ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.8K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ስለዚህ አላህ ማለት ግኡዛን ነገሮችን ህያው የሚያደርግበት ንጥረ-ነገር አይደለም። አላህ ፈጣሪ እንጂ ፍጡር አይደለም። ስለዚህ ሩህ እውቀት የተሰጠን እውቀት አናሳ ነው፤ ዋናው ሩህ ከአፈር ሳይሆን ከጌታ ነገር መሆኑን መቀበል ነው፦
17:85 ከሩሕም ይጠይቁሃል፤ ሩሕ *ከ* ጌታዬ ነገር مِنْ أَمْرِ رَبِّي ነው፤ ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም፤ በላቸው።

ይህንን ካየን በባይብል መንፈስ የሚለው ቃል በዕብራይስጥ “ሩዋህ” ר֫וּחַ በግሪክ ደግሞ “ኑማ” πνεῦμα ሲሆን ፈጣሪ አደምን ከምድር አፈር ሰርቶ በአፍንጫውም “የሕይወት እስትንፋስን የሆነውን መንፈስ እፍ ሲልበት አደም ህያው ነፍስ ሆነ፤ ይህንን መንፈስ በአካል ውስጥ ሰራው፦
ዘፍጥረት 2፥7 እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም “የሕይወት እስትንፋስን እፍ”” አለበት ሰውም ሕያው ነፍስ ሆነ። NIV
ዘካርያስ 12፥1 ስለ እስራኤል የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል ሸክም ይህ ነው። ሰማያትን የዘረጋ፥ ምድርንም የመሠረተ፥ “”የሰውንም መንፈስ በውስጡ የሠራ”” እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦

ይህም መንፈስ ከአምላክ እንደተሰጠ በሞት ጊዜ ወደ አምላክ ይመለሳል፦
መክብብ 12፥7 አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ “መንፈስም” ר֫וּחַ ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ። NIV

ይህ የሰው መንፈስ የእግዚአብሔር መብራት ነው፦
ምሳሌ 20፥27 የሰው መንፈስ የእግዚአብሔር መብራት ነው የሆዱን ጕርጆች ሁሉ የሚመረምር።

ሌላው መላእክት መንፈስ ናቸው፦
መዝሙር 104፥4 “መላእክቱን መንፈስ የሚያደርግ”፥ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል።
ራእ 4፥5 ከዙፋኑም መብረቅና ድምፅ ነጐድጓድም ይወጣል፤ በዙፋኑም ፊት ሰባት የእሳት መብራቶች ይበሩ ነበር፥ እነርሱም ሰባቱ “”የእግዚአብሔር መናፍስት”” ናቸው።
ራእ 5፥6 ሰባትም ቀንዶችና ሰባት ዓይኖች ነበሩት እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ የተላኩ “የእግዚአብሔር መናፍስት” ናቸው።

“ቄስ” በብዜት “ቄሶች” ለማለት “ቀሳውስት” እንደሚባል፣ “አምላክ” በብዜት “አምላኮች” ለማለት “አማልክት” እንደሚባል ሁሉ “መንፈስ” በብዜት “መንፈሶች” ለማለት “መናፍስት” ይባላል፤ እነዚህም ሰባት የእግዚአብሔር መንፈሶች ሰባቱም የእግዚአብሔር መላእክት ናቸው፦
ራእ 16፥1 #ለሰባቱም መላእክት”። ሄዳችሁ የእግዚአብሔርን ቁጣ ጽዋዎች በምድር ውስጥ አፍስሱ የሚል ታላቅ ድምፅ ከመቅደሱ ሰማሁ።
ራእ 8፥2 በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን #ሰባቱን መላእክት” አየሁ፥ ሰባትም መለከት ተሰጣቸው።

ሌላው “እግዚአብሔር መንፈስ ነው” ማለት “ሥጋና አጥንት የለውም” ማለት ነው እንጂ መንፈስ ማለት የማይታይ ረቂቅ ማለት ብቻ አይደለም፦
ዮሐንስ 4:24 “እግዚአብሔር መንፈስ ነው”፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።
ሉቃስ 24:39 እኔ ራሴ እንደ ሆንሁ እጆቼንና እግሮቼን እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት፥ “መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና” እኔን ዳስሳችሁ እዩ አላቸው።

ምክንያቱም እግዚአብሔር በዚህ ዓለም ሆነ በትንሳኤ ቀን እንደሚታይ ስለሚናገር፦
ዘጸአት 24:10 የእስራኤልንም አምላክ “”አዩ””፤ “ከእግሩም” በታች እንደ ሰማይ መልክ የሚያበራ እንደ ብሩህ ሰንፔር ድንጋይ የሚመስል ወለል ነበረ።
ማቴዎስ 18፥10 ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን “”የአባቴን ፊት ያያሉ”” እላችኋለሁና።
ኢዮብ 19፥ 26-27 ይህ ቁርበቴም ከጠፋ በኋላ፥ በዚያን ጊዜ ከሥጋዬ ተለይቼ “”እግዚአብሔርን እንዳይ”” አውቃለሁ። እኔ ራሴ አየዋለሁ፥ “”ዓይኖቼም ይመለከቱታል””፥
ራእይ 22፥3 ከእንግዲህም ወዲህ መርገም ከቶ አይሆንም። የእግዚአብሔርና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፥ ባሪያዎቹም ያመልኩታል፥ “”ፊቱንም ያያሉ””፥

ሲጀመር “እግዚአብሔር መንፈስ ነው” የሚለው ቃል ኢየሱስ ይናገረው አይናገረው እርግጠኛ አይደለንም። ምክንያቱም አራቱ ወንጌላት ላይ አሉ የሚባሉት የኢየሱስ ንግግር ከመቶ 82% የኢየሱስ አይደለም የሚል የአዲስ ኪዳን ምሁር የዶክተር ሄርማን ሙግት ስላለም ጭምር።

ሲቀጥል “እግዚአብሔር መንፈስ ነው” ማለት ሥጋና አጥንት የለውም” ነው፤ ለምሳሌ አምላክ እሳት ነው ተብሏል፦
ዘዳግም 4፥24 አምላክህ እግዚአብሔር “የሚበላ እሳት” ቀናተኛም አምላክ ነውና።
ዕብራውያን 12:29 አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና።
ዘዳግም 9፥3 አምላክህም እግዚአብሔር “እንደሚበላ እሳት” ሆኖ በፊትህ እንዲያልፍ ዛሬ እወቅ፤ እርሱ ያጠፋቸዋል፥

እግዚአብሔር “እንደሚበላ እሳት” ስለሚያጠፋ እሳት ተባለ እንጂ ነበልባል የሆነ ኦክሲዴሽን ማለት እንዳልሆነ ሁሉ መንፈስ ነው ማለት ልክ እንደ መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውም ማለት እንጂ ንጥረ-ነገር የሆነ መንፈስ ነው ማለት አይደለም።

ሲሰልስ መንፈስ በእግዚአብሔርም ፊት ቆሞ መናገሩ እና መላኩ መንፈስ እርሱ ከእግዚአብሔር ይለያል፦
1ኛ ነገሥት 22፥20-23 እግዚአብሔርም፦ ወጥቶ በሬማት ዘገለዓድ ይወድቅ ዘንድ አክዓብን የሚያሳስት ማን ነው? አለ። አንዱም እንዲህ ያለ ነገር፥ ሌላውም እንዲያ የለ ነገር ተናገረ። መንፈስም ወጣ “”በእግዚአብሔርም ፊት ቆሞ””፦ እኔ አሳስተዋለሁ አለ። እግዚአብሔርም፦ በምን? አለው እርሱም፦ ወጥቼ በነቢያቶቹ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ እሆናለሁ አለ። እግዚአብሔርም፦ ማሳሳትስ ታሳስተዋለህ፥ ይሆንልሃልም ውጣ፥ እንዲሁም አድርግ አለ። አሁንም፦ እነሆ፥ እግዚአብሔር በእነዚህ በነቢያትህ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ አድርጎአል፤ እግዚአብሔርም በላይህ ክፉ ተናግሮብሃል።
2ኛ ነገሥት 19፥7 እነሆ፥ በላዩ “”መንፈስን እሰድዳለሁ””፥ ወሬንም ይሰማል፥ ወደ ምድሩም ይመለሳል፤ በምድሩም በሰይፍ እንዲወድቅ አደርገዋለሁ በሉት አላቸው።

መደምደሚያ
መንፈስ ከጌታችን “ነገር” ነው፦
17:85 ከሩሕም ይጠይቁሃል፤ ሩሕ *ከ* ጌታዬ ነገር مِنْ أَمْرِ رَبِّي ነው፤ ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም፤ በላቸው።

መንፈስ ከነገር አንዱ ከሆነ ነገር ሁሉ ፍጡር ነው፦
39:62 አላህ “የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው”፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው።
40:62 ይሃችሁ፣ ጌታችሁ አላህ ነው፤ “የነገር ሁሉ ፈጣሪ ነው”፤ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ ታዲያ ከእምነት ወዴት ትመለሳላችሁ?።
6:102 ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ “ነገርን ሁሉ ፈጣሪ” ነው፡፡ ስለዚህ አምልኩት፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነው፡፡

ስለዚህ አላህ ነገር ሳይሆን የነገር ፈጣሪ ስለሆነ ፍጡር የሆኑትን አካል እና መንፈስ ነገር ስለሆኑ አላህ አካል እና መንፈስ አይደለም። አላህ መንፈስ ነው ወይስ አካል ነው? ብሎ መሞገት መደዴነት ነው፤ አላህ መለኮት ነው፤ መለኮታዊ ማንነትና ምንነት አለው፤ ማንና ምንድን እንደሆነ ቁርአን ላይ ጥልልና ጥንፍፍ ባለ መልኩ ተቀምጧል፤ ለመጣጥፉ እርዝመት ይቅርታ እጠይቃለው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም