ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.8K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ኢልሃም እና ወሕይ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

መግቢያ
ሚሽነሪዎች በቁርአን ሴት ነብይ አለች እርሷም የሙሳ እናት ናት፤ ምክንያቱም ነብይ ማለት ወሕይ የሚወርድለት ማለት ነው ብለው ይሞግታሉ፦
28፥7 ወደ ሙሳም እናት፦ “አጥቢው፣ በእርሱም ላይ በፈራሽ ጊዜ በባሕሩ ውስጥ ጣይው አትፈሪም፣ አትዘኝም፣ እኛ ወደ አንቺ መላሾቹና ከመልክተኞቹም አድራጊዎቹ ነንና” ማለትን “አመለከትን” وَأَوْحَيْنَآ إِلَىٰٓ أُمِّ مُوسَىٰٓ፡፡

“አመለከትን” ተብሎ የተቀመጠው “አውሐይና” أَوْحَيْنَا ሲሆን ” ገለጥን” በሚል ይመጣል እንጂ ነብይነትን ብቻ ሁሌ ያሳያል ማለት አይደለም፤ ምክንያቱን ይህ ግስ “አውሓ” َأَوْحَىٰ በሚል ለምድርና ለንብ “አስታወቀ” በሚል መጥቷል፤ ታዲያ ንብ እና ምድር ነብያት ነበሩን?፦
99፥5 ጌታህ “ለእርሷ በማሳወቁ” أَوْحَىٰ لَهَا ምክንያት፡
16፥68 ጌታህም ወደ ንብ እንዲህ ሲል “አስታወቀ” وَأَوْحَىٰ رَبُّكَ إِلَى ٱلنَّحْلِ ፦ “ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ ሰዎች ከሚሠሩትም ቤቶችን ያዢ””፡፡

አንድ ቃል ሁልጊዜ አንድ ትርጉም አለው ብሎ ማሰብ ቂልነት ነው፤ ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው ሃሳብና አረፍተ-ነገር ይወስነዋል፤ ለምሳሌ ሰይጣናትም ወደ ወዳጆቻቸው “ያሾከሹካሉ” ተብሏል፦
6፥121 በእርሱም ላይ የአላህ ስም ካልተጠራበት ነገር አትብሉ፡፡ እርሱም በእርግጥ አመጽ ነው፡፡ ሰይጣናትም ወደ ወዳጆቻቸው በክትን በመብላት ይከራከሯችሁ ዘንድ “ያሾከሹካሉ” لَيُوحُونَ ፤ “ብትታዘዙዋቸውም” እናንተ በእርግጥ “አጋሪዎች” ናችሁ፡፡

“ያሾከሹካሉ” ለሚለው ቃል የተቀመጠው “ለዩሑነ” لَيُوحُونَ የሚለው ግስ “አውሃ” أَوْحَىٰٓ “ገለጠ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ማሳወቅ” በሚል ሊመጣ ይችላል፤ ስለዚህ ጥንቃቄ ይጠይቃል፤ ታዲያ ይህ የሙሳ እናት ጉዳይ ወሕይ ካልሆነ ምን ይባላል? ብሎ አንድ ሰው ቢጠይቅ “ኢልሃም” ይባላል ነው መልሳችን፤ እስቲ ስለ ወሕይ እና ኢልሃም ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
“ኢልሃም”
“ኢልሃም” إلهام ማለት አላህ ለሰዎች እና ለነገሮች የሚያሳውቀው ፍንጥቅታ”inspiration” ነው። ለምሳሌ፦ ለተራራ፣ ለሰማይና ምድር፣ ለጀሃነም፣ ለንብ፣ ለዙልቀርነይን፣ ለህዝቦች እና ለሙሳ እናት ተጠቃሾች ናቸው፦

ለተራራ
34:10 ለዳውድም ከኛ የሆነን ችሮታ በእርግጥ ሰጠነው፤አልንም፦ *ተራራዎች ሆይ*! ከእርሱ ጋር ውዳሴን መላልሱ፤ በራሪዎችንም ገራንለት፤ ብረትንም ለእርሱ አለዘብንለት።

ለሰማይና ምድር
41:11ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ሆና ሳለች አሰበ፤ ለእርሷም ለምድርም ወዳችሁም ሆነ ወይም ጠልታችሁ፣ *ኑ፤ አላቸው*። ታዛዦች ሆነን መጣን አሉ።

ለጀሃነም
50:30 ለገሀነም «*ሞላሽን?* የምንልበትንና ጭማሪ አለን? የምትልበትን ቀን» አስጠንቅቃቸው፡፡

ለንብ
16:68 ጌታህም ወደ ንብ እንዲህ ሲል አሳወቀ፥ ከተራራዎች፥ ከዛፍም ሰዎች ከሚሠሩትም ቀፎ ቤቶችን *ያዢ*።

ለዙልቀርነይን
18:86 ወደ ፀሐይ መግቢያም በደረሰ ጊዜ ጥቁር ጭቃ ባላት ምንጭ ውስጥ ስትጠልቅ (አገኛት፤ ባጠገቧም ሕዝቦችን አገኘ፤ *ዙልቀርነይን ሆይ*! ወይም በመግደል ትቀጣለህ ወይም በነርሱ መልካም ነገርን መማረክን ትሠራለህ አልነው።

ለሙሳ እናት
28:7 ወደ ሙሳም እናት «አጥቢው፣ በርሱም ላይ በፈራሽ ጊዜ በባሕሩ ውስጥ ጣይው አትፈሪም፣ አትዘኝም፣ እኛ ወዳንቺ መላሾቹና ከመልክተኞቹም አድራጊዎቹ ነንና» ማለትን *አመለከትን*፡፡

ለህዝቦች
19፥11ከምኩራቡም በሕዝቦቹ ላይ ወጣ፡፡ በጧትና በማታ ጌታችሁን አወድሱ በማለትም ወደ እነርሱ “ጠቀሰ” فَأَوْحَىٰٓ إِلَيْهِمْ ፡፡

ይህ ለአንዳንድ ሷሊሂን እና ሷሊሃት በከራማህ የሚሰጥ ነው፤ “ከራመት كرامت ማለት “ድንቅ” ወይም “ታምር” ማለት ነው።

ነጥብ ሁለት
“ወሕይ”
“ወሕይ” وَحْى የሚለው ቃል “አውሐ” أَوْحَىٰٓ “ገለጠ” ወይም “አወረደ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ግልጠት”Revelation” ማለት ነው፤ በግሪክ ደግሞ “አፖካሊፕስ” ἀποκάλυψις ነው፤ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ-ቃላት ላይ “ቀለምሲስ” ወይም “አስተርእዮ” ይለዋል(ኪዳነ ወልድ ክፍሌ አሌፍ 198 ገፅ 198)። ወሕይ ለነብያት የሚወርድ የአላህ ቃል ነው፤ ይህንን ለማመልከት “አውሐይና” أَوْحَيْنَا “አወረድን” ብሎ ይናገራል፦
4:163 እኛ ወደ ኑሕና ከርሱ በኋላ ወደ ነበሩት ነቢያት #እንዳወረድን أَوْحَيْنَا ፣ ወደ አንተም #አወረድንأَوْحَيْنَا ፤ ወደ ኢብራሂምም፣ ወደ ኢስማዒልም፣ ወደ ኢስሐቅም፣ ወደ ያዕቆብም፣ ወደ ነገዶቹም ወደ ዒሳም፣ ወደ አዮብም፣ ወደ ዩኑስም፣ ወደ ሀሩንና ወደ ሱለይማንም #አወረድን وَأَوْحَيْنَا ፤ ለዳዉድም ዘቡርን ሰጠነው።

ወህይ ነብያት ለሆኑ ሰዎች ብቻ የሚወርድ ነው፦
21፥7 ከአንተም በፊት ወደ እነርሱ *የምናወርድላቸው* የኾነን *ሰዎችን* እንጂ ሌላን አላክንም፡፡ የማታውቁም ብትኾኑ የመጽሐፉን ባለቤቶች ጠይቁ፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا قَبْلَكَ إِلَّا رِجَالًۭا نُّوحِىٓ إِلَيْهِمْ ۖ فَسْـَٔلُوٓا۟ أَهْلَ ٱلذِّكْرِ إِن كُنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ

ይህ ለነብያት በሙእጂዛ የሚሰጥ ነው፤ “ሙእጂዛ” مُعجِزة ማለት “እፁብ ታምር” ወይም “ምልክት” ማለት ነው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም