አካል እና መንፈስ
ክፍል ሁለት
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
17:85 ከሩሕም ይጠይቁሃል፤ ሩሕ *ከ* ጌታዬ ነገር مِنْ أَمْرِ رَبِّي ነው፤ ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም፤ በላቸው።
ነጥብ ሁለት
“መንፈስ”
“ሩሕ” رُوح የሚለው ቃል “መንፈስ” ማለት ሲሆን በቁርአን 21 ጊዜ ተጠቅሷል፤ ይህም ቃል እንደየ አውዱ ለተለየየ አጠቃቀም ይጠቀምበታል፤ ለምሳሌ ቁርአን “መንፈስ” ተብሏል፦
42፥52 እንደዚሁም ወደ አንተ ከትእዛዛችን ሲኾን “መንፈስን” አወረድን፡፡ መጽሐፉም እምነቱም ምን እንደኾነ የምታውቅ አልነበርክም፡፡ ግን ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት “ብርሃን” አደረግነው፡፡ አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትመራለህ وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَآ إِلَيْكَ رُوحًۭا مِّنْ أَمْرِنَا ۚ مَا كُنتَ تَدْرِى مَا ٱلْكِتَٰبُ وَلَا ٱلْإِيمَٰنُ وَلَٰكِن جَعَلْنَٰهُ نُورًۭا نَّهْدِى بِهِۦ مَن نَّشَآءُ مِنْ عِبَادِنَا ۚ وَإِنَّكَ لَتَهْدِىٓ إِلَىٰ صِرَٰطٍۢ مُّسْتَقِيمٍۢ ፡፡
እዚህ አንቀፅ ላይ “መንፈስ” እና “ብርሃን” ተለዋዋጭ ቃል ሆነው ገብተዋል፤ ብርሃን የሃይድሮጂን፣ የሂልየም እና የአርገን ብርሃን ማለት እንዳልሆን ሁሉ መንፈስ የተባለውም አካል ህያው የሚሆንበት ንጥረ-ነገር ሳይሆን ቁርአን ነው፤ “መንፈስ” እና “ብርሃን” እዚህ ጋር “ሒስሲይ” ማለትም “እማሬአዊ” ሳይሆን “መዕነዊይ” ማለትም “ፍካሬአዊ” ነው። በተጨማሪም ጂብሪል *ታማኙ መንፈስ* እና *ቅዱሱ መንፈስ* ተብላል፦
26:192-194 እርሱም ቁርአን በእርግጥ ከዓለማት ጌታ የተወረደ ነው፡፡ እርሱን #ታማኙ* #መንፈስ* አወረደው፤ ከአስጠንቃቂዎቹ ትኾን ዘንድ #በልብህ* ላይ አወረደው፡፡
19:17 ከእነሱም መጋረጃን አደረገች፣ #መንፈሳችንንም (ጂብሪልን) ወደርሷ ላክን፤ ለእርሷም ትክክለኛ ሰው ሆኖ ተመሰለላት።
16:102 እነዚያን ያመኑትን ለማረጋጋት ሙስሊሞቹንም ለመምራትና ለማብሰር ቁርአንን #ቅዱሱ* #መንፈስ*(ጂብሪል) እውነተኛ ሲሆን #ከጌታህ* مِنْ رَبِّكَ *አወረደው* በላቸው።