራ “ተገናኙዋቸው”፡፡ አላህ ከኃጢኣት ተመላሾችን ይወዳል፤ ተጥራሪዎችንም ይወዳል በላቸው وَيَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلْمَحِيضِ ۖ قُلْ هُوَ أَذًۭى فَٱعْتَزِلُوا۟ ٱلنِّسَآءَ فِى ٱلْمَحِيضِ ۖ وَلَا تَقْرَبُوهُنَّ حَتَّىٰ يَطْهُرْنَ ۖ فَإِذَا تَطَهَّرْنَ فَأْتُوهُنَّ مِنْ حَيْثُ أَمَرَكُمُ ٱللَّهُ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلتَّوَّٰبِينَ وَيُحِبُّ ٱلْمُتَطَهِّرِينَ ፡፡

የሚሽነዎች ጉዳይ መላ ቅጡ፣ ውጥን ቅጡ እና ቅጥ አንባሩ የጠፋበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፤ እስልምና በፍጥነት ማደጉ ከሚያብከነክናቸውና ከሚከነክናቸው የኢስላም ጠላቶች አንዱ ሚሽነሪዎች ናቸው፤ እስልምናን ለማጠልሸት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የማይደረምሱት መሬት የለም፤ ጭራሽ ነብያችንን ለማነወር ሲቃጡ፦ “ነብያችሁ በወር አበባ ጊዜ ተራክቦ ያደርጉ ነበር” ወሊ-አዑዝቢሏህ ብለው እርፍ። ሆነም ቀረ ይህ ትችት የሚያሳየው ሴትን ዝቅ ለማድረግ የተቃጣ ትችት ነው። ወደዱም ጠሉም ሴት ልጅ በኢስላም ክቡድና ክቡር ናት፤ ይህንን ከእኔ ከተባእቱ ሳይሆን ወደ ኢስላም ከሚጎርፉት እንስታት ማረጋገጥ ይቻላል፤ በኢስላም አንድ ተባእት ከተራክቦ በስተቀር ተቃራኒ ከሆነች እንስት ጋር በወር አበባዋ ጊዜ መሳሳም፣ መተቃቀፍ፣ መተሻሸት እና መተኛት ሃላል ነው፤ አምላካችን አላህ “የተበከለ” ወይም “ቆሻሻ” የሚለው ሴቷን ሳይሆን ከሴቷ የሚወጠውን የወር አበባ ነው፤ በዚህ ጊዜ ተራክቦ ማድረግ ሃራም ነው፤ “ራቋቸው” እና “አትቅረቡዋቸው” የሚለው ቃል የ”ተገናኙዋቸው” ተቃራኒ ሆኖ ስለመጣ ራቁ ማለትና አትቅረቡ ማለት ተራክቦ አታድርጉ ማለት ነው፤ ለምሳሌ ዝሙት ማለት ከጋብቻ ውጪና በፊት የሚደረግ ተራክቦ ነው፤ ይህንን ተራክቦ “አትቅረቡ” ይላል፤ ያ ማለት “አትገናኙ” ማለት እንጂ ከሰው ጋር ጤናማ ግኑኝነት አይኑራችሁ ማለት እንዳልሆነ ሁሉ ሴት ራቁ ማለትና አትቅረቡ ማለት ተራክቦ አታድርጉ ማለት እንጂ አትቀፏቸው፣ አትሳሟቸው፣ አብራችሁ አትተኙ ማለት አይደለም፦
2፥222 ከወር አበባም ይጠይቁሃል፡፡ እርሱ “የተበከለ” ነው፡፡ ሴቶችንም በወር አበባ ጊዜ “ራቋቸው”፡፡ ንጹሕ እስከሚኾኑም ድረስ “አትቅረቡዋቸው”፡፡ ንጹሕ በኾኑም ጊዜ አላህ ካዘዛችሁ ስፍራ “ተገናኙዋቸው”፡፡ አላህ ከኃጢኣት ተመላሾችን ይወዳል፤ ተጥራሪዎችንም ይወዳል በላቸው وَيَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلْمَحِيضِ ۖ قُلْ هُوَ أَذًۭى فَٱعْتَزِلُوا۟ ٱلنِّسَآءَ فِى ٱلْمَحِيضِ ۖ وَلَا تَقْرَبُوهُنَّ حَتَّىٰ يَطْهُرْنَ ۖ فَإِذَا تَطَهَّرْنَ فَأْتُوهُنَّ مِنْ حَيْثُ أَمَرَكُمُ ٱللَّهُ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلتَّوَّٰبِينَ وَيُحِبُّ ٱلْمُتَطَهِّرِينَ ፡፡
17፥32 ዝሙትንም “አትቅረቡ”፡፡ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፡፡ መንገድነቱም ከፋ وَلَا تَقْرَبُوا۟ ٱلزِّنَىٰٓ ۖ إِنَّهُۥ كَانَ فَٰحِشَةًۭ وَسَآءَ سَبِيلًۭا !

በተለይ ሱረቱል በቀራህ 2፥222 የወረደበት ምክንያት አይሁዳውያን ሴት በወር አበባ ጊዜ ስትሆን ምግብ አብረው አይበሉም በቤታቸውም አይኖሩም ስለነበርና ሰሃባዎችም ይህንን ጉዳይ ወደ ነብያችን”ﷺ” ጥያቄውን በማምራታቸው ነው፤ ነብያችንም”ﷺ” የመለሱት በወር አበባ ጊዜ ከተራክቦ በስተቀር ሁሉንም ማድረግ እንደሚቻል ነው፦
ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 3 , ሐዲስ 16:
አነሥ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦
አይሁዳውያን ሴት በወር አበባ ጊዜ ስትሆን ምግብ አብረው አይበሉም በቤታቸውም አይኖሩም፤ የነብዩም”ﷺ” ባልደረቦች ነብዩን”ﷺ” ስለ ጉዳዩ ጠየቁ፤ ከሁሉ የላቀው አላህም ይህንን አንቀፅ አወረደ፦
2፥222 ከወር አበባም ይጠይቁሃል፡፡ እርሱ “የተበከለ” ነው፡፡ ሴቶችንም በወር አበባ ጊዜ “ራቋቸው”፡፡
የአላህም መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ “ሁሉን ነገር አድርጉ ከተራክቦ በስተቀር”። عَنْ أَنَسٍ، أَنَّ ال يَهُودَ، كَانُوا إِذَا حَاضَتِ الْمَرْأَةُ فِيهِمْ لَمْ يُؤَاكِلُوهَا وَلَمْ يُجَامِعُوهُنَّ فِي الْبُيُوتِ فَسَأَلَ أَصْحَابُ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم فَأَنْزَلَ اللَّهُ تَعَالَى ‏{‏ وَيَسْأَلُونَكَ عَنِ الْمَحِيضِ قُلْ هُوَ أَذًى فَاعْتَزِلُوا النِّسَاءَ فِي الْمَحِيضِ‏}‏ إِلَى آخِرِ الآيَةِ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ اصْنَعُوا كُلَّ شَىْءٍ إِلاَّ النِّكَاحَ

በሥነ-ቃላት ጥናት”Morphology “የአንድን ቃል አማራጭ ትርጒም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው፤ ለምሳሌ፦ በኢንግሊሽ  “Volume” ማለት፦ ስለ ሥነ-አካል የምናወራበት የዐውድ ፍሰት ላይ “ይዘት” ማለት ሲሆን፣ ስለ ድምጽ አጨማመር እና አቀናነስ የምናወራበት የዐውድ ፍሰት ላይ “መጠን” ማለት ሲሆን፣ ስለ ሥነ-ጽሑፍ የምናወራበት የዐውድ ፍሰት ላይ ደግሞ “ቅጽ” ማለት ነው። ይህንን ከተረዳን ለምሳሌ በዐረቢኛ፦ “መሥ” مَسّ ማለትም “መንትካ” የሚለው ቃል “ተራክቦን” “መዳሰስን” መፈለግን” ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል፦

1ኛ “ተራክቦ”፦
3፥46 ፡-ጌታዬ ሆይ! “ሰው ያልነካኝ ስኾን ለእኔ እንዴት ልጅ” ይኖረኛል?” አለች قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِى وَلَدٌۭ وَلَمْ يَمْسَسْنِى بَشَرٌۭ ۖ ፡፡
19፥20 « ሰው “ያልነካኝ” ሆኜ አመንዝራም ሳልሆን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል?» አለች قَالَتْ أَنَّىٰ يَكُونُ لِى غُلَٰمٌۭ وَلَمْ يَمْسَسْنِى بَشَرٌۭ وَلَمْ أَكُ بَغِيًّۭا ፡፡
2፥236 ሴቶችን “ሳትነኳቸው” ወይም ለእነሱ መህርን ሳትወስኑላቸው ብትፈቷቸው በእናንተ ላይ ኃጢኣት የለባችሁም لَّا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ إِن طَلَّقْتُمُ ٱلنِّسَآءَ مَا لَمْ تَمَسُّوهُنَّ أَوْ تَفْرِضُوا۟ لَهُنَّ فَرِيضَةًۭ ۚ ፡፡

“ሰው ያልነካኝ ስኾን ለእኔ እንዴት ልጅ” ይኖረኛል?” ማለቷ መቼም ሰው በእጁ ሳይዳስሰኝ እንዴት ልጅ” ይኖረኛል እያለች እንዳልሆነ ቅቡል ነው፤ መቼን በእጅ በመነካት ልጅ የሚኖራት እንስት የለችምና፤ በተጨማሪ ሴቶችን ሳትነኳቸው ብትፈቷቸው በእናንተ ላይ ኃጢኣት የለባችሁም ሲባል በእጅ ሳትዳስሷቸው ማለት እንዳልሆን እሙን ነው።
2ኛ “መዳሰስ”፦
6፥7 በአንተም ላይ በወረቀት የተጻፈን መጽሐፍ ባወረድንና *በእጆቻቸው በነኩት* ኖሮ እነዚያ የካዱት ሰዎች «ይህ ግልጽ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም» ባሉ ነበር፡፡ وَلَوْ نَزَّلْنَا عَلَيْكَ كِتَٰبًۭا فِى قِرْطَاسٍۢ فَلَمَسُوهُ بِأَيْدِيهِمْ لَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِنْ هَٰذَآ إِلَّا سِحْرٌۭ مُّبِينٌۭ

“በነኩት” ተብሎ የመጣበት ቃል እና መርየም “ያልነካኝ” ብላ የተናረችበት ቃል አንድ ነው፤ ያ ማለት አንድ ትርጉም ይኖረዋል ማለት አይደለም።

3ኛ “መፈለግ”፦
72፥8 ‹እኛም ሰማይን ለመድረስ *ፈለግን*፡፡ ብርቱ ጠባቂዎችንና ችቦዎችንም ተሞልታ አገኘናት፡፡ وَأَنَّا لَمَسْنَا ٱلسَّمَآءَ فَوَجَدْنَٰهَا مُلِئَتْ حَرَسًۭا شَدِيدًۭا وَشُهُبًۭا
57፥13 መናፍቃንና መናፍቃት ለእነዚያ ለአመኑት «ተመልከቱን፤ ከብርሃናችሁ እናበራለንና» የሚሉበትን ቀን አስታውስ፡፡ «ወደ ኋላችሁ ተመለሱ፡፡ ብርሃንንም *ፈልጉ*» ይባላሉ፡፡ ግቢው በውስጡ ችሮታ ያለበት ውጭውም ከበኩሉ ስቃይያለበት የኾነ፡፡ يَوْمَ يَقُولُ ٱلْمُنَٰفِقُونَ وَٱلْمُنَٰفِقَٰتُ لِلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱنظُرُونَا نَقْتَبِسْ مِن نُّورِكُمْ قِيلَ ٱرْجِعُوا۟ وَرَآءَكُمْ فَٱلْتَمِسُوا۟ نُورًۭا فَضُرِبَ بَيْنَهُم بِسُورٍۢ لَّهُۥ بَابٌۢ بَاطِنُهُۥ فِيهِ ٱلرَّحْمَةُ وَظَٰهِرُهُۥ مِن قِبَلِهِ ٱلْعَذَابُ

ይህን የሥነ-ቃል እሳቤ ይዘን ሂስ የተሰጠበትን ሐዲስ እንልመከት፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 6 , ሐዲስ 6:
ዓኢሻ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦
ነብዩም”ﷺ” እና እኔ ጁኑብ በሆንን ጊዜ በአንድ መታጠቢያ እንታብጠ ነበር፤ እንዲሁ በወር አበባ ጊዜ ከወገብ በታች እንድለብስ ያዙኝና ይዳብሱኝ ነበር፤ በተመሳሳይ በኢዕቲካፍ በወር አበባዬ ጊዜዬ ራሳቸውን ወደ እኔ ያቀርቡና እራሳቸውን አጥባቸው ነበር። عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كُنْتُ أَغْتَسِلُ أَنَا وَالنَّبِيُّ، صلى الله عليه وسلم مِنْ إِنَاءٍ وَاحِدٍ، كِلاَنَا جُنُبٌ‏.‏ وَكَانَ يَأْمُرُنِي فَأَتَّزِرُ، فَيُبَاشِرُنِي وَأَنَا حَائِضٌ‏.‏ وَكَانَ يُخْرِجُ رَأْسَهُ إِلَىَّ وَهُوَ مُعْتَكِفٌ، فَأَغْسِلُهُ وَأَنَا حَائِضٌ‏.‏
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 6 , ሐዲስ 7:
የምእመናን እናት ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንዲህ አለች፦ “ከእኛ ውስጥ አንዳችን በሐይድ ላይ ከሆነች እና የአላህ መልክተኛም”ﷺ” እሷን ለመንካት ከፈለጉ ከሐይድ ወቅት ጀምሮ ልብስን እንድታሸርጥ ያዟት ነበር፤ ከዛም ገላዋን ይዳብሷት ነበር፤ የአላህ ነቢይ”ﷺ” ስሜታቸውን ይቆጣጠሩ እንደነበረው ማንኛችሁ ነው ስሜቱን መቆጣጠር የሚችለው? አለች፡፡ عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ كَانَتْ إِحْدَانَا إِذَا كَانَتْ حَائِضًا، فَأَرَادَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم أَنْ يُبَاشِرَهَا، أَمَرَهَا أَنْ تَتَّزِرَ فِي فَوْرِ حَيْضَتِهَا ثُمَّ يُبَاشِرُهَا‏.‏ قَالَتْ وَأَيُّكُمْ يَمْلِكُ إِرْبَهُ كَمَا كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم يَمْلِكُ إِرْبَهُ‏.‏ تَابَعَهُ خَالِدٌ وَجَرِيرٌ عَنِ الشَّيْبَانِيِّ‏.‏

“ፈዩባሺሩኒ” فَيُبَاشِرُنِي ማለት “ይዳብሱኝ ነበር” He used to fondle me” ነበር ማለት ነው፤ “ዩባሺሩሃ” يُبَاشِرَهَا ማለት “ይዳብሷት ነበር” He used to fondle her” ነበር ማለት ነው፤ የቋንቋ ምሁራንም በኢንግሊዚኛው ትርጉም ላይ በዚህ መልኩ ነው ያስቀመጡት እንጂ “ተራክቦ”Intercourse” በሚል አላስቀመጡትም። ምክንያቱም ሴት ልጅ በወር አበባዋ ጊዜ ላይ እያለች ተራክቦ ማድረግ ክልክል ብቻ ሳይሆን ክህደትም ነው፦
ጃሚዒ አት-ተርሚዲህ : መጽሐፍ 1, ሐዲስ 135
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንዳለው፦ “ነብዩ”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ ማንም በሓይድ ላይ ካለች ሴት ወይም በመቀመጫዋ በኩል ተራክቦ ቢያደርግ በሙሐመድ”ﷺ” ላይ በተወረደው ክዷል። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ مَنْ أَتَى حَائِضًا أَوِ امْرَأَةً فِي دُبُرِهَا أَوْ كَاهِنًا فَقَدْ كَفَرَ بِمَا أُنْزِلَ عَلَى مُحَمَّدٍ صلى الله عليه وسلم ‏”‏

ሲቀጥል ተራክቦን እንደማያመለክት ለመግለጽ፦ “ሽርጥን እንድታሸርጥ ያዟት ነበር” የሚል ሃይለ-ቃል አለ፤ ይህ የሚያሳየው ተራክቦን አለመሆኑን ያሳያል፤ በተራክቦ ጊዜ ልብስን እንድትለብስ ማዘዝ ትርጉም የለውም።
ሢሰልስ በሐዲሱ ማብቂያ ላይ እናታችን ዓኢሻ”ረ.ዐ.” ስለ ነብዩም”ﷺ” ስትደመድም፦ “ስሜታቸውን ይቆጣጠሩ እንደነበረው ማንኛችሁ ነው ስሜቱን መቆጣጠር የሚችለው?” በማለቷ ተራክቦን ጭራሽ አያሳይም፤ ምክንያቱም ተራክቦ በራሱ ስሜት ማርኪያ እንጂ መቆጣጠሪያ ስላልሆነ።
ሲያረብብ፦ በኢዕቲካፍ በወር አበባዬ ጊዜዬ ራሳቸውን ወደ እኔ ያቀርቡና እራሳቸውን አጥባቸው ነበር” ብላለች፤ “ኢዕቲካፍ” اعتكاف‌‎ ማለት “ማዘውተር” ማለት ሲሆን በስብስብ ሶላት ላይ በመስጂድ ውስጥ ለመዘውተር በመነየት የተወሰነ ጊዜ ቆይታ ማድረግ ነው፤ በተለይ የረመዷንን የመጨረሻዎቹን አሥርት ቀናት ላይ የሚረግደ ቆይታ ነው። በዚህ ወቅት ተራክቦ ማድረግ ሃራም ነው፦
2፥187 እናንተም በመስጊዶች ተቀማጮች ስትኾኑ “አትገናኙዋቸው”፡፡ وَلَا تُبَٰشِرُوهُنَّ وَأَنتُمْ عَٰكِفُونَ فِى ٱلْمَسَٰجِد

እዚህ አንቀጽ ላይ “ቱባሺሩሁነ” تُبَٰشِرُوهُنَّ ማለት “ተራክቦ አታድርጓቸው” ማለት ነው፤ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጒም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ እሙንና ቅቡል ነው፤ ይህ ሙግት የሥነ-ቋንቋ ሙግት እና የዐውድ ሙግት ታሳቢና ዋቢ ያደረገ ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም